BOX Office (hanan📚) @box_office_hanan Channel on Telegram

BOX Office (hanan📚)

@box_office_hanan


"Strong minds discuss ideas, average minds discuss events, weak minds discuss people."
Rinu Ruzvelt

BOX Office (hanan📚) (English)

Welcome to BOX Office - the ultimate destination for those with strong minds! Our channel, @box_office_hanan, is dedicated to discussing ideas that will stimulate your intellect and broaden your perspective. As the famous quote by Rinu Ruzvelt suggests, strong minds focus on ideas, not people or events. If you're tired of superficial conversations and crave intellectual stimulation, then this is the channel for you. Join our community of like-minded individuals who are passionate about engaging in meaningful discussions and exploring thought-provoking topics. From philosophy to literature, science to art, our channel covers a wide range of subjects to keep your mind sharp and curious. Don't settle for average discussions when you can elevate your thinking with BOX Office. Challenge yourself to think deeper, question assumptions, and engage with diverse perspectives. Let's join forces to create a space where ideas reign supreme and strong minds thrive. Welcome to BOX Office - where intellectual curiosity meets vibrant discussion!

BOX Office (hanan📚)

31 Aug, 17:27


https://t.me/rwwi1417

BOX Office (hanan📚)

16 Aug, 01:49


የሚጠብቀን አይተኛም !

ሁላችንም የፈጠረን ፈጣሪ እጅ ላይ ነን በራሳችን የቆምን አደለንም የምድር ባለቤት የሁላችን ፈጣሪ ሁሌም እኛን ለመጠበቅ አይተኛም አያንቀላፋም ስለዚህ ምንድነው ታድያ የሚያስፈራን ?

ቤታችንን ከሌባ ለመጠበቅ  ዘበኛ ወይም አደገኛ አጥር ወይ ደግሞ ውሻ አስቀምጠን ነፃ ሆነን ያለስጋት እንተኛ የለ ታድያ ከሁሉ በላይ ሁሉን የፈጠረ ፈጣሪ እየጠበቀን ካለ ምንም ነገር ሊያሸንፈን እንዴት ይቻለዋል  ?
           
         ያማረ ቀን ይሁንላችሁ
         
@BOX_Office_hanan
@BOX_Office_hanan
@BOX_Office_hanan

BOX Office (hanan📚)

05 Aug, 18:53


የሆን ቀን ..
በሆነ ጊዜ ...
አንድ ቀን ...
ሀሳባችሁ እንደሚሳካ፣ ልፋታችሁ ፍሬ እንደሚያፈራ፣ ህልማችሁ እዉን እንደሚሆን ለቀልባችሁ ንገሩት።

የከበባችሁ መከራ ሁሉ እንደ ክረምት ጎርፍ ያልፋል፣ የጭጋጉ ጊዜ ሄዶ ብራው ይመጣል። ፈገግታችሁም ይመለሳል።

እኛ በዚህች ምድር ላይ እንግዶች ነን። ችግሮቻችንም ሆኑ እኛ እናልፋለን።
የማያልፍ ነገር የለም።
ላያልፍ የመጣ ነገርም የለም።

የቀናትን አፈጣጠን እያያችሁ ነው ግን!?
የመከራውን ላይ በላይ መሆንስ

        መልካም ምሽት
       
@BOX_Office_hanan
@BOX_Office_hanan
@BOX_Office_hanan

BOX Office (hanan📚)

01 Aug, 19:35


መልካም ሰዉ ከሆንክ አንተ የምታጣዉ ሰዉ የለም። አንተን ግን ሚያጡህ ብዙ ሰዎች አሉ። so ስለሰዉ አትጨናነቅ መልካምነትህን ቀጥልበት……………
@BOX_Office_hanan

BOX Office (hanan📚)

20 Jul, 16:36


እስቲ ስለራሣችንና ስለ ሰው ልጅ ሁኔታ ጥቂት እናውጋ፡፡

❶ የሰው ልጅ ከእድሜው የመጀመሪያዎቹን አሥራ ምናምን ዓመታት ሕፃን ነው። ገና ታዳጊ፡፡ ነገር ያልገባው፣ ሕይወትን ያልተረዳ፣ በወጉ ያልበሠለ፣ የሚጠቅም የሚጎዳውን በሥርዓቱ ያልለየ፡፡

❷ ከአሥራ ስምንት እስከ ሠላሣ አምስት ዓመታት ባሉት ጊዜ ውስጥ ደግሞ አትንኩኝ አትጠጉኝ!› የሚል ለያዠ ለገናዠ የሚያስቸግር፤ ታላቁን የማያከብር፤ መምህሩን የሚዳፈር፤ በገዛ ወላጆቹ ላይ ምላሱን የሚያስረዝም፤ ገመድ የማይዘው፤ ሠንሰለት የማይጥለው ፤ ከሱ በስተቀር በዚህች ምድር ላይ ሰው ስለመኖሩ የሚጠራጠር፤ ቢወድቅ የሚሠበር ቢሞት ሥጋው በአፈር የሚደፈር የማይመስለው፤ ከመሬት ከፍ ከሠማይ ዝቅ ብሎ የሚበር <ፍንዳታ› ነው፡፡

❸ ከሰላሣ ስድስት እስከ አርባ አምስት ባለው እድሜ ውስጥ ደግሞ ለማንና ለምን እንደሚሠራ የማያውቅ ጠንካራ ሠራተኛ ነው፡፡ በዚህ የእድሜ እርከን ላይ ምራቅ ይውጣል፤ ይበስላል› ተብሎ ስለሚታሰብ የዚህችንም ዓለም ባህሪ በወጉ ይረዳል፡፡ በመሆኑም የእድሜ ፀሐዩ ሣትጠልቅ ይወራጫል… ይሠራል፤ ይጥራል… አንድም ለራሱ አሊያም ለልጁ ካልሆነም ለወራሹ፡፡ እሱም ሌሎች ሰዎች እንደሆኑት ለመሆን ሲል እንደ በሬ ይተጋል፤ እንደ አህያ ይፈጋል…. መኪና ለመያዝ ፣ ቤት ለመያዝ ፤ ብር ለመያዝ ፤ ኑሮውን ለማስተካከል፤ እንዳይወድቅ እግሩን አርቆ ከመሬት ውስጥ ለመትከል፡፡

❹ ከአርባ ስድስት እስከ [ስልሳ*] ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ደግሞ በአርባዎቹ እድሜ ላይ የጀመረው አባዜ ያልተወው፤ ቢጠሩት የማይሠማ፤ ቢነግሩት የዱኒያ ስካር ያልለቀቀው፤ የማይገባው፤ ዱኒያ ዐቅሉን ስርቅ ሀሣቡን ውስድ፤ ልቡን ጥፍት ያደረገችው የለየለት ሠካራም ነው… በዱኒያ የሠከረ.. ፍቅረ ነዋይ ያልበረደለት ለብር የሚንከለከል እሷኑ የሚያነሣ የሚጥል ባገኘም ቁጥር ጨምሪ እንጂ! ብሎ የሚጠይቅ በእጅጉ እንደተጠማ ውሻ አፉን ከፍቶ የሚያለከልክና ጥሙም የሚቆርጥለት የማይመስል ነው።

❺ ከስልሣ በላይ ሲሆን ደግሞ ከእድሜው መግፋት ጋር ተያይዘው የሚመጡበትን በሽታዎች የሚታገል፤ ወኔ ያለው ጉልበት የከዳው፤ ምኞት የሞላው ሩጫ ያጠረው፤ እቅድ የተረፈው ጤና የናፈቀው፤ መዝለል የሚከጅል መነሣት ያቃተው. አሁንማ ዋ.! እያለ በየደቂቃና በየሰከንዱ በትዝታ ርቆ የሚሄድ፤ ቁጭ ባለበት በሀሣብ
የሚቆዝም… አይኑ እያየም ሞቱን የሚጠብቅ እስረኛ ሽማግሌ ነው።
------
'ልብ ላላሉ ልቦች' ከሚለው የMuhammed Seid Abx መፅሐፍ የተቀነጨ
@BOX_Office_hanan

BOX Office (hanan📚)

13 Jul, 13:07


ፈተናዎችን ሁሉ እንዴት እንደማልፍ ታውቃላችሁ?


ፈጣሪ የወደደልኝን ከልብ በመውደድ
       @BOX_Office_hanan
        @BOX_Office_hanan

BOX Office (hanan📚)

03 Jul, 07:02


#ትዳርና_ንብ
ትዳር ከንብ ጋር መኖር ነው ። የማትናደፍ_ንብ ከፈለክ 🤮ከዝንብ ጋር ተጋባ ። 👌ትዳር ከንብ ጋር መኖር ነው ። ለማሩ ስንል ንድፊያውን መታገሥ ፡፡ ቆይተህ ደግሞ ንድፊያውን መልመድ ፡፡ገበሬ ቀፎ ሰቅሎ ንብ ሲያንብ ፣ ንብ እንደምትናደፍ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም ፡፡ የማትናደፍ ንብ ከፈለገ በየደጁ ቆሻሻ ፍለጋ የምትጓዘው ዝንብ ነበረችለት ፡፡ ዝንብ ምን ጠባይዋ ሸጋ ቢሆን ፤ ጠብ የሚላት ግን ሌላ ነገር ነው ፡፡ ይህን ያውቃል ገበሬው ፡፡ እያወቀም ንብ ያንባል ፡፡ ማነብ ብቻ ሳይሆን ከንብ ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻልም ያውቃል ፡፡ ንብ ትናደፋለች ፤ ግን እንዳትናደፍ ማድረግም ይችላል ፡፡ የምትወደውና የማትወደው ሽታ አለ ፡፡ ስትቀርብህ ምን ማድረግና ምን አለማድረግ እንዳለብህ ገበሬው ያውቃል

የምትቀስመው አበባ ትፈልጋለች ፣ ንጹሕ አካባቢ ትፈልጋለች ፣ ከጉንዳንና ከአውሬ ነጻ የሆነ ቀፎ ትፈልጋለች ፡፡ ግን ትናደፋለች ፡፡ ደግሞም ማር ትሰጣለች ፡፡ ትዳር አስደሳች ነገር ብቻ ሳይሆን አስመራሪ ፣ አስጠሊታ ፣ ጨጓራ አንዳጅ ፣ ልብ አቃጣይም ክፍል አለው ፤ ይናደፋል ፡፡ ግን ደግሞ ክብካቤም ይፈልጋል ፡፡ ንጹሕ ልብ ፣ ታማኝ ኅሊና ፣ ቻይ አንጀት ፣ ታጋሽ ሆድ ፣ ጠቢብ አእምሮ ፣ አሳላፊ ልቡና ይፈልጋል ፡፡ ለምን ቢሉ ? ማር ይሰጣልና!!!
@BOX_Office_hanan
@BOX_Office_hanan

BOX Office (hanan📚)

26 Jun, 16:06


መዓዛችሁን አትልቀቁ! 

“የጽጌሬዳ አበባን ምንም አይነት ሌላ ስም ብንሰጠውም እንኳን ፈጽሞ መልካም መዓዛውን አይለቅም” (William Shakespeare)

ሰዎች ስለ እናንተ የሚያስቡት ሃሳብ፣ የሚያወሩት ወሬም ሆነ የሚለጥፉባችሁ ስም ምንም ሆነ ምንም፣ ያላችሁን መልካም ማንነትም ሆነ የምትከተሉትን አስገራሚ ራእይና ዓላማ በፍጹም ሊነካው አይችልም፡፡

ከላይ የተጠቀሰው አይነት የሰዎች ሁኔታ እናንተን የሚነካችሁ በእነሱ ንግግርና ተግባር ምክንያት በራሳችሁ ላይ ያላችሁ አመለካከት ሲበላሽና ተገቢ ወዳልሆነ ባህሪይና ተግባር ስትወርዱ ብቻ ነው፡፡

ሰዎች ሲያወሩ እናንተ ስሩ!

ሰዎች ሲያፈርሱ እናንተ ገንቡ!

በሰዎች ምክንያት መልካም መዓዛችሁን አትልቀቁ!

         @BOX_Office_hanan
           @BOX_Office_hanan
         @BOX_Office_hanan

BOX Office (hanan📚)

23 Jun, 05:26


🦋"የምትወዱትን ሰው እንደምትወዱት በግልፅ ንገሩት         ግንኙነታችሁን ለማጠናከር ይረዳቹሀልና"       
                       ነብያችን ሙሀመድ( ﷺ )🥰
🤍
@BOX_Office_hanan

BOX Office (hanan📚)

22 Jun, 06:06


ቀናተኛ አፍቃሪ ላለመሆን ሞክር፤ በግልፅነት ቅናትን ለማስወገድ ሞክር፤ አለበለዚያ በመጨረሻም ደስታንም ፍቅርንም እራስህንም ታጣለህ፡፡ 💞✌️
       share&share👇👇
          @BOX_Office_hanan

BOX Office (hanan📚)

21 Jun, 17:46


ጥሩ ከመፈለግ ጥሩ ሆኖ መገኘት ይቀድማል!
"አንተ ጠዋት ተነስተህ ስትታጠብ ሌላኛው ደግሞም
ጠዋት ተነስቶ
#ኩላሊቱን የሚያሳጥብ አለና ምንም
ባይኖርህም ጤናህን አሟልቶ ለሰጠህ ፈጣሪ ሁሌ
አመስግነው''!! 💞🙏

    @box_office_kemal

BOX Office (hanan📚)

15 Jun, 20:49


እንኳን ለ1445ኛው ዓመተ ሂጅራ የዒድ አል አድሃ ዐረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ዒድ ሙባረክ

BOX Office (hanan📚)

15 Jun, 06:05


ሕይወትን  ወደ ዕድሜያችሁ ጨምሩ እንጂ ዕድሜን ወደ ሕይወታችሁ አትጨምሩ። ዕድሜ ከዉብ ሕይወታችሁ ከመስረቁ በፊት ሕይወትን ከዕድሜያችሁ ስረቁ።
ገብቷችኋል አይደል ...።

      @box_office_kemal

BOX Office (hanan📚)

08 Jun, 09:14


ትልቅ ሰው ነው፣ ታዋቂ ነው ... እንዴት አሳፍረዋለሁ ማለቱን ተዉና እንቢ ማለት በሚገባ ቦታ እንቢ ማለትን ልመድ፤ ይለኛል አንደኛው ስሜቴ።
ምክንያቱም የእሺን ዋጋ የምከፍለው ብቻዬን ነዋ። በእሺ የሚመጣን መከራ ማንም አይጋራኝም መቸስ።

ብዙዎች ዕዳ የገቡት እኮ ትልቅ ሰው ብለው "መርሐባ" እያሉ ነው ።

@box_office_kemal
@box_office_kemal
 
      @box_office_kemal

BOX Office (hanan📚)

29 May, 16:38


ጠቢቧና ጠንካራዋ ሴት!

ላላገባችሁ ሴቶች . . .

“በሕይወትህ ውስጥ ስፍራ እንዲኖረኝ ከፈለክ በቂ ስፍራን ስጠኝና አስገባኝ፡፡ ያንን ካላደረክ ግን በአንተ ሕይወት ውስጥ አስፈላጊውን ስፍራ ለማግኘት እንደማልፋለም ከወዲሁ እወቀው!” - ካልታወቀ ምንጭ

የእሱን ትኩረት፣ ጊዜና የፍቅር ቃላት ለማግኘት የምትፋለሚ ከሆነና ከሌሎች ጋር ታግለሽ በእሱ ሕይወት ስፍራን ማግኘት እንዳለብሽ የሚሰማሽ ከሆን፣ ብዙ ተፋልመሽ ዓመታቶችሽን ከመክሰርሽና ከመቆሳሰልሽ በፊት እንደ ጠቢቧና ጠንካራዋ ሴት የመሆንን ምርጫ ዛሬውን ብትመርጪና የትኩረት ለውጥ ብታመጪ ምን ይመስልሻል?

          @box_office_kemal
           @box_office_kemal
             @box_office_kemal

BOX Office (hanan📚)

27 May, 14:05


💎 ስልጡን ሰው ደስ ይላል ። ተረጋግቶ ነው የሚያወራው ፣ አይመፃደቅም ፣ ሁሉንም አውቃለሁ አይልም ፣ሰው ያከብራል ፣ ያልገባውን ይጠይቃል ።

   ቀልድ ይገባዋል ፣ የግል ጉዳይህ  ውስጥ ዘው  ብሎ አይገባም ፣ ሃሳብ ላይ መወያየት ይችላል ፣  አመስጋኝ ነው ቅር ስላለው ጉዳይ በትህትና ይጠይቃል ።

በረባው  ባረባው አይሞግትም  ። አብሮት ያለውን ሰው ስሜት ያጤናል ። መበሻሸቅ ውስጥ አይሳተፍም ።

ስልጡን ሰው ደስ ይላል

⛵️⛵️⛵️
   @box_office_kemal
    @box_office_kemal
     @box_office_kemal

BOX Office (hanan📚)

23 May, 07:11


ወጣትነት፣የማይመለሱ አመታት፣ተመልሰው የማይመጡ እድሎች !የሚገባህን ህይወት ለመኖር ወስን🌿
        @box_office_kemal
         @box_office_kemal
        @box_office_kemal

BOX Office (hanan📚)

10 May, 06:45


"ምን አርጌው ነው ግን የቦለከኝ?" ብለህ አሁን ድረስ የምትብከነከንበት ሰው አጋጥሞህ ያውቃል ?
ካላጋጠመህ ወደፊት ያጋጥምሃል አብሽር  ።

ያኔ ባጋጠመህ ጊዜ ደግሞ ብዙ አትገረም።

ሞኝ አትሁን፣ አትብሰልሰል፣ ብቻህንም አታውራ።
ቆይ እጠይቀዋለሁም አትበል።

ወዳጄ!
ሰው ከራሱ ጋር ተጣልቶ ምንም ሳታረገው ሰው ላይ በብሎኬት ማለቴ በብሎክ ብሶቱን የሚወጣበት ዘመን ላይ ደርሰናል ።

አትረበሽ፡፡
ዝምብለህ ኑር ያልኩህ እኔ ነኝ።
 
      መልካም ጁማአ
    @box_office_kemal
    @box_office_kemal

BOX Office (hanan📚)

08 May, 03:11


ግማሹ ኩራተኛ ነው ይልሃል፡፡ ሌላው እንደርሱ ያለ ትሁት ሰው ገጥሞኝ አያውቅም ይላል፡፡ አንዳንዱ ገና ስምህ ሲነሳ በርግጎ ይጠፋል፤ ሌላው ስላንተ አውርቶ አይጠግብም፡፡ ከፊሉ ያንተን መገኛ ሲያስስ ይውላል፤ ሌላው አንተ ያለህበት ምቾት አይሠጠዉም ይሸሻል፡፡

በአንድ አቋምህ ብቻ አንቅረው የተፉህ እንዳሉ ሁሉ፤ በአንድ አቋምህ የተነሳ ከልባቸው ሊያወጡህ የተቸገሩ አሉ፡፡ አንዳንዱ ለትችትህ ሲሽቀዳደም ሌላው ሲያድንቅህ ዉሎ ቢያድር አይደክመዉም፡፡ አንዱ እሱ ጥሩ ሰው ነው ሲልህ፤ ሌላው በጣም መጥፎ ነው ብሎ ይሞግታል፡፡ አውቀዋለሁ መልካም ሰው ነው የሚል እንዳለ ሁሉ አታውቁትም መሰሪ ሰው ነው ብሎ የሚከራከርም አለ፡፡ ያለምክንያት እንደሚጠሉህ ያሉ ሁሉ ያለምክንያት የሚወዱህም ብዙ ናቸው፡፡

ይህ ሁሉ እንግዲህ አንድ አንተው ብቻ ነህ። አንተ አንድ ነህ፤ ሰዎች ላንተ ያላቸው እይታ ግን ብዙ ነው። የተለያየ መልክን ስብእና ይዘህ በሰዎች ልብ ዉስጥ ትኖራለህ፡፡ ሁላችንም እንደዚያው ነን፡፡

አይግረመን፡፡ ብቻ ትክክል ለመሆን እንጣር፣ እውነትን ይዘን እንኑር፣ ከፈጣሪ አንጻር እንሥራ፡፡ ለፈጣሪ ስንሠራ የሰዎችን ጉዳይ የሚያስተካክልልን እሱ ነው፡፡  ይገርማል የፈጣሪ ሥራ፡፡
        
            @box_office_kemal