Últimas publicaciones de Bilal Nur (@bilalnur1) en Telegram

Publicaciones de Telegram de Bilal Nur

Bilal Nur
#ETHIOPIA
2,392 Suscriptores
89 Fotos
7 Videos
Última Actualización 06.03.2025 15:05

El contenido más reciente compartido por Bilal Nur en Telegram

Bilal Nur

05 Jan, 08:58

828

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ :- ሊገባን ይገባል አሁን እየተፋፈርን ስለሆነ ነው እንጂ ማንም ኑሮን እየተቋቋመው (Afford) እያደረገ አይደለም፡፡

ከሁለትና ሦስት ዓመት በፊት 10 እና 15 ሺህ ደመወዝ የሚያገኙት ሠራተኞች ጥሩ ነበሩ፡፡
አሁን ግን :- 30 ሺህ እና 40 ሺህ ብር
ደመወዝ የሚያገኙት ጥሩ ደረጃ ላይ ናቸው አልልም፡፡
* የቤት ኪራይ
* የትምህርት ቤት ክፍያው
* የኑሮ ውድነት ሰማይ ወጥቷል::
ሙሉውን ቃለ መጠየቅ
የሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎችን ይዞ በገበያ ላይ ይገኛል
በድረገጻችን https://www.ethiopianreporter.com/ ላይም ያገኙታል።
Bilal Nur

04 Jan, 05:02

854

" የአሁኑ ከእስከዛሬው ሁሉ ይለያል ፤ በጣም ያስፈራ ነበር " - ነዋሪዎች

በርካቶችን ለሊት ከእንቅልፍ የቀሰቀሰ ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ለሊት ተከስቷል።

ከለሊቱ 9:52 ላይ ከአቦምሳ 56 ኪሎ ሜትር ርቀት በሬክተር ስኬል 5.8 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

ንዝረቱ አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች በከፍተኛ ሁኔታ ተሰምቷል።

የቤተሰብ አባላቶቻችን ምን አሉ ?

➡️ " ሩፋኤል አካባቢ ነው ያለሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የሰማሁት ያስፈራል እስካሁን አዲስ አበባ ላይ ሲባል ነው ስስማ የነበረው። "

➡️ " በጣም በሚያስፈራ ሁኔታ ከእንቅልፍ ነው የቀሰቀሰኝ። እንዲህ ከፍ ብሎ ተሰምቶኝ አያውቅም። "

➡️ " ሰሚት ነው የምኖረው ፤ እግዚኦ የአሁኑ 9:52 የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እና የቆየበት ሰከንድ ያስፈራ ነበር። "

➡️  " የአሁኑ በጣም ከበድ ያለ እና ረዘም ያለ ነው ከአያት ኮንዶሚኒየም። "

➡️ " ከአራብሳ ኮንዶሚኒየም ነበር። የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ በጣም ከፍ ያለ ነው። "

➡️ " ከእስካሁኑ ጠንካራውን ንዝረት ነው የሰማነው። ከቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም። እቃዎች ሲወድቁም አስተውያለሁ። "

➡️ " በከባዱ ነበር የዛሬው ደግሞ ከሌሎቹ የተለየ ነበር። "

➡️ " እኔ ባለሁበት ቀጨኔ ከወትሮው ርዝማኔው የጨመረ የመሬት መንቀጥቀጥ ጠንከር ያለ ንዝረት ተከስቷል። "

➡️ " ዱከም ነው ያለነው ንዝረቱም ጠንክሮ እዚህም ተሰምቷል። "

➡️ " ኧረ ያአሏህ ጎሮ ሰፈራ ላይ ነኝ ያለሁት እና የመሬቱ መንቀጥቀጥ ንዝረት ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ ወይስ በህልሜ ይሁን ያረቢ ብቻ ከባድ ነው በጣም ነው የሚያስጠነግጠው። "

➡️ " በከሚሴ  የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተሰምቶናል። በጣም ያስፈራ ነበር  አሏህ መጨረሻችንን ያሳምርልን ! '

➡️ " ከለሊቱ 9:53 ላይ ለ5 ሰከንድ የቆየ ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ነበር። የካ ክፍለ ከተማ ነው። ድምጹም ከመኝተየ የቀሰቀሰኝ የቤታችን ቁም ሰጥን ሲንቀጠቀጥ ሰምቸ ነው። መሬቱም በጣም ነበር ከተኜውበት የቀሰቀሰኝ። ያስፈራ ነበር። "


በሬክተር ስኬል 5.8 ከተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ በኃላ ዳግም በሬክተር ስኬል 4.4 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥም ተከስቶ ነበር።

ውድ ቤተሰቦቻችን "  ነገሩ ተለምዷል ፤ ምንም ሊፈጠር አይችልም " ብላችሁ እንዳትዘናጉ በድጋሚ አደራ እንላለን።

Via Tikvah
Bilal Nur

04 Jan, 05:01

670

በሬክተር ስኬል 5.8 የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ለሊት በአፋር ክልል ተከሰተ

በኢትዮጵያ በሬክተር ስኬል 5.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ከለሊቱ 9:52 መድረሱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት አስታወቀ።

ሰሞኑን ሲከሰቱ ከነበሩት የመሬት መንቀጥቀጦች ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየው ርዕደ መሬት፤ ንዝረቱ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ተሰምቷል።

የለሊቱ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው በአፋር ክልል መሆኑን የአውሮፓ ሜዲትራንያን ሴይስሞሎጂ ማዕከል (EMSC) ተቋም መረጃ ያሳያል።

ርዕደ መሬቱ የተከሰተበት ቦታ ከአቦምሳ ከተማ 56 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከአዳማ ከተማ 137 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ መሆኑን የአሜሪካ እና የአውሮፓ ተቋማት ገልጸዋል።

ታኀሣሥ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
Bilal Nur

03 Jan, 10:22

897

🔥 🔥 🔥

በዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከሰተ

ታሕሳስ 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ የቮልካኖ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡

ይህን ተከትሎም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደረስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ተናግረዋል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል፡፡

በዚሁ መሠረት በተቀናጀ ሁኔታ ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የሟጓጓዝ ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ አሁንም በተደጋጋሚ መቀጠሉን ጠቅሰው፤ የቮልካኖ ፍንዳታ ዛሬ ተከስቷል፤ ንዝረቱም ከሰሞኑ ከፍያለ እና ጠንካራ ነበር ሲሉም ተናግረዋል፡፡

Ahadu fm
Bilal Nur

01 Jan, 19:31

866

የአክሱም ከተማ ፖሊስ ሒጃብ ለብሰው ለማማር ወደ ትምህርትቤት የሄዱ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት "ለምን ሒጃብ ለብሳችሁ ለማማር መጣችሁ?" በሚል ወደ ፖሊስጣቢያ በመውሰድ ተማሪዎቹን ሲያስፈራሩ የሚያሳይ በድብቅ የተበረፀ አጭር ቪድዮ ደርሶናል። ተማሪዎቹ የለበሷት ስካርፍ ሒጃብ ተመልከቱ። It's just a piece of cloth እኮ።
ተጨማሪ ሌሎች መረጃወችን ለማገኘት
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/bilalnur1
Bilal Nur

27 Dec, 08:48

1,942

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በድጋሚ የሚፈተኑ ተፈታኞች የሚመዘገቡበት አድራሻ ይፋ ተደረገ

ታሕሳስ 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በድጋሚ የሚፈተኑ ተፈታኞች በራሳቸው የሚመዘገቡበትን አድራሻ በመጠቀም፤ በበየነ መረብ መመዝገብ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ይህ የበይነ መረብ ምዝገባ መተግበሪያ ራስ አገዝ (self-services) ሲሆን፤ ተመዝጋቢዎች የሚፈልጉትን ድጋፍ በመጠየቅ ከማዕከል ማግኘት እንደሚችሉ አገልግሎቱ አስታውቋል።

በዚህም መሠረት ፈተናውን በድጋሚ የሚፈተኑ ተፈታኞች https://register.eaes.et/Online በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል፡፡

በ2016 ዓ.ም. 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን 684 ሺሕ ተማሪዎች ለፈተና ተቀምጠው፤ 36 ሺሕ 409 ተማሪዎች ብቻ (5.4 ከመቶ) 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለፊያ ውጤት ማምጣታቸው ይታወሳል።

👉 ከዚህ መልዕክት ጋር የተያያዙ መረጃዎች ተመዝገቢዎች በቀላሉ መመዝገብ እንዲችሉ አጋዥ ስለሆኑ እንዲጠቀሙባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ትክክለኛ youtube channel👇👇
https://www.youtube.com/@BILALNURR
Subscribe አርጉልኝ
Bilal Nur

22 Dec, 13:34

993

🚨 “ የሚላስ የሚቀመስ የለም ” - የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

🔴 “ ችግር እንዳለ ይታወቃል ” - የአማራ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በምግብ እጥረት ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተጎዱ፣ በተለይ ጨቅላ ህፃናት የከፋ ስቃይ ላይ እንደሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

“ ጉዳዩ በጣም አሳዛኝ ነው። በእኛ ቦታው ያልሆነ ሰው አይገባውም ” ሲሉም የሁነቱን አስከፊነት አስረድተዋል።

ስሜ ከመነገር ይቆይ ያሉ የመረጃ ምንጭ በበኩላቸው፣ “ በቡግና ወረዳ ጉልሃ ቀበሌ አንድ ህፃን በምግብ እጥረት ሞቷል ” ብለዋል።

የቡግና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረ መስቀል አለሙ በበኩላቸው፣ በክልሉ ባለው ግጭትና ተፈጥሯዊ ተፅዕኖ ምክንያት ወረዳው ለድርቅና ለምግብ እጥረት በመጋለጡ ህፃናትን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውን ሰሞኑንን ለቢቢሲ አማርኛ መናገራቸው አይዘነጋም።

በወረዳው በተከሰተ የምግብ እጥረት በተለይ ጨቅላ ህፃናት ስለተጎዱ ነዋሪዎቹ የድረሱልን ጥሪ ማሰማታቸውን በመግለጽ ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቀው የቡግና ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት፣ “ እኛ ጋር ስራ የለም ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥቷል።

ጽሕፈት ቤቱ፣ “ እውቅናው የለኝም ” ያለ ሲሆን፣ ጉዳዩን እንደሚያውቁት ነዋሪዎች መናገራቸውን ብንገልጽለትም፣ “ እስካሁም ምንም አይነት በሪፓርትም የመጣ ነገር የለም ” ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቡግና ወረዳ በተጨማሪም ለአማራ ክልል ስጋት አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ ችግሩ መኖሩን አምኗል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ ፍቅሬ ሙሉጌ በሰጡን ቃል፣ “ ጉዳዩ በኛ ቁጥጥር ውስጥ ነው። ከእኛ አቅም ውጪ የሆነ ነገር የለም ” ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም፣ “ ችግር እንዳለ ይታወቃል። ድጋፍ እየቀረበ ነው። ምንም የተለዬ ነገር የለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ የአምናውን ድርቅ ችግር ተቋቁመናል አሁን እንዲያውም ጥሩ ነው ምርት አምርተዋል ” ሲሉ ተናግረዋል።

ድጋፍ እየተደረገላቸው ከሆነ ምን ያክል ድጋፍ ተደርጓል ? ሰሞኑን ያደረጋችሁት ድጋፍ ነበር ? በተለይ ሰሞኑን ህፃናቱን የሚመግቡት እንደተቸገሩ ነዋሪዎቹ እየገለጹ ነው፣ ስንል ለወ/ሮ ፍቅሬ ተጨማሪ ጥያቄ አቅርበናል።

እሳቸውም በምላሻቸው፣ “ በቂ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው በተለመደው አግባብ (ድጋፉ የሚሰጥበት ቀመር አለው) ድጋፍ እየደረሳቸው ነው ” ከማለት ውጪ የችግሩን አስከፊነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ነዋሪዎቹ የላኳቸው ፎቶዎች ህፃናቱ በምግብ እጥረት እንደተጎዱ የሚመሰክሩ እንደሆኑ ገልጸን፣ ድጋፍ ካለ ጉዳዩ እንዴት በዚህ ልክ ጉዳት እንዳደረሰ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኃላፊዋን ጠይቋል።

በዚህም፣ “ ይለካል እኮ ማልኑውትሬሽን፣ ሞዴሬት የሆኑት እየተለካ ምግብ ሁሉ ይሰጣቸዋል ለእናቶች፣ ለህፃናት ” የሚል ምላሽ ሰጠተዋል።

“ ለዩኒሴፍም ይቀርባል። ለአዋቂዎች ደግሞ እህል ይቀርባል። የገንዘብ ደጋፍም ይሰጣልና ክትልትል እየተደረገ ነው ” ያሉት ወ/ሮ ፍቅሬ፣ “ በመሀል ደግሞ በህመምም በምንም ጉዳት ሊያጋጥም ይችላል ” ነው ያሉት።

የቡግና ወረዳ ኮሚዩኒኬሽንና ኮሚሽኑ ይህን ይበሉ እንጂ የቡግና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ግን ለቢቢሲ አማርኛ በሰጠው ቃል፣ “ ማህበረሰቡ ምርት ባለማግኘቱ እናቶች ልጆቻቸውን ባግባቡ መግበው የተሻለ የጤና እድገት እንዳይኖራቸው አድርጓል ” ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የሰሜን ወሎ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር ዛሬ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል " አካባቢው በፋኖ ታጣቂዎች ስር በመሆኑ ለተከሰተው የምግብ እጥረት መንግሥት በቶሎ ምላሽ መስጠት አልቻለም " ብለዋል።

የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በአደረጉት ጥረትም አሁን ላይ የርዳታ እህል ወደ ስፍራው እየተጓጓዘ መሆኑን አስታውቀዋል።

የወረዳው ነዋሪ ያለበትን የምግብና የጤና ችግር ለፋኖ ታጣቂዎችና ለመንግሥት አካላት ለማስረዳት ከተመረጡት 18 ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበርኩ ያሉት ቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዝናቤ ይርዳው " በአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረሰው ስምምነት መድኃኒቶችንና አልሚ ምግቦች ወደ ወረዳው እየገቡ ነው " ብለዋል።

የኤሪካ ኤምባሲ ደግሞ ፤ የምግብ እጥረት ቀውስ ሰለመኖሩ የወጡ ሪፖርቶችን እየተከታተለ እንደሆነ አመልክቷል።

ቀውሱ መወገዱን ለማረጋገጥ እንደሚሠራም ጠቅሷል።

ኤምባሲው ቀውሱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን አላካተተም።

የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመደገፍ ፣ አጋሮቹ በአሁኑ ሰዓት በችግሩ በተጠቁት አብዛኞቹ ስፍራዎች የምግብ እና አልሚ ንጥረ ምግቦች ስርጭትን ያጠናከሩ መሆናቸውን አክሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Bilal Nur

19 Dec, 08:49

643

ታህሳስ 10፣2017

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚፈፀሙ #የእገታ_ወንጀሎች በአጋቾች የሚጠየቀው የቤዛ ክፍያ በባንክ ተከፈለ ሲባል ይደመጣል፡፡

ታጋቾቹን ለማስለቀቅ በታጋች ቤተሰቦችና በአጋቾቹ መካከል በሚደረግ ድርድር አጋቾቹ በሚመርጡት የገንዘብ መቀበያ መንገድ ገንዘቡ እንደሚላክ ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ ታገተብን የሚሉ ሰዎች ወደ መገናኛ ብዙሃን ብቅ ብለው ሲናገሩ ተሰምቷል፡፡

ለአብነትም ባሳለፍነው ነሐሴ 24 2016 ዓ.ም በ #ጎንደር_ከተማ ከመኖሪያ ቤቷ ታግታ የተወሰደችው የ2 ዓመቷ ህፃን ኖላዊት ዘገየ ጉዳይ ብዙዎችን ያሳዘነ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በአጋቾቹ ለቤዛ ክፍያ 1 ሚሊዮን ብር ተጠይቆ የነበረ ቢሆንም በድርድር ገንዘቡ ወደ 300 ሺህ ብር ቀነሰ፣ ኋላም 200 ሺህ ብር ተዋጥቶ ለአጋቾቹ የተሰጠ ቢሆንም ህፃኗን መግደላቸው የዚያን ወቅት አሳዛኝ ክስተት ነበር፡፡

ይህንን ያነሳነው መንግስት ራሱ ስለመፈፀሙ እውቅና የሰጠበት እገታ ጉዳይ መኖሩን ለማንሳት እንጂ ተመሳሳይ ብዙ ታሪኮች የብዙዎችን ቤት እንዳናኳኩ ይነገራል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በተደጋጋሚ በሚያወጣቸው ሪፖርቶቹ እገታ የገንዘብ ማግኛ መንገድ እየሆነ መምጣቱን ይናገራል፡፡ 

ለመሆኑ በዚህ መንገድ ለሚፈፀሙ እገታዎች በ #ባንክ የሚደረገውን የገንዘብ ዝውውር በመጠቀም እገታ ፈፃሚዎቹን ለምን መያዝ አልተቻለም ስንል የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽንን ጠይቀናል፡፡

አቶ ጄይላን አብዲ በኮሚሽኑ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ ናቸው፡፡

እገታዎቹ በአብዛኛው የሚፈፀሙት አሸባሪ ባሉዋቸው ቡድኖች እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ጄይላን እነርሱን በቀላሉ ማግኘት አለመቻሉ አንዱ ችግር ነው ብለዋል፡፡

እነዚህ ቡድኖች በባንክ የሚያደርጉትን የገንዘብ ዝውውር መቆጣጠሪያ መንገድ በባንኮች ሊኖር ይገባ ነበር ይህ የእኛም ጥያቄ ነው ብለውናል፡፡

በሌላ በኩል እገታዎች እንዲበራከቱ አንዱ ምክንያት የሆነው በማህበራዊ ሚዲያ ስለ እገታ የሚነገርበት መንገድ ነው፤ የሚዘገበው ወንጀሉን ሊስቆምና ሊያስጠነቅቅ በሚችል መልኩ ሳይሆን ጉልበተኛ ሁሉ በእገታ ገንዘብ ሊያገኝ እንደሚችል ጥቆማ በሚመስል ሁኔታ መዘገቡ እንደሆነ ፖሊስ ኮሚሽኑ ባደረገው ዳሰሳ ተመልክቷል ብለዋል አቶ ጄይላን፡፡

እንዲህ ያሉ የእገታ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ጥቆማ መስጫ የሞባይል መተግበሪያ ( tiny.cc/TiqomaMescha ) አልምቶ ወደ ስራ ማስገባቱንም ነግረውናል፡፡

ፖሊስ ኮሚሽኑ የእገታ ወንጀሎች ሲፈፀሙ ተከታትሎ ለመያዝ እንድችል የሞባይል መተግበሪያ የወንጀል አፈፃፀሙን በዝርዝር ብትነግሩኝ ተከታትዬ መያዝ እችላለሁ ብሏል፡፡

መረጃ ሰጪዎች ማንነታቸውን መግለፅ ካልፈለጉ ሚስጥራቸው ይጠበቅላቸዋል፤ በዚህ መንገድ መረጃዎችን በመቀበል ወንጀል ፈፃሚዎችን ለህግ እያቀረብኩ ነው ብሏል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://youtu.be/Q5NrOpiQF8w

ምንታምር ፀጋው
Bilal Nur

14 Dec, 09:14

700

ጃዋር ምንም አይጸጽተውም?

ጃዋር ባለፉት ዓመታት በተለይም በኦሮሚያ ክልል የተካሄዱ አመጾችን ከጀርባም፣ ከፊትም ሆኖ በማስተባበር ይታወቃል።

ከአምስት ዓመታት በፊት ጃዋር "በፌደራል ፖሊስ ተመድበውልኝ የነበሩት ጠባቂዎች 'በአስቸኳይ መሣሪያችሁን ይዛችሁ ውጡ' ተባሉ" በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የጻፈውን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ እና ንብረት መውደሙ አይዘነጋም።

የፌደራል ፖሊስ በወቅቱ በሰጠው መግለጫ "ጃዋር መሐመድ ለተከታዮቻቸው እና ለደጋፊዎቻቸው ልታሰር ነው፣ ጥቃት ሊደርስብኝ ነው በማለት ያስተላለፉት መልዕክት ስህተት ነው" ሲል ማስተባበሉ ይታወሳል።

ጃዋር ለመጽሐፉ 'አልፀፀትም' የሚል ርዕስ መስጠቱን በመጥቀስ፣ በፖለቲካ ሕይወትህ የሚጸጽትህ ነገር የለም ወይ? በሚል ከቢቢሲ ጥያቄ ቀርቦለታል።

ፖለቲከኛውም "በሕይወቴ ውስጥ ባደረግኩት የፖለቲካ ተሳትፎ ውስጥ ብዙ ዋጋ ከፍዬበታለሁ። የግለሰብ ኑሮዬን፣ የቤተሰብ ኑሮዬን መስዋዕት አድርጌበታለሁ። ሆኖም ግን የተሳካ ጉዞ ስለነበረ፣ ያለፍኩበት ሕይወት ከከሰርኩት ያተረፍኩት ይበልጣል። ስለዚህ ልጸጸት አይገባም" ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

አያይዞም "በሄድኩበት ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ስህተቶች የሉም ማለት አይደለም። በጣም ብዙ ስህተቶች ነው የሠራሁት። እነዚያ ስህተቶች ግን ያለኝን አላማ ለማሳካት፣ በውስን ሪሶርስ እና በከፍተኛ ጫና ሥር ሳደርጋቸው ስለነበር የተፈጸሙ እንጂ፣ አንድን ሰው ለመጉዳት፣ አንድን ቡድን ለመጉዳት አይደለም። ዓላማውን ለማሳካት ነው" ብሏል።

". . . በስተመጨረሻ ደግሞ ስትራቴጂ የመለወጥን ትግል ስላሳካን፤ ስኬቱ፣ የነበሩ ስህተቶችንም፣ የነበሩ ጉድለቶችንም፣ በእኔም ላይ የደረሱ ጉዳቶችንም የሚያካክስ ነው። ሁሉንም ነገር ዞር ብዬ ሳየው ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዘነ ሆኖ ስላየሁት፣ ለደረሰብኝም ለሁሉም ነገር አይቆጨኝም።" ሲል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል።
Bilal Nur

07 Dec, 18:57

113

#update

" የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነው " - የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል

" ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነው " ሲል የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።

ማዕከሉ እንዳስታወቀው የሲስተሙን ቮልቴጅ በማረጋጋት የተቋረጠውን ኃይል ደረጃ በደረጃ ለመመለስ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው።

በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች እንዲሁም በክልል ከተሞች የተቋረጠው  ኃይል ወደነበረበት መመለሰ መጀመሩን ገልጿል።

የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ አልተፈታም።

ችግሩ ሙሉ በሙሉ እስኪፈታ ድረስ በትዕግስት ተጠባበቁ ተብሏል።