ADISS ABEBA UNIVERSITY @adissabebauniversity Channel on Telegram

ADISS ABEBA UNIVERSITY

@adissabebauniversity


University

ADISS ABEBA UNIVERSITY (English)

Welcome to ADISS ABEBA UNIVERSITY Telegram channel! Here, you will find all the latest updates and information about one of the leading universities in Ethiopia. Adiss Abeba University is known for its academic excellence, innovative research, and commitment to shaping the future through education. Whether you are a current student, alumni, or just interested in learning more about this prestigious institution, this channel is the place to be

Adiss Abeba University offers a wide range of programs in various fields such as arts, sciences, engineering, business, and more. The university is dedicated to providing high-quality education and fostering a culture of learning and growth among its students. With state-of-the-art facilities, experienced faculty members, and a supportive community, Adiss Abeba University is the perfect place to pursue your academic goals

Stay informed about upcoming events, seminars, workshops, and other activities happening at Adiss Abeba University through this channel. Get insights into the latest research breakthroughs, student achievements, and alumni success stories. Join a community of like-minded individuals who are passionate about education and making a difference in the world

Whether you are considering applying to Adiss Abeba University, are a current student looking for resources, or simply want to stay connected with the university community, this Telegram channel has something for everyone. Don't miss out on the opportunity to be part of a vibrant and dynamic academic environment. Join ADISS ABEBA UNIVERSITY channel today and discover the endless possibilities that await you at this esteemed institution.

ADISS ABEBA UNIVERSITY

27 Jan, 14:47


https://t.me/Addisababauniversity/171

ADISS ABEBA UNIVERSITY

27 Jan, 14:46


Online Registration Procedure for First Year Graduate Students (Regular and Extension)

Dates of Registration: October 31, 2022 for Regular Students
October 29 and 30, 2022 for Extension Students

First Semester classes begins: November 03, 2022

Please See Online Registration Procedure Below:
https://t.me/adissabebauniversity

ADISS ABEBA UNIVERSITY

27 Jan, 14:45


All students of Addis Ababa University

Addis Ababa University wishes you a safe and successful 2022/23 (2015) academic year. As per the academic calendar, the upcoming registration of regular and extension existing and new students will be as follows.

1.2nd year and above undergraduate student’s registration is on November 01 and November 02, 2022.

2.Registration of new and existing regular postgraduate students is on October 31, 2022.

3.Registration of new and existing extension postgraduate students and 2nd year and above undergraduate extension students is on October 29 and October 30, 2022.

4.Classes for all postgraduate students and 2nd year and above undergraduate students will start on Thursday, November 03, 2022.

5.First Year undergraduate students who entered in 2014 will report to their campuses on Saturday October 29, 2022 and classes will resume on October 31, 2022.

Addis Ababa University Registrar

https://t.me/adissabebauniversity

ADISS ABEBA UNIVERSITY

27 Jan, 14:44


ቅሬታ ማቅረብ ተጀምሯል ‼️

👉ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።
https://t.me/adissabebauniversity

ADISS ABEBA UNIVERSITY

27 Jan, 14:43


20 ሺሕ ተማሪዎች በፈተና ደንብ ጥሰት ተቀጥተዋል

በ2014 የትመህርት ዘመን ለፈተና ከተቀመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል፣ 20 ሺሕ 170 ተማሪዎች በተለያዩ የፈተና ደንብ ጥሰቶች መቀጣታቸው ታውቋል።

ተማሪዎቹ የተቀጡት በሦስት ዓይነት የፈተና ደንብ ጥሰቶች ሲሆን፣ በግል የፈተና ደንብ ጥሰት 1 ሺሕ 151 ተማሪዎች፣ በቡድን የፈተና ደንብ ጥሰት የፈጸሙ 5 ሺሕ 329 ተማሪዎች፣ እንዲሁም ፈተና ጥለዉ በመሄድ የተቀጡ 13 ሺሕ 690 ተማሪዎች ናቸዉ።

የፈተና ደንብ ጥሰት ፈጽመዋል ተብለው ከተቀጡ ተመሪዎች መካከል፣ 19 ሺሕ 604 ያክሉ የአማራ ክልል ተማሪዎች ናቸው። ምንም ጥሰት ያልተገኘባቸው ጋምቤላና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ናቸው።

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡ 985 ሺሕ 354 ተማሪዎች መካከል፣ 77 ሺሕ 98 ተማሪዎች በተለያዩ ምክንያቶች ፈተና አልወሰዱም።

እንዲሁም ፈተናውን ከወሰዱ 908 ሺሕ 256 ተማሪዎች መካከል፣ በፈተና ደንብ ጥሰት የተቀጡ ተማሪዎችን ሳይጨምር 896 ሺሕ 520 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።
https://t.me/adissabebauniversity

ADISS ABEBA UNIVERSITY

27 Jan, 13:32


ትምህርት ሚኒስቴር ፦

- በሀገር ደረጃ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት በተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 ፤ 666 ሲሆን በማህበራዊ ሳንይንስ ከ600 ፤ 524 ሆኖ ተመዝግቧል።

- በፆታ በተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 ፤ ወንድ 666 ሴት 650 ፤ በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ወንድ 516 ፤ ሴት 524

- በአጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ በማህበራዊ ሳይንስ ከ500 እና በላይ ያስመዘገቡ 10 ተማሪዎች፤

- በአጠቃላይ በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እና በላይ ያስመዘገቡ 263 ተማሪዎች ናቸው።

https://t.me/adissabebauniversity

ADISS ABEBA UNIVERSITY

27 Jan, 13:30


#MoE

ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አሰራር ለመከተል ማቀዱን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት ከግማሽ በላይ ያመጡት 30 ሺህ ገደማዎቹ ተማሪዎች በሚቀጥለው ዓመት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲ ገብተው የአንደኛ ዓመት ተማሪ ይሆናሉ።

ቀሪዎቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም መሰረት በማድረግ፤ የተሻለ ያመጡት ተመርጠው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ እንደሚደረግ አስረድተዋል።

ይሁንና እነዚህ ተማሪዎች በቀጥታ የዩኒቨርስቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንደማይሆኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቁመዋል።

ተማሪዎቹ " የደከሙባቸው ትምህርቶችን” ለአንድ ዓመት በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እየተማሩ ከቆዩ በኋላ፤ በዓመቱ መጨረሻ ፈተና ወስደው ካለፉ በዩኒቨርስቲዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪ ሆነው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።

Credit : ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

https://t.me/adissabebauniversity

ADISS ABEBA UNIVERSITY

27 Jan, 13:29


መግለጫ‼️

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት ዋና ዋና ግኝቶችን ይፋ አደርጓል!

የትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት ዋና ዋና ግኝቶችን ይፋ አድርጓል።የትምህርት ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2014 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች በአዲስ መልክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርስቲዎች  መሰጠቱን አስታውሰው ይህ አዲስ አካሄድ ቀጣይ እርምጃዎቻችንን የሚለኩ ነበሩ ብለዋል።

ሀቀኛ እና ትክክለኛ የተማሪዎችን የትምህርት ክህሎት በመለካት  የፈተና ሂደቱ ከኩረጃ፣ የፈተና ስርቆት የፀዳ ነው ተብሏል።በዚህ ፈተና ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ የሚኮሩበት ነው ተብሏል።

በ2014 ዓም የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985ሺ 3354 ተማሪዎች ሲሆኑ ለፈተና የቀረቡት 92.2 % 908ሺ ሺህ 256 ተማሪዎቹ ሲሆኑ 77ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም ተብሏል።

በደንብ  ጥሰት ፣ለመኮራረጅ በመፈለግ እና በሌሎች ምክንያቶች 50ሺህ 170 ተማሪዎች ሳይፈተኑ ቀርተዋል።

በ2014 የትምህርት ዘመን 899ሺህ 520 ተማሪዎች ተፈትነዋል ።

በፆታ ማዕከልነት የአማካይ ውጤት በወንዶች 30.2 እንዲሁም ሴቶች 28.09 % አማካይ ውጤት አስመዝግበዋል።

በትምህርት ዘርፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ በተሻለ ውጤት ያስመዘገቢ ሲሆን  የተፈጥሮ ሳይንስ 31.63 ከመቶ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ 27.79 ከመቶ በአማካኝ አስመዝግበዋል።

በክልል ደረጃ ይህየ ነው የሚባል የውጤት ልዮነት እንደሌለ የተገለፀ ሲሆን አዲስ አበባ፣ሀረሪ እና ድሬደዋ የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል።

ከተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወንድ ከ 700፤  666 ያስመዘገበ ሲሆን 650 ሴት ተማሪ አስመዝግባለች።በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ወንድ 524 አስመዝግቧል።እነዚህ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎይ በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና እና ሽልማት ይሰጣቸዋል ተብሏል።

https://t.me/adissabebauniversity

ADISS ABEBA UNIVERSITY

27 Jan, 13:28


ትምህርት ሚኒስቴር ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደማይቀላቀሉ ገለፀ‼️

ነገር ግን የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት በውጤታቸው መሰረት ተጨማሪ ተማሪዎችን በመቀበል ለቀጣይ ዓመት ዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት እንዲያገኙ ይሰራል መባሉን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግባል።

https://t.me/adissabebauniversity

ADISS ABEBA UNIVERSITY

27 Jan, 13:28


በ12ኛ ብሄራዊ ፈተና ተማሪ ሚኪያስ አዳነ ከደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ከፍተኛ ነጥብ 666 ማስመዝገቡን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ገለጹ።

የደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር በለጠ ሀይሌ በሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ትምህርት ቤቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ካስፈተናቸው 69 ተማሪዎች ከ20 በላይ የሚኾኑት ከ600 በላይ ነጥብ አስመዝግበዋል ብለዋል።
አስካሁን በተገኘ መረጃ 5 ሴት ተማሪዎች ከ600 በላይ ነጥብ ማምጣታቸውንም ነግረውናል።

ተማሪ ሚኪያስ አዳነ ከደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ወገል ጤና ከተማ የተገኘ ተማሪ መኾኑን የገለጹት ርዕሰ መምህሩ የኮቪድ እና የጦርነት ተፅዕኖ ባይኖር ከዚህ በላይ ነጥብ ማስመዝገብ ይቻል ነበር ብለዋል። እስካሁን የ47 ተማሪዎች ወጤት መረጋገጡን የተናገሩ ሲኾን 25 ተማሪዎች ከ500 በላይ አስመዝግበዋል።

https://t.me/adissabebauniversity

ADISS ABEBA UNIVERSITY

02 Jan, 11:20


https://youtube.com/shorts/GNqSpTdc6hg?feature=share

ADISS ABEBA UNIVERSITY

13 Oct, 17:45


የ2014 ዓ.ም የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም ፈተናውን ይወስዳሉ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች የጊዜ ሰሌዳ፦

➤ ጥቅምት 05 እና 06/2015 ዓ.ም
      ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።

➤ ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም
     ገለጻ ( ኦሬንቴሽን) ለተፈታኞች ይሰጣል።

➤ ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም
     ፈተናው ይሰጣል።

➤ ጥቅምት 12 እና 13/2015 ዓ.ም
      ተፈታኞች ወደ አካባቢያቸው ይመለሳሉ።

https://t.me/adissabebauniversity

ADISS ABEBA UNIVERSITY

10 Oct, 16:37


ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የመጀመሪያ ቀን ውሎ ተጠናቋል።

ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች በ130 ማዕከላት ብሔራዊ ፈተናውን እየወሰዱ ሲሆን በ128ቱ ማዕከላት በሰላም ተሰጥቷል፡፡

ፈተናው እየተሰጠባቸው ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል በሁለት የመፈተኛ ማዕከላት ችግር ማጋጠሙ ተገልጿል።

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ በምስራቅ ጎጃም እናርጅ እናውጋ ወረዳ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት "አንፈተንም" በማለት ለቀው መውጣቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ረፋዱን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

የተማሪዎቹ ምክንያት በአግባቡ ተጣርቶ የሚወሰደው እርምጃ ይገለጻል ብለዋል።

በሌላ በኩል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ የሚገኝ ድልድይ ተደርምሶ በተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል።

በአደጋው ጉዳት ያጋጠማቸው ተማሪዎች ህክምና የተደረገላቸው ሲሆን ተማሪዎቹ ካገገሙ በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ እንደሚደረግ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በድልድዩ መደርመስ አደጋ የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን የሲዳማ ክልል ሠላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ተናግረዋል።

በአደጋው 310 ተማሪዎች ቀላልና 110 ተማሪዎች ላይ መካከለኛና ከባድ ጉዳት ደርሷል። 20 ተማሪዎች የአጥንት ስብራት እንዳጋጠማቸው ኃላፊው አስረድተዋል።

ቢሮው ተማሪዎች ተረጋግተው ወደ ግቢው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ፈተናውን አስመልክቶ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን መመሪያ እንዲከታተሉ አሳስቧል።

       https://t.me/adissabebauniversity

ADISS ABEBA UNIVERSITY

10 Oct, 05:59


መልካም እድል ለተፈታኞች🙏🙏🙏🙏

በመላ ሀገራችን ዛሬ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መሰጠት ተጀምሯል።

ለሁሉም ተፈታኞች መልካም ዕድል እንመኛለን።
https://t.me/adissabebauniversity

ADISS ABEBA UNIVERSITY

09 Oct, 09:40


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዛሬዉ እለት በተዘጋጀላቸው ተሽከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ዙር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ፌደራል ቴክኒክና ስልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዉ ከ11ዱም ክፍለ ከተማዎች ሽኘት የተደረገላቸዉ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዛሬዉ እለት ወደ መፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

ከነዚህ የመፈተኛ ጣቢያዎች አንዱ በሆነዉ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመግባት ላይ የሚገኙ ሲሆን በቦታዉ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፎ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በመገኘት ምልከታ በማድረግ ተማሪዎችን አበረታተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዛሬዉ እለት በተዘጋጀላቸው ተሽከርካሪ ወደፈተና ጣቢያዎች ገብተው በዩኒቨርሲቲዎቹ ኦረንቴሽን ተሰቷቸው የፊታችን ሰኞ ፈተናውን መፈተን እንደሚጀምሩ ቀደም ብሎ መገለጹ ይታወቃል።

https://t.me/adissabebauniversity

ADISS ABEBA UNIVERSITY

09 Oct, 09:39


የ12ኛ ክፍል ፈተና ፈታኞች እና አስተባባሪዎች በፈተና አሰጣጡ ዙሪያ በዩኒቨርሲቲዎች ገለጻ ተደረገላቸው።

የተለያዩ ዩኒቨርሲዎች ለፈታኞች እና አስተባባሪዎች በፈተናው አሰጣጥ ዙሪያ ገለጻ መስጠታቸው ተመላክቷል፡፡

ከመላው ኢትዮጽያ ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በፈታኝነት ወደ ተለያዩ ዩኒቨርሲቲያችን ለተመደቡ መምህራን ኦረንቴሽን ተሰጥቷል።
https://t.me/adissabebauniversity

ADISS ABEBA UNIVERSITY

09 Oct, 09:37


የሀገራችን የነገ ተስፋዎች ሆይ--ደ/ር አብይ

ኢትዮጵያ እናንተን ስታይ ተስፋ ነው የሚታያት። ይህ የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ። እናንተን እዚህ ለማድረስ ወላጆች፣ መምህራን እና መላው ማኅበረሰብ ለዓመታት ለፍቷል። ውጤቱን የምታሳዩት ከኩረጃና ከስርቆት ነጻ ሆናችሁ፣ በራሳችሁ ተማምናችሁ፣ ፈተናውን ስትፈተኑ ነው።

የተሰጣችሁን መመሪያ አክብሩ፤ ተረጋግታችሁ ፈተናችሁን ሥሩ፤ በምንም አትሸበሩ፤ የኢትዮጵያ አምላክ ዕውቀቱን ይግለጥላችሁ።
https://t.me/adissabebauniversity

ADISS ABEBA UNIVERSITY

08 Oct, 18:50


ማሳሳቢያ

ተፈታኞቻችን ወደ መፈተኛ ማዕከላት ገብተዋል፡፡ የተከለከሉ ነገሮችን ማንም ተፈታኝ ይዞ እንዳይገባ ከወረዳ ጀምሮ ገለጻ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም አካላዊ ፍተሻ ተደረጓል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተለያየ የማጭበርበሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም የተከለከሉ ነገሮችን በተለይም ተንቀሳቃሽ ስልክን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፡፡ ድርጊቱ ከፍተኛ የፈተና ደንብ ጥሰት በመሆኑ ውሳኔው ከሁሉም ፈተና የሚሰረዙ ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ ከዚህ በኃላም የተከለከሉ ነገሮችን መፈተኛ ማዕከላት (የኒቨርሲቲ) ግቢ ውስጥ ማንኛውም ተፈታኝ ይዞ ቢገኝ ከሁሉም ፈተና የሚሰረዝ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ገለጻውን ባለመቀበልና አካላዊ ፍተሻዎችን በማጭበርበር ስለፈጸመው ጉዳይ ተጨማሪ ህጋዊ ምርመራ የሚካሄድ ሲሆን እንደግኝቱም ተመጣጣኝ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል፡፡

ፈተና የሁሉም ማህበረሰብ ሀብት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለፈተና ደህንነትና ፍትኃዊነት የበኩሉን አዎንታዊ ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

https://t.me/adissabebauniversity