♨️የቀጠለ፡ ቤተ-ክርስትያን ከተነጠቀች በኃላ በሰማይ ከሙሽራው ጋር አንድ ሱባኤ ትቆያለች ሰባት አመት።ታድያ በምድር በዚህ በሰባት አመት ታላቅ መከራ ሲሆን በሰማይስ ምን አይነት ትንቢቶች ይፈጸማሉ የሚለውን እንመልከት።የበጉ ሰርግ የእራት ግብዣ ስነ ስርዕት የሚፈጸመው በሱባኤው መጨረሻ ኢየሱስ የአርማጌዶ ጦርነት ለመግጠም፣ በእስራኤል ምድርም የሺህው አመት መንግስት ለመመስረት ሊመጣ ሲል አከባቢ ከቤተ-ክርስትያን ጋር ለዘላለም ቃልኪዳን ቀለበት የሚያስርበት ድንቅ የሆነ ጊዜ ይኖራል።ያን ጊዜ ቤተ-ክርስትያን በበጉ ፊት ምንም እድፍ ነውር የሌሌባት ሁኗ ትቀርባለች።የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሤትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ።
♨️ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል።ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።ራዕይ 19፥7 እርሱም፦ ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው ብለህ ጻፍ አለኝ። ደግሞም፦ ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው አለኝ።ራዕይ19፥9 በዚህ ታላቅ የሰርግ እራት ላይ የተጠሩት ታድያ እነማን ናቸው!?እኛ በዋናነት ስንሆን በፀጋው የዳነው፣ በመቀጠል ከታላቁ መከራ የመጡ እነዚያ መልክቱን አንቀበልም ያሉትም ጭምር በክብር በበጉ ሰርግ ነጭ የተልባ ልብስ ተሰጥተዋቸው አብረው የዚህ ክብር ተቋዳሽ ይሆናሉ።እንዲሁም አማኞች በምድር ስለሰሩት ሥራ አክሊል የሚሸለምቡት ጊዜ ነው።ጳውሎስ የአክሊል ሽልማት እንደተዘጋጀለት የተናገረው።ለሱ ብቻ ሳይሆን በምድር ለምንሰራው ሥራ ሽልማትን የምንቀበልበት ጊዜ ይሆናል።2 ተኛ ጢሞ 4፥8
♨️ወደ ምድር ልመልሳችሁ በአንድ ሱባኤ ከሚፈጸሙ ትንቢቶች መካአል አንዱ የመንግስቱ ወንጌል ለአሕዛብ መመስከር ነው።ይሄ ማለት ታድያ በዛ ሱባኤ በጣም ለማመን የሚከብዱ ጊዜአት የሚታዩበት በዋናነት መለኮታዊ ፍርድ በምድር የሚፈስበት ወቅት ነው።በክፍል አንድ ሐሰተኛው ክርስቶስ ሲገለጥ በመጀመርያ ሱባኤ አጋማሽ ላይ ዓለምን ሰላም እንደሚያደርግ ከዓለም መንግስታት ጋር እስራኤልን ጨምሮ እንደሚስማማ አይተናል።ነገር ግን ሁለተኛው ሱባኤ መቆጠር በሚጀምርበት ጊዜ ከእስራኤል ጋር የተፈራረመውን የሰላም ስምምነት ያፈርሰዋል።ከሌሎቹ ጋር ያለውን ስምምነት ግን እንደተጠበቀ ነው።ይሄ የሆነበት ምክንያት ይሄ ሐሰተኛው ክርስቶስ ክብርን ስግደትን በአጭሩ አምልኮን ይፈልግና እስራኤላውያን ይሄንን ለማድረግ አእምረዋቸው አልፈቀደምና የመጣውን መከራ ለመቀበል እንቢ ይላሉ።
♨️በዚህ ጊዜ ሐሰተኛው ክርስቶስ ከሌሎች የዓለም መንግስታት ጋር በማበር እስራኤልን ለመውጋት እንቅስቃሴ የሚጀምርበት ወቅት ይሆናል ይሄ ሁለተኛው ሱባኤ መጀመርያ።አሁን ያሉት ኃያል ሀገር ከሚባሉት አንድዋ በስተምስራቅ የምትገኘው ራሽያ ናት።ራሽያና አብዛኛው የዓረብ ሀገሮች እስራኤልን ለመውጋት በሐሰተኛው ክርስቶስ መሪነት የሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ነው።በዚህ ጊዜ ሶስተኛው የዓለም ጦርነትም የሚገለጥበት ወቅት ነው።እኛ እንኳን ይሄው እያየን ለሶስተኛው የዓለም ጦርነት መንስኤ የሚመስሉ ነገሮችን ራሽያና ዩክረን እየተመለክትን ነው።በቀጣይም ስለዚህ የመጨረሻ ጦርነትና ስለ 144,000 ሰዎች ማንነት በሰፊው እንመለከታለን።
ይ----ቀ----ጥ----ላ----ል
⛩⛩ @Yezelalemhiywet ⛩⛩
⛩⛩ @Yezelalemhiywet ⛩⛩
⛩⛩ @Yezelalemhiywet ⛩⛩