ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

@orthodoxtewahedoot


በዚህ ቻናል ‘electronic (soft copy)’ ቅዱሳት መጻሕፍትና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምሮን መሰረት ያደረጉ ቪድዮዎችና ልዩ ልዩ ወቅታዊ መልዕክቶች ይተላለፉበታል።

ቀሲስ ዶ/ር ብዙአየሁ አምባዬ
ሲያትል ዋሽንግተን

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

21 Jan, 00:24


https://youtu.be/cZS-2TwMYuo

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

21 Jan, 00:24


In just 3 years, Saint Cyricus proved that salvation is not about a long life but about faithfulness to God, for "the last will be first, and the first will be last" (Matthew 20:16).
S: Own summary from Betremariam Abebaw 's recent post on Oct 20, 24

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

21 Jan, 00:23


#እንደ_አንተ_ይቅር_ባይ_ማነው?

✍️እንኳን ለሦስተኛው ሳምንት ጽጌ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

በሦስተኛው ሳምንት የሚባለውን ቃለ እግዚአብሔር ከመዝሙር እስከ ሰላም ንባቡንና ትርጓሜውን ከማብራሪያውና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሱ ጋር እነሆ!

👇መዝሙር  ከ፲  እስከ ፲፮ ቀን የሚባል።

በ፫ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ ወሥነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ወከመ ወሬዛ ኃየል መላትሒሁ ጕርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ሰማየ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
በከዋክብት ሰማየ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኵሉ ዕለት
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ወኵሉ ይሴፎ ኪያከ።

            💥ትርጉም
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ከኖኅ ጋር ቃል ኪዳንን ያቆምክ (ያደረግኽ)
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ከኖኅ ጋር ቃል ኪዳንን ያቆምክ (ያደረግኽ) ለእስራኤል ልጆችም መናን ያወረድኽ
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረድኽ በአበቦችም ምድርን ያስጌጥኽ
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
በአበቦች ምድርን ያስጌጥኽ የምድረ በዳ እንስሳት አራዊትንም ከቅዱሳንህ ጋር ያስማማኽ
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ጉንጮቹ እንደ ወይፈን (ለጋ) ዋላ ናቸው፤ ጉሮሮው ጣፋጭ ነው፤ አረማመዱ እንደ ፌቆ ነው
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ሰማይና ምድርን የፈጠርኽ አንተ ነህ፤ ጨሐይን ጨረቃን የአስማማኽ አንተ ነህ
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ሰማይን በከዋክብት ያጋረድኽ፤ ምድርንም በአበቦች ያስጌጥኽ
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ሰንበትን ቀደሳት (ለያት) አከበራት ከፍ ከፍ አደረጋት ከዕለታት ሁሉ በላይ አደረጋት
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ሁሉ አንተን ተስፋ ያደርጋል።
            👇ማብራሪያ
👉ጠቅለል አድርጎ ለማብራራት ያህል፦

✔️መጀመሪያ ላይ ሁለት ጊዜ "እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው? (፪)" ማለቱ ለአጽንዖተ ነገር ነው።
በብሉይም በሐዲስም ደጊመ ቃል የተለመደ ነው። "አዳም አዳም፣ አብርሃም አብርሃም፣ ማርታ ማርታ፣ አልዓዛር አልዓዛር ፣ አማን አማን እብለክሙ" እንዲል
ነገሩን ለማጽናት ለማጉላት ደጋግሞ ይነገራልና ከእዚህም ሊቁ የእግዚአብሔርን ይቅር ባይነት አጉልቶ ለመናገር ገና ሲጀምር በደጊመ ቃል ጀምሮ ያንኑ ኃይለ ቃል አዝማች በማድረግ ይዘልቀዋል።
በዚህ መዝሙር እግዚአብሔር በቸርነቱ ምድርን ዳግመኛ በጥፋት ውኃ እንደ ማያጠፋት ለኖኅ ቃል ኪዳን መግባቱን ያስረዳናል (ዘፍ፱፥፲፩) ለእስራኤላውያን መና ከደመና አውርዶ መመገቡን (ዘጸ፲፮፥፴፭) በአበቦች ምድርን ማስጌጡን የሰማይም የምድርም ፈጣሪ መሆኑን (ዘፍ፩፥፩)  እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰማይና ምድርን ፈጠረ ሲል ሙሴ እንደ ወርቅ አንከብሎ እንደ ሸማ ጠቅልሎ መሆኑን ልብ ይሏል።
ሰንበትን የቀደሳት ያከበራት ከሌሎች ዕለታት ይልቅ ከፍ ከፍ ያደረጋትና ለእኛም ዕረፍት ትሆነን ዘንድ የሰጠን እሱ ባለቤቱ እግዚአብሔር መሆኑን (ዘፍ፪፥፫) ገልጦ ከነገረን በኋላ፤
#ሁሉ_አንተን_ተስፋ_ያደርጋል!
በማለት የፍጡራን ተስፋቸው እሱ እግዚአብሔር መሆኑን መስክሮ ይፈጽማል።(መዝ፻፵፭፥፲፭)
እውነት ነው ከእሱ ውጪ ማን ተስፋ አለን ሰውንማ በእየለቱ እያየነው አይደል ወገኖቼ ሲያደማን ሲያሳድደን እንጂ ምን ተስፋ ይሆነናል። "ተስፋየ እምንዕስየ" (ቅዱስ ያሬድ) እንዲል ከእናታችን ማኅፀን ጀምሮ ይበላችው ተጭኖ ፣ የጠጣችው አንዝዞ እንዳይገድለን በማድረግ ተስፋ የሆነን እግዚአብሔር አሁንም ተስፋችን ነው።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም
“በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። (ሮሜ፭፥፭) ብሏል።


             👇ዓራራት
"በኵሉ ጊዜ ወበኵሉ ሰዓት በኵሉ ሌሊት ወበኵሉ መዓልት እግዚኣ ለሰንበት አኰቴተ ነዓርግ ለመንግሥትከ ምድረ በጽጌ አሠርጎከ"
              👇ትርጉም
የሰንበት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በጊዜው ሁሉ በሰዓቱም ሁሉ በሌሊትም ሁሉ በቀንም ሁሉ ለጌትነትህ ምስጋናን እናቀርባለን። ምድርን በአበባ አስጌጥህ።
              👇ማብራሪያ

" እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤
አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ።
እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ።
ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው።
በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ።
በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው።(ዘዳ፮፥፬-፱)  እንዲል
ጊዜ ሳንወስን በሁሉም ጊዜያት ማመስገን እንዳለብን ያስረዳል።

           👇ዕዝል
"ልዑል ውእቱ እምልዑላን፤ መሐሪ ውእቱ ዘየዓርፎ ለዓለም፤ ጻድቅ ውእቱ ይባርክ ጻድቃነ፤ ጠቢብ ውእቱ ይመይጥ ስሑታነ፤ ሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት፤ አሠርገዋ ለምድር በጽጌያት"

           👇ትርጉም
ከልዑላን ይልቅ ልዑል ነው፤ ዓለምን የሚያሳርፈው እሱ ይቅር ባይ ነው፤ የባሕርይ አምላክ ነው ጻድቃንን "ንዑ ኃቤየ ቡሩካኑ ለአቡየ" ብሎ ያመሰግናቸዋል፤ ጠቢብ ነው ስሑታንን ይመልሳል (አዳምና ሔዋን ስተው ዕፀ በለስን በልተው በበለስ ቅጠል በተሸሸጉ ጊዜ "አዳም አዳም ወዴት አለህ?" ብሎ በጥበብ ሳያስደነግጥ ጠርቶ መልሷቸዋል ንስሐ  እንዲገቡ አድርጓልና "ጠቢብ ነው ስሑታንን ይመልሳል" አለ ሊቁ) ሰንበትን ለዕረፍት ሠራ ምድርንም በአበቦች አስጌጣት"

          👇ሰላም
በ፫ ናሁ አስተርአየ ጽጌ ነው። እንደ መጀመሪያው ሳምንት ነው ትዌድሶ ላይ ተጽፏል ።

👉የሊቁ በረከት ይደርብን  የእመቤታችን ምልጃ አይለየን!!!

👇በዚህ ዕለት በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ቅዱሳት መጻሕፍት።
             ፩ኛ,  ፩ቆሮ ፲፥፩  እስከ ፲፬
             ፪ኛ,  ራእይ ፲፬፥፩ እስከ ፮
             ፫ኛ,  የሐዋ ፬፥፲፱  እስከ ፴፩

ምስባክ፦  ጻድቅሰ ከመ በቀልት ይፈሪ
               ወይበዝኅ ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ
                ትኩላን እሙንቱ ውስተ ቤተ እግዚአብሔር
ወንጌል፦ ማቴዎስ ፲፪፥፩   እስከ ፴፪
ቅዳሴ፦ ዘእግዝእትነ (ጐሥዓ)

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

21 Jan, 00:22


''ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤''፩ኛ ተሰ. ፭፥፲፬
''ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።''፩ኛ ቆሮ. ፲፬፥፵
https://youtu.be/9DoBH0Nya3E

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

21 Jan, 00:22


https://youtu.be/lqGJ6kx49DQ

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

21 Jan, 00:21


Saint Photius, Patriarch of Constantinople

Join for updates👇

youtube.com/@OrthodoxTewahedo-

https://t.me/OrthodoxTewahedoOT

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

21 Jan, 00:21


Blessed Theophylact, Archbishop of Ochrid and Bulgaria

Join for updates👇

youtube.com/@OrthodoxTewahedo-

https://t.me/OrthodoxTewahedoOT

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

21 Jan, 00:21


የአቋም መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ የአቋም መግለጫ

“ትውልደ ትውልድ ይንእዱ ምግባሪከ ወይዜንዉ ኃይለከ - የልጅ ልጅ ሥራህን ይናገራሉ፤ ያመሰግናሉ፣ ከሃሊነትህን ይናገራሉ ያስተምራሉ” መዝ 144 ቁ 4

ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት፣ ዓለምአቀፋዊት የሆነቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያዊ ተልዕኮዋ ረጅም ዘመናትን ሰማያዊውን ጥበብንና ምድራዊውን ዕውቀትን በማስተማር፣ የሀገርና የወገንን እምነትና ፍቅር ምንነት ከተግባር ጋር፣ ሰላምና አንድነትና በማስፈን፣ ለሰው ልጅ ዘለዓለማዊ ድኅነት ሌሌት ከቀን ያለማቋረጥ ሰዓት ሳይገድባት፣ መልክዓ ምድር ሳይገድባት፣ የሰው ባሕልና ቋንቋ ሳይወስኗት፣ ትውልድን፣ ከትውልድ፣ ዘመንን ከዘመን፣ ሰማያውያን ከምድራውያን፣ ፍጡራንን ከፈጣሪ ስታገናኝ ኖራለች፡፡ ለሰው ዘር ጥበብን፣ ለትወልድ ታሪክና ትውፊትን፣ ስትቀምር፣ ነፃነትና ሰብዓዊ ክብርን በዐውደ ምኅረቷ ስታውጅ፣ በአባቶችና በሊቃውንት በሕየወት ሰሌዳ፣ በደመቀ ቀለም በቃልም በመጽሐፍም ስታስተጋባ እስከ አሁን አለች ወደፊትም ትኖራለች፡፡

ከዚህ መሠረታዊ የታሪክ ዕሴት በመነሣት ለዛሬው 43ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ደርሰናል፡፡

በዚሁ ጉባኤው በቆየባቸው ቀናት ውስጥ የቅዱስነታቸውንና የብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ አባታዊ መልእክቶች፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሪፖርት፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር አህጉረ ሰብከት ዘገባዎች፣ ከውይይት ሐሳቦች፣ ከአበው ሊቃነ ጳጳሳት መልእክቶች፣ ከቡድን ውይይትና ዘገባ በመነሣት ከቃለ ጉባኤ ሐሳብ በተጨማሪ በቅዱስ ሲኖዶስ ትኩረት ተሰጥቶባቸው በአጀንዳ ተቀርጸው ውይይትና ምክክር ተደርጎባቸው ውሳኔና መመሪያ ይደረግባቸው ዘንድ እኛም ለተፈጻሚነቱ የራሳችንን ድርሻ መወጣት እንድንችል ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የአቋም መግለጫ አቅርበናል፤

1. በጉባኤው መክፈቻ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ያስተላለፉፉልንን ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተቀብሎታል፣ ለተግባራዊነቱ ቃል ይገባል ፡፡

2. ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፉልንን አባታዊ መልእክት ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ ቃል እንገባለን፤፡፡

3. በብዙ የሀገራችን ክፍል ባለው የሰላም እጦት የተፈጠሩት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምክንያት የካህናት፣ የመነኮሳትና የምእመናን ሞትና ስደት በጥብቅ እያወገዝን በዚህ ታሪክ የማይረሳው በምድር ወንጀል፣ በመንፈሳዊው ዓለምና በሰማይ ኃጥያት የሆነ እኩይ ተግባር የተሰማራችሁ ሁሉ ወደ ርኃራኄ ልብ እንድተመለሱ ጉባኤው በአጽንኦት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

4. የሰላም ዕጦት ጉዳይ ምንም እንኳ ዓለም አቀፍ ቢሆንም ሀገራችንም በተከሰተው ግጭትና ጦርነት ምክንያት ሰላም ካጣች ሰንብታለች፣ ስለሆነም ቅዱስ ሲኖዶስ በዓለም የሚደነቅ፣ ለሀገር ተገን የሚሆን አስደነቂ ውሳኔ እንደሚወስን ተስፋችን ጽኑ ነው፣ ጸሎታችንም ነው፤ የአገልጋዮች እንባ የሚታበስበት፣ ለነገ ታሪክ የትውልድ ተወቃሽ ከመሆን ይልቅ፤ የሰላምና እርቅ ምሳሌ የምንሆንበት ከፍተኛ የሰላም ሥራ ልዩ የሆነ የሰላም ኮሚቴ ተቋቁሞ ዘላቂ ሰላምን ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን የሚያመጣ ሥራ እንዲሠራ ጉባኤው ያሳስባል፡፡

5. የዚህን ዓለም ተድላ ንቀው፣ ዳዋ ለብሰው ጤዛ ልሰው በገዳም ተወስነው ድምጸ አራዊቱን ግርማ ሌሊቱን ታግሰው ለመላው የሰው ዘር የሚጸልዩ ይህን ይደግፋሉ ያንን ይቃወማሉ የማይባሉ ገዳማውያን መነኮሳት ከየበዓታቸው ተጎትተው ወጥተው የተገደሉበት ሁኔታ በሀገራችን መከሰቱ ጉባኤውን እጅግ አሳዝኖታል፤ ይህ ጉዳይ ቀጣይነቱ እየታየ ስለሆነ የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን የሕግ ሥራ በመሥራት የሰው ልጅ ከአምላክ የተሰጠውን የመኖር መብት፣ የእምነት ነፃነት፣ የመዘዋር ተፈጥሯዊና ሰብዓዊ መብት በሀገራች እንዲከበር ያሳስባል፡፡

6. በታሪካችን ያላየነው ከአባቶቻችን ያልሰማነው በመጻሕፍት ያላነበብነው ከኢትዮጵያ ባሕልና ሥነ ልቡና ውጪ በሆነ መንገድ ሰዎችን ለገንዘብ ሲባል ማገት በተለይም ፊትና ኋላ፣ ግራና ቀኝ፣ እሳትና ውኃ ያለዩ ሕጻናት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው፣ ወጣቶችና አረጋውያን ሳይቀር እያተገቱ የሚሰቃዩበትና የሚደፈሩበት ሁኔታ የገጠመንን ፈተና ክብደቱን የሚያሳይ መሆኑ ይህ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት መፍትሔ እንዲበጅለት ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፡፡

7. ጥላቻና የጥፋት ቅስቀሳዎች፣ በዜጎች መካከል አለመተማመንና መለያየት፣ ለሀገር አንድነትና የሕዝብ አብሮነት ጠንቅ፣ ለወደፊቱ አስጊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች የበዙበት፣ የትውልዱ የወደፊት በሰላምና በተረጋጋ ሁኔታ የመኖር ዋስትና እየጠፋ፣ በርካታ ወጣቶች በስደትና በመፈናቀል ላይ ያሉበት ሁኔታ በመኖሩ የጥላች ንግግር፣ ዘለፋና ያልተገባ ትችትና መናናቅ ማንንም የማያንጽ ክፉ ትምህርት፣ ለሀገርም፣ ለሕዝብም የማይጠቅም ሁሉንም የሚያጠፋ ስለሆነ በእንዲህ ያለ ተግባር መገናኛ ብዙኃን በመጠቀም የተሰማራችሁ፣ ሁሉ በሚያፋቅርና በሚያዋድድ ተግባር እንድትሰማሩ ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፣ ቅዱስ ሲኖዶስም ለዚሁ ትኩረት ሰጥቶ መመሪያና ውሳኔ ያወጣ ዘንድ በአጽንኦት እንጠይቃለን፡፡

8. በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 20 በእንተ ሰማዕታት የጌታችንን ትምህርት መሠረት በማድረግ በተሠራው ቀኖና ካህናትና ምእመናን ሰማዕትነትን የተቀበሉበትን ቀን መዘከርና ማክበር፣ የከበረ አጽማቸውን በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን በክብር ማስቀመጥ፣ ቤተሰቦቻቸውንና በእነሱ ሥራ ይተዳደሩ የነበሩ የሰማእታት ቤተሰብ በሚል መርዳት የተደነገገ ቀኖና ነው፤ ይህን በማድረግ የሰማዕትነት ዋጋን እናገኛለን፣ ቤተ ክርስቲያነን እናጸናለን፤ በዚህ ቀኖና መሠረትና ከሰብዓዊ ርኅራሄ በመነሣት በሰማዕትነት የተለዩን ወገኖች መታሰቢያቸው እንዲደረግ፣ ቤተሰቦቻቸውና ጉዳተኞችን ወላጆቻውን ያጡ የካህነትና የምእመንና ጨቅላ ሕጻናትና ያልደረሱ ልጆች፣ ያለጧሪ የቀሩ አረጋውያን የቤተ ክርስቲያንን እንክብካቤ በጥብቅ ይፈልጋሉ፤ ለዚህ መፍትሔ እንዲሆን በውጭና በሀገር ውስጥ ያሉ አህጉረ ሰብከት ያካተተ አስቸኳይ ዓለም አቀፍ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጥበት እያሳሰብን ለተግባራዊነቱም ሁላችንም ቃል እንገባለን፡፡

9. በአንዳንድ አካባቢዎች ሕግንና የአምልኮ ነፃነት ሰብዓዊ መብትን በመጣስ የመስቀል ደመራና የባሕረ ጥምቀት ቦታ መወሰድ ሃይማኖታዊ አለባበስና መስቀል መያዝን በመከልከል የአንገት ማዕተብን መበጠስ፣ በኦርቶዶክሳውያን ላይ እንግልትና ወከባ መፍጠር አሳዛኝ በመሆኑ ድገርጊቱን አጥብቀን እየተቃወመን በቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ውይይት እንዲደረግበት ጉባኤው ያሳስባል፡፡

10. ቤተ ክርስቲያን እንኳንስ ተናግራ ሰማች ሲባል የሚያስደነግጥ ግርማና መታፈር፣ መከበርና መወደድ የነበራት በመሠረተችው ሀገር የምትሳደድበት፣ የመሪዎቿ አባቶች ጥሪ የማይከበርበት፣ የሰላም ጥሪ ድምጽዋ የማይሰመባት፣ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በመፈተሸ ክብርና ልዕልናዋ እንዲመለስ በቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ውይይትና ጥልቅ ምክክር እንዲደረግ መፍትሔም እንዲፈለግለት ጉባኤ ያሳስባል፡፡

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

21 Jan, 00:21


11. ሙስና፣ ዘረኝነት፣ ጎሠኝነት፣ ቡድነኝነት፣ አድሎዓዊነትና ግለኝት በተመለከተ በጋራ በአንድ ድምጽ በመነሣት ይህንን ክብረ ነክና አጋላጭ፣ ለቤተ ክርስቲያን እድገትና ለሐዋርያዊ ተልእኮ እንቅፋት፣ የቤተ ክርስቲያን ማንነት ለሌላቸው ግለሰቦች መደበቂያ፣ በጥቂት ግለሰቦች በደልና ጥፋት በንጽሕና በቅድስና የሚያገለግሉ፣ ካህናትንና ሠራተኞችን የሚያሳፍሩ፣ ምእመናንን የሚያሸማቅቁ በመሆናቸው እነዚህን ክፉ ደዌያት ስም አጠራራቸውን ከቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለማስወገድ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በጥናትና በቁርጠኝነት ላይ የተመሠረተ፣ የጥፋት በራቸውን በዘላቂነት የሚዘጋ ሥልት እንዲቀይስ ጉባኤው ያሳስባል ፡፡

12. በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት እስከ አሁን ቤተ ክርስቲያን በፈረሱባት ሕንጻዎችና ቤቶች ምትክ ቦታ በመስጠት ጉዳቷን ለመቀነሰ የተደረገውን ጥረት ጉባኤው እያደነቀ፤ በተሰጡት ይዞታዎች ላይ በአጭር ጊዜ ግንባታውን በማካሄድ የአባቶችቻንን አሻራ መልሶ በመትከል፣ ይዞታውን ማስከበርና የተቋረጠውን ገቢ ማስቀጠል እንዲቻል ብርቱ ጥረት እንዲደረግ ጉባኤው እያሳሰበ፤ የኮሪደር ልማት የተባለው ጉዳይ በሌሎች የክልል ከተሞችም እየተስፋፋ ስለሆነ በቀጣይ ለሚነሡ የይዞታ ጥያቄዎች ለሚከሰቱ ችግሮች ከወዲሁ ዝግጅት እንዲደረግ፡፡

13. አዳዲስ አማኞችን አሳምኖ ለሥላሴ ልጅነት ማብቃት፣ የአዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት መተከል፣ መታነጽና መባረክ የታየው ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ እመርታ ሁሉን ያስደሰተ በመሆኑ ከዚህ በበለጠ አጠናክረን ለመሥራት ቃል እንገባን፡፡

14. የቅዱስ ባኮስ የቅድስና ዕውቅና ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ስትዘግበው የቆየ ቢሆንም ጽላት ተቀርፆ እንዲከበር መደረጉ አስደሳች ሲሆን ለሀገር በረከት፣ ለትውልድ የመንፈሳዊ ሕይወት አርአያ፣ ለቅድስና ፍኖት የሆኑ ነገርግን የማይታወቁ የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ቅዱሳን ታሪክና ገድል በማጥናት እንዲዘከሩ እንዲደረግ ጉባኤው ያሳስባል፡፡

15. በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የተከፈቱ መንፈሳውያን ኮሌጆችና የካህናት ማሠልጠኛዎችም በአጥጋቢ ሁኔታ ሥራ መጀመራቸው፣ በዚህ ዘርፍ በእጥፍ እየጨመረ የመጣው ዕድገትና ውጤት ጉባኤው ያደነቀ ሲሆን ወደ ሥራ ለመግባት በሂደት ላይ ያሉት በርካታ መንፈሳዊ ኮሌጆች እየተስፋፉ ያሉ የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ ዘመናዊ የትምህርት ተቋማት በአጠቃላይ ሁሉም ትምህርትን የሚመለከት ጉዳይ በትምህርት ኮሚሽን ተቋቁሞ ጥናት በማድረግ እንዲስፋፉ ጉባኤው ያሳስባል፡፡

16. በሰላም መታጣትና በቀኖና ጥሰት ምክንያት መላው ወለጋ አህጉረ ስብከት ለበርካታ ወራት ከማእከሉ ጋር ያለው ግንኙነት ተቋርጦ ከቆየ በኋላ በቅርቡ በሀገረ ሰብከቱ ሊቀ ጳጳስ ወደ መዋቅር መመለሳቸው ጉባኤውን በእጅጉ አስደስቷል፤ ስለሆነም ቀሪ ሥራዎች ተጠናቀው የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እንዲጠበቅ፣ በሌሎችም አካባቢዎች ለተፈጠሩት የመዋቅር ጥሰቶች ቀኖናዊ መፍትሔ እንዲበጅለት ጉባኤ ያሳስባል፡፡

17. ሐዋርያዊትና የክርስቶስ አገልጋይ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ቋንቋን በማክበር ታገለግልበታለች እንጅ በቋንቋም አትገደብም፤ ስለዚህ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ሐዋርያዊ ተልእኮ መፈጸሟ እንደተጠበቀ ሆኖ ለወደፊት የሁሉም መዓረገ ክህነት ሢመት፣ በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር ሥራ የኀላፊነት ምደባዎች፣ መሠረት እምነትን፣ ቀኖና ቤተክርስቲያንን፣ ዕውቀትና ሙያዊ ብቃትን ብቻ መሠረት ያደረገ ይሆን ዘንድ ጉባኤው በጥብቅ ያሳስባል፡፡

18. ሰበካ ጉባኤን ማጠናከር፣ ሰንበት ትምህርት ቤትን ማደራጀት፣ አብነት ትምህርት ቤቶች ማጎልበትና ማስፋፋት፣ ሕጎችና ደንቦችን በማዘጋጀት የተደረገውን ጥረት የሚያስመሰግን ሆኖ አሁን ወቅቱን የጠበቁ ሕጎችና ደንቦችን በማውጣት ሁሉም እንዲሠራበት ማድረግን፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣ የራስ አገዝ ልማትን ማሳደግና በገቢ ራስን መቻል፣ በጸደቀው የዐሥር ዓመቱ መሪ ዕቅድ መሥራት የቤተ ክርስቲያናችን ዓይነተኛ ተልእኮ በመሆኑ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ለመፈጸም ቃል እንገባለን፡፡

19. የቤተ ክርስቲያናችን የውጭ ሀገር አገልግሎት እየሰፋና እያደገ መምጣቱ በጉልህ የሚታይ ሲሆን ይህ እድገትና አደረጃጀት እንዲጠናከር፤ በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ተሳትፎ የበለጠ እንዲያድግ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ ጉባኤው ያሳስባል፡፡

20. ከውይይትና ከብፁዓን አበው መልእክቶች እንደተሰጠው መመሪያ የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና ለመመለስ፣ ለሀገራንችን ሰላምና ደኅንነት ለሰው ልጆች ሁሉ መልካም ግንኙነት የጋራ ጸሎት በኅብረት ይደረግ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ እንዲሰጥበት ጉባኤ በአክብሮት ይጠይቃል፡፡

በመጨረሻም እስከ ዛሬ ስንሰበሰብበት ከነበረው መቃረቢያ አዳራሽ ወጥተን ይህ ዛሬ የተገኘንበት አዳራሽ በአጭር ጊዜ አሁን ባለበት ደረጃ እንዲህ ጸድቶና ተውቦ የ43ኛውን አጠቃላይ ጉበኤ እንዲከናወንበት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አመራር መስጠታቸው ቁርጠኝነት ካለ ብዙ መሥራት እንደሚቻል ያሳየ፣ የሥራ ክትትልና አፈጻጸም አድናቆታችንን በመግለጽ ሐዋርያው እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖርና እንዳለው የአዳራሹ ቀሪው ሥራ ተጠናቆ በቅርቡ እንደሚመረቅ ተስፋችንን እንገልጻለን፡፡

ይህ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲፈጸም ያደረጉ በቅዱስነታቸው አባታዊ ርእሰ መንበርነት፣ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በሳልና የተረጋጋ አመራር ሁሉም መርሐ ግብሮች በተያዘላቸው ሰዓትና ጊዜ ተጠናቀው እንዲፈጸሉ የመሩንን አባቶች በረከታችሁ ይድረሰን እያልን፡፡

የጉባአው ዋና አዘጋጅ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ኀላፊና መላው ሠራተኞች፣ ሁሉም ተባባሪ አካላት በገንዘብም በጉልበትም ትብብር ያደረጉ ሁሉ በአጠቃላይ ጉባኤው አመስግኗል፡፡

ከሁሉም በላይ ለዚህ ለ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ ያደረሰንና ያስፈጸመን የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአሔር ምስጋና ይግባው አሜን ሎቱ ስብሐት ወባርኰት ወጥበብ፣ ወአኰቴት፣ ወኃይል ወጽንዕ ለአምላክነ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ቴሌቪዥን

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

21 Jan, 00:16


https://youtu.be/_h6A1gZN6EA

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

21 Jan, 00:15


የቅዱስ ፓትርያርክ መልእክት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ብፁዕ አቡነ አብርሃም 
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ
የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ 
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤
የተከበራችሁ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያውና የየድርጅቱ ኃላፊዎች፤ 
የአዲስ አበበ ሀገረ ስብከት ኃላፊዎች፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ተወካዮች፤
ከሀገር ውስጥና ከውጭ የመጣችሁ የየሀገረ ስብከቱ ኃላፊዎችና ተሳታፊዎች፤ 
በአጠቃላይ በ43ኛው ዓመታዊ ዓለም ዐቀፍ የጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ ለመሳተፍ በዚህ የተገኛችሁ በሙሉ፤
“አሠንዩ ፍኖተ ዘተሰመይክሙ ኖሎተ ከመ ትርዓዩ መርዔተ ከመ ዐሠርቱ ወክልኤቱ ሐዋርያቲሁ እለ መሀሩ በስሙ፡- ኖሎት የተባላችሁ ሆይ በስሙ እንዳስተማሩ እንደ ዐሥራ ሁለት ሐዋርያት መንጋውን ትጠብቁ ዘንድ መንገድን አሳምሩ” (ቅዱስ ያሬድ)
በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቀው ሹመት ወይም ኃላፊነት ካለ ተጠያቂነት የማይቀር ጉዳይ ነው፤ ምክንያቱም ሹመት የሚሰጠው ስራ እንዲሰራበት እንጂ እንዲሁ ለከንቱ ስላልሆነ ማለት ነው፡፡
ሹመት የመፈጸምና የማስፈጸም ሕጋዊ መሳሪያ ነው፤ መሳሪያውን በአግባቡ ከተጠቀምንበት የምንመሰገንበት፣ ያ ካልሆነ ግን የምንወቀስበት፣ ምናልባትም የምንቀጣበት አጋጣሚ ሊያስከትል ይችላል፤ ይህም በየጊዜው በሥዩማን ላይ ሲደርስና ሲፈጸም የምናየው እውነታ ነው፡፡ እኛ ካህናትና ምእመናን የእግዚአብሔርን መንግሥት ተልእኮ ልናስፈጽም በሕዝበ እግዚአብሔር ላይ የተሾምን ሥዩማን ነን፤ የመንግሥተ እግዚአብሔር ተልእኮ ከሰው ወገን አንድ ስንኳ እንዳይጠፋ መጠበቅ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የልጅነት ሥልጣን የተሰጠን እኛ ወደ መንግሥቱ በረት ያልገቡትን የማስገባት፣ ገብተው የወጡትን መልሶ የማስገባት፣ በበረቱ ያሉትን በጥሩ ውሀና በለመለመ መስክ በማሰማራት የመጠበቅ ኃላፊነት አለብን፡፡
 
ይህንን ኃላፊነታችን በትክክል ለመወጣት ከሁሉ በፊት እኛ ሥዩማን ተልእኮአችንን በውል መገንዘብ አለብን፤ ለተመደብንበት ተልእኮም በጽናት መቆም አለብን፣ በትጋትም መስራት ይጠበቅብናል፤ ከዚህም ጋር በእምነት በሥነ ምግባር በሥራ አፈጻጸም ከምንጠብቃቸው መንጋዎች በእጅጉ የላቅን ሆነን መገኘት በጣም አስፈላጊያችን ነው፡፡ በመንግሥተ እግዚአብሔር ተሹሞ ወደሥራ የተሠማራ ሰው ሥራው ፍጹም የተቃና ይሆንለት ዘንድ “ራሱን ክዶ” መስቀሉን መሸከም ግድ ይለዋል፤ ያለዚያ ውጤታማ መሆን አይቻልም፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት!
የተከበራችሁ እንግዶች!
አሁን ያለነው ሥዩማን በዚህ ዘመን ላለችው ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያት ሆነን የተሾምን ነን፤ ወደ በረቱ ያልገባ፣ ገብቶም የወጣ ካለ ማስገባትና መመለስ ያለውም በተመቻቸ መልካም አስተዳደር፣ በለመለመ ትምህርተ ወንጌል፣ በጥሩ ሥነ ምግባር አርአያ ሆኖ መጠበቅ ከኛ ይጠበቃል፡፡ ታድያ ይህንን በተግባር መተርጐም ችለናል ወይ? በጎቻችን አልቦዘኑም ወይ? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ከሁላችን ይጠበቃል፡፡ 
ይህ ዓቢይ ጉባኤ የተሰበሰበበት ምክንያትም ይህንን ተልእኮ ለማስፈጸም በሚደረገው ጥረት ያጋጠሙ ነገሮች ካሉ ለመስማትና ለመገምገም እንደዚሁም የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ በተቀመጠው መሪ ዕቅድ አማካኝነት ተልእኮውን ለመወጣት ነው፤ ‹‹የሚደርስበትን የማያውቅ የሚሄድበትን አያውቅም›› የሚለው ብሂል በአሠራራችን ቦታ እንዳይኖረው መጠንቀቅ አለብን፡፡
በአሁኑ ጊዜ የቤተ ክርስቲያናችን መዳረሻ የማይታወቅ አይደለም፤ ቤተ ክርስቲያናችን በቀጣዮቹ ዐሥር ዓመታት የት ልትደርስ እንደምትችል ቅዱስ ሲኖዶስ ባጸደቀው መሪ ዕቅድ በግልጽ ተቀምጦአል፤ ይህ መሪ ዕቅድ ሁላችንም ትኵረት ሰጥተን ለተግባራዊነቱ መረባረብ ይኖርብናል፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት!
የተከበራችሁ እንግዶች!
እንደ እውነቱ ከሆነ አሁን ባለን ክህነታዊ አገልግሎትና አስተደደር ክፍተቶች እንዳሉን የማይካድ ነው፤ ዘመኑ የፈጠረብን ጫና ሳያንስ በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጐደላቸው አሰራሮችም ለተልእኮአችን ከባድ ዕንቅፋት እየሆኑብን ነው፡፡ ሰበካ ጉበኤ የተቋቋመው በተዘረጋው መዋቅር አማካኝነት ቤተ ክርስቲያንን በማኅበረ ካህናት ወምእመናን የጋራ ጥበቃ ለአዲሱ ትውልድ ለማሸጋገር እንደሆነ ሁላችን አንስተውም፡፡ ይሁን እንጂ በቤተ ክርስቲያናችን ይህን ያህል የመልካም አስተዳደር ክፍተት እየታየ የሰበካ ጉባኤ ዓላማ ግቡን መትቶአል ለማለት ስለማያስደፍር በዚህ ዙሪያ ያሉትን ችግሮች በሙሉ ሊቀርፍ የሚችል አሰራር ቀይሶ ችግሩን ለመቀልበስ በጥናት ላይ የተመሠረተ ዘላቂና ፈጣን መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል፡፡ 
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት!
የተከበራችሁ እንግዶች!
ያለፈው ዓመት በዝቋላ ገዳምና በሌሎች አካባቢዎች አበው መነኮሳት፣ ቀሳውስት እንደዚሁም በርከት ያሉ ምእመናን በግፍ የተገደሉበት ሆኖ አልፎአል፤ አሁንም ችግሩ እየቀጠለ ነው፤ በቅርቡም በምሥራቅ ሸዋ ከነቤተሰባቸው የተገደሉ አዛውንት ካህን ሁናቴ የችግሩን ቀጣይነት ይጠቁማል፡፡ 
               በመጨረሻም፤
በሀገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ ካህናትና ምእመናን ልጆቻችን፣ የቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና ሃይማኖት፣ ቀኖና እና ሥርዓት ተጠብቆ እንዲቀጥል ለማስቻል በሚደረገው ጥረት ሁላችንም ተባባሪ እንድንሆን፣ በሀገራችን ያለው አለመግባባት በሰላምና በውይይት ተፈትቶ ፍጹም ሰላም ይሰፍን ዘንድ በጸሎትና በአንድነት እንድትተጉ አባታዊ መልእክታችንን እያስተላለፍን 43ኛው ዓመታዊ ዓለም ዓቀፍ ጠቅላላ መንፈሳዊ ሰበካ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የተከፈተ መሆኑን እናበስራለን፡፡ 
መልካም ጉባኤ ያድርግልን፤
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን፡፡ 
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፤

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

21 Jan, 00:12


https://www.youtube.com/live/FJCNmu9tGe0

1,404

subscribers

1,306

photos

9

videos