TIKVAH-ETH

@tikfahethiopia


Buy ads: https://telega.io/c/tikfahethiopia

TIKVAH-ETH

22 Oct, 18:52


❗️በመርካቶ ሸማ ተራ የደረሰውን የእሳት አደጋ መንስኤ የሚያጣራ የፎረንሲክ ምርመራ ቡድን ስራ ጀምሯል!

✍️ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል፣

✍️ በአደጋው በ7 ሰዎች ቀላል፤ በ2 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፣
              
ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓም ምሽት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሸማ ተራ ነባር የገበያ ማዕከልና በአካባቢው በአጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።የአደጋውን መንስኤ የሚያጣራ የፎረንሲክ ምርመራ ቡድን በማቀናጀት ምርመራ መጀመሩን ፖሊስ አስታውቋል።

አደጋውን እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራና ከአደጋው ጋር በተያያዘ በ7 ሰዎች ቀላል በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡አደጋውን ለመከለከል የፀጥታ ተቋማትና የአካባቢው ህብረተሰብ ላደረገው ድጋፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ አመስግኗል።

@Tikfahethiopia

TIKVAH-ETH

21 Oct, 20:30


#Update

ምሽት 1 ሰዓት አካባቢ በመርካቶ ሸማ ተራ የተነሳውን እሳት እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር ማዋል አልተቻለም።

ርብርቡ ግን እንደቀጠለ መሆኑ ተሰምቷል።

የአዲስ አበባ እሣትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሬ ግዛው ምን አሉ ?

- የእሳት አደጋው የተከሰተው 1 ሰዓት ገደማ ነው።

- እሳት መነሳቱን በሰማን ጊዜ አብዛኛዎቹ የእሳት ማጥፊያ መኪናዎች ርብርብ እንዲያደርጉ አሰማርተናል።

- መኪናዎች በወቅቱ ነበር የደረሱት፤ ከደረሱ በኃላ የእሳቱ ባህሪና ሁኔታ ሲታይ ለሌሎች አጋዥ አካላት ፦
° አየር መንገድ
° ፌዴራል ፖሊስ
° ሌሎች ከተማ ውስጥ ያሉ ውሃ አቅራቢ ተቋማት በሙሉ እንዲረባረቡ ተደርጎ እሳቱን ለማጥፋት ጥረት እያደረግን ነው።

- ቦታው በጣም አስቸጋሪ ነው።

- በሁሉም አቅጣጫ በኩል መኪና ገብቶ እሳቱን ለማጥፋት በጣም ፈትኖናል። በተለይ በዙሪያ የሚቀመጡ እቃዎች ቶሎ ተገብቶ የእሳቱን መሰረት እንዳይመታ አድርጓል።

- አካባቢው በቆርቆሮ የተያያዘ ነው። መንገዱ በጣም ጠባብ ነው። ገብተን ለማጥፋት ተቸግረናል።

- በአጋጣሚ ባለሱቆች፣ ነጋዴዎች ዘግተው ወጥተው ነበር። የቆሙ መኪኖችንም ለማስነሳት ችግር ሆኖብን ነበር።

- አሁን ላይ ከቅድሙ እየተሻሻለ ነው። የመቀነስ እና የመጥፋት አዝማሚያ አለው። በተለይ ከዚህ እንዳይሰፋ ወደታች ከወረደ በጣም ሰፊ ቦታ ነው ያለው ቆርቆሮ በቆርቆሮ እሱ ጋር እንዳይደርስ ከበን ለመያዝ ሞክረናል።

- አጋዦች ከመጡ በኃላ እሳቱ ባህሪው እንዳይሰፋ ተሞክሯል። አሁንም ህብረተሰቡ አግዞን ለማጥፋት እየሞከርን ነው። እናጠፋዋለን ብለን እናምናለን።

    @Tikfahethiopia

TIKVAH-ETH

21 Oct, 17:53


መርካቶ ሸማ ተራ ህንፃ ጀርባ ከፍተኛ እሳት አደጋ ተከስቷል
@Tikfahethiopia

TIKVAH-ETH

17 Oct, 19:26


❗️#ሰበር

የእስራኤል መንግስት የሃማስ አለቃ ያህያ ሲንዋር መሞታቸውን አረጋግጫለው አለ!

የሳራኤሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የሀማስ መሪ ያህያ ሲንዋር በእስራኤል ወታደራዊ ሃይሎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

እስራኤል ቀደም ሲል በጥቅምት 7 በሃማስ የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት በማቀነባበር ሲንዋርንበመወንጀል የእስራኤል መንግስት በጋዛ ሰርጥ አጸፋዊ ጥቃት ሰነዝራ ነበር::

በጋዛ ስትሪፕ ውስጥ የሃማስ መሪ የነበረው እስማኤል    ሃኒዬህ  በነሀሴ ወር ላይ በኢራን መገደሉን ተከትሎ ያህያ ሲንዋር መረከባቸው ይታወሳል::

@Tikfahethiopia

TIKVAH-ETH

16 Oct, 20:41


#Alert🚨

ከደቂቃዎች በፊት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ንዘረት እንደሰሙ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።

" በተለይም ፎቅ ላይ በደንብ ይታወቅ ነበር " ብለዋል።

ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በቀናት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።

ሰሞኑን በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል።

ይህም የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች ድረስ እየተሰማ ነው።

@tikfahethiopia

TIKVAH-ETH

16 Oct, 06:28


ባሕር_ዳር

የተወዳጇ ድምፃዊት አምሳል ምትኬ የባህል ምሽት ቤት እና የምግብ አዳራሽ ትናንት ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12:30 አካባቢ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ መውደሙ ተሰምቷል።

የባሕር ዳር ነዋሪ እሳቱን ለመቆጣጠር ያደረገው ርብርብ ጥሩ ነበር። ሆኖም የእሳቱ ሁኔታ ከባድ ስለነበር ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን እና በሰው ላይ እስካሁን ጉዳት አለማድረሱን ሰምተናል።

@Tikfahethiopia

TIKVAH-ETH

14 Oct, 18:50


❗️የፐርፐዝ ብላክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱን (ዶ/ር) ጨምሮ 10 ግለሰቦች በማታለል ሙስና ወንጀል ተከሰሱ

#Ethiopia  | የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ የፐርTዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ አባልና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱን (ዶ/ር) ጨምሮ በ10 ግለሰቦች እና ሁለት ድርጅቶች ላይ ክስ መስርቷል።

ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሾቹ 1ኛ የፐርTዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ አባልና ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱ (ዶ/ር)፣2ኛ የተቋሙ ም/ስራ አስፈጻሚ ኤርሚያስ ብርሃኑ (ዶ/ር)፣ 3ኛ የተቋሙ ቺፍ  ኦፕሬሽን ኦፊሰር እና የቦርድ አባል ወ/ሮ ኤፍራታን ነጋሽን ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ግለሰቦች እንዲሁም ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ እና ኖትር ዲዛይን ሃ/የተ/የግ/ማህበር ናቸው፡፡

ተከሳሾቹ በአዲስ አበባ ከተማ መሃል ሜክሲኮ ላይ በ100 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ  ባለ 3 መኝታ ቤት መኖሪያ ቤት  በ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚሸጥ መሆኑን በሚዲያ በማስተዋወቅ ሰዎች ቤት ለመግዛት ሲሄዱ "መጀመሪያ ገንዘቡን አስገቡና ውሉን ትመለከታላችሁ "በማለት ከሌሎች ግብረዓበሮቻቸው ጋር በመሆን አሳሳች ቃላቶችን በመጠቀም፣ ሰዎች ገንዘቡን ካስገቡ በኋላ ደግሞ የአክሲዮን ግዢ ውል እንዲፈርሙ በማድረግ ምንም አይነት የግንባታ ቦታ ባልተረከቡበት ሁኔታ 2 ቢሊየን 234 ሚሊየን 200 ሺህ ብር በመሰብሰብ፣ ቤቱን ሰርተው ሳያስረክቡ በመቅረት እንዲሁም ግማሹን ገንዘብ ወደ ውጭ እንዲሸሽ በማድረግ፣ ኮሚሽን በመቀበልና በማታለል  ወንጀል ተጠርጥረው  በአዲስ አበባ ፖሊስ በኩል በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ሲከናወን እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

በዚህ መልኩ ፖሊስ  ሲያከናውነው የቆየው የምርመራ ማጣሪያ ሥራ መጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ዐቃቤ ሕግ ተደራራቢ ዝርዝር ክሶችን  በየደረጃቸው  አቅርቦባቸዋል።

ከቀረቡ ክሶች መካከል በአንደኛው ክስ ላይ ከ1ኛ-9ኛ ባሉ ተከሳሾች ላይ እንደተመላከተው፤ በኢፌዲሪ የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ሀ) እና (ለ)  እንዲሁም  የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 32 (2) ላይ የተመላከተውን ድንጋጌ መተላለፍ የሚል ክስ ይገኝበታል።

እንደ አጠቃላይ በቀረበው ተደራራቢ ክስ ዝርዝር ችሎት ለቀረቡ 4 ተከሳሾች ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን ÷የተከሳሾቹ ጠበቆች በደንበኞቻቸው ላይ የቀረበውን ክስ ዝርዝር ተመልክተው ዋስትና ላይ ክርክር ለማድረግ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም ዋስትና ላይ የሚደረገውን የግራ ቀኝ ክርክር ለመከታተል ለፊታችን ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ተዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ችሎት ያልቀረቡ ተከሳሾችን ፖሊስ በአድራሻቸው አፈላልጎ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

በታሪክ አዱኛ

Via Fidel
Via Addis news

@Tikfahethiopia

TIKVAH-ETH

14 Oct, 17:06


ሰሞኑን ተጠናክሮ በቀጠለዉ የአማራ ክልሉ ዉጊያ የፌደራሉ መንግስት ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት እንደከፈተ ተነግሮል ፡፡

በተለይ በጎጃም አካባቢ ተከታታይ ድብደባዎች መደረጋቸዉን አዲስ ነገር ከአካባቢዉ ያገኘችዉ መረጃ ያመለክታል ፡፡

@Tikfahethiopia

TIKVAH-ETH

13 Oct, 18:08


ወልዲያ‼️

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ የተኩስ ድምፅ እየተሰማ መሆኑን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።

ተኩሱ ከወልዲያ ወደ ቃሊም አቅጣጫ ሲሆን የመድፍ ተኩስ ጭምር እየሰማን ነው ብለዋል። (Ayu)


@Tikfahethiopia

TIKVAH-ETH

13 Oct, 16:21


መረጃ‼️


በአማራ ክልል እየተደረገ ያለዉ ዉጊያ በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል እንደቀጠለ ነዉ ፡፡

መከላከያ ሰራዊቱ ሰሞኑን እያደረግሁት ነዉ ባለዉ ዘመቻ ድል እየተቀናጀሁ ነዉ ሲል በፋኖ ሀይሎች በኩል በጀመርንዉ ወታደራዊ ዘመቻ አዳዲስ ቦታዎችን ለመያዝ ችለናል ሲሉ ይገልፃሉ ፡፡

በዛሬው እለት በሰሜን ጎጃም ዞን ሜጫ ገርጭጭ አካባቢ የፋኖ ሀይሎች ወደ ከተማዉ  ለመግባት ተኩስ መክፈታቸዉን የአካባቢዉ ነዋሪዎች ገልፀዋል ፡፡

የመከላከያ ሰራዊቱ በበኩል አካባቢዉን ሊቆጣጠሩ የመጡት የፋኖ ሀይሎች አባላትን ደምስሻለሁ ሲል ገልፆል ፡፡

ሰሞኑን የፋኖ ሀይሎች በርካታ ቁጥር ያለዉ ማርከናቸዋል ያሎቸዉንየመከላከያ ሰራዊት አባላት  ወታደሮች በተንቀሳቃሽ ምስል አስደግፈዉ ሲያቀርቡ ተስተዉሏል፡፡

በክልሉ በተጀመረዉ የሁለቱ ሀይሎች ፍልሚያ የክልሉን ህዝብ ለበርካታ ሰበአዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እየዳረገ እንደሚገኝ ይገለፃል ፡፡

@Tikfahethiopia

TIKVAH-ETH

10 Oct, 07:37


አስፈሪ የተፈጥሮ ክስተት

ሚልተን የተሰኘው አውሎ ነፋስ በፍሎሪዳ ታምፓ አካባቢ 15 ጫማ የሚደረስ ማዕበል ሊያመጣ እንደሚችል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

እ.ኤ.አ በ 2022 በፎርት ማየርስ ከተማ ተከስቶ ከነበረው ኢያን አውሎ ነፋስ በበለጠ አደገኛ እንደሆነ የሚያሳይ ቪዲዮ ተሰራጭቷል። ሀገሪቱ የተፈጥሮን አደጋ ለመቋቋም ዝግጅት ላይ ነች።

@Tikfahethiopia

TIKVAH-ETH

09 Oct, 18:57


❗️40 በመቶ የአዲስአበባ ከተማ ክፍል ፈራሽ ነዉ ተባለ

40 በመቶ የአዲስአበባ ክፍል ፈራሽ መሆኑን መሠረት ሚዲያ ዘግቧል። የዜና ምንጩ ፈረሳዉ በሁለተኛዉ ምዕራፍ የአዲስአበባ የኮሪደር ልማት መስመሮች የተነሳ ነዉ ብሏል።

የኮሪደር ልማቱን ለመከወን ከ 110 ቢሊዮን ብር በላይ ይጠይቃል መባሉንም ዳጉ ጆርናል ከዘገባዉ ሰምቷል። በመጀመሪያዉ ዙር የኮሪደር ልማት ቀደምት የአዲስአበባ ሰፈሮች መፍረሳቸዉ ይታወቃል።

በአጠቃላይ በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት 2817 ሄክታር የቦታ ስፋት ሲኖረው 132 ኪሎሜትር ርዝመትን እንደሚሸፍን ዳጉ ጆርናል መዘገቡ አይዘነጋም።

#dagu Journal from Meseret media

@Tikfahethiopia

TIKVAH-ETH

07 Oct, 20:47


❗️መረጃ

ምንጃር...!

በዛሬው ዕለት በምንጃር ሸንኮር ለረጅም ሰዓታት የፈጀ ውጊያ ሲደረግ መዋሉን ከአካባቢው የተገኘው መረጃ ያመለክታል ። የፋኖ ሀይል ወደ #ባልጪ ከተማ መግባቱም ተነግሯል።

ምንጃር አረርቲ ከተማም የትላንትናው ውጊያ ዛሬም እንደቀጠለ ስለመሆኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

via gion

@Tikfahethiopia

TIKVAH-ETH

07 Oct, 17:53


❗️ደንበጫ..!

ከ3 ቀን ውጊያ ሲካሄድባት የነበረችው የደንበጫ ከተማ የተኩስ ድምፅ ባይሰማም ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ በከተማዋ ውስጥ እንንደማይታይ አንድ የአይን እማኝ ገልጠውልናል፡፡
 
ፈረስ ቤት...!

ከትናንት ጀምሮ እስከዛሬ ጠዋት ድረስ በምዕራብ ጎጃም ዞን ፈረስ ቤት ከተማና በዙሪያው ጦርነቶች እንደነበሩና ዛሬ ረፋድ ላይ ተኩሱ በተወሰነ ደረጃ መቀነሱን አንድ ነዋሪ ቀን ቀትር ላይ ነግረውናል፡፡“ከሁለት ሰዓት ጀምሮ ከባድ ውጊያ ነበርና አመሻሽ ላይ በረድ ብሏል፡፡” ብለዋል፡፡

ትናንትና ወደ ገጠሩ አካባቢ ሙሉ ቀን ጦርነት እንደነበር የጠቀሱት አስተያየት ሰጪው፣ በተለይ “አቅላት” በሚባል አካባቢ ውጊያ እንደነበርና ዛሬ ደግሞ በከተማው ዙሪያ፣ በተለይም “ሻንጊ” በተባለ ቦታ ላይ ከባድ ውጊያ ቀትሎ ማርፈዱን ገልጠዋል፡፡ “ ነዋሪው ነፍስ ግቢ፣ ነፍስ ውጪ ላይ ነው ሲሉ ነው አክለዋል፡፡

ሌላ የአካባቢው ነዋሪ በበኩላቸው ጦርነቱ በሁለቱ ኃይሎች መካከል የተጀመረው ከመስከረም 21/2017 ጀምሮ መሆኑን አመልክተው፣ አሁንም በአራቱም አቅጣጫ ውጊያ መኖሩን ዛሬ ቀትር ላይ ተናግረዋል፡፡

ከመስከረም 21/2017 ዓ ም ጀምሮ በክር አቦ ፈረስ ውሀ ላይ ውጊያዎች እንደነበሩ ተናግረዋል። ዛሬ ደግሞ በከተማዋ ዙሪያ ጦርነቱ ቀጥሎ መዋሉን ገልጠዋል፡፡

አማኑኤል...!

በምስራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል ከተማ ነዋሪም ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በከተማዋና አካባቢው ጦርነት መቀጠሉን አስረድተዋል፡፡ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በከተማዋና ዙሪያዋ ከባድ ውጊያ መቀስቀሱን አስረድተዋል፣ ትናንትናም ከከተማ ወጣ ብሎ ውጊያ እንደነበር እኚሁ አስተያየት ሰጪ አመልክተዋል፡፡

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአማራ ክልል በተለይም በጎጃም ቀጠናዎች በፋኖ ታጣቂዎችና በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች መካከል ውጊያ ሲካሄድ ሰንብቷል።

በተለይ ባለፈው አርብና ቅዳሜ በምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫና ጂጋ በተባሉ ከተሞች ከባድ ውጊያ እንደነበር ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬሌ ገልጠዋል፡፡አንድ የደንበጫ ከተማ ነዋሪ ዛሬ ለዶቼ ቬሌ እንዳሉት ዛሬ በከተማዋና አካባቢው የተኩስ ድምፅ ባይሰማም፣ በከተማዋ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንደሌለ ነው ያስረዱት፡፡

የመንግስት ኃይሎች በከተማዋ እንደሚታዩ አስተያየት ሰጪው ተናግረዋል፡፡አንድ የጂጋ ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው በሳምንቱ መጨረሻ አካባቢ በጅጋና “ሆድ አንሺ” በተባሉ አካባቢዎች ውጊያዎች እንደነበሩ አስታውሰው አሁን የተኩስ ድምፅ አይሰማም ብለዋል፣ በጂጋ ከተማ የፋኖ ታጣቂዎች እንደሚታዩም አብራርተዋል፡፡

Via Gion and Germany Voice

@Tikfahethiopia   

TIKVAH-ETH

07 Oct, 07:06


በአዋሽ ፈንታሌ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ ቤቶችን ማፍረሱን ሰመራ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ

በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ትናንት ምሽት የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ መኖሪያ ቤቶችን ማፍረሱን ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ባወጣው መረጃው አመልክቷል። በመሬት መንቀጥቀጡ መሬት መሰንጠቁንም ዩኒቨርቲው ዛሬ ሰኞ ማለዳ አስታውቋል።

በፈንታሌ ተራራ ላይ ተከስቶ ንዝረቱ አዲስ አበባ ከተማ ድረስ የተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ከሁለት ሳምንታት በላይ በተለያየ አጋጣሚ መከሰቱን ባለሞያዎቹ ገልፀዋል። ትናንት መስከረም 26/2017 ምሽት 2፡10 ገደማ የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበበት ነበር።

ከሰሞኑ የሚስተዋለው የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ከፍተኛ ሥጋት ፈጥሯል ያለው ዩኒቨርሲቲው፣ አደጋው በተከሰተበት ሳቡሬ ቀበሌ ተገኝቶ መረጃ የመሰብሰብ እና ለማህበረሰቡ ጥንቃቄ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መሥራቱንም ገልጿል።

የዩኒቨርሲቲው ጂኦሎጂስቶች ነዋሪዎች ከፈንታሌ ኮረብታማ ቦታ እና ከከሰም ግድብ ርቀው እንዲቆዩ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

እሑድ ምሽት የተከሰተውና በአዲስ አበባ በነዋሪዎች ላይ መደናገጥ የፈጠረው የመሬት መንቀጥጠጥ ለ18 ሴኮንድ የቆየ እንደነበረ ባለሞያዎች ተናግረዋል።
via_atc

@Tikfahethiopia

TIKVAH-ETH

06 Oct, 18:56


❗️#Update ማብራሪያ ከዶክተር ኤልያስ ሌዊ

" እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የለም፤ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ ነው ፤ አዋሽ አካባቢ ነው የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4.9 ነው " - ዶክተር ኤልያስ ሌዊ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" እስካሁን ባለው መረጃ እዚህ የመሬት መንቀጥቀጡ እዚህ አዲስ አባባ የተከሰተ ሳይሆን አዋሽ አካባቢ የተከሰተ ነው።

ግን በመሬት ውስጥ አልፎ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ልዩ ልዩ ቦታዎች ተሰምቷል።

ይሄን ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ አይደለም። ግን በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ እዚህ ያሉ ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል።

በሪክተር ስኬል 4.9 ነው ያገኘነው። ይሄም ከፈንታሌ የሚባል ተራራ አለ ወደ መተሃራ አካባቢ ነው የተከሰተው። እስካሁን ያለው መረጃ ይሄ ነው።

ሰውም ይረጋጋ እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይሆን ከሩቅ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ በተለይ እዚህ ሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በጣም ተረብሸዋል። ልክ ነው ከዛም ሊሰማ ይችላል።

በሬክተር ስኬል 4.9 ነው ይሄ ነው ያለው መረጃ።

ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን በግልጽ እንነግራለን። " ብለዋል።

ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ምክንያት በተለይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች ህንጻቸው ሲንቀጠቀጥ እንደነበር ገልጸውልናል። በዚህ ምክንያት ከቤታቸው ወጥተው መሬት ላይ ወርደው ተሰባስበዋል።

@Tikfahethiopia