ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

@taggmk


TAGG is ass. of students in TASH learning orthodoxy @ Gola St. Micheal under Mahibere Kidusan Addis Ababa center

Phone +251984811212

''የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን'' ንሕ ፪፥ ፳

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

20 Oct, 10:00


የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ናችሁ?

ዛሬ 9:00ስዓት ላይ የአብነት ትምህርት ስላለን ሁላችንም ተቀሳቅሰን በሰዓቱ እንገኝ።


ማስታወሻ

👉ቅዳሴ
👉ቁጥር
እና ሌሎችንም እንማራለን
መልካም ቀን

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

19 Oct, 07:20


ሥርዓተ ማኅሌት ዘሣልሳይ ጽጌ ወበዓለ መስቀል (የሦስተኛ ሳምንት ጽጌና የመስቀል ማኅሌት)

ግእዝና አማርኛ 

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

አቤቱ ጽሎቴን ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጩኸቴም ከፊትህ ይድረስ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፊትህንም ከእኔ ላይ አታዙርብኝ በጭንቀቴ ዕለት ጆሮዎችህ ያድምጡኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ  በጠራሁህ ዕለት ፈጥነህ ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዘላለሙ ሃሌ ሉያ
ይህም ማለት፡ በልዕልናው ያለውን እግዚአብሔርን እናመስግነው ፣ ዓለምን በአንዲት ቃል የመሠረተ እርሱ ፈጽሞ ምስጉን ነው።

📖መልክአ ሥላሴ

ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በህላዌ አካል ትክክል ለሚሆኑ ኩልያቶቻችሁ ሰላምታ ይገባል። ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፤ ከእናንተ ከሦስቱ
አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ቃል ይቅርታ ለማድረግ ዓለምን በጎበኘ ጊዜ የአባቶች ተስፋ በድንግል ማርያም ተፈጸመ። የነፃነት ዓርማ መስቀልም በቀራንዮ አደባባይ ተተከለ።

ዚቅ፦

ዝኬ ዘተዘርዓ ቃለ ጽድቅ በትውክልተ መስቀል፤ ወፍሬሁኒ ኮነ መንፈሰ ሕይወት፤ ተስፋሆሙ ለእለ ድኅኑ፤ ወበጽጌሁ አርዓየ ገሃደ አምሳለ ልብሰተ መለኮት፤ ዕቊረ ማየ ልብን፤ ጽጌ ወይን ተስፋሆሙ ለጻድቃን።

ይህ የእውነት ቃል በመስቀል ትምህክትነት የተዘራ ነው፤ ፍሬውም የሕይወት መንፈስ ኾነ፤ ለሚድኑም ተስፋቸው ነው፤ በአበባውም (በክርስቶስም) መለኮት መልበሱን በመልኩ በግልጥ አሳየ፤ ማየ ልብን የተባለ ዕጣንን የያዘ ሲኾን የወይን አበባ የጻድቃንም ተስፋቸው ነው።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል፤ ወጸገይኪ ጽጌ በኢተሰቅዮ ማይ ወጠል፤ ወበእንተዝ ያሬድ መዓርዒረ ቃል፤ ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ወይብል፤ ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል።

ሳይተክሏት የበቀለች የለመለመች! ውኃ ሳያጠጧት ያበበች፣ ያፈራች፣ የአሮን በትር ማርያም ሆይ! ተአምር አሳየሽ፤ ስለዚህም ጥዑመ ልሳን ያሬድ፤ የወንጌል አጥር ይከባታል፤ ጽጌረዳም በመስቀል አምሳል ብሎ ከሱራፌል ጋራ አመሰገነሽ፡፡

🌷ወረብ

በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል/፪/
ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ያሬድ ወይብል ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል/፪/

ዚቅ

በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ወባቲ ይገብሩ ተአምረ በውስተ አሕዛብ እስመ አርአያ መስቀል ይዕቲ።

የአሮን በትር ለመለመች በርሷም በአሕዛብ መካከል ተአምርን ያደርጋሉ የመስቀል ምሳሌ ናትና።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ፤ካዕበ (ወካዕበ) ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤ ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኪ ዕረፍተ።

ማርያም ሆይ እናትሽ አበባን ያስገኘች ዕለተ ማክሰኞን፣ ብሩህ ፀሐይን ያስገኘች ዕለተ ረቡዕን ትመስላለች፤ ዳግመኛም ሰባተኛውን ቀን ትመስላለች፤ በሰማይና በምድር ላሉ ዕረፍት የኾንሽ፤ የነፃነት ቀን ዕለተ ሰንበት አንቺን በተአምር አፍርታለችና።

🌷 ወረብ

ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እም/፪/
ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም/፪/

ዚቅ

እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ወእምኲሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ከመ ትኩኖ ማኅደረ ለመንፈስ ቅዱስ ወምስጋድ ለኲሉ ዓለመ።

ከዕለታት ኹሉ ሰንበትን አከበረ ፤ ከሴቶች ኹሉም ማርያምን ወደደ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያውና የዓለም ኹሉ መስገጃው ትኾነው ዘንድ።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

" በመንጻት ወራት፣ በተአምርም ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ስትገቢ፤ ነጭ እና ቀይ አበባ የሚባል ልጅሽን ታቅፈሽ፤ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ርግቤ ሆይ ነይ፤ መልካም እናቴ ሆይ ደስ የሚል ዜና ከያዘ ከገብርኤልና፤ እንደ አንቺ ርኅሩኅ ከሆነ ከሚካኤልም ጋራ ነይ።"

🌷ወረብ

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/

ዚቅ

ንዒ ርግብየ ሰላማዊት፤ ተመየጢ ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ በአምሳለ ወርቅ ይግበሩ ለኪ ኮሰኮሰ ዘብሩር፤ አመ ወለደቶ አርአያ ወሰደቶ፤ በትእምርተ መስቀል፤ ትፍሥሕትኪ ውእቱ፤ ብርሃንኪ ውእቱ ሰላምኪ።

ሰላማዊቷ ርግቤ ሆይ ነይ፤ ተመለሽና በአንቺ ሰላምን እንይ፤ በወርቅ አምሳል የብር ገንቦ ይሥሩልሽ ፤ በወለደችው ጊዜ በመስቀል ምልክት የመውሰዷ ተምሳሌት ነው፤ እርሱ ደስታሽ ፣ ብርሃንሽና ሰላምሽ ነው።

ዓዲ ዚቅ

ወይቤላ ንዒ ንሑር፤ኀበ ደብረ ከርቤ ውስተ አውግረ ስኂን፤ እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት

እኅቴ ሙሽራዬ መልካሟ ርግቤ ሆይ ወደ ከርቤ ተራራ የሉባንጃ ኮረብቶች መካከል ነይ እንሒድ ይላታል።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ ዘይኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኩሎ ታሰግዲ ሎቱ ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።

"እመቤቴ! የሞቱ መታሰቢያ፤ የስሙ ምልክት የተጻፈብሽ፤ ከሚያበራ የባሕርይ እንቊ የጠራሽ የራስ ወርቅ ክበብ ነሽ፤
የአበባ ጉንጉን የተሣለብሽ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ ማርያም ሆይ!! አንቺ ሁሉን ታሰግጂለታለሽ እሱ ግን ለአንቺ ይሰግዳል።"

🌷ወረብ

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየሐቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/

ዚቅ

ነያ ሠናይት ወነያ አዳም፤ አግዓዚት ማርያም ጽርሕ ንጽሕት፤ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤  ወዲበ ርእሳኒ አክሊል፤ ፅሑፍ በትምህርተ መስቀል።


እነኋት መልካሚቱ እነኋት ውቢቱ፤ ንጽሒቷ አዳራሽ ነጻ አውጪዋ ማርያም፤ በወርቅ ልብስ የተጎናጸፈች የተሸፋፈነች ፤ በራሷም ላይ በመስቀል ምልክት የተጻፈ አክሊል አላት።

ዓዲ ዚቅ

በወርቅ ወበዕንቍ ወበከርከዴን፤ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት፤ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ፤ትርሢተ መንግሥቱ አንቲ መድኃኒቶሙ ለነገሥት።

" በወርቅ ከርከዴን በተባለ ዕንቍ በምስጋናም ያጌጥሽ ነገሥታት ላንቺ ይገዙልሻል የመንግስታቸው ክብር ጌጥ ለነገሥታትም መድኃኒታቸው አንቺ ነሽ"

ሰቆቃወ ድንግል

ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ።


ያዘናችሁ ሆይ ስደቷን እያሰባችሁ አልቅሱ፤ ደስተኞችም የበዛ መልካምነቷን እያስታወሳችሁ እዘኑ፤ ማርያም የአባቷን ሃገር ኤፍራታን አጥታ እንደ ወፍ ብቻዋን በግብጽ ተራሮች መካከል ትጮሃለችና ፤ የሕፃናት ደምም በመንገዷ ኹሉ ይፈሳል።

🌷ወረብ

ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም/፪/
ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ተዓይል/፪/

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

18 Oct, 09:38


የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ዋላችሁ?

ዛሬ 11፡00 ሰዓት ላይ የአብነት ትምህርት ይኖረናል።ለጽጌ መርሃግብር የሚሆን ወረብ ጥናት እንጀምራለን እና ግቢ ያላችሁ ልጆች ተጠራርታችሁ ኑ።

መልካም ቀን

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

15 Oct, 06:00


ለጥቁር  አንበሳ ግቢ ተማሪዎች በሙሉ:
ዲቫ ሳሙና በ65 ብር እንዲሁም ብስኩት በ20 ብር ያቀረብን መሆኑን እያበሰርን ውድ ደንበኞቻችን እንደእናንተ ፍላጎት እያየን ሌሎች የፍጆታ እቃዎችንም ስለምናመጣ÷ ግብይታችሁን ከኛ ሱቅ በማድረግ ህይወትዎን ያቅልሉ ÷ ግቢ ጉባኤችሁንም ይደግፋ እንልዎታለን።

መገኛ÷ በወንዶች ዶርም  first floor ዶርም ቁጥር 19 እና
በሴቶች  second floor ዶርም ቁጥር 117 ነው።

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

14 Oct, 06:23


ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ pinned «»

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

12 Oct, 10:57


ሰቆቃወ ድንግል

በቤተ መቅደስ ዘልሕቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ሥሩዓ፣ ኅብስተ ኅቡዓ ወጽዋዓ ወይን ምሉዓ፤እፎ ከመ ነዳይ ሲሳየ ዕለት ዘኃጥአ፤ተአገሠት በብሔረ ግብጽ ረኃበ ወጽምዓ፤አልቦ ከማሃ ዘረከበ ግፍዓ።


ተሠርቶ የተዘጋጀ ሥውር ኅብስትን ምሉዕ የወይን ጽዋን እየተመገበች በቤተ መቅደስ ያደገች የካህናት ልጅ ፤ እንዴት የዕለት ምግቡን እንደ አጣ ደሃ በግብጽ ሃገር ረኃብና ጥምን ታገሰች፤ እንደርሷ ግፍስ ያገኘው ማንም የለም።

🌷ወረብ

እፎ ከመ ነዳይ ዘኃጥአ ሲሳየ ዕለት/፪/
በቤተ መቅደስ ዘልሕቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ኅብስተ መና ኅቡዓ/፪/

ዚቅ

እሴብሕ ጸጋኪ ኦ ዑጽፍተ ልብሰ ወርቅ እግዝዕትየ ወለተ ዳዊት ንጉሥ ዘተሐፀንኪ በቤተ መቅደስ ወተዓንገድኪ በፈሊስ እምሀገር ለሀገር እንዘ ተዓውዲ በተፅናስ።

በቤተመቅደስ ያደግሽ የንጉሥ ዳዊት ልጅ ከሃገር ለሃገር በመሰደድም ዕንግዳ በመሆን በችግር ዙሪያ የዞርሽ፤ የወርቅ ልብስን የተጎናጸፍሽ እመቤቴ ሆይ ጸጋሽን አመሰግናለሁ።

መዝሙር

ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ፤ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ ለዘሀሎ መልእልተ አርያም።አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ።ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት ብሩህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወለምድርኒ አሠርገዋ በጽጌያት ንፁህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወሠርዓ ሰንበተ ለነባረ ያዕርፉ ባቲ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌ:ማ- መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት። ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ።


ኪነ ጥበቡ ድንቅና ዕጹብ በአርያም ከፍታ ያለው ኪነ ጥበቡ ድንቅና ዕጹብ ነው። ምሕረቱን በእኛ ላይ አሳየ፤ ብሩህ በሆኑ ከዋክብት ሰማይን የጋረደው ምሕረቱን በእኛ ላይ አሳየ፤ ምድርንም በንፁሕ አበቦች ያስዋበ ምሕረቱን በእኛ ላይ አሳየ፤ሰንበትንም ያርፉባት ዘንድ የሠራ ምሕረቱን በእኛ ላይ አሳየ፤ (በኅብረት)፡ በዱር ውስጥ እንዳሉ የቆላ አበቦች የቅዱሳን መአዛቸው ቀንሞስና ናርዶስ የተባሉ ሽቱዎችን አፈሩልን።

አመላለስ

መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት/፪/
ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ/፬/

እንኳን አደረሳችሁ! በአካባቢያችን ካለ አጥቢያ በመሄድ የዚህ ድንቅ ምስጢር ተሳታፊ እንሁን!

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

12 Oct, 10:57


ሥርዓተ ማኅሌት ዘካልዓይ ጽጌ ወበዓለ በዓታ ለማርያም (የኹለተኛ ሳምንት ጽጌና የበዓታ ለማርያም ማኅሌት)

ግእዝና አማርኛ 

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

አቤቱ ጽሎቴን ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጩኸቴም ከፊትህ ይድረስ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፊትህንም ከእኔ ላይ አታዙርብኝ በጭንቀቴ ዕለት ጆሮዎችህ ያድምጡኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ  በጠራሁህ ዕለት ፈጥነህ ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዘላለሙ ሃሌ ሉያ
ይህም ማለት፡ በልዕልናው ያለውን እግዚአብሔርን እናመስነው ፣ ዓለምን በአንዲት ቃል የመሠረተ እርሱ ፈጽሞ ምስጉን ነው።

📖መልክአ ሥላሴ

ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በህላዌ አካል ትክክል ለሚሆኑ ኩልያቶቻችሁ ሰላምታ ይገባል። ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፤ ከእናንተ ከሦስቱ
አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ቃል ይቅርታ ለማድረግ ዓለምን በጎበኘ ጊዜ የአባቶች ተስፋ በድንግል ማርያም ተፈጸመ። የነፃነት ዓርማ መስቀልም በቀራንዮ አደባባይ ተተከለ።

ዚቅ፦

ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤እንተ በሥሉስ ትትገመድ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከተ፤ሐረገ ወይን፤ሲሳዮሙ ለቅዱሳን፤ሐረገ ወይን፤ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ ወጸገወ ሰላመ ለኩሉ።

ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ የወይን ሐረግ፤ ሥሮቿ በምድር ጫፎቿ በሰማይ የወይን ሐረግ ፤ በሥሉስ ተቆርጣ የበረከት ዘለላ የምታፈራ የወይን ሐረግ ፤ የቅዱሳን ምግባቸው የወይን ሐረግ ፤ በቃሉ ሰንበትን ሠራ ሰላምንም ለኹሉ ሰጠ።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ(ጽላተ) ኪዳን፤ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፤ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን፤ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን፡፡

" መጽሐፍ በፈጣሪና በፍጡራን መካከል ለዕረፍት የተሾምሽ የቃል ኪዳን ምልክት ነሽ ብሎ እንደተናገረ፣ የሰንበታት ሰንበት የብርሃን ቀን ማርያም ሆይ፤ አበባ ያላት የገነት ጻድቃን በአንቺ ይደሰታሉ፤ ኃጥአንም በአንቺ ከኩነኔ ይወጣሉ"

🌷ወረብ

በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ ኪዳን/፪/
ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ብርሃን ዕለተ ብርሃን/፪/

ዚቅ

ሰንበቶሙ ይእቲ ለጻድቃን ትፍሥሕት፤ሰንበቶሙ ይእቲ ለኃጥአን ዕረፍት፤ኅቡረ ንትፈሳሕ ዮም በዛቲ ዕለት፡፡

" ለጻድቃን የደስታቸው ሰንበት ለኃጥአንም የዕረፍታቸው ሰንበት ይህቺ ናት በዚህች ዕለት በኅብረት እንደሰት"

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዓረብ ወተርሴስ፤በድንግልና ማርያም ሥርጉተ ሥጋ ወነፍስ፤ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ፤ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ፤ እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ።

ማርያም ሆይ በአረብና በተርሴስ ወርቅ እንደ ተለበጠች ታቦት፣ በነፍስና በሥጋ በድንግልና የተለበጥሽ ነሽ፤ ኢያቄምና ሐና ቀንሞስና ቀናንሞስ የተባሉ ሽቱዎች ፤ መለኮት የጠበቀሽን አንቺን በሦስት ዓመት ካስገኙ በኋላ በቤተመቅደስ መኖር ተአምርን አሳየሽ።

🌷 ወረብ

እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ  ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ/፪/
ተአምረ ነቢር አርአይኪ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ/፪/

ዚቅ

አንቲ ውእቱ ንጽሕት እምንጹሐን ድንግል ኅሪት ዘነበረኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ ሥርግው በወርቅ ንጡፍ ወልቡጥ በዕንቍ ባሕርይ ዘየኃቱ ዘብዙኅ ሤጡ ከመዝ ነበርኪ በቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽሑ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ አሠርተ ወክልኤተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ።

ከንጹሓን ይልቅ ንጽሕት የሆንሽ አንቺ ነሽ ከማይነቅዝ ዕንጨት እንደ ተሠራ በወርቅ እንደ ተጌጠና ዋጋው ብዙ በሆነ በሚያበራ ዕንቁ እነደተለበጠ ታቦት በቤተ መቅደስ ውስጥ የኖርሽ የተመረጥሽ ድንግል ነሽ። እንዲህ ሆነሽ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖርሽ መላእክትም ዘወትር ምግብሽን ያመጡ ነበር በመላእክት እየተጽናናሽ እንዲህ ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖርሽ። መጠጥሽም የሕይወት መጠጥ ነበር ምግብሽም የሰማይ ኅብስት ነበር።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

" በመንጻት ወራት፣ በተአምርም ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ስትገቢ፤ ነጭ እና ቀይ አበባ የሚባል ልጅሽን ታቅፈሽ፤ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ርግቤ ሆይ ነይ፤ መልካም እናቴ ሆይ ደስ የሚል ዜና ከያዘ ከገብርኤልና፤ እንደ አንቺ ርኅሩኅ ከሆነ ከሚካኤልም ጋራ ነይ።"

🌷ወረብ

ንዒ ርግብየ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሰናይትየ ወንዒ ሰናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ/፪/

ዚቅ

ንዒ ርግብየ አግዓዚት ከመ ጎሕ ሠናይት ታቦተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ዕፀ ጳጣስ ደብተራ ፍጽምት ማኅደረ መለኮት

እንደ ማለዳ ብርሃን መልካም የሆንሽ ፤ ቅድስተ ቅዱሳን የተባልሽ የመቅደስ ታቦት ፤ የማትቃጠለዋ ቁጥቋጦ ተክል፤ የመለኮት ማደርያ ፍጽምት ድንኳን ነጻ አውጪዋ ርግቤ ሆይ ነይ።

ዓዲ ዚቅ

ንዒ ርግብየ ኲለንታኪ ሠናይት ፀምር ፀዓዳ እንተ አልባቲ ርስሐት መሶበ ወርቅ እንተ መና በትረ አሮን እንተ ሠረፀት።

ኹለመናሽ መልካም ፤ እድፍ የሌለብሽ ነጭ ፀምር ፣ መና ያለብሽ መሶበ ወርቅ፤ የበቀለች የአሮች በትር የተባልሽ ርግቤ ሆይ ነይ።

ወቦ ዘይቤ ዚቅ

ይዌድስዋ ትጉሃን፤ይቄድስዋ ቅዱሳን፤ሰሎሞን ይቤላ ርግብየ ሠናይት፤ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ፍጽምት፤ዳዊትኒ ይቤላ ስምዒ ወለትየ ወርይዪ ወአጽምዒ ዕዝንኪ

ትጉሃን ያወድሷታል ፤ ቅዱሳን ይቀድሷታል(ያመሰግኗታል) ፤ ሰሎሞን መልካሟ ርግቤ ይላታል ፤ ጳውሎስ ፍጽምት ድንኳን ይላታል፤ ዳዊት ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮዎችሽንም አዘንብዪ ይላታል።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ ዘይኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኩሎ ታሰግዲ ሎቱ ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።

"እመቤቴ! የሞቱ መታሰቢያ፤ የስሙ ምልክት የተጻፈብሽ፤ ከሚያበራ የባሕርይ እንቊ የጠራሽ የራስ ወርቅ ክበብ ነሽ፤
የአበባ ጉንጉን የተሣለብሽ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ ማርያም ሆይ!! አንቺ ሁሉን ታሰግጂለታለሽ እሱ ግን ለአንቺ ይሰግዳል።"

🌷ወረብ

ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየሐቱ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
ማርያም አክሊለ ጽጌ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ/፪/

ዚቅ

ከርካዕ ዘተተክለት በቤተ መቅደስ፤መራኁቱ ለጴጥሮስ፤አንቲ ውእቱ ደብተራ ስምዕ ዘጳውሎስ፤አማን አክሊሉ ለጊዮርጊስ


በቤተ መቅደስ የተተከለች ሎሚ ፤ የጴጥሮስ መክፈቻ ቁልፍ ፤ አንቺ የጳውሎስ ምሥክር ድንኳን በእውነትም የጊዮርጊስ አክሊሉ ነሽ።

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

12 Oct, 05:41


ሰላም የእግዚአብሄር ቤተሰቦች

📖መጽሀፍ ቅዱስ
📚የቤተክርስቲያን መፅሐፍት
📚የፀሎት መፅሐፍት
🙏ነጠላ
👍 በገና
🙏ክራር

የት ልግዛ ብለዉ ተቸግረዋል? እንግድያዉስ የ ግቢ ጉባኤ ሱቃችን ስራዉን ስለጀመረ ይደዉሉ ይዘዙን

📞0945294421
@Hann_Be
@Hailemaryam_21

ሰላመ እግዚአብሔር ከናንተጋር ይሁን

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

11 Oct, 07:42


የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ዋላችሁ?

ዛሬ 11፡00 ሰዓት ላይ የአብነት ትምህርት ይኖረናል።እንደ ባለፈው የዚህን ሳምንት የጽጌ ወረቦች እናጠናለን እና ግቢ ያላችሁ ልጆች ተጠራርታችሁ ኑ።

መልካም ቀን

ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ

06 Oct, 16:35



🌿የአንድነት መርሐ ግብር

ሰላም የልዑል እግዚአብሔር ቤተሠቦች እንደምን አመሻችሁ?

ነገ የአንድነት መርሐ ግብር ስለሚኖር እርስ በእርስ በመቀሳቀስ ወንድም እህቶቻችንን ይዘን በሰዓት እንገኝ።

📍 ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን፣ ትልቁ አዳራሽ
🕕ከምሽቱ 12:00


ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ