STEM with Murad 🇪🇹

@stemwithmurad


Welcome to STEM with Murad! This is your one-stop destination for all things related to Science, Technology, Engineering, and Mathematics (STEM). I will share updates and insights from the exciting world of STEM. You'll also get a sneak peek into my works

STEM with Murad 🇪🇹

21 Jan, 00:26


ጥቆማ
=======
iCog Labs ላይ internship መውጣት የምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ተመዝገቡ። አውቃቸዋለሁ፤ አሪፍ ቦታ ነው።

https://forms.gle/UHoqKsSfAmDsQBkm9

STEM with Murad 🇪🇹

21 Jan, 00:25


የቴክኖሎጂ ኮርሶችን መማር ለምትፈልጉ
============================
ከአሁን በፊት የጠቆምኳችሁ Mizan Institute of Technology በበርካታ ኮርሶች ምዝገባ ጀምረዋል። ለሚማሩ ተማሪዎቻቸውና ለሚሰለጥኑ ሰልጣኞቻቸው ትኩረት ሰጥተው በሚገባ እንደሚያስተምሩ ስለማውቅ ከታች በፎቶው ላይ ከተዘረዘሩት ኮርሶች የፈለጋችሁትን ኮርስ ምረጡና ስትፈልጉ በኦንላይን፣ ሲያሻችሁ በአካል በቀንም፣ በማታም፣ ቅዳሜና እሁድም፤ ከግል ትምህርትና ሥራችሁ ጋር በማይጋጭ መልኩ ተማሩባቸው። ምዝገባ ከጀመሩ አንድ ሳምንት የሚያልፍ ይመስለኛል። ሳይጠናቀቅባችሁ ተማሩ። መክፈል ለማትችሉ በብድር የምትማሩበት አማራጭ አመቻችተዋል። ምን መማር እንዳለባችሁ ግራ ከገባችሁ ደግሞ ነፃ የማማከር አገልግሎት ስላላቸው ከመመዝገባችሁ በፊት አማክሯቸው። የበለጠ መረጃ ከራሳቸው ገፆች ማግኘት ትችላላችሁ።

መመዝገቢያ ድረ ገጻቸው፦ https://mizantechinstitute.com

በቂ መረጃ የቴሌግራም ቻነላቸው t.me/MizanInstituteOfTechnology ላይ ስላለ ወደ ኋላ እየተመለሳችሁ አንብቡ፣ በድረ ገፃቸውም ላይ ዝርዝሮችን ተመልከቱ።

በውስጥ ለማዋራት በዚህ ዩዘር ኔም አናግሯቸው፦ http://t.me/MizanInstituteOfTechnologyEthio

በአካል ደግሞ ቤተል ቢጫ ፎቅ ፊት ለፊት በሚገኘው አፕል ፕላዛ 7ኛ ፎቅ ላይ ይገኛሉ።

STEM with Murad 🇪🇹

21 Jan, 00:24


«ተነሡ!

idea 011/2017ዓ.ም።
የክህሎት ሥልጠና የሚሠጥ የኦንላይን መተግበሪያ/ ፕላትፎርም ሥራ።

ወጪው .....የፕላትፎርም መተግበሪያ ማሠራት፣ቁሣቁሦች ማደራጀት፣ፈጣን ዳታ መግዛት፣ ኔትዎርክ መገንባት።

ገቢው ከsubscription እና ከማሥታወቂያ።

ዘመኑ የክህሎት ነው።
"Skills Just Rather Than Degrees" የሚል መጽሃፍ በ ፐኝሮፌሠር Isa Ali Panthami...አንብቡት

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

~~~~~~
ለምሣሌ ለዘመኑ የሚመጥኑ -ሥልጠናው ሊያካትታቸው የሚችለው .....(ሊኖራችሁ የሚገባ ክህሎት)
~~~~~~
Data Analysis, Machine Learning,Machine design, Artificial Intelligence, Cloud Computing, Cybersecurity, Blockchain Development, 3D Modeling, Graphic Design, Video Editing, Animation, Web Development, Mobile App Development, Digital Marketing, Social Media Management, Search Engine Optimization (SEO), Content Writing, Copywriting, UX/UI Design, Front-End Development, Back-End Development, DevOps, Data Science, Python Programming, Java Programming, C++ Programming, JavaScript Programming, SQL Database Management, NoSQL Databases, IT Project Management, Product Management, Agile Methodologies, Scrum Mastery, Virtual Reality Development, Augmented Reality Development, Game Development, Network Security, Ethical Hacking, Penetration Testing, Cyber Forensics, Cloud Architecture, Cloud Storage Solutions, SaaS Development, E-commerce Development, Online Advertising, PPC Management, Influencer Marketing, Affiliate Marketing, Branding Strategies, Email Marketing, Business Analytics, Financial Modeling, Business Intelligence, Accounting Principles, Human Resources Management, Leadership Training, Public Speaking, Negotiation Skills, Conflict Resolution, Strategic Planning, Entrepreneurship....በመጠኑ ናቸው።

በርቱ!»
ቤጃይ

STEM with Murad 🇪🇹

21 Jan, 00:24


ለጥንቃቄ!


እዚህ ሃገር ከአንድ ማዕከል ስልጠናና ስምሪት የሚሰጥ በሚመስል መልኩ የማታለል ወንጀሎች በየጊዜ እየተቀያየሩ ብቅ ይላሉ።
ከዚህ በታች በምስሉ ላይ የሚታዩቱ ተንቀሳቃሽ ስልኮች Samsung A74 ሞዴል እንደሆኑ ተደርጎ ሽፋናቸው ተቀይሮ፣ በተንቀሳቃሽ ስልኮቹ የውስጥ መረጃም በዚሁ መልክ 'edit' ተደርጎ በማይታወቁ ግከሰቦች እየተሸጠ ይገኛል። የማታለሉን ወንጀል እየፈፀሙ ያሉት እነዚህ ሰዎች፣ ይህን አዲስ ያስመሰሉትን ስልክ የተላያየ ምክንያት በመጠቀም ምንም ጥርጣሬ እንዳይገባዎ በማድረግ በዝቅተኛ ዋጋ ያቀርቡላቹሃል። ስልኩን ገዝተው ቤት ገብተው ለመጠቀም ሲከፍቱ ግን ጉዳዩ ሌላ ሆኖ ያገኙታል።
በመሆኑም ይህ አይነት ነገር ሲገጥሞት ተመሳሳይ ነገር ሊሆን ስለሚችል፣ ከመታለል የሚያድኖትን ነገር ያድርጉ፣ አቅራቢያዎ ላለ ፖሊስ ወይም የፀጥታ አካል ያሳውቁ።

STEM with Murad 🇪🇹

21 Jan, 00:24


https://www.linkedin.com/posts/murad-tadesse-a0a919160_ai-artificialintelligence-innovation-activity-7253671704512598016-OS1q?utm_source=share&utm_medium=member_android

STEM with Murad 🇪🇹

21 Jan, 00:23


«ተነሡ!
idea 010ዓ.ም።

ለንግሥቲቷ የሚሠራውን Royal jelly ሠብሥቦና አሽጎ መሸጥ።

ንቦች ለንግሥቲቷ ብቻ የሚሠሩት ምግብ ሮያል ጄሊ ይባላል።
ይህ ሮያል ጄሊ የአለም ገበያ ላይ አንዱ ኪሎ እሥከ 25,000 ብር ድረሥ ይሸጣል።
ለቆዳ ውበት፣የደም ሥኳርን ለመቆጣጠር፣ለፈርቲሊቲ፣ለሃይልና ኢሚዩኒቲ ቡሥተር፣ኮሌሥትሮልን ለመቀነሥ፣ለብሬይን ፈንክሽን ወዘተ ይጠቅማል።በፈሣሽ፣በዱቄትና በሚዋጥ መልኩ ማዘጋጀት ይቻላል።

በርቱ!»

ቤጃይ

STEM with Murad 🇪🇹

21 Jan, 00:22


ባለፈ ስለ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስና ቴክ ነክ ጉዳዮች አርፍ ሃሳቦችን ያቀረቡልን ተጋባዥ እንግዶች (ሰዒድ ዒሳ እና አሸናፊ ፋሲል - PhD Candidates in AI) ኤአይና ማሽን ለርኒንግ መማር ለምትፈልጉ ሮድማፕ እንልክላችኋለን ባሏችሁ መሠረት ይሄውና ፋይሉ። ሌሎች ኮርሶችንም መማር ለምትፈልጉ roadmap.sh ላይ በቂ ነገሮችን ማግኘት ትችላላችሁ።

||
t.me/MuradTadesse

STEM with Murad 🇪🇹

21 Jan, 00:22


ብዙ አስመጪ ነጋዴዎች ከባንኮች የውጪ ምንዛሪ መውሰድ ለምን አልፈለጉም?

1ኛ : ስፖት ትሬዲንግ(spot trading)

ነጋዴው የውጪ ምንዛሬ ለምሳሌ 200 ሺ ዶላር በ120 ብር ተመን ዛሬ አስፈቅዶ ዕቃውን ከወር በኋላ ሲያስገባ ያለው ምንዛሬ 125 ብር ቢሆን ተጨማሪ 1ሚሊዮን ብር ያስፈልገዋል።
ይሄን ፍራቻ ነጋዴዎች ዕቃ ከማስመጣት ተቆጥበዋል።

ለዚ መፍትሄው hedging contract አሰራር ባንኮች ቢጀምሩ ለተወሰኑ ውል ቀናት( ለምሳሌ አንድ ወር) የምንዛሬ ተመኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ያደርገዋል።

2ኛ :የኢኮኖሚ መቀዛቀዝና ኢንፍሌሽን።

የሸማቹ የመግዛት አቅም መዳከም እና የብር የመግዛት አቅም መዳከም አስመጪው የውጪ ምንዛሬ ቢቀርብም ከውጪ እቃ አምጥቶ ለመሸጥ አይበረታቱም።

3ኛ:የሞኒታሪ ፖሊሲው ቂጥጥር

ከውጪ ውቃ የሚያስመጣ ነጋዴ የጠየቀውን ዶላር 50 በመቶ ወይም 100 በመቶ በብር ማስያዝ ግድ ይለዋል።አሁን ካለው የብር እጥረት አኳያ አዳጋች ያደርገዋል።

4ኛ: የውጪ ምንዛሬ ድልድል ችግር

በአራት ዙር ብሄራዊ ባንክ በድልድል ከሸጠው 282 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ አስመጪ ነጋዴዎች 28 በመቶ ብቻ ነው የተጠቀሙት።

ለመድሃኒትና የህክምና መገልገያዎች 208.2 ቢ$
ለማሽነሪ 42.7 ቢ $
ለጥሬ ዕቃና ለፍጆታ ዕቃዎች 18.1 ቢ $
ከአዲስ ኢንሳይት

Ashenafi Fekadu

STEM with Murad 🇪🇹

21 Jan, 00:22


ተሳተፉ!

STEM with Murad 🇪🇹

21 Jan, 00:21


ስለ ሸሪዓዊ ብይኑ ከመጠየቃችሁ በፊት ቴክኒካሊ ብናስበው፤ የ300 ሺህ ብር ሼር ከኢትዮ ቴሌኮም ከገዛችሁ በአመት ውስጥ የሚያተርፋችሁ 27 ሺህ ብር ብቻ ነው። እንደዛ ከሆነ ደግሞ ለኔ ስጡኝና 30 ሺህ ብር አተርፍላችኋለሁ¡


«የኢትዬ ቴሌኮም ሼር ልግዛ ወይንስ አልግዛ?

ሼር ለመግዛት ስናሰብ የድርጅቱን አሰተዳደራዊና የፋይናንስ ጤንነት ማረጋገጥ አለብን። የአንድ ድርጅት የፋይናንሰ ጤንነት ለማወቅ መጠናዊ (quantitative)እና አይነታዊ (qualitative) መለኪያዎች አሉ።

✍🏽 ቀዳሚው የድርጅት ፋይናንሰ መጠናዊ መለኪያ አጠቃላይ የገበያ ዋጋ (Market Capitakization) ነው። ኢትዮ ቴሌኮም ለአክሲዮን ሸያጭ ያወጣው የሸያጭና የድርጅት ቁመና መግለጫ ሪፖርት (prospectus) እንደሚያሳየው የእያንዳንዱ ዋጋ 300 ብር የሆነ አጠቃላይ 1 ቢሊየን ሼሮች አሉት። ይህም ማለት አጠቃላይ የገበያ ዋጋዬ ነው ብሎ ያሰቀመጠው 300 ቢሊየን ብር ነው። ከዚህ ውሰጥ ለሽያጭ የቀረበው እያንዳንዳቸው 300 ብር የገጽ ዋጋ ያላቸው 1 ሚሊየን ሼሮችን ነው። የድርጅቱ አጠቃላይ የገበያ ዋጋ 300 ቢሊየን ነው ስለተባለ ነው ማለት አይደለም። ይሄ የሚያመለክተን የሼሮቹን ዋጋ ወይም በስቶክ ማርኬት ውስጥ የሚኖረውን ዋጋ ነው። የሚጠቅመንም ኢንደስትሪው ውስጥ ካሉ ሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች ጋር ለማነጻጸር ነው። የድርጅቱን ትክክለኛ ዋጋ የምናውቀው Enterprise value በማሰላት ነው። ይህ በቀላሉ የድርጅቱን የገበያ ዋጋ ላይ ድርጅቱ ያለበትን ብድር በመደመርና ያለውን ጥሬ ገንዘብ በመቀነስ ማስላት ይቻላል። በተጨማሪ አይነታዊ የሆኑ መለኪያዎችን በመጨመር ድርጅቱ ያለውን ሀብት፥ የዘረጋውን መሰረተ ልማት፥ የሰበሰባቸውን ደንበኞች፥ ማፍለቅ የሚችለውን ገቢ፥ የገነባውን ብራንድ፥ በገበያው ውስጥ ያለውን ድርሻ እንዲሁም ያለበትን እዳ ግምት ውስጥ አሰገብተን ማሰላት እንችላለን።

✍🏽 የገቢና የትርፍ (Revenue& Earning)ልኬት ነው። ቢያንሰ ባለፉት አምስት አመታት የድርጅቱ ገቢ ምን ያክል ነበር? በምን ያህል እያደገ ነው? የትርፉ ምጣኔስ? የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ማስላትና ሂደቱን መረዳት እንችላለን። ለምሳሌ የኢትዬ ቴሌኮምን የገቢና ትርፍ እድገት ስንመለከት በ 2020 ገቢው 56 ቢሊየን ብር አካባቢ የነበረ ሲሆን በሰኔ 2024 ደግሞ 93•7 ቢሊየን ብር ደርሷል። ይህ በአማካይ የገቢው እድገት 21% አካባቢ እንደሆነ ያሳያል።

✍🏽ሌላው የፋይናንሰ ጤንነት መለኪያ የሼር ገቢ (Earning per share)ነው። በዚ ቀመር የድርጅቱ አንድ ሼር በአመቱ ምን ያክል የትርፍ ምጣኔ አገኘ የሚለው ይሰላል።
ለምሳሌ: ኢትዬ ቴሌ ኮም ባለፈው የሂሳብ አመት የተጣራ ትርፉ 21•79 ቢሊየን ብር እንደሆነ ተገልጽዋል። ይህ ትርፍ ድርጅቱ ላለው አጠቃላይ የሼር ብዛት (1 ቢሊየን) ሲካፈል 21•79 ብር የሼር ገቢ ምጣኔ ይኖረዋል። ይህም ማለት አንድ ሼር 21•79 ብር ትርፍ ይኖረዋል። አሁን ባለው የሼር ዋጋ አንዱ ሼር 300 ብር የሚሸጥ በመሆኑ የ 300 ብር ኢንቨሰትመንት በአመት 22 ብር አካባቢ ትርፍ ያሰገኛል። ይህ ትርፍ ያለፉት አመታት እድገቱን ከተከተለ በየአመቱ በአማካይ 21 ፐርሰንት እያደገ ይሄዳል።

✍🏽ሌላኛውና ወሳኝ የሚባለው የፋይናንሰ መለኪያ PEG ratio ይባላል። የአንድ ሼርን ትርፍ እድገትን ግምት ውስጥ አሰገብተን የምናሰላበትና የሼሩ ዋጋ ተገቢ ነው? በዝቶበታል? ወይንስ ርካሸ ነው የሚል የሚያመላክተን ነው።

የቴሌን ምሳሌ ቀጠለን ብንመለከተው የአንድ ሼር ትርፍ 22 ብር አካባቢ እንደሆነ አይተናል። ይህን የአንድ ሼር ትርፍ ለአመታዊ እድገቱ ማለትም 21 ፐርሰንት (በሙሉ ቁጥር) ሰናካፍለው 1•04 አካባቢ ይመጣል። የአንድ ሼር PEG ratio ከ1 በላይ ከሆነ የሼር መሸጫ ዋጋው ውድ መሆኑን ያመላክታል።

✍🏽ከነዚህ በተጨማሪ ለውሳኔ የሚያግዙን ንፅፅራዊ የሆኑ የፋይናንሰ ጤንነት መለኪያዎች አሉ። ከነዚህ ቀዳሚው የሼር ትርፍ ንጻሬን(EPS ratio) ከሌሎች ትርፎች ጋር ማነጻጸር ነው። ከላይ እንዳየነው የኢትዬ ቴሌኮም የአንድ ሼር ትርፍ 22 ብር አካባቢ ነበር። ይህን ትርፍ በአንድ ሼር መሽጫ ዋጋ ስናካፍለው (22/300)= 7 ፐርሰንት አካባቢ ነው። ሰለዚህም ባለፈው የሂሳብ አመት የቴሌ ሼር የትርፍ ምጣኔ 7 % ብቻ ነበር። ይህ ደግሞ ከባንክ የቁጠባ ወለድ በታች ከመሆኑ በተጨማሪም ከሌሎች ኢንቨሰትመንቶች የትርፍ ምጣኔ ያነስ ነው።

✍🏽 ግምት ውስጥ መግባት ካለበት የአይነታዊ መለኪያ አንዱ የድርጅቱ የቢዝነሰ ሞዴል የእድገት ተስፋ ነው። ኢትዮ ቴሌኮም ከቴሌኮም ሰርቪስ በተጨማሪ ግዙፉ የዲጂታል ፋይናንሰ(Fin-Tech) ተቋም እየሆነ መጥቷል። ይህም የድርጅቱን እድገት ብሩህ ያደርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ ኢትዬ ቴሌኮም ለመሰረተ ልማት ዝርጋታ ከፍተኛ መዋለ ንዋይ ያፈሰሰ በመሆኑ ባለፉት አመታት ትርፉ ያነስ የመሆን እድሉና ወደፊት የማደግ ተሰፋ እንዳለው አመላካች ነው።

✍️የአንድ ድርጅትን ሼር ለመግዛት እነዚህ መለኪያዎች በቂ አይደሉም። ወሳኙ መለኪያ መግዛት የፈለግንበት ምክኒያት ነው። ከትርፍ ባሻገር ባለቤት የመሆን፥ ተጽዕኖ የመፍጠር፥ ውርስ የመሳሰሉ ምክኒያቶች ሊኖሩን ይችላሉ። ሌላው እጃችን ላይ ያለው የገንዘብ መጠንና ያሉን አማራጭ ኢንቨሰትመንቶች ውሳኔያችን ላይ ተፅዕኖ ያሳድራሉ።»

«የኢትዬ ቴሌኮም የሼር ሽያጭን በተመለከተ ለውሳኔ የሚያግዙ የፋያናንሰ ጤንነት መለኪያዎችን በተመለከተ አንድ ልጥፍ አቅርቤ ነበር። ሆኖም የተወሰኑ ግልፅ አልሆነልንም የሚል ጥያቄዎች ደርሰውኛል። በቀላል ነጥብ ለማሰረዳት ልሞክር።

ለሽያጭ የቀረበው ሼር የአንዱ መግዢያ ዋጋ 300 ብር ነው። በተጨማሪ 1•5 ፐርሰንት ሰርቪስ ቻርጅና ከሰርቪሰ ቻርጁ ላይ የሚሰላ ተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ አለው። አንድ ስው 1000 ሼር መግዛት ቢፈልግ
👉 የሼር ክፍያ 300 ሺ ብር
👉 ሰርቪሰ ቻርጅ 4500 ብር
👉 የተጨማሪ እሴት ታክሰ 675 ብር

በድምሩ 305,175 ብር ይከፍላል።

ይህን ሼር የሚገዛው ለትርፍ ከሆነ፥ በዚህ ብር ምን ያክል አተርፋለሁ የሚለው ዋነኛ ጥያቄ ይሆናል። መልሱን ለማግኘት መጀመሪያ ኢትዬ ቴሌኮም ባለፈው አመት ሰንት አተረፈ እና የትርፍ እድገቱስ ስንት ፐርሰንት ነው የሚለውን ማወቅ ያሰፈልጋል።

በዚህ መሰረት የኢትዬ ቴሌኮም ያለፈው አመት

👉 የአንድ ሼር ትርፍ 22 ብር አካባቢ ነበር።
👉ያለፉት አመታት አማካይ የትርፍ እድገት 21 ፐርሰንት አካባቢ የነበረ ሲሆን እድገቱ በዚሁ ከቀጠለ የዚህ አመት የአንድ ሼር ትርፍ 27 ብር አካባቢ ይሆናል።

👉 ይህም አንድ በ300 ብር የተገዛ ሼር 27 ብር አካባቢ ያተርፋል ማለት ነው። 1 ሺ ሼሮችን 305 ሺ ብር አካባቢ አውጥቶ የገዛው ሰው ትርፉ 27 ሺ ብር ይሆናል።

ይሄን መግዛት ያዋጣኛል አያዋጣኝም ግላዊ ውሳኔ ነው።»

©: Ibrahim Abdu

STEM with Murad 🇪🇹

21 Jan, 00:20


የኢትዮ ቴሌኮምን ሼር እንግዛ ወይ⁉️
=========================

«ይህ የብዙዎች ጥያቄ ነው። የዚህ ዓይነት ጥያቄ ከሀገር ውስጥም ከውጭ ሀገርም በውስጥ በኩል እየቀረበልኝ ነው። በተመሳሳይ ለአንዳንድ ወዳጆቼም እንዲህ ዓይነት ጥያቄ እንደቀረበላቸው እገምታለሁ።

ለእንደዚህ ዓይነት ጥያቄ "ግዙ" ማለትም "አትግዙ" ማለትም ተገቢ አይሆንም። ምክንያቱም ብዙ የማይታወቁ መረጃዎች ስላሉ ነው።

ለእያንዳንዱ ግለሰብ ውሳኔ እንዲረዳ ግን አንዳንድ ነጥቦችን ማየት ይጠቅማል።

፩) አብዛኛው አክሲዮን የተያዘው በማን ነው?

ከ20-25 % በላይ የሚሆነው አክሲዮን በ1 አካል ከተያዘ ትኩረትን የሚስብ ነው። በ1 አካል የተያዘው አክሲዮን ከ33% በላይ ከሆነ ደግሞ አሳሳቢ ነው። 50% በላይ ከሆነ ደግሞ ያንን አክሲዮን መግዛት አደገኛ ነው። ከ75% በላይ አክሲዮን በ1 አካል ከተያዘ ደግሞ የተለየ ምክንያት ከሌለህ እና አክሲዮን ሻጩን በጣም የምታምነው ካልሆነ በቀር አክሲዮን የምትገዛበት ልዩ ምክንያት ያስፈልግሃል።

ምክንያቱም ባለ ብዙ አክሲዮኑ በፈለገ ጊዜ አክሲዮን እያወጣ እየሸጠ ያንተን ድርሻ ያመነምነዋል። ይህ Dilution (ማቅጠን) ይባላል። ለምሳሌ : 1% ቢኖርህ ባለ ትልቅ አክሲዮኑ አዲስ አክሲዮን በመሸጥ ድርሻህን ወደ 5% ሲለው ደግሞ ወደ 0.5% ያወርደዋል። አንተም እያየኸው ሼርህ ይሟሟል። ብር ምንዛሪው ሲቀንስ አላየህም? እያየኸው ዓቅሙ አልላሸቀም? እንደዚያ ማለት ነው።

ECX ላይ መጀመሪያ ወንበር ሲሸጥ ለ100 ገዢዎች ብቻ ተብሎ ነበር የተሰበከው። በኋላ ግን ያለገዢዎች ምክክር ወደ 400 አደገ። አሁን ስንት እንደሆኑ አኣውቅም። በንግድ ስትሻረክ መተማመን ወሳኝ ጉዳይ ነው።

አንድ 3/4ኛ ድርሻ ያለው አካል ካለ፣ ውሳኔው በሙሉ በእርሱ ቁጥጥር ስር ነው። ያ ችግር የማይኖረው፣ ውሳኔ ሰጪው አንድም ታማኝ ሲሆን፣ ሲቀጥልም አንተ ሌላ አማራጭ ሳይኖርህ ቀርቶ ይህ እድል በልዩነት ሲሰጥህና አንተም ተስፋ ስታደርግበት ነው።

የኢትዮቴሌኮም ኢንዱስትሪ አሁን ባለው ሁኔታ አትራፊ ነው። አትራፊ መሆኑ ብቻ ግን አዋጭ ኢንቨስትመንት ነው ማለት አይደለም። ሌሎች መታየት ያለባቸው ጉዳዮች ይኖራሉ።

አሁን በተነገረው መሠረት መንግስት 90% ድርሻን ይዞ 90% ለሌሎች የሚሸጥ ነው። የመንግስት ድርሻ ከ30% ባይበልጥ ግሩም ነበር።

የባለቤቱ (የመንግስት) ታማኝነት ዋናው ጉዳይ ነው። አሁን ባለው የ90% አክሲዮን ድርሻ ሁኔታ መንግስት ሌሎች ባለአክሲዮኖችን ሳያወያይ ዋና ዋና ጉዳዮችን መቀየር የሚያስችል መብት ህጉ ይሰጠዋል። አንተ ባለ ትንሽ አክሲዮኑ የተባለውን ከመቀበል ውጪ መብት የለህም።

የምታምነውና በጥሩ % ትርፋማ የሆነ እና በየዓመቱ ትርፍ የሚያከፋፍል አክሲዮን ሻጭ ካገኘህ ግን 0.001% ድርሻም ትልቅ ነውና ብትገዛ ጥሩ ነው።

ባለ ትልቅ አክሲዮኑ ፈቃደኛ ካልሆነ ግን ድርጅቱ አትርፎም ትርፍ እንዳይከፋፈል ሊወስን ይችላል። አንተም ሁሌ ወሬህ አክሲዮን አለኝ ከማለት ባለፈ "ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም እላይ" እያልህ መክረም ነው። እንደዚያ የሆኑ ብዙ የሀገራችን አክሲዮኖች አሉ።

መንግስት "ቴሌ የምትታለብ ላም ናት" ሲል ከርሞ አሁን ለምን አክሲዮኑን ይሸጣል? የዚህ ምክንያት እንደየአመለካከታችን ይለያያል። ዋናው ምክንያት የሚመስለኝ የገንዘብ ግሽበትን ለመቆጣጠር ገበያ ውስጥ ያለውን ብር መምጠጥ ነው። ይሄ በታክስ፣ ቅጣት እና የመንግስት አገልግሎቶች ዋጋ መናር የታየ ነው።

መንግስት እያደረገ ያለው ነገር ሲታይ ለዜጎች ትርፍ ማጋራት አስቦ አይመስልም። ይልቅስ ተቀማጭ ገንዘብ ካላቸው ግለሰቦች ላይ ገንዘባቸውን መምጠጥ ይመስላል። አይደለም ያላችሁም ልክ ትሆኑ ይሆናል። ለእኔ የታየኝ ግን እንዲያ ነው።

፪)

፫)

፬)

ብዬ የማቀርባቸው ሌሎችም ማብራሪያዎች ነበሩኝ። ግን ምን አስጨነቀኝ? ለገባው ይሄው 1 ምክንያት በቂ ነው።

ውሳኔውን ግን በራሳችሁ ወስኑ።»

ታዋቂው የንግድ አማካሪ እና አሰልጣኝ ጌቱ ከበደ በማህበራዊ ሚድያ አድራሻው የጻፈው!

||
https://t.me/STEMwithMurad

STEM with Murad 🇪🇹

21 Jan, 00:20


«ተነሡ!

idea 008/2017።
ከባኦባብ(Adansonia digitata) ፍሬ ዱቄት ማምረት እና ኤክሥፖርት ማድረግ።

ባኦባብ(Adansonia digitata)ዛፍ በኛ ሃገር ሠሜኑ ክልል ለምሣሌ ሠቆጣ አይቼዋለሁ። ከፍሬው የሚገኘውን ፐልፕ አድርቆ፣ፈጭቶና አሽጎ ለሃገር ውሥጥም ለውጪም ገበያ ማቅረብ ይቻላል።

ልክ እንደሞሪንጋ ባኦባብ ዱቄት ድንቅ ነው። ለምግብነት፣ለጤንነት፣ለውበት፣ለመድሃኒትነት ይጠቅማል።
የfruit pulp ኡ rich in vitamin C, antioxidants, and other essential minerals, such as potassium, magnesium, iron, and zinc.የ Leaves ኡcontain calcium and high-quality proteins that can be digested easily.Seeds ኡ high in fiber, fat, and macronutrients, such as thiamine, calcium, and iron.Baobab oil contains antioxidants and nutrients, such as omega-3 fatty acids, vitamins A, D, and E.Baobab powder is highly nutritious with high vitamin C content, vitamin B6, niacin, iron, and potassium.

ለ ሥኳር ታማሚዎች፣ለውፍረት ቀናሾች፣ለልብ ፣ለጨጓራ፣ወዘተ ይጠቅማል።ፍራፍሬ እንደሚበላው መውሠድ ይቻላል።
The high fiber content, particularly soluble fiber, acts as a prebiotic, promoting a healthy gut microbiome.

በዓለም ገበያ በኪሎ ከ 100እሥከ 200 ዳላር ይሸጣል።ሠርቲፋይድ ሁኑ፣ህጋዊ ሁኑ።ከተማ ያላችሁ በብዛት እየተረከባችሁ በማሸግና በመሸጥ ትሥሥር መፍጠር ትችላላችሁ።

በርቱ!»

ቤጃይ

STEM with Murad 🇪🇹

21 Jan, 00:19


#ScamAlert የካናዳ መንግስት ለ10 ሺህ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የስራ እድል አመቻቸ በማለት ከሚፈጸም የማጭበርበር ድርጊት እንጠንቀቅ

የውጭ ሀገር የስራ እድሎችን እናመቻቻለን በሚል የሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ ይገኛሉ።

እንደ ፌስቡክ እና ቴሌግራም ያሉ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና ፈጣን መልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎች ደግሞ መሰል የማጭበርበር ድርጊት ለሚፈጽሙ አካላት አመቺ ሁኔታን ፈጥረዋል።

እነዚህ አካላት በግልጽ የስልክ ቁጥሮችን እና የባንክ ሂሳብ ቁጥሮችን በማጋራት የተሻለ ገቢ እና ህይወትን ተስፋ በማድረግ ወደነሱ የሚሄዱ ግለሰቦችን ያጭበረብራሉ።

ከሰሞኑም “የስራ ማስታወቂያ” የሚል ርዕስ ያለው እና የካናዳ መንግስት ለ10 ሺህ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የስራ እድል እንደሰጠ፤ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያንም ስልክ በመደወል እንዲመዘገቡ የሚያሳስብ ደብዳቤ በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እየተጋራ ይገኛል።

ይህ ደብዳቤ የሁለቱ ሀገራት ባንዲራ፤ ‘CANADA EMBASSY’ የሚል አራት ማዕዘን “ማህተም” እንዲሁም የቃላት እና ይዘት ግድፈት ያለበትና ሀሰተኛ መሆኑ የሚያስታውቅ ክብ ማህተም አርፎበታል።

ኢትዮጵያ ቼክ መሰል የማጭበርበር ድርጊቶችን በተመለከተ በተለያዩ ወቅቶች መረጃዎችን ከሚመለከታቸው አካላት በማጣራት ለተከታዮቹ ሲያቀርብ ቆይቷል።

በካናዳ መንግስት የተመቻቹ የስራ እድሎች እና ቪዛ ሎተሪ በሚል በግለሰቦች ስልክ ቁጥር እና የቴሌግራም አድራሻዎች አማካኝነት የሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶችም ከዚህ በፊት ከሰራንባቸው ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል።

በወቅቱ ኢትዮጵያ ቼክ ከካናዳ ኤምባሲ መረጃን ጠይቆ በኢንተርኔት አማካኝነት የሚፈጸሙ በርካታ የማጭበርበር ድርጊቶች መኖራቸውን እና ሰዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና መሰል መረጃዎችን በደንብ መመርመር እንዳለባቸው ኤምባሲው ገልጾ ነበር።

በተጨማሪም ኤምባሲው ሰዎች የሀገሪቱን ኢሚገሬሽን ፕሮግራሞች በተመለከተ ሁልጊዜ ትክክለኛ የሀገሪቱን ድረ-ገጾች እና ማህበራዊ ትስስር ገጾችን እንዲመለከቱ መክሯል።

በዚሁ መሰረት “የካናዳ መንግስት ለ10 ሺህ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የስራ እድል ሰጠ” በሚል እየተጋራ የሚገኘው ደበዳቤ ላይ ባደረግነው ማጣራት ደብዳቤው በራካታ የጽሁፍ ግድፈቶች ያለበት፤ ግልጽ ያልሆነ እና አጠራጣሪ “ማህተሞች” ያረፉበት መሆኑን ተመልክተናል።

በተጨማሪም የካናዳ ኢሚግሬሽን፤ ስደተኞች እና ዜግነት ተቋም ድረ-ገጽን የተመለከትን ሲሆን “ለ10 ሺህ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የስራ እድል መሰጠቱን” የሚገልጽ ምንም አይነት መረጃ አለመኖሩን አረጋግጠናል፡ https://www.canada.ca/en/immigration-refugees-citizenship/news.html

የተቋሙን ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የኤክስ (ትዊተር) አካውንትም የሀገሪቱን ኢሚግሬሽን ጉዳዮች የሚመለከቱ መረጃዎችን በየጊዜው የሚያጋራ ቢሆንም ስለ “10 ሺህ የስራ እድሉ” ምንም አይነት መረጃ አለማጋራቱን አረጋግጠናል፡ https://twitter.com/CitImmCanada?s=20&t=9JlcTQWzQhB6JyFrFKtJrQ

ስለዚህ አጓጚ የስራ እድሎችን እንደ ማታለያ በማቅረብ ለሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶች እንዳንጋለጥ ህጋዊ መንገዶችን እንምረጥ፣ እንዲሁም ትክክለኛነታቸው የተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን እንደ መረጃ ምንጭ እንጠቀም።

©: ኢትዮጵያ ቼክ

STEM with Murad 🇪🇹

21 Jan, 00:19


ተነሡ!
(ድሮ ቀዝቃዛ ውሃ በጣሣ ሢቸለሥባችሁ 😍 imagine ነፍ ጩኸት።ዳይ ወደ ት/ቤት፣አሁን ግን ወደ ሃሣብ )

idea 007/2017 ዓ.ም።
የንቦች ምግብ አምርቶ መሸጥ::

አሁን ባለው ኢኮሎጂ ሠው ሢበዛ ንቦች ይቀንሣሉ የማር እጥረት ይከሠታል።አበቦች ይጠፋሉ።እናሥ ማር እንዴት እናመርታለን???

የአበባ ፖለን ሠብሣቢ ቀፎ (የቀፎ መግቢያቸው ላይ መሹለኪያ ቀዳዶች/ወንፊት በማሥቀመጥ...)ጫካ ወይንም አበባ ያለበት እናሥቀምጣለን።50gm ድረሥ በቀን ከአንድ ቀፎ ቢሠበሠብ አሪፍ ነው።ክፍለሃገር ያሉ ወጣቶች በዚህ ግብአት ትሥሥር መፍጠር ይችላሉ።

ከተሞች ውሥጥ ንብ ቀፎ ለማሥቀመጥ የንቦች ምግብ እጅጉን አሥፈላጊ ነው።አረብ ሃገራት፣ቻይና፣አውሮፓ፣አሜሪካ፣አንድ አፍሪካ ሃገራት፣ላቲን ከሜሪካ ወዘተ።

የኛ ሃገር የማር ምርት መጨመር አለበት።የንቦች ምግብ ማዘጋጀት ደግሞ አንዱ እርምጃ ነው።

እናዘጋጅ.....

ምግቡ ለክረምት፣ለበጋ፣ለፀደይና ለመጸው ሦሥት አምድ አለው።

የሥኳር ሽሮፕ፣ፖለን ሠብሥቲቲውት፣የፕሮቲን ፓቲሥ።

1-ሥኳር ሽሮፕ: ሞቅ ባለ ውሃ (50% ) ውሥጥ 50% ሥኳር መበጥበጥ።
2.ፖለን ሠብሥቲቲውት:የአኩሪ አተር ዱቄት 30%፣የወተት ዱቄት30%፣የቢራ እርሾ29% ፣ትንሽ ፖለን 1% አቡክቶ ማድረቅ።
3.ፕሮቲን ፓቲሥ: ትንሽ ዋክሥ/ሠምና 1 እና ሁለትን እሽት አድርጎ መቀላቀል።
አሽጋችሁ መሸጥ።

በዚህ ምርት ንቦች ድካማቸውንና ግዜአቸውን ሥለሚቀንሥላቸው ጀምረው የሚያቋርጡት ሠም አይኖርም ።እሥከ ጥግ በመግባት ሰሙንና ምግቡን ያመርቱታል፣ጥናቶች የሚያሣዩት በእጥፍ የማር ምርትን ይጨምራል።የንብን ድካም የቀነሠ ሡፐር ማርኬት በሉት ።
በጣም አዋጪ ነው።

በርቱ!

ቤጃይ

9,867

subscribers

227

photos

8

videos