የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ገጽ

@snnprs_revenue_bereau


Central Ethiopia Regional state Revenue Bureau

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ገጽ

22 Aug, 13:10


16/12/2016
“ተቋምን በልኅቀት ገቢን በስኬት”
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ሰራተኞች የ2017 የተቋሙ መልካም አስተዳደር ዕቅድ ላይ ውይይት ተደረገ፡

በውይይቱ ማስጀመሪያ ላይ የቢራ ኃላፊ አቶ ዘይኔ ቢልካ በ2016 በጀት ዓመት በአዲስ በመደራጀት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራ ከጀመርን አንድ አመት የሞላን መሆኑን በማንሳት ከአደረጃጀት ጋር ባለ የማቴሪያል እጥረት ተቋቁመን የተሻለ የፊዚካል እና የገቢ ዕቅድ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የሰራተኛውን ተነሳሽነት ቁርጠኝነት በማድነቅ ሠራተኛው ላሳየውን ትጋት በተቋሙ ማኔጅመንት ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
አቶ ዘይኔ አያይዘው ሁሌም ተግባራችንን በምንፈፅምበት ወቅት ለምን የሚለውን ጥያቄ እየመለስን መሄድ እንዳለብንና እንደገቢ ተቋም ሠራተኛ ተግባራችንን ከናከናውን ለክልላች ልማት የሚያስፈልገውን ሃብት የክልሉ አቅም በሚያመነጨው ልክ ገቢ መሰብሰብ መቻል እንዳለብን ትርጉም ሠጥቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ የ2017 መልካም አስተዳደር ዕቅዱን ያቀረቡ ወ/ሮ መነን ወልዴ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተርም በበኩላቸው የተሸለ የገቢ አሰባሰብ እንዲኖር እና በግብር ከፋዩና በህብረተሰቡ ዘንድ የሚኖረን ተቀባይነት ለማረጋገጥ ተግባራችን መልካም ሥነ-ምግባር በመላበስ እንድናከናውን እና የሥነ-ምግባር ጉድለት ያለባቸው ፈፃሚዎች ሲኖሩ ጥቆማ በመስጠት ሃላፊነታችንን መወጣት ይገባናል ብለዋል፡፡
በተሳታፊዎች በኩልም የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች በቶሎ ወደ ተግባር መግባት ቢችሉ፣ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች በጊዜ ቢጀመሩ፣ የመረጃ አያያዝ ሥርዓታችን ቢሻሻል፣ ሥራዎችን ስንሰራ በቴክኖሎጂ ብናስደግፍ የሚሉ ሃሳቦች ተነስተዋል፡፡

በመጨረሻም በ2017 በጀት አመት የሪፎርም ሥራው ተሠርቶ ተጠንቶ የተዘጋው ቢፒአር ተግባራዊ እንደሚደረግ በዚህም መሠረት የተቋም ሠራተኞች የላቀ አፈፃፀም ሲያስመዘግቡ እውቅና የሚሰጥበት እንዲሁም ድክመት ሲኖራቸው የአቅም ግንባታ ሥራ እንደሚሰራ በውይይቱ ተመላክቷል፡፡

የማዕላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ
+2510461457815/ +2510461457282
+2510461454993/ +2510461457229

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ገጽ

10 Aug, 12:23


እንኳን ደስ አለን! ኢትዮጵያ በኦሊምፒኩ የመጀመሪያ ወርቋን አገኘች 

በፓሪስ 2024  የኦሊምፒክ ወድድር በማራቶን ኢትዮጵያ በአትሌት ታምራት ቶላ አማካኝነት የመጀመሪያ ወርቋን አግኝታለች፡፡

ሀምሌ 04/2016 ዓ/ም

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ
+251 046 145 78 15 /+251 046 145 72 82
+251 046 145 49 93 / +251 046145 72 29

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ገጽ

06 Aug, 10:36


ደረሰኝን
***
ደረሰኝን በመጠቀም ሂደት ውስጥ ድርሻ ያላቸው ተዋናዮች በተለይም ሸማቾች፣ ታክስ ከፋዮች እና በየደረጃው የሚገኙ ታክስ ሰብሳቢ ተቋማት በታክስ ሕጉ የተቀመጡትን የደረሰኝ አጠቃቀም ስርዓቶች የማስከበር ሕጋዊ እና ሞራላዊ ኃላፊነትና ግዴታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ
+251 046 145 78 15 /+251 046 145 72 82
+251 046 145 49 93 / +251 046145 72 29

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ገጽ

05 Aug, 06:33


ግብራችሁን በበወቅቱ ለከፈላችሁ የደረጀ "ሐ"ግብር ከፋዮች ምስጋናችን ይድረሳችሁ!
የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮችም እንዲሁ ግብራችሁን በቅድሚያ በመክፈል አገራዊ እና ክልላዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ከወዲሁ እናሳስባለን!!!
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ
+251 046 145 78 15 /+251 046 145 72 82
+251 046 145 49 93 / +251 046145 72 29

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ገጽ

25 Jul, 11:33


ታክስን በወቅቱ አስታውቆ መክፈል ያለው ጠቀሜታ
🇪🇹
ታክስ የመክፈል ግዴታን ያለመወጣት የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ ስርዓቱን ለማስተዳደር በወጡ ህጐች ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡ ባደጉ አገራት የሚኖሩ ዜጐች የሚፈለግባቸውን ታክስ በወቅቱ አስታውቀው አለመክፈል በህግ ከማስጠየቅ ባለፈ መልካም ስምን ጨርሶ እስከማጥፋት የሚደርስ አስነዋሪ ተግባር እንደሆነ በሁሉም ዘንድ ይታመናል፡፡
በንግድ ሥራ ውስጥ መሰማራት የሚፈልጉ ዜጐች መሰማራት በሚፈልጉት የንግድ መስክ ውጤታማ ሊያደርጋቸው የሚያስችላቸውን መንገድ አስበው እንደሚገቡበት ሁሉ በሀገሪቱ ያሉ የታክስ ህጐችን አክብረው ግዴታቸውን ሊወጡ ስለሚችሉበት ሁኔታ አስቀድመው ሊያስቡበትና ሊዘጋጁበት ይገባል፡፡
ወደ ንግድ ሥራ የሚገቡ ወይም በንግድ ስራ ውስጥ ያሉ አካላት ከታክስ አከፋፈል ጋር ተያይዞ ትኩረት ሰጥተው ሊተገብሯቸው ከሚገቡ መሠረታዊ ጉዳዮች ቀዳሚው ተግባር ሊሆን የሚገባው የሥራቸውን ወይም የገቢያቸውን ሁኔታ በመግለፅ በግብር ከፋይነት የመመዝገብና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር መውሰድ ነው፡፡
ወደ ንግድ ስራው ከገቡም በኋላ ተቀባይነት ያላቸውን የሂሳብ አያያዝ ስርዓቶችን በመከተል የሂሳብ ሰነዶችን የመያዝ፣ በንግድ ድርጅቱ ላይ የሚደረጉ ማናቸውንም ለውጦች በጊዜው የማሳወቅ ኃላፊነትና ግዴታን መወጣት አለባቸው፡፡
በተጨማሪም ለንግድ ሥራቸው ህጋዊ ፈቃድ መያዝና በየወቅቱ ማደስ እንደዚሁም በህግ በተደነገገው መሠረት በሂሳብ ጊዜ ውስጥ የሚፈለግባቸውን ታክስ ለታክስ ባለስልጣን ማሳወቅና በዚያው ጊዜ ወስጥ አጠናቆ መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡
የታክስ ግዴታን በመወጣት ሂደት ውስጥ ከግብር ከፋዮች ከሚጠበቁ መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ በህጉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ታክስን አሳውቆ መክፈል እንደመሆኑ የታክስ ማስታወቂያን በወቅቱ ማቅረብና ታክስ መክፈል አለባቸው፡፡
የታክስ ማስታወቂያ የሚባሉት በገቢ ግብር አዋጁ መሰረት የሚቀርቡ የግብር ማስታወቂያዎች፣ ወደ ሀገር ውስጥ በገቡ እቃዎች ላይ የሚከፈል የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም የኤኬሳይዝ ታክስን የሚያሳይ የጉሙሩክ ዴክለራሲዮን፣ የኤክሳይዝ ታክስ ማስታወቂያዎች፣ የተርን ኦቨር ታክስ ማስታወቂያዎች፣ በቅድሚያ የሚከፈሉ የታክስ ማስታወቂያዎች ወይም በታክስ ህግ መሰረት የታክስ ማስታወቂያ ተብለው የሚጠቀሱና በታክስ ከፋዩ የሚዘጋጁ የታክስ ስሌት ማስታወቂያዎች ናቸው፡፡
የታክስ ማስታወቂያን አዘግይቶ ማቅረብ፣ አሳንሶ ማሳወቅ እና ታክስን አዘግይቶ መክፈል በታክስ ህጉ መሠረት ቅጣት የሚያስከትል ከመሆኑም ባሻገር መልካም ስምን ያጐድፋል፣ የንግድ ሥራን ህጋዊነትና ውጤታማነትን አስጠብቆ ለማስቀጠል የማያስችሉ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ምክንያት ይሆናል፡፡
የታከስ ግዴታን በወቅቱና በተገቢው መጠን ለመወጣት የሚያዙ የሂሳብ መረጃዎችና ሰነዶች መክፈል ያለበትን ትክክለኛ ታክስ ለማወቅ ያስችላሉ፡፡ የንግድ ስራው እያተረፈ ይሁን እያከሰረ መሆኑን ለማወቅና የድርጅቱን ቀጣይ እጣ ፋንታ በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ ለመወስንም ያግዛሉ፡፡
በግብር ከፋዩና በግብር ሰብሳቢው ተቋም መካከል በቀላሉ ሊያግባባ የሚችል ጤናማ ግንኙነት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ እንደባንክና ኢንሹራንስ የመሳሰሉ ድርጅቶችን ጨምሮ በሌሎችም መንግስታዊ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተገቢው ለማግኘትም የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችንም ይፈጥራል፡፡
የንግድ ድርጅቱን ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዙ የአሰራርና የአስተዳደር ስልቶችን ለመቀየስ፣ የድርጅቱ የሰው ሀብትና ንብረት በተገቢው ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን በየጊዜው ለመከታተልና የንግድ ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ጠቀሜታዎች ያሉት በመሆኑ ግብር ከፋዮች የሂሳብ ሰነዶችን በተገቢው መያዝና በወቅቱ ታክስን አሳውቆ መክፈል አለባቸው፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ
+251 046 145 78 15 /+251 046 145 72 82
+251 046 145 49 93 / +251 046145 72 29

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ገጽ

24 Jul, 13:22


በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ቀበሌ ስለደረሰው አደጋ የሀዘን መግለጫ!
***
ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት ናዳ ምክንያት በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ በደረሰው ከፍተኛ ጉዳት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ገቢዎች ቢሮ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ
+251 046 145 78 15 /+251 046 145 72 82
+251 046 145 49 93 / +251 046145 72 29