የሰለምቴዎች ቻናል

@slmatawahi


وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ

ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?

የሰለምቴዎች ቻናል

23 Oct, 00:08


ሱረቱል ዋቂዓ📖🎧
فَأَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ مَا أَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ

የቀኝ ጓዶችም ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡

◍ ወንድም ቶፊቅ

የሰለምቴዎች ቻናል

22 Oct, 23:43


የፕሮቴስታንት ሊቅ አስተማሪ ተብሎ የሚታወቀው ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ ስለ ኡሥታዝ ወሒድ የሰጡት ምስክርነት

አላህ መልካም ስራውን ይቀበለው መምህራችን።

የሰለምቴዎች ቻናል

22 Oct, 23:11


「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」

╭┄┈┈⟢
│❏ አል ቀዋዒዱል ሒሳን القواعد الحِسان

│አል ሙተዐሊቀቲ ቢተፍሲሪል ቁርኣን
╰─────────────────╯    
🎙የደርሱ አቅራቢ:-
├────⟢
🎧 ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም
╰──────────────
╭⧿⧿⛉
├⎙አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ
│ይጠቀሙ!

┝ለሌሎችም ሼር በማድረግ የአጅሩ
│ተቋዳሽ ይሁኑ!
╰───────────
╭╼──────────────
┢⎘  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን

🖇 t.me/SheikhMuhammedZainadam
╰╼───────────────────────╯

የሰለምቴዎች ቻናል

22 Oct, 21:29


◆▮ውይይት▮◆

"የኢየሱስ ስም ወሎ ነው"እየሱስ እጃችሁን ሳትታጠቡ ብሉ ይላል? ኢየሱስ እጁን ሳይታጠብ በላ ? "


◍ ወንድም ዒምራን
◍ ወንድም አቡ ሳለህ
         🅥🅢
◍ወገናችን ኪንግ
◍ወገናችን ኢስጢፍኖስ
ሌሎችም  ወገኖች ጋር

የሰለምቴዎች ቻናል

22 Oct, 21:24


መደምደሚያ
አላህ ሰዎች ሳያውቁ በሚሰሩት መጥፎ ሥራ አይጠይቃቸውም፤ የራሱን መልእክተኛ እስከሚልክ ድረስ ማንንም ያለ ፍትሕ አይቀጣም፦
33:5 *በእርሱ በተሳሳታችሁበትም ነገርም በእናንተ ላይ ሐጢያት የለባችሁም፤ ግን ልቦቻችሁ ዐዉቀው በሠሩት ሐጢያት አለባችሁ* አላህም መሃሪ አዛኝ ነው። وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌۭ فِيمَآ أَخْطَأْتُم بِهِۦ وَلَٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًۭا رَّحِيمًا
17፥15 *መልእክተኛንም እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም*፡፡ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبْعَثَ رَسُولًۭا

ከመልክተኞቹ መላክ በኋላ ሰዎች አልሰማንም ብለው በአላህ ላይ አስረጅ እንዳይኖር አብሳሪዎች እና አስጠንቃቂዎች የኾኑን መልክተኞች ልኳል፦
4፥165 *ከመልክተኞቹ በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ አስረጅ እንዳይኖር አብሳሪዎች እና አስጠንቃቂዎች የኾኑን መልክተኞች ላክን*፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡ رُّسُلًا مُّبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَى اللَّهِ حُجَّةٌ بَعْدَ الرُّسُلِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا

አላህ ባለማወቅ ለሠራነው መጥፎ ሥራ በዱንያ ተውበት ማድረግ ነው፤ በስሕተት መጥፎን ለሠሩና ከዚያም ከዚህ በኋላ ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው፦
16፥119 ከዚያም ጌታህ *ለእነዚያ በስሕተት መጥፎን ለሠሩና ከዚያም ከዚህ በኋላ ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው*፡፡ ثُمَّ إِنَّ رَبَّكَ لِلَّذِينَ عَمِلُوا السُّوءَ بِجَهَالَةٍ ثُمَّ تَابُوا مِن بَعْدِ ذَٰلِكَ وَأَصْلَحُوا إِنَّ رَبَّكَ مِن بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥54 እነዚያም በተአምራታችን የሚያምኑት ወደ አንተ በመጡ ጊዜ «ሰላም በእናንተ ላይ ይኹን፡፡ ጌታችሁ በነፍሱ ላይ እዝነትን ጻፈ፡፡ *እነሆ ከእናንተ ውስጥ በስሕተት ክፉን ሥራ የሠራ ሰው ከዚያም ከእርሱ በኋላ የተጸጸተና ሥራውን ያሳመረ እርሱ አላህ መሓሪ አዛኝ ነው»* በላቸው፡፡ وَإِذَا جَاءَكَ الَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِنَا فَقُلْ سَلَامٌ عَلَيْكُمْ ۖ كَتَبَ رَبُّكُمْ عَلَىٰ نَفْسِهِ الرَّحْمَةَ ۖ أَنَّهُ مَنْ عَمِلَ مِنكُمْ سُوءًا بِجَهَالَةٍ ثُمَّ تَابَ مِن بَعْدِهِ وَأَصْلَحَ فَأَنَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

እንግዲህ ኢሕሳን የዲን ሦስተኛው ደረጃ ሲሆን መልካም ሥራ በኢማንና በተውሒድ ከተሰራ አላህ "ሙሒሢን" የሚላቸው ባሮቹ እንሆናለን፦
2፥195 በአላህም መንገድ ለግሱ፡፡ በእጆቻችሁም እራሳችሁን ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡ *በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና*፡፡ وَأَنفِقُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةِ ۛ وَأَحْسِنُوا ۛ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ

አላህ ሙሕሢኒን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም

የሰለምቴዎች ቻናል

22 Oct, 21:24


ነዚያ በስሕተት መጥፎን ለሠሩና ከዚያም ከዚህ በኋላ ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው*፡፡ ثُمَّ إِنَّ رَبَّكَ لِلَّذِينَ عَمِلُوا السُّوءَ بِجَهَالَةٍ ثُمَّ تَابُوا مِن بَعْدِ ذَٰلِكَ وَأَصْلَحُوا إِنَّ رَبَّكَ مِن بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ
27፥11 «ግን *የበደለ ሰው ከዚያም ከመጥፎ ሥራው በኋላ መልካምን የለወጠ እኔ መሓሪ አዛኝ ነኝ*፡፡ إِلَّا مَن ظَلَمَ ثُمَّ بَدَّلَ حُسْنًا بَعْدَ سُوءٍ فَإِنِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
4፥40 *አላህ የብናኝን ክብደት ያህል አይበድልም፡፡ መልካም ሥራ ብትኾንም ይደራርባታል፡፡ ከእርሱም ዘንድ ታላቅን ምንዳ ይሰጣል*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ ۖ وَإِن تَكُ حَسَنَةً يُضَاعِفْهَا وَيُؤْتِ مِن لَّدُنْهُ أَجْرًا عَظِيمًا
29፥7 *እነዚያም ያመኑ፤ መልካሞችንም የሠሩ መጥፎዎቹን ሥራዎቻቸውን ከእነሱ ላይ እናብስላቸዋለን፡፡ በዚያም ይሠሩት በነበሩት መልካም ሥራ በእርግጥ እንመነዳቸዋለን*፡፡وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَنُكَفِّرَنَّ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَحْسَنَ الَّذِي كَانُوا يَعْمَلُونَ
6፥160 *በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት*፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

ነገር ግን "ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ" ይዘው በሚሠሩት መጥፎ ሥራ ተውበት ካላደረጉ ብጤዋን እንጅ አይመነዱም፤ በመጥፎም የመጡ ሰዎች ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ ይደፋሉ፤ በክፉም ሥራ የመጡ ሰዎች እነዚህ መጥፎዎችን የሠሩ ይሠሩት የነበሩትን እንጅ አይመነዱም፤ ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ተያዥ ናት፦
27፥90 *በመጥፎም የመጡ ሰዎች ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ ይደፋሉ፡፡ «ትሠሩት የነበራችሁትን እንጅ አትመነዱም?»* ይባላሉ፡፡ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَكُبَّتْ وُجُوهُهُمْ فِي النَّارِ هَلْ تُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
29፥4 *ይልቁንም እነዚያ መጥፎዎችን ሥራዎች የሚሠሩት ሊያመልጡን ይጠረጥራሉን?* ያ የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ፡፡ أَمْ حَسِبَ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ السَّيِّئَاتِ أَن يَسْبِقُونَا ۚ سَاءَ مَا يَحْكُمُونَ
28፥84 *በደግ ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ከእርሷ በላጭ ምንዳ አለው፡፡ በክፉም ሥራ የመጡ ሰዎች እነዚህ መጥፎዎችን የሠሩ ይሠሩት የነበሩትን እንጅ አይመነዱም*፡፡ مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ خَيْرٌ مِّنْهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَى الَّذِينَ عَمِلُوا السَّيِّئَاتِ إِلَّا مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
74፥38 *ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ተያዥ ናት*፡፡ كُلُّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ رَهِينَة

ለአማንያን ሥራዎቻቸው የሚመዘንበት ሚዛን ያላቸው ለዛ ነው፤ ከሃድያን ግን የጀነት ስላልሆኑ ሥራዎቻቸው የሚመዘንበት ሚዛን የላቸውም። አማንያን "ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ" በመያዛቸው በሠሩት መጥፎ ሥራ ልክ ተቀጥተው የጀነት ናቸው፤ ከሃድያን ደግሞ በመካዳቸው ጀሃነም ሲዘወትሩ በሚሠሩት መጥፎ ሥራ እንደሥራቸው ያገኛሉ፦
41፥27 *እነዚያንም የካዱትን ብርቱን ቅጣት እናቀምሳቸዋለን፡፡ የእዚያነም ይሠሩት የነበሩትን መጥፎውን ፍዳ በእርግጥ እንመነዳቸዋለን*፡፡ فَلَنُذِيقَنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا عَذَابًا شَدِيدًا وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَسْوَأَ الَّذِي كَانُوا يَعْمَلُونَ

የሰለምቴዎች ቻናል

22 Oct, 21:24


መልካምና መጥፎ ሥራ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

53፥39 *ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም*፡፡ وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَٰنِ إِلَّا مَا سَعَىٰ

ነጥብ ሁለት
"አኺራህ"
"አኺራህ" آخِرة ማለት "መጨረሻይቱ" ማለት ሲሆን የሚቀጥለውን ዓለም ያመለክታል፤ አምላካችን አላህ በትንሣኤም ቀን ትክክለኛ ሚዛኖችን ያቆማል፤ ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም፤ ሥራው የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ቢኾንም አላህ ያመጣዋል፦
21፥47 *በትንሣኤም ቀን ትክክለኛ ሚዛኖችን እናቆማለን፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም፡፡ ሥራው የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ቢኾንም እርሷን እናመጣታለን*፡፡ ተቆጣጣሪዎችም በኛ በቃ፡፡ وَنَضَعُ الْمَوَازِينَ الْقِسْطَ لِيَوْمِ الْقِيَامَةِ فَلَا تُظْلَمُ نَفْسٌ شَيْئًا ۖ وَإِن كَانَ مِثْقَالَ حَبَّةٍ مِّنْ خَرْدَلٍ أَتَيْنَا بِهَا ۗ وَكَفَىٰ بِنَا حَاسِبِينَ

እነዚያም ያመኑት መልካም ሥራዎችንም የሠሩት በመደሰቻ ገነቶች ውስጥ ይገባሉ፤ የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ለእነዚያ ላመኑትና ይጠነቀቁ ለነበሩት የበለጠ ነው፦
22፥56 በዚያ ቀን ንግሥናው የአላህ ብቻ ነው፡፡ በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡ *እነዚያም ያመኑት መልካም ሥራዎችንም የሠሩት በመደሰቻ ገነቶች ውስጥ ናቸው*፡፡ الْمُلْكُ يَوْمَئِذٍ لِّلَّهِ يَحْكُمُ بَيْنَهُمْ ۚ فَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فِي جَنَّاتِ النَّعِيمِ
12፥57 *የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ለእነዚያ ላመኑትና ይጠነቀቁ ለነበሩት የበለጠ ነው*፡፡ وَلَأَجْرُ الْآخِرَةِ خَيْرٌ لِّلَّذِينَ آمَنُوا وَكَانُوا يَتَّقُونَ

አማንያን በዚያ ቀን ለሁሉም ከሠሩት መልካም ሥራ የተለያየ የምንዳ ደረጃዎች አሏቸው፦
46፥19 *ለሁሉም ከሠሩት ሥራ ደረጃዎች አሏቸው፡፡ ሥራዎቻቸውንም ይሞላላቸው ዘንድ ይህንን መነዳቸው እነርሱም አይበደሉም*፡፡ وَلِكُلٍّ دَرَجَاتٌ مِّمَّا عَمِلُوا ۖ وَلِيُوَفِّيَهُمْ أَعْمَالَهُمْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ
6፥132 *ለሁሉም ከሠሩት ሥራ የተበላለጡ ደረጃዎች አሏቸው*፡፡ ጌታህም ከሚሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ وَلِكُلٍّ دَرَجَاتٌ مِّمَّا عَمِلُوا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا يَعْمَلُونَ

"መልካም ሥራ" ሁሉ አምልኮ ነው፤ “ዒባዳህ” عِبَادَة ማለትም “አምልኮ” አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢቲባዕ ናቸው።
“ኢማን” إِيمَٰن ማለት “እምነት” ሲሆን ያለ ኢማን ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም።
“ኢኽላስ” إخلاص ማለት ደግሞ ከእዩልይና ስሙልኝ እና ከሙገሳና ወቀሳ ነጻ ሆኖ ለአላህ ውዴታ ተብሎ የሚነየት መተናነስ፣ ማጎብደድ፣ ማሸርገድ እና ማጥራት ሲሆን ያለ ኢኽላስ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም።
ሦስተኛው “ኢቲባዕ” إتباع ነው፤ “ኢቲባዕ” የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ “ተከተለ” ከሚለው የመጣ ሲሆን “መከተል” ማለት ሲሆን ቁርኣንና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ሑክም ማምለክ ነው፤ ያለ ኢቲባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም።

የከሃድያን መልካም ሥራ ያለ እነዚህ ሦስት መስፈርት በዲንያ የሚያከትም ሲሆን በትንሣኤ ቀን መልካም ሥራቸው የሚመዘንበት ሚዛንን አይቆምላቸውም፤ ይሠሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው፤ አይጠቅማቸውም፦
18፥104 *እነዚያ እነርሱ ሥራን የሚያሳምሩ የሚመስላቸው ሲሆኑ በቅርቢቱ ሕይወት ሥራቸው የጠፋባቸው ናቸው*፡፡ الَّذِينَ ضَلَّ سَعْيُهُمْ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَهُمْ يَحْسَبُونَ أَنَّهُمْ يُحْسِنُونَ صُنْعًا
18፥105 *እነዚያ እነርሱ በጌታቸው ማስረጃዎችና በመገናኘቱ የካዱት ናቸው፡፡ ሥራዎቻቸውም ተበላሹ፡፡ ለእነሱም በትንሣኤ ቀን ሚዛንን አናቆምላቸውም*፡፡ أُولَـٰئِكَ الَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِ رَبِّهِمْ وَلِقَائِهِ فَحَبِطَتْ أَعْمَالُهُمْ فَلَا نُقِيمُ لَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَزْنًا
11፥16 *እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ ከእሳት በቀር የሌላቸው ናቸው፡፡ የሠሩትም ሥራ በእርሷ ውስጥ ተበላሸ፤ ይሠሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው*፡፡ أُولَـٰئِكَ الَّذِينَ لَيْسَ لَهُمْ فِي الْآخِرَةِ إِلَّا النَّارُ ۖ وَحَبِطَ مَا صَنَعُوا فِيهَا وَبَاطِلٌ مَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ

የእነርሱ መልካም ሥራ ያለ እምነት ስለሆነ በበረሃ ሜዳ እንዳለ ሲሪብዱ የጠማው ሰው ውሃ ነው ብሎ እንደሚያስበው በመጣውም ጊዜ ምንም ነገር ኾኖ እንደማያገኘው ነው፤ አላህ የተበተነ ትቢያም ያደርገዋል፤ በሠሩት ሥራ በምንም ላይ ሊጠቀሙ አይችሉም፦
24፥39 *እነዚያም የካዱት ሰዎች መልካም ሥራዎቻቸው በበረሃ ሜዳ እንዳለ ሲሪብዱ የጠማው ሰው ውሃ ነው ብሎ እንደሚያስበው በመጣውም ጊዜ ምንም ነገር ኾኖ እንደማያገኘው ነው*፡፡ وَالَّذِينَ كَفَرُوا أَعْمَالُهُمْ كَسَرَابٍ بِقِيعَةٍ يَحْسَبُهُ الظَّمْآنُ مَاءً حَتَّىٰ إِذَا جَاءَهُ لَمْ يَجِدْهُ شَيْئًا وَوَجَدَ اللَّهَ عِندَهُ فَوَفَّاهُ حِسَابَهُ ۗ وَاللَّهُ سَرِيعُ الْحِسَابِ
25፥23 *ከሥራም ወደ ሠሩት እናስባለን፡፡ የተበተነ ትቢያም እናደርገዋለን*፡፡ وَقَدِمْنَا إِلَىٰ مَا عَمِلُوا مِنْ عَمَلٍ فَجَعَلْنَاهُ هَبَاءً مَّنثُورًا
14፥18 *የእነዚያ በጌታቸው የካዱት ሰዎች ምሳሌ መልካም ሥራዎቻቸው በነፋሻ ቀን ነፋስ በእርሱ እንደ በረታችበት አመድ ነው፡፡ በሠሩት ሥራ በምንም ላይ ሊጠቀሙ አይችሉም፡፡ ይህ እርሱ ሩቅ ጥፋት ነው*፡፡ مَّثَلُ الَّذِينَ كَفَرُوا بِرَبِّهِمْ ۖ أَعْمَالُهُمْ كَرَمَادٍ اشْتَدَّتْ بِهِ الرِّيحُ فِي يَوْمٍ عَاصِفٍ ۖ لَّا يَقْدِرُونَ مِمَّا كَسَبُوا عَلَىٰ شَيْءٍ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الضَّلَالُ الْبَعِيدُ

"ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ" لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ ማለትም "ከአሏህ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ብሎ ጣዖታትን ውድቅ አድርጎ እና አንዱን አምላክ አላህ በብቸኝነት ያመለከ ሰው ለሠራው መጥፎ ሥራ ተውበት ከገባ አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጥለታል፤ ተጸጽቶ በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ ይደራረብለታል፦
25፥70 *ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው*፡፡ إِلَّا مَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صَالِحًا فَأُولَـٰئِكَ يُبَدِّلُ اللَّهُ سَيِّئَاتِهِمْ حَسَنَاتٍ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
16፥119 ከዚያም ጌታህ *ለእ

የሰለምቴዎች ቻናል

21 Oct, 18:49


ነጥብ አንድ
“ዱንያ”
“ዱንያ” دُّنْيَا ማለት “ቅርቢቱ” ማለት ሲሆን የምንኖርበት ይህንን ዓለም ያመለክታል፤ አምላካችን አላህ የትኛችን ሥራችን ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊፈትነንና ነፍስም ሁሉ በሠራችው ሥራ ትመነዳ ዘንድ ሞትንና ሕይወትን በዱንያ የፈጠረ ነው፦
67፥2 *ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊፈትናችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው*፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡ الَّذِي خَلَقَ الْمَوْتَ وَالْحَيَاةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْغَفُورُ
45፥22 አላህም ሰማያትንና ምድርን ለችሎታው እንደሚያመለክትባቸውና *ነፍስም ሁሉ በሠራችው ሥራ ትምመነዳ ዘንድ በትክክል ፈጠረ፡፡ እነርሱም አይበደሉም*፡፡ وَخَلَقَ اللَّهُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ وَلِتُجْزَىٰ كُلُّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

አንድ አማኝ በእምነት የሚሰራው መልካም ሥራ አላህ በዱንያ መልካም ኑሮን ይመነዳዋል፤ መልካምም ያደርግለታል፦
16፥97 *ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን*፡፡ مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً ۖ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
28፥77 «አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ፡፡ *ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታህን አትርሳ፡፡ አላህም ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ ለሰዎች መልካምን አድርግ*፡፡ በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ፡፡ አላህ አጥፊዎችን አይወድምና» አሉት፡፡ وَابْتَغِ فِيمَا آتَاكَ اللَّهُ الدَّارَ الْآخِرَةَ ۖ وَلَا تَنسَ نَصِيبَكَ مِنَ الدُّنْيَا ۖ وَأَحْسِن كَمَا أَحْسَنَ اللَّهُ إِلَيْكَ ۖ وَلَا تَبْغِ الْفَسَادَ فِي الْأَرْضِ ۖ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُفْسِدِينَ
3፥145 ለማንኛይቱም ነፍስ በአላህ ፍርድ ቢኾን እንጅ ልትሞት አይገባትም፡፡ ጊዜውም ተወስኖ ተጽፏል፡፡ *የቅርቢቱንም ምንዳ የሚፈልግ ሰው ከእርስዋ እንሰጠዋለን፡፡ የመጨረሻይቱንም ምንዳ የሚፈልግ ሰው ከእርስዋ እንሰጠዋለን፤ አመስጋኞችንም በእርግጥ እንመነዳለን*፡፡ وَمَا كَانَ لِنَفْسٍ أَن تَمُوتَ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ كِتَابًا مُّؤَجَّلًا ۗ وَمَن يُرِدْ ثَوَابَ الدُّنْيَا نُؤْتِهِ مِنْهَا وَمَن يُرِدْ ثَوَابَ الْآخِرَةِ نُؤْتِهِ مِنْهَا ۚ وَسَنَجْزِي الشَّاكِرِينَ
16፥30 ለእነዚያም ለተጠነቀቁት «ጌታችሁ ምንን ነገር አወረደ» ተባሉ፡፡ «መልካምን ነገር» አሉ፡፡ *ለእነዚያ ደግ ለሠሩት በዚች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ኑሮ አላቸው*፡፡ የመጨረሻይቱም አገር በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ የጥንቁቆቹም አገር ምን ታምር! وَقِيلَ لِلَّذِينَ اتَّقَوْا مَاذَا أَنزَلَ رَبُّكُمْ ۚ قَالُوا خَيْرًا ۗ لِّلَّذِينَ أَحْسَنُوا فِي هَـٰذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةٌ ۚ وَلَدَارُ الْآخِرَةِ خَيْرٌ ۚ وَلَنِعْمَ دَارُ الْمُتَّقِينَ
39፥10 «እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ለእነዚያ *በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ለሠሩት መልካም ምንዳ አላቸው*፡፡ قُلْ يَا عِبَادِ الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا رَبَّكُمْ ۚ لِلَّذِينَ أَحْسَنُوا فِي هَـٰذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةٌ ۗ وَأَرْضُ اللَّهِ وَاسِعَةٌ ۗ إِنَّمَا يُوَفَّى الصَّابِرُونَ أَجْرَهُم بِغَيْرِ حِسَابٍ

በተመሳሳይ አንድ ካሃዲ ያለ እምነት የሚሰራው መልካም ሥራ አላህ በዱንያ ይሞላለታል፤ ምክንያቱም የመልካም ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ አይደለም፤ የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፦
11፥15 *ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሰዎች ሥራዎቻቸውን በእርሷ ውስጥ ወደ እነርሱ እንሞላላቸዋለን፡፡ እነርሱም በእርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸውም*። مَن كَانَ يُرِيدُ ٱلْحَيَوٰةَ ٱلدُّنْيَا وَزِينَتَهَا نُوَفِّ إِلَيْهِمْ أَعْمَٰلَهُمْ فِيهَا وَهُمْ فِيهَا لَا يُبْخَسُونَ
55፥60 *የመልካም ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን?* هَلْ جَزَاءُ الْإِحْسَانِ إِلَّا الْإِحْسَانُ
99፥7 *የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል*፡፡ فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ

የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ አማኝም ይሁን ከሃዲ በዱንያ ያገኘዋል፦
99፥8 *የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል*፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ

ነገር ግን ሁልጊዜ አማኝ በሚሰራው መልካም ሥራ በዱንያ አሊያም ከሃዲ በሚሰራው መጥፎ ሥራ በዱንያ ያገኛል ማለት ላይሆን ይችላል፤ ፍትሕ የሚዳኝበት እውነተኛ ምንዳ በመጨረሻይቱ ዓለም ነው። ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ስለ አኺራህ እንቀጥላልን……..

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም

የሰለምቴዎች ቻናል

21 Oct, 18:49


መልካምና መጥፎ ሥራ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

53፥39 *ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም*፡፡ وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَٰنِ إِلَّا مَا سَعَىٰ

መግቢያ
በኢስላም “ነገረ-ደህንነት”Soteriology” እራሱን የቻለ ትልቅ ነጥብ ሲሆን “ፈላህ” فلاح ይባላል፤ አምላካችን አላህ አንድ ሰው ከጀሃነም ለመዳን ከፈለገ አራት መስፈርቶችን አስቀምጦልናል፤ እነርሱም፦ 1ኛ “ተውበት” تَوْبَة ማለትም “ንስሃ” 2ኛ “ኢማን” إِيمَٰن ማለትም “እምነት” 3ኛ “ዐሚሉስ ሷሊሐት” عَمِلُوا الصَّالِحَات ማለትም “መልካም ስራ” 4ኛ “ኢስቲቃማ” استقامة ሰው በንስሃ ቃል በገባበት፣ ባመነበትና በሚሰራው መልካም ስራ “መፅናት” ናቸው።

ዲን የፈላህ ግብና አላማ፣ ፋይዳና ሚና ነው፤ “ዲን” دِين ማለት ደግሞ “ሃይማኖት” “ፍትህ” “ፍርድ” “ሕግ” “መርህ” ማለት ነው፤ “ዲን” ደግሞ ሦስት ደረጃ አሉት፦ “ኢሥላም” إِسْلَٰم ፣ “ኢማን” إِيمَٰن እና “ኢሕሣን” إِحْسَٰن ናቸው፤ “ኢሥላም” ማለት “አንዱን አምላክ ብቻ ማምለክ” ሲሆን “ኢማን” ማለት ግን “እምነት” ማለት ነው፤ “ኢሕሣን” ማለት “አላህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፤ አሊያም አላህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ ነው።

“ኢሕሣን” إِحْسَٰن ማለት ቋንቋዊ ፍቺው “መዋብ” “ማማር” “መልካም” “በጎ” “ጥሩ” ማለት ነው፤ ለምሳሌ “ሐሠን” حَسَن ማለት “መልካም” “ውብ” ማለት ሲሆን “ሑሥን” حُسْن ማለት ደግሞ “የተዋበ” “መልካም” “ያማረ” ማለት ነው፤ አንድ ሰው በኢስላም “ሙሥሊም” مُسْلِم ሲባል፣ በኢማን “ሙእሚን” مُؤْمِن ሲባል፣ በኢሕሣን ደግሞ “ሙሕሢን” مُحْسِن ይባላል፤ “ሙሕሢን” مُحْسِن ማለት “ጥሩ ሠሪዎች” “መልካም ሠሪዎች” “በጎ ሠሪዎች” ማለት ነው፤ የዲን መዋቢያውና ማሳመሪያው “መልካም ሥራ” ነው፤ አንድ ሥራ መልካም ወይም መጥፎ ማለት የሚችለው አላህ ብቻ ነው፤ ነፍስያህ ለእኛ መልካም የሆነን ነገር ትጠላለች መጥፎ የሆነን ነገር ትወዳለች፤ የሚሻለውን ነገር አላህ ያውቃል እኛ ዐናውቅም፤ ሰው መልካምን ነገር እንደሚለምን ሁሉ፤ መጥፎንም ነገር ይለምናል፦
2፥126 *አንዳች ነገርን እርሱ ለእናንተ የበለጠ ሲሆን የምትጠሉት መኾናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አንዳችንም ነገር እርሱ ለእናንተ መጥፎ ሲሆን የምትወዱት መሆናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አላህም የሚሻላችሁን ያውቃል ግን እናንተ አታውቁም*፡፡ كُتِبَ عَلَيْكُمُ الْقِتَالُ وَهُوَ كُرْهٌ لَّكُمْ ۖ وَعَسَىٰ أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ ۖ وَعَسَىٰ أَن تُحِبُّوا شَيْئًا وَهُوَ شَرٌّ لَّكُمْ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
17፥11 *ሰው መልካምን ነገር እንደሚለምን ሁሉ፤ መጥፎንም ነገር ይለምናል፡፡ ሰውም ቸኳላ ነው*፡፡ وَيَدْعُ الْإِنسَانُ بِالشَّرِّ دُعَاءَهُ بِالْخَيْرِ ۖ وَكَانَ الْإِنسَانُ عَجُولًا

ለምሳሌ አንድ ሰው ቢገድል ያ ገዳዩ መገደሉ ፍትሕ ቢሆንም ለሰው የተጠላ ሊመስለው ይችላል፤ ነገር ግን የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ መሆኗ ፍትሕ ነው፦
42፥40 *የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው፡፡ እርሱ በደለኞችን አይወድም*፡፡ وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا ۖ فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الظَّالِمِينَ

የሥነ-ምግባር መርህ ላይ፦ “ይህ ነገር እኩይ ነው፤ ይህ ነገር ሰናይ ነው” ማለት የሚችለው የዓለማቱ ጌታ አላህ ብቻ ነው፤ ያ ካልሆነ ነፍስ ሁሉ አላህ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና፦
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ

አላህ በነቢያቱ መልካም ነገር ያዛል፤ በተቃራኒው ሸይጧን በውስዋስ መጥፎ ነገር ያዛል፦
7፥28 መጥፎንም ሥራ በሠሩ ጊዜ በእርሷ ላይ አባቶቻችንን አገኘን አላህም በእርሷ አዞናል ይላሉ፡፡ *«አላህ በመጥፎ ነገር አያዝም*፡፡ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን» በላቸው፡፡ وَإِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً قَالُوا وَجَدْنَا عَلَيْهَا آبَاءَنَا وَاللَّهُ أَمَرَنَا بِهَا ۗ قُلْ إِنَّ اللَّهَ لَا يَأْمُرُ بِالْفَحْشَاءِ ۖ أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
23፥51 እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ፡፡ *በጎ ሥራንም ሥሩ፤ እኔ የምትሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ*፡፡ يَا أَيُّهَا الرُّسُلُ كُلُوا مِنَ الطَّيِّبَاتِ وَاعْمَلُوا صَالِحًا ۖ إِنِّي بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ
2፥268 *ሰይጣን እንዳትለግሱ ድኽነትን ያስፈራራችኋል፡፡ በመጥፎም ያዛችኋል*፡፡ الشَّيْطَانُ يَعِدُكُمُ الْفَقْرَ وَيَأْمُرُكُم بِالْفَحْشَاءِ
24፥21 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *የሰይጣንን እርምጃዎች አትከተሉ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች የሚከተል ሰው ኀጢአትን ተሸከመ፡፡ እርሱ በመጥፎና በሚጠላ ነገር ያዛልና*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ وَمَن يَتَّبِعْ خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ فَإِنَّهُ يَأْمُرُ بِالْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ

እዚህ ድረስ ከተግባባን መልካም ሥራ እና መጥፎ ሥራ በዱንያ ሆነ በአኺራህ የሚኖረውን አዎንታዊ እና አሉታዊ ምንዳ ነጥብ በነጥብ ኢንሻላህ እንመለከታለን፦

የሰለምቴዎች ቻናል

21 Oct, 17:59


ግቡ ኡስታዝ ወሒድ ገብቷል

የሰለምቴዎች ቻናል

21 Oct, 08:50


ግቡ ኡስታዝ ወሒድ ገብቷል

የሰለምቴዎች ቻናል

20 Oct, 22:54


ነገ ሰኞ ነው ጹሙ ቤተሰብ

የሰለምቴዎች ቻናል

20 Oct, 22:54


ሱረቱል ዩውሱፍ📖🎧

إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

እኛ (ፍቹን) ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው፡፡

◍ ወንድም ጧሪቅ
◍ ወንድም ቶፊቅ
◍ ወንድም ሙዓዝ

የሰለምቴዎች ቻናል

20 Oct, 22:54


◆▮ውይይት▮◆

"አምላኩን የማያውቅ ነብይ?እራሱ ነብይ እንደሆነ የማያውቅ ነብይ  ?ገነት በባይብል እና በቁርአን ? ሌሎችም ጥያቄች የተካተቱበት ውይይት"

◍ ኡስታዝ ወሒድ
◍ ወንድም ዒምራን
◍ ወንድም አሕመድ
         🅥🅢
◍ወገናችን ሚስተር
◍ወገናችን ኤቢ
ሌሎችም  ወገኖች ጋር

የሰለምቴዎች ቻናል

20 Oct, 19:40


በተጨማሪም ኢብኑ ከሲር ነብዩላህ ዩኑስ የተላከው ለነነዌ ሰዎች እንደሆነ የነነዌ ሰዎች ደግሞ መውሲል እንደሆኑ ይናገራል፤ መውሲል ያሁኑ ሰሜናዊ ኢራቅ እንደሆነ የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ፤ ኢብኑ ሳድ በኪታቡ ዩኑስ ከቤተ-እስራኤል እንደሆነ ይተርካል፣ ታዲያ ህዝብ ማለት የትውልድ የዘር ሃረግ ቢሆን ኖሮ አላህ የነነዌ ሰዎችን የዩኑስ ህዝብ ብሎ ባልተናገረ ነበር፦
10:98 *”የዩኑስ ሕዝቦች” َ “ባመኑ ጊዜ” በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ከእነሱ ላይ አነሳንላቸው፡፡ “እስከ ጊዜም ድረስ አጣቀምናቸው”*፡፡ فَلَوْلَا كَانَتْ قَرْيَةٌ ءَامَنَتْ فَنَفَعَهَآ إِيمَٰنُهَآ إِلَّا قَوْمَ يُونُسَ لَمَّآ ءَامَنُوا۟ كَشَفْنَا عَنْهُمْ عَذَابَ ٱلْخِزْىِ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَمَتَّعْنَٰهُمْ إِلَىٰ حِينٍۢ
37:147 *ወደ መቶ ሺሕ ሰዎችም “ላክነው”፡፡ ከቶውንም ይጨምራሉ፡፡ “አመኑም”፡፡ “እስከ ጊዜ ድረስም አጣቀምናቸው”*፡፡ وَأَرْسَلْنَٰهُ إِلَىٰ مِا۟ئَةِ أَلْفٍ أَوْ يَزِيدُونَ فَـَٔامَنُوا۟ فَمَتَّعْنَٰهُمْ إِلَىٰ حِينٍۢ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም

የሰለምቴዎች ቻናል

20 Oct, 19:40


ቋንቋ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

55፥3-4 ሰውን ፈጠረ፡፡ *መናገርን አስተማረው*፡፡ خَلَقَ ٱلْإِنسَٰنَ عَلَّمَهُ ٱلْبَيَانَ

መወለድ፣”መሞት፣መብላት፣ መጠጣት፣ ያ የተበላውንና የተጠጣውን ነገር በሌላ መልኩ ከሰውነት ማስወገድ፣ መተኛት፣ ከተቃራኒ ጥንድ ጋር ተራክቦ ማድረግ ሰው ከእንስሳ የሚጋራበት ተፈጥሮ ነው፤ ነገር ግን ሰው ከእንስሳ፣ ከእጽዋት፣ ከማዕድናት በተፈጥሮ ይልቃል፤ አላህ ሰውን ከሌላው ፍጡር አክብሮታል፤ ከፈጠረውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አብልጦታል፦
17፥70 *የአደምንም ልጆች በእርግጥ ከሌላው ፍጡር አከበርናቸው*፡፡ በየብስ እና በባህርም አሳፈርናቸው፡፡ ከመልካሞችም ሲሳዮች ሰጠናቸው፡፡ *ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው*፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِىٓ ءَادَمَ وَحَمَلْنَٰهُمْ فِى ٱلْبَرِّ وَٱلْبَحْرِ وَرَزَقْنَٰهُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَفَضَّلْنَٰهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍۢ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًۭا

አላህ የአደምንም ልጆች ከሌላው ፍጡር ያከበረበት እና ያበለጠበት በሁለት ነገር ነው፤ አንደኛው ዐቅል በመስጠት ነው፤ ዐቅል” عَقل ማለት “ግንዛቤ”Metacognition” ማለት ነው፤ የሰው ልጅ “አዕምሮ” እራሱ “ዐቅል” ይባላል፤ ዐቅል የጥበብ ተውህቦ”faculty” ነው፤ አላህ አደምን ስሞችን ሁሏንም አስተማረው፤ ሰው ያላወቀውን ሁሉ አሳውቆታል፦
2፥31 *አደምንም ስሞችን ሁሏንም አስተማረው*፡፡ ከዚያም በመላእክት ላይ ተጠሪዎቹን አቀረባቸው፡፡ «እውነተኞችም እንደኾናችሁ የእነዚህን ተጠሪዎች ስሞች ንገሩኝ» አላቸው፡፡ وَعَلَّمَ ءَادَمَ ٱلْأَسْمَآءَ كُلَّهَا ثُمَّ عَرَضَهُمْ عَلَى ٱلْمَلَٰٓئِكَةِ فَقَالَ أَنۢبِـُٔونِى بِأَسْمَآءِ هَٰٓؤُلَآءِ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
96፥4-5 ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡ *ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን*፡፡ ٱلَّذِى عَلَّمَ بِٱلْقَلَمِ عَلَّمَ ٱلْإِنسَٰنَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

ሁለተኛው ቀውል በመስጠት ነው፤ “ቀውል” قَوْل ማለት “አንደበት”articulate speech” ማለት ነው፤ ሰው ስሜቱንና ሃሳቡን የሚገልፅበት ቋንቋ ነው፤ ሰውን መናገር ያስተማረው አላህ ነው፦
55፥3-4 ሰውን ፈጠረ፡፡ *መናገርን አስተማረው*፡፡ خَلَقَ ٱلْإِنسَٰنَ عَلَّمَهُ ٱلْبَيَانَ

የሥነ-ቋንቋ ጥናት”Linguistics” ምሁራን እንደሚያትቱት የሰው ልጆች የጋራ የሆነ ሰዋስው”grammar” አላቸው፤ በዚህ አንዱ የሌላውን ቋንቋን በመልመድ ይግባባል፤ ሁሉም ቋንቋ ውስጥ ጋር ስም፣ ተውላጠ-ስም፣ ግስ፣ ተውሳከ-ግስ፣ ገላጭ፣ መስተጻምር፣ መስተዋድድ እና ቃል-አጋኖ አለ።
በዓለማችን ላይ ከአምስት ሺ እስከ ስምንት ሺ ቋንቋዎች አሉ፤ እነዚህ ቋንቋዎች የመጡበት የራሳቸው ቤተሰብ አላቸው፤ አፍሮ-አሲያቲክ፣ ኢንዶ-ኢሮፒያን፣ ናይሎ-ሰሃራን፣ አዩስትሮ-አሲያቲክ ወዘተ ይባላሉ። አፍሮ-አሲያቲክ ቤተሰብ ውስጥ ሴሚቲክ፣ ኦሞቲክ፣ ኩሸቲክ፣ ቻዲክ ወዘተ ናቸው። የሴሜቲክ ዝርያ ውስጥ ዐረማይክ፣ ዕብራይስጥ፣ ዐረቢኛ፣ ግዕዝ፣ ዓካድ ወዘተ ናቸው። ወደድንም ጠላን እነዚህ ሁሉ ቋንቋዎች መሰረታቸው አንድ ቋንቋ ነው፤ ለምሳሌ በዐረቢኛ “አሊፍ” ا በዐረማይክ “አሊፍ” ܐ በዕብራይስጥ “አሌፍ” א በግሪክ “አልፋ” Άλφα ነው፤ በዐረቢኛ “ባ” ب በዐረማይክ “ባ” ܒ በዕብራይስጥ “ቤት” ב በግሪክ “ቤታ” βῆτα ነው፤ ይህ መመሳሰል ቋንቋዎች መሰረታቸው አንድ ቋንቋ መሆኑን ያሳያል፤ እያንዳንዱ ፊደላት ትርጉሙ በሁሉም አንድ ነው፤ ለምሳሌ “አሌፍ” ማለት “መጀመሪያ” ወይም “በሬ” ማለት ነው፤ “ባ” ማለት “ቤት” ማለት ነው፤ “ጂም” ማለት “ግመል” ማለት ነው። ይህንን በሌሎች ቋንቋዎች ተመሳሳይ ትርጉም አለው።

ይህ የመጀመሪያው የአደም ቋንቋ ማን ነው? የሚለው ብዙ መላምት ቢኖርም፤ አብላጫውን የቋንቋ ምሁራን መላምት ዐረማይክ የሚል መረጃ ነው ያለው፤ ለማንኛውም የቋንቋዎቻችን መለያየት ከአላህ አስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት፦
30፥22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ *የቋንቋዎቻችሁና የመልኮቻችሁም መለያየት፣ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው*፡፡ በዚህ ውስጥ *ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት*፡፡ وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦ خَلْقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱخْتِلَٰفُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَٰنِكُمْ ۚ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍۢ لِّلْعَٰلِمِينَ

አላህ ነብያትን ሲልክ በወቅቱ የተወለዱበት ማህበረሰብ ሊግባቡበት በሚችል ቋንቋ ነው፦
14፥4 ከመልክተኛ ማንኛውንም ለእነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ *በህዝቦቹ ቋንቋ እንጂ በሌላ አልላክንም*፡፡ ﻭَﻣَﺂ ﺃَﺭْﺳَﻠْﻨَﺎ ﻣِﻦ ﺭَّﺳُﻮﻝٍ ﺇِﻟَّﺎ ﺑِﻠِﺴَﺎﻥِ ﻗَﻮْﻣِﻪِۦ ﻟِﻴُﺒَﻴِّﻦَ ﻟَﻬُﻢْ ۖ ﻓَﻴُﻀِﻞُّ ﭐﻟﻠَّﻪُ ﻣَﻦ ﻳَﺸَﺂﺀُ ﻭَﻳَﻬْﺪِﻯ ﻣَﻦ ﻳَﺸَﺂﺀُ ۚ ﻭَﻫُﻮَ ﭐﻟْﻌَﺰِﻳﺰُ ﭐﻟْﺤَﻜِﻴﻢُ

“ቀውም” قَوْم “ህዝብ” በአንድ አካባቢ ተመሳሳይ ባህል፣ ቋንቋ፣ አኗኗር፣ ታሪክ፣ መንግሥት እና ቦታ ያለው ማህበረሰብን ያመለክታል፣ ሙሳ ነብይ ሆኖ በተነሳበት ዘመን አላህ ሙሳን ወደ ህዝቦቹ “በታምራታት” እንደላከው እነዚያም ህዝቦች “ፈሮዖንና ሹማምንቶቹ” የሚጠቀልል መሆኑን ለማመልከት “ወደ ፈሮዖንና ወደ ሹማምንቶቹ በእርግጥ ላክን” በማለት ይናገራል፦
14:5 ሙሳንም፤ “ሕዝቦችሀን” ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አውጣ፤ የአላህንም ቀኖች አስገንዝባቸው፤ በማለት *”በታምራታችን” በእርግጥ “ላክነው”*፤ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ أَنْ أَخْرِجْ قَوْمَكَ مِنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ وَذَكِّرْهُم بِأَيَّىٰمِ ٱللَّهِ
43:46 ሙሳንም *”በታምራቶቻችን” ወደ ፈሮዖንና ወደ ሹማምንቶቹ በእርግጥ “ላክን”*፤ እኔ የአለማት ጌታ መልክተኛ ነኝ አላቸውም። وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَإِي۟هِۦ فَقَالَ إِنِّى رَسُولُ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

የሰለምቴዎች ቻናል

20 Oct, 13:54


ሁላችሁም እንዳትቀሩ አብዱል ከሪም ቤት ፕሮግራም አለ

https://www.tiktok.com/@abdulkerim1100?_t=8qhcDJjyC8O&_r=1

3,862

subscribers

960

photos

1,300

videos