ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

@mogesabreham123


<<በተለያዩ ርዕሰ ጎዳዩች ላይ የሚሰጡ የስነ ልቦና ትምህርቶች( Psychology Lessons)እንዲሁም ጠቃሚ ምክሮች (Tips) ማህበረሰባዊ ፍልስፍናዋች( Social philosophies) የሚቀርቡበት ቻናል ነው>>ሞገስ አብረሀም

https://t.me/joinchat/AAAAAFNFGBxM7CRSIEwftg


@Mogesabreham

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 16:14


........
✍️ትኩረት የማይሻቸው ጉዳዮች ላይ ምታብክናቸው ጊዜዎች ምን አልባት ዓለም ላይ ተዓምር የምትስራባቸው ጊዝያቶች ነበሩ።

✍️የማይጠቅሙህን ሰዎች እሾክ አሜኬላ እንዳይሆኑብህ አርቃቸው ነገር ግን ከፍትህን የሚያዩበት ቦታ አስቀምጣቸው።

✍️በጣም ሰላማዊው ሕይወት የሚጀምራው መንፈሳዊ ስብእናህን ስታነቃቃ ነው ነገር ግን በስጋዊ ዓይን ምታያቸው ሰይጣናዊ አመለካከቶች እንዳሉ ልብ በል።

✍️ላንተ ብቸኝነት በሰዎች የተከበቡ ጓደኞችህን አትውቀስ። ከተጠቀምክበት በሺ ሰዎች ከተከበቡት በላይ ታሪክ መሥራት ትችላለህ።

✍️በቅናት የሚመላለስብህን ሰው ክፉ ቃል አትናገረው ቅናቱ ህመም እንጂ ጤና አይሆንለትምና።

✍️ትልቁ ውድቀት የሚጀምረው ሞትን ከመከራ መገላገያ መንገድ ስናደርገው ነው። ሞት በራሱ መንገድ ካለንበት ሳያረፍድ ይመጣል። ወደ እርሱ ከመሔድ ጸንንቱ መጠበቅ ሕይወት ነው።m@

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 11:29


ሰዎች በራሳቸው ከሚጎዱት በላይ በሰዎች ስህተት የሚጎዱት ይልቃል።አስተውል!! ያለ ሰው ሰው መባል የለም! ባንተ ዝምታ የሚጮሁ ባንተ ጩህት ዝም የሚሉ አሉ።ባንተ ንግግር የሚያለቅሱ ባንተ ተግባር የሚበግኑ አሉ።ከመቶ አንድ ሰው ይህ ተግባር ያስደስተዋል።
የምትፈጽማቸው ክንዋኔዎች የምትሰነጥቃቸው ቃላቶች ሰዎችን የሚጎዱ እንዳልሆኑ አረጋግጥ።

አንድ ትኒሽ ጥበብ አለ! አመልህ ከከፋ ለጊዜው በዓመልህ ሊጎዱ ከሚችሉ ሰዎች ራቅ ርቀትህ ግን የአካል ብቻ ሳይሆን የተግባርም ይሁን።ርቆ አለው ማለትም ሌላም ተጨማሪ ጉዳት ነው። የደስታቸው ምንጭ ባትሆን የእንባቸው መንስኤ ግን አትሁን።በአራቱም መዓዘን የሚገጥሙህን ሰዎች ካንተ ስብእና ጋር አጣጥማቸው። ጉድጓድ ቆፍርላቸው ነገር ግን አበባ እንዲተክሉበት እንጂ እንዲወድቁበት አታድርግ።ሌላኛው ጥበብ ደግሞ ሰዎችን በመጎዳት ለበለጸገው ስብእናህ ልጓም አበጅለት።

ህይወት ልክ እንደ ጦር መሽግ ናት ጥይት ድምጽ ስትሰማ ትሸበርበታለህ ከበረታህ ደግሞ ድል ትሳበታለህ።አንድ አንዴ መሽገህ መረበሽን ድል መንሳት ከቻልክ ትልቅ ጠቢብ ነህ። የሚጎዳህን ሰው ተሸሽገህ እለፈው አድብተህ ደግሞ በተግባር አስተምረህ እለፈው።ሰዎችን አስተምሮ መግደል መክሮ ማሸነፍ እየተቻለ ጠልቶ ማሸማቀቅ ሰድቡ ማስጎንበስ ከደቶ ማስረበሽ ነጥቆ ማስነባት የሰብአዊነት መገለጫ አይደለም።
m@

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 11:01


1. ‹‹ትምህርት ቤትንና ትምህርትን አታምታቱ፡፡ እኔ ሃርቫርድ አልገባሁም ነገር ግን ሃርቫርድ የገቡትን ቀጥሬ አሰርቼአለሁ፡፡››

2. ‹‹ተራ ሰዎች ተራ ያለመሆንን ምርጫ መምረጥ ይችላሉ፡፡››

3. ‹‹ወይ አንድ ነገር እውን ሲሆን ማየት እችላለሁ አልያም ደግሞ እውን ከሚያደርጉት አንዱ መሆን እችላለሁ፡፡››

4. ‹‹በተለይ ከቅርብ ጓደኞቻችሁ ለሚነሱ አሉታዊ አስተያየቶች ትኩረት ስጡ፡፡ ያንን ካደረጋችሁ ትጠቀማላችሁ፡፡››

5. ‹‹ነፃ ፈቃድህ ነገህን ለመተንበይ ምርጡና ትክክለኛው መንገድ ነው፡፡››

6. ‹‹ጊዜን ባግባቡ ለመጠቀም የሚረዱ መፃህፍትን አላነበብኩም››

7. ‹‹ዕውቀትህ ሃይል ይሰጥሃል፡፡ ሠናይ ምግባርህ ደግሞ ክብርን ያድልሃል፡፡››

8. ‹‹ውድቀት ምርጫ ነው፡፡ ነገሮች ፈታኝና አዳላጭ ካልሆኑ አዲስ ነገር አትፈጥርም፡፡››

9. ‹‹ኮሌጅ እያለሁ ዓለምን በሚለውጥ ነገር ላይ መሳተፍ እፈልግ ነበር፡፡››

10. ‹‹ከእንቅልፍህ ስትነሳ ቀንህ ጥሩ እንደሚሆን ካሰብክ ውሎህ የፈካ ይሆናል፡፡››

11. ‹‹ታጋሽነት ጥንካሬ ነው፡፡ ስለዚህ ትዕግሰትን እየተማርኩ ነው፡፡ እንደትዕግስት ያለ ከባድ ትምህርት የለም፡፡››

12. ‹‹ብቻቸውን የሚበሩ ጠንካራ ክንፍ ያላቸው ብቻ ናቸው፡፡››

13. ‹‹ሁሌም ነገሮችን በተሻለ መንገድ ለማከናወን አስብ፡፡ ራስህን መጠየቅ አታቋርጥ፡፡››

14. ‹‹በሳምንት 100 ሠዓት የሚሰሩ ስራ ፈጣሪዎች እብዶች ናቸው፡፡ ለሌላ ሰው 40 ሰዓት የሚሰሩበት ጊዜ የላቸውም፡፡››

15. ‹‹ረጅም ጊዜ ቂም ለሚይዙ ሰዎች ሕይወት አጭር ናት፡፡››

16. ‹‹በሕይወትህ ብዙ ሽንፈቶችን ትከናነባለህ፡፡ ነገር ግን አንተነትህ ይሸነፍ ዘንድ በጭራሽ አትፍቀድ፡፡››

17. ‹‹ሕይወት ችግርን ከመቅረፍ በላይ መሆን አለባት፡፡››

18. ‹‹ሰዎች ግባቸውንና ምክንያታቸውን ካወቁ የተሻለ ይሰራሉ፡፡››

19. ‹‹የኤሮስፔስ ዲግሪ የለኝም፡፡ ነገር ግን ብዙ መፅሐፍትን አንብቤአለሁ፡፡ ከምርጥ ሰዎች ጋር አውርቼአለሁ፡፡ ከታላላቅ ስብስቦች ጋር ሰርቼአለሁ፡፡››

20. ‹‹ተጨንቄ ነበር፡፡ ተበድዬ ነበር፡፡ ተሰድቤ ነበር፡፡ ሁሉም ነገር አልፏል፡፡››

ኤለን ማስክ

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 09:31


በመከፋት😔 ውስጥ ያለው ምርጥ ነገር ምን እንደሆነ ታውቃለህ..? ሁሉም ነገር መጮኸ🗣እና መፈንዳት ይጀምራል... ይሄም በህይወት ውስጥ አንድ ነገር ልትማርበት እንደምትችል ያሳያሃል።...ያም በጭራሽ የማይወድቀው ብቸኛው ነገርህ ነው።

...በአጥንቶችህ ውስጥ ያለው መቅኔ አርጅቶ መንቀጥቀጥ ትጀምር ይሆናል...በእኩለ ለሊት ነቅተህ የደም ስሮችህን ህመም ልታዳምጥ ትችላለህ...ብቸኛዋን ፍቅርህን ልታጣም ትችላለህ💔... የገነባኸው አለምህ  ለሰይጣን ምሳ ሆነው ሲደመሰሱ ልታይ ትችላለህ👹...ወይም በሰዎች አዕምሮ  ምልከታ ውስጥ ክብርህ እንደተረገጠ ልታውቅ ትችላለህ።...በእነዚህ ሁነቶች ውስጥ አንድ ነገር ብቻ ነው የምታገኘው ---ምን..? ካልከኝ ትምህርት!!

ስትማር አለም እንዴት እየተሰቃየች እንደሆነ እና ስቃዩ ምን እንደሆነ ተማርበት::...  ያ ብቸኛው ነገር አእምሮ በጭራሽ የማይዝልበት፣ የማይታወክበት ፣ የማይሰቃይበት፣ በጭራሽ በፍርሀት የማይታወክበት እና በጭራሽ የማይጸጸት ህልም ነው ፡፡...መማርህ ላንተ ያለህ ብቸኛው ነገር ነው...እስኪ ተመልከት ምን ያህል ብዙ ነገሮች እንድትማርበቸው እንደተዘጋጁልህ...
🦋

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 09:15


#ይሉኝታ

#ይሉኝታ_ምንድን_ነው?
ይሉኝታ ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ሰበብ፤ የራስን ፍላጎት ገትቶ ሌሎችን ለማስደሰት መጣር፤ ሌሎችን ማስቀደም ማለት ነው፡፡ ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እና ግዴታ በላይ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ይሉኝታ የራሳቸንን ስራና አጀንዳ ወደ ጎን አድርገን ፤ ፍላጎታችንና እና ምርጫችን ተጭነን ሌሎችን ለማስደሰት የመፈለግ ውጤት ነው፡፡

#የይሉኝታ_መንስኤዎች
✿ከመጠን በላይ የሆነ የሌሎችን ሰዎች ተቀባይነትና ትኩረት ለማግኘት መሻት

✿በራስ መተማመን ማነስ

✿ሌሎች ስለእኛ የሚያስቡት ጥሩ ብቻ እንዲሆን መጨነቅ፡-ስለራሳችን ጥሩነት የሚሰማን ሌሎች በሚሰጡን አስተያየት እና ማሞካሸት ከሆነ

✿የውስጥ መረጋጋት ከሌለን

✿አስተዳደግ፡- ያደግንበት ቤተሰብ ሰዎችን ማስደሰት እንደ ትልቅ መርህ የሚያይ ከነበረ፤ ወይም ደግሞ ቤተሰባችን ውስጥ በረባ ባልረባው የሚቆጣ ሰው ከነበረና ያንን ሰው ለማስደሰት ፍላጎታችንን እየተጫንን ያደግን ከሆነ

✿ያደግንበት ማኅበረሰብ ወግና ልማድ፡- በማኅበረሰባችን በማንኛውም መንገድ ቢሆን በመረዳዳት፤ ያለንን ለሰዎች በማከፈልና “እሺ ባይነትን” እንደ መልካም ባህሪያት መውሰድና ግለኝነትንና እምቢ ባይነትን ደግሞ እንደ እኩይ ባህሪይ የመውሰድ ልማድ

#ይሉኝታን_ለመቀነስ_የሚረዱ_መንገዶች

✿ለሰዎች መልካም በመሆንና በይሉኝታ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት

✿ለምናደርገው ነገር ከስሜት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም፡፡ ለምንድን ነው ይህን ጉዳይ የምፈጽመው? ሰው ምንይለኛል ብየ ስለፈራሁ? ወይስ ስለሚያስደስተኝ? ወይስ ኃላፊነት ስለሚሰማኝ?

✿በማድረጋችን፤ ወይም በመፈጸማችን ቆይተን የምንጸጸትበትን ጉዳይ ከማድረግ መቆጠብን መልመድ

✿አስፈላጊ ሲሆን “አይሆንም” ማለትን ወይም ደግሞ “ላስብበት” ማለትን መልመድ

✿በራስ መተማመንን ሊያዳብሩ የሚችሉ የህይወት ክህሎቶችን መለማመድ

✿ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ጤናማ ወሰን እንዲኖረን መጣር

✿ለራሳችን ክብር መስጠት፡- ሰዎች ስለኛ ምንም ቢያስቡ፤ በማንነታችን ላይ ሊያመጣው የሚችለው ተጽእኖ ብዙ እንዳልሆነ ለራሳችን መንገር

✿ያደግንባቸውንና ከማኅበረሰብ ያገኘናቸውን ልምዶች በህይወታችን ያመጡልን በጎና መጥፎ ጎን መከለስ፤ማስተዋል

©zepsychology

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 09:14


ሁል ጊዜ የምንኖረው ህይወት የአስተሳሰባችን (የምናወጣው አዕምሯዊ ሃይል) ውጤት እንደሆነ ማስታወስ ያስፈልጋል ፣ ይህ ሃይል ደግሞ በአዎንታዊነት የተሞላ ከሆነ ለእያንዳንዱ ሁኔታ የምንሰጠውን ማንኛውንም ትርጉም መወሰን የምንችለው እኛ ራሳችን ነን ማለት ነው ፣ በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ እና ጊዜ ውስጥ እንኳን ሆነው ከአሉታዊ አስተሳሰብ ይልቅ አዎንታዊ የሆኑ ሰዎችን ልናገኝ እንችላለን በዚህም አስተሳሰባቸው በችግር ውስጥ የብርሃን ጭላንጭልን ማየት ስለሚችሉ ከብዙ ፈተናዎች የአሸናፊነትን ስነ ልቦና ፈጥረው መእጣት የሚችሉት እነዚሁ ሰዎች ናቸው።

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 08:30


ደካማ ጎኖትን እና ጠንካራ ጎኖትን ለማወቅ የሚረዱ ጥቂት ጥያቄዋች

 ካሉኝ ክሂሎቶች ወይም ችሎታዎች በጣም ጥሩ ውጤት ያስመዘገብኩበት ምንድነው?

 ለውጤታማነቴ የበለጠ የምተማመንበት ችሎታዬ ምንድነው?

 የበለጠ እውቀት ያለኝ ስለምንድነው?

 የበለጠ ለመማር/ለማወቅ የምወደው ምንድነው?

 ካከናወንኳቸው ሥራዎቼ የበለጠ የምኮራበት ምንድነው?

 ሌሎች ሰዎች ለእኔ የተሻለ ሥራ ነው ብለው የሚያስቡት ምንድነው?

 ከሰዎች ባለኝ ግንኙነት ሰዎች የሚወዱልኝ ጠባይ ምንድነው?


 ለእኔ ብዙ ጊዜ አስቸጋሪ የሆነው ክሂሎት ወይም ችሎታ ምንድነው?

 ማወቅ የሚገባኝንያህል የማላውቀው ነገር ምንድነው?

 ብዙውን ጊዜ ሰዎች የሚወቅሱኝ በምን ጉዳይ ነው?

 የበለጠ የተስፋ መቁረጥ ስሜት የሚፈጥርብኝ ጉዳይ ምንድነው?

 እርግጠኛ ሁኜ መሥራቴን የምጠራጠረው ሥራ ምንድነው?

 እኔ በጣም ጥሩ ያልሆኩበት ክሂሎት ብለው ሌሎች ሰዎች የሚያስቡት ነገር ምንድነው?

 በምሠራበት ተቋም የበለጠ ጠቃሚ ሠራተኛ መሆን እየቻልኩ ያልሆንኩበት ጉዳይ ምንድነው?
እራሶን ይጠይቁ

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 08:27


ሊሞቱ የደረሱ ሰዎች የሚቆጫቸው 10 ነገሮች

#Ethiopia | በተለያየ ህመም ምክኒያት በህይወት ጥቂት ጊዜ የቀራቸው ሰዎች ቀሪ ጊዜያቸውን ያለ ስቃይ እንዲያሳልፉ ህክምና የሚያገኙበት ቦታ Hospice ይባላል። ሆስፒስ ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች እነዚህን ከጥቂት ሳምንታት እስከ ጥቂት ወራት የቀራቸው ሰዎች በህይወታቸው ምን እንደሚቆጫቸው ጠይቀዋቸው የሚከተሉትን 10 ነጥቦች አግኝተዋል።

1) ደስተኛ አልነበርኩም- ህይወቴን በሚገባ enjoy አላደረግሁም።

2) በእውቀት ራሴን አላሳደግሁም። ለመማር ብዙ እድል ነበረኝ ግን አልተማርኩም።

3) እራሴን አልተንከባከብኩም-ጥሩ እንቅልፍ አልተኛሁም፤ ስፖርት አልሰራሁም፤ አመጋገቤ ላይ አልተጠነቀቅኩም፤ የጤና ምርመራ በሰአቱ አላደረግሁም።

4) የኖርኩት በቂምና በጥላቻ ነው-ሁሉም ነገር እንደዚህ ማለፉ ለማይቀር ለምን በቂምና በጥላቻ ራሴንም ሰዎችንም ጎዳሁ?

5) ለቤተሰቤ ጊዜ አልሰጠሁም-ላይ ታች ስል ከልጆቼ ጋር አልተጫወትኩም፤ ወላጆቼን እንደምወዳቸው አልነገርኳቸውም። አብሬያቸው ጊዜ አላሳለፍኩም።

6) ሰዎችን አልረዳሁም- ብዙ የእኔን እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ነበሩ። አቅሙ እያለኝ እኔ ግን 'ቢዚ' ስለነበርኩ አልደረስኩላቸውም።

7) ህልሜን አልኖርኩም- ለብዙ አመታት ለአንድ መስሪያቤት ተቀጥሬ ነው የሰራሁት እንጂ የራሴን ህልም አልኖርኩም።

8) ያለምክኒያት ነው የለፋሁት- በማይጠቅሙኝ ነገሮች ተጠምጄ በጣም ስለፋ ነበር።

9) ለሰዎች ፍቅሬን አልገለፅኩም- ለምወዳቸው ሰዎች 'እወድሀለሁ' ወይም 'እወድሻለሁ' አላልኩም።ፍቅሬን ከመግለፅ ይልቅ እኮሳተራለሁ።

10) ሀይማኖትን እንቅ ነበረ- መንፈሳዊነትን እጠላ ነበር። አሁን መጨረሻዬ ላይ እስከምደርስ ወደ አምላኬ ዞር አላልኩም ነበር።

ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ Dawit Dreams ላይ ከተናገረው የተወሰደ።

ሞት መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም። በየሰአቱ በአለማችን 7500 ሰዎች ይሞታሉ። በየቀኑ በአለም አቀፍ ደረጃ 180ሺ ሰዎች ይሞታሉ። ሞት ማን ጋር መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም። ደስተኛ ሆነን፣ ህልማችንን እየኖርን፣ ራሳችንን እየተንከባከብን፣ብዙም ኮስታራ ሳንሆን፣ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ጊዜ እያሳለፍን በይቅርታ ልብ እንዲሁም በመንፈሳዊነት መኖር ሞት ሲመጣ እዳንፀፀት የሚያግዙ ነጥቦች ይመስሉኛል።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 08:23


አቅም ማጣት...

አቅም እንደማጣት ምን የከፋ ነገር አለ። ልትደርስለት የሚገባ ሰው እና ወገን አለህ ግን አቅም የለህም😔። ልትሟገትለት እና ልታድነው ምትፈልገው ሰው አለህ ነገር ግን ማዳን የምትችልበት አቅም የለህም😔። አንድ አንድ ጊዜ ውስጥህ ይደማል ምንም አለማድረግህን ስታስበው ደግሞ ልብህ ይቆስላል። ምንም ማድረግ አለመቻል እና አቅም ማጣት የሆድ በሽታ ክፉ ሕመም ነው። ብታወራ ሰሚ አድማጭ እንደሌለህ ስታስብ ነው አቅም ምታጣው😔። የምታያቸውና የምትሰማቸው ሁሉ ህመም ይሆኑበሀል ሚያሳዝነው ግን ምንም ማድረግ አትችልም ከሩቅ ጩህት ይሰማሀል ሲቃና ለቅሶ ታደምጣለህ ግን በምን አቅምህ እና በምን ሀይልህ ደረሰህ ያንን ጩህትና ሲቃ ታቆመዋለህ😢። በሟች ለቅሶ ዳንኪር ሚደልቀውን ስትመለከት ደግሞ አቅም ማጣትህ ይበልጥ ይቆጭሀል😡። ሕይወት እንዲ ናት ደስታህን ነጥቃህ ሳታበቃ አቅም ታሳጣሀለች። ብዙ ነገሮችን ማድረግ ትፈልጋለህ ግን እንድታደረገው የሚያግዱህ ግዙፍ ተራሮች አሉ። እነዚህን ተራሮች እያየህ ከማዘን ውጪ ሌላ መፍተሔ ማበጀት አትችልም ነገር ግን እነዚህ አቅም ያሳጡህ ጉዳዩች ገሸሽ እስኪሉ ድረስ መታገስ ነው🙄። ትዕግስት ለሁሉም ነገር መልስ አለው። አቅም በማጣት እና በትዕግስት መሐል ሕይወት ትቀጥላለች....😌
M@ 2013

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 08:17


በሰው ልጅ አፈጣጠር ላይ ትልቁ የማይዳሰስ እና ዋጋ የሚሰጠው አካል ህሊና ነው።የህሊና ወቀሳ ከሰዎች ወቀሳ በእጅጉ ይለያል።ሰው ሲወቅስህ ለጊዜው ነው።ህሊናህ ግን እረፍት አይሰጥህም በተኛህና በነቃህ ቁጥር ተከታትሎ ይወጋሀል።ለህሊናህ መኖር ስትጀምር የዓለምን ሀብት ሁሉ በእጆችህ እንደጨበጥክ ማሰብ ትጀምራለህ።

ለህሊናህ መኖር ስትጀምር የአንተ ምርጥ ጠላቶች ውሽትና ስርቆት ይሆናሉ።በሰዎች ልቦና ውስጥ ለመቀመጥ ማስመሰል በበዛበት ሳቅና ውሸት በሞላበት መውደድ ውስጥ መመላስ ሳይሆን መፍትሔው በጎ ህሊና መያዝ ብቻ ነው።ህሊና በሰዎች መቸገር እና መውደቅ ውስጥ ተባባሪ እንድትሆን አይሻም።ለህሊናህ መገዛት ስትጀምር ከሚያከብሩህ ብዙ ሰዎች ይልቅ ለሚጠሉህ ጥቂት ሰዎች ማሰብ ትጀምራለህ።

ያንተ ትልቁ ጠላት ህሊና ቢስነትህ ነው።ህሊና ቢስ ከሆንክ በሰዎች ንግግር የራስህን ተንኮል ታሴራለህ።የሰውችን እንባ እንደሙሉ ደስታ ትቆጥረዋለህ።ዱካ ላይ ለመቀመጥ እንኳን የሚቀፍህ ኩራት ይከበሀል።ምን አለፋህ ህሊና ቢስ ስትሆን ሙሉ ለሙሉ ስበአዊነት የተለየህ ትሆናለህ።ያለሥራቸው ደግና ጥሩ መባል የሚፈልጉ÷በሐሰት ክብር ለመጎናጸፍ የመረያስቡ÷ በአስመሳይነት መወደድን ለመሸመት የሚዋልሉ ሰዎች አልገጠሙህም ከገጠመህ እነዚህ ሰዎች ሙሉ ለሙሉ ለህሊናቸው ሳይሆን ለክብራቸው የሚኖሩ መሆናቸውን እወቅ።

ለህሊናህ መኖር ስትጀምር ታይቶ ለሚጠፋው ክብርህ መጨነቅ ታቆማለህ።ዓለም ምትታመሰው ህሊና ባጡ ሰዎች መሆኑን አትርሳ።ማንም ሰው ከህሊና ወቀሳ ማምለጥ አይችልም።ስለዚህ ትልቁ ጥበብ መልካም እያሰቡ ጥሩ እየሰሩ ከህሊና ወቀሳ መዳን ብቻ ነው።
M@

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 06:35


ምክር ለወዳጅ
10 ሩ የሕይወት መርሆዎች ለደስተኛ ሕይወት፡-

1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ
አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል።
ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር
ማፎካከር ነው።


2. አትኩሮትህ በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ ይሁን፡- ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።


3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? ውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል… ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፡፡


4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ
እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።


5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ
መካከል ትልቅ ልዩነት አለ።
የውሸት ደስታ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች
የሚመጣ ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ሲሆን እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፣ አላማችንና ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዘን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበትም ነው፡፡


6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦ ሰዎችን አትና፤ በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡


7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ከአቅምህ
በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ
የሆነውን ነገር ለአምላክህ/ለፈጣሪህ ስጠው።


8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ራስህን መውደድ ተለማመድ፤
የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ
በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው እራስህን ሲያጠፋ ይቅር በማለት፣ ሲደክም በማበርታት፤ ሲሳካለት በማሞካሠት ተንከባከበው፡፡


9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው
ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት
ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።


10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን
ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ
አመለካከት ይቀየራል፡፡

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 05:30


👉ቤተሰብህን ለመቀበል የሚያስፈሩ አበይት ነጥቦችን ለማንሳት እንሞክር
Important points to accept family

✍️በኤልሳ(መጽሔተ ሕይወት)


ለልጅህ በቂ መሆን እንደማትችል ማሰብ(Thinking that you can't be enough for a child)

💧ሐላፊነት ለመቀበል ለልጅህ የሚሆን ሀይል እንደሌለህ ማሰብ
(Thinking that you dont have the strength respnsibility to the child)

ስራ የማጣት ፍራቻ (fear of jop loss) ወዘተ የሚመስሉ ችግሮች በህይወትህ ውስጥ ትልቅ ፍራቻ የሚያመጡብህ ነገሮች ናቸው።
ወዳጄ :- አሸወይናን ናፍቀው አግባ የሚሉህ ሰዎች የማህበረሰብ ደስታ ተመልካች እንይ የሚሉ ባዮች ናቸውና በህይወትህ ውስጥ እንዲገቡ አትፍቀድላቸው አባትነት ማለት ልክ አንተን እንደወለደክ አባት መሆን መቻል ነው ከሱ የወረስካቸው እያንዳንዱ ገጸባህሪያት ስትኖርባቸው ክፍ አባት ወይም የአለም ምርጥ አባት ትሆናለህ ምክንያቱም አንተ የአባትነት ድክመት ስላለብህ የምትወርሳቸው እያንዳንዱ ነገሮች የቤተሰብህ ተጽእኖች ናቸው።

  ወዳጄ:- አሁን አንተ የራስህን ጎጆ የምትቀልስበት እና የራስህ ዓለም የምትኖርበት ሰዓት አሁን ነው ለዚህም ደግሞ ማህበረሰቡ አንዱ የስነልቦናህ ጭንቀት ናቸውና ከነሱ ዓለም ለመራቅ ስትሞክር ቤተሰብ ምንያህል የፍቅር ዓለም መሆኑን ትረዳለህ።

  👉የአለም ምርጡ አባት ሆይ:-

💧ሚስትህን አክብር እና በፍጹም ፍቅርህን አትንፈጋት

ኋላቀር ንዴትህን የመተው ልማድን አካብት

💧ለልጆችህ የምታሳየው ባህሪህን ተጠንቀቅ

💧በቤተሰብህ እርግጠኛ ሁን

ያሳለፍከውን ህይወት ጥሩን ብቻ ተጠቀም

  ወዳጄ አንተ ዛሬ አባት ልትሆን ነው የልጅህንም መሰላል አጥብቀህ ያዝ ካለበዛያ የመሰላሉ አቀማመጥ ልጅህን ይጎደዋል።

https://t.me/AAAAAFEloxR

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 05:23


ትርጉም የለሽ ፍልሚያ!

አንድ የከራረመ የጠቢባን ምክር እንዲህ ሲል አንድን እውነት ያስታውሰናል፡- “አሳማ መቆሸሽ በፍጹም አያስፈራውም፡፡ ስለዚህ ከዚህ ቆሸሸም አልቆሸሸም ምንም ትርጉም ከሌለው ፍጥረት ጋር ‘የአቆሽሽሃለሁ … አታቆሽሸኝም’ አይነት ፍልሚያ ውስጥ ከመግባት ተቆጠቡ”፡፡

ቢሸነፉም ባይሸነፉም፤ ስማቸው ቢጠፋም ባይጠፋም፤ ቢከስሩም ባይከስሩም፤ ቢታሰሩም ባይታሰሩም፤ ምንም ግድ ከማይሰጣቸውና ምንም ነገር እንደማይጎድልባቸው ከሚያስቡ ሰዎች ጋር ፍልሚያ ይቅርባችሁ፡፡

ፍልሚያችሁን በጥንቃቄ ምረጡ፡፡ የምትመርጡት ፍልሚያና ከምን አይነት ሰዎች ጋር እንደምትፋጠጡ የምትወስኑት ውሳኔ ለራሳችሁ የሰጣችሁትን ከብር አመልካች ነውና

Dr.eyob mamo

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 05:19


የፍቅር ግንኙነትዎን ሊገድሉ የሚችሉ
ጉዳዮች(በሰብለወንጌል አይናለም)ዘሳይኮሎጂስት
💑💑💑💑💑💑💑💑💑
የፍቅር ህይወት በተሞክሮ ውስጥ የምናልፍበትና በሂደት የምናዳብረው ክህሎት ነው፡፡ እንደ ሰው በፍቅር ግንኙነት ውስጥ መፈጸም የማይገባንና የፍቅር አጋራችንን ስሜት
ሊጎዱ የሚችሉ ስህተቶችን ልንፈጽም እንችላለን፡፡
💑💑💑💑💑💑💑💑💑
ለምሳሌ፡ የጓደኛችንን የልደት ቀን መርሳት፡ በቀጠሮ ሰዓት መዘግየት፡ የፍቅር ጓደኛችንን የስጦታ ምርጫ አለማወቅናየመሳሰሉት ለጊዜው ቅሬታ ቢፈጥሩም፤ ተወቃቅሰንና
ተነጋግረን በይቅርታ ልናልፋቸው የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው፡፡
💑💑💑💑💑💑💑💑💑
ይሁን እንጂ የፍቅር ግኑኝነታችን ጤናማ ሆኖ እንዳይቀጥል የሚያደርጉና ቀጣይነቱን እንድንጠይቅ የሚያስገድዱን ስህተቶችም ይኖራሉ፡፡
💑💑💑💑💑💑💑💑💑
የሚከተሉት አምስት ስህተቶች በፍቅር ግንኙነት ላይ አዳጋ ሊያስከትሉ ከሚችሉ ጉዳዮች
ውስጥ ይካተታሉ፡፡
💑💑💑💑💑💑💑💑💑
1. ምልዑነትን መጠበቅ (Expecting Perfection):-
ብዙዎቻችን ወደ ፍቅር ግንኙነት የምንገባው ፍቅረኛችን ውብ እንደሆነ/ች እና በሁሉም ነገር ደግሞ ብቁ እንደሆኑ አድርገን አስበን ነው፡፡ በጊዜ ሂደት ውስጥ የፍቅር አጋራችን ጉደለቶች መታየት ሲጀምሩ ያንን ሰው አስበነው ወደ ነበረው ምልዑነት ለመቀየር ግርግር
መፍጠር እንጀምራለን፡፡ ሰዎች ደግሞ በባህሪያቸው በማንነታቸው እንዳሉ ተቀባይነት እንዲያገኙ እንጂ “የመቀየር አለብህ/አለብሽ ” ግፊት ብዙም ምቾት አይሰጣቸውም፡፡ ለዚህ መፍትሄው የፍቅር አጋርዎን አሁን ባለበት ሁኔታ ሳያቅማሙ መቀበል፤ ሁሉም ሰው (እራስዎን ጨምሮ) ጉድለቶች እንዳሉበት መረዳትና
የፍቅረኛችንን ክፍተቶች እኛ መሙላት የምንችልበት መንገድ ካለ መሞከር የተሻለ ነው፡፡

💑💑💑💑💑💑💑💑💑
2. መወስለት (Cheating)፡- ፍቅር በመርህ ደረጃ የሁለት ተቀራኒ ፆታዎች የአካልና የመንፈስ ውህደትን ይጠይቃል፡፡ ከፍቅረኛችን አሻግረን ሌላ ይምናይ ከሆነ፤ ይባስ ብሎም ከሌላ ተቃራኒ ፆታ ጋር የስሜት ትስስር
መፍጠር ወይም ወሲብ መፈጸም የፍቅር ግንኙነትን በፍጥነት ከሚገድሉ ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ስህተት ውስጥ የገቡ ከሆነ ማድረግ የሚገባዎት የፈጸሙትን ስህተት ለፍቅረኛዎ ነግሮ፤ በቀጣይ መደረግ ስለሚገባው ጉዳይ መወያየት ነው፡፡ውስልትናን ከፍቅር ጓደኛ ደብቆ ማቆየት ቢቻልም በግንኙነታችን ላይ ተጽዕኖውን በተለያየ መንገድ ስለሚያሳርፍ ፍቅራችንን ይገድለዋል፡፡

💑💑💑💑💑💑💑💑💑
3. ማኩረፍ (Silent treatment):- በፍቅር ግንኙነት ውስጥ አለመግባባቶችና ጸቦች ይከሰታሉ፡፡ ይሁን እንጂ ችግሮችን ለመፍታት የምንመርጠው መንገድ ማኩረፍ፤ ስልክ መዝጋትና መሸሽ ከሆነ የፍቅር ግንኙነታችን እየገደልነው ነው፡፡ ፍቅርን ጠብቀው ከሚያቆዩ ምሰሶዎች አንዱ ግልጽ ውይይት ነው፡፡ ንዴታችን እስኪበርድልን ጠብቀን በአልተግባባንበት ጉዳይ ላይ መነጋገር ወደተሻለ መንገድ ይመራናል፡፡ በተቃራኒው ያልተወያየንባቸው አለመግባባቶች በውስጣችን በተጠራቀሙ ቁጥር፤ ግንኙነታችን
በየጊዜው ይረበሻል፡፡

💑💑💑💑💑💑💑💑💑
4. ውሸት (Lying ):-የፍቅር ግንኙነትን ጤናማነት ጠብቀው ከሚያቆዩ ነገሮች አንዱ ሀቀኝነት ነው፡፡ ማንኛውንም ጉዳይለፍቅረኛችን/ የትዳር አጋራችን በግልጽ የመናገር ልምድ ሲኖረን ግንኙነታችን ይጠነክራል፡፡ ነገር ግን ጓደኛችን በሆነ ጉዳይ ላይ ስንዋሽ ከያዘን/ከያዘችን በቀጣይ ለመታመን ዋስትና
የለንም፡፡ ለምሳሌ፡- ስራ ቦታ አምሽቼ ወደ ቤት
እየገባሁ ነው ያሉት አፍቃሪዎ ከሌሎች ጓደኞችዎ ጋር ካፌ ውስጥ ሲዝናኑ እንደነበር ቢያውቅ በሌላ ቀን ስራ ቦታ ቢያመሹ እንኳን የፍቅረኛዎን እምነት ማግኘት ይከብዳል፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን እውነቱን ብቻ
የመነጋገር ልምድን ማካበት ይኖርብናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በዝርዝር የመወያየት ባህል ቢኖረን ግንኙነታችን ይጠነክራል፡፡ ከፍቅር
አጋራችን ደብቀን የምንይዛቸው ጉዳዮች ካሉ በጊዜ ሂደት ግንኙነታችንን ሊያሻክሩ ይችላሉ፡፡

💑💑💑💑💑💑💑💑💑
5. ቂም መቋጠር (Holding a grudge ):- ማንም ሰው ከስህተት የጸዳ አይደለም፡፡ ከዚህ በፊት የተሰሩ ስህተቶችንና ይቅርታ የተጠየቀባቸውን ጉዳዮች ሁልጊዜ እንደ አዲስ እያነሱ ፍቅረኛን መውቀስ፤ አንቺኮ ከዚህ በፊትም እንዲህ አድርገሽኛል፤ አንተኮ
ባለፈውም እንዲህ በድለኸኛል እየተባባልን
የምንነታረክ ከሆነ ፍቅራችንን ውሃ እያስበላነው ነው፡፡ ከቂምና በቀል ያልጸዳ ግንኙነት መሰረቱ ጽኑ አይሆንም፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ያለፉ ስህተቶቸን በይቅርታ መርሳት፤ ወደፊት ደግመው እንዳይከሰቱ ደግሞ መፍትሄ መቀየስ ያሻል፡፡

👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAFNFGBxM7CRSIEwftg

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 05:17


በዘዴ መጨነቅ 1
(በነጋሽ አበበ©ዘ-ሳይኮሎጂስት)
🔻🔻🔻🔻

ጭንቀት ጨርሶ አስፈላጊ ነገር እንዳልሆነ የምንገልፅባቸው ብዙ ዓይነት ዘይቤዎች አሉን፡፡ “ሺህ ዓመት አይኖር” እንላለን፤ ድመቷም “ያው በገሌ ነው” ብላለች አሉ፡፡

🔯🔯
ምንም እንኳን ከልክ በላይ የሆነ ጭንቀት አጥፊ ቢሆንም በልኩ የሆነ ጭንቀት ግን አልሚ እንደሆነ የሳይኮሎጂ ባለሙያዎች ያምናሉ፡፡ ብዙ ጊዜ ብዙ ነገሮች አጥፊ የሚሆኑት ወሰናቸውን ሲያልፉ ይመስላል፡፡

🔯🔯
ከዓመታት በፊት አንድ በግብፅ በረሀ ውስጥ ስለሚኖሩ ባህታዊያን አንድ መጽሐፍ እንዳነበብኩ አስታውሳለሁ፡፡

🔯🔯
አንብቤ ከጨረስኩ በኋላ አሁንም ድረስ ውስጤ የቀረ የአንድ ትልቅ አባት አባባል አለ፡፡ “ከልክ በላይ የሆነ ነገር ሁሉ ከሰይጣን ነው” ይሰኛል፡፡ ልክ እንደዚሁ ሁሉ ከልክ በላይ የሆነም ጭንቀት የአእምሮ ህመምን ይወልዳል፡፡

🔯🔯
አእምሮ ሲታመም መላ አካል፣ ማንነት፣ እና ሕይወት ይታመማል፡፡ ስራ ሰርቶ ውሎ መግባት ይከብዳል፤ ከሰዎች ጋር ተግባብቶ መኖር አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ልክ የለሽ ጭንቀት የስኬት ጠርም ነው፡፡ በጭንቀት ሀሳብ የተሞላ
አእምሮ ጥርት ባለ መንገድ ማሰብ አይችልም፤ የፈጠራ አቅሙ ዝቅተኛ ነው፤ ለሌሎች በቅርብ ርቀት የሚታይ ነገርለእሱ ከአድማስ በአሻገር የተቀመጠ ላም አለኝ በሰማይ ዓይነት ነገር ይሆንበታል፡፡

🔯🔯
በሌላ በኩል ግን በመጠኑ መጨነቅ ጥቅም ይሰጣል፡፡ ይህንን ሊንዳ ፊልድ “Just do it now” የሚለው መጽሐፏ ውስጥ “በዘዴ መጨነቅ” ትለዋለች፡፡ ጭንቀቱ በቁጥጥራችን ስር ሆኖ የመፍትሄ እና መድኃኒት፣ ስኬት እና ሙላት፣ ጤናና ጥንካሬ ምንጭ መሆን ይችላል ማለት ነው፡፡
🔯🔯🔯🔯🔯🔯🔯🔯🔯🔯🔯🔯🔯🔯🔯🔯🔯🔯🔯🔯🔯

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 05:16


ለራሳችን መንገር የሌለብን 4 ነገሮች


የተለያዩ ችግሮች ውስጥ የምታልፉበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለችግሮቹም ራሣችሁን ተጠያቂ ታደርጉ
ይሆናል፡፡ በየትኛውም አይነት ሁኔታ ውስጥ
ብትሆኑም ግን ደካማነታችሁን የሚያጎሉና
ከሠዎች በታች ሆናችሁ እንድትታዩ የሚያደርጉ
ቃላትን መጠቀም የለባችሁም በማለት የሥነ-ልቦና ምሁራን ይመክራሉ፡፡ እነኚህ ቃላት አስተሳሰባችን ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የመፍጠር
አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡ ፡


ለራሳችን የምንናገራቸው አሉታዊ ቃላት ከፍተኛ
ጉዳት እንዳላቸው ከሕይወት ልምዴ ተገንዝቤያለሁ የሚሉት የሥነ-ልቦና ባለሙያው
ማይክ ቡንድራንት በተለይ የሚከተሉትን ቃላት ለራሳችሁ ፈፅሞ መንገር የለባችሁም ይላሉ፡፡


1. የማልረባ ነኝ

ይህ በራስ መተማመናችሁን በቀጥታ የሚገድል አነጋገር ነው፡፡ የማትረቡ ወይም አንዳች ዋጋ የሌላችሁ መሆኑን ለራሳችሁ
መንገር አሉታዊ አስተሳሰብ በአእምሯችሁ እንዲሰርፅ የማድረግ ኃይል ስላለው ቃሉን መጠቀም ተገቢ አይደለም፡፡


2. አልችልም

አንዳንድ ነገሮችን በምትፈልጉት ደረጃ መስራት የማትችሉባቸው ሁኔታዎች በሚፈጠሩበት ጊዜ አቅማችሁን ልትጠራጠሩ ትችላላችሁ፡ ፡ የምታደርጉት ነገር ጥቅም እንደ ሌለው ለራሳችሁ መንገር ለሥራ ያላችሁን የተነሳሽነት ስሜት ይቀንሠዋል፤ አቅማችሁን ያሣጣችኋል፡፡ ይህ አነጋገር እውነታውን ከመግለፅ በላይ ራሳችሁን መልሶ የማጥቃት አቅም አለው፡፡ አንድ ነገር ከመሥራታችሁ በፊት እወድቃለሁ/ አይሣካልኝም ከማለት ይልቅ ደጋግሞ በመሞከር ለውጤት መብቃት እንደምትችሉ ማመን አለባችሁ፡፡


3. ሠዎች አይወዱኝም

ሠዎች አይወዱኝም የሚለውን ስሜት በአእምሯችን ማስረፅ ሌሎች ከእኛ የተሻሉ እንደሆኑ እንድናስብና ለራሳችን ጥረት
ተገቢ ውጤት እንዳንሠጥ ያደርገናል፡፡ በሌሎች ያለመወደድ ስሜት ከተሠማን ደግሞ ለራሳችን የምንሠጠው ክብርም ይቀንሳል::


4. ለውጥ ማምጣት አልችልም

አንድን ነገር ለመለወጥ አቅማችሁ ካልፈቀደ ራሣችሁን አታስገድዱት፡፡ ፍፁም መሆንንም ከራሣችሁ አትጠብቁ፡፡ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ የምትሠጧቸው ሀሳቦች የራሳቸው
አዎንታዊ ተፅእኖ አላቸው፡፡ ስለዚህ ‹ለውጥ ማምጣት አልችልም›› የሚለው ቃል ለራሳችሁ መንገር ከሌለባችሁ አሉታዊ ቃላት መካከል አንዱ ነው፡፡


በአጠቃላይ ስሜታችሁን የሚጎዱ እንዲህ ዓይነት ቃላትንና አነጋገሮችን መጠቀም ትታችሁ አንደበታችሁን በመጠበቅ በየዕለቱ ለምታከናውኗቸው ተግባራት ትኩረት በመስጠት ውጤታማ መሆን ትችላላችሁ፡፡



ምንጭ፡- Psychcentral.com

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 05:12


ስብሃት ገብረእግዚአብሄር አንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፥

"በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ፤ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ፤ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ፤ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ፤ ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ይችላሉ።"በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል።አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው
አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ
ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።
"ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!" አንድ ነገር ልንገራችሁ፥ በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ፤ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡልችሀል፤ መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑችሁዋል። ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆናቹኋል፤ ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑላችሁዋል።

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 04:56


ጥያቄ፡-

ሰላም ዶ.ር ስለምታደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እ/ር ውለታህን ይክፈልህ...

ዶ.ር የዩኒቨርሲቲ መምህር ነኝ ሰወች ለምን አታገባም እያሉ ይጨቀጭቁኛል፣ማተራመስ ፈልገህ ነው ይሉኛል ...እኔ ግን ፍቅረኛ አጣሁ ምንም አሁን ላይ ሁሉም ሴቶች ከኔ ጋር ላለመሆን የተስማሙ እስኪመስለኝ ድረስ ብቼኝነት እየተጫወተብኝ ነው ከፍተኛ ድብርት ውስጥ ገብቻለሁ...ማንም አይፈልገኝም የሚል ስሜት እያደረብኝ ነው...አቊሜ እና መልኬ ቆንጆ ከሚባሉት ብሆን እንጅ አስቀያሚ አይዴለሁም....ምን ላድርግ

መልስ፡-

ከሁሉ በፊት በአንድ ነገር እንስማማና፣ ትዳር መያዝ ያለብህ ለትዳር እድሜህ ስለደረሰ፣ ትዳር የመያዝ ፍላጎት ስላደረብህ፣ ለትዳር የምትሆን የፍቅር አጋር ስላገኘህና ወደጋብቻ ለመሄድ ትክክለኛው ጊዜ እንደደረሰ ስላመንክበትና የፍቅር አጋርህም ስላመነችበት ነው፡፡

ሰዎች “ለምን አታገባም” ስላሉህ መጨነቅና እንደዛ እንዳይሉህ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብህ ማሰብ የማይሆን ውሳኔ ውስጥ እንድትገባ ይገፋፋሃል፡፡ ትዳር ከያዝክ በኋላ ያንን ትዳር እድሜ ልክህን የምትኖረው አንተ ነህ እንጂ ካላገባህ በማለት የሚነዘንዙህ ሰዎች አይደሉም፡፡

ሶስት ነገሮች በሚገባ እንደታጤን ላሳስብህ

1. ከላይ እንደጠቀስኩልህ የሰዎች ንዝነዛ ካስጨነቀህ ፍቅረኛ ለማግኘት ስለምትፍጨረጨር ሂደቱን ያበላሽብሃል፡፡ ትክክለኛ ምልከታና ምርጫ የሚኖረህ ካለምንም የውጪ ግፊት ተረጋግተህ ስትኖር ነው፡፡

2. የጠቀስከው “ድብርት” እና የመሳሰሉት ስሜቶች በራስህ ላይ ጫና ከማምጣታቸው ባሻገር ሰዎች በአንተ ላይ ያላቸውን አመለካከት ይነካዋል፡፡ የተጨናነቀ፣ የተደበረና ግራ የገባው ሰውን ለመቅረብ የማይፈልጉ ሴቶች ብዙ ናቸው፡፡ አሉታዊ ስሜቶችን ትተህ አዎንታዊ ስትሆን ጥሩ ጥሩ ሰዎች ከአንተ ጋር ለማሳለፍና አንተን ለማወቅ ክፍት ይሆናሉ፡፡

3. “አቋሜ እና መልኬ ቆንጆ” ነው ያልከውን አመለካከትህንም መለስ ብለህ አስብበት፡፡ ይህ አመለካከት በራሱ ምንም ችግር ባይኖውም፣ ምናልባት ብዙዎችን ሴቶች አይመጥኑኝም የሚል እሳቤ ይዘህ እንዳይሆን፡፡

በተረፈ፣ ሰዎች ስላንተ የሚያስቡትንና የሚናገሩትን ነገር፣ በሴቶች ላይ ያለህን አመለካከትና ሴቶች ሁሉ ያደሙብን ይመስለናል የሚሉትን የከረሩ ሁኔታዎች ረገብ አድርጋቸውና ራስህንና ዓላማህን በማግኘትና በማሳደግ ስትኖር ሁሉም ነገር ተከትሎ ይመጣል፡፡

✍️ዶክተር ኢዮብ ማሞ

የዶክተር ኢዮብ ማሞን ስነልቦናዊ ጽሑፎች ለማግኘት እነዚህን ሊንኮች ይጠቀሙ።

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 04:49


ለውጡን ቀስ በቀስ አድርገው!

አንድ ትልቅ ድርጅት በወቅቱ ዋና ዳይሬክተር ስላልነበረውና መቅጠር ያስፈልገው ስለነበር የድርጅቱ ቦርድ ከብዙ ውይይትና አማራጭ ካመለከቱት ሰዎች መካከል የአንዱ ሰው የስራ ልምድና ብቃት ስለሳባቸው ይህንን ሰው ቀጠሩት፡፡ ይህ ሰው በጣም ተራማጅና አራማጅ፣ እንዲሁም ለውጥን የሚወድ ፈጣን ሰው ነው፡፡

በዚያ መስሪያ ቤት ተቀጥሮ ጥቂት ከሰራ በኋላ አንድን በእንግዳ መቀበያው አካባቢ በአጉል ቦታ ለብዙ አመታት ተቀምጦ የነበረ ዴስክ ቦታውን ለመቀየር ፈለገ፡፡ ይህንን ሃሳቡን ግን ቦርዱ አላመነበትምና ብዙ ተከራከሩ፡፡ በመጨረሻ በራሱ ፈቃድ የዴስኩን ቦታ ቀየረው፡፡

በዚህ ምክንያት ቦርዱ ከተሰበሰበ በኋላ፣ ይህ ሰው እኛን የማይሰማን ከሆነ መባረር አለበት ብለው ስለወሰኑ አባረሩትና ሌላ ዳሬክተር ቀጠሩ፡፡

ይህ አዲስ ዳይሬክተር ገና ስራ እንደጀመረ ከታዩት ሁኔታዎች አንዱ የዚህ የዴስክ አጉል ቦታ መደንቀር ነበር፡፡ ስለሁኔታው ጸሃፊዋን ሲጠይቃት፣ “ይህንን ዴስክ ከዚህ ዘወር የሚያደርግልን ሰው ብናገኝ ጥሩ ነበር፡፡ ሆኖም፣ ከአንተ በፊት የነበረውን ዳይሬክተር እንዲባረር ያደረገ ዴስክ ስለሆነ ባትነካው ይሻልሃል” አለችው፡፡ ይህ አዲስ ዳይሬክተር ግን ብልህ ሰው ስለነበረ ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቅ ነበር፡፡

አንድ ቀን ከብዙ ጊዜ በኋላ የቀደመው ዳይሬክተር ወደዚያ መስሪያ ቤት ሲመጣ እርሱ እንዲባረር ምክንያት የሆነው ዴስክ ከነበረበት ስፍራ እርሱ ቀድሞውኑ ሊቀይረው ወደነበረበት ስፍራ ተንቀሳቅሷል፡፡ በጣም በመገረም አዲሱ ዳይሬክተር ከቢሮው እስከሚወጣ በመጠበቅ ራሱን ካስተዋወቀው በኋላ፣ “ይህንን ዴስክ ከነበረበት ስፍራ አሁን ወዳመጣኸው ስፍራ ለመቀየር ሞክሬ በዚያ ምክንያት ነው ስራዬን ያጣሁት፡፡ ለመሆኑ እንዴት አድርገህ አንቀሳቀስከው? ቦርዱስ እንዴት ዝም አለህ?” በማለት ጠየቀው፡፡

መልሱ አጭርና ግልጽ ነበር፡- “ብዙ ጊዜ ቢፈጅብኝም፣ በየገዚው አንዲት ሴንቲሜትር ብቻ በማንፏቀቅ እዚህ አመጣሁት!” አለው፡፡ ዴስኩ ያለበትን አዲስ ቦታ ቦርዱ ያስተዋለው ከብዙ ጊዜ በኋላ ነበር፡፡

እንደሚወራው ከሆነ አዲሱን ቦታ ስለወደዱት ነው ዝም ያሉት፡፡
አንዳንድ ጊዜ ማድረግ የምንፈልገው ነገርና ማምጣት የምንፈልገው ለውጥ ትክክለኛ ሆኖ ሳለ ካለአግባብ የምንጋጨው፣ ያሰብነውን ከማከናወን የምንገታውና ተስፋ የምንቆርጠው እኛ የታየንንና ሌሎቹ ያልታያቸውን ነገር በቶሎ ለማድረግ ስንሞክር ነው፡፡

ለውጥ ሂደት ነው! ለውጥ ጊዜን ይፈልጋል! ትልቅ ለውጥ በየቀኑ የሚደረግ የጥቂት ነገር ጥርቅም ነው፡፡ ስለዚህ፣ ከሰዎች ጋር መታገላችሁንና መከራከራችሁን አቁሙና ለውጡን ቀስ በቀስና ሰዎች በማያስተውሉት መልኩ “አንቀሳቅሱት”፡፡ ለውጡ ከመጣ በኋላ ጥቅሙንና ብልጫውን ሲያዩ ያን ጊዜ ሰዎች ይገነዘቡዋችኋል፡፡

Dr eyob mamo

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

20 Jan, 04:23


ቅን የሆኑ ሰዎች ጠንካራ ስብእና ከገነቡ ሰዎች ውስጥ ይመደባሉ። ቅንነት የተጣመመውን ነገር አቃንቶ ማዳመጥ ብቻ ሳይሆን መጥፎውንም ተገባር በመልካም ጎኑ ማሰብ እና መመልከት መቻል ነው። የቅን ሰው ጥያቄና መልስ ከየትኛውም ተንኮል የጸዳ ነው። በርግማን አንደበት የበለጸገን ሰው አፉ እንጂ ሆዱ ባዶ ነው ÷ሰርቆ አደሩን ቢቸግረው እንጂ ወዶ አይደለም ÷ነፍሰ ገዳዩን ደግሞ ሰይጣን አሳስቶት ነው የሚሉ ቅን ሰዎች ሁሉንም ክስተቶች በቀና መንገድ መመልከታቸው ዋጋ ቢያስከፍላቸው ሁሉንም ክስተት በክፋት ከሚተረጉሙ ሰዎች የተሻል የልብ ንጽሕና አላቸው።

ቅንነት ሞኝነት አልያም አለማወቅ አይደለም። ቅንነት በጣም የተወሳሰቡ ችግሮችን መፍታት ምንችልበት ለተንኮል የተጠነሰሱ ሀሳቦችን የምናከሽፍበት ልዩ ጥበብ ነው።ተራራ የሚያክል ስጋትህን በቅኖች መሀል ይዘህ ስትገኝ ድንገት ሳታስበው ሸክምህ ይቀልሀል።ከብዙ አንድ ይህ ቅንነት በተፈጥሮ ይቸረዋል ምኒሽር የሚያስመዝዝ ስራ ሰርተህ ፊታቸው ስትቆም ሥራህ እኮ ይሔ ይሔ ጠቀሜታ አለው ብሎ ፍርሀትህን ሁሉ በአንዴው ሲያከስመው ስታይ የዓለም ሰላም ማጣት የቅኖች ማነስ እንደሆነ ትረዳለህ።

ምክርህን ስድብ÷ምርቃትህን ርግማን÷ሀሳብህን ትንኮሳ አድርገው የሚያቆስሉህ ሰዎች በእርግጠኝነት በቅንነት መረዳት ከእነሱ የተለያቸው ናቸው። ቅንነት ቅናትን የሚያስቀር እና ግጭቶችን የሚያጠፋ በጥቂቶቹ ብቻ የሚገኝ ስጦታ ነው። በቅንነትህ ውስጥ ማግኘት ያለብህን ነገሮች ታጣ ይሆናል ቅንነትን አጥቶ ከአእምሮ ጭንቀት ውስጥ ከመዘፈቅ ግን በቅንነት ኖሮ የሚፈልጉትን እስኪያገኙ መታገስ የተሻለ ነው።

M@2012

1,573

subscribers

22

photos

142

videos