❖መዝሙረ ዳዊት❖

@mezmure_dawitt


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን፡፡
በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ
❖ኦርቶዶሳዊ መዝሙሮች

❖በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ መልዕክታት

❖የቅዳሴና የማህሌት ምስባኮች እንዲሁም

❖የቅዱሳንን በአላትና ገድሎች ይከታተሉ፡፡

@Mezmure_Dawitt

~~~~~~~~~~~

❖መዝሙረ ዳዊት❖

06 Oct, 18:46


ፆመ ፅጌ / የፅጌ ፆም /

የእመቤታችንን ስደት በጾም በጸሎት የምታስቡ ወይም የምታሳልፉ የእመቤታችን የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች እንኳን አደረሳችሁ

ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡

በነዚህም ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩት መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡

ወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሰዊ አገልግሎት መነሻው "መልአኩ ሕፃኑንና እናቱን ወደ ግብፅ ይዘሃቸው ሽሽ፣ የሕፃኑን ነፍስ ሊገድሉት ይፈልጋሉና" ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሠረተ ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው፡፡

ከእመቤታችን በረከት ያሳትፈን አሜን!!!


#JOIN & #SHARE

https://telegram.me/Mezmure_Dawitt

❖መዝሙረ ዳዊት❖

19 Sep, 07:09


#ሰንበተ_ክርስትያን

በኩር ናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእሷ ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን

በዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና
መልካም ስራ የሚሰራባት
ሰንበት ቅድስት ናት እና
ከጨለማ ብርሀን ከመገዛት ነፃነት
እግዚአብሔር ይህን ሰጠን
ደስ ይበለን በሰንበት
#አዝ
ለአብርሃም ተገልጣለች
ለሙሴም በደብረ ሲና
በነቢያት የታወቀች
ሰንበት ዳራዊት ናት እና
በሳምንቱ ሰለጠነች
ተሰበከች በሐዋርያት
ሃሌ ሉያ ዕለተ ሰንበት
ተሰጠችን ልናርፍባት
#አዝ
በእልልታ እንሞላ እንደ ነቢዩ አሳፍር
በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ
በመቅደሱ ናቸው እና ቅዱስነትና ግርማ
ውዳሴያችን ይሰማልን
ከምድር እስከ እዮር እራማ
#አዝ
እግዚአብሔር አብ የባረካት
እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት
ከእለታት ሁሉ መርጦ
መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያደረጋት
በእርሷ ሀሴት እናድርግ
እናክብራት እንድንከብር
የደጀሰላሙ ታዛ በመቅደሱ እንሰብሰብ


#JOIN & #SHARE

https://telegram.me/Mezmure_Dawitt

❖መዝሙረ ዳዊት❖

11 Sep, 14:39


ሥርዓተ ማኅሌት ዘመስከረም ምትረተ ርእሱ ለቅዱስ ዮሐንስ "መስከረም ፪"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።

ነግሥ
ሰላም ለአብ ገባሬ ኲሉ ዓለም፤ ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤ ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።

ዚቅ
ዛቲ ይእቲ ትንቢቶሙ ለነቢያት፤ ስብከቶሙ ለሐዋርያት፤ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት።

ዓዲ
ዚቅ
ዛቲ ይእቲ እኅተ ትጉሃን መላእክት፤ ወለተ ኄራን ነቢያት፤ እሞሙ ለሐዋርያት፤ ሞገሶሙ ለጻድቃን ወሰማዕት።

ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ንትፈሣሕ ኲልነ በዝክረ ስምኪ ጥዑም፤ ወበደመ ዮሐንስ መዓድም፤ ቅድስት ማርያም ቤዛዊተ ኲሉ ዓለም።

መልክአ ዮሐንስ
ሰላም ለሥእርተ ርእስከ እንተ ደለዎ እኳቴ፤ ወለርእስከ ሰላም ዘተመትረ ከመ ናቡቴ፤ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ፤ መብልዕ ዜና ፍቅርከ ወነገረ ጽድቅከ ስቴ፤ ያስተፌሥሕ መላእክተ ወሰብአ መዋቴ።

ዚቅ
አመ ይገብር ሄሮድስ በዓለ ዘዕለተ ልደቱ፤ መጽአት ወለተ ሄሮድያዳ ወዘፈነት ሎቱ፤ አሥመረቶ ወትቤሎ ሀበኒ በፃህል ርእሰ ዮሐንስ ወንጌላዊ።

ወረብ
አመ ይገብር ሄሮድስ በዓለ ዘዕለተ ልደቱ መጽአት ወለታ ለሄሮድያዳ/፪/
አሥመረቶ ወትቤሎ ሀበኒ በጻሕል ርእሰ ዮሐንስ ወንጌላዊ/፪/

መልክአ ዮሐንስ
ሰላም ለጒርኤከ ወለክሣድከ ዓዲ፤ እምዓጸደ ሞት በሊህ ዘኢያጎነዲ፤ እመ ይሄሉ ሕያወ ዮሐንስ አስካለ ጋዲ፤ ጊዜ ቀሠመከ ንጉሠ ዓመፃ ረዋዲ፤ እምበከየ እፎ አቡከ ወላዲ።

ዚቅ
ዘሕማማተ እግዚኡ መዋቅሕተ ፆረ፤ ወርእሶ አምተረ ዓቢያተ ተናገረ፤ አስተምህር ለነ ዮሐንስ ዘአጥመቀ ቃለ።

አመላለስ
ዘሕማማተ እግዚኡ መዋቅሕተ ፆረ/፪/
ወርእሶ አምተረ ዓቢያተ ተናገረ/፪/

ወረብ
ዘሕማማተ እግዚኡ መዋቅሕተ ፆረ ወርእሶ አምተረ/፪/
ዓቢያተ ተናገረ አስተምሕር ለነ ዮሐንስ ዘአጥመቀ ቃለ/፪/

መልክአ ዮሐንስ
ሰላም ለመከየድከ በአስተሐምሞ ወጻሕቅ፤ ወለአጻብዒከ ሰላም ዘአእዋመ ሥጋ አዕጹቅ፤ ለመንግሥተ ሰማይ ዮሐንስ በእንተ ኪዳንከ ጽድቅ፤ ብዙኃን ይትመሐፀንዋ እንበለ ብሩር ወወርቅ፤ በሕፍነ ማይ ወክልኤ ጸሪቅ።

ዚቅ
ግፉዓን ይትመሐፀንዋ፤ ለመንግሥተ ሰማያት፤ አንተ ውእቱ ዮሐንስ ምስለ ኲሎሙ ሰማዕት።

ወረብ
ግፉዓን ይትመሐፀንዋ ለመንግሥተ ሰማያት/፪/
አንተ ውእቱ ዮሐንስ ምስለ ኲሎሙ ሰማዕት/፪/

ዓርኬ
ተዘኪረከ ምትረተ ርእሱ ለዮሐንስ ግዩር፤ በቅናተ ዓዲም ዘዔለ ወበሠቀ ጸጒር፤ ማዕበለ ጌጋይየ አቅም እግዚአብሔር፤ በከመ አቀምከ ተከዜ ዮርዳኖስ ባሕር፤ እስከ ካህናት ዐደዉ በእግር።

ዚቅ
መጽአት ወለተ ሄሮድያዳ ወዘፈነት ሎቱ፤ አሥመረቶ ወትቤሎ፤ ሀበኒ በፃህል ርእሰ ዮሐንስ ወንጌላዊ።

አመላለስ
መጽአት ወለተ ሄሮድያዳ ወዘፈነት ሎቱ/፪/
አሥመረቶ ወትቤሎ/፪/

ወረብ
መጽአት ወለተ ሄሮድያዳ ወዘፈነት ሎቱ/፪/
ሀበኒ በፃሕል ርእሰ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወንጌላዊ ክቡር (መጥምቅ)/፪/

ምልጣን
እምሄሶ ለሄሮድስ ይብላዕ መሐላሁ፤ እምያምትር ርእሶ ለዮሐንስ፤ ዓቢይ ነቢይ ሰባኬ ጥምቀት ለንሥሐ ከመ ይእመኑ ሕዝብ በብርሃኑ።

ወረብ
እምኄሶ ለሄሮድስ ይብላዕ መሐላሁ ይብላዕ መሐላሁ እምያምትር ርእሶ ለዮሐንስ/፪/
ዓቢይ ነቢይ ዓቢይ ነቢይ ሰባኬ ጥምቀት/፪/

ወረብ
እምኄሶ ለሄሮድስ ይብላዕ መሐላሁ እምያምትር ርእሶ ለዮሐንስ/፪/
ዓቢይ ነቢይ ሰባኬ ጥምቀት ለንሥሐ ሰባኬ ጥምቀት/፪/

ቅንዋት
መጽአ ዮሐንስ ሰማዕተ ይኩን በእንተ ብርሃን፤ መጽአ ዮሐንስ በፍኖተ ጽድቅ ወኢአምንዎ፤ ወንሕነኒ እለ አመነ፤ በመስቀሉ ድኅነ።

አመላለስ
ወንሕነኒ እለ አመነ/፪/
እለ አመነ በመስቀሉ ድኅነ/፪/

ወረብ
መጽአ ዮሐንስ ሰማዕተ ይኩን በእንተ ብርሃን በእንተ ብርሃን/፪/
በፍኖተ ጽድቅ ወኢአምንዎ ወንሕነኒ እለ አመነ በመስቀሉ በመስቀሉ በመስቀሉ ድኅነ/፪/


🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌼

#JOIN & #SHARE

https://telegram.me/Mezmure_Dawitt

❖መዝሙረ ዳዊት❖

11 Sep, 14:36


​​​​🌼 "የዕንቁጣጣሽ" ሥያሜ አመጣጥ?

ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡

በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡

ሁለተኛው ደግሞ የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡

ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡

ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡

አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡

መልካም አዲስ አመት ይሁንልን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር


#JOIN & #SHARE

https://telegram.me/Mezmure_Dawitt

❖መዝሙረ ዳዊት❖

10 Sep, 17:59


🌼ምስባክ
መስከረም 1/1/2014 ዓ.ም

🌼በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ 2 ቆሮ 6÷1-11
ንፍቅ ዲያቆን፦ ያዕ 5÷8-13
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 5÷12-17

#ምስባክ ፦ መዝ 141÷ 6-8
አድኅነኒ እምእለ ሮዱኒ እስመ ይኄይሉኒ።
ወአውጽኣ እሞቅሕ ለነፍስየ።
ከመ እግነይ ለስምከ እግዚኦ።

#ትርጉም ፦
እጅግ ተቸግሬያለኹና ወደ ልመናዬ አድምጥ
በርትተውብኛልና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።
አቤቱ ስምክን አመሰግን ዘንድ።

#ወንጌል ፦ ማቴ 11÷1-20
#ቅዳሴ ፦ ዘወልደ ነጎድጓድ



#JOIN & #SHARE

https://telegram.me/Mezmure_Dawitt

❖መዝሙረ ዳዊት❖

10 Sep, 17:54


❖መዝሙረ ዳዊት❖ pinned «የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የዘመን አቆጣጠር (ባሕረ- ሐሳብ ) የዘመነ ማርቆስ/ የ2014 ዓ.ም የአጽዋማትና የበዓላት ማውጫ ስሌት “በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ” መዝ. 64(65)፥11 ዓመተ ዓለም = ዓመተ ምህረት + ዓመተ ኩነኔ (ፍዳ) = 2014+ 5500 =7514 ወንጌላዊ፦ በዓመቱ የሚሾም ወንጌላዊ ማለት ነው፡፡ ዓመተ ዓለም፥4 7514 ÷ 4 = 1878 1878…»

❖መዝሙረ ዳዊት❖

10 Sep, 17:24


👆👆👆
የቀጠለ

29 +7=36
36 ን በ30 ገድፍን ቀሪው 6 ሲሆን ሰኔ 6 ሰኞ የሐዋርያት ጾም ይገባል።
ፆመ ድህነት ተውሳኩ
1 ነው፡፡
= 1 + 7 =8 በመሆኑም ጾመ ድህነት(የረቡዕና ዓርብ ጾም) ሰኔ 8 ይገባል።
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
የአጽዋማትና የበዓላት ኢይወርድ ኢይዓርግ(ገደብ)
➛ጾመ ነነዌ ከጥር 17 በታች አይወርድም ፤ ከየካቲት 21 በላይ አይወጣም።
➛ ዐቢይ ጾም ከየካቲት 1 በታች አይወርድም ፤ ከመጋቢት 5 በላይ አይወጣም።
➛ ደብረዘይት ከየካቲት 28 በታች አይወርድም ፤ ከሚያዝያ 2 በላይ አይወጣም።
➛ ሆሣዕና ከመጋቢት 19 በታች አይወርድም ፤ ከሚያዝያ 23 በላይ አይወጣም።
➛ ስቅለት ከመጋቢት 24 በታች አይወርድም ፤ ከሚያዝያ 28 በላይ አይወጣም።
➛ ትንሣኤ ከመጋቢት 26 በታች አይወርድም ፤ ከሚያዝያ 30 በላይ አይወጣም።
➛ ርክበ ካህናት ከሚያዝያ 20 በታች አይወርድም ፤ ከግንቦት 24 በላይ አይወጣም።
➛ ዕርገት ከግንቦት 5 በታች አይወርድም ፤ ከሰኔ 9 በላይ አይወጣም።
➛ ጾመ ሐዋርያት ከግንቦት 16 በታች አይወርድም ፤ ከሰኔ 20 በላይ አይወጣም።
➛ ጾመ ድኅነት ከግንቦት 18 በታች አይወርድም ፤ ከሰኔ 22 በላይ አይወጣም።
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
አስተውል:-
• ጾመ ነነዌ፣ ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ሐዋርያት ከሰኞ አይወጡም።
• በዓለ ደብረዘይት፣ ሆሣዕና፣ ትንሣኤና ጰራቅሊጦስ ከእሁድ አይወጡም፡፡
• ዕርገት ከሐሙስ
• ስቅለት ከዓርብ አይወጣም።
• ርክበ ካህናትም ከረቡዕ አይወጣም።
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
የዘመናት ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ ፣ ከ2013 ዓ.ም ወደ 2014 ዓ.ም በሰላም በጤና ያሻግረን፤ አሜን።

❖መዝሙረ ዳዊት❖

10 Sep, 17:23


የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የዘመን አቆጣጠር (ባሕረ- ሐሳብ )
የዘመነ ማርቆስ/ የ2014 ዓ.ም የአጽዋማትና የበዓላት ማውጫ ስሌት
“በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ” መዝ. 64(65)፥11
ዓመተ ዓለም = ዓመተ ምህረት + ዓመተ ኩነኔ (ፍዳ) = 2014+ 5500 =7514
ወንጌላዊ፦ በዓመቱ የሚሾም ወንጌላዊ ማለት ነው፡፡
ዓመተ ዓለም፥4
7514 ÷ 4 = 1878
1878 ፦ መጠነ ራብዒት ይባላል፡፡
7514 - 4×1878 = 2
ቀሪው ' 1 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ
ቀሪው ' 2 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ
ቀሪው ' 3 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ
ቀሪው ' 0 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይሆናል።
ስለዚህ ቀሪው '2' ስለሆነ የዘንድሮው ወንጌላዊ ማርቆስ ሲሆን ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ ይባላል።
•••
ዕለተ ቀመር፦ መስከረም አንድ የሚውልበት ቀን ነው፡፡
ዕለተ ቀመር= ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት÷7
= 7514 + 1878 =9392
= 9392 ÷ 7 = 1341 ቀሪ 5
ቀሪው '0 'ከሆነ ሰኞ
ቀሪው '1' ከሆነ ማክሰኞ
ቀሪው '2 'ከሆነ ረቡዕ
ቀሪው '3 'ከሆነ ሐሙስ
ቀሪው '4 'ከሆነ ዓርብ
ቀሪው '5 'ከሆነ ቅዳሜ
ቀሪው '6 'ከሆነ እሁድ መባቻ ይሆናል። በመሆኑም ዘንድሮ ቀሪው '5'ስለሆነ ዕለተ ቀመር ቅዳሜ ይሆናል።
•••
መደብ = ዓመተ ዓለምን በ19 በመግደፍ እናገኛለን። = 7514፥19=395 ደርሶ 9 ይቀራል። ስለዚህ መደብ 9 ይሆናል፡፡
•••
• ወንበር = ከመደብ አንድን ለዘመን በመተው ወንበርን እናገኛለን።
ወንበር =9 - 1= 8 ይሆናል።
• አበቅቴ ፦ጥንተ አበቅቴን በወንበር አባዝተን በ30 ገድፈን እናገኛለን።
አበቅቴ =11*8=88
88፥30= '2' ደርሶ ቀሪው '28' ሲሆን ዘንድሮ አበቅቴ '28'ይሆናል።
አበቅቴን ለማግኘት ሌላው አማራጭ ጥንተ አበቅቴ ላይ 11 በመጨመር ነው። ይህም ማለት የ2013 ዓ.ም አበቅቴ 17 ነበር፤ ስለዚህ የ2014 ዓ.ም አበቅቴን ለማግኘት 17+11=28 ይሆናል ማለት ነው።
• መጥቅዕ፦ ጥንተ መጥቅዕን በወንበር አባዝተን ለ30 በመግደፍ(በማካፈል) እናገኛለን።
መጥቅዕ = 19×8 = 152
152 ÷ 30= 5 ቀሪው '2 'ስለሆነ መጥቅዕ ዘንድሮ '2 'ይሆናል።
መጥቅዕንን ለማግኘት ሌላው አማራጭ ጥንተ መጥቅዕ ላይ 19 በመጨመር ነው። ይህም ማለት የ2013 ዓ.ም መጥቅዕ 13 ነበር፤ ስለዚህ የ2014 ዓ.ም መጥቅዕን ለማግኘት 13+19=32 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 2 ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ የ2014 መጥቅዕ 2 ይሆናል ማለት ነው።
“አበቅቴ ወመጥቅ ክሌሆሙ ኢይበዝሁ እም30 ወኢይኅዱ እም 30 ወትረ ይከዉኑ 30 ፤ አበቅቴ ቢበዛ መጥቅ ቢያንስ መጥቅ ቢበዛ አበቅቴ ቢያንስ ከ30 አይበዙም አያንሱም” ይህም ማለት በሌላ አገላለጽ መጥቅዕና አብቅቴ ተደምረዉ ዉጤቱ ከ30 መብለጥና ማነስ የለበትም፤ ሁሌ 30 ይሆናል፡፡ የዘንድሮዉ የ2013 ዓ.ም = 28+2= 30
መጥቅዕ ከ14 በላይ ከሆነ በመስከረም ይዉላል፤
መጥቅዕ ከ14 በታች ከሆነ በጥቅምት ይዉላል፤
መጥቅዕ በመስከረም ቢዉል ጾመ ነነዌ በጥር፣ መጥቅዕ በጥቅምት ቢዉል ጾመ ነነዌ በየካቲት ይብታል።
ስለዚህ በዚህ ዓመት መጥቅዕ 2 ሲሆን ከ14 ያንሳል፤ ስለዚህም መጥቅዕ በጥቅምት ይዉላል፤
•••
ስለዚህ የ2014 መጥቅዕ ጥቅምት 2 ነው ሲሆን ዕለተ መጥቅዕ ማግሰኞ ይሆናል፡፡
•••
መባጃ ሐመር፦ መጥቅዕንና የባለመጥቅዕን ተውሳክ በመደመር በ30 በመግደፍ እናገኛለን፡፡ ከዕለተ መጥቅዕ ጀምረን እስከ ነነዌ ጾም መግቢያ ስንቆጥር 128 ቀን ይሆናል፡፡ በ30 ብንገድፈዉ 4 ቀሪ 8 ይሆናል፡፡ ይህም የቅዳሜ ተውሳክ ነው። ልብ ይበሉ የዕለት ተውሳክ ከቅዳሜ ይጀምራል፡፡
• ቅዳሜ፡ 128፥30= 4 ቀሪ 8
• እሁድ፡127፥30= 4 ቀሪ 7
• ሰኞ፡ 126፥30=4 ቀሪ 6
• ማግሰኞ፡ 125 ፥30= 3 ቀሪ 5
• ረቡዕ፡124 ፥30= 2 ቀሪ 4
• ሐሙስ፡ 123፥ 30= 2 ቀሪ 3
• ዓርብ፡122፥ 30= 2 ቀሪ 2
ስለዚህ የዕለታት ተውሳክ ቀሪዎቹን በመያዝ ይታወቃል። ይህም የቅዳሜ 8፣ የእሁድ 7፣ የሰኞ 6፣ የማግሰኞ 5፣ የረቡዕ 4፣ የሐሙስ 3 እንዲሁም የዓርብ 2 ይሆናል ማለት ነው። መባጃ ሐመርን ለማግኘት መጥቅዕንና በዓለ መጥቅዕ የዋለበትን ዕለት ተውሳክ መደመር ነው።
መባጃ ሐመር= 2+5=7
መባጃ ሐመር ከ30 ስለሚያንስ ራሱ 7 ይያዝና መጥቅዕ በጥቅምት ስለዋለ ጾመ ነነዌ በየካቲት 7 በዕለተ ሰኞ ይውላል ማለት ነው።
• ጾመ ነነዌ፦ መጥቅዕና የዕለቱን ተውሳክ
በመደመር በ30 ገድፈን እናገኛለን፡፡ይህ ጾም ሕጸፅ የለውም፡፡ ሌሎችን አጽዋማት ተውሳኩን ከነነዌ ደምረን ከ30 ከበለጠ ለ30 እያካፈልን እናገኛለን።
•••
፩፥ ከነነዌ ጾም እስከ ዐቢይ ጾም 14 ቀናት አሉ። ስለዚህ የዐቢይ ጾም ተውሳክ 14 ይሆናል፡፡
፪፥ ከነነዌ እስከ ደብረዘይት 41 ቀኖች አሉ፡፡
41 ÷ 30 = 1 ደርሶ ቀሪው 11 የደብረዘይት ተውሳክ ይሆናል፡፡
፫፥ ከነነዌ እስከ ሆሣዕና 62 ቀኖች አሉ፡፡
62 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 2 የሆሣዕና ተውሳክ ይሆናል፡፡
፬፥ ከነነዌ እስከ እስከ ስቅለት 67 ቀኖች አሉ፡፡
67 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 7 የስቅለት ተውሳክ ይሆናል፡፡
፭፥ ከነነዌ እስከ ትንሣኤ 69 ቀኖች አሉ፡፡
69 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 9 የትንሣኤ ተውሳክ ይሆናል፡፡
፮፥ ከነነዌ እስከ ርክበ ካህናት 93 ቀኖች አሉ፡፡
93 ÷ 30=3 ደርሶ ቀሪው 3 የርክበ ካህናት ተውሳክ ይሆናል፡፡
፯፥ ከነነዌ እስከ ዕርገት 108 ቀኖች አሉ፡፡
108 ÷ 30 = 3 ደርሶ ቀሪው 18 የዕርገት ተውሳክ ይሆናል፡፡
፰፥ ከነነዌ እስከ ጰራቅሊጦስ 118 ቀኖች አሉ፡፡ 118 ÷ 30 = 3 ደርሶ ቀርው 28 የጰራቅሊጦስ ተውሳክ ይሆናል፡፡
፱፥ ከነነዌ እስከ ጾመ ሐዋርያት 119 ቀኖች አሉ፡፡ 119 ÷ 30 =3 ደርሶ ቀሪው 29 የጾመ ሐዋርያት ተውሳክ ነው፡፡
፲፥ ከነነዌ እስከ ጾመ ድኅነት 121 ቀኖች አሉ፡፡ 121 ÷ 30 = 4 ደርሶ ቀሪው 1 ሲሆን የጾመ ድኅነት ተውሳክ 1 ይሆናል፡፡
•••
ከዚህ ተነስተን አጽዋማትንና በዓላትን ተውሳኮቻቸውን ከነነዌ ጋር እየደመርን እናገኛለን፡፡ ስለዚህ የ2014 የነነዌ ጾም መግቢያ የካቲት 7 ይሆናል፡፡
2+7= 9 ስለሆነ ነው፡፡
★ ዓብይ ጾም ተውሳኩ 14 ነው
= 14 +7= 21 ሲሆን ስለዚህ ዘንድሮ በዘመነ ማርቆስ ዓብይ ጾም በየካቲት 21 ይገባል ማለት ነው፡፡
* ደብረ ዘይት፡ ተውሳኩ 11 ነው፡፡
11+7 =18 ይሆናል፡፡ 18 ከ 30 ስለሚያንስና በየካቲት ስላለፍን ቀጣዩን በመጋቢት እናገኛለን። ስለዚህ በመጋቢት 18 እሁድ ደብረዘይት ይሆናል።
★ ሆሣዕና ተውሳኩ 2 ነው፡፡
= 2+7 =9 ሲሆን ከ30 ስለሚያንስና በመጋቢት ስላለፍን ቀጣዩን ሚያዚያን እናገኛለን፡፡ ስለዚህ ሚያዚያ 9 እሁድ ይሆናል፡፡
★ ስቅለት ተውሳኩ 7 ነው፡፡
7+7= 14 ሲሆን ዘንድሮ በሚያዝያ 14 ዓርብ ስቅለት ይሆናል፡፡
★ ትንሣኤ ተውሳኩ 9 ነው፡፡
9 +7 = 16 ሲሆን ሚያዝያ 16 በዓለ ትንሣኤ ይውላል።
★ ርክበ ካህናት ተውሳኩ 3 ነው፡፡
3 +7 = 10 ሲሆን 18ን በሚያዝያ ስላለፍን በግንቦት 10 ረቡዕ ርክበ ካህናት ይሆናል።
★ ዕርገት ተውሳኩ 18 ነው፡፡
18 +7 = 25 ሲሆን ዘንድሮ ግንቦት 25 ሐሙስ በዓለ ዕርገት ይሆናል።
★ ጰራቅሊጦስ ተውሳኩ 28 ነው፡፡
28 +7= 35 በ30 ገድፈን ቀሪው 5 ሲሆን ሰኔ 5 እሁድ በዓለ ጰራቅሊጦስ ይውላል።
★ ጾመ ሐዋርያት ተውሳኩ 29 ነው፡

❖መዝሙረ ዳዊት❖

09 Sep, 18:17


ሥርዓተ ማኅሌት ዘዓውደ ዓመት "መስከረም ፩"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለገበዋቲክሙ እለ ዕሩቃን እምልብሰ ወርቅ፤ ሥሉስ ቅዱስ ሥርግዋነ መፍርህ መብረቅ፤ መንገለ ፍኖቱ ምጽዋት ለቆርነሌዎስ ጻድቅ፤ ይምርሐኒ ወንጌልክሙ እግዚአ ፍኖት ረቂቅ፤ ዘጸያሔሁ ዮሐንስ መጥምቅ።

ዚቅ
ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ፤ እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ።

ዓዲ
ወንጌል ቅዱስ ዘሰበከ ዮሐንስ፤ ቃለ ወልደ እግዚአብሔር።

ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም መሠረተ ጽድቅ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ወአዘዘ ደመና በላዕሉ።

ነግሥ
ምስለ ራጉኤል ስዑል በነበልባል ወዮሐንስ ድንግል፤ ወበርተሎሜዎስ ሐዋርያ ሰባኬ ወንጌል፤ ወኢዮብ ዓዲ ተወካፌ ቊስል፤ ዓውደ ዓመት ለባርኮ እምጽርሐ አርያም ጌልጌል፤ ማርያም ንዒ ለምሕረት ወሣህል።

ወረብ
ዓውደ ዓመት ለባርኮ ባርኮ ዓውደ ዓመት/፪/
ንዒ ማርያም ለምሕረት ወሣህል/፪/

ዚቅ
ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ዮሐንስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ።

ዓዲ
በምድረ ጽዮን ኢይኩን ሐከክ፤ ወበገራኅታ ኢይብቊል ሦክ፤ ጸሊ ኀበ አምላክ ራጉኤል መልአከ፤ ዓውደ ዓመት ከመ ይትባረክ።

መልክዐ ዮሐንስ
በስመ እግዚአብሔር እሳት በሐቅለ ኅሊና ነዳዲ፤ ወበስመ ማርያም ድንግል መጥበቢተ ዓለም አባዲ፤ ማኅቶተ ጸዳል ዮሐንስ ጽልመተ አበሳ ሰዳዲ፤ ከመ እዜኑ ኂሩተከ እደ ኃጣውእየ ይፍዲ፤ በአየረ ሰማይ ይጸርሕ ቃልከ ዓዋዲ።

ዚቅ
እገኒ ለከ እግዚኦ በኲሉ ልብየ፤ ወእዜኑ ኂሩተ ዚአከ፤ እትፌሣሕ ወእትሐሠይ በአድኅኖትከ።

ዓዲ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ማኅቶተ ጥበብ ውስተ አልባቢነ አኅቱ፤ ኀበ አዘዝከነ ኑፈር ወንዕቱ።

ወረብ
እገኒ ለከ እግዚኦ በኲሉ ልብየ/፪/
እትፌሣሕ ወእትሐሠይ በአድኅኖትከ/፪/

መልክዐ ዮሐንስ
ሰላም ለሥዕረተ ርእስከ እንተ ደለዎ እኳቴ፤ ወለርእስከ ሰላም ዘተመትረ ከመ ናቡቴ፤ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ፤ መብልዕ ዜና ፍቅርከ ወነገረ ጽድቅከ ስቴ፤ ያስተፌሥሕ መላእክተ ወሰብአ መዋቴ።

ወረብ
"ርእሰ ዓውደ ዓመት ዮሐንስ"/፪/ ወላዴ መጥቅዕ/፪/
ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ ወላዴ መጥቅዕ/፪/

ዚቅ
ውስተ ርእሰ ዓውደ ዓመት ተጽሕፈ ተዝካርከ፤ ባርከኒ እንሣእ በረከተከ።

መልክዐ ዮሐንስ
ሰላም ለአዕይንቲከ እለ ሠኑየ ይትኌለቁ፤ ወለአእዛኒከ ሰላም እለ ይትላጸቁ፤ ዮሐንስ ከማከ ሶበ ፈተዉ ወጽሕቁ፤ እሳተ ነዳዴ ኢተክህሎሙ ያጥምቁ፤ ራጉኤል በትጋሁ ወኢዮብ በጽድቁ።

ወረብ
"እሳተ ነዳዴ" ኢተክህሎሙ ያጥምቁ/፪/
ዮሐንስ ከማከ ሶበ ፈተዉ ወጽሕቁ/፪/

ዚቅ
ሰላማዊ ብእሲሁ፤ ቅዱሳት እደዊሁ እለ አጥመቃሁ፤ ለመድኃኔዓለም።

መልክዐ ዮሐንስ
ሰላም ለአማዑቲከ እግዚአብሔር ዘገብሮ፤ ወለንዋየ ውስጥከ ሰላም መንጦላዕተ ሥጋከ እንተ ሰወሮ፤ ዮሐንስ ልብው መዝገበ ጥበብ ወአእምሮ፤ እፎ ኢያጽራከ ለሀቅለ ገዳማት ፃዕሮ፤ ፍጹመ መኒነከ አብያተ ዘውቅሮ።

ወረብ
"አብያተ ዘውቅሮ"/፪/ መኒነከ/፪/
ፍጹመ መኒነከ ዮሐንስ ልብው/፪/

ዚቅ
አብያተ ዘውቅሮ መኒነከ፤ በተዘከሮ ማኅደር ዘበሰማያት፤ ፀጒረ ገመል ረሰይከ ዓራዘከ።

መልክዐ ዮሐንስ
አምኃ ስብሐት አቅረብኩ ለመልክዕከ በጽዋዔ፤ እንዘ አስተዋድድ ቃለ መጠነ ራብዕ ሱባኤ፤ ተወክፈኒ ዮሐንስ ምስለ በርተሎሜዎስ ቀርነ ጉባኤ፤ ከመ ተወክፈ እግዚእከ ቅድመ ወንጌላዊት ትንሣኤ፤ እምደ አሐቲ ብእሲት ጸራይቀ ክልዔ።

ዚቅ
ዮሐንስ እዴከ መጥወኒ፤ ወበርተሎሜዎስ አቡየ ለባርኮ ቅረበኒ።

ወረብ
ዮሐንስ እዴከ መጥወኒ/፪/
ወበርተሎሜዎስ አቡየ ለባርኮ ቅረበኒ/፪/

አንገርጋሪ
ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ፤ ዓርኩ ለመርዓዊ ትሰመይ፤ ወአዝማዱ በሥጋ ትሰመይ፤ ተፈኖከ ታርኁ አናቅጸ ጽድቅ።

ወረብ
ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ ነቢየ ልዑል/፪/
ዓርኩ ለመርዓዊ ትሰመይ ነቢየ ልዑል/፪/

ቅንዋት
ዲበ ዕፀ መስቀል ተ ቀነወ: ማ- ወዲበ ምጽንጋዕ ተጠብለለ: ዘዮሐንስ ሰበከ ጥምቀቶ

#JOIN & #SHARE

https://telegram.me/Mezmure_Dawitt

❖መዝሙረ ዳዊት❖

08 Sep, 05:02


​​ፈታሔ ማሕፀን

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ " የዘለዓለም ሕይወትን እንዲወርሱ ቅዱሳን መላእክት ምእመናን ለመርዳት ለማገልገል ከእግዚአብሔር የሚላኩ ረቂቃን ፍጥረታት አይደሉምን? ( ዕብ ፩÷፲፬) ብሏል። ቅዱስ ዮሐንስም "የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ"( ራእዩ ለዮሐንስ ፰÷፬) በማለት ተናግሯል።

ቅዱሳን መላእክት ያለማያቋረጥ ለፈጣሪያቸው ምስጋና የሚያቀርቡ ረቂቃን ፍጥረታት ናቸው። በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ለተልእኮ ይፋጠናሉ። የሰውን ጸሎትና ልመና ወደ እግዚአብሔር ያደርሳሉ፤ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ምሕረት ወደ ሰው አድርሰው በእምነት ያጸናሉ። "በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው" (ራእ. ፰÷፪) የሚለው የሚያስረዳን ለተልእኮ መፋጠናቸውን ነው። ሄኖክም “በሰው ሰውነት ላይ የተሾሙ ከከበሩ ፯ቱ ሊቃነ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል አንዱ ነው” (ሄኖ.፮÷፩-፵፪) ብሏል።

የሰዎችን ልመና ወደ እግዚአብሔር፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እና በረከት ወደ ሰው የሚወርድባት ዕለት"ርኅወተ ሰማይ” ትባላለች። ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት፣ አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት፣ ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ስለሆነች "ርኅወተ ሰማይ-ሰማይ የሚከፈትባት ቀን" ትባላለች። እንዲህ የሚባለው በሰማይ መዘጋት መከፈት ኑሮበት አይደለም። የሰው ልጆችን ልመና ቅዱሳን መላእክት የሚያሳርጉበት፣ አንድም ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገብ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ እንጂ።

ቅዱስ ሩፋኤል ልቡናን ደስ የሚያሰኝ፣ ባለ መድኃኒት፣ የጸሎት መዝገብ መክፈቻ ቍልፍ የተሰጠው፣ የሴቶችን ማሕጸን የሚፈታና ሳይጨነቁ እንዲወልዱ ምጥን የሚያቀል መልአክ ነው። "ለሰብእ ወለእንሰ ፈታሔ ማሕጸኖሙ አንተ" እንዲል። የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረና ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነትም ከሚያገቡ ከከበሩ መላእክት መካከል አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ "(ጦቢያ ፲፪÷፲፭) የሚለው የሚያስገነዝበው ተራዳኢነታቸውን፣ ባለሟልነታቸውን፣ አማላጅነታቸውን ነው።

ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን ዐረገ"(ሐዋ. ፲÷፬) የሚለው የመላእክትን አገልግሎት የሚገልጥ ነው። መላእክት ሰዎችን ይራዳሉ፣ የሰውን ጸሎት ያሳርጋሉ፣ ያማልዱሉ፣ ሰዎችን ከመከራ ነጥቀው ያወጣሉ። "የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ። አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህን ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ፣ እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው። ስለዚህም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ። ስበክ እንዲህም በል። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል (ዘካ፣ ፩÷፲፪÷፲፬) የሚለው አማላጅነታቸውን የሚገልጥ የማጽናኛ ቃል ነው።

ጦቢያና መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ወደ ራጉኤል ቤት በደረሱ ጊዜ ሣራ ተቀብላ ደስ አሰኘቻቸው። መልአኩም ለጦቢያ አባትህ ከዘመዶችህ ወገን አግባ ያለህን ቃል አስብ አለው። ራጉኤልም ልጁ ሣራን ለጦቢያ አጋባት። ተመግበውም ከጨረሱ በኋላ ጦቢያን ወደ እርሷ አገቡት፤ ወደ እርሷም በገባ ጊዜ የመልአኩ የቅዱስ ሩፋኤልን ነገር አሰበ፤ የዕጣን እራሪ ወሰደ፤ ከዚያም ዓሣ ከልቡና ከጉበቱ ጨምሮ አጤሰው። ሽታውም ያን ጋኔን በሸተተው ጊዜ እስከ ላይኛው ግብፅ አውራጃ ድረስ ሸሸ። መልአኩም ጋኔኑን አሰረው( ጦቢ ፰÷፩) የተባለው የሚያስረዳን የመላእክትን ተራዳኢነት ነው።

ጦቢያ የሰርጉን በዓል በጨረሰ ጊዜ ወደ አባቱ ቤት ከሚስቱ ከሣራና ከመልአኩ ከቅዱስ ሩፋኤል ጋር ተመለሱ። ሩፋኤልም አለው፥ "ያባትህ ዐይኖች እንዲበሩ አውቃለሁ፤ አንተ ግን ያን ሐሞት ያባትህ ዓይን ኳለው፤ በተኳለም ጊዜ ብልዙ ከአይኑ ይወጣል በደህናም ያያል። ጦቢያም የአባቱን አይን ኳለው ዓይኑም በራለት”( ጦቢ ፲፩÷፮) ተብሎ እንደተነገረው እግዚአብሔር ከዚህ ክፉ ወረርሽኝ ጠብቆን በሰላም በጤንነት ለሚመጣው ዓመት ያድርሰን። የጦቢትን ዓይን ያበራውን የቅዱስ ሩፋኤልን ዓመታዊ በዓል አክብረን በረከት ለማግኘት ያብቃን።አሜን!!

ዲ/ን ተመስገን ዘገየ
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!

#JOIN & #SHARE

https://telegram.me/Mezmure_Dawitt

❖መዝሙረ ዳዊት❖

18 Aug, 13:36


#ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ? #ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል? #ሙልሙል ልምን ይታደላል? በቡሄ ወቅት #ጭራፍ ለምን ይጮሃል ?

#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡
፨፨፨

#ጅራፍ
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡
፨፨፨


#ችቦ
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ #በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡
፨፨፨

#ሙልሙል
በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡ ሕፃናቱ
የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ
….” ይላሉ፡፡
በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና
ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡

ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበረካታ ዓመታት ሰወረድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል ፡፡
ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡


✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥

#JOIN & #SHARE

https://telegram.me/Mezmure_Dawitt

❖መዝሙረ ዳዊት❖

13 Aug, 01:06


​​#ነሃሴ_7
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

#ቁጽረታ_(ጽንሰታ)ለማርያም

ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል።

#ስለ\ምን_ነው_ቢሉ :- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው። አንድም ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ።

"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ።" - "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው።"
(መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9, መኃ. 4)

ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል።

የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ(አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር።

ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር። ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ። እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም።

የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው። አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች። "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች።

ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ። ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ። በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ: በማኅጸኗ ስትደርስ አየ።

እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች። ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ።

በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው። እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች።
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ" - "ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ። (ቅዳሴ ማርያም)

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!

#JOIN & #SHARE

https://telegram.me/Mezmure_Dawitt

❖መዝሙረ ዳዊት❖

12 Aug, 17:36


#ሴት_በወር_አበባዋ_ጊዜ_መጸለይ_ትችላለች?

ጸሎት ከፈጣሪ የምንገናኝበት መንገድ ስለሆነ እግዚአብሔር ጊዜን እየጠበቀ በዚህ ጊዜ እሰማችኋለሁ በዚህን ጊዜ አልሰማችሁም አይልም፡፡ በወር አበባ ጊዜ አይጸልይም ማለት የቤተ-ክርስትያን አስተምህሮ ሳይሆን የሰነፉ ሰይጣን የተንኮል እና የእንቅፋት ስብከት ነው፡፡

የሰይጣንን እንኳን ጸሎት ትተን ቀርቶ እየጸለይን ፈተናችንን እኛና እግዚአብሔር ነው የምናውቀው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በዘመኑ እንደ እኛ ግራ ለተጋቡት የተሰሎንቄ ምእመናን "ሳታቋርጡ ፀልዩ" በማለት ፀሎት በየትኛውም ሁኔታ እና አጋጣሚ ማቋረጥ እንደሌለባቸው ፅፎላቸዋል። (1ኛ ተሰሎ 5÷18)

ወዳጆቼ ፀሎትን የለመደች ሴት በወር አበባዋ ምክንያት ለሰባት ቀን ፀሎትዋን ብታቋርጥ ስንፍናን ትለምዳለች፡ትዘናጋለች አጋንንቱም በዚህ አጋጣሚ ፈተናዋን ያበዛል።

ሴት በወር አበባዋ ጊዜ እስከ መንጻቷ ቤተክርስትያን ነው መግባት የማትችለው እንጂ፣ ጸሎት ማቋረጥ የለባትም፡፡ ጊዜን ተብቆ አለመጸለይ ለሰይጣን በር መክፈት ነውና ትንሿን ጸሎታችንን ማቋረጥ የለብንም፡፡

እኛ በወር አበበ ጊዜ ንፁህ አይደለንም ብለን ሥጋዊ ምግብ እንደማንተው ሁሉ ጸሎት የነፍስ ምግብ ነውና ነፍሳችን ለ7 /ሰባት/ ቀን ከውዳሴ ማርያም ፣ ከሰኔ ጎለጎታ ፣ከአርጋኖን፣ከሰይፈ ሥላሴ፣ከሰይፈ መለኮት እና ከተለያዩ የጸሎት ማዕድ እየከለከልን ሕያዊት ነፍሳችንን ማስራብ የለብንም፡፡ ይልቁንም ዘወትር በመጸለይ ነፍሳችንን መመገብ ይገባናል፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!

#JOIN & #SHARE

https://telegram.me/Mezmure_Dawitt

❖መዝሙረ ዳዊት❖

07 Aug, 01:15


​​​​ፍልሰታ ምን ማለት ነው?

ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ለዚህ ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፤ "ፍልሰታ ማለት ፈለሰ /ተሰደደ/ ከሚለው ግስ የወጣ ነው።"

‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ  ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው  ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡››

ቀሲስ ስንታየሁ አባተም በተመሳሳይ መልኩ ስለ ፍልሰታ እንዲህ በማለት ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ 

‹ፍልሰታ ለማርያም› የሚለው የግእዝ  ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡

ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው  ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡›› 

ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ካሣ እንዳብራሩት ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡

በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡

ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ በማለት ሊቀ ማእምራን ደጉ ያስረዳሉ፡፡

እንደ እርሳቸው አገላለጽ ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡

የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?

የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ሊቀ ማእምራን ደጉ ምላሽ ሲሰጡም "ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር በመሆኗ እና ሕዝበ ክርስትያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡ 

ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡ ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው›› በማለት ያብራራሉ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!

#JOIN & #SHARE

https://telegram.me/Mezmure_Dawitt

❖መዝሙረ ዳዊት❖

01 Apr, 19:32


Follow

❖መዝሙረ ዳዊት❖

25 Sep, 17:26


❖መዝሙረ ዳዊት❖ pinned Deleted message