❓ንስሀ ማለት ምን ማለት ነው
🔸ሊሰሩት የማይገባ ስራ ወይም ኃጢአት ከሰሩ በኋላ ምነው ባልሰራውት ምነው ባላደረኩት ብሎ ማዘን መቆጨት ነው።
🔹በሰራነው ኃጢአት ተፀፅተን የምንመለስበት ነው።
📖ማቴ 12፥31
❓ንስሀ እንዴት እንገባለን
🔹ካህናት ዘንድ ቀርበን መሆን እንዳለበት መጽሃፍ ቅዱስ ይነግረናል።
📖ኢያ 7፥16፤
📖ማቴ 18፥13
🔸ኃጢአታችን በመናዘዝ ማለትም የሠሩትን ኃጢአት በመዘርዘር ልቡናን ታዛቢ አንደበተን ከሳሽ፣ ካህኑን ዳኛ አድርጎ ራስን መውቀስ ማለት ነው፡፡
👌በተጨማሪም በጸሎትና በመራራ ልቅሶ፣ በስግደትና በምጽዋት መሆን አለበት።
📖ማቴ 26፥75
💠በንስሃ ከተመለስን በኋላ
🔸ዳግመኛ መበደል አይኖርብንም።
🔹ንሰሃ የሚደገም ቢሆንም ከኃጢያት መራቅ አለብን። 📖ዩሐ 5፥14፤
📖ሮሜ 6፤14
🔸ሥጋ ወደሙን መቀበል ይገባናል።
📖ዩሐ 6፥56፤
📖1ኛ ቆሮ 11፥26
🔹ፍጹም ሰላምን እናገኛለን። 📖ዩሐ 14፥27
‼️አስተውሉ
🔔ማንኛውም ክርስቲያን ነፍስ ካወቀ በኋላ የንስሃ አባት መያዝ አለበት፡፡
🔔የንስሃ አባት የሚሆነው ካህን በአጥቢያው ቢሆን ይመረጣል፡፡
👌ምክንያቱም በየጊዜው እየተገናኙ ለሠሩት ኃጢአት ቀኖና ለመቀበል እንዲሁም መንፈሳዊ ምክርን ለማግኘት ሲባል ነው፡፡
❓ቀኖና ማለት ምን ማለት ነው
🔸 መስፈሪያ፣ መለኪያ ማለት ነው።
👌በአንድ ሰው ንሰሃ መግባት በሰማይ ሳይቀር ደስታ እንደሚሆን ተገልጿል።
📖ሉቃ 15፥7፤
📖 ማቴ 9፥13
…✍እንማማር ሼር-JOIN ያደርጉ
👉ስለ ሃይማኖታችን መማር ይፈልጋሉ? ??
ከፈለጉ JOIN ያደርጉ በማርያም🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@Maryam_Maryam2127
@Maryam_Maryam2127
@Maryam_Maryam2127