የ ኦርቶዶክስ ስብከት

@orthodox_sebket


የ ኦርቶዶክስ ስብከት

21 Jan, 00:26


.መልካም ወዳጅ
መልካም ወዳጅ ስለወንድሙ ብሎ ሁሉን ይከፍላል ነፍሱንም እስከ መስጠትም ቢሆን ።ታድያ ምን ያህል ውለታ ቢያደርግ እንኳን  አድርግልኝ ተብሎ(ተጠይቆ) አይደለም  እንደስጦታ በገዛ ፍቃዱ ነው እንጂ ።ቅዱስ ዮሀንስ አፈ ወርቅ ስለ መልካም ወዳጅ ሲናገር ..''መልካም ወዳጅ የታመነ መድሀኒት ነው''ይላል ለምን እንዲ አልክ ትለኝ እንደሆን መድሀኒት  ሲውጡት ይመራል ኋላ ግን አድኖ ደስ ያሰኛል..መልካም ወዳጅም  ተቆጥቶ ሲመክር ያሳዝናል ኋላ ግን ምክሩ ከክፉ መንገድ እንደጠበቀችን ስናይ ደስ ያሰኛል..ብሎ ነግሮናል .ሁላችንንም  በዙሪያችን ላሉት መልካም ወዳጅ ያድርገን ቸር ቆዩ🙏

@anu_yehabtye✍️

https://t.me/orthodox_sebket

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

21 Jan, 00:26


https://youtu.be/QRSZ_LIFWdU?si=6oA5b-nsA1ni3yzw

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

21 Jan, 00:26


ውድ የ ኦርቶዶክስ ስብከት አባላቶቻችን እንደምን አላችሁ ? የጌታችን የመድኃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ከ ሁላችን ጋር ይሁን።
እንደሚታወቀው ይሄ ቻናል ከ ዜሮ ተነስቶ እዚ የደረሰው በናንተው ድጋፍ ነው ለዚህም እግዚአብሔር ያክብርልን🙏
ነገር ግን በጣም ተቀዛቅዟል እናም እንደመፍትሄ ከዚው ከ አባላቶቻችን ስብከቶችን ሚለቅልን ወንድም ወይንም እህትም ካላችሁ በዚህ አካውንት
@yemariyam_1621
እንድታናግሩኝ በ ትህትና እጠይቃለሁ እና ደግሞ የ መዝሙር ቻናል በ YouTube ከፍተናል https://www.youtube.com/@orthodox82
ገብታችሁ subscribe እንድታደርጉን አሁንም በ ትህትና እንጠይቃለን 🙏
የ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን❤️🙏

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 20:16


🌷ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤዉን በሚመስል ትንሣኤም ከእርሱ ጋር እንተባበራለን እግዚአብሔር አምላክ ከሁሉ አስቀድሞ የነበረ ነው!

አድምጡ 👉👂❤️ 🙏

https://t.me/orthodox_sebket

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 20:16


📚ርዕስ:- ሕማማት
📝ደራሲ:- ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
📜ዘውግ፦ ሃይማኖታዊ
📖የገፅ ብዛት:- 460
📅ዓ.ም:- 2010

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 20:11


#ሆሳዕና 🙏
በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው  ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15)

#የዘንባባ_ዝንጣፊ፡-
☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡

#የቴምር_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።

#የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።

በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡

ወስብሀት ለእግዚአብሔር 🙏🙏🙏

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 20:06


እሺ ብትሉ…

ልጆቼ! እስኪ ምላሴን ላሰናብትባችሁና እናንተም በትዕግሥት አድምጡኝ! የቤት ሠራተኛ አላችሁ እንበል፡፡ ይህቺ የቤት ሠራተኛችሁ የለበሰችውንና በወጥ፣ በአመድ እንዲሁም በሌላ ቆሻሻ እድፍ ያለ ልብሷን ትለብሱ ዘንድ ትፈቅዳላችሁን? በእርግጠኝነት አትፈቅዱም፡፡ ግን የብዙዎቻችን ሰውነት ከዚህ ልብስ በላይ መቆሸሽዋስ ታውቃላችሁን?

ልጆቼ! ንግግሬ በጣም እንደሚያሳምም አውቃለሁ፤ ግን ምን ላድርግ? የተስተካከለ ሕይወት ቢኖረን እንዲህ የምናገር ይመስላችኋልን? በፍጹም! አንድ የቆሰለ የሰውነት ክፍል ቢኖራችሁ ሐኪሙ ይህን ቁስላችሁ በጣቱ ሳይነካካ ማከም ይችላልን? አይችልም! እኔም እንዲህ ቁስላችሁን ካልነካካሁት በስተቀር ማከም አልችልም፡፡ ለነገሩ ሰው ሰውነትህን አትንካ ማለት ይቻላልን አይቻልም! ታድያ እኔና እንናተ እኮ አንድ አካል ነን፡፡ በክርስቶስ አንድ ኾነን የለምን? እንግዲያውስ ንግግሬን አትጥሉት፤ ክፉ ግብራችሁን እንጂ፡፡

ችግሩ ከማን ነው ከእኛው ወይስ ከቆሻሻው? አንድ ወደ ትዕይንት (ቲያትር) ቤት የሄደ ወጣት ገላዋን ገላልጣ የምትተውን ተዋናይትን አይቶ ዝሙትን መፈጸም የማያስብ ማን ነው? ደጋግሞ የዝሙት ዘፈንን የሚሰማ ሰው ዝሙትን ከመፈጸም መቋቋም እችላለሁ የሚል ማን ነው? ቀኑን ሙሉ የዝሙት ጽሑፎችን ሲያነብ የሚውል ሰው ዝሙትን ከመፈጸም መጠበቅ እችላለሁ የሚል ማን ነው?

ልጆቼ! ትዕይንቱን እያየነው፣ ዘፈኑን እየዘፈንነው፣ መጽሐፉንም እያነበብነው ኾኖም ግን መፍትሔ ካላገኘንበት ችግሩ እየባሰ የሚሄድ አይደለምን? እኛ ፈቃደኞች ከኾንን ግን መፍትሔው በሥጋችን ላይ ካለው ደዌ በላይ በጣም ቀላል ነው፡፡ ምክንያቱም የሥጋችን ቁስል ሐኪም፣ መድኃኒት፣ ጊዜ ያስፈልጓል፡፡ የነፍሳችንን ቁስል ግን ፈቃድ በቂ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሕዛብ ከእኛ በላይ በንጽሕና ሲኖሩ ሳይ በጣም አፍራለሁ፡፡ እንግዲያውስ ልጆቼ እንመለስ፡፡ ያቆሸሹንን ነገሮች እንጣላቸው፤ እንቁረጣቸው፤ እናስወግዳቸው፡፡ ሰነፎች አንሁን፡፡

ውሳኔው የእኛው ነው፡፡ መጽሐፍ ሲናገር “እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም ሰይፍ ይበላችኋል” ይላል /ኢሳ.1፡19-20/፡፡ ስለዚህ ሁሉም ነገር በእኛ እሺታና እምቢታ የተወሰነ ነው ማለት ነው፡፡ የምንኮነነውም የምንመሰገነውም በዚሁ መሠረት ነው ማለት ነው፡፡ መድኃኒዓለም በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን ከሚላቸው ጋር በቸርነቱ ይደምረን አሜን፡፡

ምንጭ፦ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 20:02


ዮሐንስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦
² መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው።
³ ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።
⁴ ኒቆዲሞስም፦ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው።
⁵ ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።
⁶ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።
⁷ ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁህ አታድንቅ።
⁸ ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፥ ድምፁንም ትሰማለህ፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው።
⁹ ኒቆዲሞስ መልሶ፦ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? አለው።
¹⁰ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን?
¹¹ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም አትቀበሉትም።
¹² ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 20:02


ኒቆዲሞስ

ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ክቡር
ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር

በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ
በመከራው ፅናት ይህን ዓለም ናቀ
መምህር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ
የትዕቢትን ጅረት በትህትና ተዋርዶ አደረቀ

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አዝ
ፍርሃትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ
ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ
የመግነዙን በፍታ በሽቶ አከበረ
ከመቅደሱ አንቀፅ ላይረሳ አምድ ሆኖ ታጠረ

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አዝ
ለሊትም ለሊት ዕውቀትን ነገረች
ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች
ከጨለማ ሀጢያት  ነግታ ብርሃን ከአየች
እንደ ኒቆዲሞስ ነፍስህም ተምራ ተመለሰች

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ

   ዲያቆን ዘማሪ ቀዳሚፀጋ

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 19:51


#ገብርኄር (የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት)

ታላቁን የጌታችንን ጾም ከጀመርን ስድስተኛ ሳምንት ላይ ደርሰናል፡፡ ይህን ሳምንት ቅድስት ቤተክርስቲያን ”ገብርኄር” የሚል ስያሜ ሰጥታዋለች፡፡ ገብርኄር በጎ አገልጋይ ማለት ሲሆን የስያሜውን መነሻ የምናገኘው በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው የወንጌል ክፍል ማቴ. 25:14-30 ነው፡፡

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ መስሎ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ የዛሬው ወንጌል አስተማሪ የሆኑ መሠረታዊ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል፡፡ በተለይ ምንም እንኳን የቤተክርስቲያን ሓላፊነት የእገሌና የእገሊት ተበሎ ባይወሰንም ቤተ ክርስቲያን ባላት የአገልግሎት መዋቅር መሠረት የሓላፊነትን ቦታ ይዘው ለሚያገለግሉ ሰዎች አትኩሮት ሊሰጡባቸው የሚገባቸውን ነጥቦች ይጠቁማል፡፡ ይህን ለማየት ያመቸን ዘንድ ከታሪኩ የመጀመያ ክፍል በመነሣት ዋና ዋና የሆኑ ዐሳቦችን በአትኩሮት መመርመር  ጠቃሚ ነው፡፡

በምሳሌያዊው ታሪክ መጀመሪያ ላይ የምናገኘው አንድ መንገድ ሊጀምር ያሰበ ሰው ከመሔዱ በፊት አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን ለአንዱ አምስት ለአንዱ ሁለት እንዲሁም ለሌላኛው አንድ መክሊት ነግደው ያተርፉበት ዘንድ እንደሰጣቸው ነው፡፡ ገና ከታሪኩ መጀመሪያ እንደምንረዳው የአገልጋዮቹ ጌታ ምንም እንኳን እርሱ ለመንገድ ቢዘጋጅም ሀብቱ ግን በተዘጋ ቤት ውስጥ ተቆልፎበት እንዲቀመጥ አልፈለገም፡፡ በዚህም አገልጋዮቹን ጠርቶ ገንዘቡን በአደራ ተቀብለው እንዲያተርፉበት ማዘዙን እንደማስረጃ ልናቀርብ እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ማትረፍ በመፈለጉ ብቻ ገንዘቡን ያለአግባብ አልበተነም፡፡ ነገር ግን ለእርሱ ቀረቤታ የነበራቸውን አገልጋዮቹን ጠርቶ ያውም እንደየችሎታቸው መጠን ሓላፊነቱ ሳይከብዳቸው እንዲሠሩበት ገንዘቡን አከፋፈላቸው፡፡

ይህ #ጌታ ቅንነትና ርኅራኄ የበዛለት እንደሆነ የሚያመላክተን ነገር አለ፡፡ ይኸውም ለአገልጋዮቹ ሓላፊነትን ቢሰጥም እንኳን ከእነርሱ ጋር በነበረው ቀረቤታ ማን ምን መሥራት ይችላል የሚለውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለእያንዳንዳቸው እንደ ሓላፊነት የመሸከም አቅማቸው አምስት ሁለት አንድ እያደረገ መስጠቱ ነው፡፡ ምናልባት ስስት ባልተላቀቀው ስሜት ለሚያስብ ሰው የዚህ #ጌታ መክሊት አሰጣጥ አድልዎ ያለበት ሊመስለው ይችላል፡፡ ታሪኩን እስከ መጨረሻው ብንከታተለው ግን የሚያሳየን የባለ መክሊቱን ባለቤት ቅንነት ነው፡፡ ቀጥለን እንደምናነበው ይህ #ጌታ ለአገልጋዮቹ አትርፉበት ብሎ መክሊቱን ሰጥቷቸው በሔደበት ሀገር አልቀረም፡፡ ይልቁንም እያንዳንዱ በተሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩበት ሊቆጣጠራቸው እንደመጣ እናነባለን፡፡ ስለዚህ አገልጋዮቹ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩ እንደሚጠይቃቸው እያወቀ ከአቅማቸው በላይ የሆነ መክሊትን በመስጠት ምን ሠርተው የተሰጣቸውን መክሊት ያህል ማትረፍ እንደሚችሉ በማሰብ እንዲጨነቁ አልፈለገም፡፡ በተቃራኒው የምናየው ያለምንም ጭንቀት ከአእምሯቸው በላይ ሳይሆን ባላቸው ኀይል ተጠቅመው መሥራትና ማትረፍ የሚችሉትን ያህል መክሊት እንደሰጣቸው ነው፡፡

ከብዙ ጊዜም በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩበት ሊቆጣጠራቸው ሲመጣ አምስት መክሊት ተቀብሎ የነበረው ሌላ አምስት እንዲሁም ሁለት መክሊት ተቀብሎ የነበረው ሌላ ሁለት መክሊት አትርፎ #ጌታቸው ፊት እንደቆሙ ያ ጌታም በእነዚህ አገልጋዮቹ ታማኝነት ተደስቶ ወደ ደስታው እንዳስገባቸው እናያለን፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ያ አንድ መክሊት ተቀብሎ የነበረው ምድርን ቆፍሮ ያተርፍባት ዘንድ የተሰጠችውን መክሊት እንደቀበረ ከዚህም አልፎ ምን አደረክባት ተብሎ ሲጠየቅ የአመጽ ንግግር እንደተናገረ በዚህ ከፊቱ ያዘነው ጌታውም ያን ክፉ አገልጋይ እንዲቀጣ እንዳደረገው አናነባለን፡፡

በዚህኛው ክፍል ከተጠቀሰው ታሪክ ሦስቱን አካላት ማለት የመክሊቱን ሰጪ ጌታ፣ በጎ የተባሉ አገልጋዮችና ክፉ እና ሰነፍ የተባለውን አገልጋይ በተናጥል እንመልከታቸው፡፡

1, #የአገልጋዮቹ_ጌታ፡–

ይህ ሰው ለገንዘቡ ጠንቃቃ ከመሆኑ ባሻገር በአገልጋዮቹ ላይ ሙሉ ሥልጣን እንዳለው እናያለን፡፡ በክፉው አገልጋይ ላይ ባለመታዘዙ ምክንያት የፈረደበትን ፍርድ /ልቅሶና ጥርስ ማፏጨት ወዳለበት በውጪ ወዳለ ጨለማ እንደአወጡት/ ስንመለከት የሚያሳየን የአገልጋዮቹን ጌታ ታላቅ ሥልጣን ነው፡፡ ምንም እንኳን ሥልጣኑ ጽኑ ቢሆንም ይህ ጌታ ፍርዱ ግን በእውነት ላይ የተመረኮዘ መሆኑን ደግሞ በድካማቸው ታግዘው በተሰጣቸው መክሊት ላተረፉት በጎ አገልጋዮች የሰጣቸውን ፍጹም ደስታ መጥቀስ ይቻላል፡፡

2, #በጎ_አገልጋዮች:-

በአገልጋዮቹ ጌታ በጎ አገልጋዮች የተባሉት አምስት መክሊት የተቀበለውና ሁለት መክሊት የተቀበለው ናቸው፡፡ እዚህ ጋር ማስተዋል የሚገባው እነዚህ ሁለቱ አገልጋዮች በጎ አገልጋዮች ለመባል ያበቃቸው አስቀድመው ብዙ ወይንም የተሻለ ቁጥር ያለው መክሊት ለመቀበል መብቃታቸው አይደለም፡፡ ጉዳዩ የመክሊቱ ቁጥር ሳይሆን በተሰጣቸው መክሊት መጠን የሚገባቸውን ያህል ደክመው ማትረፍ መቻላቸው ነው፡፡ ወይንም ያ ባለ አንድ መክሊት አገልጋይ ከሁለቱ ያሳነሰው ከአንድ በላይ መክሊት መቀበል የማይችል መሆኑ ሳይሆን በዚያችው በአንዷ መክሊት እንኳን መሥራት አለመቻሉ ነው፡፡

3, #ክፉና_ሰነፍ_አገልጋይ:-

ይህ ሰው የተጠቀሱ ሦስት መሠረታዊ ችግሮች አሉበት፡፡

የአገልጋዮቹ #ጌታ ወደ መንገድ ሊሔድ በተዘጋጀበት ወቅት አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዳቸው እንደችሎታቸው ገንዘቡን ሲሰጣቸው አትርፈው እንዲቆዩት ነው፡፡ ከላይ እንደተነገጋገርነው እንደ አቅማቸው መስጠቱም አቅማቸው በሚፈቅደው የሥራ ደረጃ እንዲሰማሩ በማሰብ ነበር፡፡ ይህ ሰነፍ አገልጋይ ግን ያደረገው ከታዘዘበት ዓላማ በተቃራኒው መልኩ ነው፡፡ ሊሠራበት የሚገባውን መክሊት ቀበረው፡፡ ይህም ለጌታው ትዕዛዝ ያለውን ቸልተኝነት ያሳያል፡፡
#ጌታው በመጣ ጊዜ አመጽ የተመላበት የሐሰት ንግግር ተናግሯል፡- ከሔደበት ቦታ ተመልሶ ጌታው በተሰጠው መክሊት ምን እንዳደረገ ሲጠይቀው «አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበትም የምትሰበሰብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ አውቃለሁ ስለፈራሁም ሔድሁና መክሊትህን በምድር ውስጥ ቀበርሁ፡፡» ሲል መለሰለት፡፡ ይህ ንግግር ከአመጽ ንግግርነቱ በተጨማሪ ውሸት አለበት፡፡ ምክንያቱም እርሱ እንዳለው #ጌታው ካልዘራበት የሚያጭድ ካልበተነበት የሚሰበሰብ ጨካኝ ሰው ቢሆን ኖሮ ያደርግ የነበረው ምንም መክሊት ሳይሰጠው ከነትርፉ ሁለት መክሊቶችን ይጠይቀው ነበር፡፡ ነገር ግን ተጽፎ የምናነበው ትርፉን ከመጠየቅ በፊት አንድ መክሊት ሰጥቶት እንደነበረ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አስቀድሞ ገንዘቡን ዘርቶ ነበር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ #ጌታ ዘርቷልና ማጨድ ይገባዋል፤ በትኗልና መሰብሰብም መብቱ ነው፡፡
እርሱ መሥራት ሲሳነው እንኳን ዕድሉን ለሌሎች አልሰጠም፡- ይህ ሰው የተሰጠው መክሊት በትርፍ ሊመለስ እንደሚገባው ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ምክንያቱም ገና ሲቀበል ከጌታው የተቀበለው ትዕዛዝ ነውና፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን መውጣት መውረዱ ቢከብደውም ወጥተው ወርደው ማትረፍ ለሚችሉ ሰዎች አለመስጠቱ ተጨማሪ ጥፋቱ ነው፡፡ ይህን እንዳያደርግ ያሰረው ደግሞ ውስጡ የተቀረጸው የአመጽ መንፈስ ነው፡፡ #ጌታው መጥቶ ስለ ትርፉ ሲጠይቀው የሚመልስለትን ረብ የለሽ ምክንያት እንደ መከላከያ አድርጎ ማሰቡ አእምሮው ሌላ አማራጭ እንዳያስብ የዘጋበት ይመስላል፡፡

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 19:41


#ደብረ_ዘይት
ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ነው፡፡ ቦታው ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ የሚገኝ የወይራ ዛፍ የበዛበት ተራራ ሲሆን ስሙም ከወይራ ዛፉ:- ደብረ ዘይት (የወይራ ዛፍ ተራራ) በመሰኘት ተገኝቷል። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ደብረ ዘይት በዓል ሆኖ የሚከበርበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረዘይት ተራራ ላይ ሳለ ለቅዱሳን ደቀመዛሙርቱ ስለ ዓለም ፍጻሜ እና ስለ ዳግም ምጽአቱ ስላስተማራቸዉ በጌታችን ትምህርት መሠረት ነገረ ምጽአቱን እንድናስታውስ ወይም እያሰብን እንድንዘጋጅ ለማድረግ ነው።

ስለ ዓለም መጨረሻና ስለ ዳግም ምጽአቱ ምልክቶች ምን እንደሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ላይ በሦስት መሠረታዊ ክፍሎች ከፍሎ ጽፎልናል፡፡

#ሃይማኖታዊ_ምልክቶች

እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ” /ማቴ.24፥5/፡፡

#ፖለቲካዊ_ምልክቶች

“ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ” /ማቴ.24፥6/፡፡
• “ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና” /ማቴ.24፥7/፡፡

#ተፈጥሯዊ_ምልክቶች

“ራብም ቸነፈርም የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል” /ማቴ.24፥7/፡፡

ከላይ ያየናቸውን ምልክቶች በዓለማችን ላይ ዕለት ተዕለት የምናየው የምንሰማው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ የነገራቸውን ምልክቶች የቤተ ክርስቲያናችን አራት አይና ሊቃውንት የወንጌሉን ገጸ ንባብ እንዲህ ብለው ያመሰጥሩታል፡፡

“እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያዎች ናቸው” /ማቴ.24፥8/፡፡

ምጥ ሲመጣ አስቀድሞ የምጡ መጀመሪያ ሕመም (ጣር) እንዳለ ሁሉ የዓለምም ፍጻሜ በጣር ነው የሚጀምረው። ይህንንም ጌታችን በግልጽ አስረድቶናል፦ ጦርና የጦር ወሬ መሰማት፣ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ መነሳት፣ ርሃብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ መታየት ለዓለም ፍጻሜ የምጥ ጣር መጀመሪያዎች ናቸዉ። እነዚህ ነገሮች በሁሉም ቦታ በአንድ ጊዜ ላይከሰቱ ይችላሉ፤ ነገር ግን በልዩ ልዩ ቦታዎች ለብዙ ዘመናት ታይተዋል፤ እየታዩም ናቸው።

“ስለ ስሜ በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ” /ማቴ.24፥9/፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ስሜ ክርስቲያኖች በመሆናችሁ በዓለም ዘንድ ትጠላላችሁ ብሎናል። ዓለም ክፉ ስለሚሠራ የጥሩ ነገር ተቃራኒ ሆኖ ለብዙ ዘመናት ቆይቷል። ጌታችን “ብርሃንም ወደ ዓለም ስለመጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፣ሥራዉም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል” /ዮሐ. 3፥19-21/ እንዳለን በክፉ ሥራ ውስጥ ያለው ይህ ዓለም በጎ ሥራ የሚሠሩትን የክርስቶስን ተከታዮች ይጠላል። ጨለማ ብርሃንን ብርሃንም ጨለማን እንደሚጠላ፤ ይህ ዓለም እኛን እንዲጠላን፣ እኛ ክርስቲያኖች ደግሞ ይህንን ዓለም ልንጠላው ይገባል።
አሁን ባለንበት ዘመን ክርስትና እየተጠላ፣ እየተናቀ ነው ያለው። “ባደጉት” ዓለማት ባዶ አብያተ መቅደሶች ቀርተው እነሆ እንመለከታቸዋለን፤ ትውልዱ በዓለም ስሜትና በሥጋ ፈቃድ ብቻ እየሔደ ነው። ክርስቲያን ነን በሚሉትም አውሮፓውያን ዘንድ የአንገት በላይ የማስመሰል ክርስትና እንጂ እንደ ቅዱስ ቃሉ የሚጓዝ አማኝ ማግኘት አይቻልም። እውነተኞች አይወደዱም፤ ይገፋሉ፤ ይናቃሉ። ሁኔታው የዘመኑ ፍጻሜ እጅግ እየቀረበ መምጣቱን በእርግጥ ያስረዳል።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህም በላይ “ስለ ስሜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችሁማል” ብሏል። ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ማንንም ሳይበድሉ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ በልዩ ልዩ ሀገራት ክርስቲያኖች ሰማዕትነትን እስከ አሁን ድረስ እየተቀበሉ ነው፡፡ቅዱስ ጳዉሎስ “ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን” /ሮሜ 8፥36/ እንዳለው። ይህ በቅዱሱ በክርስቶስ ስም መጠላትና መከራ መቀበል ከዓለም የሚጠበቅ የፍጻሜዉ ዘመን ምልክት መሆኑን አውቀን መዘጋጀትና ከሐዋርያው ጋር “በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን” /ሮሜ 8፥37/ እያልን በእምነታችን ጸንተን መጋደል ይገባናል።

የክርስቲያኖች ቁጥር እያነሰ መምጣት፣ የአብያተ ክርስቲያናት መዘጋት፣ ሰው ሰው የሚያሰኘውን ክብርና ሞገስ ትቶ በግብሩ እንስሳትን ሲመስል የቅድስና ሕይወት ሲጠላና ሲናቅ፤ በአንጻሩ ደግሞ የሰው ልጅ ለረከሰው ለዚህ ዓለም ምኞትና ፈቃድ ሲገዛ ስናይ የዚህ ዓለም ፍጻሜ ጊዜው እየደረሰ መሆኑን አውቀን፤ ኖኅ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ቢኖርም ራሱን በቅድስና ጠብቆ እንደኖረ /ዘፍ.6-8/፤ ሎጥም እንዲሁ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ሲኖር በነርሱ ኃጢአት እንዳልተባበረ /ዘፍ. 19/ ከዚህ ዓለም ክፉ ሥራ ተለይተን ራሳችንን በቅድስና በመጠበቅ እንጋደል። ዓለሙ ስለ እምነታችን ቢጠላንም እኛም ስለ ክፉ ሥራው ንቀነው መኖር የግድ መሆኑን እንወቅ እንጂ ስለ እምነት፣ ስለ ቅድስናም ከዓለም በጎ ነገር አንጠብቅ። በተለያዩ ሁኔታዎች የሚደርሱብንን ፈተናዎች ሁሉ በትዕግስት እንቀበላቸው እንጂ በማማረር አንዘን፤ ምክንያቱም ስለ ስሜ በዓለም ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ ተብለናልና።

“የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል!” ማቴ.24፥15/፡፡

ዓለም ራሱን በማርከስ ብቻ ሳይወሰን በፍጻሜ ዘመን በተቀደሰው ስፍራ እንኳን ሳይቀር የጥፋትን ርኩሰት ያቆማል። የተቀደሰው ስፍራ የተባለው በተቀደሰ ሃይማኖት የሚኖሩትን ሀገራት፣ ሕዝቦች የሚመለከት ነው። እንደ ኢትዮጵያ የመሳሰሉትን ሀገራት ዲያብሎስ በመልእክተኞቹ ላይ አድሮ በብዙ ርኩሰት ተፈታትኗቸዋል፤ እየተፈታተናቸውም ነው። የየሀገራቱን እምነትና ታሪክ ለማጥፋት ጥሯል፤ ብዙውንም የቅድስና ሥርዓት በርዞአል፤ የቻለውንም ከነጭራሹ አጥፍቶታል። አሁን እንኳ አምልኮተ እግዚአብሔር በሚፈጸምባቸዉ ቅዱሳት መካናትና ገዳማት ሳይቀር በልዩ ልዩ ምክንያት የጥፋት ርኩሰት አዉጇል። ይህም የፍጻሜ ዘመኑ አንዱ ምልክት ስለሆነ አንባቢዉ ያስተዉል እንደተባለ የዘመኑን መፍጠን የጊዜውን መድረስ በመረዳት መዘጋጀት ይገባናል።

“ብዙ ሐሰተኛዎች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ” /ማቴ.24፥11/፡፡

ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት በየዘመኑ ተነስተው እውነተኛይቱን ቤተ ክርስቲያን ታግለዋታል፤ ሊያጠፏት ባይችሉም እንኳን ብዙ ልጆቿን ነጥቀው ወስደውባታል። የነዚህን ሐሰተኞች ሠራተኞች አመጣጥ ከባድ የሚያደርገው በተአምራትና በድንቅ ምልክቶች መምጣታቸው ነው። ጌታችን እንደተናገረ “ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳን እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ” /ማቴ.24፥24/ ስለዚህ በምትሐታዊ ምልክቶቻቸው የብዙ የዋሐንን ልብ በማታለል ከተቀደሰ እምነታቸው እያስኮበለሉ አጥፍተዋቸዋል፤ በማጥፋትም ላይ ይገኛሉ። ስለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ “ወዳጆች ሆይ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነዉ እንደሆነ መርምሩ”/1ዮሐ.

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 19:38


꧁ ༒ ꧂ የበገና ምሳሌነት የመጨረሻ ክፍል ꧁༒ ꧂

12. ከድምጽ ሳጥኑ (ገበቴው) ጀርባ ላይ ያለው ቀዳዳ (የመስቀል ቅርጽ ምልክት)
ይህ ከበገናው ጀርባ የሳኦል ጦር የበሳው ቀዳዳ ቅዱስ ዳዊትን መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ነግሮት ከተወረወረበት ጦር በበገናው አማካኝነት መክቶ ስለመዳኑ ለማስታወሻ የተደረገ ምልክት ነው። ይህንን ታሪክ ለማጠየቅ ብዙዎቹ የጥንት የበገና ሠሪዎች ከበገናቸው ጀርባ ክብ ብስ በማድረግ በገናቸውን ይሠሩ ነበር።
ብዙዎቹ የቅርብ ጊዜ በገና ሠሪዎች ደግሞ ከጀርባ ያለውን ብስ የመስቀል ቅርጽ ወይንም የድምጽ ሳጥኑን ድፍን አድርገው ያበጁታል።
አንዳንድ የበገና አባቶች፣ የበገና ሠሪዎች እና መምህራን የድምፅ ሳጥን የእመቤታችን የቅድስት የድንግል ማርያም፣ የማኅፀነ ድንግል ይልቁንም የድንግልናዋ ምሳሌ በመሆኑ፤ የድምጽ ሳጥኑ ምንም ዓይነት ቀዳዳ እና ክፍተት ሊኖረው አይገባምና ከበገናው ጀርባ ያለውን ቀዳዳ የተቀረጸ የመስቀል ምልክት ብቻ አድርገው ከውጭ በመለጠፍ(በመፈልፈል) የበገናቸውን ድምጽ ሳጥን ድፍን አድርገው ይሠራሉ።
ሌሎች ደግሞ ከበገናው ድምጽ ሳጥን ጀርባ ያለውን ብስ የመስቀል ቅርጽ እንዲኖረው አድርገው ቀዳዳውን ያበጁታል። ቀዳዳው የመስቀል ቅርጽ እንዲኖረው መደረጉ ቅዱስ ዳዊት በበገናው ምከታ ከሳዖል ጦር (ፍላፃ) እንደዳነ፤ በሐዲስ ኪዳንም በመስቀሉ ያመንን እኛ ክርስቲያኖች መስቀል ከድያብሎስ ፍላፃ የዳንበት፤ የምንድንበት ምልክታችን የመሆኑ ምሳሌ ነው። አባቶቻችን እንዳስተማሩን ይህንን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን መስቀል በዘወትር ጸሎታችን

["… መስቀል ኃይልነ መስቀል ጽንዕነ መስቀል ቤዛነ መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ አይሁድ ክህዱ ንሕነሰ አመነ
ወእለ አመነ በኃይለ መስቀሉ ድኅነ፤ … መስቀል ኃይላችን፣ ጽንዓችን፣ ቤዛችን፣ የነፍሳችን መዳኛ ነው፡፡
አይሁድ ይክዱታል፤ እኛ ግን እናምንበታለን፡፡ ያመነውም እኛ በመስቀሉ ኃይል እንድናለን፤ ድነናልም።"]
እያልን ለመስቀሉ ያለንን ክብር እንገልጻለንና፤ በክርስቶስ መስቀል ኃይል መዳናችንንም ስንመሰክር እንኖራለንና፣ እንዲሁም በበገናችንም ዘወትር ስለ ነገረ መስቀሉ እንዘምራለና፣ እንጸልያለንና ይሄን ለማጠየቅ ከበገናው ጀርባ ያለውን ቀዳዳ የመስቀል ቅርጽ እንዲኖረው ተደርጓል በማለት ያስረዳሉ።
(ከላይ በተነሱት ኹለት ሐሳቦች ላይ የበገና አባቶችን፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን መጠየቅና የበለጠ ጥናት ማድረግ ያሻዋል።)"

የበገና ዓይነቶች በመጽሐፍ ቅዱስ
በገና በመጽሐፍ ቅዱስ ዓይነቱ እና ቅርጹ በውል ባይገለጽም ባለ ስምንት አውታር እና ባለ ዐሥር አውታር ያላቸው በገናዎች እንደነበሩ ያስረዳናል።

ባለ ስምንት አውታር በገና
[ዜና መዋዕል ቀዳማዊ ፲፭፥ቁ ፲፮-፳፩]
• [፲፮]. ዳዊትም በዜማ ዕቃ በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን ወንድሞቻቸውን ይሾሙ ዘንድ ለሌዋውያን አለቃዎች ተናገረ።
• [፲፯]. ሌዋውያኑም የኢዮኤልን ልጅ ኤማንን፥ ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሣፍን፥ ከወንድሞቻቸውም ከሜራሪ ልጆች የቂሳን ልጅ ኤታንን።
• [፲፰]. ከነርሱም ጋራ በኹለተኛው ተራ የኾኑትን ወንድሞቻቸውን ዘካርያስን፥ ቤንን፥ ያዝኤልን፥ ሰሚራሞትን፥ ይሒኤልን፥ ዑኒን፥ ኤልያብን፥ በናያስን፥ መዕሴያን፥ መቲትያን፥ ኤሊፍሌሁን፥ ሚቅንያን፥ በረኛዎችንም ዖቤድኤዶምንና ይዒኤልን አቆሙ
• [፲፱]. መዘምራንም ኤማንና አሣፍ ኤታንም በናስ ጸናጽል ከፍ አድርገው ያሰሙ ነበር።
• [፳]. ዘካርያስ፥ ዓዝዔል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ ዑኒ፥ ኤልያብ፥ መዕሴያ፥ በናያስ በመሰንቆ ምስጢር ነገር ያዜሙ ነበር። መቲትያ፥ ኤልፍሌሁ፥ ሚቅኒያ፥ ዖቤድ ኤዶም፥ ይዒኤል፥ ዓዛዝያ ስምንት አውታር ባለው በገና ይዘምሩ ነበር።

ባለ ዐሥር አውታር በገና
• [መዝሙረ ዳዊት ፴፪፥፪] እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፥ ዐሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት።
• [መዝሙረ ዳዊት ፻፵፫፥፱] አቤቱ፥ ዐዲስ ቅኔ እቀኝልኻለኹ ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልኻለኹ።
• [መዝሙረ ዳዊት ፺፩፥ቁ ፩-፫]
፩. እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምኽም ዝማሬ ማቅረብ፤
፪. በማለዳ ምሕረትን፥ በሌሊትም እውነትኽን ማውራት፤ ዐሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋራም በመሰንቆ"

➥ ወስብሐት ለእግዚአብሔር 
     ይቆየን

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 19:38


꧁ ༒ ꧂ የበገና ምሳሌነት ቀጣይ ክፍል አራት ꧁༒ ꧂

6. የድምጽ ሳጥን (ገበቴ)
ከአንድ ወጥ እንጨት ተፈልፍሎ(ገበቴ) ወይም የጣውላ እንጨቶችን በማገጣጠም እና የደረቀ ቆዳ ተፍቆና ተዳምጦ በማልበስ የሚሠራ ነው። የሚለብሰው ቆዳም አገልግሎት ድምፅን ማስተላለፍ ሲሆን፤ የበገናው ድምፅ የሚወጣውም ከዚህ ሳጥን ነው።
ምስጢሩ፦ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ። ከድምጽ ሳጥኑ (ገበቴው) የበገናው ድምጽ እንደሚገኝ ከእመቤታችን አካላዊ ቃል ወልድ ጌታችን መድኃኒታችን እና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገኘቱን ያጠይቃል።

7. በርኩማ፦
ትንሽ ዱካ መሳይ ከእንጨት የሚሠራ ሲሆን፣ይህም ዐሥሩን እንዚራዎች ለማስቀመጥ ያገለግላል። በድምፅ ሳጥኑና በአውታሩ መካከል በመግባት እንዚራና አውታሩ በርሱ ላይ ተቀናብረው የንዝረትን ድምፅ እንዲፈጥሩ ያገለግላል። ይህም ድምፅ ደግሞ ወደ ገበቴው ገብቶ ጎልቶ እንዲሰማ ያደርጋል። ምስጢሩ፦ ነብዩ ሙሴ ዐሥርቱን ትዕዛዛት ከእግዚአብሔር የተቀበለበት የደብረሲና ተራራ ምሳሌ ነው።

8. መወጠሪያ
ከእንጨት የሚሠራ ሲሆን ከታችኛው የበገና ክፍል የሚገኝ ሆኖ አውታሮቹን ከቀንበሩ ጋር ለመወጠር ይጠቅማል። ምስጢሩ፦ መወጠርያ በሰዎች መኖርያ /ምድር/ ምሳሌ ነው፡፡ አንድም፦ መወጠሪያ በምድር ላይ ያሉ የአዳም ዘር (የሰው ልጆች) ምሳሌ ነው።
ዐሥሩ አውታሮች ቀንበሩንና፣ መቃኛውን፣ መወጠሪያውን ማገናኘታቸው አንዳች ትምህርት ያለው ነው። ይህም "የሰው ልጆች (መወጠሪያ) በትዕዛዛተ እግዚአብሔር (አውታር) መሰላልነት ከምድር መኖሪያቸው (መወጠሪያ) ተጋድሎዋቸውን ጨርሰው (መቃኛ) ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባታቸው እና ከፈጣሪያቸው እግዚአብሔር (ቀንበር) ጋር ለዘለዓለም በደስታ የመኖራቸው ምሳሌ ነው።"

የመወጠሪያ ጠፍር
• ዐሥሩን አውታሮችን የያዘ ከእንጨት የተሠራውን አግዳሚ መወጠሪያ ከግራ እና ከቀኝ በመሆን ከበገናው የድምጽ ሳጥን ላይ ወጥሮ የያዘ ከቆዳ የሚሠራ ጠፍር ነው።
• የብዙዎቹ የጥንት በገኖች መወጠሪያ ጠፍር የድምጽ ሳጥኑን(ገበቴውን) ከላይ ያለበሰውን ቆዳ በመብሳት ከውስጠኛው የድምጽ ሳጥን ክፍል ላይ የሚታሰሩ(የሚመቱ) ሲሆን በአሁን ጊዜ ያሉት በገናዎች ደግሞ ይህንኑ ጠፍር ከድምጽ ሳጥኑ የውጪኛው ክፍል ላይ በምስማር የሚመታ ተደርገው ይበጃሉ።
• አንጋፋው የበገና ደርዳሪ መጋቤ ስብሐት ዓለሙ አጋ ስለ በገና አካል ክፍሎች በዘመሩት የበገና መዝሙራቸው ላይ ስለ መወጠሪያ ጠፍር እንዲህ ብለዋል።
 አውታሩ ግና የያዘውን እንጨት፣
 መስሎታል በድንግል መሰረተ ሕይወት።
 የዚህን የመያዣውን ጠፍር፣
 መስሎታል በኪሩቤል አምሳል።
ምስጢሩ፦ የእግዚአብሔርን ዙፋን የተሸከሙት የኪሩቤል (ኪሩብ) ምሳሌ።"

9. እንዚራ
ከቊርጥራጭ ቆዳዎች የሚሠራ ሲሆን በገና በሚደረደርበት ጊዜ አውታሮቹ ድዝዝዝ.... እና ጥዝዝዝ.... የሚል የንዝረት ድምፅ እንዲያወጡ የሚያደርግ ነው። ቦታውም በርኩማ ላይ ሲሆን፤ አውታሮቹ በርኩማ ላይ አርፈው በሚያልፉበት በሚሸፍኑት ርቀት አማካይ ላይ በአውታሩና በበርኩማው መካከል በመግባት ከፍና ዝቅ አድርጎ በማስተካከል ተፈላጊውን የንዝረት ድምፅ እንዲሰጡ ያደርጋል።
ምስጢሩ፦
• እንዚራ ተጋድሎ ላይ ባሉ ክርስቲያኖች ይመሰላል፡፡
• እንዚራ በዐሥሩ አውታር ላይ እንዳሉ፤ ክርስቲያኖችም ዐሥሩ አውታር የተመሰሉባቸውን
አጠቃላይ ትዕዛዛተ እግዚአብሔርን መሪ በማድረግ፤ በዓለም ኑሯቸው መንፈሳዊ ሕይወትን ለማበልፀግ ይጋደላሉና ነው፡፡

10. ድሕንጻ(መግረፊያ)
ከቀንድ ወይንም ከእንጨት የሚሠራ መግረፊያ ሆኖ በግራ ምሰሶ ላይ የሚታሰር ሲሆን አገልግሎቱም ዐሥሩን አውታሮች ከወዲያ ወዲህ እያለ በመግረፍ ልዩ ድምፅ እንዲሠጡ የሚያደርግ ነው። "በድኅንጻ መንፈስ ዝብጢ አውታረ መሰንቆሁ ለልብየ ወአስተንፍሲ ውስተ አፉየ ከመ እኩን እንዚራሁ ለበኵርኪ...." እንዲል [መጽሐፈ ሰዓታት]
ምስጢሩ፦ድሕንጻ በክርስቶስ ይመሰላል፡፡ ድኅንጻ ዐሥሩን አውታሮች እየተመላለሰ እንደሚገርፋቸው፤ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስም በብሉይ ኪዳን የሰጣቸውን ዐሥሩን ትዕዛዛት በሐዲስ ኪዳንም አጽንቷልና።

የድሕንጻ ጠፍር
የበገናውን ድሕንጻ በአንደኛው ጫፍ በኩል አንጠልጥሎ በሌላኛው ጫፍ ደግሞ ከግራ ምሰሶ ላይ ሸምቅቆ በመያዝ ድሕንጻውን ከበገናው ጋር በአንድነት አስተሳስሮ የሚኖር ጠፍር ነው። አንጋፋው የበገና ደርዳሪ መጋቤ ስብሐት ዓለሙ አጋ ስለ በገና አካል ክፍሎች በዘመሩት የበገና መዝሙራቸው ላይ ስለ ድሕንጻ ጠፍር እንዲህ ብለዋል።
 ድሕንጻውም የዚህ የዐሥሩ አውታር፣
 ቅዱስ ቅዱስ የሠማይ ጌታ የምድር።
 የታሪኩ የድሕንጻው ጠፍር፣
 መስሎታል በፊታቸው ወርቅ አምሳል።
 ( የዚህን ምስጢር የበገና አባቶችን እና ሊቃውንተ ቤተ-ክርስቲያን መጠየቅ ያሻዋል)

11. ማፈኛ
ማፈኛ፦ የድምጽ ሳጥኑን (ገበቴውን) ያለበሰውን ቆዳ ዙሪያውን ወጥረው በመያዝ ከገበቴው ላይ ረግቶ እንዲቀመጥ እና እንዳይረግብ ያደረገው ጥልፍልፍ ስፌት ነው።
ምስጢሩ፦
• ምድርን ተሸክመው ባሉ ብሔሞት እና ሌዋታን የሚባሉ ግሩማን ዘንዶዎች ምሳሌ ነው።
• አንዳንድ መምህራን ደግሞ ማፈኛ ማለት መወጠሪያ ማለት ነው ይላሉ...
(በዚህ ሐሳብ ላይ አባቶችን መጠየቅ እና የበለጠ ጥናት ማድረግ ያሻዋል።)"

➥ ይቆየን

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 19:23


꧁༒꧂ የበገና ምሳሌነት ቀጣይ ክፍል ሦስት ꧁༒꧂

➥ አንድም የበገና አውታሮች የሦስቱ ዓይነት የቅዱስ ያሬድ የዜማ ስልቶች (ድምጸ ዜማ) ምሳሌ፡፡ እነዚህም ግዕዝ፣ አራራይ፣ ዕዝል ሲሆኑ የእያንዳንዷ የበገና አውታርን ይወክላሉ፡፡
በቊጥር እና በፊደል ሲተነተኑ (፩=ግ፣ ፪=ዕ፣ ፫=ዝ፣ ፬=አ፣ ፭=ራ፣ ፮=ራ፣ ፯=ይ፣ ፰=ዕ፣ ፱=ዝ፣ ፲=ል) ይሆናል፡
በፊደላት ብቻ ያለ ቊጥር ሲጻፍ (ግ፣ ዕ፣ ዝ፣ አ፣ ራ፣ ራ፣ ይ፣ ዕ፣ ዝ፣ ል)
ዕዝል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ሆኖ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከተወለደ በኋላ በቅዱስ ያሬድ ጊዜ ነው የመጣው። ዕዝል ከላይ የስም ተራውን ሳይጠብቅ መንፈስ ቅዱስን አልፎ በወልድ የተሰየመው ለዚህ ነው በማለት ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ትርጉማቸው፦
ግዕዝ፦ በአብ ዕዝል፦ በወልድ አራራይ፦ በመንፈስ ቅዱስ፣
✓ አንድም ለቅዱስ ያሬድ ድምጸ ዜማን ባቀበሉት የ ፫ቱ ዓይነት በራሪ ወፎች ምሳሌ
✓ አንድም የበገና አውታሮች የዐሥሩ የስሜት ሕዋሳት ምሳሌ
ግነዩ ለእግዚአብሔር በመሰንቆ ወበመዝሙር ዘዐሥርቱ አውታሪሁ።
"እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት ዐሥር አውታር ባለው በበገና ዘምሩለት" [መዝ ፴፪/፴፫፡፪]
ወበመዝሙር ዘዐሥርቱ አውታሪሁ። ትርጉሙም:-
ዐሥር አውታር ያለውን በገና እየደረደራችሁ ተገዙ። [ቆላ ፫፡፲፮]
አንድም ፡ ዐሥር ሕዋሳት ባለው ሰውነት ምግባር ይዛችሁ ተገዙ።
አንድም ፡ ሕግጋቱ ዐሥር በሚሆኑ በኦሪት ጸንታችሁ በማዓልትም በሌሊትም ተገዙ።
አንድም ፡ ወበስብሐተ ሐዲስ ቃል ሥጋ ሆነ እያላችሁ አመስግኑ።"
➥ የስሜት ሕዋሳት
 ውጫዊ ሕዋሳት ውሳጣዊ ሕዋሳት፤ ዓይን ዓይነ ልቦና ፤ አፍንጫ አንፈ ልቦና ፤ ጆሮ እዝነ ልቦና ፤ ምላስ አፈ ልቦና ፤ መዳፍ እደ ልቦና
✓ አንድም የበገና አዉታሮች የዐሥሩ የስሜት ሕዋሳት ምሳሌ አፍንጫ፣ ጆሮ፣ ምላስ እና አንደበት፣ ብልት፣ ኹለት ዐይን፣ ኹለት እጅ፣ ኹለት እግር እነዚህን የስሜት ሕዋሳት ዐሥር በሚሆኑ በአሪት ሕግጋት አጽንታችሁ በማዓልትም በሌሊትም ተገዙ።
✓ አንድም የበገና አውታሮች የ አስሩ የቅዱስ ዳዊት መዝሙራት አርዕስት ምሳሌ ለቅዱስ ዳዊት ከተሰጠት ሀብቶች መሐከል ሀብተ ትንቢት ነው። ይህም ፻፶ውን መዝሙሮች አስተካክሎ ለጸሎት ለምስጋና ማቅረቡ ነው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ፻፶ ውን መዝሙሮች በዐሥር አርዕስት ከፋፍሎ አስቀምጧል፡፡ እነዚህም፡-
o ተግሳጽ ለኩሎ o ትንቢት በእንተ ክርስቶስ o ትንቢት በእንተ ርዕሱ o ትንቢት በእንተ መነናዊያን o ትንቢት በእንተ ትሩፋት
o ትንቢት በእንተ ሕዝቅያስ o ትንቢት በእንተ ኤርምያስ o ትንቢት በእንተ መቃብያን o ትንቢት በእንተ ዘለፋ ካህናት
o ትንቢት በእንተ ሰሎሞን ወልዱ"
"✓ አንድም የበገና አውታሮች የዐሥሩ የቅዱሳን ማዕረጋት ምሳሌ
• ዐሥር ቊጥር በዕብራውያን የፍጹምነት መገለጫ በመሆኑ ፍጹምነት ደረጃ መድረሳቸውን ለመግለጥ
• አንድም ዐሥርቱን ሕግጋቱን በመፈጸም የሚገኝ በመሆኑ
• አንድም በዐሥርቱ የስሜት ሕዋሳት ንጹህነት የሚገኙ በመሆኑ።
➥ ዐሥሩ የቅዱሳን ማዕረጋት በሦስት ክፍል ይመደባሉ
• ንጽሐ ሥጋ፦ በውስጡ ሦስት ማዕረጋት ይገኛሉ። ወጣንያን ናቸው ባለ ሰላሳ(፴) ፍሬ
• ንጽሐ ነፍስ፦ በውስጡ አራት ማዕረጋት ይገኛሉ። ማዕከላዊያን ናቸው ባለ ስልሳ(፷) ፍሬ
• ንጽሐ ልቦና፦ በውስጡ ሦስት ማዕረጋት ይገኛሉ። ፍጹማን ናቸው ባለ መቶ(፻) ፍሬ
➥ ንጽሐ ሥጋ(ወጣኒያን)
• ጽማዌ፦ ዝምታ ወይም አውቆ ፈቅዶ በመናገርና በመቀባጠር ከሚመጣው ኃጢአት መቆጠብ።
• ልባዌ፦ ልብ ማድረግ።
• ጣዕመ ዝማሬ:- ሳይሰልቹና ሳይቸኩሉ ምስጢርና ትርጓሜውን እያወጡ እያወረዱ በንቁ ሕሊና ማመስገንና መጸለይ።
➥ ንጽሐ ነፍስ(ማዕከላውያን)
• አንብዕ:- ስለ ራስ ኃጢአት ማልቀስ፣ ስለ ወገን ማንባት፣ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጽዋትወ መከራ እያሰቡ፣ በእመቤታችን ላይ የደረሰውን ዐምስቱ ሀዘናትን እያሰቡ ማዘን።
• ሑሰት:- ባሉበት ስፍራ ሆነው ሌላ ቦታ የሚደረገውን ነገር ማወቅ።
• ኩነኔ:- ሥጋን ለነፍስ ማስገዛት።
• ፍቅር:- ሰውን ሁሉ በአንድ ዐይን መመልከት።
➥ ንጽሐ ልቦና(ፍጹማን)
• ንጻሬ መላእክት:- ቅዱሳን መላእክትን በዐይነ ሥጋ መመልከት
• ተሰጥሞ ብርሃን:- እግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ በሆነው በሚያስደንቀው ብርሃን ውስጥ መዋኘት።
• ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ:-(ከዊነ እሳት):- ሰውነት ለአጋንንት የሚያቃጥልና የማያስቀርብ መሆን።"
✓ አንድም የበገና አውታሮች የዐሥርቱ ዓለመ መላእክት(ከተሞች) ምሳሌ ነው። እነዚህም ከተሞች በሦስት ሰማያት ይገኛሉ።
• ኤረር (፩ኛ ሰማይ) • ራማ (፪ኛ ሰማይ) • ኢዮር (፫ኛ ሰማይ)
✓ አንድም የበገና አዉታሮች የዐሥሩ የዜማ ምልክቶች ምሳሌ ነው። እነዚህም፦
• ድፋት • ሂደት • ቅናት • ይዘት • ቁርጥ • ጭረት • ርክርክ • ደረት • ድርስ • አንብር"
➥ አጥኚዎች አባታችን ቅዱስ ዳዊት ይደረድርበት የነበረው በገና ባለ ፲፪ አውታር እንደነበረ በመላምት ያስቀመጡበት መረጃዎች
• እስራኤላውያን ናቫል የሚባል የዜማ መሣሪያን ቅዱስ ዳዊት የደረደረበት በገና ነው ብለው ያምናሉ
• ናቫል የተባለው የዜማ መሳሪያንም ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ይውል እንደነበረም ያስረዳሉ
• ፲፪ አውታሮችም አሉት። ከዚህ ተነስተው በዘርፉ ያሉ የጥናት እና የምርምር ባለሙያዎች በገና ባለ ፲፪ አውታር የሆነ የዜማ መሣሪያ ነው የሚል መላምት አስቀምጠዋል። ባሕረ ጥበባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም እንዲህ ለሚሉ መላምቶች ምሳሌ መስላ አስቀምጣልናለች ።
የ ፲፪ ቱ የበገና አዉታሮች ምሳሌነትም እንደሚከተለው ታስቀምጣለች
• በአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ። እኒህን ቢቆጥሯቸው ፲፪ ይመጣሉ።
• አንድም በቅድስት ድንግል ማርያም ይመሰላሉ። እኒህን ቢቆጥሯቸው ፲፪ ይመጣሉ።
• አንድም፦ የ፲፪ቱ ደቂቀ ያዕቆብ (ነገደ እሥራኤል) ምሳሌ።
• አንድም፦ የ፲፪ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት ምሳሌ።

➥ይቆየን...

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 19:23


꧁༒꧂ የበገና ምሳሌነት ቀጣይ ክፍል꧁༒꧂

➥ አንድም ቀርነ በግዕ የመስቀል ምሳሌ

ከላይ እንደገለጽነው ቀንድ አንድም በጠላት ላይ መበረታቻ አንድም ለጠላት ድል የማድረጊያ ትእምርት/ምልክት ነው። መስቀል የጌታ(የበጉ) ቀንድ ይባላል። በግ ቀንዱን ለመውጋት አይጠቀምበትም (ጠላትን አይወጋበትም) እንዲሁ ለትእምርት የተቀመጠ ነው እንጂ። እንዲህ ስንል እንዳይጸንብን "ምሳሌ ዘየሐጽጽን ልብ እንበል። በግ ነጣቂ ተኩላ በመጣበት ጊዜ ከዚያ ቦታ ይሸሻል እንጂ ዞሮ ጠላቱን እንደማይወጋ እንዲሁ ጠላት ዲያብሎስ በልበ አይሁድ አድሮ በግዕ በተባለ ጌታ ላይ ነገር በሠራበት መከራ ባጸናበት ጊዜ ቀንድ በተባለ መስቀሉ ሊወጋውና ሊጥለው እየተቻለው "አምላኪየ አምላኪየ ነጽረኒ ወለምንት ኃደገኒ፣ ጸማህኩ፣ ኦ አባ ኅድግ ሎሙ እስመ በዘኢየአምሩ ይገብሩ" እያለ በመሸሽ አምሳል ይለምንላቸው ራሱ ዲያብሎስንም ያታልለው ነበር እንጂ ቀጥቅጦ ያለፈቃዱ በኃይል አልገዛውም። ነገር ግን ጠላት የበጉን ቀንድ እያየ ቀንድ አለውና ይወጋኛል ብሎ እየፈራ በበጉ ላይ እንዳይበረታታበት እንዲሁ ዲያብሎስም የመስቀሉን ኃይልና ትእምርትነት አንድም አምላክነቱን ከሩቅ እያየ ፈራ ተባ እያለ ክብር ይግባውና ዕሩቅ ብእሲ መስሎት "ሔጄ የዚህን ሰው እንደ አባቶቹ ሥጋውን ወደ መቃብር ነፍሱን ወደ ሲዖል ላውርድ ይሆንን?" እያለ ይፈራ ይጨነቅ እንደነበርና በመጨረሻም "አምላኬ አምላኬ፣ ተጠማሁ ሲል ቢሰማው 'ይህስ ዕሩቅ ብእሲ ነው' ብሎ እንዳለው ሊያደርግ ሲጠጋ በመለኮታዊ ኃይሉ በእሳት ዛንዠር በነፋስ አውታር አሥሮ ሲዖልን እንደበዘበዛት ትምህርተ ኅቡዓት የተባለ የቤተ ክርስቲያናችን መጽሐፍ በግልጽ ያስረዳል።

 ➥ አንድም በጎች የምዕመናን ቀንድ የመስቀል ምሳሌ
እኛ ምእመናን በቀንድ መስቀል ትእምርትነት ዲያብሎስን ድል እያደረግነው እንኖራለንና ነው። ለዚህም ነው መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት "ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ ከመ ያምሥጡ እም ገጸ ቅስት ወይድኃኑ ፍቁራኒከ፤ ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሀቸው ወዳጆችህም እንዲድኑ" ብሎ የተቀኘው። [መዝ. ፶፱፥፬፤ ፺፬፥፮፤ ፺፱፥፫-፬፤ ማቴ. ፳፭፥፴፫ ፣ ሕዝ. ፴፮፥፴፰፣ ዮሐ. ፲፥፬፤ ፲፬፥፭] አንድም፦ በግ በቀንዱ ጠላቱን እንዲወጋበት ጌታም ሥጋውን በቆረሰበት ደሙን ባፈሰሰበት በቅዱስ መስቀሉ ሠይጣንን፣ ሞትና መቃብርን ቀጥቅጦ ከኃይሉ በታች አድርጎታልና ቀንድ በመስቀል ይመሰላል። ቅዱስ ጳውሎስ " እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከኹለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።" ብሎ ገልጦታል። [ኤፌ. ፪፥፲፬-፲፮] ዳግመኛም ጥልን በመስቀሉ ከገደለ በኋላ ሰላምና እርቅን ደግሞ ያደርግበታል። " እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና።" እንዲል። [ቆላ. ፩፥፲፱] ልሣነ ዕፍረት ቅዱስ ጳውሎስ በድጋሜ "...ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ መስቀል በቀር ሌላ
ትምክህት (ኃይል፣ ሥልጣን፣ ክብር፣ መውጊያ) ከእኔ ይራቅ።" ያለው። [ገላ. ፮፥፲፬]

 ➥ ማጠቃለያ
ቀርነ በግዕ፦ የመስቀል አንድም የኃይለ እግዚአብሔር፣ የሥልጣነ እግዚአብሔር ምሳሌ ነው። ኃይለ እግዚአብሔርም ሥልጣነ እግዚአብሔርም የሚገለጠው/የተገለጠው በዙፋኑ በመስቀል ነውና በመስቀል ይጠቃለላል።"


4. ምሰሶ
በግራ በቀኝ የሚገኝ ቋሚ እንጨት ሲሆን፤ የሚሠራውም ልክ እንደ ቀንበሩ ከእንጨት ተጠርቦና ለዝቦ እንዲሁም በልዩ ጥበብ ተውቦና አጊጦ ነው። ምስጢሩ፦
• የቀኝ ምሰሶ፦ የፍቅረ እግዚአብሔር ምሳሌ፣ አንድም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ፣ አንድም የመጋቤ ብሉይ የቅዱስ ሚካኤል ምሳሌ
• የግራ ምሰሶ፦ የፍቅረ ቢጽ(ሰው) ምሳሌ፣ አንድም የሐዲስ ኪዳን ምሳሌ፣ አንድም የመጋቤ ሐዲስ የቅዱስ ገበርኤል ምሳሌ
• ኹለቱ ምሰሶዎች የግራ እና የቀኝ ምሰሶ በአንድ ቀንበር መያያዛቸው አንዳች ትምህርት የያዘ ነው። ይህም "ፍቅረ እግዚአብሔርን እና ፍቅረ ቢጽን (ቀኝ ምሰሶ እና ግራ ምሰሶ) አንድ ላይ ብንጠቀልላቸው ፍቅር የሚልን ትርጉም ይሰጡናል፤ ፍቅር ደግሞ በበገናው ቀንበር የተመሰለው አኀዜ ኵሉ እግዚአብሔር ነው።"

5. አውታር
ከበግ አንጀት ወይም ከበሬ ጅማት ታጥቦና ተልጎ፣ ተገመዶ፣ ተወጥሮ፣ ከሮ፣ በግኖና ደርቆ በቊጥር ተቀምሮ ይሠራል።
ምስጢሩ፦
 ➥ የበገና አውታሮች የዐሥርቱ ትዕዛዛት ምሳሌ ነው። እኒህም:-
• ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አታምልክ፣ [ዘፀ ፳፡፫-፮]
• የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፣ [ዘፀ ፳፡፯]
• የሰንበትን ቀን አክብር፣ [ዘፀ ፳፡፰-፲፩]
• አባትህንና እናትህን አክብር፣ [ዘፀ ፳፡፲፪]
• አትግደል፣ [ዘፀ ፳፡፲፫]
• አታመንዝር፣ [ዘፀ ፳፡፲፬]
• አትስረቅ፣ [ዘፀ ፳፡፲፭]
• በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር፣ [ዘፀ ፳፡፲፮]
• የባልንጀራህን ገንዘብ አትመኝ፣ [ዘፀ ፳፡፲፯]
• ባልንጀራህን አንደ ራስህ ውደድ፣ [ዘሌ፲፱፡፲፰]
➥አንድም የበገና አውታሮች በጽላቱ (በታቦቱ) ላይ የሚጻፉ ኅቡዕ ቃላቶች ምሳሌ:- አልፋ፣ ወዖ፣ ቤጣ፣የውጣ
ትርጉማቸውም አልፋ ምስራቅ፤ ወዖ ምዕራብ፤ ቤጣ ሰሜን፤ የውጣ ደቡብ ማለት ነው።
የበገናው አውታሮች በቊጥር ሲተነተኑ፡-፩ =አ፣ ፪= ል፣ ፫ =ፋ፣ ፬ =ወ፣ ፭ =ዖ ፣ ፮= ቤ፣ ፯ =ጣ፣ ፰= የ፣ ፱= ው፣ ፲= ጣ ይሆናሉ።
እንዲሁም በፊደላት ብቻ የበገናው አውታሮች ስም በመሆን ያገለግላል [አ፣ ል፣ ፋ፣ ወ፣ ዖ፣ ቤ፣ ጣ፣ የ፣ ው፣ ጣ]

➥ይቆየን...

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 19:20


#ምኩራብ {{{የዐቢይ ጾም ሦስተኛው ሳምንት}}}

ሦስተኛው ሰንበት ምኩራብ ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት በዚሁ ዕለት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ሰላሙ ድረስ በዕለተ ሰንበት «ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ»

«ምኩራብ» ማለትም ቀጥተኛ ፍችው ኮረብታ፣ ተራራ የሚያኸል ታላቅ ሕንጻ ማለት ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ የአይሁድ ቤተ ጸሎት ወይም ቤተመቅደስ ማለት ይሆናል፡፡ ዐቢይ ፍሬ ቃሉ ግን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያነ ሥጋን በትምህርቱ፣ ድውያነ ነፍስን በታምራቱ ሲፈውስ በምኩራብ እየተገኘ የፈጸመውን የማዳን ሥራ በኀሊና እያሳሰበ የሚያስተምር ሦስተኛ ሳምንት ነው፡፡ {{ዮሐ. 2:12}}

«ኢየሱስ በሰንበት ቀን ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ» እያለ ኢየሱስ በአይሁድ ምኩራብ ማስተማሩን እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ይህን ሰንበት ለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  በምኩራብ እየገባ ለማስተማሩና በምኩራብ የሚሸጡ የሚለውጡ ነጋዴዎችን ለማስወጣቱ ቤተ መቅደሱን ለማስከበሩ መታሰቢያ ሆኖ ስለተሰጠ ነው፡፡ የዚህም በዓል ታሪክ ዝርዝር ሁኔታው {{በማቴዎስ ወንጌል ምዕ 21፡12-13 ተጠቅሷል፡፡ {{ቆላስ 2፡16-23}} «እንግዲህ በመብል ወይ በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፣ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው፡፡ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፣ ባላየውም ያለፈቃድ እየገባ፣ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም
አይፍረድባችሁ፤ እንደዚህ ያለ ሰው ራስ ወደሚሆነው አይጠጋም፣
ከእርሱም አካል ሁሉ በጅማትና በማሰሪያ ምግብን እየተቀበ እየተጋጠመም፣ እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ ያድጋል፡፡
ከዓለማዊ ከመጀመሪያት ምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፣ እንደሰው ሥርዓትና ትምህርት፡- አትያዝ አትቅመስ፣
አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም ሁሉ እንደምትኖሩ ስለምን ትገዛላችሁ እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና፡፡ ይህ እንደገዛ ፈቃድህ በማምለክና በትሕትና ሥጋንም በመጨቈን ጥበብ ያለው ይመስላል፣ ነገር ግን ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ለመከልከል ምንም አይጠቅምም፡፡» {{ያዕ 2፡14-26}} « ወንድሞቼ ሆይ፣ እምነት አለኝ የሚል፣ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል) እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፣ ከእናንተ አንዱም በደህና ሂዱ፣ እሳት ሙቁ፣ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል) እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው፡፡

ነገር ግን አንድ ሰው አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፣ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል፡፡ በእግዚአብሔር አንድ እንደሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል፡፡
አንተ ከንቱ ሰው፣ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፣ በሥራም እምነት እንደተፈጸመ ትመለከታለህን) መጽሐፍም አብርሃምም እግዚአብሔር አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ፡፡

ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ፡፡ እንደዚሁም ጋለሞይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን) ከነፍስ የተለየሥጋን የሞተ እንደሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው፡፡»
{{የሐዋ.ሥራ 1ዐ፡1-9}} « በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነው ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበር፡፡ እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና
የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ
እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ፡፡

ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል፡- ቆርኔሌዎስ ሆይ የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው እርሱም ትኩር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ ጌታ ሆይ ምንድር ነው አለ፡፡ መልአኩም አለው፡-ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን ዐረገ።

አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን
ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ፡፡ እርሱ ቤቱ በባሕር አጠገብ ባለው በቁርበት ፋቂው በስምዖን ዘንድ እንግድነት ተቀምጦአል፤ ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል፡፡ የተናገረውም መልአክ በሄደ ጊዜ ከሎሌዎቹ ሁለቱን፣ ከማይለዩትም ጭፍሮቹ እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንዱን ወታደር ጠርቶ፣ ነገሩን ሁሉ ተረከላቸው ወደ ኢዮጴም ላካቸው፡፡ እነርሱም በነገው ሲሄዱ ወደ ከተማም ሲቀርቡ፣ ጴጥሮስ በስድስት ሰዓት ያህል ይጸልይ ዘንድ ወደ ጣራው ወጣ፡፡
መዝ 68፡9
እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡

የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፤
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና፤
ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፡፡
{{ዮሐ 2፡12-25}} «ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ
ከደቀመዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፣ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ፡፡ የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም
ወጣ፡፡ ወደ መቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም  የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፣ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ፣ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፣ ርግብ ሻጪዎችንም ይህን ከዚህ ውሰዱ፡፡ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደተጻፈ
አሰቡ፡፡ ስለዚህ አይሁድ መልሰው ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየናለህ አሉት፡፡ ኢየሱስም መልሶ ይህን ቤተመቅደስ አፍርሱት በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው ስለዚህ አይሁድ ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፣ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን አሉት፡፡ እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተመቅደስ ይል ነበር፡፡


ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ
ደቀመዛሙርቱ ይህን እንደተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ፡፡
በፋሲካ በዓልም በኢየሩሳሌም ሳለ፣ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜብዙ ሰዎች በስሙ አመኑ ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር፣ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና፡፡»
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 19:19


꧁༒꧂ የበገና ትምዕርትነት( ምሳሌነት) ꧁༒꧂

ቀንበር (ጋድም)
ቀንበር ከበገና ከላይኛው ክፍል የሚገኝ አግዳሚ ሲሆን ቀጥ ያለ ወይም የቀንደ መለከት ቅርጽ ሊኖረው ይችላል። አውታሩ የሚወጠርበት እና መቃኛው የሚያርፍበት ክፍል ነው። የሚሠራውም ከደረቅ እንጨት ተጠርቦ እና ለዝቦ እንዲሁም በልዩ ጥበብ ተውቦ ነው። ምስጢሩ፦
• ቀንበር የአኀዜ ኵሉ እግዚአብሔር ምሳሌ ነው።
• ቀንበር ከበገናው በላይ መገኘቱም፦ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር በላይ በሰማይ ያለ ሁሉን የፈጠረ፣ ሁሉን የሚያስተዳድር ጌታ፣ የሁሉ የበላይ መሆኑን ያጠይቃል።
• አንድም የሥልጣነ የእግዚአብሔር ምሳሌ
• አንድም የእግዚአብሔርን ልዕልና ያመለክታል።

መቃኛ
ከቀጫጭን ጠንካራ እንጨቶች የሚሠራ ሲሆን አውታሩን ቀንበሩ ላይ አሥሮ ይይዛል። አስተሳሰሩም የራሱ ብልሃት ያለው ነው። ለመቃኘት አውታሮቹን ለማጥበቅና ለማላላት እንዲረዳ ተደርጎ ይታሠራል። ምስጢሩ፦
• መቃኛ በመንፈስ ቅዱስ ይመሰላል፡፡ ሕግጋትን በመስጠት የምዕመናን ሕይወት የሚጠብቅ እርሱ ነውና፡፡
• አንድም ዐሥሩ ትዕዛዛት መንፈሳውያን የሚያደርጉ የመንፈስንም ፍሬ የሚሰጡ በመሆናቸው ነው።
• አንድም ምድራዊ ሕይወታቸውን በቅድስና፣ በሰማዕትነት፣ አሸንፈው ወይም ይህን ዓለም ድል ነስተው ወደ አሸናፊዋ ሰማያዊቷ ቤተ-ክርስቲያን አካል በተቀላቀሉ ቅዱሳንና ጻድቃን ሰማዕታት ይመሰላል፡፡
• አንድም የመላእክት ምሳሌ ነው"

ጌጥ (መስቀል፣ ቀርነ በግዕ)
• መስቀል፦ እግዚአብሔር ስለ ሰው ልጆች ፍጹም ፍቅሩን የገለጠበት ነው።
• ቀርነ በግዕ፦ የበግ ቀንድ ማለት ነው። በብሉይ ኪዳን የተለያዩ ንዋያተ ቅድሳት ከቀንድ ይሠሩ ነበር ለምሳሌ
• ቀርነ ቅብዕ/የዘይት መያዣ [፩ኛ ሳሙ፲፮፥፩]
• ቀንደ መለከት. [ኢያ፮፥፭] መጽሐፍ ቅዱስ ቀንድ ኃይልን፣ ሥልጣንን፣ ክብርን፣ ንግሥናን ያመለክታል።

በግዕ(በግ)
በግ በየዋህነቱ የሚጠቀስ የቤት እንስሳ ሲሆን በብሉይ ኪዳን ለመሥዋዕት ከሚሆኑ እንስሳት ዋነኛውና በተለይም በፋሲካ የሚሠዋ እንስሳ ነው። በቅዱሳት መጻሕፍት በግ የክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ ተጠቅሷል። ምእመናንም በበጎች ተመስለዋል። በግ በመጽሐፍ ቅዱስ
• እስራኤል ከግብጽ በወጡበት ቀን የሠዉት የፋሲካው በግ። [ዘጸ ፲፪፥፫-ፍጻሜ] ይህ በግ የክርስቶስ ምሳሌ እንደሆነ ንዋይ ኅሩይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በ [፩ኛ ቆሮ ፭፥፯-፰] ላይ "...እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤ ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ
እርሾም አይደለም።" ብሎ ገልጦ አብራርቶታል።
• በይስሐቅ ፋንታ የተሠዋው "እግዚአብሔር ያዘጋጀው በግ" ። አብርሃም ልጅህን ሠዋልኝ ብሎ እግዚአብሔር የጠየቀውን ጥያቄ ለመፈጸም ልጁንና ለመሥዋዕት የሚሆነውን እንጨት ይዞ ከልጁ ከይስሐቅ ጋር እግዚአብሔር ወደ አዘዘው ስፍራ ለመሄድ ተነሳ፤ አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱም እሳቱንና ቢላዋውን በእጁ ያዘ፥ ኹለቱም አብረው
ሄዱ። ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን ተናገረው። አባቴ ሆይ? አለ እርሱም እነሆኝ ልጄ አለው። እሳቱና እንጨቱ ይኸው አለ፤ የመሥዋዕቱ በግ ግን ወዴት ነው?" አለው። [ዘፍ ፳፪፥፮-፯] አብርሃምም ልጄ ሆይ የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል አለው፤ ኹለቱም አብረው ሄዱ። " [ዘፍ ፳፪፥፰]
• እንዳለውም እግዚአብሔር በግን አዘጋጀ። ይህ በግ የአማናዊው በግ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ይህንንም የሐዲስ ኪዳኑ ነቢይ የብሉዩ ሐዋርያ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ብላቴናው ይስሐቅ ከሺህ ዓመታት በፊት "የመሥዋዕቱ በግ ወዴት ነው?" ብሎ የጠየቀውን ጥያቄ በሐዲስ ኪዳን "ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየአትት ወያሴስል ኃጢአት ዓለም። "እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ የእግዚአብሔር በግ አለ።"ብሎ መልሶለታል። [ዮሐ ፩፥፳፱፣፩፥፴፮] ስለዚህ በግ የክርስቶስ ምሳሌ ነው።"

"• ቀርን(ቀንድ)
የኃይለ እግዚአብሔር፣ የሥልጣነ እግዚአብሔር፣ የመስቀል ምሳሌ ነው። ቀንድ ያለው ማንኛውም ፍጥረት በእርሱ ላይ ነጣቂ ጠላት በመጣበት ጊዜ በጠላቱ ላይ በቀንዱ እንዲበረታታበትና ራሱንና መንጋዎቹን ሁሉ ከመነጠቅ እንዲታደግና እንዲያድን እንዲሁ በአምሳሉ የተፈጠረው የሰው ልጅ በነጣቂው ጠላት ዲያብሎስ የተንኮል ወጥመድ ውስጥ ገብቶ ከአባቱና ከጠባቂው እንዲሁም ከመንጋው ተለይቶ ሊነጠቅ ባለ ጊዜ ልዑል አምላክ የሆነ እርሱ አርዓያውን ነሥቶ ፍጹም ሰውን ሆኖ በጠላቱ ላይ በቀንዱ እንዲበረታታ በአምላክነቱ ኃይልና ሥልጣን አዳምን ጠልፎ በጣለው ኃጢአትና ሞት፣ በሞት ጌታዋም በዲያብሎስ ላይ ተበረታታባቸውና አርዓያውን ይዞ በዲያብሎስ ግዛት ስር የነበረውን በግ አዳምን እረኛም በግም ሆኖ አዳነው። ይህንን ሲያስተውል ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ከአንድ ሺህ ዓመት በፊት በትንቢት መነጽር ዓይቶ ታላቅ ምስጢር ተናገረ እንዲህ ሲል "...እስመ ኃረያ እግዚአብሔር ለጽዮን...ወበህየ አበቊል ቀርነ ለዳዊት ወአስተዴሉ ማኅቶተ ለመሲሕየ ወአለብሶሙ ኃፍረተ ለጸላእቱ ወቦቱ ይፈሪ ቅድሳትየ። " ትርጉሙም "እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ "ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ፤ አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ፤ ካህናቶችዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል፤ በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለቀባሁትም ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ። ጠላቶችንም እፍረትን አለብሳቸዋለሁ፤ በእርሱ ግን ቅድስናዬ ያብባል።" [መዝ ፻፴፩፥፩-ፍጻሜ] ትርጉሙም፦ "እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ “ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ፤ አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ፤ ካህናቶችዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል።" ያለው ስለ እመቤታችን ሲሆን "በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለቀባሁትም ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ። ጠላቶችንም እፍረትን አለብሳቸዋለሁ፤ በእርሱ ግን ቅድስናዬ ያብባል" ያለው ደግሞ ስላለው ኃይልና ሥልጣን እንደሆነ ግልጽ ነው። ቀንድ ኃይልና ሥልጣንን እንደሚያመለክት የሚያስረዱ ሌሎች በርካታ ጥቅሶችም አሉ። [፩ኛ ነገ፳፪፥፲፩፣
ሉቃ፩፥፷፱፣፩ኛ.ሳሙ. ፪፥፩፣፪፥፲፣ ሕዝ፳፱፥፳፩] "

➥ይቆየን...

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 19:19


꧁༒꧂ ስለ በገና ቀጣይ ክፍል ꧁༒꧂

ለተመስጦ
በገና በፍጹም እርጋታ፣ ያለምንም የሰውነት ውዝዋዜ፣ በተረጋጋና በማስተዋል መንፈስ የሚደረደር በመሆኑ፣ እንዲህ ተደርጎ ሲደረደርና ሲዘመርበት ትልቅ የተመስጦን ሁኔታ ይፈጥራል። በዚህም ተመስጦ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙ፣ ሰውን የሚያስተምሩ እና የሚመክሩ፣ የተፈጥሮን ጥልቅ ምስጢር እየመረመሩ፣ ምስጋናን ለፈጣሪ የሚያቀርቡ ድንቅ ዝማሪዎችን እና ቅኔዎችን እንደተቀኘ ከመዝሙሩ የምንረዳ ሲሆን አባቶቻችንም ብዙ እንዳተረፉበት እና በተመስጦ እንደተቀኙበት ዘመናትን ከዘለቁ የመዝሙር ግጥሞቻቸው ማስተዋል እንችላለን።
ታቦተ ሕጉን በዝማሬ ለማክበር
በገና የእግዚአብሔርን የቃልኪዳን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ዳዊት ከተማ ገብታ በድንኳን በኖረችበት ጊዜ [፩ኛ ዜና. ፲፭፡፳፰] የእግዚአብሔርን ታቦት ከዳዊት ከተማ ንጉሥ ሰሎሞን ወደ አሠራው ቤተመቅደስ በምትገባበት ጊዜ ዕብራውያን በደስታ ሆ እያሉ ቀንደ መለከት እና እምቢልታን እየነፉ ጸናጽልና መሰንቆም በገናንም እየመቱ የእግዚአብሔርን የቃልኪዳን ታቦት እንዳመጡ እና እንዳመሰገኑ መጽሐፍት ያስረዳሉ፡፡
በጠላት ላይ ድል ለማግኘት
እግዚአብሔር በጠላቶቻቸው ላይ ድል በሰጣቸው ጊዜ... [፪ኛ ዜና. ፳፯-፳፰]፤ ያዕቆብ ከላባ በኮበለለ ጊዜ ላባ ለያዕቆብ ሲናገረው... [ዘፍ. ፴፩፡፳፯] ከላይ የተጠቀሱት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በገና እንደ ሌሎች የቤተ መቅደስ የዜማ ዕቃዎች አገልግሎት ይሰጥ እንደ ነበረ ተገልጧል፡፡
ከኀዘን ለመጽናናት
በገና በተለያየ ምክንያት ከሚደርስ ኀዘን ለመጽናናት ወይንም ለማጽናናት አገልግሎት ላይ ይውላል። ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ ከተጠቀሰበት የዩባል ልጆች ዓላማ ጋር የሚገናኝ ነው። የዩባል ልጆች ዓላማ በዘራቸው ከሆነው የእርስ በርስ መገዳደል ታሪክ ኀዘን መጽናናት ነው። በዚህም በገና ቃለ ማኅዘኒ ተብሏል። ይሄው ፈለግ በመዝሙረ ዳዊት እንደምንረዳው በአሳዛኝ ወቅቶች ሁሉ የበገና አገልግሎት የማይቋረጥ መሆኑን ነው። በኢትዮጵያውያን ዘንድም እንዲሁ በተለይ በጾምና በጸሎት፣ በጽሞና፣ በንስሐ እና ሰዎች
በሞት በሚለዩበትም ጊዜ በገና ለመጽናናት አገልግሎት ሲውል ይታያል። 
ትንቢት ለመናገር
ቅዱስ ዳዊት የተናገራቸው ቃለ ትንቢቶች በሙሉ በበገና እየደረደረ ነው፡፡ "ወደዚያም ወደ ከተማይቱ በደረስሱ ጊዜ፥ በገናና ከበሮ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢት እየተናገሩ ከኮረብታው መስገጃ የሚወርዱ የነቢያት ጉባኤ ያገኙሃል" 
ከመናፍስት ሥቃይ ለመዳን
"እንዲህም ሆነ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፡፡ ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር" [፩ኛሳ ፲፮፡፳፫] እንዲል፡፡"
የሀገር ሉዓላዊነትን ለመግለጽ
በገና የሃገር ሉዓላዊነት የሚያወሱ መዝሙሮችን ለመዘመር ይረዳል። "ኢትዮጵያ ሆይ ተነሽ"... የሚለው መዝሙር ለዚህ አገልግሎቱ ተጠቃሽ መዝሙር ነው።
ነፍስን ያለ ጣር ከሥጋ ለመለየት
በገና ጻረ ሞት ወይም ስቃይ ሳይኖር ነፍስን ከስጋ የመለየት ሃብት እንዳለው ሐምሌ የሚነበበው መጽሐፈ ስንክሳር ያስረዳል።
ምእመናን ስለ እመቤታችን መዝሙር በሚዘምሩበት ወቅት እግዚአብሔር እልፍ አእላፍ መላእክት፣ ነቢያትን ሐዋርያትን እንጦንስና መቃርስን ይዞ እንደ ወረደ ያን ጊዜም ቅዱስ ዳዊት በአካለ ነፍስ አብሮ እንደተገኘ ያስረዳሉ። ቅዱስ ዳዊት ጻድቁ አባታችን አባ ኪሮስን “በማንኛው አውታር፣ በማንኛው ዜማ፣ በማንኛውስ ወገን በመጀመሪያው ነውን? በኹለተኛ ነውን? ወይስ በሦስተኛ ልዘምርልህ?” ባላቸው ጊዜ “የዐሥሩን አውታር በየወገናቸው ዜማቸውን ልሰማ እወዳለሁ” አሉት፡፡ ያን ጊዜም ዳዊት በገናውን አዘጋጅቶ እየደረደረ “ፈጽመን ደስ እንሰኝባት ዘንድ አግዚአብሔር የሠራት ቀን ናት እግዚአብሔርን በመፍራት በሕጉ የሚኖሩ ብጹዓን ናቸው” እያለ ዘመረ፡፡
ዳግመኛም “ጎረመስኩ ነገር ግን የሚጣል ጻድቅ አላየሁም” ብሎ ሲጮህ የአባ ኪሮስ ነፍስ ከሥጋ ተለየች ይላል። ዳግመኛ የጻድቅ ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው እያለ በልብሱ ዘርፍ እንኳ አውታር እየመታ ይደረድር ነበረ፡፡" [ገድለ አቡነ ኪሮስ]
በተመሳሳይ ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በበገና ጣዕመ ዝማሬ ነፍሷ ከሥጋዋ በሚለይበት ወቅት ጻእረ ሞት ወይም ያያት ስቃይ ሳይኖራት በበገና ጣዕመ ዝማሬ አማካኝነት ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየ። "ዳዊት በበገና ዕዝራ በመሰንቆ እያጫወቷት፣ ሳታውቀው አለፈች ያን መልአከ ሞት።" የሚለው በክብረ በዓል የሚዘመረው መዝሙር እውነታውን ያስረዳናል። ከዚህ በተጨማሪም፣ በብዙዎቹ ቅዱሳን እረፍት ጊዜ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ለመቀበል ሲመጣ ቅዱስ ዳዊትም እንደሚገኝ በርካታ ገድላት እና ድርሳናት ይናገራሉ።"
የበገና ማህበራዊ ግልጋሎት በቀደምት ክርስቲያኖች
• በገና በንግሥ ወቅት
• በቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጋብቻ ላይ
• ድል በማድረግ ጊዜ ባሉ የደስታ ጊዜያትም እግዚአብሔር ይመሰገንበታል
• በበጎ ሥራቸው ለሃይማኖትና ለሀገር ውለታ ለዋሉ
• ታላላቅ እና ልዩ የሆኑ ሀገራዊ ክስተቶች የቤተ-ክርስቲያን ታሪክን የበገና ደርዳሪዎች በበገናቸው መወድስ በማቅረብ ያነሷቸዋል።
• በኃዘን ጊዜ (ሰው ሲሞት)
• ቁጣና መቅሰፍት ሲደርስ እና የመሳሰሉት አሳዛኝ ክስተቶች ሲገጥሙ
• ለተማጽኖ እና ለማጽናኛ
የበገና ማህበራዊ ግልጋሎት አሁን ባሉ ክርስቲያኖች
• በደስታ ጊዜ
• በሠርግም ጊዜ
• ሰው ሲሞት (በሐዘን ወቅት)
• በታላላቅ የአደባባይ በዓላት (እንደ ጥምቀት፣ መስቀል፣ እና የንግሥ በዓላት) በታቦቱ ፊት በጉዞ ወቅት ለበገና የታሪክ ምንጭ የሆኑት መጽሐፍ ቅዱስ የታሪክ ድርሳናት እና ትውፊት እንደሚነግሩን በገና በማንኛውም ቦታ ዝም ተብሎ የሚደረደር አለመሆኑን ነው።
በገና መቼ ነው የሚደረደረው
በምእመናን ዘንድ የበገና መዝሙር መስማት የሚዘወተረው በአጽዋማት ወቅት በተለይም በዐቢይ ጾም ጊዜ ቢሆንም፤ ከዚህ ወቅት ጋር ብቻ የሚገድበው ነገር ኖሮ አይደለም። ታሪኩን የሚያውቁ ሲናገሩም እንዲህ ያለው ኹኔታ የመጣው በቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት፣ ቤተ ክርስቲያን በነበራት የሬድዮ መርሐ ግብር፤ በዐቢይ ጾም ወቅት ይተላለፍ የነበረው መዝሙር የበገና ስለነበረ ሕዝቡ ከዚህ በመነሳት በዚህ ጾም ወቅት የበገና መዝሙር መስማትን ባሕል እያደረገው እንደ መጣ ይታመናል። ይሁን እንጂ በገና በቀደምት ኢትዮጵያውያን ዘንድም ሆነ፤ በዕብራውያን ዘንድ፤ በማናቸውም ጊዜ ዓመቱን ሙሉ አገልግሎት ላይ የሚውል የዜማ መሳሪያ ነው።"

➥ይቆየን...

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

20 Jan, 19:19


꧁༒꧂ በገና በኢትዮጵያ ꧁༒꧂

ስለ በገና ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ አመጣጥ ታሪክ ኹለት(፪) ዓይነት አመለካከቶች አሉት፡፡
በገና ኢትዮጵያዊ መነሻ ያለው ስለመሆኑ በገና የሀገራችን ኢትዮጵያ የሥልጣኔዋ ውጤትና በሕገ ልቡና የማመንዋ ውጤት ነው፡፡ ወይም በገና መሥራትና ማመስገን የተጀመው እዚሁ ሀገራችን ነው የሚል አስተምህሮ ነው፡፡ መዛግብት የቀዳማዊ ምኒልክ አያት የንግሥት ሳባ (ንግሥት ማክዳ) እናት ንግሥት "አዝሚና" በገና ደርዳሪ እንደነበሩ ይናገራሉ።
መጽሐፈ ሱባኤ ከአዝሚና በተጨማሪ "አፄ" የተባለ የኢትዮጵያ ንጉሥ በመቶ የሚቆጠሩ በገና ደርዳሪዎችና መዘምራን እንደነበሩት ይናገራል። የ"ተዋሲያ" ወይም የ"ሳቢ" የመጨረሻ ሴት ልጁ አዝሚና የምትባል ቆንጆና ዘፋኝ ልጅ ነበረችው። እርሱም ከዋይዝ ከተማ እንድታስደስተው መጥታ በሳባ ትኖር ነበር። ለ አፄ አምላኩን በበገና፣ በከበሮ፣ በእምቢልታ እየዘመሩ በፊቱ የሚያመሰግኑለት መቶ ጃንደረቦች ሦስት ሞቶ ደናግላን ሴቶች ነበሩት።” [መጽሐፈ ሱባኤ ገጽ ፻፷፰]

➥ በገና ፍጹም ኢትዮጵያዊ ነበር የሚለውን አመለካከት በተመለከተ ተጨማሪ ማስረጃዎች
• በበገና የምናዜማቸው ዝማሬዎች ኢትዮጵያዊ ቃና እና ጣዕም ያላቸው መሆን።
• በገና ላይ የምንጠቀምባቸው ቅኝቶች ፍጹም ኢትዮጵያዊ መልክ መያዛቸው እንዲሁም
• በገና የሚሠራባቸው ግብዓቶች ከጥንትም ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለመሥራት የሚጠቀሙባቸው ግብዓቶች መሆናቸውና፤ ከሥነ ቃሉ ሁሉ ጋር ተደምሮ ሲታይ ኢትዮጵያዊ የመሆኑ ሚዛን ይደፋል ይላሉ።"

➥ "ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው በገና ትክክለኛው በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰው በገና ስለመሆኑ ማስረጃዋች
• ቅዱስ ዳዊት ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምራለሁ ባለው መሠረት አሁን ያለው በገና ዐሥር አውታር ያለው መሆኑ።
• ኢትዮጵያ ለእግዚአብሔር የምስጢር ሀገሩ ስለሆነች በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ይመሰገንባቸው የነበሩት የዜማ ዕቃዎች እንደ መሰንቆ፣ ከበሮ፣ ጸናጽል፣ መለከት እና የመሳሰሉት ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የሚውሉት ንዋየ ቅዱሳት ቅርጻቸው ሳይለወጥ መኖራቸው።
• በገና በታቦተ ጽዮን ፊት አገልግሎት ይሰጥ ስለነበረ እና ታቦተ ጽዮንም በፈቃደ እግዚአብሔር በንጉሥ ሰሎሞን ልጅ (ምንሊክ) ዘመን ወደ ኢትዮጵያ መጥታ በሀገራችን መኖሯ።
• በኢትዮጵያውያን ባሕል ለቤተ ክርስትያን እና ለቤተ መንግሥት ዕቃዎች ልዩ ክብር ስለሚሰጥ በገና በቤተ-ክርስትያንም በቤተ-መንግሥትም አገልግሎት የሚሰጥ ስለሆነና ስለነበረ ቅርጽና ይዘቱን ሳይለቅ የመኖር ዕድል በማግኘቱ። የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ቅዱስ ያሬድ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ መምህርት ወለተማርያም፣ እንዲሁም ከሀገራችን ነገሥታት አፄ ቴዎድሮስ፣ አፄ ዩሐንስ፣ አፄ ምኒልክ፣ እቴጌ ጣይቱ፣ ልጅ እያሱ (በነጋድራስ ተሰማ እሸቴ) ተምረው፤ እንዲሁም ንጉሡ ሚካኤልና ሌሎችም ይደረድሩ እንደነበር የሚናገሩ አፈታሪኮች አሉ፣ ነገሥታቱም በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያደጉ ስለነበር በገና መደርደር ባይችሉም እንኳ የራሳቸው በገና ደርዳሪ እንደ ነበራቸው ይነገራል።

በገና እስራኤላዊ መነሻ ያለው ሰለመሆኑ አንድም በቀዳማዊ ምኒሊክ ጊዜ ከታቦተ ጽዮን ጋራ አብረው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት የዜማና የሥርዓተ አምልኮ ንዋያተ ቅድሳት፣ መጻሕፍት...ወዘተ አንዱ ሆኖ የመጣ ነው የሚሉ አሉ። በተጨማሪም፣ በቀዳማዊ ሚኒልክ ዘመን በሊቀ ካህናቱ በዘካሪያስ እጅ ታቦተ ጽዮንና ሌዋዉያን ሲመጡ የመዝሙር መጻሕፍትና በተመሳሳይ የመዝሙረ ዳዊት ንባባዊ ዜማ ወይም ዜማዊ ንባብ ከበገናው ጋር አብረዉ መጥተዋል የሚሉም አሉ፡፡ ለዚህም ማሳያ በዘመነ ኦሪት የመጡ የዜማ መሳሪያዎች፤ አለባባስና የመዝሙር አጠቃቃም ስልቶች ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን ቅርጻቸው እና ትውፊታቸው ሳይቀየር ለዘመናት እየተገለገለችባቸው መገኘቷ ነው፡፡ ከዜማ መሳሪያዎች መካከልም ከበሮ፤ ጸናጽል፤ መለከት፤ መሰንቆ፤ በገና ይገኙበታል፡፡ ከአለባበስም ረጅም ቀሚስ፤ ጥምጥም፤ መጎናጸፊያ (ጋቢ) እና ካባ ይገኙበታል፡፡ ይህ አመለካከትም ይበልጥ በሀገራችን ጠበብት ሊቃውንት በስፋት ይተረጉማል፣ ይተረካል... ይታመናልም፡፡"
የበገና መንፈሳዊ አገልግሎት
በገና እግዚአብሔርን ለማመስገን፤ ጸሎት ልመናን ወደ እርሱ ለማቅረብ ያገለግላል። የበገና አገልግሎት ለመንፈሳዊ ትሩፋት ማለትም ለምሥጋናና ለልመና ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ተመርጦ ለቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት ይውላል፡፡ ዝማሬ ከሚቀርብባቸው መንገዶች በገና አንዱ እና በብዙ ምክንያቶች ተመራጭ በመሆኑ፣ ለእግዚአብሔር እንዲሁም እርሱ ይመሰገኑ ዘንድ ላለላቸው ሁሉ ምስጋና መሠውያ መሳሪያ ነው። በገና ሰማያዊ ንዋየ ማኅሌት መሆኑን በዮሐንስ ራዕይ ተመዝግቦ እናገኛለን። “በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ ዐየሁ፤ ሰባትም ቀንዶችና ሰባት አይኖች ነበሩት፣ እርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው። መጥቶም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፍን ወሰደው። መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ እንስሶችና ሃያ አራቱም ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበት የወርቅ እቃ ያዙ። መጽሐፍንም ትወስድ ዘንድ፣ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ተገድለሃልና፣ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ
ከቋንቋም ሁሉ፣ ከወገንም ሁሉ፣ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው በምድርም ላይ ይነግሳሉ እያሉ አዲስ ቅኔን ይዘምራሉ።" [ራዕይ ፭፥፮ -፲] ስለዚህ በገና ከመላእክት ወገን የሆኑት አርባዕቱ እንስሳ እና ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት የክብር ዕቃቸው ነው። እንዲሁም በመጽሐፈ ሔኖክ ዘአዶናይ ራፋኤል ስለበገና ሲያብራራ "ቅዱሳን የሆኑ መላእክት በጽርሐ አርያም መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ለሕያው እግዚአብሔር ፳፬ ሰዓታት ሙሉ ምስጋና የሚያቀርቡበት የተቀደሰ መሳሪያ ነው" በማለት በሚገባ አረጋጥዋል፡፡
➥ መንፈሳዊ ሕይወትን ለማጠንከር

በገና በዝማሬ እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት በመሆኑ የምሥጋናን ሕይወት እንድንኖር በማድረግ መንፈሳዊ ሕይወታችንን ያለመልማል። እግዚአብሔርን ማመስገን እርሱ ያከበራቸውንም እንደየማዕረጋቸው ምስጋና ለሚገባቸው ምስጋና ማቅረብ የመንፈሳዊ ሰው ቀዳሚ ሃብቱ ነው። ከዚህም ባሻገር በበገና የምናገኘው ተመስጦ እራሳችንን መመልከት እንድንችል ስለ ኃጢአታችን
የሚወቅሰንን መንፈስ ቅዱስን በማቅረብ ለንስሐ እና ለፈሪሃ እግዚአብሔር እንድንበረታ ያደርጋል። በዚህ ተመስጦ ውስጥ ከበገና ዝማሪያት ከምናገኘው መልእክት ጋር ተደምሮ የእግዚአብሔርን ቸርነት እና ለኛ ያለውን ጽኑ በምህረትና በይቅርታ የተሞላ የማያቋርጥ ፍቅሩን እንድናስተውል ይረዳናል። ይህ ሁሉ ተደምሮ በገና በቤታችን ጭምር ዕለት ዕለት አብሮን የሚኖር መሳሪያ መሆኑ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ያለው አስተዋጽኦ የጎላ ያደርገዋል።"
ለተመስጦ
ይቆየን...

1,733

subscribers

39

photos

18

videos