የንግሥ ጉዞ ወደ #የበረሃው_ገነት_አስደናቂው_ጋስጫ_ገዳም
* መነሻ ሐምሌ 5 ⏱ ከሌሊቱ 11:00
* መመለሻ ቀን ሐምሌ 8
* የጉዞ ዋጋ ስንሄድ ምሳን ጨምሮ 3000 ብር
ለበለጠ መረጃ፦
☞ 0901070707 / 0911289877
✥ ስለ አስደናቂው ጋስጫ ደብረ ባህርይ አባ ጊዮርጊስ እና አባ በጸሎተ ሚካኤል አንድነት ገዳም ምን ያህል ያውቃሉ?
☞ ከ12ኛው መ/ክ/ዘ ጀምሮ የታላቁ ጻድቅ አባ በጸሎተ ሚካኤል ጸሎተ በዓት የነበረ፣
☞ ዕውቁ የድጓ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ ከ47 በላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የጻፉበት ሙራደ ቃል በርካታ ደቀ መዛሙርት ያፈሩበት መካነ አእምሮ፣
☞ ከመጀመሪያው የቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጉባዔያት ማስመስከሪያ ሐይቅ ቅ.እስጢፋኖስ ቀጥሎ ዓቢይ መካነ ትምህርት የነበረ፣
☞ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለ10 ዓመታት ምነና እና የምንኩስናን ትምሕርት ከአባ በጸሎተ ሚካኤል የተማሩበት፣
☞ ከአቡነ በጸሎተ ሚካኤል እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ክቡር ዓፅማቸው በተጨማሪ የ6000 መናንያን ዓፅመ ቅዱሳን የሚገኝበት፣
☞ የሁለቱም ግኁሣን ቅዱሳን አበው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እና አባ በጸሎተ ሚካኤል እጅግ ጥንታዊና ታሪካዊ የዋሻ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙበት፣
☞ ከ95 - 130 ሜትር ቁመት ያለው ተራራ ላይ የተመሠረተ እና 46 ሜትር ቁመት ባለው መሰላል የሚወጣ ጥንታዊ ገዳም ነው፡፡
☞ ከአዲስ አበባ እሰከ ገዳሙ ድረስ በደሴ ከላላ 600 ኪ.ሜ በሙከጡሪ ዓለም ከተማ 270 ኪ.ሜ ብቻ ነው፡፡
✥ በገዳሙ ያሉ አስደናቂ አብያተ መቃድስና ታሪካዊ ቦታዎች፦
☞ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለ10 ዓመት የምንኩስናን ትምህርት የተማሩበት የአባ በጸሎተ ሚካኤል ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ፣
☞ በየዓመቱ የሰሙነ ሕማማት ከየት እንደሚመጣ የማይታወቅ ከአስደናቂ ኅብረ ቀለም ጋር ፬ እግሮችና ፪ ክንፍ ያለው እንስሳ ከመናኒያኑ ጋር ስግደቱን ጨረሦ ወዴት እንደሚሄድ ሳይታወቅ የሚሰወርበት፣ ሊቁ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋሻውን ካነፀ በኋላ ቅ/ሚካኤል በሰይፍ የሸነቆረለት ጣሪያው ክፍት ሆኖ ዝናብ የማያስገባው ጻድቁ የከበረ ቃልኪዳን የተቀበሉበት መካነ መቃብራቸው የሚገኝበት ተአምረኛው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ፣
☞ በገዳሙ በር ላይ ከመንገዱ ስር በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና በቅ/ኪዳነ ምሕረት ስም ከአንድ ወጥ ነጭ ድንጋይ የተፈለፈለ የዋሻ ቤተ መቅደስ፣
☞ ጻድቁ ካነጸው በኋላ የተሰወረውና በፈቃደ እግዚአብሔር በቁልቋልና እሾሃማ ዕፅዋት ታጥሮ በዘንዶና በነብር ዘወትር እየተጠበቀ ኅቡዓኑ ቅዱሳን አበው የሚርመሰመሱበት የግኁሣን በዓት ስውሩ ገዳም፣
☞ ያለምንም ማሰሪያ ሚስማርና ሐረግ (ገመድ) ሳይጠቀሙ የቅንጭብ እንጨቶችን በአስደናቂ ጥበብ በማወናገር ብቻ የተሰራ የገዳሙ መወጣጫ 46 ሜትር ጥንታዊ መሠላል፣
☞ በርካቶች ከጨጓራ፣ ከሆድ ሕመም፣ ከኩላላትና ከማንኛውም ዓይነት የውስጥ ደዌ የዳኑባት ተአምረኛዋ የጻድቁ መራሪት ጠበል፣
☞ እንደ ግሸን አንድ ብቻ የሆነውና ከአንድ ወጥ አለት ድንጋይ የተፈለፈለው አስገራሚ መግቢያና መውጫ በር፣
☞ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫና አባ ጽጌ ድንግል በእፍኝ
አፈር ረጭተው የጸናላቸው የእግዜር ድልድይ፣
✥ የገዳሙ ቃል ኪዳን ፦
👉 በበዓልህ ቀን ከቦታው የረገጠውን ባንተ ስም ለተራበ ያበላውን ለተጠማ ያጠጣውን በስምህ ቤተ ክርሰቲያን ያሳነጸውን በስምህ መባ ያስገባውን የማታልፍ መንግስትን አወርስልሃለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ገበቶላቸዋል፡፡
✥ በታላቁ ገዳማችን ውስጥ ያሉ ዓመታዊ ክብረ በዓላት፦
👉 የወርቃማው ዘመን ወርቃማ ደራሲ፣ መናኝ፣ ጻድቅ፣ ሊቅ፣ የሕዝብ መምህር፣ ፈላስፋ፣ የሥነ ምሕንድስና ባለሙያ፣ እንደ ሙሴ ኦሪትን የተረጎመ የተዋህዶ ጠበቃ “ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ ዐምደ ሃይማኖት”፣ “ለመናፍቃን መዶሻ የነገረ መለኮት ሊቅ ዳግማዊ ዮሐንስ አፈወርቅ”፣ “የድጓውና የጾመ ድጓው አደላዳይ ዳግማዊው ቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ”፣ መናኝ እንደ ኤልያስ፤ ልሳነ እረፍት አንደ ጳውሎስ፤ መሃንዲስ እንደ ላሊበላ፤ ኮከበ ክብር፤ ባህረ ጥበብ፤ በመለኮት ጨው የጣፈጠ፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በድርሰቱ ያንቆጠቆጣት ጥበበኛ፣ ታላቁ ምሁር ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
→ ጽንሰታቸው ጥቅምት 3 ቀን
→ ልደታቸውና ዕረፍታቸው ሐምሌ 7 ቀን በዓለ ንግሥ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።
👉 የታላቁ ጻድቅ የአባ በጸሎተ ሚካኤል
→ ግንቦት 21 በዓለ ልደታቸው፣
→ ሐምሌ 21 በዓለ ዕረፍታቸው፣
→ የካቲት 12 በዓለ ቅዳሴ ቤታቸው ዓመታዊ የንግሥ ክብረ በዓል በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ያሬዳዊ አገልግሎት ደምቆ ይከብራል፡፡
★ ወደዚህ ቅዱስ ስፍራ ታላቅ የበረከት ጉዞ ተዘጋጅቷል፤ ሊሞላ ጥቂት ወንበሮች ብቻ ናቸው የቀሩን።
✞❖✞ ጦማሩን አንብበው Share, Tag, Like, Comment & Forward... በማድረግ ለሌሎችም ያካፍሉት!
ጌታችን በወንጌል፦ “የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው። እውነት እላችኋለሁ፥ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም።” እንዳለ። ማቴ ፲፫፥ ፲፮- ፲፯
እነዚህን ቅዱሳት መካናት ተሳልሞ የቃልኪዳን በረከታቸውን ለማግኘት የታደለ ማን ነው?
• በጉዟችን የምንሳለማቸው ቅዱሳት መካናት፦
→ ደብረ ባሕርይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም (ዋሻ)፣
→ ጋስጫ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም (ዋሻ)፣
→ ደብረ ጽጌ አባ ጽጌ ድንግል ገዳም (ዋሻ)፣
→ ተአምረኛው ደብረ መድኃኒት አቡነ መልከ ጼዴቅ ገዳም (ዋሻ)፣
→ ጥንታዊው በልበሊት ኢየሱስ ገዳም፣
→ ታሪካዊቷ ትርንጎ ማርያም፣ እና ሌሎችም...
✞❖✞ እነዚህን ቅዱሳት መካናት መሳለም የምትሹ ኦርቶዶክሳዊያን ሁሉ ይደውሉልና አብረውን ይጓዙ!
👉 0901070707
👉 0911289877
ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
• ባላችሁበት አካባቢ ትኬት ለመቁረጥ (ለምዝገባ)፦
👉 በሚከተሉት የመ/ር አንተነህ ውብሸት የባንክ አካውንቶች በካሽ (በሞባይል ባንኪንግ) አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ።
☞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000099794899
Swift Code: CBETETAA
☞ አቢሲኒያ ባንክ 73439825
Swift Code: ABYSETAA
☞ አሐዱ ባንክ 0042939910101
☞ አማራ ባንክ 9900001752271
☞ ዓባይ ባንክ 1931019728607012
☞ አዋሽ ባንክ 01320104564900
☞ ዳሽን ባንክ 5248723384011
☞ ቴሌ ብር 0901070707
* መነሻ ቀን ሐምሌ 5
* መመለሻ ቀን ሐምሌ 8
* መነሻ ቦታዎች፦ መገናኛ አደባባይ እና አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ
#ማሳሰቢያ:-
🎫 መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ልትይዙ ይገባችኋል።
🌌 አካባቢው የመንገድ መብራት ስለሌለው የእጅ ባትሪ ይያዙ፤
🥾 የምንሳለማቸው ገዳማት የእግር መንገድ ስላላቸው ቀድሞ መዘጋጀትና ሽፍን ጫማ ማድረግ ይገባል።
✥✞✥ ጽሑፉን ሌሎች እንዲያነቡትም Like እና Share ያድርጉ፤ ፔጁን Like / Follow በማድረግ ያግዙን።
👇 በቴሌግራም ይቀላቀሉን 👇
☞ @waldiba
☞ @negeretewahido
❖ የዩቲዩብ ቻናላችንን « መኮሬታ Mekoreta Tube »ን በሚከተለው ሊንክ ከፍተው Subscribe, Like, Share, Comment & Copy Link በማድረግ ያግዙን
☞ https://youtube.com/@mekoreta