ኢንፍራኮን ሚዲያ - Infracon Media

@infraconmedia


Stay connected and informed with Infracon Media!
Please call 0979060678 or contact https://t.me/infraconmedia

ኢንፍራኮን ሚዲያ - Infracon Media

22 Oct, 11:30


ኦቪድ ግሩፕ በፒያሳ የንግድ ሞሎችንና የመኖሪያ ቤቶችን ለፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሊገነባ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንና ኦቪድ ግሩኘ የፒያሳ መልሶ ማልማት አካል የሆኑ ዘመናዊ የንግድ ሞሎችንና የመኖሪያ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።

የግንባታ መግባቢያ ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል እና የኦቪድ ግሩኘ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዮናስ ታደሰ ተፈራርመዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ የፒያሳ መልሶ ማልማት አካል በሆነው 9.5 ሄክታር መሬት ላይ አራት ግዙፍ የንግድ ሞሎችንና የመኖሪያ ቤት ግንባታን በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ማስረከብ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ስምምነቱ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የንግድ ሱቆችን፣ ሞልና መዝቦልድ ሞል እንዲሁም የጣይቱ የመኖሪያ አፓርትመንት በአልሙኒየም ወርክሾፕ ቴክኖሎጂ ሠርቶ በተያዘው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ መሆኑ ተጠቅሷል።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል፥ ኦቪድ ኩባንያ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በሥራ ላይ እያዋለ የሚገኝ ተቋም በመሆኑ ስምምነቱን ታሪካዊ ያደርገዋል ብለዋል።

ስምምነቱም የመንግሥትና የግል አጋርነት ትብብርን በማሳደግ አዲስ የሥራ ባህል እንዲፈጠር የሚያደርግ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።

ኦቪድ በሦስት ወራት ውስጥ እጅ አጠር ለሆኑ ዜጎች ቤትን ገንብቶ በማስረከብ፤ ከተሠራ ለውጥና ስኬት ማምጣት እንደሚቻል ያስመሰከረ ኩባንያ መሆኑን ተናግረዋል።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በፒያሳ መልሶ ልማት የሚያስገነባቸውን የንግድ ሞልና መኖሪያ ቤቶችም በፍጥነትና በጥራት አጠናቆ እንደሚያስረክብ እምነታቸው መሆኑን ገልፀዋል።

ኢንፍራኮን ሚዲያ - Infracon Media

21 Oct, 09:02


አደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም እየመጣ ነው
🎆🌠🌄
ከአምስት አመት በኃላ የሚካሄደው 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት የያዘችው እቅድ ለማሳካት ጥረቶች እየተካሄዱ መሆኑን ለማስተዋል ይቻላል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔን እና ከካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የአደይ አበባ ስታዲየምን በጋራ ጎብኝተዋል።

በታህሳስ 2008 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረ የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም 62 ሺህ ሰዎችን በወንበር የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን፣ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ከተጠናቀቀ በኃላ በቅርቡ ሁለተኛው ምዕራፍ ተጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በግላቸው ባደረጉት ጥረት የውጭ ምንዛሬ የሚያስፈልጋቸው የሁለተኛ ምዕራፍ ሥፍራዎችን ወጪ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግሥት ለመሸፈን መስማማቱ የሚታወስ ነው።

የስታዲየሙ ግንባታ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) እና የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ማስተናገድ በሚችል ደረጃ ሁለተኛው ምዕራፍ እየተገነባ እንደሚገኝ ታውቋል።

ለብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ ለመጀመሪያው ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ የሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ ጣሪያ ማልበስ፣ ወንበር መግጠም፣ የሰው ሰራሽ ሀይቅ ግንባታ፣ ዘመናዊ የደህንነት ካሜራ መግጠም፣ ሳውንድ ሲስተም መዘርጋት፣ የፓርኪንግ ቦታዎች፣ የተጫዋቾች የመለማመጃ ሜዳ እና ሌሎች ሥራዎችን በውስጡ አካቷል።

ኢንፍራኮን ሚዲያ - Infracon Media

13 Oct, 08:05


ደረጃቸውን ያልጠበቁ ግንባታዎችን የሚያከናውኑ ላይ ከእስራት እስከ ፈቃድ ዕገዳ ቅጣት የሚጥል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ
▬▬
ደረጃቸውን ያልጠበቁ ግንባታዎች በሚያከናወኑና ሌሎች የወንጀል ድንጋጌዎችን የሚጥሱ ባለሙያዎች፣ የሥራ ተቋራጮችና አማካሪዎች ላይ ከእስራት እስከ ፈቃድ ማገድ ቅጣት የሚጥል በሕንፃ ረቂቅ አዋጅ ተካቶ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡

ረቂቁ የቀረበው ሐሙስ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በተካሄው ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አራተኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ ስብሰባ ነው፡፡ በረቂቅ አዋጁ ክፍል ዘጠኝ የተቀመጠው አስተዳደራዊ የወንጀል ቅጣቶችን በተመለከተ፣ አዋጁን ለማስፈጸም የሚወጡ ድንጋጌዎችን በሚተላለፉ ሰዎች ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ ይደነግጋል፡፡

በአሠሪ ስለሚፈጸሙ ወንጀሎች፣ የአማካሪነት የሙያ ኃላፊነት መጣስና በረቂቅ አዋጁ የተቀመጡ ዝርዝር ድንጋጌዎችን ተላልፈው የተገኙ ግለሰቦች፣ የሥራ ተቋራጮችና የሚመለከታቸው አካላት በፍርድ ቤት ጥፋተኛ በተባሉበትና አንቀጽ እስከ ተመለከተው ከፍተኛ እስራት ዘመን ቅጣት በተጨማሪ፣ የሙያ ወይም የሥራ ፈቃዳቸው እንደሚታገድ ተደንግጓል፡፡

በሕንፃ በረቂቅ አዋጅ ዘጠኝ የተቀመጠው አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶችን በተመለከተ፣ አዋጁን ለማስፈጸም የሚወጡ ድንጋጌዎችን በሚተላለፉ ሰዎች ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ በረቂቁ ተመላክቷል፡፡

ያላግባብ በተሰጠ የግንባታ ፈቃድ፣ እንዲሁም የመቆጣጠር ግዴታን ባለመወጣት ሕገወጥ ግንባታ እንዲከናወን የረዳ ግለሰብ ከአምስት ዓመታት እስከ አሥር ዓመታት የሚደርስ ፅኑ እስራት፣ ከአሥር ሺሕ ብር ጀምሮ እስከ አምስት ሺሕ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚቀጣ ተደንግጓል፡፡

ደረጃው የማይፈቅድለት ወይም ተገቢው ፈቃድ ሳይኖረው ግንባታ ያከናወነ ግለሰብ (ሥራ ተቋራጭ) እስከ አሥር ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራትና እስከ አሥር ሺሕ የሚደርስ የገንዘብ መቀጫ እንደሚቀጣ በረቂቁ ተዘርዝሯል፡፡

ማንኛውም የተመዘገበ የሥራ ተቋራጭ ደረጃውን ያልጠበቀ ግንባታ ሲያከናውንና ግንባታው አደጋ ያስከተለ ከሆነ፣ ከአምስት ዓመታት እስከ አሥር ዓመታት ፅኑ እስራትና ከ50,000 እስከ 100,000 ብር እንደሚቀጣ በረቂቁ ተቀምጧል፡፡

የሕንፃ ረቂቅ አዋጅ የሕዝብ ጤንነትና ደኅንነት መጠበቅ፣ የሕንፃ ተደራሽነት ለአካል ጉዳተኞችና ለሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ለማረጋገጥ የሚያስችል፣ በአገሪቱ በአጠቃላይ ተፈጻሚ የሚሆን ዝቀተኛውን ደረጃ ለመወሰን አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ነባሩ ሕግ በአፈጻጸም ወቅት የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ስላሉበት፣ የአካል ጉዳተኞችን ተደራሽነት የሚያረጋግጥ፣ የግንባታ ጥራትና የሀብት ብክነት ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ግልጽና ለአተገባር ምቹ የሆኑ አሠራር መዘርጋት ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቁ አዋጅ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

ረቂቁ በአሥር ክፍሎችና በ54 አንቀጾች የተዋቀረ መሆኑን፣ የተፈጻሚነት ወሰኑ ስለሕንፃ ግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ፣ ክትትልና ቁጥጥር፣ አስፈጻሚ አካላት ተግባርና ኃላፊነት፣ አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶችን የተመለከቱን ጨምሮ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ተካተውበታል፡፡

የሕንፃ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 2/2017 ሆኖ ለፓርላማው የከተማ መሠረተ ልማትና ትርንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡ (Reporter)

በቴሌግራም ይከተሉን
t.me/infraconmedia

ኢንፍራኮን ሚዲያ - Infracon Media

11 Oct, 05:18


የበለስ - መካነ ብርሃን አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ 75.2 በመቶ ደረሰ

▬ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ይፈጃል
▬ መከላከያ ገንቢ፣ በለስ አማካሪ ነው
📈📈📈📈📈📈📈📈📈
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የደባርቅ እና ጃናሞራ ወረዳዎችን የሚያገናኘው የበለስ - መካነ ብርሃን አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ አፈጻጸም 75.2 በመቶ ደርሷል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ 36.42 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲኾን፥ ግንባታው በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ እየተካሄደ ይገኛል። በለስ ኮንሰልቲንግ የግንባታውን ጥራት የመቆጣጠር እና የማማከር ሥራ ይሠራል።

አሁን ላይ እየተሠሩ ከሚገኙ ዋና ዋና ሥራዎች መካከል የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የሰቤ ቤዝ፣ የውሃ መፋሰሻ ቱቦ እንዲሁም የጠጠር ማምረት ሥራዎች ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም የአስር አነስተኛ እና ከፍተኛ ድልድዩች ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቋል።

ለግንባታው የተመደበው ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በፌደራል መንግሥት ነው የሚሸፈነው።

በአካባቢው የሚስተዋለውን ተደጋጋሚ የጸጥታ ችግር ተከትሎ የግንባታ ጥሬ እቃ እና ማሽነሪዎች በቀላሉ ማቅረብ አለመቻል እንዲሁም የሥፍራው አስቸጋሪ መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥ የፕሮጀክቱ ፈተና መኾናቸው ተመልክቷል።

የመንገዱ መገንባት በተለይም በመንገድ እጦት ተራርቆ የቆየውን ሕዝብ በቅርበት እና ደረጃውን በጠበቀ መንገድ የሚያገናኝ ነው። በመንገዱ ክልል እና በዙሪያው የሚገኙ የበለስ፣ ወይና፣ ሚጊራ እና መሰል ከተሞች ዕድገት ያፋጥናል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ቀድሞ ይወስድ የነበረውን 8 ሰዓት የጉዞ ጊዜ ወደ 1 ሰዓት ያሳጥረዋል።

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መዳረሻ እንደመኾኑም የቱሪዝም ዘርፉን በማነቃቃት በኩል የጎላ ሚና ይጫወታል።

በቴሌግራም ይከተሉን
t.me/infraconmedia