አቡ አዒሻ العلم نور

@hussenhas


የዚህ ቻናል ዋና አላማ ሱናን ማንገስ ሽርክን ማርከስ ነው!!

የሱና መሻይኮችና የሱና ዳዒዎች የሚላክበት የዳዕዋ የደርስ ሴንተር ቻናል ነው

ሐሳብ አስተያትን ያለምንም ጥበት እንቀበላለን

ቅድሚያ ለተውሂድ በተግባር

አቡ አዒሻ العلم نور

22 Oct, 16:45


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ውድና የተከበራችሁ የሃራ ውላጋ እና አካባቢዋ የምትገኙ ብርቅየ ሰለፍዮች ሆይ አዋጅ ስሙ ‼️

እንደሚታወቀው ሱናን መርዳት ያለብን በተግባር በሁለተናችን በምንችለው አቅም መጠናከር ስላለብን ይህ ወር የከስብ ወር እንደሆነ የሚታዎቅ ነገር ነው

በጤፍ አጨዳ በማሽላ ጋጠጣና ቆረጣ የመውቃትና የአገዳ መከመር ሂደቱ ይቀጥላል መሰል የግብርና ስራላይ ለተሰማሩ የሱና ወንድሞችንና እንድሁም የየቲሞችን በጠና ታመው ከስብ መከሰብ ለማይችሉ አቅም ያጠራቸውን ወንድሞቻችን ችግራቸው የኛም ችግር እንደሆነ አውቀን ልናግዛቸው ከጎናቸው ልንቆም ይገባል አላህ እኛንም ያግዘናል ይረዳናል በባለፉት አመታቶች ለምን ድናችሁን ተማራችሁ በማለት ለድን ትኩረት በሰጠት የሱና ወንድሞች ላይ ካሃገር ከቀየ ከዕድርና ቅሬ ማሓበራውይ ኑሮ በቀላሉ ከህዝበ ሙስሉሙ ጋር ተረዳድተው እንዳይ ሰራ በማሴር ሲሳደዱ የነበሩ የሱና ሰዎች ነበሩ

እኛም በምንችለው ከጎናቸው እንደሆን በተግባር አብሮነታችነን አሳይተናል ከነሱ ጋር አረም በማረም አጨዳ በማጨድ አገዳ በመጋጠጥ በመውቃትና እንድሁም የመኖሪያ ቤት ሳይቀር ሰርተናል አሁላይ በዳዕዋ መስፋፋት ምክኒያት ትልቅ ተፅኖ ፈጥሮ ትናንት ባይተዋር ብቸኛ የነበሩት የሱና ወንድሞች ዛሬ ብዝተው ተባዝተው ለራሳቸው አልፎው ለሌላም የሚተርፉ ኡማ ሁነዋል አልሃምዱሊላሂ ረቢል አለሚን ለዛ ነው

ዘንድሮ የግብርና ስራላይ የእርዳታ ጥሪ ያልተደረገው ለውጥ አለ ከባለፈው አመት

ስለሆነም ለየቲሞችና ታመው መከሰብ ያልቻሉ የሱና ወንድሞችን  እንድሁም ለሰራተኛ የሚከፍሉት ገንዘብ አጥተው የሚሳሱለትን አዝመራቸውን በዝናብና መሰል የሸተውን አዝሪት የነሱ ወደ ኋላ በመቅረት ከብት ሊነጥቃቸው ያሉትን የሱና ዎንድሞቻችን በገንዘባችን በጉልበታችን አሁንም መርዳት አለብን እንረዳቸው

ስለሆነም ነገ ታሪክና አሻራ ጥለን ለመመለስ አስበናል እናንተም ያአጅሩ ተካፋይ ሁኑ ኑኑኑ የፊታችን እሮብ ጥቀምት ቀን/13/2017/ነገ እሮብ አንድ የሱና ወንድማችን በጠና  ታሞ ቆይቷል አሁላይ ከህመሙ ቢገግምም ከስብ ለመከሰም አልቻለምና በመተኛቱ ምክኒያት ጤፉ ሊፈስበት ስለሆነ ነገ በመስጅዴ ሶፋ ግቢ በመገኘት ተሰባስበን ጉዞ ወደ አላ ውሃ ይሆናል እንዳትረሱ አስታውሱ

 
የነገ ስምሪታችን ኢንሻ አላህ ወደ አላ ውሃ ይህ ወንድማችን የቀዶ ህክምና ቆይታ ስለነበረው ተቀምጦም ቆሞም ስራ መስራት ስላልቻለ ካለበት ሃሳብ እንታደገው በምንችለው አቅም አይዞህ ልንለው ይገባል

ማሳሰቢያ ለአዝመራው መሰተሪያ የሚወሉ መሳሪያዎችን የመሰተሪያ ግባአቶችን እንዳንረሳ እነሱም ጋሽ ማጭድ ናቸው የለለን በጎረቤት ለምነን ቢሆንም ይዘን መገኘት  አለብን እንዳንረሳ ከሱቢሂ ሶላት ቦኋላ ወደ ተባለው ቦታ በጧት ስለምናመራ እንዳታረፍዱ አደራ አጭደን ከምረን ነገሩን አሳምረን ለቁርስ በጧት መመለስ እንዳለብን ንያ እንናፍስ _

ባረከሏሁ ፊኩም

ጥቅምት ቀን/13/2017የፊታችን እሮብ
https://t.me/hussenhas
ሃራ ውላጋ
https://t.me/hussenhas

አቡ አዒሻ العلم نور

20 Oct, 17:32


የውላውላ ፕሮግራም የዳዕዋ ሂደት ↩️

ርዕስ"

በጥያቄና መልስ ዙሪያ የተወሳበትና መልስ የተሰጠበት ⁉️

1.በሞተ ሰው ኢስቲጋሳ መጠየቅና ሙሽሪኮችን ሶላት ተከትሎ መስገድ እንድሁም ያረዱትን መብላት እንደት ይታያል ይብራራልኝ ይላል ???

2.ካገር እንዳል ወጣ ብሎ ቅጣ መቀጣት እንደት ይታያል ?

3.እነዚህ ወህብዮች እምነታቸውን የያዙት ከመሃመድ አብዱል ወሃብ ዘመን ወድህ ነው
እንጅ ከዛ በፊት የዚህ አይነት እመለካከት አልነበረም እያሉ ይላሉና ስለሱ ምን ይመክሩናል ?

4. አንድ ሰው ሲሞት ተሰብስቦ ያሲንንና ፋቲሃን መቅራት እንደት ይታያል ስለሱስ ምን ይመክሩናል ?

5.አንዳድ ሰዎች አነዚህ ወህብዮች ሰላዋት አይወዱም ሶደቃ በልተው ፋቲሃ አይሉም ዱዓ አወዱም ሸይኽ አያከብሩ ሶሃባዎች ተሰብስበው በሙታን ላይ ፋቲሃን ቀርተዋል እያሉ ይላሉ ሰለሱ ምን ይመክራሉ በዚህ ዙሪያ ?????

6.አንዳንድ ወንድሞች ልጆቻቸውን መድረሳ ከመላክ ተገድበዋል ምክኒያት እንቀጣለን በማለት ፈርተው ከዕንደዚህ አይነት መደረሳ ከላካችሁ ትቀጣላችሁ ሰለሚባሉ ምን ይመክሩናል?

7.በአካባቢያችን የመሴት ዶሪህ አለ ኪታብ ፅፋለች ይባላል ስለሷ ምን ያውቃሉ?

8.አንዳንድ ሰዎች ወደ ተውሂድ ኑ ስንላቸው እናተ ከነ ሸይኽ እከሌ ትበልጣላችሁ እንደ እነሱ እሱን አልጠቆሙነም በማለት ይላሉ ?

🎙 በሸይኽ ሙሐመድ ሃያት
{ሃፊዘሁሏህ}

https://t.me/hussenha

ጥቅምት ቀን/08/2017

አቡ አዒሻ العلم نور

20 Oct, 11:13


🕌 ↪️መስጅድ አልፉርቃን ውላውላ

በኡስታዝ ሱልጧን ሀሰን ሀፊዘሁአሏህ

🗒እርዕስ አልስቲቃማህ በሚል

አሏህ ሱብሀነሁወተአላ እዳዘዘን
ግራኝ ቀኝ ሳንል መፅናት ቀጥ ማለት
እንዳለብን መጨመር መቀነስ
♻️እንድሁም ሙሽሪኮችጋ ሙብተድኦችጋ
መደመር አሏህ እንደከለከለን መጠንቀቅ እንዳለብን በሰፊው ተብራርቶል
📚አንድ የሚደርገን ተውሂድ ነው !

ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር አድርጉ
↙️↙️↙️↙️↙️↙️↙️↙️
https://t.me/YweIaweIachanneI
https://t.me/YweIaweIachanneI

አቡ አዒሻ العلم نور

20 Oct, 10:24


የውላውላ ፕሮግራም የዳዕዋ ሁኔታ ሂደቱ ↩️

ርዕስ"
ቅድሚያ ለተውሂድ በተግባር

ተውሂድ የነብያቶች ሁሉ ጥሪ የመጀመሪያው ተውሂድ ነው

📚 ቁርዓን ሁሉ ሰለተውሂድ ሳይናገር ሳያዎሳ አያለፍም ቁርአን ሁሉ ተውሂድ ነው

ስለተውሂድ መማርና መናገር ትልቅ የሆነ ነጃ የመውጫ መንገድ ነው

ነብዩሏህ ኢብራሂም ለተውሂድ ሲሉ እሳት ላይ ተወርውረዋል አላህ በቂየ ነው
ምንኛ መጠጊያና ያማረ መሸሺያ ነው
ብለው ወደ አላህ ነገራቸውን አስጠግተዋል ከእሳትም ተጠብቀዋል።

ለየትኛውም ስራ ያለተውሂድ ተቀባይነት አይኖረውም

በውስጡ ስለተውሂድ አስፈላጊነትና የመጀመሪያ የነብያቶች ዋና መሰረቱ ተውሂድ እንደሆነ በሰፊው ተወስቶበታል ተዳሷል

🎙 በኡስታዝ ሙሐመድ ሰልማን
{ሃፊዘሁሏህ}

🕌 መስጅደ ፉርቃን ውላውላ

🗓 ጥቅምት ቀን /08/2017/እለተ ጁሙዓ

https://t.me/hussenhas

አቡ አዒሻ العلم نور

20 Oct, 09:51


🔭በውላውላ መስጂድ አልፉርቃ

🔭በኡስታዝ አብዱሮህማን ሰኢድ ሀፊዘሁአሏህ↪️ ነሲሀ ስለሂጃብ

↗️በሂጃብ ማሀበረሰባችን እንደሚታወቀው ደካማ ነው
↗️🎙ሂጃብ ትዝ የሚላቸው ጀበና እና ረከቦት ሲቀርብነው!

↗️🎙ነገር ግን ሂጃብ በደስታም በሀዘንም
በማንኛውም ሁኔታችን የማይለየን የአሏህ ሱብሀነሁ ወተአላህ ትእዛዝ ነው !
ሂጃብ ሌሎች እንደሚሉት የአፍጋኒስታን ፋሺን አይደለም!

↗️እንድሁም ለወንድሞች ጠቃሚ ምክር ተሰጥቶበታል ➡️ግዜን በአግባቡ እንጠቀም
↗️ለቤተሰብ ሸክም አንሁን ጫት ሁለነገራችንን ይጨርሳል //ግዜ ሰይፍ //እንቃ ሳይቆርጠን !

↙️↙️↙️↙️↙️↙️↙️
https://t.me/YweIaweIachanneI
https://t.me/YweIaweIachanneI

አቡ አዒሻ العلم نور

20 Oct, 06:11


📢ዳዕዋ ዳዕዋ ዳዕዋ

ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም ዝግጅት ጥሪ 👌

ውድና የተከበራችሁ የሱና እህቶችና ወንድሞች በያላችሁበት ቦታ ሁናችሁ ያአላህ እርዳታ አይለየን አይለያችሁ እነሆ ዛሬም በደጋሜ ብቅ ዘለቅ ብለናል ሱናን ለማስፋፋት ቢዳዓን ለማጥፋት በፍፁም ማንቀላፋት አይሻም አያስፈልግምና እንዳንሰላች የዳዕዋ ቦታዎችን ሁላችነም እናመቻች በገጠርም በከተማም የተውሂድ ጥሪ ከምንም በላይ ተጨማምሮ የበላይ መሆን አለበት የባጢል ሰዎች ይርበትበቱ

🗓 የፊታችን ማክሰኞ  ማለትም ጥቅም ቀን /12/2017/ በአይነቱ ለየት ያለ የዳዕዋ ዝግጅት ፕሮግራም ተደግሶለታል ስለሆነም ሁላችሁም  ታድማችኋላ የዝግጅቱ ቦታ እራያ ወርቄ ያያሆሞ ቆቦ ወረዳ  የምትገኝ ገጠር ቀበሌ ነች በዛች ቦታና አካባቢ ላይ የሽርክና የቢዳዓ መነኻሪያ ሁኖ ይስተዋላል

🟢 ምርቱን ከገለባው ኡማው ማወቅ አለበት  ትልቅ የምክር ክትባት የሚከተብበት ስለሆነ ችላ ብለው እንዳይቀሩ ያስታውሱ እንዳይረሱ

🪑 በቦታው ላይ ተጋባዥ እንግዶቻችነን እነሆ ብለናል ↩️

1.ሸይኽ ሙሃመድ ሃያት ከሃራ
2.ሸይኽ ሁሴን አባስ ከወርቄ
3..ሸይኽ ሁሴን ከረም ከሃራ
4.ኡስታዝ ሱልጧን ሃሰን ከሃራ
5.ኡስታዝ ሙሃመድ ሰልማን ከሃራ
6.ኡስታዝ ኑራድስ ከመርሳ
{ሃፊዘሁሏህ}ጀሚአን

ርዕስ> በእለቱ የሚነግገር ይሆናል

🟢 ኢንሻ አላህ ሌላም ተጋባዥ እንግዳ ይኖረናል

በራያ ወርቄና አካባቢዋ የምትገኙ ሙስሊምች በሙሉ በተባለው ቀንና ቦታ በመገኘት የዳዕዋው ተካፋይ ይሁኑ ኑኑኑ

ፕሮግራሙን ለመከታተል ሊንኩን በመጫንይቀላቀሉ።

በቻናል እና በጉርፖች ሸር በማድረግ ሃላፊነታችነን እንወጣ

ጥቅምት ቀን /12/2017/ የፊታችን ማክሰኞ የራያ ወርቄ የያያሆሞ ሰለፍያ ጀማአዎች

https://t.me/hussenhas

አቡ አዒሻ العلم نور

18 Oct, 18:10


ዛሬ የውላውላ የመጀመሪያ ጁሙኣ ሶላት የተቋቋመበት ቀን ነው
ጥቅምት ቀን /8/2017/ታሪካውይ ቀን ና
____

የጁሙዓ ኹጥባ ወሳኝ ምክር

ርዕስ"
ሙሐመድ የአላህ መልክተኛ ናቸው ሲባል ምን ማለት ነው

ባዘዙት ነገር ሁሉ መታዘዝ
በተናገሩት ሁሉ ዕውነት ማለት
የከለከሉትን በልቅም ይሁን በዝርዝር መራቅ መጠንቀቅ ነው

በውስጡ ጠቃሚ ፋኢዳዎች ተወስተውበታል

🎙 በሸይኽ ሙሃመድ ሃያት ሃራ
[ሃፊዘሁሏህ]

🕌 መስጅደ ፉርቃን ውላውላ

🗓 ጥቅምት ቀን /8/2017/እለተ ጁሙአ በሰላም ተፈፀመ

https://t.me/hussenhas

አቡ አዒሻ العلم نور

18 Oct, 17:47


የዉላዉላ ፕሮግራም የዳዕዋ ሁኔታና ሂደቱ ↩️

ርዕስ"
💥 ሽርክን ማስተዋዎቅና አይነቶችን መግለፅ

🟢 ከአለህ ውጭ ሌላን ድረሱልኝ ማለት ልጅ ስጡኝ ያላቱ ማን አለኝ ብሎ በነሱ መመካት መጠጋት የጠቅማሉ ይጎዳሉ በሎ ማመን ሽርክ ነው

🟢 አላህ የሽርክን ወንጀል አልምርም በማለት ተናግሯል ከሽርክ ውጭ ያለን ወንጀል ለሻው ይምራል ከቀጣውም በጥፋቱ ልክ ይቀጣዋል

💥የሽርክ ወንጀል ትልቅ በደል ነው ጀነት መግባት አይችልም በአላህ የሚጋራ ሰው ዘላለም አለሙን በጀሃነም መቃጠል ነው

ተውሂድ የጀነት ዋስትና የነብዩን ሸፈኣ ምልጃን ለማግኘት ሰበብ ምክኒያት ነው

💥 ሸርክ የአንድን ሰው ደምና ገንዘቡን ሃላል ያደርዋል

🎙 በሸይኽ ሁሴን ከረም ሃራ ውላጋ
[ሃፊዘሁሏህ]

🕌 መስጅደ ፉርቃን ውላውላ

🗓 ጥቅምት ቀን /8/2017/ እለተ ጁሙዓ በሰላም ተጠናቋል

https://t.me/hussenhas

አቡ አዒሻ العلم نور

18 Oct, 17:13


የውላውላ ፕሮግራም ዳዕዋ ሁኔታና ሂደቱ↩️

ርዕስ"
የተውሂድ አስፈላጊነትና የሽርክ አስከፊነት

💶 ሰዎች በገንዘባቸው እራሳቸው ገበያ ላይ ገዝተውት ከበሽታ ያድኑናል በማለት የፃጉር ከረን በመምረጥ  የሚያምኑት ብዙሃን ናቸው

አንበሶ ጨንገር ቀይ ቆልማ ጥቁር ቆልማ አይነ ኩልሌ ሎልማ  ነጨበላ ጥቁረበላ በማለት ለጅን ለቆሌ ለዛፍ መጥቻ ማረድ ለዶሪህ ማረድ ትልቅ ሸርክ ነው።

🟢 ማነም ቢሆን ማነም ቢመጣ ከአላህ ውጭ ጠቃሚና ጎጅ የለም የሚጠቅመው አላህ የሚጎዳው አላህ የሚሰጠው አላህ የሚነሳውም አላህ ነው።

ስለሆነም ወደ አላህ እንመለስ አላህን በአምልኮ ዘረፎች ላይ  በብቸኝነት ነጥለን በኢኽላስ እናምልከው እንገዛው የሞተሰው አይጠቅምም ዶሪህ መገንባት እረገማን አለበት አብዶየ ሸይኽ እገሌ ልጅ የሰጡኛል ካለሁበት ጭንቅ መከራ ያዎጡኛል ማለት በአላህ ላይ ማጋራት ነው

🎙 በኡስታዝ አብዱረህማን መርሳ
{ሃፊዘሁሏህ}

🕌 መስጅደ ፉርቃን ውላውላ

🗓 ጥቅምት ቀን/8/2017/ጁሙዓ በሰላም ተጠናቀቀ አንደኛ ዙር የምክር ክትባቱ
ሁለተኛው ዙር ቢኢዝኒላህ ይቀጥላል

https://t.me/hussenhas

አቡ አዒሻ العلم نور

17 Oct, 08:58


🔊📢 ዳዕዋ ዳዕዋ ዳዕዋ

ታላቅ የዳዕዋ ዝግጅት ጥሪ በሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ ቀበሌ ቁጥር(021) ጥቅምት ቀን /8/2017/የፊታችን ጁሙዓ የውላውላ ሰለፍዮች ሁላችሁንም ጋብዘዋችኋል ስለሆነም መቅረትና በቦታው ላይ አለመገኘት የኋላ ኋላ ነዳማና ፀፀትን ያዎርሳል  በአይነቱ ለየት ያለ የዳዕዋ ፕሮግራም ዝግጅት ሲሆን በቦታው ላይ በአካል በመገኘት የዳዕዋው ተቋዳሽና ተካፋይ ይሁኑ ያስታውሱ እንዳይረሱ ቦታው ላይ በጣፋጭ አንድበት ንቁና ብርቅየ የሆኑ ምክርን ፈትፍተው የሚያጎርሱ መሻይኮችና ኡስታዞች ዳዕዋ ሰለፍያ ያፈራቸው ትላልቅ እንግዶችም ይገኙበታል የዛኔ ይለያል

🪑 ታጋባዥ እንግዶቻችን እነሆ ብለናል↩️

🎙1_ሸይኽ ሰይድ ሙሀመድ  ከሃራ
🎙2- ኡስታዝ ኑር ሞላ         ከሃራ
🎙3-ኡስታዝ ሙሃመድ ሰልማን  ከሃራ
🎙4-ሸይኽ ሙሐመድ ሃያት     ከሃራ
🎙5-ኡስታዝ ኑራድስ ሙሀመድ ከመርሳ
🎙6_ሸይኽ ሙሐመድ ሲራጅ  ከሀሮ
🎙7- ሸይኽ ሁሴን ከረም    ከሀራ
🎙8_ኡስታዝ አብዱረህማን ከሰዶማ
🎙9-ኡስታዝ  ሱልጧን ሃሰን ከሃራ
{ሃፊዘሁሏህ} ጀሚአን>

ርዕስ በእለቱ የነገራን ይገለፃል

🟢 ኢንሻ አላህ ሌላም ተጋባዥ እንግዶች ቦታው ላይ ይኖሩናን በውላውላና አካባቢዋ የምትገኙ ሙስሊምች በሙሉ በተባለው ቦታ ላይ ተገኙና ከሽርክ ወረርሽኝ ታከሙ ከሽርክ ከቢዳዓ ከመሰረተቢስ እምነት ከአስቀያሚ ተግባራት ለመራቅና ለመጠንቀቅ ለመጠበቅ ያስችላችኋልና ታድማችሁል ኑኑኑኑኑ

በተባለው ቦታ በጧት በመገኘት ከጅማሮው እስከፍፃሜው ድረስ ለመጠቀም ከጧቱ 2:ዐዐ በታባለው ቦታ ላይ መገኘት ትልቅ ጥቅም አለውና እንዳታረፍዱ አደራ ተብላችኋል

🔄ሙሉ ፕሮግራሙን ለመከታተል ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ

በታለያዩ ቻናልና ጉርፖች ላይ ሼር በማድረግ ሁላችነም ሃላፊነታችነን እንወጣ

የፕሮግራሙ አዘጋጆች

የውላውላ ሰለፍዮች ጀመዓወች

🗓 ጥቅምት ቀን/8/2017/የፊታቻን ጁመዓ
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
https://t.me/YweIaweIachanneI

https://t.me/hussenhas

አቡ አዒሻ العلم نور

15 Oct, 03:36


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
የተከበራችሁ እህትና ወንድሞች ውድ ሰለፍዮች
ለአሏህ ስል ሁላችሁንም እወዳችሗለሁ

እናም ስለምወዳችሁ እኔ እምወደውን ነገር ለናንተም ስለወደድኩላችሁ
((كما قال النبي صلى الله عليه وسلم لايؤمن أحدكم حتى
يحب لأخه مايحب لنفسه
ስላሉ እናም እኔ የምወደውን አቂዳ ወድኩላችሁ ኑ ኑኑኑኑኑኑኑኑ
እንቃራ ስለ እምነታችን

በሰሜ ወሎ ዞን በሃራ ከተማ አስተዳደር 🕌 መስጅዴ ሶፋ ኢስላማውይ እውቀትን ሸምታችሁ የእውቀት አቅማድችሁን ሞልታችሁ እናንተም ትጠቀማላችሁ ኡማውንም ትጠቅማላችሁ ኑ ወደ እውቀት ሴንተር ሃራ ከተማ አስተዳደር የእውቀት ማአከል ሁኖ ታገኙታላችሁ ድናችነን እንማር እንቅራ እንወቅ የነገ የአኼራ ስንቅ ነውና የአቂዳ ኪታቦችን የሓድስ የፊቅህ የሶርፍ የነህው ኪታቦችን ለመማር ወደ ሃራ ውላጋ ይዝለቁ ጠቃሚ የሆኑ ኢስላማውይ የኪታብ አይነቶችን ለመማር አሁንም ወደ ሃራ ከተማ ብቅ ዘለቅ ይበሉማ ኑኑኑ ትጠቀሙ በታላችሁ ዋና አቅሪና ሙደሪስ

🎤 በታላቁ በሸይኽ ሙሃመድ ሃያት ሃራ ውላጋ
{ሃፊዘሁሏህ}

ባረከሏሁ ፊኩም

@hussenhas

አቡ አዒሻ العلم نور

14 Oct, 07:43


የወጨቃ ዳዕዋ ዝግጅት ለታ ወሳኝ ምክር

ርዕስ"
አላህን ከዛም መልክተኛው ያዘዙትን ነገር ታዘዙ

አላህን መፍራት ማለት ምን ማለት ነው
ስራን ሁሉ ለአላህ በኢኺላስ መስራት ያለው
ጥቅም ምንድን ነው
የኢባዳ ዘርፎችን ሁሉ ለአላህ መስጠት አለብን
ለአላህ እጅ እግር መስጠት ከአንድ አማኝ
የሚጠበቅ ተግባር ነው
መልክተኞች ይዘውት የመጡትን ነገር ሁሉ
ጨምድደን መያዝ አለብን ሱናን ችላ ማለት የለብነም
የነብያቶች የዳዕዋ የመክፈቻ መግቢያ በድን ላይ ጭማሬ
የሚባል ነገር የለም በድን ላይ የለለን ነገር ማምጣት ፈጠራ
ነው ፈጠራ ደግሞ ወደ እሳት ይመራል ሲሉ ከሸርክና ከቢዳዓ ከመሰረተ ቢስ ተግባሮች ሁሉ ተናግረዋል
ህዝባቸውን ያስጠነቅቁ ነበር
ቀደምት ሰለፎቻችን ለድናቸው ምን ያክል ቦታ ነበራቸው ድንን የተቃረነው ሰው ልጃቸውም አባታቸውም የቅርብ ዘመዳቸውም ቢሆን ሱናን ከተቃረኑ አያናግሯቸውም ነበር ሞት እስከሚመጣ ድረስ

በውስጡ ብዙ ነጥቦች ተውስተው በታል ተዳሳዋል ምንኛ ያማረ የሚጥም የማይሰለች የማይጠገብ ባማረ አንድበት ሳታዳምጡ እንዳታልፉት አላህ ሰምተው ከሚጠቀሙት ያድርገን

🎤 በአስታዝ ሙሐመድ ሰልማን
[ሃፊዘሁሏህ]

🕌 መስጅዴ ፉርቃን ወጨቃ ሰዶማ

ጥቅምት ቀን /3/2017/ሃብሩ ወረዳ ቀበሌ (23)

@hussenhas

አቡ አዒሻ العلم نور

14 Oct, 03:23


🔊ያላወቁት እንዲያውቁ ያልነቁት እንዲነቁ
👇👇👇👇👇👇👇
አድ🥀
አድድ🥀
አድድድ🥀
አድድድድ🥀
አድድድድድ🥀
አድድድድድድ🥀
አድድድድድድድ🥀
አድድድድድድድድ🥀
አድድድድድድድድድ🥀
አድድድድድድድድድድ🥀
አድድድድድድድድድድድ🥀
አድድድድድድድድድድድድ🥀
አድድድድድድድድድድድድድ🥀
አድድድድድድድድድድድድድድ🥀
አድድድድድድድድድድድድድድድ🥀
አድድድድድድድድድድድድድድድድ🥀
አድድድድድድድድድድድድድድድድድ🥀 አድርጉ ባረከሏሁ ፊኩም


وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ

ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን አለ ?


https://t.me/haraselefi
https://t.me/haraselefi

አቡ አዒሻ العلم نور

14 Oct, 03:02


🎤 ታላቅ የዳዕዋ  ፕሮግራም ጥሪ↩️

ለየት ያለ የዳአዋ ፕሮግራም በሀብሩ ወረዳ
021ቀበሌ በውላውላ ሰለፍያ ጀመአወች
መዘጋጀቱን ሰናበሰራችሁ በታላቅ ደሰታ ነው

የፕሮግራሙ አዘጋጆች፦
 
   የውላውላ  ሰለፍያ  ጀመዓወች

🪑 የእለቱ ተጋባዠ እንግዶቻችን ፦↩️

🎙ሸይኽ ሙሀመድ ሀያት حفظه الله

🎙ሸይኽ ሁሴን ከረም حفظه الله

🎙ሸይኽ ሰኢድ ሙሀመድ حفظه الله

🎙ኡሰታዝ አብዱረህማን حفظه الله

🎙ኡሰታዝ ኑራድሰ ሙሀመድ حفظه الله

🎙ወንድም አብዱረህማን حفظه الله

🎙
ወንድም ኑሩ ከሀራ حفظه الله

ሀፊዘሁሏህ ጀሚአን

   ዕርስ፦ በእለቱ ይነገራል

🟢 ኢንሻአላህ ሌላም ተጋባዥ እንግዳ ይኖራል

🗓  በውላውላ አቅራቢያ የምትገኙ
ሙሰሊሞች ይህን ሙሂም ዳአዋ
እንዳያመልጣችሁ  የፕሮግራማችን ቀን
የፊታችን ጁመአ ቀደማችሁ
በመገኘት የፕሮግራሙ ተካፋይ ይሁኑ
!!!

♻️ ፕሮግራሙን ለመከታተል ሊንኩን
በመጫን ይቀላቀሉ።

በቻናል እና በግሩፓች ሼር በማድረግ
ሀላፍትናችንን እንወጣ


➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/YweIaweIa_Groups
https://t.me/YweIaweIa_Groups

🌐 ሸር በማድረግ ሀላፊነታችንን እንወጣ

አቡ አዒሻ العلم نور

11 Oct, 16:51


ኮንፈረንሱ የሚካሄድበት ቀን መተላለፉን ስለማሳወቅ

ጥቅም 3 አዲስ አበባ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ የነበረው ታላቁ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ በፕሮግራም መደራረብ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

ኮንፈረንሱ የሚካሄድበትን ጊዜ ወደ ፊት የምንገልፅ መሆኑን ከይቅርታ ጋር እናስታውቃለን።

የኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

አቡ አዒሻ العلم نور

10 Oct, 01:09


ምስጋና መግለጽን ይመለከታል

የኢትዮዽያ አህሉሱና ኢስላማዊ ማህበር አዲስ አበባ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ፣ ጥቅምት 3/2017 የሚያካሂደው ታላቅ ኢስላማዊ ኮንፈረስ እንዲሳካ ከቀልጣፋ አገልግሎት ጋር ከፍተኛ ትብብር ላደረጉለት:–
➡️ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት
➡️  ለሰላምና አስተዳደር ቢሮ
➡️  ለመረጃና ደህንነት ዋና ቢሮ
➡️  ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና
➡️  ለአ/አ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን
     በራሱና በሱናው ማህበረሰብ ስም ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል ።

የኢትዮዽያ አህሉሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/hussenhas

አቡ አዒሻ العلم نور

09 Oct, 18:44


🔷   ሰበር የምስራች

         የታላቁ ኮንፈረንስ ቀንና ቦታ 

በኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር የተዘጋጀውና በአይነቱ ልዩ የሆነው  ታላቁ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ፣ አዲስ አበባ ላይ ይካሄዳል።
ቀን:- ጥቅምት 3/2017
ቦታ:- በሚሊኒየም አዳራሽ
(ቦሌ ኤርፖርት አጠገብ)

የኮንፈረንሱ መሪ ሀሳብ:-
ዲናችንን ማወቅ፣ መተግበርና ማስተማር

የመግቢያ ትኬትዎን ቶሎ ከእጅዎ ያስገቡ!

የኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

አቡ አዒሻ العلم نور

08 Oct, 03:02


በአይነቱ ልዩ የሆነ ታላቅ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ

የኮንፈረንሱ መሪ ቃል “ዲናችንን ማወቅ መተግበርና ማስተማር”

🏝 የኢትዮጵያ አህለ ሱና ኢስላማዊ ማህበር ታላቅ ሀገር ቀፍ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ ጥቅምት ላይ   በአዲስ አበባ ከተማ ለማካሄድ አስቧል።
ለዚህ ፕሮግራም የአዳራሽ ኪራይ፣ ለተሳታፊዎች ሻይ ቡና ፣ ለዑለማዎች ትራንስፖርትና ማረፊያ ወዘተ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን እንዲቻል የአንድ ሰው መግቢያ ትኬት 1000 ብር ነው።

🔹 ስለሆነም ትኬት በአካል መግዛት ለምትፈልጉ፦
➡️  አል ኢስላሕ መድረሳ
➡️  ዳሩ ሱና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

🔹በባንክ አካውንት ለምትጠቀሙ
የባንክ አካውንት ቁጥር፦ 1000650550718
          ሙሒዲን ሳሊሕ እና ዩሱፍ ኸድር

https://t.me/hussenhas

አቡ አዒሻ العلم نور

05 Oct, 18:34


➪ተውሒድ_የጀነትን_ደጃፍ_መክፈቻ_ቁልፍ_ነው!🗝

➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻
·
⇨,ተውሂድ ማለት በሸሪዓ ምን ማለት ነው?
ተውሂድ ማለት አላህን ለእሱ ብቻ በሚገባው አምልኮ መነጠል  《መለየት》 ማለትም ፦
በጌትነቱ,በአምልኮ,እና በስምና ባህሪያቱ አንድ
ማድረግ ወይም መነጠል ማለት ነው።

⇨,ተውሂድ ወደ 《ሶስት ክፍል》 ይከፈላል

▫️➫ተውሂደል  ሩቡብያህ
▫️➫ተውሂደል  ኡሉህያህ
▫️➫ተውሂደል  አስማኢ_ወሲፋት

⇨,በዚህ የቁርዓን አንቀፅ ሶስቱም የተውሂድ ክፍሎች በአንድ ላይ ተሰብስበዋል።
{رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا فَٱعْبُدْهُ وَٱصْطَبِرْ لِعِبَٰدَتِهِۦ هَلْ تَعْلَمُ لَهُۥ سَمِيًّا۝}
(እርሱ) የሰማያትና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው፡፡ እርሱን በመገዛትም ላይ ታገስ፡፡ ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን።መሬም:65

⇨,በርግጥም ኡለሞች ተውሂድን በሶስት ከፍለው
    《ያስተምራሉ》

❶- ተውሂደል ሩቡብያ፦ በጌትነቱ አንድ ማድረግ :ይህ ማለት አላህን በፈጠረው ስራና ተግባራት አንድ ማድረግ።
➻ለምሳሌ፦  በመፍጠሩ,, በንግስናው,, በማስተናበሩ,, አንድ ማድረግ በመፍጠር አላህን አንድ ማድረግ ወይም መነጠል ማለት፦ ከአላህ ውጪ ፈጣሪ የለም ብሎ በፍፁም እርግጠኝነት በአላህ ብቻ ማመን ማለት ነው።

⇨በንግስናው አላህን አንድ ማድረግ ወይም መነጠል ማለት ፦የፍጠራን ባለቤት ወይም ንጉስ የለም የፈጠራቸው አላህ እንጂ በማለት ጥርጣሬ በሌለው እርግጠኝነት ማመን ማለት ነው።

⇨,በማስተናበር አላህን አንድ ማድረግ ወይም መነጠል ማለት፦ፍጡራንን የሚያስተናብር ከፈጠራቸው አላህ ውጪ ሌላ ፈጣሪ የለም ብሎ በፍፁም እርግጠኝነት ማመን ማለት ነው።

⇨,ተውሂደል ሩቡብያህ ማለት አላህ በስራው አንድ ማድረግ, ሁሉንም ፍጥረት ብቻውን ያለማንም ረዳት መፍጠሩን መመስከርና ማመን ማለት ነው።

❷-ተውሂደል ኡሉህያህ፦በአምልኮ አላህን አንድ  ማድረግ፦ይህ ማለት በአምልኮ አላህ ከፍጡራን በመነጠል አንድ ማድረግ ማለት ነው። እንዲህም ይባላል፦ተውሂደል_ኢባዳ በመባል ይጠራል ይህ የፍጡራን አምልኮ በማስጠጋት ሲሆን ተውሂደል_ኡሉህያህ የተባለው ወደ አላህ   《ኢላህ》በማስጠጋት ነው።

⇨,በዚህ የተውሂድ አይነት አላህን መጠል ወይም አንድ ማድረግ ማለት አላህን በብቸኝነት መገዛት ማለት ነው።ለእሱ በመዋራድ, እሱን በመውደድ, እሱን በማላቅ,አላህ በደነገውና መልክተኛው በሱና በደነገጉት መሰረት እሱን ብቻ በመገዛት ከሌላ ፍጡራን መለየት ወይም መነጠል ማለት ነው።
➷.
⇨,ተውሂደል 《ኡሉህያህ》 ማለት በአምልኮ ተግባራት አላህን አንድ ማድረግ ማለት ነው።
➷.
⇨,ልክ እንዲሁ ጠቅላላ የኢባዳ አይነቶችን ፍራቻ,
ውዴታ, ክጃሎት, በተስፋ መፍራት, በፀፀት, መመለስ ,በክጃሎት መመካት, መረዳት, መታገዝ, ስለት, እርድ,ልመና, ፀሎት, የመሳሰሉት አምልኮዎችን)ለአላህ ብቻ  መስጠት።
➴.
❸- ተውሂደል አስማኢ ወሲፋቲ፦በስምና ባህሪያት አንድ ማድረግ፦ማለትም አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላን በቁርዓን ነፍሱን በጠራበት ስያሜ ወይም ራሱን በገለፀበት ባህሪያት እንዲሁ መልክተኛው በሱናቸው ለአላህ በተናገሩት ስምና ባህሪያት አላህ ከፍጡራን መነጠል ወይም አንድ
ማድረግ።ይህን የምናደርገው ,አላህ ያፀደቀውን በማፅደቅ, በራሱ ላይ ውድቅ ያድገውን ውድቅ በማድረግ፣ ፊደሉ ላይ ሳንጨምር ሳንቀንስ, ትርጉም አልባ ሳናደርግ,ያለ ሁኔታ ወይም ገፅታ 《ከይፍያ》እንዲሁ ከፍጡራን ሳናመሳስል።
➴.
⇨,ለራሱ እንዳስቀመጠው ማስቀመጥ ማለት ነው።በስምና ባህሪያቱ አንድ ማድረግ
《 ሁለት ጭብቶች አቅፎ ይዟል፦》
➴.
⇨የመጀመሪያ ማፅደቅ 《ኢስባት》
ይህ ማለት አላህ ለነፍሱ ያፀደቃቸውን ስምና ባህሪት ልክ ቁርዓን እና ሱና ባፀደቀው መሰረት ማፅደቅ ትርጉምን ሳናጣም, ሳንቀይር, ሁኔታ ሳናደርግና ቃሉን ሳናራቁት  ማፅደቅ።
➴.
⇨,ሁለተኛው ውድቅ ማድረግ 《ነፍይ》
አላህ በቅዱስ መፀሃፉ, መልክተኛው በሱናቸው ውድቅ ያደረጉት ባህሪያት ውድቅ በማደረግ በተቃራኒው ያለው ባህሪ ሙሉ ለሙሉ ማፅደቅ። ይህ ማለት ከአላህ ላይ የጎዶሎነት ባህሪው ውድቅ በማድረግ ሙሉነትን ባህሪ ማፅደቅ, አለመቻል ደካማነት ሙሉ ለሙሉ ውድቅ
በማድረግ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ መሆኑን ማፅደቅ, በደልን ሙሉ ለሙሉ ውድቅ በማድረግ ፍትሃዊነቱን ማፅደቅ።
➴.
⇨,እንቅልፍ ወድቅ በማድረግ አለመተኛትን ለአላህ ማፅደቅ።ይህ ማለት አላህ ከጎዶሎ ነገር የፀዳ ፍፁም ሙሉ ፍትሃዊ, ቻይ,ፈፅሞ የማይተኛ የሆነ ሀያል ጌታ መሆኑን ማፅደቅ የዚህን ተቃራኒ ውድቅ ማድረግ።
↫اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ
↬ቀጥተኛውን መንገድ ምራን።

https://t.me/hussenhas

አቡ አዒሻ العلم نور

05 Oct, 17:57


➭◉አላህን መፍራት ያለው ቱርፋትና

➭◉አላህን አለመፍራት ያለው ክስረት

➭◉አላህን ከፈራን ተውሂድን ለማዎቅ ከሁሉም ነገር በስተፊት ቅሚያ ቦታ እንሰጣለን
➭◉አላህን ከፈራን አላህን በብቸኝነት ለማምለክ ፍቃደኞች እንሆናለን
➭◉አላህን ከፈራን ያዘዘንን እነሰራለን የከለከለነን እንጠናከራለን
➭◉አላህን ከፈረን የምንናገረውን እናውቃለን
➭◉አላህን ከፈራን ዚና ከመስራት እንቆጠባለን
➭◉አላህን ከፈራን ወለድ ከመብላትም እንቆጠባለን
➭◉አላህን ከፈራን ለጅን ማረድን እርም እናደርጋለን
➭◉አላህን ከፈራን ኸምርን መጣትን እተዋለን
➭◉አላህን ከፈራን ጫት ከመቃም እንርቃለን
➭አላህን ከፈራን ወላጆቻችንን እንታዘዛለን
➭◉አላህን ከፈራን የባልንና የሚስትን ሐሽ እንጠብቃለን
➭◉አላህን ከፈራን የጎረቤት ሐቅን እጠብቃለን
➭◉አላህን ከፈራን ዋሽቶ ከማስዋሸት እንቆጠባለን
➭◉አላህን ከፈራን የቲሞችን ገንዘብ ከመብላት እንቆጠባለን
➭◉አላህን ከፊላችን በከፊሉ ያለሐቅ መተቸትንና ማማትን እንርቃለን

👉አላህን ካልፈራንና ካለፈርንውስ

ልባችን ይደርቅና  ኢማናችን ቀንሶ ሐራሙ ሐላል ሐላሉን ሐራም በማድረግ ላይ እናደባልቃለን

መጥፎነገር እየሰራን እንኳን ምንም አይመስለን በል እድሰማልንና ባደባባይ ያመጥፎ ድርጊት እንድታይልን የምንሻ ሰዎች እንሆናለን

ያጀማዓ አላህን መፍራት የቱጋ ነው እራሳችነን ልንፈትሽ ይገባል

በሰዎች ላይ ሲሆን ቁልቁለት በራሳችን ሲሆን አቀበት ለምን

ሁላችንም በምንችለው አላህን መፍራት አለብን

አላህን ከፈራን አላህ ምልካም ነገሮችን እንድን ሰራ ያገራልናል

አላህን የሚፈሩትና የሚያፍሩት እነዛ ናቸው የውቀት ባለቤት

የጃሂል ኢባዳ መጨረሻው እዳ ነውና ነገር እውቀት አላህን የመፍራት ትልቅ ውጤት ነው

አላህን ትክክለኛውን ፍራትና አምልኮት ከሚተገብሩት ያድርገን

ቀጥተኛውንም መንገድ ይምራን


https://t.me/hussenhas

1,938

subscribers

133

photos

31

videos