ጎዶልያስ ቲዩብ - Godoliyas Tube

@godolias_page


የዩቲዩብ ቻናሌን ቤተሰብ እንሆን እናመሰግናለን
https://www.youtube.com/channel/UCJjmgy0CjHsjfIDNw6AZ2Zg

ጎዶልያስ ቲዩብ - Godoliyas Tube

08 May, 01:28


https://youtu.be/veo66rJJ_yc?si=IiUlo1Inxc3Mbp8o

ጎዶልያስ ቲዩብ - Godoliyas Tube

24 Dec, 04:41


እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብር ኤል ነኝ( የሉቃስ ወንጌል ም 1፩፤፩፱)
በተባበሩት አረብ ኤሜሬት በአልአይን ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ22 \04\2015 ዓ.ም Dec31\12\2022

የቅዱስ ገብርኤል በአል ይከበራል ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ የሊባኖስ በተባበሩት ዓረብ ኤሜሬት እና የአካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሁሉም አደባራት አስተዳዳሪዎች

ከኢትዮጱያ የመጡ ሰባክያነ ወንጌል የየአድባራቱ ሰንበት ተማሪዎች በመላው ኤማራት የሚኖሩ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀትይከበራል በዚሁ ዕልት እርሶም በበአሉ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል ።

ጎዶልያስ ቲዩብ - Godoliyas Tube

17 Oct, 10:13


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን 41ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በጸሎት ተጀምሯል::

"እርስ በርስ እየተላለቀ ያለው ትናንትና አስተምረን ያጠመቅነውና ማኅተም ያሰርንለት ክርስቲያን ነው"...ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

ለረጂም ጊዜያት በሕክምና የቆዩት ብፁዕ አቡነ አረጋዊ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት፣የውጭ ግንኙነትመምሪያ፣የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በ41ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው።

ጎዶልያስ ቲዩብ - Godoliyas Tube

25 Sep, 20:54


እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ

ጎዶልያስ ቲዩብ - Godoliyas Tube

16 Aug, 05:28


የሰማችሁ ሸር አድርጉልን ላልሰሙት አሰሙልን ይህም ትልቅ በረከት ነው የአባቶች መልእክት ‼️
👉 ከታች ያለውን ቪድዮ አድምጡት?
# ጀበራ ኪዳነምህረት በ1921 የተመሠረተች ሲሆን እንሰራለን ብለን ብንጀምርም በአሁኑ ስአት ከአቅማችን በላይ ሆነብን ።
👉 የአካባቢው ህዝብ ከ3 አመት በላይ በድርቅ የተጎዳ
👉 አንድ አመት በጦርነቱ ምክንያት በኢኮኖሚ የተጎዳን ሲሆን በአሁኑ ስአት ላምና በሪያችን ሽጠን ከዚህ ያደረስናትን ቤተክርስቲያን አሁን ለተከታታይ 3 አመታት በበጋው ፀይ በክረምት ዝናብ ሊያፈርስብን ነው?
👉 ይህንን መረጃ ላልሰሙት ማሰማት በራሱ ትልቅ እርዳታ ነው እርዱን ብለዋል።

Account 1000323523979 Jebera k/ kiidane mihiret bete kiristian
እባካችሁ ስለ ኪዳነምህረት ብላችሁ እርዱን ብለዋል።

ለበለጠ መረጃ በ0905401198 ይደውሉ ?

ጎዶልያስ ቲዩብ - Godoliyas Tube

02 Aug, 17:10


ለቅዱስነታቸው የተያዘው ጸሎት
በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስነታቸውን መድኃኔዓለም ፈውሱን ሰጥቶ ወደ መንበራቸው በሰላም ይመልስልን።

በታሪካዊው የቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ያየሁት አርማ ነው የለጠፍኩት ትላንትና ለገዳማችን የሚያስፈልጉ ነገሮችን ለማየት በሄድኩበት ሰዓት ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም ስገባ የተመለከትኩት ነው።

በሁለቱም የቤተ ክርስቲያኑ በሮች ከተዘረጋው ባንዲራና ቤተ ክርስቲያኑን ካሸበረቀው የባንዲራ ዲኮር ከፍ ብሎ የቤተ ክርስቲያን ርዕሰ መንበር የሆኑትን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ፎቶ በትላልቅ ባነሮች በሚያምር መልኩ ተዘጋጅቶ አየሁ።

በባነሩ ራስጌ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኩስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ይላል
በባነሩ ግርጌ
ከህመምዎ ድነው ወደ መንበረ ክብርዎ እንዲመለሱ ቤተ ክርስቲያን እና የመንፈስ ቅዱስ ልጆችዎ እንጸልያለን ይላል።
ደስ አለኝ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ለአባቶቻቸው ዋጋ ይከፍላሉ

ስመለከተው ቅዱስነታቸውን አሰብኳቸው አሁን በምን ዓይነት ሁኔታ አሉ ይሆን ከሄዱባት ቅጽበት ጀምሮ አሜሪካ ለህክምና ሄደው በሰላም እንደደረሱ ሰማን።

አሁን ያሉበት ነባራዊ ሁኔታ ግን ማንም የነገረን የለም ሚድያውና ዩቲበሮች የሆነውና ያልሆነውን ዘባርቀው ሐሳብ ውስጥ ከተቱን እንጂ አንዳችም አሁን ስላሉበት ደረጃ ሊነግሩን አልፈለጉም።

የE.O.T.c ሚድያ
የማህበረ ቅዱሳን ሚድያ
በጣም ይገርማል በየዕለቱ እየተከታተሉ ቅዱስነታቸው ያሉበትን ሁኔታ የት እየታከሙ እንደሆነ ሊነግሩን ይገባ ነበረ አልተነገረንም የቅዱስ ፓትርያርኩ ጉዳይ የመላው የኦርቶዶክሳውያን ጉዳይ ነው

በረከታቸው ይድረሰን ብፁዕ አቡነ አብርሃም
ጊዜ ሁኔታ ሰዓት ተመቻቸልኝ ያለው ሁሉ ባልተገባ መንገድ በቅዱስነታቸው ላይ ሲናገር በአጭር ጊዜ ከሀገረ ስብከታቸው በአስቸኳይ መጥተው የሚያሳርፍ መልስ በግላጭ ሰጥተው በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚነገሩ ያልተገቡ ንግግሮች ሁሉ በቤተ ክርስቲያን እንደ ተነገሩ እንቆጥራቸዋለን ስለዚ እያሰባችሁ ተናገሩ በይሆናል እየተናገራችሁ ቤተ ክርስቲያንን አትጉዷት ብለው የማያዳግም መልስ ስጥተዋል በረከታቸው ይድረሰን።

ሚድያዎች ባይናገሩም ባሉበት ሆነው በመንፈስ ይመለከቱናል እኛም ልጆቻቸው በጸሎት እያሰብናቸው ነው ብለው በውስጥ ያለውን የልጅነት ፍቅራቸውና በጸሎት እያሰቧቸው እንደሆነ የቅዱስ ዑራኤል ልጆች አስመስክረዋል።

ሌሎቻችንስ እያሰብናቸው ይሆን በእያንዳንዷ ጸሎታችን ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ርዕሰ መንበር ልንጸልይ ይገባል።

በርግጥ በቤተ ክርስቲያናችን ጸልዩ በእንተ ርእሰ ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ማትያስ ትላለች አሁን ደግሞ በተለየ መንገድ ሁላችንም በጾማችን በጸሎታችን ልናሳስባቸው ይገባል።

የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ወጣቶችና ሰንበት ትምህርት ቤትን ግን ሳላመሰግን አላልፍም አርአያነታችሁን ገልጣችኋልና እናመሰግናለን።

የቤተ ክርስቲያኒቱ ሚድያዎች አሁንም ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ እንድትገልፁልን እንፈልጋለን።

የቅዱስነታቸው በረከት አይለየን በሰላም በጤና ይመለሱልን

ጸልዩ በእንተ ርዕሰ ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ማትያስ ወበእንተ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ወበእንተ ብፁዕ አቡነ ዮናስ ወበእንተ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ

ስለ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ስለ አባ ማትያስ
ስለ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ
ስለ ብፁዕ አቡነ ዮናስ
ስለ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ጸልዩ

ጸልዩ በእንተ ሰላም
ስለ ሰላም እንጸልይ
ስለ ቤተ ክርስቲያን እንጸልይ
ስለ ሚራቡ ስለ ሚጨነቁ እንጸልይ
ስለ ታመሙት በየ ሆስፒታሉ በየጸበሉ በመከራ በጭንቅ ስላሉት እንጸልይ
ያለበደላቸው ያለ ኃጢአታቸው ደማቸው አየፈሰሰ ስላሉ ንፁሃን እንጸልይ አምላከ ሰላም ሰላሙን ይስጠን

አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ
አዲስ አበባ 26/11/2014

ጎዶልያስ ቲዩብ - Godoliyas Tube

02 Aug, 00:14


ወጣት ሳምራዊት ደስታ እንታደጋት በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵይዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዴሁም በአገር ውስጥ የምትገኝ ለሳምሪ የህክምና ወጪዋን ለመሸፈን በተከፈተ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቅም ያለው በገንዘብ አቅም የሌለው በሜችለው በፀሎትም ሼር በማድረግም ለልጆ ለህልሞ ስንል እንታደጋት እንርዳት::

ዘወትር ለበጎ ነገር የማትታክቱ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ የአቅማችሁን እንድታደርጉ በእግዚአብሔር ስም እንማፀናለን።

ንግድ ባንክ
Commercial Bank of Ethiopia (CBE)
1000180776145 ገነት ጀምበሩ ዳምጠው (እናቷ)
ለተጨማሪ መረጃ +251 91 038 4728 / +251 91 337 9447