ESSA YUSUF

@essayus


This is essa yusuf official telegram channel

ESSA YUSUF

19 May, 10:01


መሊክ አምባር (ዋቆ)
ከምስራቅ ሃረርጌ እስከ ህንድ ንጉስነት የዘለቀው ጀብድ

ከሰሞኑ የአንዱአለም ጎሳ ሙዚቃ የቢሊሌን ታሪክ ወደ ኃላ ተመልሰን እንድናስታውስ አድርጎናል።

ይህ ጀግኖቻችንን ፍለጋ አሁን ላይ ደግሞ ወደ መሊክ አምባር ወይም ዋቆ መዞር አለበት።

ከሐሮማያ ተነስቶ ህንድን ስለመራው ንጉስ አምበር መዘከሪያው ሰአት አሁን ነው።

በባርነት ከኦሮሚያ ተሽጦ ሄዶ የባርነትን ቀንዲል ደርምሶ ንጉስ የሆነ የኛው ጀግና መሊክ አምባር ዋቆ።

በህንድም ከ50,000 በላይ ወታደሮችን መርቷል ጠቅላይ ሚኒስትርም ሆኖ ሃገሪቱን ገዝቷል።

በስልጣን ዘመኑም ለህንድ ሃገር እድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዳበረከት የታሪክ ድርሳናት ይገልጻሉ።

የሐሮማያው ተወላጅ መሊክ አምባር ከ1548 እስከ 1626 በምድር ላይ የኖረ ሲሆን ኦሮሚያ በነበረበት ወቅት ስሙ ዋቆ የነበረ ሲሆን በኃላ ላይ ይህ ስያሜው ወደ መሊክ አምባር እንደተቀየረ መረጃዎች ይጦቅማሉ።

ታድያ ከሰሞኑ አንዱአለም ጎሳ ቢሊሌን በሙዚቃው እንዳስታወሰን ማን ነው ጀግና ታሪክ አስታዋሽ ሙዚቀኛ ስለዚህ ጀግና ንጉስ መሊክ ወይም ዋቆ ሚዘክርልን።

መንግስት እነዚህን የመሳሰሉ ታሪኮቻችንን መንገድ በስማቸው በመሰየም፣ ሃውልት በማቆም፣ የፖስታ ቤት ቴምብር በእነሱ ስም በማዘጋጀት እና የተለያዩ ነገሮችን በስማቸው በማቆም ለቱሪዝሙ ዘርፍ እንዲረዳ መስራት አስፈላጊ ነው።

የባርነትን ቀንዲል የሰበረው የምስራቁ ሃረርጌ ንጉስ መሊክ አምባር ወይም ዋቆ።

✍️ ኢሳ ዩሱፍ

ESSA YUSUF

17 Nov, 16:02


https://youtube.com/live/7REllXdxQ-8

ESSA YUSUF

16 Nov, 17:39


https://youtube.com/live/OX5YBYSSdsc

ESSA YUSUF

16 Nov, 16:50


https://youtube.com/live/OX5YBYSSdsc

ESSA YUSUF

15 Nov, 14:05


https://youtube.com/live/5WFozrCyuJE

ESSA YUSUF

13 Nov, 18:57


https://youtube.com/live/nR3zcXEbjuQ

ESSA YUSUF

10 Nov, 13:38


https://youtube.com/live/HXM_lBwFGts

ESSA YUSUF

01 Nov, 09:13


የቁንድዶ ፈረሶች

ስንቶቻችሁ ስለነዚህ አስገራሚ ፈረሶች ታሪክ ታውቃላችሁ?

ቁንድዶ እጅግ በጣም በተፈጥሮ የተዋበ ተራራ ነው:: የሚገኘው በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሃረርጌ በጃርሶ እና ጉርሱም ወረዳ ነው:: ይህ ተራራ ጫፉ ላይ ውሃ አለ:: አረንጓዴ እና በተፈጥሮ ፀጋ የታደለ ነው:: ብዙ የውጭ እና የሃገር ውስጥ ተመራማሪዎች ስለዚህ ተራራ እና ፈረሶቹ ብዙ ምርምር አካሂደዋል::

በአለም ላይ ብቸኛ ባለቤት የሌላቸው የዱር ፈረሶች እዚሁ ላይ ይገኛሉ:: ፈረሶቹ አመጸኛ ናቸው፤ ሰዎችን ሲያዩ ማንፏረር፣ ጆሮ መቀሰር፣ ለጸብ መጋበዝ ይቀናቸዋል:: የኤጀርሳ ጎሮ ገበሬዎች ወደ ተራራው ይልኳቸው የነበሩ ማቲ እረኞች ሳይቀሩ በፈረሶቹ ይነከሱ፣ ይገደሉም እንደነበር ተዘግቧል:: በአሁን ሰአት የፈረሶቹ ቁጥር እየተመናመነ መጥቷል::

ታሪካቸው እስካሁን ድረስ ህዝቡን ለሁለት ከፍሏል:: ግማሹ የአህመድ ግራኝ ወታደሮች ፈረሶች ናቸው ሲሉ ገሚሶቹ ደግሞ የዐጼ ገላውዲዮስ ፈረሶች ናቸው በማለት ይከራከራሉ:: ብዙም ያልተነገረላቸው እና በሚገባው ልክ እንክብካቤ ስላልተደረገላቸው ባክኖ የቀረ የቱሪዝም ሃብት ሆኗል::

የኦሮሚያ ቱሪዝም ቢሮ አይኑን ገልጦ ልክ እንደ ወንጪ አይነት ፕሮጀክቶችን እዚህ አከባቢ ማድረግ አለበት:: አስገራሚ የቱሪዝም መዳረሻ ይወጣዋል:: ፈረሶቹና ተራራው ለአከባቢው ልዩ ግርማ ሞገስን ሰተውታል:: ባለሃብቶችም በአከባቢው የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችን ቢገነቡ ለቱሪስቶች ማረፊያነት ጠቃሚ ነው::

ትኩረት ለቁንዳዶ ተራራ ፈረሶች

ESSA YUSUF

27 Oct, 05:39


https://www.youtube.com/live/t7HhrTtct4o?si=8PtP_mW-ELMgu5sl