ሙግት ሁለት
እኛ ከፈለግን ጌታና አምላክ የሚለው አብን ብቻ ነው ብለን መሞገት እንችላለን ከላይ ልናገር እደሞከርኩት መታወቅ ያለበት ጥቅሱ ለኢየሱስ ቢሆንም አምላክ ሊያደርገው እንደማይችል ነው ነገር ግን እውነታው ምንድነው የሚለውን እንድትረዱት በሚለው ነው እንጂ ለኢየሱስም ቢሆን የሚያመጣው ለውጥ የለም ሆኖም እስኪ ቶማስ ጌታዬ እና አምላኬ ያለው አብን ነው ብለን እንሞግት ከጥቅሱ ጋር ተመሳሳይ ናሙና እንይ
ዘፍጥረት 19፥18 “ሎጥም አላቸው፦ ጌታዬ ሆይ፥ እንዲህስ አይሁን፤”
እንግሊዝ ኛውን KJV ተመልከት
And Lot said unto them, Oh, not so, my Lord
አማርኛው ላይ ጌቶች ብሎ አስቀምጦታል ነገር ግን ኢንግሊዝኛዎችን ብታዩ ጌታዬ ብሎ ነው ያስቀመጠው እንዴ ነጃ ምን ነካህ መልአክቶች እኮ መልእክተኞች ናቸው ሉጥ እኮ ጌታዬ ሲል በመልአክቶቹ አማካኝነት ጌታዬ እያለ የሚያናግረው እግዚአብሔርን ነው የምትሉን ከሆነ እንግዲያውስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ስለሆነ ቶማስ ጌታዬ እና አምላኬ ያለው በኢየሱስ በኩል አብን ነው ኢየሱን የአብ ተላኪ እና መልክት አቀባይ ስለሆነ
ዮሐንስ 17፥3 “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”
1ኛ ጢሞቴዎስ 2:5 አንድ አምላክ Θεοῦ አለና፥ በአምላክ Θεοῦ እና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም *ሰው* የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን ከአምላክ Θεοῦ የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤
የሐዋርያት ሥራ 2:22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ አምላክ Θεοῦ በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከአምላክ Θεοῦ ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤
እንግዲህ ኢየሱስ ሰው ከሆነ እና አንዱ አምላክ የላከው ከሆነ ሰው የሆነው ኢየሱስ እና አንዱ አምላክ ሁለት የተለያዩ ማንነት እና ምንነት ናቸው ማለት ነው፤ ኢየሱስ የሚያመልከው የራሱ አምላክ እንዳለው አይተናል የዛ የሚያመልከው ተላላኪ እና መልክት የሚያደርስ ከሆነ ቶማስ ጌታዬ እና አምላኬ ያለው በኢየሱስ በኩል ለአብ ነው!
መዝጊያ
ክርስቲያኖች ብድግ ይሉና አይ ቀጣይ ላይ እኮ “ኢየሱስም፦ ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው።” ስለዚህ ቶማስ ያለው ኢየሱስን ነው ይሉናል ኢየሱስን ቢሆንም ለኛ የሚያመጣው ለውጥ የለም ለምን እንዲህ እዳልኩኝ ላስረዳቹ እደ ባይብል ጌታ የሚለው ሆነ አምላክ የሚለው ለሁለት ይከፈላሉ
የበሀሪ ጌትነት እና የሹመት ጌትነት
የባህሪ አምላክነት እና የሹመት አምላክነት
በሚል ለሁለት ይከፈላሉ
ነጥብ አንድ
የባህሪ ጌትነት እና አምላክነት
የባህሪ ጌታ እና አምላክ ማነው ከተባለ እደ ባይብል አብ ነው ያ አምላክ በጌትነቱ ላይ ባርነት የሌለበት በጥበቃው ላይ እንቅልፍ የሌለበት በህያውነቱ ላይ ሞት የሌለበት አንዱና ብቸኛው አምላክ አብ ነው የኢየሱስ የሀዋሪያቱ የስጋ ለባሽ ሁሉ አምላክና ጌታ አብ ነው
ኤርምያስ 32፥27 “እነሆ፥ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ በውኑ እኔን የሚያቅተኝ ነገር አለን?”
ዮሐንስ 20፥17 “ኢየሱስም፦ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ #አምላኬና ወደ #አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።”
ሮሜ 1፥7 በአምላክ ለተወደዳችሁና ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ በሮሜ ላላችሁት ሁሉ፥ ከአምላክ ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።”
1ኛ ቆሮንቶስ 1፥3 “ከአምላክ ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።”
2ኛ ቆሮ 1፥2 “ከአምላክ ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።”
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤”
በሉቃስ 1:32 ጌታ አምላክም የተባለው አብ መሆኑን ክርስቲያኖች ያምናሉ ያ ጌታ አምላክ የኢየሱስ የሀዋሪያት የሁሉም ፍጥረት አባትና አምላክ እንዲሁም ጌታ ስለሆነ ጌትነቱ የእርሱ የግሉ በሀሪው እንጂ ከጊዜ ቡሀላ ስላልተቀበለው የባህሪ ጌታ እና አምላክ የሚወስደው አብ ነው ሲቀጥል
ነጥብ ሁለት
የሹመት ጌትነት እና አምላክነት
የሹመት ጌትነት እና አምላክነት ምንድነው ሲባል እደባይብል ጌታም አምላክም የተባሉ ፍጥረታት አሉ ለምሳሌ ነቢያቶች መልዐክቶች ፃድቃን ሰዎች ጌታም አምላክም ተብለዋል እነዚህ ፍጡራን ጌታ እና አምላክ ሲባሉ የባህሪ ጌትነትን እና አምላክነትን የሚይዘውን ከአብ እኩል ሳይሆን ሹመትን አመልካች ነው እነዚህ ጌታ እና አምላክ የተባሉ ፍጡራን የሚያመልኩት አምላክ አላቸው በጌትነታቸው ላይ ባርነት አለባቸው ጌታ ወይም አምላክ ቢባሉም ባሪያ የሆኑለት አምላክ ስላላቸው ከጊዜ ቡሀላ ያገኙት ስለሆነ የሹመት ጌትነት ውስጥ ይመደባሉ ለናሙና አምላክ የተባሉ
ዘጸአት 7፥1 መዝሙር 82:1-6 ዮሐንስ 10:34-35
"አምላክ" በነጠላ ሲሆን "አማልክት" ደሞ በብዜት ነው ስለዚህ ነቢያቶች መልዐክቶች እንዲሁም ፃድቃን ሰዎች አምላክ ሲባሉ አምላክ የሚለውን ሹመት ከጊዜ ቡሀላ የተሰጣቸው በመሆኑ ከሹመት አምላክነት ውስጥ ይመደባሉ በተመሳሳይም ጌታ የተባሉ ነቢያት መልዐክት እዱሁም ፃድቃን ሰዎች አሉ
ለናሙና ጌታ የተባሉ
ዘፍጥረት 18፥12 ዘፍጥረት 23፥11 ዘካርያስ 6፥4
እነዚህ ነቢያትና መልዐክት ጌትነትንም ሆነ አምላክነትን ያገኙት ከሀያሉ አምላክ ስለሆነ ከጊዜ ቡሀላ ያገኙት እና የተሾሙበት ስለሆነ ጌትነታቸው የሹመት ጌትነት ነው ኢየሱስም ጌትነቱን እደሌሎች ነቢያቶች ከጊዜ ቡሀላ ነው ያገኘው
ሐዋርያት 2፥36 እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን አምላክ ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።”
እዚኛውም ጥቅስ ላይ አምላክ የተባለው አብ ነው ያ አምላክ ኢየሱስን ጌታ እና ክርስቶስ አድርጎታል ስለዚህ ቶማስ ኢየሱስን ጌታዬ ማለቱ ምንም የሚገርም ነገር አይደለም ምክንያቱም ነቢያቶች መልዐክትም ፃድቃን ሰዎች ጌታዬ ስለተባሉ በተመሳሳይ ዮሴፍ ጌታ ተደርጓል ልክ እደ ኢየሱስ
ዘፍጥረት 45:9
እግዚአብሔር በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ጌታ አደረገኝ፤ ወደ እኔ ና፥ አትዘግይ፤”
ስለዚህ ኢየሱስ የሚመደበው የሹመት አምላክነት እና ጌትነት ውስጥ ነው ምክንያቱም ኢየሱስ እደሌሎች ነቢያቶች ጌትነቱን ከጊዜ ቡሀላ ነው ያገኘው የሚያመልከው አምላክ አለው የአምላክ ባሪያ ነው ስለዚህ ኢየሱስ የሹመት ጌትነት ውስጥ ይመደባል በአጭሩ ቶማስ ጌታዬ እና አምላኬ ያለው ኢየሱስን ነው ቢባል እራሱ ሌሎች ነቢያቶችና መልዐክቶች በተባሉበት ልክና መጠን እንጂ የባህሪ አምላክና ጌታ ለማለት አይደለም ምክንያቱም ኢየሱስ ጌታ እንዳለው ሊናገር እንጂ እዲያመልሉት ስላልመጣ የኢየሱስ ጌታውም አምላኩም ደሞ አላህ ነው
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል "ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩ" ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡
እንደ ኢየሱስ ለጌታችን ባሪያ መሆን ምንኛ መታደል ነው? ስለዚህ የኢየሱስን ጌታ እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። ጌታችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።
✍ከወንድም NEJA 𝑺𝒕𝒖𝒅𝒆𝒏𝒕 🇵🇸
@eslmnan_teqebelu
ወሠላሙ ዐለይኩም