The Jubair || The ጁበይር

@thejubair00


ይህ የ The Jubair official የቴሌግራም ገፅ ነው

አላማዬ ለኡማው ዲናዊም ሆነ ጠቃሚ ዱንያዊ ጉዳዮችን በአላህ ፍቃድ ከማቀውም ይሁን በትክክል ከሚያቁት በመውሰድ ለእናንተ ለማስጨበጥ መሞከር ነው .

📛 ማሳሰቢያ ከላይ እንደጠቀስኩት እዚህ ቻናል ላይ ከዲናዊ ጉዳዮች ባሸገር ሌሎች የተለያዩ ዱንያዊ ሀሳቦችን እንዲሁም ደግሞ ሃላል ማስታወቂያዎችን ልታዩ ትችላላቹ !!

@Thejubair

The Jubair || The ጁበይር

04 Oct, 10:27


ኢሬቻ ኃይማኖታዊ በዓል አይደለም፣ ሺርክ አይደለም ለሚሉ፤ ይህን ምን እንበለው በሏቸው። ቪድዮውን አሰራጩት። ብዙዎች የሚያከብሩት ባለማወቅ ይሆናልና ይህን ሲያዩ የሚታረም አንድ ሰው እንኳ ሊኖር ይችላል።
||
https://t.me/MuradTadesse

The Jubair || The ጁበይር

29 Sep, 15:19


شرح دبرذيت

The Jubair || The ጁበይር

26 Sep, 08:44


«🔹በካፊሮች በዓል እንኳን አደረሳችሁ ማለት ይፈቀዳልን?

    በበአላት ሰሞን በተደጋጋሚ እገሌና እገሌ ላይክ አድርገውታል ከሚለን ፖስቶች መካከል ከፊሎቹ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቶች ናቸው። ለጌታ መወለድ፣ ለጌታ መሰቀል፣ ለጌታ ሞቶ መነሳት (ትንሳኤና) መሰል ክስተቶች እንኳን አደረሳችሁ ሲባል ሼር ወይም ላይክ የሚያደርጉ ብዙ እህትና ወንድሞችን አስተውያለው። አንዳንዴ በስህተት ሌላ ግዜም ነገሩን እንደቀላል በመውሰድ የሚፈፀም ሊሆን ይችላል። ሆኖም እጅግ ከባድና በአኼራ ዋጋ የሚያስከፍል መዘናጋት ነው!!

    በካፊሮች በአል፤ እንኳን አደረሳችሁ... እንኳን ደስ አላችሁ... እንኳን አብሮ አደረሰን ማለት እነሱን ለማስደሰትም ይሁን ለመመሳሰል ከአላህ ዲን መንሸራተት እና የካፊሮችን ኩፍር የመናገር ስነልቦና መካብ ስለሆነ
ክልክል ነው። መከባበር እና አብሮነትን ለማሳየት ከእምነታችን መንሸራተት አይጠበቅብንም። ዲን ከምንም በላይ ነውና ሸሪዓን መተላለፍ ፍፁም ጥፋት ነው!!

   ፈጣሪ ወለደ ተወለደ የሚለው አስተምህሮ የጥፋትነቱ ክብደት ሰማያትንና ምድርን ሊሰነጥቅ እንደሚቀርብ ቁርአን ይነግረናል። አላህን የሚያስቆጣ ተግባር በመፈፀማቸው እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት ከሙስሊም አይጠበቅም!!

(وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحۡمَـٰنُ وَلَدࣰا * لَّقَدۡ جِئۡتُمۡ شَیۡـًٔا إِدࣰّا *  تَكَادُ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تُ یَتَفَطَّرۡنَ مِنۡهُ وَتَنشَقُّ ٱلۡأَرۡضُ وَتَخِرُّ ٱلۡجِبَالُ هَدًّا *  أَن دَعَوۡا۟ لِلرَّحۡمَـٰنِ وَلَدࣰا *  وَمَا یَنۢبَغِی لِلرَّحۡمَـٰنِ أَن یَتَّخِذَ وَلَدًا *  إِن كُلُّ مَن فِی ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضِ إِلَّاۤ ءَاتِی ٱلرَّحۡمَـٰنِ عَبۡدࣰا *  لَّقَدۡ أَحۡصَىٰهُمۡ وَعَدَّهُمۡ عَدࣰّا *  وَكُلُّهُمۡ ءَاتِیهِ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ فَرۡدًا)

አልረሕማንም ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ፡፡ ከባድ መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ፡፡ በእርሱ (በንግግራቸው ምክንያት) ሰማያት ሊቀደዱ፣ ምድርም ልትሰነጠቅ፣ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ፡፡ ለአልረሕማን ልጅ አለው ስለአሉ፡፡ ለአልረሕማን ልጅን መያዝ አይገባውም!! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ (በትንሣኤ ቀን) ለአልራሕማን ባሪያ ኾነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም]
Surah Maryam 88 - 95

   ለመሆኑ አንድን ካፊር ለሀይማኖታዊ በአል እንኳን አደረሰህ ስትለው፤ ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ አይደለምን?

እንኳን አደረሰህ...
ጌታ ተወልዶ ተሰቅሎ ሞቷል ብለህ ለማወጅ፣ ለመስቀል ለመስገድና  የፈጣሪን ክብር የሚነኩ ንግግሮችን ለመናገር እንኳን በቃህ!

እንኳን አደረሰህ...
ማርያም ፈጣሪዋን ወለደችው፤ በመጠቅለያም ጠቀለለችው እያልክ ለመዘመር እንኳን በቃህ!

የኩፍር ተግባርን ለመከወን ከሆነ የደረሰው ለምንስ እንኳን አብሮ አደረሰን እንላለን?

   እውቁ አሊም ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላህ ይህ ተግባር የተከለከለ ስለመሆኑ የኡለማዎች የጋራ አቋም መሆኑን በመጠቆም እንዲህ ብለዋል፤ «ኩፍርን ብቻ በሚያንፀባርቁ የሀይማኖታቸው መገለጫዎች እንኳን አደረሳችሁ...እንኳን ደስ ያለችሁ ማለት ሀራም መሆኑ የሁሉም ሊቃውንት ስምምነት ያለበት ነው።
ለምሳሌ አንድ ሙስሊም በነሱ በዓላትና ፆም ጊዜ፤ «በአሉን የተባረከ ያድርግልህ» ወይም «መልካም የደስታ በአል ያድርግልህ» እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ቢያስተላልፍ፤ ተናጋሪው ከኩፍር ቢድን እንኳ ከባድ ወንጀል ነው የፈፀመው። ይህም፤ ልክ «እንኳን ለመስቀል ሰገድክ» ብሎ ደስታን እንደመግለፅ ነው!

ይህ እንደውም፤ አንድ ሰው ነብስ በማጥፋቱ፣ አልኮል በመጠጣቱ፣ ዝሙት በመፈፀሙና በመሰል ተግባራት እንኳን ደስ ያለህ ከማለት በወንጀልነት የከበደ እና አስቀያሚ ነው። ለኢስላማዊ ድንጋጌዎች ተገቢዉን ክብር የማይሰጡ ብዙ ሰዎች ይህንን ይፈፅማሉ።  ምን ያክል የሚያስጠላ የግባር እንደፈፀሙም አያስተውሉም። ቢድአ፣ ኩፍር እና ወንጀሎች በመፈፀማቸው እንኳን አደረሰህ፣ እንኳን ደስ ያለህ እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ያስተላለፈ፤ እራሱን ለአላህ ቁጣና ጥላቻ የተገባ እንዲሆን የሚያደርግ ምክኒያት ፈፅሟል»  አህካም አህሉዚማህ

   የዘመናችን ፈቂህ ሸይኽ ኡሰይሚን ረሂመሁላህ እንዲህ አሉ «ካፊሮችን እንኳን አደረሳችሁ ማለት ኢብኑል ቀይም እንዳለው የዚህን ያክል ከባድ የሆነበት ምክኒያት እነርሱ የሚፈፅሟቸውን የኩፍር መገለጫዎች ማፅደቅ ስለሆነ ነው። ምንም እንኳን ለራሱ ይህንን ኩፍር መፈፀምን ባይወድም እነሱ መፈፀማቸውን ወዷልና። ሙስሊም ደግሞ የኩፍር መገለጫዎችን መውደድም ይሁን ሌሎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት አይፈቀድለትም።»
መጅሙዑ ፈታዋ ወረሳኢል አሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን 3/44 

በተመሳሳይ መልኩ፤ ክሪስማስም ሆነ ሌሎች በአላት ላይ ስጦታ ወይም ፓስት ካርዶችን መለዋወጥ፤ እንዲሁም ማንኛውም ደስታን መግለጫ የሆኑ ነገሮችን መፈፀም በአሉን መካፈል ስለሆነ የተከለከለ ነው!!

   በዚህ ፅሁፍ መጠቆም የፈለኩት ምንም አይነት ማህበራዊ ግንኙነት ሀራም ነው የሚል መልእክት አይደለም። በተለይም ከክርስቲያን እና አይሁዶች ጋር ባለን ማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ የተፈቀዱ ብዙ በመልካም የመኗኗር እሴቶች አሉን።  ሆኖም ሀይማኖታዊ ወሰኖች የሉም ማለት አይደለም። የተፈቀደውን ስንተገብር እንደ ያልተፈቀደ ጋብቻ፣ በአላት ላይ መሳተፍ፣ ለሞቱት የአላህን ማርታ መለመንና ባጠቃላይ በዲን መመሳሰልን ግን በፍፁም አንፈፅምም። ይህንን የእምነትና የሀይማኖት ወሰን መናድ አይቻልም። ማንነታችንን ማክበር፣ ግንኙነታችንን በዲናዊ ገደቦች ማጠር ብሎም አለመሟሟት ለሌሎች ሞራል ዲንና ማንነት ከመጨነቅ ይቀድማል። ዲን ከምንም በላይ ነውና ከመሸማቀቅ እንውጣ። ይህ  የዲናችን መገለጫ እንጂ እንደ ማክረርና ፅንፈኝነት የሚታይ አይደለም። በነገራችን ላይ የአንድ እምነት ተከታይ ከሌሎች ለመቀራረብ ብሎ ከራሱ እምነት ጋር የሚጣላበት ሁኔታ ድሮ ቀርቷል። ሌሎቹም ቢሆኑ ይህ በኛ ሀይማኖት አልፈቀድም እና ይቅርታ ይሉሀል።
(فَلَا تُطِعِ ٱلۡمُكَذِّبِینَ * وَدُّوا۟ لَوۡ تُدۡهِنُ فَیُدۡهِنُونَ * وَلَا تُطِعۡ كُلَّ حَلَّافࣲ مَّهِینٍ)

አስተባባዮችንም አትታዝዙ፡፡ ብትመሳሰላቸውና ቢመሳሰሉህ ተመኙ፡፡
[Surah Al-Qalam 8 - 10]

ወላሁ አዕለም

አላህ ከጥፋት ሁሉ ይጠብቀን!»
         منقول

The Jubair || The ጁበይር

10 Sep, 12:06


መውሊድ በሸሪዓ ሚዛን

የጁሙዓህ ኹጥባህ

በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

©:NesihaTv

The Jubair || The ጁበይር

09 Sep, 12:08


📻 መውሊድ መቼ ተጀመረ?
🎙ሸይኽ ሙሐመድ ወሌ ረሒመሁ'ላህ

©: Hanif Multimedia

The Jubair || The ጁበይር

31 Aug, 09:17


3ቱም ደግሞ የሰውን ልጅ ቀዳሚውን ፍላጎት ከሚይዙ ናቸው።

The Jubair || The ጁበይር

30 Aug, 14:51


https://youtu.be/fi6eE_iWQf8?si=lS68uK0h37rW6mj8

The Jubair || The ጁበይር

17 Aug, 05:42


https://youtu.be/8GuCB49rLCo?si=8C9rEWPkUl_nnpSL

The Jubair || The ጁበይር

16 Aug, 04:33


🔴   ጁምዐችንን ሱረቱል ከህፍ በመቅራት
        እና ሰለዋት በማብዛት እናድምቀው🤍


إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡

[ሱረቱል-አሕዛብ - 56]

•●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ
      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ 😊

•●° መልካም ጁምዐ 🤍



🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

15 Aug, 16:09


ሚስት ሆይ...
የቤትሽን ምስጢሮች በወሬዎችሽ መሀል የወሬ ማጣፈጫ ላለማድረግ ፣ ሚስጥር እንዳያመልጥሽ ጥንቃቄ አድርጊ!  ጓደኛሽም ልብሸ መቋጠር ያልቻለውን ሚስጥርና ገመና የምትጠብቅልሽ እንዳይመስልሽ..!!
#የትዳር_ህይወት



🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

11 Aug, 10:26


ወዳጆቼ በእነዚህ 8 ጉዳዮች ምክንያት ዱዐችን ተቀባይነት አይኖርም እና  ይህን ቪድዮ አንድ አፍታ በመመልከት እነዚህን 8 ጉዳዮች ሳይረፍድ አሁኑኑ እናስተካክል !


አንድ አፍታ ቪድዮውን እዩትና ቪዲዮው ጠቃሚ ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ነቢያችን ሰ.ዐ.ወ አንድን ኸይር ነገር ያመላከተ ሰው ልክ ያ ያመላከተውን ስራ እንደ ሰራው ሰው አይነት አጅር እንደሚያገኝ ነግረውናልና ይህን ቪድዮ አንድ አፍታ  SHARE በማድረግ መልዕክቱ ለብዙ ሰዎች እንዲዳረስ አድርጉ አላህ በዚህ ስራቹ ካሰባቹት በላይ ትልቅ አጅርን ይስጣቹ ! ባረከላሁፊኩም !


🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

03 Aug, 16:50


ወዳጆቼ ያለ አት-ተሒያቱ ወይም ያለ ተሸሁድ ሰላታችን ተቀባይነት የለውም እና ይህን ቪዲዮ አንድ አፍታ በመመልከት የአት-ተሒያቱ አባባላችንን እንፈትሽ !


ይህን ቪዲዮ በቲክቶክ ላይ ከ200ሺ ሰዎች በላይ አይተውታል እንዲሁም ደግሞ ከ21ሺ በላይ ለሆኑ ወዳጅ ዘመዶቻቸውም ሰዎች ሼር አድርገውላቸዋል !


እኛስ ሀባይቢ ለምን አሻራችንን አናሳርፍም አንድ አፍታ ቪድዮውን እዩትና ቪዲዮው ጠቃሚ ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ነቢያችን ሰ.ዐ.ወ አንድን ኸይር ነገር ያመላከተ ሰው ልክ ያ ያመላከተውን ስራ እንደ ሰራው ሰው አይነት አጅር እንደሚያገኝ ነግረውናልና ይህን ቪድዮ አንድ አፍታ  SHARE በማድረግ መልዕክቱ ለብዙ ሰዎች እንዲዳረስ አድርጉ አላህ በዚህ ስራቹ ካሰባቹት በላይ ትልቅ አጅርን ይስጣቹ ! ባረከላሁፊኩም !




🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

03 Aug, 12:28


تفسير السعدي

﴿وَلَقَدْ كُذِّبَتْ رُسُلٌ مِنْ قَبْلِكَ فَصَبَرُوا عَلَى مَا كُذِّبُوا وَأُوذُوا حَتَّى أَتَاهُمْ نَصْرُنَا﴾ فاصبر كما صبروا، تظفر كما ظفروا. ﴿وَلَقَدْ جَاءَكَ مِنْ نَبَإِ الْمُرْسَلِينَ﴾ ما به يثبت فؤادك، ويطمئن به قلبك.



🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

28 Jul, 15:28


🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር
       አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍


خُذِ الْعَفْوَ وَأْمُرْ بِالْعُرْفِ وَأَعْرِضْ عَنِ الْجَاهِلِينَ

ገርን ጠባይ ያዝ፡፡ በመልካምም እዘዝ፡፡ ባለጌዎቹንም ተዋቸው፡:

وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

ከሰይጣንም (በኩል) ጉትጎታ ቢያገኝህ በአላህ ተጠበቅ፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡

إِنَّ الَّذِينَ اتَّقَوْا إِذَا مَسَّهُمْ طَائِفٌ مِّنَ الشَّيْطَانِ تَذَكَّرُوا فَإِذَا هُم مُّبْصِرُونَ

እነዚያ የተጠነቀቁት ከሰይጣን የኾነ ዘዋሪ በነካቸው ጊዜ (ጌታቸውን) ይገነዘባሉ፡፡ ወዲያውም እነሱ ተመልካቾች ይኾናሉ፡፡

وَإِخْوَانُهُمْ يَمُدُّونَهُمْ فِي الْغَيِّ ثُمَّ لَا يُقْصِرُونَ

ወንድሞቻቸውም ጥመትን ይጨምሩላቸዋል፤ ከዚያም (እነርሱ) አይገቱም፡፡

.
.
.

በተዓምርም ባልመጣሃቸው ጊዜ (በራስህ) «ለምን አትፈጥራትም» ይላሉ፡፡ ከጌታዬ ወደኔ የተወረደውን ብቻ እከተላለሁ፡፡ ይህ (ቁርኣን) ከጌታችሁ ሲኾን ለሚያምኑ ሕዝቦች መረጃዎችና መምሪያ እዝነትም ነው በላቸው፡፡


[ሱረቱል አዕራፍ : 199-203 ]



•●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ
     ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ 😊

•●° መልካም ምሽት 🤍



🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

28 Jul, 03:24


🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር
       አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍

وَلَوْ تَرَىٰ إِذْ وُقِفُوا عَلَى النَّارِ فَقَالُوا يَا لَيْتَنَا نُرَدُّ وَلَا نُكَذِّبَ بِآيَاتِ رَبِّنَا وَنَكُونَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ

በእሳትም ላይ በተቆሙ ጊዜ ምነው (ወደ ምድረ ዓለም) በተመለስን በጌታችንም አንቀጾች ባላስተባበልን ከምእምናንም በኾንን ዋ ምኞታችን! ባሉ ጊዜ ብታይ ኖሮ (የሚያሰደነግጥን ነገር ባየህ ነበር)፡፡

بَلْ بَدَا لَهُم مَّا كَانُوا يُخْفُونَ مِن قَبْلُ ۖ وَلَوْ رُدُّوا لَعَادُوا لِمَا نُهُوا عَنْهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ

ይልቁንም ከዚህ በፊት ይደብቁት የነበሩት ሁሉ ለእነርሱ ተገለጸ፡፡ (ወደምድረ ዓለም) በተመለሱም ኖሮ ከእርሱ ወደ ተከለከሉት ነገር በተመለሱ ነበር፡፡ እነሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡

وَقَالُوا إِنْ هِيَ إِلَّا حَيَاتُنَا الدُّنْيَا وَمَا نَحْنُ بِمَبْعُوثِينَ

እርሷም (ሕይወት) «የቅርቢቱ ሕይወታችን እንጅ ሌላ አይደለችም እኛም ተቀስቀቃሾች አይደለንም» አሉ፡፡

.
.
.

[ሱረቱል አንዓም : 27-32]



•●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ
     ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ 😊

•●° መልካም ቀን 🤍

🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

27 Jul, 15:27


🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር
       አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍


كَلَّا إِذَا بَلَغَتِ التَّرَاقِيَ
ንቁ (ነፍስ) ብሪዎችን በደረሰች ጊዜ፤

وَقِيلَ مَنْ ۜ رَاقٍ
«አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፡፡

وَظَنَّ أَنَّهُ الْفِرَاقُ
(ሕመምተኛው) እርሱ (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መልለየት መኾኑን ባረጋገጠም ጊዜ፡፡

وَالْتَفَّتِ السَّاقُ بِالسَّاقِ
ባትም በባት በተጣበቀች ጊዜ፡፡

إِلَىٰ رَبِّكَ يَوْمَئِذٍ الْمَسَاقُ
በዚያ ቀን መነዳቱ ወደ ጌታህ (ፍርድ) ነው፡፡

فَلَا صَدَّقَ وَلَا صَلَّىٰ
አላመነምም አልሰገደምም፡፡

وَلَٰكِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ
ግን አስተባበለ፤ (ከእምነት) ዞረም፡፡

ثُمَّ ذَهَبَ إِلَىٰ أَهْلِهِ يَتَمَطَّىٰ
ከዚያም እየተንጎባለለ ወደ ቤተሰቡ ኼደ፡፡

أَوْلَىٰ لَكَ فَأَوْلَىٰ
የምትጠላውን ነገር (አላህ) ያስከትልህ፡፡ ለአንተ ተገቢህም ነው፡፡

ثُمَّ أَوْلَىٰ لَكَ فَأَوْلَىٰ
ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ለአንተ የተገባህም ነው፡፡

أَيَحْسَبُ الْإِنسَانُ أَن يُتْرَكَ سُدًى
ሰው ስድ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን?

أَلَمْ يَكُ نُطْفَةً مِّن مَّنِيٍّ يُمْنَىٰ
የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን?
.
.
.

[ሱረቱል ቂያማህ : 26-40]




•●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ
     ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ 😊

•●° መልካም ምሽት 🤍

🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

27 Jul, 03:24


🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር
       አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍

وَهَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ مُوسَىٰ
የሙሳም ወሬ በእርግጥ መጥቶሃል፡፡

إِذْ رَأَىٰ نَارًا فَقَالَ لِأَهْلِهِ امْكُثُوا إِنِّي آنَسْتُ نَارًا لَّعَلِّي آتِيكُم مِّنْهَا بِقَبَسٍ أَوْ أَجِدُ عَلَى النَّارِ هُدًى
እሳትን ባየና ለቤተሰቦቹ፡- (እዚህ) «ቆዩ፤ እኔ እሳትን አየሁ፡፡ ከእርሷ ችቦን ላመጣላችሁ፤ ወይም እሳቲቱ ዘንድ መሪን ላገኝ እከጅላለሁ» ባለጊዜ (አስታውስ)፡፡

فَلَمَّا أَتَاهَا نُودِيَ يَا مُوسَىٰ
በመጣትም ጊዜ «ሙሳ ሆይ» በማለት ተጠራ፡፡

إِنِّي أَنَا رَبُّكَ فَاخْلَعْ نَعْلَيْكَ ۖ إِنَّكَ بِالْوَادِ الْمُقَدَّسِ طُوًى
«እኔ ጌታህ እኔ ነኝ መጫሚያዎችህንም አውልቅ፡፡ አንተ በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ ነህና፡፡

وَأَنَا اخْتَرْتُكَ فَاسْتَمِعْ لِمَا يُوحَىٰ
«እኔም መረጥኩህ፤ የሚወረድልህንም ነገር አዳምጥ፡፡

إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي
«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡
.
.
.

[ሱረቱ ጣሃ : 9-16]



•●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ
     ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ 😊

•●° መልካም ቀን 🤍

🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00

.