بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዓመታዊ የሥራ ግምገማ ተጀመረ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ (ተቅዪም) ቦንጋ ከተማ በሚገኘው የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት እየተካሄደ ነው።
ዛሬ የተጀመረውና በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ሑሴን ሐሰን የተመራው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በ2016 ዓ.ል በምክር ቤቱ በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ትኩረት አድርጓል።
ግምገማው በ2016 ዓ.ል በከፍተኛ ምክር ቤቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠል የታዩ ውሱንነቶችን በመለየትና የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ በ2017 ዓ.ል. የክልሉ እስልምና ምክር ቤት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት የተሻለ ውጤት ያስመዘግባል ብለው እንደሚጠብቁ ሸይኽ ሑሴን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነሐሴ 18፣ 2016 ዓ.ል በአዲስ አበባ ባደረገው የ2ኛ ዓመት፣ 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደር የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች የ2016 ዓ.ል የሥራ አፈጻጸማቸውን እንዲገመግሙ አቅጣጫ ማመላከቱ ይታወሳል።
ዛሬ በቦንጋ ከተማ በክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተጀመረው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በነገው ዕለትም እንደሚቀጥል ከቦታው የሚገኘው ቃል አቀባያችን የላከው መረጃ ያመለክታል።
•••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1