Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

@selsebilzumekan


Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

05 Oct, 19:25


https://youtu.be/P-ibsJqjhWk?si=avSNXllHnbfHqd3g

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

05 Oct, 11:23


Share '04_122704.pdf'

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

05 Oct, 10:31


መረጃዎቹን ጨምቄ ነው ያመጣኋቸው። የፈለገ ሰው የተጠቀሰውን ኪታብ 8ኛ ቅፅ ከገፅ 31 እስከ 44 መመልከት ይችላል። ተጨማሪ መረጃዎችን የፈለገ አልመቅሪዚይ እና አሰኻዊይ የፃፉትን ማየት ይችላል።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 25/2017)
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

05 Oct, 10:30


ሐበሻ በአልዑመሪ እይታ
~
የፀሐፊው ሙሉ መጠሪያ አቡል ዐባስ ሺሃቡዲን አሕመድ ብኑ ፈድሊላህ ብኒ የሕያ አልዑመሪ ይባላል። ባጭሩ ኢብኑ ፈድሊላህ አልዑመሪ ወይም አልዑመሪ በመባል ይታወቃል። በሂጅራ አቆጣጠር ከ 700 እስከ 749 ባለው ነው የኖረው። በአውሮፓው አቆጣጠር ሲታይ በ1349 ነው የሞተው። ታዋቂ የታሪክ፣ የጂኦግራፊ እና የ'ኢትኖግራፊ' ምሁር ነው። ከበርካታ ኪታቦቹ ውስጥ مسالك الأبصار في ممالك الأمصار ስራው በሰፊው ይታወቃል። የሙስሊሙን ዓለም እና አጎራባች ህዝቦችን ባህል፣ ልማድ፣ ቋንቋ፣ ጂኦግራፊ፣ የአየር ንብረት፣ ... በ 27 ቅፅ (ሙጀለድ) የዳሰሰ ስራ ነው። ይሄ ትልቅ ስራ ስለ ሃገራችን ኢትዮጵያ በሃገር ውስጥ ምንጮች ውስጥ የማይገኙ በርካታ መረጃዎችን አጭቆ ይዟል። በተደጋጋሚ በዚህ ስራ ውስጥ ያሉ መልእክቶችን ጨምቄ ማቅረብ እየፈለግኩኝ ሳይሆንልኝ ቀርቶ ነበር። ዛሬ ባጭሩ ነካ ማድረግ እፈልጋለሁ።
በቀደምት ምንጮች ላይ እንደሚታወቀው ሐበሻ በሚል ነው የሚገልፃት። በዚህ ስያሜ የሚታውቀው ግዛት ዛሬ ካለችው ኢትዮጵያ በእጅጉ የሰፋ ነው። በምስራቅና ሰሜን ምስራቅ በኩል የሃገሪቱ ድንበር ህንድ ውቅያኖስና የመን ነው። ቀይ ባህርንም የሐበሻ ባህር በሚል ነው የሚጠራው።
ሐበሻ ቀደም ባለው ዘመን መናገሻ ከተማዋ አክሱም እንደነበረች የምትገኘውም በሰሐርት ግዛት ውስጥ እንደሆነ፣ ሰሐርት ቀደም ብሎ ቲክራይ (ትግራይ?) በመባል ትታወቅ እንደነበር ይገልፃል። በፀሀፊው ዘመን የመንግስቱ ዋና ከተማ በአምሐራ ግዛት ውስጥ እንዳለ ሲገልፅ መርዐዲ በመባል ትታወቃለች ይላል። ከአምሐራ ቀጥሎ ሸዋ፣ ዳሞት፣ ላምናን፣ ሲሁ፣ ዘንጅ፣ ዐድሉል ኡመራእ ( ፍትሐ ነገስት?) ፣ ሐማሳ፣ ባሪያ፣ ሰባቱ ኢስላማዊ ሱልጧኔቶች እንዳሉ ሲጠቅስ እነዚህ ሁሉም የየራሳቸው ንጉስና ሰራዊት አላቸው። ትልቁ መሪያቸው በቋንቋቸው አፄ በመባል ይጠራል። በዘመኑ ያለው ንጉስ አፄ አምደ ፅዮን ነው ይላል።

የአባይን ወንዝ ሲሁን ብሎ ነው የሚጠራው፣ ግዮን የሚለው ይመስለኛል። የህዝቡ አለባበስ በክረምትም በበጋም አንድ አይነት ነው። ከጥጥ የሚሰራ ያልተሰፋ ልብስ ሲሆን እያንዳንዱ ሰው ሁለት ልብሶች አሉት፤ ከላይ የሚለበስ አንድ ከስር የሚታጠቁት ሌላ። ቁምጣና ቦላሌው ብዙም አልነበረም ማለት ይሆን?
አብዛኛው ግብይታቸው እቃ ለእቃ ልውውጥ ነው። ከሰባቱ የኢስላማዊ ሱልጧኔቶች ውስጥ በአምስቱ የነበረው ግን ከዚህ ይለያል። የኢፋት ሱልጧኔት ዋና ከተማ ላይ የወርቅና የብር ሳንቲሞችን ይጠቀማሉ። ደዋሮ፣ አሪቢኒ (አርባቢኒ?)፣ ሸርኻ እና ሀዲያ ሱልጧኒቶች ሐከና ብለው የሚጠሩት በትልልቅ መርፌ ቅርፅ ያለ መገበያያ ይጠቀማሉ።
የሐበሻ ህዝቦች በአመት ሁለት ጊዜ ዝናብ ተጠቅመው ያመርታሉ። በሁለቱ ወቅቶች የሚገኘውን ዝናብ በል (በልግ?) እና ክረም (ክረምት) ብሎ ጠቅሷል። ስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎ፣ ጧፊ (ጤፍ) እና ሌሎችም የእህልና የጥራጥሬ አይነቶች፣ ፍራፍሬዎች እንዳሉ ያወሳል። በኢስላማዊ ሱልጧኔቶቹ ውስጥ በተለይም በኢፋት ሸንኮራ አገዳ እንዳለ ይጠቅሳል።
በሐበሻ ምድር የሚገኙ የሙስሊም ሱልጧኒቶችን በተመለከተ በቁጥር ሰባት እንደሆኑ ሲጠቅስ ከነዚህ ውስጥ ሰፊው ኢፋት (እሱ አውፋት እያለ ነው የሚጠቅሰው) ሲሆን በሰራዊት ብዛት ጠንካራው ደግሞ ሀዲያ እንደሆነ ይጠቅሳል። እነዚህ ሱልጧኔቶች አቅማቸው ደካማ፣ ሀብታቸው አነስተኛ፣ በመካከላቸው መጣጣም የሌላቸው የተለያዩ እንደሆኑ ያነሳል። አብዛኞቹ ስፋታቸው በጣም አነስተኛ ነው። ከአምሐራው ገዢ በኩል ጫና እንዳለባቸውና በመካከላቸው ያለውን ፉክክር ትተው ቢግባቡ ኖሮ መጋፈጥ ይችሉ እንደነበር የነስቡ ራያን ኪታብ አዘጋጀ ታዋቂውን ዘይለዒይን ያጣቅሳል።
የነዚህ ሰባት ግዛቶች ነዋሪዎች እምነታቸውን የሚተገብሩና የሚጠብቁ ናቸው፣ መድረሳዎችና የሱፍያ ዛውያዎች እንደሌሉ ያወሳል።
የኢፋት ሱልጧኔት ግዛት ከመሀል ሃገር እስከ ዘይላ እንደሚዘረጋ ይገልፃል። የአብዛኛው ነዋሪ አለባበስ ሽርጥና ኮፍያ እንደሆነ ፉቀሃኦቹ ዘንድ ደግሞ ቀሚስና ጥምጣም እንደሚለበስ ይጠቅሳል። ይሄ እንግዲህ እነዚህ ልብሶች በቅርብ ከዐረቢያ የመጡ ለሚመስላቸው የሚሰጠው ጥቆማ አለው። ሱሪ መልበሱም ቢሆን ጦሩ አካባቢ እንዳለ ጠቁሟል።
ቋንቋቸው ሐበሽኛ እና ዐረብኛ ነው። ዐረብኛ በሰፊው እንደነበር አስተውሉ። ኋላ በምን ምክንያት ጠፋ ታዲያ? ሐበሽኛ የሚለው ሌሎች ቦታዎች ላይ ከተጠቀሱ ነጥቦች ጋር ስናዛምደው አማርኛውን ነው የሚመስለው። እያወራን ያለነው ስለ ኢፋት ሱልጧኔት እንደሆነ ይታወስ።
ኢፋት ውስጥ የሚገኙ የእህል፣ ጥራጥሬ፣ ፍራፍሬና የአትክልት አይነቶችን ከዘረዘረ በኋላ የጠቀሰው ነገር ቢኖር ጫት ነው። ፍሬ እንደሌለው፣ የሚበላው ቅጠሉ እንደሆነ፣ ማስተዋልን እንደሚጨምር፣ የሽምደዳ (ሒፍዝ) ችሎታን ለማዳበር እንደሚያግዝ፣ የረሳን እንደሚያስታውስ፣ ደስታን እንደሚሰጥ (ምርቃናውን ማለቱ ይሆን?)፣ የምግብ፣ የእንቅልፍና የግንኙነት ፍላጎትን እንደሚቀንስ፣ ሁሉም እንደሚበሉትና እንደሚጓጉለት ይገልፃል። ስለዚህ የጫት ወረራው የጥንት ነው ማለት ነው። አፄዎቹ አሰራጭተውብን ነው የሚለውን የአንዳንዶች ክስ እዚህ ላይ አስታውሱት። በተለይ ደግሞ ዒልም ፈላጊ ደረሶች፣ በስራ እና በሌሊት ጉዞ ምክንያት ሌሊቱን ነቅተው ማሳለፍ የሚሹ ሰዎች ይጠቀሙታል። እዚህ ላይ ከጫት ጋር ተያይዞ የየመኑ ጫት ራሱ መነሻው ሐበሻ እንደሆነ ጥቆማ የሚሰጥ አስገራሚ ታሪክ ጠቅሷል። ስለ ኢፋት ህዝብ አመጋገብ ሲያነሳ ብዙም ዶሮ መብላትን አይፈልጉም፤ ቆሻሻ ስለምትበላ ይፀየፋሉ ይላል።
የደዋሮ ሱልጧኔትን በተመለከተ የኢፋት ጎረቤት እንደሆነና ስፋቱ ትንሽ ቢሆንም ከኢፋት ጋር የሚቀራረብ ጠንካራ ሰራዊት እንደነበረው ይገልፃል።
የሀዲያ ሱልጧኔት ስፋቱ ትንሽ ቢሆንም ከሰባቱ ሱልጧኔቶች ሁሉ ጠንካራ ሰራዊት ያለው እንደነበር ጠቅሷል።
የደዋሮ፣ የሀዲያ፣ የአራቢኒ፣ የሸርኻ፣ የዳራ እና የባሊ ሱልጧኔቶች አንዱ ከሌላው ጋር ሁለ ነገራቸው ተመሳሳይ ነው። ከኢፋት በተለየ ሁሉም የሐነፊያ መዝሀብ ተከታይ ናቸው። በኢፋት ግን የሻፍዒያ መዝሀብ በሰፊው እንዳለ ይጠቅሳል።

እነዚህ ሱልጧኔቶች ሁላቸውም ለኢፋት ሱልጧኔት አክብሮት አላቸው። በአንዳንድ ጊዜም ከጎኑ ይቆማሉ።
የሐበሻ ህዝብ ብዙ እንዳላቸው፣ ሃይለኞች ስለሆኑ ከነሱ ውጭ ያለ አካል ገዝቷቸው እንደማያውቅ፣ ጦረኞች ናቸው። ከጀግንነታቸው ባሻገር ይቅር ባዮች እንደሆኑና በጦርነት ላይ መሳሪያውን የጣለን ሰው አይነኩም። እንግዳ አክባሪዎች ናቸው። ለዚህም የነጃሺን ቁረይሽን መቀበሉን ማጣቀሻ ያደርጋል። ሌላ ያነሳው ነገር ማስመሰል የላቸውም። በእውነተኝነትና በታማኝነት ይታወቃሉ። እነዚህ መልካም ስብእናዎች ዛሬ የሐበሻ ህዝብ ላይ ምን ያህል አሉ?
ሌላ ያነሳው ነገር ዘራቸው አይነቱ አንድ ቢሆንም ከ50 የሚበልጡ ቋንቋዎች እንዳሉ የሁሉም መፃፊያ ፊደል አንድ እንደሆነ እሱም ሐበሽኛ (አማርኛ?) እንደሆነ ነው። የሚፃፈውም ከቀኝ ወደ ግራ ነው፣ ልክ እንደ ዐረብኛው ማለት ነው። መቼ ይሆን ታዲያ ዛሬ ያለው የአማርኛ አፃፃፍ ከግራ ወደ ቀኝ ወደ መፅፃፍ የዞረው? የፊደል ገበታው 16 ፊደሎችን የያዘ እንደሆነና እያንዳንዱ ሰባት ብዜት እንዳለው ጠቅሷል። እንደሚታወቀው በየጊዜው እየተጨመረ ነው ዛሬ የደረሰበት የደረሰው።

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

05 Oct, 07:56


https://youtu.be/FyJAX5XGFHY?si=5X2vE7i5wN3NoLIl

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

05 Oct, 07:07


https://youtu.be/qmjbHnjR3Cw?si=nJT5sfKi8I1Yjsto

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

28 Sep, 00:49


https://youtu.be/ORtrcMbSzaE?si=7jnb8Du5o1pSlXbk

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

28 Sep, 00:49


https://youtu.be/vtV6EQ8Y1Gs?si=ccKTQS8VdU5XaTmX

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

18 Sep, 13:23


ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ ምን አስበው ነው⁉️
==========================

መቼም የዘንድሮው መውሊድ ያልገለጠው ጭንብል የለም። በተለይ የኢኽዋኑ ቡድን መውሊድን ከሱፍያ በላይ ሕያው አድርጎ ለማክበር ደፋ ቀና ሲል ታዝበናል። ብዙዎች ይህን ያደረጉት ለስልጣን ብቻ ሳይሆን ከልብ አምነውበትም ጭምር ነው። አንዳንድ ሙነሺድ ተብዬዎች መውሊድን የተፈቀደ ለማድረግ ያለ አቅማቸው መረጃ ለማምጣት ሲጋጋጡ ታዝበናል።

አነስ ኢብኑ ማሊክ እንዲህ ይላል፦
(قدِم النبيُّ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم المدينةَ ولهم يومانِ يَلعَبونَ فيهما، فقال: ((قدْ أبْدَلكم اللهُ تعالى بهما خيرًا منهما؛ يومَ الفِطرِ والأضحى )

«ነቢዩ ﷺ መዲና ገቡ፤ በነርሱ የሚጫወቱባቸው ሁለት ቀናት ነበሯቸው። "አላህ በርግጥም ከነርሱ የተሻሉ የሆኑ የፊጥርና የዐረፋህ ቀንን ቀይሮላችኋል!" አሏቸው።»
[አቡ ዳውድ: 1134]


ኢብኑ ሐዝም ሙስሊሞች ከሁለቱ ዒዶች ውጭ ሌላ ዒድ እንደሌላቸው ኢጅማዕ ጠቅሷል።

 ((المحلى)) (5/81)

*
ኢብኑ ዑሠይሚን ከነዚህ ዒዶች ውጭ በየሳምንቱ መጨረሻ ጁሙዓህ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ሦስተኛ ዒድ የለም ብለዋል። ((الشرح الممتع)) (5/111).




እዚህ ጋ ደግሞ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ አፋቸውን ሞልተው «ከ3ቱ በዓላት መካከል ዒደል አዽሓህ ሙባረክ፣ ዒደል ፊጥር ሙባረክ፣ የመውሊድ በዓል…» እያሉ ያወራሉ።


አያውቁም እንዳንላቸው ያውቃሉ። ምን አስበው ነው እኚህ ሰዎች? ቀስ በቀስ ወደ የት እያመሩ ነው? ለዘንድሮ መውሊድ ከመግለጫ ጀምሮ የነበረ ማጨብጨብና ማዳለቅ ታዝባችኋል? ጭራሽ ደግሞ በነበረን ጉባዔ መውሊድ እንዲከበር ተስማምተናል ይላሉ። እነ አርዮስ ነበሩ በጉባዔ ተሰብስበው ሥላሴን ያጸደቁት። እና የኛም ሰዎች ተሰብስበው ከሸሪዓው ውጭ የሆነን ቢድዓህ ተሰባስበው ሦስተኛ ዒድ ሊያደርጉት ነው? ወሕይ ወርዶ አልቋል። ዲናችን የተሟላ መሆኑን አላህ ነግሮናል። ከአላህ በላይ ማን መስካሪ አለ!

ኧረ! አታስቁን ወገን። የፈለገ ጃሂል ቢሆን እናንተ የሚያዳምጥበት ገደብና ጥግ አለው። ሁሉም ዝም ብሎ በጭፍን አይከተላችሁም። በጥልቀት ባይቀራም በንፁህ አዕምሮ ይታዘባችኋል። ከሆኑ አመታት በፊት መስጅድ ላይ ስለ መውሊድ ቢድዓነት ሲያስተምሩ የነበሩ ሰዎች ተገልብጠው ዛሬ በሚዲያ እንዲህ ሲሉ ማየት ያሳፍራል። ቀልብ ቀያያሪ የሆነውን አላህን ቀልባችንን በሐቅ ላይ አፅናልን ከማለት ውጭ ሌላ ምን እንላለን?

ሐቅን እንጂ ሰዎችን አንከተልም
ሐቅ በዞረበት እንዞራለን። የምንመራው በቁርኣንና ሐዲሥ እንጂ በሰዎች አይደለም።

||
t.me/MuradTadesse

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

03 Sep, 13:48


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

📜መውሊድን በተመለከተ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነውር የተዘጋጁ ከፊል ፅሁፎችን በቀላሉ እንዚህን ሊንኮች በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ።

1, ነብዩ ﷺ መቼ ተወለዱ?
https://t.me/IbnuMunewor/893

2, መውሊድን ማን ጀመረው? በመረጃ ለሚያምኑ ብቻ
https://t.me/IbnuMunewor/869

3, መውሊድ ለምን አላማ እንደተጀመረ ያውቃሉ?
https://t.me/IbnuMunewor/876

4, መውሊድና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም! {ምስክር እራሳቸው!}
https://t.me/IbnuMunewor/884

5, “በአላህ እዝነት ይደሰቱ...” - ትልቁ የመውሊድ አጋፋሪዎች ምርኩዝ
https://t.me/IbnuMunewor/2227

6, የሰኞ ፆም እና መውሊድ
https://t.me/IbnuMunewor/2214

7, ዐቂቃ ሌላ መውሊድ ሌላ!
https://t.me/IbnuMunewor/2261

8, ዓሹራን ለመውሊድ?
https://t.me/IbnuMunewor/2269

9, መውሊድ ውስጥ እነዚህ አደጋዎች አሉ!
https://t.me/IbnuMunewor/2294

10, በመውሊድ ላይ ስለሚፈፀመው ጭፈራ ዑለማዎች ምን እንዳሉ ታውቃለህ?
https://t.me/IbnuMunewor/882

11, መውሊድን የሚፈቅዱትም አይፈቅዱትም!
https://t.me/IbnuMunewor/2298

12, መውሊድ የማያከብር ሰው የሙሐመድ ﷺ ጠላት ከሆነ፣ ገና የማያከብር ሰው የዒሳ ጠላት ነው!
https://t.me/IbnuMunewor/886

13, እውን የሡወይባ ታሪክ ለመውሊድ ማስረጃ ይሆናል?
https://t.me/IbnuMunewor/2234

14, ሸውካኒ እና መውሊድ (ወሳኝ ነጥቦች የተዳሰሱበት)
https://t.me/IbnuMunewor/898

15, ሲዩጢ፣ የመውሊድ ደጋፊዎች ሌላኛው ምርኩዝ
https://t.me/IbnuMunewor/2277

16, እውን ኢብኑ ተይሚያ መውሊድን ፈቅደዋል?
https://t.me/IbnuMunewor/878

17, በሸይኹል አልባኒ እና “መውሊድ ይፈቀዳል” በሚል ሰው መካከል የተደረገ ድንቅ ቃለ-ምልልስ
https://t.me/IbnuMunewor/34

18, ከ“ወሃብዮች” በፊት የነበሩ የመውሊድ ተቃዋሚዎች
https://t.me/IbnuMunewor/1624

19, መውሊድ ተከሽኖ
https://t.me/IbnuMunewor/2309

20, ለምንድን ነው የመውሊድ ተቃውሞ ኢኽዋኖችን ምቾት የሚነሳቸው?
https://t.me/IbnuMunewor/918

21, መሷሊሐል ሙርሰላ፣ የመውሊድ አክባሪዎች የመጨረሻው ምሽግ
https://t.me/IbnuMunewor/2302

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

27 Aug, 15:12


ዛሬ የአንድ የ30 ዓመት ታካሚዬ ወደ ህክምና ቦታ በመምጣት "ትኩሳት ነበረኝ፣ ላብ ያልበኛል፣ ብርድ ብርድ ይለኛል፣ ቁርጥማት አለኝ፣ ምግብ ከልክሎኛል፣ ራሴን በጣም ወጥሮ ይዞኛል እና ደሞ ያዞረኛል" አለኝ።

እየነገረኝ ያሉት ስሜቶች አፋጣኝ የትኩሳት ህመሞች (Acute Febrile Illness) የሚባሉትን እንደ ወባ (Malaria)፣ ታይፎይድ (Typhoid Fever)፣ ደንግ (Dengue Fever) የመሳሰሉትን እንዲሁም ተላላፊ ካልሆኑት ህመሞች ውስጥ ደሞ (Non-communicable disease) የስኳር (DKA)፣ የእባብ ንድፊያ (Snake Bite) የመሳሰሉት መላምቶች ወደ አእምሮዬ እየመጡ ነበር።

በደንብ እንዲያስረዳኝ ስጠይቀው እና ምን ምን እንደተመገበ እና ያረጋቸውን ነገሮች ስናስታውስ፤ "መናገር ፈርቼ እንጂ ትላንት በጓደኞቼ ውትወታ ጫት ለመጀመርያ ጊዜ ሞክሬ ነበር" አለኝ።

የጫቱን ነገር ሹክ ካለኝ በኃላ ግን ያሰብኳቸው የነበሩት ነገሮች በከፊልም ቢሆን ውድቅ አረኳቸው እና ቀለል ያሉ ምርመራዎች አድርጎ ተገቢው ህክምና ተደርጎለት ሊሄድ ችሏል።

የጫት ተክል እንግዲህ ቅጠሎቹ እና ግንዱ የሚታኘክ አይነት የእፅ-ዋት ዝርያ ነው። በዓለም ደረጃ በአንድአንድ ሪሰርቾችም ጭምር ተፅፎ የምናገኘው የጫት አወሳሰድ በባህላዊ መንገድ ለተሃድሶ እና ለመዝናናት እየተባለ በምስራቅ አፍሪካ በስፋት እንደሚወሰድ ያስረዳል። በዋናነት ጠቅሶም ኢትዮጰያ እና ሶማሊያ እንደ መነሻ ሀገራት ሲጠቀሱ ኬንያ፣ የመን እና የአረብ ሰርጥ ሃገራት ደግሞ እንደ ማስፋፊያ ታክለው እንመለከታለን።

ለዚህም ምክንያት የሆኑት 'ለስኳር ህመም፣ ለጡንቻ ጥንካሬ፣ የምግብ ፍላጎትን ለመቀነስ፣ የእንቅልፍ ጊዜን ለመቀነስ እና ንቃትን ለመጨመር' ይጠቅማል በሚል ሰፋ ያለ የማህበረሰብ ክፍልን ሊደርስ ችሏል። ምንም እንኳን ለተገለፁት ነገሮች ምንም አይነት ማስረጃ ባይገኝለትም በብዙሃን ዘንድ ለዘመናት እስከ ሞት ድረስ ከጥርስ ስር ሊውል ተገዷል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በጥናት የተመሰረቱ እና ጫትን መጠቀም የሚያስከትላቸውን ዋና ዋና ችግሮች በጥቂቱ ለማካተት ተሞክሯል፦

ለመጀመርያ ጊዜ ስንጠቀመው፡
1. የደም ግፊትን መጨመር እና በመድሃኒት እንኳን ለመቀነስ መቸገር
2. የስኳር መጠንን ከተያዘው እሳቤ በተቃራኒ መልኩ መጨመር
3. የእንቅልፍ እጦት
4. ከፍተኛ የልብ ምት መጨመር
5. የአእምሮ ህመሞች እንደ ድባቴ፣ ማንነትን መርሳት፣ ትኩረት መዛባት፣ ከፍተኛ ንዴት፣ ጭንቀት እና እረፍት የለሽ መሆን
6. የጉበት ኢንፌክሽን፣ ነጭ የደም ሴሎች ከፍ ማለት እና የደረት አጥንቶች ስር የህመም ስሜትን ያካትታል

በረዥም ጊዜ የሚያመጣው እክል:
1. የራስ መርዘን (Migraine)
2. የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ (Intracranial Hemorrhage)
3. የልብ ድካም (Heart Attack)
4. ከፍተኛ የጉበት መኮማተር (Liver Cirrhosis) እና የኩላሊት መቆጣት
5. የጨጓራ እና የአንጀት ካንሰር (Esophageal and Gastric Ca.)
6. የጥርስ መቦርቦር (Dental Caries)፣ የድድ ማበጥ መድማት እና መሸሽ፣ የአፍ ውስጥ ከፍተኛ ቁስለት እና ካንሰር
7. የግንኙነት ስሜት መቀነስ እና መውለድ አለመቻል
8. በእርግዝና ጊዜ የፅንሱ ክብደት እንዳይጨምር ማድረግ (Prematurity syndrome)
9. የእናት ጡት ለሚጠቡ ህፃናት የጡት ወተት ማነስ እና አደገኛ ንጥረ ነገሮች በጡት ወተት በኩል ማለፍን ጨምሮ የተለያዩ ችግሮች ሊያስከትል ይችላል

ከዚህም በተጨማሪ በታች ከተጠቀሱት መድሃኒቶች ጋር በፍፁም ጫትን መጠቀም ክልክል ነው

1. የደም ማቅጠኛ መድሃኒቶች (Warfarin)
- መድሃኒቱ ስራውን እንዳይሰራ በማድረግ የደም መርጋት እንዲባባስ ያደርጋል
2. የአእምሮ ህመም መድሃኒቶች (Antipsychotics)
3. አንቂ መድሃኒቶች (Stimulants: Epinephrine, Pseudoephedrine etc...)
- የልብ ምት እንዲሁም የግፊት መጠን እንዲጨምር ያባባሳል
4. የደም ግፊት መድሃኒቶች (Lasix, Amylodipine, Enalapril etc)
- የግፊት መጠንን ከመድሃኒቶቹ የዶዝ አቅም በላይ በመጨመር ቁጥጥሩን ከባድ ሊያደርገው ይችላል
5. የኢንፌክሽን መድሀኒቶች (Ampicillin and others)
- መድሃኒቱ በትክክል እንዳይሰራ እናም በሽታው እንዲባባስ ያደርጋል

የአለም ጤና ድርጅት (WHO) ጫትን ጥገኛ ከሚያደርጉ እፆች መሃል የመደበው ሲሆን ይህም በተደጋጋሚ እንድንጠቀመው እና እንዲያሰኘን የሚገፋፉ ንጥረ ነገሮችን እንደ ካታየን (Cathine) እና ካቲኖን (Cathinone) የተሰኙ ከከፍተኛ አደንዛዥ መድሃኒቶች እንደ ኤክተሲ (Ecstacy) እና አምፊታሚን (Amphetamine) ንጥረ ነገሮች ጋር የመወዳደር አቅም ያላቸውን የያዘ ነው። በዚህ እና በተያያዥ ምክንያቶችም በአሜሪካ እና በካናዳ ሀገራት ሙሉ ለሙሉ ታግዷል።

ለማጠቃለል ያክል በእኛ ሀገር እያመጣ ያለውን የጎንዮሽ ጉዳት ብዙሃኑ የእፁ ተጠቃሚ ሰዎች በቀጥታ ከጫት ጋር ላያያይዙት ስለሚችሉ ግንዛቤውን ማስጨበጥ የጤናው ዘርፍ ባለሞያዎች ሀላፊነት ይኖርብናል። በተለይም ደግሞ ለረዥም አመታት ጫትን እንደ አንድ የአስቤዛ ግብአት የሚጠቀሙ ሰዎች ላይ የሚያመጣው ጫና በቀላሉ ሊታለፍ የሚገባው አይደለም።

Reference List

1. Research (Pubmed): https://rb.gy/j7kv98
2. Research PDF File (EPHI): https://rb.gy/dx6a2k
3. WebMD: https://rb.gy/7gl6lg

ዶ/ር ኢዮብ ባሳዝነው: ጠቅላላ ሀኪም
Youtube: http://www.youtube.com/@Hakim207?sub_confirmation=1

@HakimEthio

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

23 Aug, 06:39


🎓 በዓይነቱ ልዩ የኮርስ ማጠናቀቂያ ፕሮግራም በኢማም አህመድ መስጂድ ተጋብዘዋል። በዕለቱም፤

⭐️ ከተለያዩ ሀገራት በመጡ ታላላቅ ኡለማዎች ምክር ይሰጣል

⭐️ ብልጫ ላሳዩ ተማሪዎች የሽልማት ስነስርዓት

⭐️ በኮርሱ ተሳታፊዎች የሚቀርቡ እና ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ይኖራሉ

🗓 እሁድ ነሀሴ 19/2016

ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ

🕌  ፕሮግራሙ የሚካሄደው አለም ባንክ በሚገኘው ኢማሙ አህመድ መስጆድ ነው


_
ibnu Mas'oud islamic Center
@merkezuna

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

19 Aug, 08:06


https://youtu.be/OghEeUiZ2BU?si=TMXNWnUKi0YaUc2g

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

18 Aug, 07:27


https://youtu.be/3gYoMuMtGPo?si=yDYTjr2fn-SivZ0g

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

16 Aug, 15:37


https://youtu.be/8uYSd2fl5zY?si=ybqjbtEeluk91xY5

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

15 Aug, 18:40


📌 دورة ميراث الأنبياء العلمية الرابعة

من ١٢ صفر ١٤٤٦هے‍ الموافق ١٦\٨\٢٠٢٤م إلى يوم الأحد  ٢١ صفر ١٤٤٦هے‍ الموافق ٢٦\٨\٢٠٢٤م

١) الدرة المضية في عقد الفرقة المرضية

🎙 د/ إسماعيل بن غصاب العدوي حفظه الله

  ےے❊❊ےے


٢) منظومة القواعد الفقهية لابن سند

🎙 د/ خالد بن شجاع العتيبي حفظه الله

ےے❊❊ےے


٣) النظم المعسول في تعليم الأصول

🎙 د/ عبد الرحمن حامد آل نابت حفظه الله
ےے❊❊ےے


٤) مقدمة في أصول التفسير لابن تيمية

🎙الشيخ إلياس أحمد محمد حفظه الله

ےے❊❊ےے


٥) لامية ابن الوردي في الآداب

🎙د/عبدالرحمن بن صالح المزيني حفظه الله

ےے❊❊ےے


٦)  متممة الآجرومية

🎙 الدكتور خليل حامد خليل حفظه الله

ےے❊❊ےے

👈 ملاحظة
* هناك محاضرات مختلفة تصاحب الدورة
* الخدمات للطلاب المسجلين فقط ولكن يحق الاستفادة من الدروس للجميع
* جميع الدروس باللغة العربية فقط
* الدروس تخص الرجال دون النساء

🕌 مكان إقامة الدورة
مركز ابن مسعود الإسلامي في حي ١٨

⛳️ الموقع على الخريطة
https://goo.gl/maps/oC7GZtpeLwkzxrVr8


___
🕌 Ibnu Mas'oud islamic center
t.me/merkezuna

Selsebil Zumekan/ሰልሰቢል ዙመካን

12 Aug, 18:00


https://youtu.be/FVlPnP_rGIg?si=QedhJhpYFaedwhcD

1,419

subscribers

186

photos

57

videos