ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

@asedullahh


قال الله تعالى ( وَلَا تَلْبِسُوا الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُوا الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ )البقرة (42)

አሏህ በእርግጥም አለ፦[እውነትን በውሸት አትሸፍኑ እናንተ እውነታውን እያወቃቹህ]

ምንጭ፦«ሱረቱ አል–በቀራህ አንቀፅ /42/


በኡስታዝ ሐምዛ
[አሰዱሏህ]

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

22 Oct, 03:52


√ ጠቃሚ ነጥብ…

مسألة: يُسْتحَبُّ تَقْبِيلُ القَادِمِ مِن السَّفَرِ، أمَّا تَقْبِيلُهُ عِندَ تَوْدِيعِهِ فَمُبَاحٌ لَيْسَ سُنَّةً.
๏ [ከጉዞ የመጣን ሰው መሳም የሚወደድ ሲሆን ነገር ግን ወደ ጉዞ ለመሄድ ሲሸኝ መሳሙ ሱናህ ባይሆንም ፍቁድነት ያለው ተግባር ነው]።
أمَّا الْتِزَامُ القَادِمِ مِن السَّفَرِ فَلا يَبْعُدُ القَوْلُ بِسُنِّيَّتِهِ، أمَّا مُصَافَحَةُ القَادِمِ والمُغَادِرِ فَسُنَّةٌ أمَّا التَّقِيُّ فَيُقَبَّلُ.
๏ [ነገር ግን ከጉዞ የሚመጣን ሰው ማቀፍ ሱናህ ነው የሚለው ፍርድ አይርቀውም። ማለትም ሱናህ ማለት ይቻላል።ነገር ግን ከጉዞ የሚመጣን ሆነ ወደ ጉዞ የሚሸኝን ሰው መጨበጥ ማለትም(ኣ·ጅነብይ/ኣ·ጅነብያህ) የሚለው የክልከላ ድንጋጌ እንዳለ ሆኖ መነካካቱ ከሚበቃልን ጋር ማለት ነው ሱናህ ነው።ነገር ግን ያ ሰው አሏህን ፈሪ ከሆነ ይሳማልም]።

# ከጉዞ የሚመጣን የሚሸኝን…
🤝#መጨበጥ
…#ማቀፍ
…#መሳም

FOR~HAMZA
..........ASEDULLAH

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

21 Oct, 19:45


☜ التوكل على الله
※"በአሏህ ስለ መመካት"

عَنْ عُمَرَ بْنِ الْخَطَّابِ رَضِيَ الله عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى الله عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: "لَوْ أَنَّكُمْ تَتَوَكَّلُونَ عَلَى اللهِ حَقَّ تَوَكُّلِهِ لَرَزَقَكُمْ كَمَا يَرْزُقُ الطَّيْرَ، تَغْدُو خِمَاصًا وَتَرُوحُ بِطَانًا" رَوَاهُ الْإِمَامُ أَحْمَدُ

※ ዑመር ብኑ ኣል–ኻጧብ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንዲህ ይላሉ፦["እናንተ እውን በአሏህ ላይ ያላችሁ መተማመን ጉድለት የሌለው (እውናዊ) ቢሆን ጠዋት ባዶ ሆዷን ወጥታ ስትገባ ቀልቧት ሆዷ ሞልቶ እንደምትመለሰው በራሪ እናንተንም ይቀልባቹህ ነበር።
ምንጭ፦<ኣል–ኢማም ኣሕመድ ዘግበውታል>

FOR~Hamza
  Asedullah

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

19 Oct, 19:00


← فائدة— قال العلاَّمةُ مُـحمَّدُ ميّارة الـمالكيُّ (1072 هـ)
๏ጠቃሚ፦ ኣል–ዓላመቱ ሙሓመድ መያራህ ኣል–ማሊክይ "1072" ዓ·ሂ የሞቱት እንዲህ ይላሉ፦

”أَجمعَ أَهْلُ الحَقِّ قَاطِبَةً على أنَّ الله تَعالى لا جِهَةَ له، فلا فوقَ له ولا تحتَ ولا يمينَ ولا شمالَ ولا أمامَ ولا خَلْفَ “.
["የእውነት ባልተቤቶች በጠቅላላዎቻቸው የተጥራራ ጌታ የሆነው አሏህ አቅጣጫ፣ላይ ሆነ ታች ፣ቀኝ ሆነ ግራ ፊት ሆነ ሃሏ እንደማያስፈልገው በጋራ አቋማቸው አፅንተዋል"]።


المصدر؛ كتاب الدُّرِّ الثمين والـمورد الـمَعين شرح الـمرشد الـمُعين على الضروريِّ من علومِ الدِّين للشيخِ عبدِ الواحدِ بن عاشر الأنصاريِّ الأشعريِّ الـمالكيِّ رحمهما الله تَعالى ما نصّه:
ምንጭ፦ <ኣ·ዱሩ ኣ·ሰሚይን ኣል–መውሪዲል ሙዒይን ሸርሒ ኣል–ሙርሺዲል ሙዒይን ዓለ ዶሩሪይ ሚን ዑሉሚ ዲን ሊ·ሸይኽ ዓብዲልዋሒድ ብኒ ዓሺር ኣል–ኣንሷርይ ኣል–ኣሽዓርይ ኣል–ማሊክይ>።

FOR ~HAMZA
      ASEDULLAH

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

09 Oct, 18:22


#‼️በሊባኖስ ዛሬ ጨረቃ የነበራት ቀለም።

🤲 #አሏህ ሆይ በዳዮችን ያዝልን።አሏህ ሆይ በእኛም ሆነ በተቀሩት ምእመናን ላይ በጎን የሻ ወደ በጎ ነገር ባጠቃላይ የሚገጠም አድርገው።ነገር ግን በእኛም ሆነ በሌሎች ምእመናኑ ላይ መጥፎን የሻ የበረታ እንዲሁ ጠንከር ያለን መልስ ስጥበት።አቅሙንም አሳጣው።አይኑንም ጋርደው።

🤲#አሏህ ሆይ ፊልስጢምን እንዲሁ ሊባኖስን የተቀሩትንም የምእመናኑን ሀገር ሰላም አድርግልን።

‼️ሒሳቡም ቀርቧል። በደሉና ሓጢያቱም ተንሰራፍቷል።🤲 ያረብ ኣል–መህዲን ብቅ አድርግልን።

አስተውል፦"ስለ ሰው ልጅ ፍትሕ አሳቢ ነን እያሉ ነገር ግን ፍትሑን ብቻ ሳይሆን ሰብኣዊ ማንነቱንም የሰውነት ዘይቤውንም አራክሰውት ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያስፋፉ ለውሻና አሳማ ክብር በማለት እነርሱን ለምንስ ከሰው ልጅ ጋር  ማጋባት አይበቃም እያሉ እንደ ጋብቻ በሕገ መንግስት ደረጃ አርቅቀው ከእንስሳ ጋር ግኑኝነትን የፈቀዱ ምዕራባውያኑ ዛሬ በጋዛህ ከ 42000 በላይ ንፁሀን ሲፈጁ በሊባኖስ በ 2 ሳምንት ውስጥ ከ 2000 በላይ ምእመናን ሲረፈረፉ ለሰው ፍትህ ነው የቆምኩት ባዩ እንኳ የኣውሮፖ ሕብረት  አፉን ይዞ አንዲትን ከአሳማ ጋር ግኑንነት ሆነ ጋብቻ የሚባል ነገር ይበቃል እፈቅዳለው ያለችን የሰውን ክብር ቅንጣት  ማታውቅን እስራኤል የሚሏትን ሀገር ከማስቆም ተስኖት ይልቅንስ ከ ጎኗ በመሰለፍ ፍትሑን አዛብተውታል።

ወንድሞቻችን ዱዓህ ይሻሉ እኛም እንሻለን።
ተበራቱ።ወሏህ አዝኛለው እኛ የት ነን በዱዓችን እውን ከእነርሱ ጋር ነን? ወደ ዲን መጃሊሶች እንቃረብ አንሰላች ቀልባችንን ወደ አሏህ መንገድ እናዙር ባረከሏሁ ፊይኩም።የዲን እውቀት የእስልምና ሕይወት ነው። እርሱን ካከሰምነው የጀነቱን መዳረሻ መንገድ አጨለምነው ማለት ነው።

FOR~HAMZA
..........ASEDULLAH

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

09 Oct, 17:17


مَا حُكْمُ عَدَمِ إِنْظَارِ الْمُعْسِرِ.
☞ "ተበድሮ ያለን ሰው ብድሩን መክፈል እያልቻለ ሳለ እርሱን አለመጠበቅ (ግዜ አለመስጠት) ፍርዱ ምንድን ነው"?

يَحْرُمُ عَلَى الدَّائِنِ تَرْكُ إِنْظَارِ الْمُعْسِرِ أَىِ الْعَاجِزِ عَنْ قَضَاءِ مَا عَلَيْهِ مِنَ الدَّيْنِ مَعَ عِلْمِهِ بِعَجْزِهِ أَىْ يَحْرُمُ إِيذَاؤهُ بِحَبْسٍ أَوْ إِزْعَاجٍ.
๏ ከአበዳሪ ላይ ገንዘብን ተበድሮ ለመመለስ የተሳነውን (የተቸገረን) ሰው አለመጠበቅ ሓጢያት ሲሆን ማለትም አበዳሪው ይህ ተበዳሪ ያለበትን እዳ ከመክፈል የዳገተው እንደሆነ ከማወቁ ጋር ግዜ ሰጥቶ ማይጠብቀው ከሆነ ማለት ነው ሓጢያት ይሆናል።ማለትም ይህን ተበዳሪ ብድሩን ከመክፈል በማዘግየቱ ምክነያት እርሱን ማስቸገር  በማሰር አልያ በማጨናነቅ ሊሆን ይችላል ይህ ነገር አይቻልም።

    رَوَى مُسْلِمٌ مِنْ حَدِيثِ أَبِى الْيَسَرِ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ قَالَ مَنْ أَنْظَرَ مُعْسِرًا أَوْ وَضَعَ لَهُ (أَىْ أَسْقَطَ شَيْئًا مِنْ دَيْنِهِ) أَظَلَّهُ اللَّهُ فِى ظِلِّهِ (أَىْ فِى ظِلِّ الْعَرْشِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ) يَوْمَ لا ظِلَّ إِلَّا ظِلُّهُ، ​​​​
※ከኣ·ቢል የሰር ሓዲይስ እንደተያዘው የአሏህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላሉ፦"ከመክፈል የተቸገረን ሰው ግዜ የሰጠ አልያ ዓፍው ያለ (ማለትም ከተበደረው ከፊሉንም ቢሆን ይቅር ያለ) አሏህ በእዛ የትንሳኤ ዕለት የእርሱ የዓርሽ ጥላ እንጂ የማንም ጥላ በሌለበት ግዜ በእርሱ ጥላ ስር እንዲጠለል ያደርገዋል"።

ምንጭ፦<ሙስሊም ዘግበውታል>።

FOR~ሓምዛ
   ኣሰዱሏህ

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

08 Oct, 21:58


ዋ ኢስላማ።


رجل في أمريكا رأى أسد يهاجم فتاة فقتل الأسد فكتبت الصحف "مواطن امريكي بطل أنقذ فتاة من الأسد مفترس"

«አንድ አሜሪካ ውስጥ የነበረ ወጣት አንዲት እንስት ላይ አንበሳ ጉዳት ሲያደርስባት ይመለከትና አንበሳውን በመግደል ሕይወቷን ያድናታል።መፅሄቶች(ጋዜጠኞችም) ይህን ክስተትም እንዲህ በማለት ዘገቡ፦"ጀግናው አሜሪካዊ ከአዳኙ አውሬ አንበሳ የወጣቱዋን ሴት ህይወቷን ታደጋት"።

فقال الرجل "أنا لست امريكي " فكتبت الصحف "أحد الاجانب الأبطال ينقذ فتاة من أسد مفترس"
※ ይህም ሰው አላቸው እኔ አሜሪካዊ አይደለሁም።መፅሄቶች (ጋዜጠኞችም) እንዲህ በማለት ፃፉ፦"አንድ ጀግና የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው ሰው ከአዳኙ አውሬ አንበሳ የወጣቱዋን ሴት ህይወቷን ታደጋት"።

فقال الرجل "أنا مسلم" فكتبت الصحف: "ارهابي يقتل اسد بريء كان يلعب مع فتاة"..!!!
※ ይህም ሰው አለ፦እኔ ሙስሊም ነኝ።መፅሄቶች (ጋዜጠኞችም) እንዲህ በማለት ፃፉ፦"አንድ አሸባሪ ሰው በአሜሪካ ከአንዲት ወጣት ሴት ጋር ሲጫወት የነበረን በዱር የሚኖርን አንበሳ ገደለ"።


ዋ ኢስላማ።ምዕራባውያኑ እስልምናን አጠልሽተውት ሰው ጋር የሚቀርበው ይህ ነው።


FOR~HAMZA
...........ASEDULLAH

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

07 Oct, 19:33


☜ قال الشيخ: وَرَدَ فِي الآثَارِ أَنَّ مِن عَلَامَاتِ خُرُوجِ المَهْدِيِّ كَثْرَةُ الزَّلَازِلِ،
قال الشيخ: ءَاخِرُ العَلَامَاتِ الصُّغْرَى لِلْقِيَامَةِ ظُهُورُ المَهْدِيِّ، وَأَوَّلُ الكُبْرَى ظُهُورُ المَسِيحِ الدَّجَّالِ.

☞ ኣ·ሸይኹ ዓብዱሏሂ ኣል–ሃረሪይ እንዲህ አሉ፦ «ከአንዳንድ ምንጮች እንደተገኘው ከመህዲ መውጫ ምልክቶች መሀከል የመሬት መንቀጥቀጥ መብዛት ይገኝበታል።

☞ ሸይኽም አሉ፦«ከትንንሾቹ የትንሳኤ ምልክቶች በስተመጨረሻ ማብቅያ የሚሆነው የመህዲ መውጣት ሲሆን የትላልቆች መጀመርያ ደግሞ ኣል–መሲይሑ ደጃል መውጣቱ ነው»።

FOR~HAMZA
..........ASEDULLAH

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

06 Oct, 19:20


ሰበር መረጃ‼️

من علامات الساعة كثرة الزلازل.
«ከትንሳኤ ዕለት ምልክቶች መሀከል የመሬት መንቀጥቀጥ መብዛት ነው»

☞ከቅርብ ሰኣት በፊት በመዲናችን አዲስ አበባ በአንዳንድ ክፍለ ከተማዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።ይህን በመሰሉ አስፈሪ ክስተቶች ምንግዜም እንደምንለው ቲክ ቶክ ቪድዮ በመስራት ማላገጥ አልያ መዝናኛ ወሬ ማድረግ ሳይሆን ወደ አሏህ ይብልጡኑ የመመለሻ ግዜ እና ምልክት ነው።! አሏህ እነኚህን ነገራቶች ይፋ የሚያደርገው ባሮችን ሊያስፈራራበት ዘንዳ ነው።የትንሳኤ ምልክቶችም መሀከል አንዱ የመሬት መንቀጥቀጥ መብዛት ነው።

FOR~HAMZA
..........ASEDULLAH

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

06 Oct, 14:52


#አግቡ ተጋቡ
በሀላሉ መንገድ
ኡስታዞቻችን በተግባር እየመከሩን ነው!
የተባረከና ያማረ እስከ ጀነት የቀጠለ ትዳር ያድርግላችሁ ኡስታዙና።

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

https://t.me/asedullahh

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

05 Oct, 19:10


⇄  فائدة— عقيدة الإمام مالك رضي الله عنه
๏ ጠቃሚ ነጥብ፦ የኣል–ኢማሙ ማሊክ ረዲየሏሁ ዓንሁ ዕምነትን በተመለከተ፦

ثبت عن الإمام مالك ما رواهُ الحافظُ البيهقي بإسنادٍ جيد (كما قال الحافظ ابن حجر العسقلاني في الفتح) في كتاب الأسماء والصفات ص 408 - من طريق عبد الله بن وهبٍ قال: كنّا عند مالكٍ فدخل رجلٌ فقالَ: يا أبا عبد الله الرحمنُ على العرش استوى كيف استوى فأطرق مالكٌ رأسه فأخذته الرحضاء ثم رفع رأسهُ فقال: الرحمن على العرش استوى كما وصف نفسهُ ولا يقالُ كيف والكيف عنه مرفوعٌ وما أراك إلا صاحب بدعة أخرجوه.اهـ
✓ ኣል–ሓፊዙ ኣል–በይሃቅይ ጥሩ በሆነ ሰነድ ከኣል–ኢማም ማሊክ ረዲየሏሁ ዓንሁ ይህ መረጋገጡን ዘግበዋል።ይህንም ኣል–ሓፊዙ ኢብኑ ሓጀር ኣል–ዓስቀላንይ በ "ኣል ፈትሑ ኣል ባሪይ" በተሰኘው ኪታባቸው ላይ ተናግረውታል።ኣል–ኢማሙ ኣል–በይሃቅይ "ኣል–ኣስማኡ ወሲፋት በተሰኘው ኪታባቸው በገፅ 408" ላይ ከ ዓብዲላህ ብኒ ወሃብ መንገድ ይዘው እርሱ እንዲህ አለ በማለት ጠቀሱ፦"ከማሊክ ጋር ነበርን: ቀጥሎም አንድ ሰው ወደ ማሊክ ገባ።እንዲህም አለ አንቱ የዓብዲላህ ኣባት ሆይ "الرحمٰن على العرش استوى " እንዴት ነው ኢስቲዋኡ ኣላቸው! እርሳቸውም አንገታቸውን ኣዘቀዘቁ።ላብም ኣጠመቃቸው።ቀጥሎም አንገታቸውን ከፍ አደረጉና እንዲህ አሉት፦
"الرحمٰن على العرش استوى"
"እራሱን እንደገለፀበት ነው።ኢስቲዋኡ እንዴት አይባልም።እንዴት¹ የሚለው ጥያቄ ከአሏህ የራቀ ነው።አንተን መጥፎ መጤን ነገር አምጪ ሰው አድርጌ ቢሆን እንጂ አላይህም ብለው እርሱ በማስወጣት ላይ አዘዙ"።

¹፦[እንዴት የሚለው ቃል ለፍጡር እና የፍጡር ባህሪ ላለው ነገር የሚጠየቅ ነው።አሏህ ደግሞ ፍጡር ሆነ "ኢስቲዋኡ" የፍጡር አይነት ኢስቲዋእ ስላልሆነ እንዴት የሚለው ጥያቄ እርሱ የሚጠየቅበት አይደለም]።

FOR~HAMZA
            ASEDULLAH

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

05 Oct, 03:20


لله تعالى

الرُّوحُ اسمُ مَلَكٍ مِن الْمَلَائِكة كَبِير الخِلْقَة፦
◥ ኣ·ሩሕ እጅጉን የገዘፈ አፈጣጠር ካላቸው መላኢካዎች ስም መሀከል የአንዱ ነው።

الرُّوحُ هُوَ مَلَكٌ كَبِيرٌ مِنَ بَيْنِ الْمَلَائِكَةِ خِلْقَتُهُ كَبِيرَةٌ جِدًّا، قَالَ تَعَالَى: *﴿يَوْمَ يَقُومُ الرُّوحُ وَالْمَلَائِكَةُ صَفًّا﴾*.
[ኣ·ሩሕ እጅጉን የገዘፈ አፈጣጠር ካላቸው መላኢካዎች መሀከል አንዱ ሲሆን አሏህም እንዲህ አለ፦[በዛህ ኣ·ሩሕ እንዲሁ መላኢካዎች ሰልፍ ይዘው በሚቆሙበት ቀን]።

هَذَا الرُّوحُ الَّذِي هُوَ مَلَكٌ يَقُومُ صَفًّا مِنْ عِظَمِ خِلْقَتِهِ، الْمَلَائِكَةُ تَقِفُ صَفًّا وَهُوَ يَكُونُ فِي صَفٍّ وَحْدَهُ" اهـ.
[ይህ ኣ·ሩሕ የሚሰኘው መላኢካህ ከአፈጣጠሩ ግዝፈት የተነሳ ለብቻው አንድን ሰልፍ ይዞ ይቆማል።ሌሎች መላኢካዎች ደግሞ በሌላ ሰልፍ የሚቆሙ ይሆናል።እርሱ ለብቻው የትንሳኤ ዕለት አንድን ሰልፍ ይዞ ይቆማል ማለት ነው]።

قَالَ النَّسَفِيُّ الْمُفَسِّرُ: "الرُّوحُ مَلَكٌ عَظِيمٌ مَا خَلَقَ اللهُ تَعَالَى بَعْدَ العَرْشِ خَلْقًا أَعْظَمَ مِنْهُ".
አል–ሙፈሲሩ ኣ·ነሰፍይ እንዲህ ይላሉ፦[ኣ·ሩሑ ግዙፍ የሆነ መላኢካህ ሲሆን አሏሁ ተዐላህ ከዓርሽ ቀጥሎ በእርሱ መጠነ ግዝፈት ያለን ሌላን አልፈጠረም]።

FOR~Hamza
  Asedullah

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

04 Oct, 11:45


[ሚዛናዊ መርህ منهج الاعتدال]

​​​​الـنِّـيَّـــة لله تَعَالى
عِـلْـمُ الـدِّيِن حَيَاةُ الإِسْــــلام.

《خطبة الجمعة في مركز الشيخ الهرريّ |أديس أبابا -إثيوبيا بعنوان:(خصال المرأة الصالحة)

بصوت فضيلة الشيخ فتحي عبد الرحمن حفظه الله تعالى وجزاه عنا خير الجزاء

☞የዛሬው የጁሙዐህ ኹጥባ
ከኣ·ሸይኽ ዐብዱሏህ መርከዝ ከአዲስ አበባ ኢትዮጲያ

☞እርዕስ [የመልካም ሴት ስብእናዎች]።

☞ድምፅ፦በኣ·ሸይኽ ፈይሒ ዐብዱራሕማን አሏህ ይጠብቃቸው። ኽይር ጀዛቸውንም አሏህ ይክፈላቸው።

''The Way Of Moderation'' ||

ሐምዛ
   አሰዱሏህ

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

04 Oct, 05:25


๏ከቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁሙዓህ ቀን ነው።๏


يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَاةِ مِن يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ وَذَرُوا الْبَيْعَ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

(ሱረቱ አል- ጁሙዓህ - 9)

【እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው ፡】

  ┈┈••◉❖◉●••

በጁምአ ሱናዎች እንበርታ!

ገላን መታጠብ
ሽቶ መቀባት ለወንድ
ልብስ መቀየር
ጥፍርን ማሳጠር
በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ
ሶለዋት ማብዛት
ሱረቱል ካህፍን መቅራት
ሲዋክ መጠቀም
ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ
ከጁምዐህ ቡሀላ የሱና ሶላት መስገድ
ዱዐህ ማድረግ.

تَعصي الإِلَهَ وَأَنتَ تُظهِرُ حُبَّهُ
هَذا مَحالٌ في القِياسِ بَديعُ
☞ [ውዴታውን እየሞገትክ አሏህን ታምፃለህ
ይህ በሰዎች አካሄድ የማይሆን አዲስ ፈጠራ ነው]።

لَو كانَ حُبُّكَ صادِقاً لَأَطَعتَهُ
إِنَّ المُحِبَّ لِمَن يُحِبُّ مُطيعُ
☞ [ለእርሱ ባለህ ውዴታህ እውነተኛ ብትሆን በታዘዝከው ነበር: ወዳጅ ለወዳጁ ወንጃይ አይደለምና]።
في كُلِّ يَومٍ يَبتَديكَ بِنِعمَةٍ
مِنهُ وَأَنتَ لِشُكرِ ذاكَ مُضيعُ
☞ [እያንዳንዱን ቀን ፀጋን እየለገሰህ ይጀምርልሀል
ነገር ግን አንተ ለዛ ውለታ ምስጋና አጥፊው ነህ]።

@ሓምዛ–ኣሰዱሏህ

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

03 Oct, 17:29


أحبابي

اغتنموا هذه الليلة المباركة فقد قَالَ الشَّافِعِيُّ فِي الْأُمِّ: وَبَلَغَنَا أَنَّهُ كَانَ يُقَالُ: إنَّ الدُّعَاءَ يُسْتَجَابُ فِي خَمْسِ لَيَالٍ: فِي لَيْلَةِ الْجُمُعَةِ، وَلَيْلَةِ الْأَضْحَى، وَلَيْلَةِ الْفِطْرِ، وَأَوَّلِ لَيْلَةٍ فِي رَجَب، وَلَيْلَةِ النِّصْفِ مِنْ شَعْبَانَ.

[ውዶቼ]፦

๏ ይህችን የተባረከች ሌሊት ተጠቀሙባት። አል–ኢማም ኣ·ሻፍዕይ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦[ፀሎት በአምስት ለሊታቶች ተቀባይነት አላት የሚል ደርሶናል፦የጁሙዐህ ሌሊት፣የዒደ ኣ·ል–ኣዱሓ ሌሊት፣የፊጥር ሌሊት፣ የመጀመርያው የረጀብ ወር ሌሊት እንዲሁ የሻዕባን ወር አጋማሽ ሌሊት] ናቸው።

FOR~ምንጭ፦<ኪታብ ኣል–ኡም>

HAMZA~ሓምዛ
   ኣሰዱሏህ

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

02 Oct, 03:16


☞ ምሽቱን በሌላ በኩል ሀዘንን ሰብሮ ልብ የሚገባ ደስታ ነገር ግን ደግሞ የንፁሀኑ ደም አይሁዳዊዋ ሀገር ምን አይነት የሓጢያት ብትሯን በሊባኖስ አልያ በገዛህ ላይ ቀጥሎ ታሳርፋለች የሚለው አልታወቀም።
ደስታውም ከወደ ኢራን ወደ ቴሌ ኣቪቭ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሮኬት ሚሳኤሎችን ምሽቱን ስታስወነጭፍ አድራለች።

💪ድል ለገዛህ ❤️
💪ድል ለሊባኖስ ❤️

ውድቀት ለአይሁድ።
ውድቀት ለአሜሪካ።

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

30 Sep, 18:58


مسألة مهمة؛ إنْ وكلَّكَ بشراءِ شيء وهو ظنَّ أنّ هذا الشيء يُشترى بمائة، فأنتَ بذكائِك بمعرفتِك بالبائِعين اشتريتهُ بثمانين، ليس لك أن تأكلَ العشرين، العشرون له. إذا جئت له وقلتَ له حصلتُهُ بثمانين، فقال لك: هذه هدية مني الزائد هدية، لحلَّ لك. أيضًا بعض الجُهال قد يأكلون الزائِد، يقول: هو أعطاني مائة لأشتري له وأنا بقوتي بمهارتي (هم يقولوا "بشطارتي") اشتريته بثمانين، يأخذ العشرين، حرامٌ عليه،
إذا واحد وكلَّك أن تشتري له لا بُدَّ أنْ تعملَ لمصلحتهِ.

☞ አንገብጋቢ ነጥብ፦

«አንድ ሰው አንድን እቃ እንድትገዛለት ውክልና ከሰጠህ ይህ ውክልና የሰጠህም ሰው ይህን እንድትገዛለት የሰጠህን እቃ ዋጋው ለምሳሌ በ 100 እንደሚገዛ ነው የሚያስበው።አንተ ውክልናውን የወሰድከው ደግሞ በብልጥነትህ ስለ ሻጮች አልያ ስለ እቃው የዋጋ ሁኔታ የበለጠ እውቀት ስላለህ በ 80 ገዛህው።

ሰውዩው በቃ መቶ ሰጥቶ ግዛ ብሎኛልና እኔ ደግሞ በራሴ መንገድ 20 አስቀንሻለውና እርሱን ሳላሳውቅ እወስዳታለው ማለት አልያ 20 ዋን መብላቱ ሓራም ነው።ይህ የቀረው 20 ብር ውክልና የሰጠህ ሰው የራሱ ነው።አንተ ምንም ብታስቀንስም እርሱ ግዛና የቀረውን ለራስህ አላለህም።እንደርሱ ሆነህ እዛ ቦታ ላይ መግዛት ስለሚጠበቅብህ ማለት ነው።አንተ ከዛ ለጥቀህም በ80 ገዛሁት ብለህው እርሱ ደህሞ በቃ 20 ውን በስጦታ መልኩ ሰጥቼሀለው ካለህ እርሱን መብላት ይበቃልህ ነበር።አንዳንዱ መሓይብ ግን እንዲህ ሲል ይሰማል፦" እርሱ 100 ሰጥቶች ግዛ ነው ያለኝ እኔ ደግሞ በብቃቴ አልያ በጥንካርዪ አስቀንሼ 80 አስደረኩት ስለዚህ 20 ውን እኔ እወስደዋለው"። ይላል ይህም ሓጢያት ነው። አይበቃም።አንድ ሰው በአንድ እቃ ዙርያ ከወከለህ ግዴታ ለእርሱ ጥቅም መስራት ነው ያለብህ»።


FOR~HAMZA
...........ASEDULLAH

ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ

30 Sep, 10:06


☞ ጥያቄ፦ወደ አሏህ መቃረብን ሽቼ መልካምን ነገር ለመስራት ስለት ተስዪ ነበር ነገር ግን ስለቴን ከነጭራሹ ረሳሁት ምን ማድረግ አለብኝ?

النذر

ስለት፦

ومَن نذَر شَيئًا تقرُّبًا إلى اللهِ تعالى ثم نَسيَ ما هو ينتَظرُ حتى يتَذكّر.
["ወደ አሏህ ይብልጡኑ ለመቃረብ (ማለትም ደረጃዊ ቅርበት የቦታዊ ቅርበት ሳይሆን ለአሏህ ቦታ አያስፈልገውምና)ይህን ደረጃዊ ቅርበት ፈልጎ ስለት የተሳለ እንደሆነ ከዛም ስለቱን ከረሳ ይህ ሰው ምን እንደተሳለ እስኪያስታውስ
ይጠብቅ።

ዝግጅት፦ሓምዛ
    ኣሰዱሏህ

1,961

subscribers

650

photos

66

videos