የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

@efgbc_ho

ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና፥ ዛሬም ለዘልዓለምም ያው ነው። ዕብ 13:8
Jesus Christ is the same yesterday and today and forever. Heb 13:8

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

21 Jan, 00:22

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ስነመለኮት ሴሚናሪ የሰነ አመራር ትምህርት በዲግሪ መርሀግብር እየሰጠ እንደ ሆነ ይታወቃል። የ2017 ፕሮግራም የሚጀምረው ሕዳር 2 ስለሆነ አዲስ ተመዝግባችሁ መማር የምትፈልጉ ሁሉ  ዶክመንታችሁን በ telegram በመላክና ክፍያ በመፈጸም መመዝገብ ትችላላችሁ። ለተጨማሪ መረጃ በ ስ.ቁ 0968001933 ወይም 0913124075  ደውላችሁ አነጋግሩን።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

21 Jan, 00:22

የወጣት መሪዎች ስልጠና ተከናወነ።
        በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የአምቦ እና አከባቢው ክልል የወጣት መሪዎች ስልጠና ተካሄደ፡፡
     ከጥቅምት 7- 9/ 2017 ዓ.ም ለሶስት ቀናት  በተካሄደው ስልጠና ላይ ከ 70 አጥቢያዎች  የተውጣጡ 70 ሰልጣኞች ተገኝተዋል።
     ስልጠናውን  እና  የቤተ ዕምነቱ የልጆች ወጣቶች ቤተሰብ አገልግሎት ሃላፊ  መጋቢ ኤርሚያስ ገብረ መድኅን እና የክልሉ ፕሬዝደንት መጋቢ ይበልጣል  ስለሺ  ሰጥተዋል።
    ስልጠናው በዋናነት የቤተክርስቲያንን ተልዕኮ ያማከለ የወጣቶች አገልግሎት መገንባት ላይ ያተኮረ ሲሆን የወጣቶች አገልግሎት አብይ ዓላማ  የቤተክርስቲያንን ተልዕኮ በወጣቶች መፈፀም መሆኑን ተገልጿል ።
    ሰልጣኞች የሰለጠኑትን በአጥቢያዎቻቸው እንዲተገብሩ  የአደራ መልዕክት ተላልፏል ፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

21 Jan, 00:21

የመሪዎች ስልጠና ተካሄደ።
    በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያ የደቡብ ኦሞ እና የጋሞ ጎፋ
አካባቢ ክልል ለቤተክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች ስልጠና አካሄደ።
      ስልጠናው የተከናወነው ጥቅምት 7 እና 8 /2/17 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ሲሆን የቤተ እምነቱ  የወንጌል ተልእኮ እና የእረኝነት መምሪያ ዳይሬክተር የሆኑት መጋቢ ታረቀኝ ኡመታ እና የክልሉ ፕሬዝዳንት መጋቢ ሣሙኤል ተገኝ እንዲሁም በክልሉ ውስጥ ካሉ ከ119 አጥቢያዎች የተወጣጡ 120 አገልጋዮች ተገኝተዋል።
       ስልጠናውን  ዘማሪ መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ "ምስባኮቻችን" በሚል ርዕስ ሰጥተዋል።
  የስልጠናው መርሃ ግብር በዋናነት ዓላማው በጋራ  የምናካሄዳቸው መንፈሳዊ ኘሮግራሞች እግዚአብሔርን የሚያከብር ፣ቤተክርስቲያንን የሚያንጽና ሌሎችን የሚባርክ እንዲሆን ታስቦ መሆኑን ታውቋል።
    በስልጠናው የተገኙት መሪዎችና አገልጋዮች ስልጠናው  እጅግ እንደጠቀማቸው፣ መንፈሳዊ መረዳት እንደጨመረላቸው ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸውልናል ።
     ስልጠናው የተዘጋጀው በዋናው ጽ/ቤት እና በክልሉ አማካኝነት መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።