በመጀመሪያው ባለው የ16ኛው ክፍለ ዘመን የሕግ ጥናት በመሰረታዊ የለውጥ ሂደት ውስጥ ነበር። ፍጹማዊ የፈረንሳይ ንጉሳዊ አገዛዝ በፍራንሲስ አንደኛው ስር እያለ አስተዳደራዊ ማዕከሉ እየጨመረ ሲሄድ ለዘመናዊቷ ፈረንሳይ ሕጋዊ የሆነ አመሰራረት እጅግ ጠቃሚ ነበር። የምስረታውን ሂደት ከማፋጠን አንጻር፣ ግቡ ሕጋዊ የሆነ ስርዓት ለመመስረት ሙሉ በሙሉ በፈረንሳይ ለማጽደቅ፣ ይህ የምሁራን ቡድኖችን እርዳታን ፈለገ፣ ማዕከሉም በቦርጀስ እና ኦርላይንስ ዮኒቨርስቲዎች ያደረገ፣ በተግባር ባልታየ ጥናታዊ በሆነ ሁኔታ ላይ በተጠመዱ ምሁራን አማካኝነት አጠቃላይ የሕግ ደንብ በዓለማቀፋዊ መርህ መሰረት ተመሰረተ። ከነዚህም ውስጥ ፈርቀዳጅ ከነበሩት ጉይላውሜ ቡዴ ሁለተኛው ሲሆን፣ ለፈረንሳይ የሚያስፈልገውን የተሳካ እና አትራፊ አዲስ ሕግ ለማግኘት ወደ ሮም ሕግ በቀጥታ መመለስ ያስፈልጋል በማለት ይሞግታል። ከጣሊያን ልማድ ከሆነው የግሪኮ ሮማ የሕግ ጽሑፎችን ማንበብ በመካከለኛው ዘመን ባሉ የሕግ አዋቂዎች የሕግ ማብራሪያ እና የጽሑፍ ስራዎች ብርሀን ውስጥ ስናነጻጽረው፣ ፈረንሳይ የመጀመሪያውን የግሪኮ ሮማ ሕጋዊ ምንጮችን በራሳቸው ቋንቋ በቅደም ተከተል አስፋፍታዋለች።
አንዱ ቀጥተኛው ውጤት የፈረንሳይ ሂውማኒስት ፕሮግራም የውይይት ዘገባዎች በቀጥታ ግልጽ የሆነ ትዕግስት በማጣት በማብራሪያ ጽሑፎች ውስጥ የተካተቱትን ነበር።እንደ አስፈላጊ ጥናታዊ መሳሪያ ሳይታይ፣ ይህም ቀዳሚውን የጽሑፍ ስራ ለማግኘት ትልቅ መሰናክልን ጨመረ። በባርቶለስ እና በአኩርሲየስ የተባሉ ጸሀፊያን በግሪኮ ሮማ የነበሩትን የሕግ ጽሑፎች የተረጎሙበት መንገድ አላስፈላጊ እና የማይገናኝ ነበር። በአንባቢውና በጽሑፉ መካከል የጠሩ ነገሮችን እንደማዛባት አስቀመጡት። እንደ ሂውማኒስት ምሁርነት ማረጋገጫዎች የበለጠ በራስ መተማመን ሲጨምር፣ የአከርሲየስ እና ሌሎችም በጥያቄ ውስጥ ገቡ። ታዋቂው ስፔናዊ ምሁር አንቶኒዮ ኔቢርጃ በአኩርሲየስ የጽሑፍ ማብራሪያዎች ውስጥ ስላያቸው ዝርዝር ዘገባዎች አሳትሟል።
👉የፈረንሳይ ሂውማኒዝም...የቀጠለ👈
ሬቤላይስ የተባለ ጸሐፊም በንቀት የአኩርሲየስ ምልከታ ያልተገባ እንደሆነ ጽፏል።
የዚህ ዕድገት አስፈላጊነት ለተሀድሶ ያደረገው አስተዋጽዖ የግድ ሊታወቅ ያስፈልጋል። በቦርጀስ እና በኦርላይንስ በፈረንሳይ ሕጋዊ የሂውማኒዝም እንቅስቃሴ ጅማሬ ላይ ተማሪ የነበረው የወደፊቱ የቤተክርስቲያን የተሀድሶ መስራች ጆን ካልቪን፣ ምናልባትም በ1528 ዓ.ም. በኦርላይንስ እንደነበር ይገመታል። ካልቪን በኦርላይንስ እና በቦርጀስ የማህበረሰብ ሕግን በማጥናቱ ቀዳሚ የሆነን ግንኙነት ከዋናው የሂውማኒዝም እንቅስቃሴ ባህሪይ ጋር ማድረግ አስችሎታል። ይህ ግንኙነት ቢያንስ ካልቪንን ብቁ ችሎታ ያለው የሕግ አዋቂ እንዲሆን አስችሎታል። ይህም በተለይም የጄኔቫ ሕግ እና አዋጅን በማርቀቅ ሂደት ላይ ረዳት ሆኖ እንዲሰራ ጥሪ ሲደረግለት አስገራሚ የሆኑ ሕጎችን ከራሱ እውቀት በማፍለቅ አርቅቋል። ካልቪን ከዚህ በላይ ብዙ ከፈረንሳይ ሂውማኒዝም የተማራቸው ነገሮች አሉ።
የካልቪን ዋና ዘዴዎች ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ በእድሜው ታላቁ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኝ እና ሰባኪ መባሉ ምናልባት በኦርላይንስ እና ቦርጀስ የሕግ ትምህርትን በከፍተኛ ደረጃ ማጥናቱ ውሸትና አከራካሪ ጉዳይ ነው። ብዙ ነገሮች ካልቪን ከቡዴ ብቁ የሆነ የቋንቋ ምርምር እንደተማረ የሚያመለክት ሲሆን፤ ይህም ከመሰረቱ መልዕክቶችን በቀጥታ ለመረዳት፣ ከስነ ቋንቋ እና ከታሪካዊ ባህሪይ አንጻር አውዳዊ በሆነ መልኩ ለመተርጎምና በነበረበት ዘመን አስፈላጊ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ ነው። ትክክለኛ በሆነ ትጋት ካልቪን መጽሐፍ ቅዱስን ሲገልጥ በተለይም በስብከቱ ዋና ዓላማው የመጽሐፍ ቅዱስን የእውቀት አድማስ ከአድማጮቹ አውድ ጋር ማገናኘት ነበር። የፈረንሳይ ሂውማኒዝም ለካልቪን ብርታትንና ያለፈውን ነገር በመተው የወደፊት በሆነው በ1550ዎቹ በነበረው የጄኔቫ ከተማ ሁኔታ ላይ ጽሑፎችን ለማዘጋጀት የሚጠቅሙ መሳሪያዎችን በመስጠት አስተዋጽኦ እንዲያደርግ አስችሎታል።
👉የእንግሊዝ ሂውማኒዝም👈
በመጀመሪያዎቹ የ16ኛው ከፍለ ዘመን የሂውማኒዝም ዋነኛውና አስፈላጊው ማዕከል የነበረው በእንግሊዝ በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ነው፣ በተጨማሪም በኦክስፎርድና በለንደንም አስፈላጊ የነበረ የማይናቅ አስተዋጽዖ ነበራቸው። ካምብሪጅ የቀድሞ የእንግሊዝ ተሀድሶ ቤት ነበር፣ ማዕከሉም "የነጭ ፈረስ ክበብ" የተባለ ሲሆን(በኋላም ይህ ስሙ ተወግዶ የመሸታ ቡና ቤቱ ተዘግቶ የንግስቶች ኮሌጅ ተባለ)፣ ይህም እንደ ሮበርት ባርነስ ያሉ የማርቲን ሉተር በ1520ዎቹ መጀመሪያ የተጻፉ ጽሑፎችን በማግኘት በጉጉት ያነበቡበት እና ውይይት ያካሄዱበት ነው። ይህ የመሸታ ቡና ቤት በቅርብ ጊዜ የቅጽል ስሙ ትንሿ ጀርመን የሚል ስያሜ ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቅ የነበረ ሲሆን፣ በኋላም በካምብሪጅ አካባቢ የንጉሱ ዋና መንገድ እና የካምብሪጅ ኮሚኒስት ፓርቲ አንደኛው ቤት ሲሆን "ትንሿ ሞስኮው" በሚል ስያሜ በ1930ዎቹ አካባቢ ይጠራ ነበር።