ራስን የመሆን ጥበብ

@beingourself


@Dawitfikadu

ራስን የመሆን ጥበብ

10 Oct, 07:32


🤩ኑ!..... አብረን እንስራ! 🤩

ወጣቶች በእርግጠኝነት ይህንን የሰማችሁ አይመስለኝም።
የትኛውም ሀገር ላይ ሆናችሁ ስራችሁን እየሰራችሁ እንዲሁም ትምህርታችሁንም እየተማራችሁ አሪፍ ገንዘብ የሚከፍላችሁ ድርጅት መጥቷል። አልሰማችሁም አይደል?
ይህንን ታላቅ የምስራች ለጓደኞቻችሁ እየላካችሁ ማንበብ ያለባችሁ፤ በደንብ ጊዜ ሰጥተን ከሰራነው በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ልናተርፍበት የምንችልበት ስራ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች የ (Online) ልትሰሯቸው ከምትችሏቸው ስራዎች መካከል ምንም ዓይነት ካፒታል አይፈልግም።
እከስራለሁ ብሎ ማሰብ ደግሞ በጭራሽ የማይታሰብ ነው። ከኢትዮጵያ ውጭ የትኛውም ክፍለ ዓለማት ለምትኖሩ የምሰራውን ገንዘብ በምን እቀበላለሁ ለሚለው ደግሞ ኢትዮጵያ ባሉ በሁሉም ባንኮች መቀበል ይቻላል።

   ✍️  ምንም አይነት የስራ ልምድ አይጠይቅም።

  CONTACT ME t.me/Dawit_Fikadu

ስ.ቁ 📞  +251906067696
ይደውሉልን
ዛሬውኑ  ይመዝገቡ!

ራስን የመሆን ጥበብ

04 Sep, 07:49


እንዴት ነህ?

ሰዎች “እንዴት ነህ?” ብለው ሲጠይቁህ፣ የምትመልሰው መልስ ምን ያክል በሕይወትህ ላይ ተጽዕኖ እንዳለው አትዘንጋ። ከዛሬ ጀምሮ፣ ሰዎች “እንዴት ነህ?” ብለው ሲጠይቁህ፣ በመጀመሪያ በእምነትህ መሰረት፣ “እግዚአብሔር ይመስገን” ወይም “አልሃምዱሊላህ” በማለት ፈጣሪህን አመስግን። ከዚያ ቀጥሎ ግን “ዛሬ ይደብራል፤ ቀኑ ይከብዳል…” የሚሉ ቃላትን በምንም ተዓምር ከአንደበትህ አታውጣ። ፈጣሪህን ካመሰገንክ በኋላ፣ ልትላቸው የሚገቡህ ቃላት “እኔ፣ ሕይወቴ፣ ቤተሰቤ፣ ቀኔ፣ ስራዬ፣ አገሬና ሁሉም ነገር ድንቅ ነው!” የሚል ብቻ መሆን አለበት። አሁን ድንቅ የሆኑ ቃላትን ከዘራህ፣ ኋላ ድንቅ የሆኑ ውጤቶችን ታጭዳለህ፤ ይህ የተፈጥሮ ህግ ነው።

“እንዴት ነህ?” ተብለህ ስትጠየቅ፣ ከተለመዱና ተራ ከሆኑ አንዳንድ መልሶች መቆጠብም አለብህ። አስቀድመን፣ እጅግ በጣም መጥፎ ከሚባል ደረጃ አንስቶ፣ እፁብ ድንቅ የሚለው ደረጃ ድረስ በጣም ብዙ ደረጃዎች እንዳሉ ተመልክተን ነበር። ለምሳሌ “እንዴት ነህ?” ተብለህ ስትጠየቅ፣ “ዛሬ ደብሮኛል” ብለህ ከመለስክ፣ በየትኛው ደረጃ እንዳለህ መገመቱ አይከብድም። “ድንቅ ነኝ” ወይም ተመሳሳይ ድንቅ የሆኑ መልሶችን ስትመልስም ድንቅ በሆነ ደረጃ ላይ እንዳለህ ግልጽ ነው።
@Dawit_Fikadu

ራስን የመሆን ጥበብ

31 Aug, 08:58


ተስፋ እኛ እስካለን አለ!

ብዙ ግዜ በህይወታችን ላይ ተስፋ አድርገን ስንጠብቃቸው የነበሩ የህይወት ታሪካችንን ይቀይሩልናል ብለን ያሰብናቸው ስንጠብቃቸው የነበሩ ነገር ግን ያልተሳኩልን ነገሮች ይኖራሉ በህይወታችን ላይ በነሱ ተስፋ ቆርጠን መቆም ከጀመርን እና አዲስ ህይወት እንዳለ ካልገባን ግን የባሰ መቆም እንጀምራለን ይባስ እንወድቃለን ነገር ግን፤ የሰው ልጅ በህይወት እስካለ ድረስ ሁሌም መንገድ አለ ! ተስፋ እኛ እስካልሞትን አይሞትም!
@Dawit_Fikadu
መልካም ቀን!

ራስን የመሆን ጥበብ

29 Aug, 07:46


🤩ኑ!..... አብረን እንስራ! 🤩

ወጣቶች በእርግጠኝነት ይህንን የሰማችሁ አይመስለኝም።
የትኛውም ሀገር ላይ ሆናችሁ ስራችሁን እየሰራችሁ እንዲሁም ትምህርታችሁንም እየተማራችሁ አሪፍ ገንዘብ የሚከፍላችሁ ድርጅት መጥቷል። አልሰማችሁም አይደል?
ይህንን ታላቅ የምስራች ለጓደኞቻችሁ እየላካችሁ ማንበብ ያለባችሁ፤ በደንብ ጊዜ ሰጥተን ከሰራነው በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ልናተርፍበት የምንችልበት ስራ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች የ (Online) ልትሰሯቸው ከምትችሏቸው ስራዎች መካከል ምንም ዓይነት ካፒታል አይፈልግም።
እከስራለሁ ብሎ ማሰብ ደግሞ በጭራሽ የማይታሰብ ነው። ከኢትዮጵያ ውጭ የትኛውም ክፍለ ዓለማት ለምትኖሩ የምሰራውን ገንዘብ በምን እቀበላለሁ ለሚለው ደግሞ ኢትዮጵያ ባሉ በሁሉም ባንኮች መቀበል ይቻላል።

   ✍️  ምንም አይነት የስራ ልምድ አይጠይቅም።

  CONTACT ME t.me/Dawit_Fikadu

ስ.ቁ 📞  +251906067696
ይደውሉልን
ዛሬውኑ  ይመዝገቡ!

ራስን የመሆን ጥበብ

27 Aug, 04:11


''በህይወት እስካለህ ልትሳሳት፤ ልትወድቅ ትቸላለህ።ሰዎች ላይቀበሉህም ይችላሉ።ወይም ሀሳብህን ላይረዱህና ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ። በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ። ሰዎች ሊጠሉህ፣ ሊያሙህ ወይም ስም ሊያወጡልህ፣ አሊያም ሊስቁብህ ይችላሉ። በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው።መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል።አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል።ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል።ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል ስለዚህ እራስን ሁን።''
@Dawit_Fikadu
🤩መልካም ቀን🤩

ራስን የመሆን ጥበብ

25 Aug, 09:04


👑ስኬትን ስትፈልግ ዛሬህን ገምግመው የዛሬ ውሎህ ነገህን ይውስነዋል ዛሬ እደፈለክ ተኝተህ እደፈለክ ተዝናንተህ ከማይጠቅሙህ ሰዎች ጋር እየዋልክ የማይጠቅሚህን መረጃ እየሰማህ እደፈለክ ተቀምጠህ ስኬትን ከተመኘህ ለውጥን ከተመኘህ እመነኝ ከምኞት አይዘልም ምኞት ሁኖ ይቀራል።
ነገር ግን!
ዛሬ መዝናናት እያማረህ ጠክረህ ከሰራህ መጫወት እየፈለክ ጠክረህ ካነበብክ ማረፍ እየፈለክ ጠክረህ የምትፈልገውን ነገር ካጠናህ ዛሬ ግዜ ሰተህ በራስህ ላይ በመስራት እና መልካም የሆኑ ሀሳቦችን ካሰብክ ቀንህን ካሸነፍክ ስኬታማ የማትሆንበት ምንም ምክኒያት የለም እና ስኬታማ ትሆናለህ።
@Dawit_Fikadu
መልካም ቀን!

ራስን የመሆን ጥበብ

01 Aug, 13:24


ጥያቄዎ:-

1️⃣.ስራ የለኝም እና ምን ሠርቼ የተሻለ ገቢ ላግኝ? ከሆነ

2️⃣. ስራ አለኝ ግን በማገኘው ደሞዝ ብቻ ኑሮ ውድነቱን መቋቋም አልቻልኩም እና
እንዴት ተጨማሪ ገቢ ላግኝ? ከሆነ

3️⃣.ተማሪ ነኝ ግን ከትምህርቴ ጎን ለጎን ቢዝነስ በመስራት ለነገዬ የሚሆን ገቢ እንዴት ማግኘት ችላለው? ከሆነ

ለዚህ ሁሉ መልስ እኛጋ ያገኛሉ።

ቢሮአችን መታቹህ ሙሉ መረጃውን ለመውሰድ  ፍቃደኛ ከሆናቹህ!

📛 ስም
📞 ስልክ
📍 አድራሻ ( ከተማ) ይላኩልን!
ክፍላገር ለሆናቹም በ online ይህን ድንቅ እድል ማግኘት ይችላሉ
👇👇👇

ለበለጠ መረጃ
0906067696
@Dawit_Fikadu
በዚህ ያገኙናል

ራስን የመሆን ጥበብ

06 Jun, 09:01


በጣም አብዛኛው ሠው አያሸንፍም ።ምክንያቱም የሚያተኩረው ከራሱ ይልቅ የሌሎችን ግብ ነውና ።

"ዝምብለህ የራስህን ነሮ ኑር::" የሚል አንድ አባባል /ጥቅስ አስታውሳለሁ ።

ብዙዎቻችን ስለራሳችን ያለን ግንዛቤ ወይ "ዝቅ" ያለ ነው ወይ "ከፍ "ያለ ነው ።ሁለቱም ልክ አይደለም ።

ሠው የራሱ ልክ እለው።
ልኩ ደግሞ ሀሳቡን: ስሜቱን: ተግባሩን: ልማዱን :ባህሪውን :መገለጫውን: እና እጣፈንታውን መወሰን በመቻሉ ነው።

አንተ/ቺ የፈቃድህ/ሽ ውጤት ነህ /ሽ::
ስለሆነም "ሆን"ብለን ፈቅደን የራሳችንን መስመር ጠብቀን እንጓዝ እንደርሳለን ።

የሚያደርስ መንገድ መጀመር: የሚያስቀጥል ስንቅ /እውቀት :አላማ :ብቃት እና ንቃት ካለን ፈጣሪም ከጎናችን ነው ።
ደስተኛና ባለውለታ ነኝ ።👍💐👌🌏

ራስን የመሆን ጥበብ

21 May, 08:31


Live stream finished (1 minute)

ራስን የመሆን ጥበብ

21 May, 08:29


Live stream started

ራስን የመሆን ጥበብ

15 May, 04:24


እውነተኛ ሕይወት ሲመዘን!

አንድ አሜሪካዊ ነጋዴ በአንዲት የሜክሲኮ የወደብ ከተማ ዳር ቆሞ ሳለ አንዲት ትንሽ ጀልባ አንድ አሳ አጥማጅ ይዛ ወደ ወደቡ ተጠጋች፡፡ በጀልባ ውስጥ አንድ የሜክሲኮ ተወላጅ አሳ አጥማጅ ያጠመዳቸው ቁጥራቸው ከመጠን ያለፈ ትናንሽ አሳዎች አሉ፡፡

አሜሪካዊው ሜክሲኮአዊውን ስለአሳ ማጥመድ ችሎታው ካደነቀው በኋላ አንድን ጥያቄ አቀረበለት፣ “እነዚህን አሳዎች ለማጥመድ ስንት ጊዜ ፈጀብህ?”

“በጣም አጭር ጊዜ” ብሎ መለሰ፣ ሜክሲኮአዊው፡፡

አሜሪካዊው፣ “ይህንን ያህል አሳ በአጭር ጊዜ ማጥመድ ከቻልክ ለምን ቀኑን ሙሉ ውለህ ብዙ አሳ ለማጥመድ አትሞክርም” ብሎ ጠየቀው፡፡

ሜክሲኮአዊው፣ “አሁን በምሰራበት ሁኔታ ለቤተሰቤ በቂ አቅርቦትን ይዤ እገባለሁ” ብሎ መለሰ፡፡

አሜሪካዊው ጥያቄውን በመቀጠል፣ “በቀረህ ጊዜ ምን ታደርጋለህ?” አለው፡፡

ሜክሲኮአዊው ገበሬ፣ “ጠዋት በቂ እረፍት እወስዳለሁ፣ በቂ አሳ ካጠመድኩ በኋላ ልጆቼ ከትምህርት ቤት ሲመለሱ ከእነሱ ጋር እጫወታለሁ፣ ከዚያም ከባለቤቴ ከማሪያ ጋር ጣፋጭና አጭር የቀን እንቅልፍ እንወስዳለን፣ ከዚያም ወደ ከተማ ወጣ እልና ከጓደኞቼ ጋር ሻይ እየጠጣን ጊታሬን መታ መታ አደርጋለሁ፤ ቀኔ በእነዚህ ሁኔታዎች ሙሉ ነው”፡፡

አሜሪካዊው በመገረምና በማሾፍ፣ “እኔ የታዋቂው የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ ተመራቂ ነኝ፡፡ ልምከርህ! ከጠዋት እስከማታ አሳ ማጥመድ አለብህ፡፡ ከዚያም ተለቅ ያለ ጀልባ መግዛት ትችላለህ፡፡ ከዚያ በአሳ ጠመዳ የምታሳልፈውን ጊዜህን ትንሽ ጨመር በማድረግ በርካታ ጀልባዎችን ትገዛለህ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ብዙ ጀልባዎች ይኖሩሃል፡፡ ከዚያም ዋና አከፋፋይ መሆን ትጀምርና ለአሳ ጠመዳ በምትወስደው ጊዜህ ላይ ጥቂት ጨመር በማድረግ የራስህን ፋብሪካ ትከፍታለህ፡፡ ከዚያም ከዚህች መንደር ትወጣና ወደ ሜክሲኮ ዋና ከተማ ትገባለህ፣ ከዚያ ወደ ሎስ አንጀለስ፣ ቀስ በቀስም የአለም የገበያ ማእከል ወደሆነችው ወደ ኒውዮርክ በመግባት ታላቅ ሰውና ሚሊየነር ትሆናለህ፡፡”

ሜክሲኮአዊው በመገረም፣ “ይህ የምትለው ጉዳይ ስንት ጊዜ ይፈጃል?” አለው፡፡

አሜሪካዊውም፣ “ከ20 እስከ 25 ዓመታት ይፈጃል” አለው፡፡

ሜክሲኮአዊውም መልሶ፣ “ከ25 ዓመታት በኋላ እዚያ ደረጃ ከደረስኩ በኋላስ?” አለው በፍጥነት፡፡

አሜሪካዊው በመሳቅ፣ “ያን ጊዜማ የሚያጓጓ ነገር ውስጥ ትገባለህ፡፡ ትክክለኛውን ጊዜ ጠብቀህ ይህንን የገነባኸውን ንግድ ለሕዝብ በማቅረብ አክሲዮን ትሸጥና ብዙ ቢልየን ብር በማግኘት እጅግ ባለጠጋ ትሆናለህ፡፡”

አሁንም ሜክሲኮአዊው መልሶ፣ “በቢልየን የሚቆጠር ብር ካገኘሁ በኋላስ” አለው፡፡

“ከዚያማ ጡረታ ትወጣና ወደነበርክበት የባህር ወደብ ከተማ ትመለሳለህ፡፡ አሁን እንደምታደርገው ጠዋት በቂ እረፍት ትወስዳለህ፣ በቂ አሳ ካጠመድ በኋላ ከልጅ ልጆችህ ጋር ትጫወታለህ፣ ከዚያም ከባለቤትህ ከማሪያ ጋር ጣፋጭና አጭር የቀን እንቅልፍ ትወስዳለህ፣ ከዚያም ወደ ከተማ ወጣ ትልና ከጓደኞች ጋር ሻይ እየጠጣህ ጊታርህን መታ መታ ታደርጋለህ”፡፡

ሜክሲኮአዊው ተገረመ፡፡ በሃሳቡ፣ “አሁን የምኖረውን የተረጋጋ የሕይወት ሁኔታ ከ25 ዓመታት ልፋት በኋላ ለማግኘት ምን አስሮጠኝ” ብሎ በማሰብና በአሜሪካዊው ሃሳብ ስቆ መንገዱን ቀጠለ፡፡

1. ራሳችንን መመዘን ያለብን በሕይወት ዘመናችን ውስጥ ባሉት ዓመታት ሳይሆን በዓመታቶቻችን ውስጥ ባለው ጣፋጭ ሕይወት ነው፡፡

2. ስኬታችን መመዘን ያለብን በገነባነው ቤት ግዝፈት ሳይሆን በቤቱ ውስጥ በሚኖረው በፍቅር የተገነባ ቤተሰብ ነው፡፡

3. አቅጣጫችንን መመዘን ያለብን እኛ በነዳነው መኪና አይነት ሳይሆን እኛን በነዳን ራእይ ምንነት ነው፡፡

ስራ፣ ገንዘብ፣ ታዋቂነት፣ ውበት፣ ስልጣን፣ እውቀትና የመሳሰሉት ቁሳቁስ-ነክ ነገሮች ሰላምና ፍቅር የሞላበትን ቤተሰባዊ ሕይወት እንድንኖር ካላደረጉን ከንቱ ናቸው፡፡

ራስን የመሆን ጥበብ

13 May, 17:36


#በራስህ_ላይ_አተኩር‼️

ስለሰዎች ጤና-ቢስ ወሬን ማራባት የዝቅተኝነት ስሜት መገለጫ ነው።
የዚህ በሽታ መነሻ እኛ የምንከበረው እና የምንተልቀው ሌላውን ስንጥል እና ስናጣጥል ስለሚመስለን ነው።

የእኛ ሁኔታ የሚደምቀው የሌላውን ሰው ስም ስናጠፋ ብቻ የሚመስለን ብዙዎች ነን፡፡ ይህ ስህተት የሚመጣው ደግሞ በራሳችን መቆምና ማደግ እንደማንችልና የተበለጥን እንደሆንን ስናስብ ነው፡፡

ስለዚህ ወደፊት ከመራመድ ይልቅ ሌላውን ለማደናቀፍ፣ ለማደግ ከመስራት ይልቅ ሌላውን ለማድቀቅ የሚታትር እጅግ ብዙ ሰው ነው፡፡

በራሱ የሚተማመን ሰው የሰውን ነገር በማውራትና ሰውን በማሳነስ እርሱ የሚተልቅ ስለማይመስለው የራሱ ስራ ላይ የሚያተኩር ሰው ነው፡፡

በራስህ ላይ አተኩር!! 🙏

ራስን የመሆን ጥበብ

18 Apr, 15:28


የመጀመር ህግ!

1) ሁሉንም ነገር ሳይሆን በአንድ ነገር መጀመር፦ አንድ ፈገግታ ዘላቂ ጓደኝነት ሊጀምር ይችላል፣ አንድ ሻማ ጨለማን ያጠፋል፣ አንድ ቃል፣ አንድ እድል፣ አንድ መምህር፣ አንድ ብእር ... አንድ መጽሐፍ ዓለምን ሊለውጡ ይችላሉ። ሁሉንም ሳይሆን አንዱን ነገር እንጀምር!

2) ከሌሎቹ የበለጠ ብልህ መሆን አይጠበቅብንም፦ ለመጀመር ከሌሎቹ የበለጠ ዲሲፕሊን እንጂ አውቀት አያስፈልገንም!

3) እራስን ማሸነፍ፦ በቀን ተቀን ሰርክ ህይወታችን ውስጥ ያገኘነው ስኬት ወይም ውድቀት በሌሎች ሰዎች ምክንያት ሳይሆን በራሳችን ተነሳሽነት ወይም ቸልተኝነት ነው። በህይወት ትልቁ ስኬት ደግሞ እራስን ማሸነፍ ነው። አሸናፊዎች በማሸነፍ ላይ ያተኩራሉ፣ ተሸናፊዎች ደግሞ በአሸናፊዎች ላይ ያተኩራሉ።

4) እይታችን አለምን የምንረዳበትን መንገድ ይቀይራል፦ ነገሮችን የምናይበት መንገድ ሲቀየር...ለነገሮች የሚኖረን አረዳድ፣ ተነሳሽነት እና የመፈፀም አቅማችን ይለወጣል። በልባችን ውስጥ የምንሸከመው አለም በነባራዊ ሁኔታችን እሱ እራሱ አለማችን ይሆናል።

5) ሀሉም የሆነው በሂደት ነው፦ እያንዳንዱ አስተማሪ በአንድ ወቅት ተማሪ ነበር። እያንዳንዱ አሸናፊ በአንድ ወቅት ተሸናፊ ነበር። እያንዳንዱ ባለሙያ በአንድ ወቅት ጀማሪ ነበር። በየቀኑ የምንወስዳቸው ትናንሽ እርምጃዎች ወደ ስኬታማነት በሂደት ይመሩናል።

6) ፅናት፦ ስኬታማነታችን የሚረጋገጠው በተሻለ ተሰጥኦ ብቻ ሳይሆን በፅናት በመበርታታችንም ጭምር ነው። ወንዝ አለቱን የሚሰነጥቀው በኃይሉ ሳይሆን በፅናት ነው። ያሰብናቸውን ደግሞ በውጤት የምናዬው.. ፍርሃቶቻችንን በመቋቋም እርምጃውን በመውሰድ፣ በመቀጠል እና በመጽናት ነው።

7) ትኩረት፦ ጭንቀት የሚመጣው ችላ ልንላቸው የማይገቡ ነገሮችን ችላ በማለታችን ነው። በትንሹ የጀመርነው በትኩረታችን ትልቅ ይሆናል...'የአንድ ሺህ ማይል ጉዞ በአንድ እርምጃ ይጀምራል!' ተነሳሽነት ማሰብ ብቻ ሳይሆን ድርጊትን ይከተላል።

8) መሻሻል፦ ጊዜ ከሰጡት እንቁላል በግሩ ይሄዳል። መውጣታችንን ከቀጠልን በሂደት የተራራው ጫፍ ላይ መድረስ እንችላለን። ያ ደግሞ የሚሆነው ከትላንቱ ተሽሎ በመገኘት ነው። በማሻሻል ወደ ስኬት ከፍታ መውጣት እንችላለን።

9) እራስን መለወጥ፦ በጉዞአችን ምንም ያህል ጊዜ ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ብንጓዝም ሁሌም መዞር እንችላለን። ሁኔታዎችን መለወጥ ባንችልም እራሳችንን መቀየር ግን ይገባናል። ብልህነት ከለውጥ ጋር መላመድ መቻል ነው።

10) ከመጸጸት ይልቅ ትምህርት መውሰድ፦ በህይወት ውስጥ ትልቁ አደጋ መሳሳት ወይም መውደቅ ሳይሆን፣ ያለንን አቅም እና የገኘነውን እድል አለመጠቀም ነው። ኖረነው የማናውቀውን ህይወት ከፈለግን ፈፅሞ አድርገነው የማናውቀውን ማድረግ አለብን።

ራስን የመሆን ጥበብ

17 Apr, 05:45


🙏አሜን በሉ...

ህልሞቻችን ከፍርሀቶቻችን በላይ ግዙፍ ይሁኑ፤
ተግባራችን ከቃላቶቻችን በላይ ይናገሩ፤
ሕይወታችን ካተናገርነው በላይ ስለኛ ይስበክ…

ስኬታችን ጫጫታችን ይሁን!

ራስን የመሆን ጥበብ

17 Apr, 05:01


👉 በህይወትህ ሊጠቅሙህ የሚችሉ ነገሮችን ብቻ አንብብ፡፡ ንባብን በቻልከዉ ቦታና ጊዜ ልማድ በማድረግ አእምሮህን መግበዉ፡፡

👉 ካንተ ከተሻሉ ሰዎች ጋር አብረህ አሳልፍ፤ አስታዉስ! የአእምሮህ ብስለት የሚለካዉ አብረህ ብዙ ጊዜ ከምታሳልፋቸዉ አምስት ሰዎች የአስተሳሰብ ዉጤት ተደምሮ ነዉ።

👉 የምትወደዉን ስራ ስራ። ሁሌም ለማሻሻል ጣር፤ ጎበዝ በሆንክበት ሙያ ከማንም የተሻልክ ሆነህ እንድትገኝ በየቀኑ አዳብረዉ።

👉 አዳዲስ ክህሎቶችን ለመማር እራስህን አዘጋጅ፤ ዉስጥህን ደስ ሊያሰኝ የሚችል ጊዜ ማሳለፊያ ወይንም ትርፍ ሙያ ለመማር ፍቃደኛ ሁን።

👉 ከሰዎች ጋር ያለህን ግንኙነት አዳብር፤ አዳዲስ ሰዎችን ለማወቅ ፈቃደኛ ሆነህ የህይወት ልምድ ተለዋወጥ።

👉 ለራስህ ህይወት ሃላፊነት ውሰድ! የምትነሳው በእራስህ ነው ፤ የምትወድቀው በእራስህ ነው ፤ የምታድገው በእራስህ ነው ፤ የኋሊት የምትጓዘው በእራስህ ነው።
ለውድቀትህ የሚጠየቅ ሌላ አካል የለም። የትም ብትሆን ፣ ምንም ብትሰራ ያንተ ህይወት ሃላፊነት የእራስህ ብቻ ነው ። ላለማደግህ ፣ ላለመቀየርህ ፣ ላለማወቅህ ...ካንተ ውጪ ሌላ ተጠያቂ አካል የለም።

👉 በእራስህ ታገል ፤ በእራስህ ተጣጣር ፤ ተፋለም ። በእራስህ ተማመን ፤ የሚመጣውን ተቀበል ፤ ያለፈው አልፏልና መጪውን ለማስተካከል ዛሬን በሚገባ ኑር። ቀጣዩን የህይወት ምዕራፍህን አስተካክለህ ፃፈው ፤ እርሱንም እመነው ፤ በነፃነት ፣ በልበሙሉነትም ተግብረው።

👉 በልዩነት አስብ! በተሻለ መንገድ አስብ ፤ የተሻለ ሃሳብ ሲኖርህ ብቻ ተመራጭ ትሆናለህ። በተለየ መንገድ አልም፣ በተለየ ሁኔታ ማለም ስትጀምር ብቻ የተለየ ነገር መፍጠር ትችላለህ ።ያለመከውን በተሻለ መንገድ አድርገው።

👉 በአምላክህ ተማመን! ከፈጣሪህ ጋር የማትችለው ፣ የማታልፈው ፣ የማትቋቋመው ምድራዊ ፈተና ፣ የማታሳካው ፣ የማታገኘው ፣ የማትኖረው ህልም የለም።

👉 ትኩረትህን ሙሉ ለሙሉ መድረስ የምትፈልግበት፣ መገኘት የምትመኘው ቦታ ላይ አድርገው ምንም ሳትሰስት የሚፈለግብህን ሙሉ ለሙሉ አድርግ ወደ ሌላ ቦታ በፍፁም እንዳታይ። የምትፈልገውን እስክታሳካ አትተኛ።

👉 ፉክክርህን ከሌሎች ጋር ሳይሆን ከትላንቱ ማንነትህ ጋር አድርግ!

👉 ሂደት በሚጠይቅ የረጅም ጊዜ ለውጥ ማመን አለብህ። እውነተኛ እርካታ እና ደስታ ያለው በመልፋትና በፅናት በሚገኝ ስኬት ውስጥ ነው። አቋራጭና ጥድፊያ የበዛበት ሰላም የሚነሳውን ህይወት ለሰነፎች ተውላቸው፤ የተሻለ ሰው የሚያደርግህ፣ የሚያስከብርህ የማይቆም ጥረትህ ነው!

👉 አስተውል! ዛሬህን ልክ እንደትላንትናህ ካሳለፈከው... የሚለወጡት አንተ ልትለውጣቸው የማትችላቸው ነገሮች ብቻ ናቸው!

👉 አስተውል! ባንተ ቁጥጥር ስር ያሉትን እውቀትህን፣ ልምድህን፣ የማኅበራዊ ህይወት ክህሎትህን፣ የገንዘብ ምንጭህን፣ የቤተሰብህን ሠላምና ደህንነት... የመሳሰሉትን ነገሮች ለመለወጥ አንዲት እንኳን እርምጃ የማትራመድ ከሆነ... መልክህ የዛሬ፣ ማንነትህ ግን የትላንት ሆኖ ነው የምትኖረው!

👉 ክቡርና ድንቅ አድርጎ የፈጠረህ አምላክም የልብህን መሻት አይቶ ከጎንህ እንደሚቆም እመን። የምትፈልገውን ጠይቀው፣ ላደረገልህ ነገር ሁሉ አመስግነው!

👉 ማደግህን አታቁም! አጋጣሚዎችን መፍጠር ፣ የተለያዩ አማራጮችን መሞከር ፣ እራስን ማብቃት ፣ እራስን ማሳደግ ፣ ከፍ ማለት የየለት ተግባሩ የሆነ ሰው ሁሌም እድገቱ ይቀጥላል ፤ ነገዎቹ በሙሉ ከዛሬ የተሻሉ ይሆናሉ።

👉 ተደላድሎ የተቀመጠን ማንም አይረዳውም ፤ ተመቻችቶ የተኛውን ማንም አይቀሰቅሰውም ፤ እንዳልደላህ በመልፋት አሳይ ፤ እንዳልተመቸህም በመንቃት አሳይ የሚያግዝህ የሚረዳህም ፈጣሪ የእራሱን ድርሻ እንዲወጣ አግዘው!!!

ፅሁፉን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #share ማድረግን አትርሱ 🙏🙏🙏

ራስን የመሆን ጥበብ

17 Apr, 03:59


https://t.me/BTC_Miner_ba_bot?start=1476161161

ራስን የመሆን ጥበብ

15 Apr, 14:36


አንድ የተቀዳደደ ልብስ የለበሰ ምስኪን የኔቢጤ ደሃ መሳይ ሰው ወደ ባንክ ጎራ ይላል። የያዘውን የባንክ ደብተርም ለአንድ የባንኩ ገንዘብ ከፋይ ይሰጥና “5,000 ብር ማውጣት እፈልጋለሁ” ይለዋል፡፡

የባንኩ ሰራተኛም ይህን ሰው “ከ 10,000 ብር በታች የሆነ ገንዘብ ለማውጣት እባክዎን ኤቲኤም ይጠቀሙ” ይለዋል ፡፡

ሰውየውም “ለምን?” ሲል ጠየቀ ፡፡ ገንዘብ ከፋዩም በቁጣና በንቀት “ይህ የባንካችን ህግ ነው፡፡ ሌላ ጉዳይ ከሌለህ እባክህ ውጣ። ከኋላህ ወረፋ የሚጠብቁ በርካታ ሰዎች አሉ፡፡ ” ብሎ የባንክ ደብተሩን ሳይመለከት ለሰውዬው መለሰ፡፡

ሰውዬው ግን በትህትና የባንክ ደብተሩን ለገንዘብ ከፋዩ እየሰጠ “እባክህ በአካውንቴ ውስጥ ያለኝን ገንዘብ በሙሉ እንድወስድ እርዳኝ” አለው፡፡

በዚህ ወቅት ገንዘብ ከፋዩ የአካውንት ቁጥሩን በማንበብ የሰውዬውን ቀሪ ሂሳብ ሲፈትሽ እጅግ ተገረመ ፡፡ ሰውዬውን ባሳየው ያልተገባ ባህሪ ተፀፅቶ እንዲህ ሲል መለሰ:-

“ይቅርታ አድርጉልኝ ጌታዬ በሂሳብዎ ውስጥ 3.5 ቢሊዮን ብር አለዎት እናም ባንኩ በአሁኑ ወቅት ያን ያህል ገንዘብ የለውም። ቀጠሮ መያዝ እና ነገ እንደገና መምጣት ይችላሉ?

ሰውዬውም “አሁን ምን ያህል ማውጣት እችላለሁ?” ሲል ጠየቀ።

ገንዘብ ከፋዩም “ማንኛውም መጠን እስከ 300,000 ብር ድረስ” አለው።

ይህ ሰው ከዛም 300,000 ሂሳቡን ከራሱ ሂሳብ ማውጣት እንደሚፈልግ ለገንዘብ ከፋዩ ነገረው።

ከፋዩም በፍጥነት ይህን አደረገ እናም ለዚህ ምስኪን ደሃ መሳይ ግን ባለሃብት ሰው በአክብሮት ሰጠው።

ሰውዬውም 5,000 በቦርሳው ውስጥ አስቀመጠና የባንኩን ሰራተኛ ቀሪውን 295,000 ብር ወደ አካውንቱ እንዲያስገባለት ጠየቀ ፡፡

ገንዘብ ከፋዩም ይህ እንግዳ ሰው ባሳየው ያልተገባ መስተንግዶ እንደተደናገጠ የተባለውን አደረገ።

ከዚህ ታሪክ ምን መማር እንችላለን ሃሳባችሁን comment በማድረግ አጋሩን።

ራስን የመሆን ጥበብ

10 Apr, 14:03


ጥያቄዎ:-

1.ስራ የለኝም እና ምን ሠርቼ የተሻለ ገቢ ላግኝ? ከሆነ

2. ስራ አለኝ ግን በማገኘው ደሞዝ ብቻ ኑሮ ውድነቱን መቋቋም አልቻልኩም እና
እንዴት ተጨማሪ ገቢ ላግኝ? ከሆነ

3.ተማሪ ነኝ ግን ከትምህርቴ ጎን ለጎን ቢዝነስ በመስራት ለነገዬ የሚሆን ገቢ እንዴት ማግኘት ችላለው? ከሆነ

ለዚህ ሁሉ መልስ እኛጋ ያገኛሉ።

ቢሮአችን መታቹህ ሙሉ መረጃውን ለመውሰድ  ፍቃደኛ ከሆናቹህ!

👉ሰም
👉ሰልክ
👉አድራሻ( ከተማ) ይላኩልን!
ክፍላገር ለሆናቹም በ online ይህን ድንቅ እድል ማግኘት ይችላሉ
👇👇👇

ለበለጠ መረጃ
0903196825
በዚህ ያገኙናል

ራስን የመሆን ጥበብ

07 Apr, 07:46


1. ‹‹”ዋጋ” የምትከፍለው ነው፤ “እሴት” ደግሞ የምታገኘው ነው፡፡ ("Price is what you pay. Value is what you get.")

2. ‹‹የዘጠኝ ወር እርጉዝ በማግባት በአንድ ወር የራስህን ልጅ ልትወልድ አትችልም››

3. ‹‹ዛሬ ዛፍ ጥላ ስር የምንቀመጠው የሆነ ጊዜ ላይ የሆነ ሰው ዛፉን ስለተከለው ነው፡፡››

4. ‹‹ዝናህን ለመገንባት ሃያ ዓመት ይወስድብሃል፡፡ ዝናህን ለማበላሸት ግን ሃያ ደቂቃ በቂህ ነው፡፡ ይሄን ጉዳይ ካሰብክ ነገሮችን በተለያየ መንገድ ታከናውናቸዋለህ፡፡››

5. ‹‹ባልገባህ ቢዝነስ ላይ ኢንቨስት አታድርግ››

6. ‹‹ስጋት ወይም ፈተና የሚመጣው የምትሰራውን ባለማወቅ ነው፡፡››

7. ‹‹በአንድ ገቢ ብቻ ጥገኛ አትሁን፡፡ ሁለተኛ የገቢ ምንጭ ፍጠር››

8. ‹‹በአሜሪካ ቢዝነስ ቁጭ ብሎ ማሰብ ያልተለመደ ነው፡፡ እኔ ግን ብዙ ጊዚዬን የማጠፋው ቁጭ ብዬ በማሰብ ነው፡፡

9. ‹‹በጣም አስፈላጊው ኢንቨስትመንት በራስህ ላይ የምታደርገው ነው፡፡››

10. ‹‹የማትፈልገውን የምትገዛ ከሆነ የምትፈልገውን ወዲያው ትሸጣለህ፡፡››

11. ‹‹ከመጥፎ ሰው ጋር ጥሩ ውል ማሰር አትችልም፡፡

12. ‹‹ደስተኛ ሰዎች የሚደሰቱት ምርጥ ነገር ስላላቸው አይደለም፡፡ እነሱ የሚደሰቱት ያላቸውን ነገር አክብረውና ወደው ስለያዙ ነው፡፡

13. ‹‹በመኝታህ ሰዓት ገንዘብ ለማግኘት አስበህ አዲስ መላ ካልፈጠርክ እስክትሞት ትሰራለህ፡፡

14. ‹‹አጥፍተህ የቀረህን አትቆጥብ፡፡ ከቁጠባ በኋላ የተረፈህን አጥፋ፡፡››

15. ‹‹ብዝሃነት ወይም ሁለገብ ዕውቀት ከመሐይምነት ይከላከላል፡፡ የሚሰሩትን ለሚያውቁ ትንሽም ቢሆን ስሜት ይሰጣል፡፡

16. ‹‹ታማኝነት በጣም ውዱ ስጦታ ነው፡፡ ይሄን ስጦታ ከርካሽ ሰዎች አትጠብቅ፡፡››

17. ‹‹ያልተለመደ ከሆነ ሰዎች ብዙ ጊዜ ትክክለኛውን ነገር ከመስራት ሊያስቆሙህ ይሞክራሉ፡፡

18. ‹‹በዓለም ላይ ሐይል ያለው ምንም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ፍቅር ነው፡፡

19. ‹‹ሁልጊዜም ሐብት ማግኛ ምርጡ መንገድ ለራስህ ዋጋ መስጠት ነው፡፡

20. ‹‹አነባለሁ፣ አነባለሁ፣ አነባለሁ! በቀን ውስጥ ከአምስት እስከ ስድስት ሰዓት ድረስ አነባለሁ፡፡››

21. ‹‹እርካታ ትልቁን ቢዝነስ ይገድላል፡፡››

22. ‹‹ብዙ በተማርክ ቁጥር ብዙ ታገኛለህ››

የትኞቹን አባባሎች ወደዳችኋቸው?comment አድርጉልን