Zawya Tv @zawyatvchannel1 Channel on Telegram

Zawya Tv

@zawyatvchannel1


The first Islamic channel based in Ethiopia broadcasting practical islamic teachings in various Ehiopian language.

Zawya Tv (English)

Welcome to Zawya Tv, the first Islamic channel based in Ethiopia! Are you looking for practical Islamic teachings in various Ethiopian languages? Look no further, as Zawya Tv is here to provide you with spiritual guidance and wisdom to enrich your life. Zawya Tv, also known as @zawyatvchannel1 on Telegram, is dedicated to spreading the message of Islam in a way that is accessible to the people of Ethiopia. Our channel offers a wide range of content, from Quranic recitations to lectures on Islamic jurisprudence, all presented in Ethiopian languages to ensure that our viewers can easily understand and apply the teachings in their daily lives. Whether you are a devout follower of Islam or simply curious to learn more about the faith, Zawya Tv has something for everyone. Our engaging programs aim to educate, inspire, and uplift our audience, fostering a sense of community and spiritual growth. Join us on Zawya Tv and embark on a journey of self-discovery and enlightenment. Let us guide you towards a deeper understanding of Islam and help you lead a more fulfilling life in accordance with its teachings. Subscribe to our channel today and experience the transformative power of Islamic wisdom in your life. Zawya Tv – your source for authentic Islamic teachings in Ethiopia.

Zawya Tv

01 Dec, 15:02


ለሁላችሁም በነፃ የተሰጠ ግን የማትጠቀሙበት እድል
*****
የዜና ባለሙያው ብሩክ News እና የዲጂታል ማርኬቲንግ ባለሙያው አሮን ካሚል በ3ኛው Tijara Bizpreneur conference ላይ ለስራ ፈጣሪዎች ሰለ 'influence market' እና 'Social media'ን ለግል እና ለስራ እንዴት መጠቀም እንደምንችል ልምዳቸውን ያካፈሉበት ልዩ ዝግጅት፡፡
አሁኑኑ ወደ ዩትዩብ በምሄድ ማየት ይችላሉ
🔗https://youtu.be/q_0qqRFu3S8🔗
#Tijara #entrepreneurship #business #ቲጃራ

Zawya Tv

09 Nov, 10:23


ችሎታዎን ወይም ሙያዎን ወደ ተጽኖ ለመለወጥ ዝግጁ ነዎት?
*
በ 3 ኛው የቲጃራ ቢዝፕሬነር ኮንፈረንስ ላይ በinfluence marketing እና content creatorነት ጉዞ ላይ ይቀላቀሉን! እሁድ ህዳር 1/2017 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በአዶት ሲኒማ:: መግቢያ 300 ብር። ምያዎን እና ችሎታዎን እንዴት እንደሚያካፍሉ ይወቁ። ተመልካቾችዎን ያሳድጉ እና እውነተኛ ተፅእኖ ይፍጠሩ - ሙያዎ ምንም ይሁን ምን እሁድ በአዶት ሲኒማ እንገናኝ::
3ኛው የቲጃራ ቢዝፕረነር ኮንፍረንስ::

*የሚያስደስትዎን ነገር ወደ ገቢ ምንጭ ለመቀየር
*በsocial media መዳረሻዎች ላይ በርካታ ታዳሚዎችን ለማግኘት
*እንዲሁም ሙያ እና ድርጅትዎን በነዚሁ መዳረሻዎች በማስተዋወቅ ወደ ሰኬት እንዴት መውሰድ እንደሚችሉ 3ኛው የቲጃራ ቢዝፕርነር ኮንፈረንስ
*የዘርፉ እውቅ ባለሙያዎችን፣
*ዘመናዊ እውቀቶችን እና
*ጠቃሚ ትውውቆችን ሁሉንም በአንድ ቦታ ይዞላችሁ መጥቷል፡፡

በዘርፉ ከፍ ካሉት ለመማር፣ ለነገ መንገዳችሁ ከሚጠቅሟችሁ ለመገናኘት እና የሶሻል ሚድያ ተፅእኖ ፈጣሪ ለመሆን ዝግጁ ከሆኑ እሁድ ህዳር 1/2017 በአዶት ሲኒማ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በ300 ብር የመግቢያ ክፍያ ብቻ ይቀላቀሉን እና influence marketን ወይም የተፅእኖ ገበያን ይቀላቀሉ።
ለበለጠ መረጃ 0989701799 ላይ 3ኛው ብለው ቴክስት ያድርጉልን፡፡
3ኛው የቲጃራ ቢዝፕረነር ኮንፍረንስ!

Zawya Tv

18 Aug, 10:26


🎪የኤግዚብሽን እና ባዛር ወጪ የማይቀመስ ሆኗል! 🎪

ለብዙዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ለማስተዋወቅ ኤክስፖና ባዛር ⛔️የማይታሰብ እየሆነ ነው::

ጀማሪ እና መካለለኛ ንግድ ያላችሁ ስራ ፈጣሪዎች ይህንን እድል ተጠቀሙበት:: የጎግል ፎርሙን ሞልታችሁ ስትልኩ ተሳትፎአችሁን በማክበር ፕሮግራሙ እውን ሲሆን ቅድሚያ ለናንተ የምንሰጥ ይሆኖል::

ይህንን ሊንክ ተጭናችሁ ገብታችሁ መረጃውን አካፍሉን
🔗 https://forms.gle/vPZKsUt5xP3jthWR6🔗

Zawya Tv

16 Aug, 13:22


ዳሸን ባንክ “ከወለድ-ነፃ ዱቤ አለ” የተሰኘ አገልግሎት አስተዋወቀ
ዛውያ ቲቪ ፦ነሀሴ 10/2016
ዳሽን ባንክ ከኤግል ላየን ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ከወለድ-ነጻ የዱቤ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል ከወለድ-ነጻ ዱቤ አለ አገልግሎትን ዛሬ ነሀሴ 10/2016 ዓል ይፋ አድርጓል።
ከወለድ-ነጻ ዱቤ አለ FB DubaAle የሸሪዐህ መርሆዎችን ተከትሎ የሚሰራ አገልግሎት ሲሆን እንደ ሽያጭ ውል የሚሰራና በደንበኛው ጥያቄ መሰረት የዱቤ አገልግሎት የሚያገኝበት አሰራር ነው ::
ስለ አገልግሎቱ ማብራሪያ የሰጡት የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በባንኩ ከወለድ ነጻ ሂሳብ ያለው ደንበኛ አገልግሎቱን መጠቀም እንደሚችል አስረድተዋል፡፡
ደንበኞች የዱቤ አለ መተግበሪያን ከጎግል ፕሌይ ወይም ከአፕ ስቶር ላይ ወደ ተንቀሳቃሽ ስልካቸው አውርደው መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን በአቅራቢያቸው በሚገኝ የዳሸን ባንክ ቅርንጫፍ ለዱቤ አለ ማመልከት እንደሚችሉም ገልጸዋል፡፡
ደንበኞች በባለሙያ ታግዘው የደንበኝነት መረጃዎችን ማሟላት እና ከገቢ አቅማቸው ጋር የተገናዘበ የዱቤ ገደብን ማስወሰን የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱንም አክለዋል፡፡
ባንኩ አዳዲስ አገልግሎቶችን የማስተዋወቅ ጥረቱን በመቀጠል አሁንም ከኤግል ላየን ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር የቆየውን የማህበረተሰቡን የዱቤ ግብይት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና አስተማማኝ የባንክ አሰራር በማገዝ ከወለድ-ነጻ ዱቤ አለ" የተሰኘና ሸማቾች በዱቤ በፈለጉት ጊዜ ያሻቸውን ገዝተው ቆይተው ከወለድ-ነጻ በሆነ መንገድ መክፈል የሚችሉበትን አሰራር እንዳስተዋወቀም ተመላክቷል፡፡
ይህን አገልግሎት ለማግኘት ደንበኛው በግል እና በመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቀጥሮ የሚሰራ ከሆነ ከሚስራበት መስሪያ ቤት የገቢ መጠን እና የቅጥሩን ማረጋገጫ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል::
አመልካቹ በግል ስራ የሚተዳደር ከሆነ የሚሰራውን የስራ አይነት እና ድርጅት የሚገልጹ ማስረጃዎችን ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡
በተጨማሪም ደምበኛው ቋሚ ንብረት ካለው እንደ ዋስትና ማስያዥያ አልያም የሶስተኛ ወገን ዋስትና ማቅረብ ይችላል። ደምበኛው በባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ካለው ጥሬ ገንዘብ (በዉጭ ምንዛሬ ወይም በብር) ዋስትና ማስያዝ እንደሚችልም ተብራርቷል፡፡
ዳሽን ባንክ አሁን ላይ ባስተዋወቀው “ከወለድ ነጻ-ዱቤ አለ አገልግሎት ደንበኞች እስከ 700.000.00 ( ሰባት መቶ ሺህ ብር) ድረስ ያሻቸውን መሸመት ያስችላቸዋል፡፡
ከወለድ ነጻ ዱቤ አለ ተጠቃሚዎች ዛሬ ለገዙት በሸሪዓህ ህግ የተፈቀዱ ምርትና አገልግሎቶች ክፍያውን ወደፊት የሚከፍሉ ሲሆን አከፋፈሉም እንደ ደንበኛው ምርጫ በ3 ወር በ6 ወር እና በ12 ወር ይሆናል፡፡ዳሸን ባንክ ከዚህ ቀደም በመደበኛው የባንክ አገልግሎት ዘርፍ “ዱቤ አለ “አገልግሎትን ማስተዋወቁ ይታወሳል ፡፡
ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ!

Zawya Tv

16 Aug, 09:27


አላህ በፈለገው ነገር መማል የሚችል ጌታ ነው!
***
የቁርአን ተፍሲር ⎹ በሸኽ ባህሩ ዑመር ⎹ #quran #zawyatv
***
ናይል ሳት
ፍሪኩዌንሲ 11636
ሲምቦልሬት 27500
ፖላራይዜሽን ቨርቲካል
***

Zawya Tv

15 Aug, 13:59


ሒጅራ ባንክ የሃላል ፋይናንስ ፅንሰ ሃሳብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ይፋ አደረገ
ዛውያ ቲቪ፦ነሀሴ 9/2016
ባንኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተለያዩ ዩኒቨሪሲቲዎችና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የሃላል ፋይናንስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ዛሬ ነሀሴ 9/2016 ዓል በስካይላይት ሆቴል ይፋ አድርጓል።
በዚህ ፕሮግራም ላይ የሂጅራ ባንክ አመራሮች፣የብሔራዊ ባንክ ተወካዮች ፣በኳታር ዩኒቨርስቲ የፊቅህና ተያያዥ ወቅታዊ ጉዳዮች ፕሮፌሰር፣ በባህሬን የሚገኘው አለም አቀፉ የኢስላሚክ ፋይናንስ ተቋም የሆነው AAOIFI አማካሪና አባል፣ የአለም የዑለማዎች ህብረት የኢጅቲሃድና ፈትዋ ኮሚቴ ቃል አቀባይ፣ የ"ፊቅሁ አል አስር" ድርጅት መስራችና ፕሬዝዳንት እንዲሁም የሂጅራ ባንክ ዓለም አቀፍ የሸሪዓ አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ዶክተር ፈድል ሙራድ ፣እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የባንኩ የዳይረክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱሰላም ከማል በበኩላቸው ሂጅራ ባንክ በዛሬው እለት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ሃሳብ ከማቅረብ ጀምሮ አተገባበር ላይ ጭምር ሰፋ ያለ ውይይት ለማድረግ ይህን መድረክ ሲያዘጋጅ ሁሉም የዚህን ጉዳይ አንገብጋቢ እና ወቅታዊነት ተረድቶ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማነሳሳት በማሰብ መሆኑን ገልፀው ሂጅራ ባንክ በቀጣይ ጊዜያትም እንደ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ በማስቀመጥ የማህበረሰብ ማብቃት ስራዎች ላይ በርትቶ በመስራት የማህበረሰቡን የኢኮኖሚ ተሳትፎ ለማሳደግ፣ እንዲሁም የሀገሪቱን የሃላል ፋይናንስ ኢኮኖሚ በማሳደግ ዘርፉ ለሃገራችን እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ለማገዝ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል ።
በዚህ መርሃ ግብር የሃላል ፋይናንስ ፅንሰ ሃሳብ ወደ ማህበረሰቡ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የፓናል ውይይት ፕሮግራም ተደርጓል።
ባንኩ ሁለተኛውን ዙር በወቅታዊ ኢስላማዊ ኢኮኖሚክስ ጽንሰ ሃሳብና ህግጋት ዙሪያ ስልጠና ለወሰዱ ከተለያዩ ክልሎች ለመጡ ታላላቅ ዑለማዓዎች የእውቅና ሰርተፍኬት አበርክቷል።
ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ!

Zawya Tv

15 Aug, 10:22


የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤት ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል
ዛውያ ቲቪ፦ ነሐሴ9/2016፣ አዲስ አበባ
የ አዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ነሀሴ9 /2016 ዓል በኤሊያና ሆቴል እየተከናወነ ይገኛል።
በጉባኤው ላይ የአዲስ አበባ እ/ጉ/ ከ/ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን ሐጅ አማን ኤባ፣ የአዲስ አበባ እ /ጉ/ ከ/ ም/ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ ፈትሑዲን ሐጅ ዘይኑ ሙቀና፣ የምክርቤቱ ዋና ፀሀፊ ሼህ ሁሴን በሽር ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ፣ኡስታዞች ፣ ከፍተኛ የመጅሊስ የስራ ሀላፊዎች ፣ የክፍለ ከተማ መጅሊስ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
በጉባኤው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ እ/ጉ/ ከ/ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን ሐጅ አማን ኤባ በንግግራቸው እንደገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት መዋቅራዊ ለውጥ ካደረገ ወዲህ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጡ በርካታ ተግባራትን ሲያከናወን የቆየ ሲሆን እነዚህን ተግባራት ለጠቅላላ ጉባኤው በማቅረብ መበረታታት እና
መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች እየተወያየ ያሳለፈ ሲሆን የዘንድሮውንም ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የ2016 የሥራ ዘመን በከተማችን ሙስሊሞች መካከል ያለው ሰላምና አንድነት ይበልጥ ተጠናክሮ የሚሄድበትን እና የሚዳብርበትን መንገድ በማመቻቸት ስራ ላይ
በማተኮር ጠንካራና ሁለንተናዊ ተግባራት ሲከናወኑ እንደቆዩ ገልፀዋል።
ጉባኤው ከሰዓት በኋላም የሚቀጥል ይሆናል።
ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ!