zemedkun bekele(ዘመዴ)

@zemdkuwnbekele


zemedkun bekele(ዘመዴ)

27 Sep, 12:05


እስቲ ዘመዶቼ ሌሎችም ነጭ ነጭዋን እንዲሰሙ ለምትወድት ሰው ሼር አርጉላቸው 👇
https://t.me/joinchat/dDljUDPAzrVmZWM0

zemedkun bekele(ዘመዴ)

27 Sep, 12:03


… እናቴ እመቤቴ የጌታዬም እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ፥ የእናት ልመና ፊት አያስመልስ፥ አንገትም አያስቀልስምና ለእኔ ለደካማው ለጎስቋላው ባርያሽ ስለኃጢአቴ፣ ስለ በደሌም ከልጅሽ ከወዳጅሽ ዘንድ ተማልደሽ አማልጅኝ። አስታርቂኝ ከልጅሽ እናት ዓለም።

... ለአባ ህርያቆስ፣ ለአባ ኤፍሬም፣ ለቅዱስ ያሬድ፣ ለቅዱስ ደቅስዮስ፣ ለበላኤ ሰብ ለቀደሙት ሁሉ የተለመንሽ እመአምላክ ሆይ ለእኔም "አክሊለ ገብርኤል" ለተባልኩ ደካማና ለጎስቋላ ባርያሽ ተለመኝኝ። ምልጃሽ አይራቀኝ።

… እናቴ፣ እመቤቴ ሆይ፥ የአንቺ የእናቴ ምስጋናሽ በዝቶልኝ እንደ ልብስ ለብሼው፤ እንደ ምግብ ተመግቤው፤ እንደ ውኃም ጠጥቼው ረከቼ እኖር ዘንድ እርጅኝ።

... እመቤቴ ሆይ የኔ ኃጢአት ያንቺን ንጽህና አያረክሰውምና በብርሃን እጆችሽ ዳሰሽ ለነፍሴ የድኅነት ምክንያት ሁኚያት። ወደ ተወዳጁ ልጅሽ መቅረቢያ መሰላሌ፣ መሻገሪያ ድልድዬ ነሽና እመካብሻለሁ። እተማመንብሻለሁ። አልጫ የሆነውን ዓለም ማጣፈጫ ጨው የሆንሽ አንቺ የእኔንም ህይወት አጣፍጪው። በጓዳዬ ያለቀውን የወይን ጠጅ ተመልክተሽ ለልጅሽም አሳስበሽ ጎዶሎዬን ሙዪው። አጣፍጪውም።

… ለታመመው ዓለም፣ ጤና ለራቃትም ምድር ፈውስን ከልጅሽ ዘንድ አሰጪ። የአሥራት ሀገርሽን ኢትዮጵያንም አትርሻት። መሃሏን ገነት፣ ዳርዳሯን በእሳት አጥር ከልያት። የሚሰደድ፣ የሚራብ፣ የሚጠማ፣ የሚገደል አይኑር። ለምኚ ድንግል። ለምኚልን።

"ድንግል ሆይ እናቴ፥ አዛኝት አማላጅቱም ሆይ! ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ።"

... “ ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት። ሃሌ ሉያ።” መዝ፣ 149፥9

… ኦ ኦ ግሸን ግን ትናፍቃለች። እንኳን ለእመቤታችን በዓለ እረፍት አደረሳችሁ። አሜን፥ ሃሌ ሉያ።
https://t.me/zemdkuwnbekele

zemedkun bekele(ዘመዴ)

10 Sep, 18:42


… ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር … !!

… ዛሬም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ በመረጃ የሳታላይት ቴሌቭዥን በኩል በቀጥታ ስርጭት ወደ እናንተ ይደርሳል።

https://t.me/joinchat/dDljUDPAzrVmZWM0

• በዕለቱ መርሀ ግብራችን

… ከዚያው ከሰሜኑ ጉዳይ አንወጣም። ወሎ ራብ ላይ ነው። የሚታይ የሚሰማው ያስፈራል። በሱ ዙሪያም የምናወጋው ይኖረናል። መጪውን አዲስ ዓመት እንዴት እንቀበለው? ስለ እሱም በጥቂቱ እናወጋለን። የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከትንም አሳፋሪ ተግባር በሰፊው እስክንመለስበት በስሱ እንዳስሰዋለን።

… የቴሌግራም ቻናሎቼንም ይቀላቀሉ።
👉🏿 https://t.me/joinchat/dDljUDPAzrVmZWM0

• ሰምታችኋል ነጭ ነጯን ብቻ !! …መጣሁ ጠብቁኝ። ኣ

zemedkun bekele(ዘመዴ)

10 Sep, 18:36


Channel created