አዳማ፤ ጥቅምት 7/2017(ኢዜአ)፦ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት መምህራን የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ለማስቻል እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ገለፀ።
37ኛው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ምክር ቤት ጉባዔ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ዮሐንስ በንቲ(ዶ/ር) በተለይ ለኢዜአ እንደገለጹት የመምህራን መብት በተለይም ጥቅማ ጥቅምና የሚያጋጥማቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት የሙያ ማህበሩ እየሰራ ይገኛል።
በተለይም በትምህርት ጥራት መረጋገጥ፣ በየደረጃው የሚካሄደው የማህበሩ ምርጫ፣ መምህራን በሀገራዊ ምክክር በሚኖራቸው ተሳትፎ ላይ በሚኖራቸው ሚና ላይ ጉባዔው በጥልቀት ይመክራል ብለዋል።
መምህራን የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲያገኙ ማህበሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
በእስካሁኑ ሂደትም ከ120ሺህ በላይ መምህራን በሀገር አቀፍ ደረጃ የመኖሪያ ቤትና ቤት መስሪያ ቦታ ማግኘታቸውን ለአብነት አንስተዋል።
መምህርነት የሚኖረው ጥራቱን የጠበቀና የተሻለ የመማር ማስተማር ሥራ ሲኖር ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የትምህርት ጥራት ችግሮችና ጉድለቶችን የሚለዩ ጥናቶችን በማካሄድ የመፍትሄ ሐሳቦች ለመንግስትና ባለድርሻ አካላት እያቀረቡ መሆናቸውን አንስተዋል።
በተለይ የትምህርት ቤቶች የፋይናንስ ድጋፍ ፈንድ የማሰባሰብና አቅማቸውን የማጎልበት፣ የትምህርት መርጃ ቁሳቁስና ተያያዥ ግብዓቶች እንዲሟሉ እንዲሁም ቤተ ሙከራዎች እንዲደራጁ ማህበራቸው ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም እንዲሁ።
ከጉባዔ ተሳታፊዎች መካከል የኦሮሚያ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ዋቅወያ ቶሌራ በበኩላቸው ባለፈው ዓመት የመምህራን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በተደረገው ጥረት በክልሉ ከሶስት ሺህ በላይ መምህራን የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
የትምህርት ጥራት ጉዳይ የማህበሩ ቀዳሚ አጀንዳ መሆኑን ገልጸው፤ የመብት ጥያቄ ብቻ ማቅረብ ሳይሆን በሙያችን የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ እየሰራን ነው ብለዋል።
ከመምህራን ጥቅማጥቅም ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰሩ መሆኑን በማንሳት።
በአዳማ ከተማ ለሶስት ቀናት በተሰናዳው ጉባዔ ላይ ከሁሉም ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የመምህራን ማህበር አመራር አባላትና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተጋበዙ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
መረጃዎቻችንን፦
በዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCSjaw-eGJSkvcXHyTpQyT1Q
በቴሌግራም፡- https://t.me/EthiopianNewsA
በድረገጽ፡- https://www.ena.et/
በትዊተር፡- https://twitter.com/ethiopiannewsa?lang=en
የኢዜአ ዜናዎችን በአጭር የስልክ መልዕክት ለማግኘት፡- 9111
ፈረንሳይኛ ድረ-ገጽ https://www.ena.et/web/fre
አረብኛ ድረ-ገጽ https://www.ena.et/web/ara
በአፋን ኦሮሞ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/TajaajilaOduuItoophiyaa/
በትግሪኛ ፌስቡክ፦ https://ww.facebook.com/ethiopianewsagencytigrigna/
በአፍ ሱማሌ ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/ethiopianewsagencyafsoomaali
በአፍ ሱማሌ ድረ-ገጽ፦ https://www.ena.et/web/som
በአፋርኛ ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/ethiopianewsagencyqafarafa
በአፋርኛ ድረ-ገጽ፦ https://www.ena.et/web/aar አድራሻዎቻችን ያገኟቸዋል።