የግጥም መንደር

@yebezigetmoch


የጥበብ መጀመሪያ ......

getem bech@

የግጥም መንደር

03 Sep, 07:21


?❤️‍🩹 መድኃኒት❤️‍🩹🥹

ክፍል ፩

በቤዛዊት የሴት ልጅ

የስልኩ ጩኸት ከእንቅልፌ አባነነኝ ተናደድኩ...... ያቋረጡኝ ምን ከመሰለ ህልም ነበር። የህይወቴ የመጨረሻዋ ስኬቴ ናት አምላኬ እሷን የሰጠኝ ዕለት እውነት በዓለም ላይ ሾሞኛል ማለት ነው። "ባሮክ ባሮክ" ጩኸቷማ እህቴ ነበረች ወደ ቆጡ መውጫ መሰላል ላይ ሆና የምትጠራኝ። "ተነስ ኧረ እንዳትበቅል" አለችኝ። ብበቅል ደስ ባለኝ እሷን እያሰብኩ ጥርሴ ቢረግፍ ጸጉሬ ቢሸብት አልኮነንም ነበር።

እንደ ምንም ተነስቼ ወረድኩኝ። ምሳ ቀርቧል የእህቴ ቆንጆ ሽሮ እንጀራው ላይ ራስ ሆኖ ይታያል ተጣጥቤ ከማዕዱ ተቋድሼ ወደ ጓደኛዬጋር ሄድኩኝ።
ባሮክ እባላለሁ በኤሌክትሪክ ኢንጅነሪንግ ከተመረኩኝ ሁለት ዓመት ሆኖኛል እንደማንኛውም ወጣት የመንግስት ስራ ባይኖርኝም ለራሴ ባመስነፍ ከአንድ ሞል ላይ አንዲት ልጅ ቀጥሬ ቡና ጠጡ እየሰራሁ ነው። አብሮ አደጌም ሳሚም የራሱ የስፖርት ቤት ከፍቶ እየሰራ የሚገኝ የቅባት ልጅ ነው። ከሁለተኛ ክፍል ጀምሮ አብረን ተምረን ያደግን ልጆች ነን። አሁንም ወደ እሱ ነው የምሄደው። ገና ስደርስ ሽሮ በልቶ የሚያድረው ህዝቤ ይሄን ብረት እየገፋ ነበር የተጨማደደ ፊቴን ፈገግ አድርጌ ወደ ሳሚ ቢሮ ገባሁ።
"እ ብሮ ቆየህ እኮ" ገና እንዳየኝ ሳሚ ተናገረ።
"ምን ከመሰለ ህልም ላይ እንደተነሳሁ ብታውቅ እንዲህ ባላልክ" አልኩት ሰላም ብዬው እየተቀመጥኩ።
"ቅዠታም ደግሞ አገረሸብህ" አለኝ ፋይሉን እየከተተ።
"የምሬን ሳም በአሁኑ እኮ ሳገባት ነው ያየኋት" አልኩት ውስጤ ያለውን ደስታ ከፊቴ እያስነበብኩት።
"ቆይ ለምን ሱባኤ አትይዝላትም እንዴ ተቆጣጠረችህ እኮ" አለኝ የባከንኩ የመሰለው አብሮ አደጌ።
"ሳምዬ ብትቆጣጠረኝማ እየበተነ ያለው በረከቴ በሰበሰብኩት የተዘጋው በሬ በተከፈተልኝ እውነት እንዴት ውብ ሆና ስታየኝ እንደነበር በተለይ የምወደው ጥርሷ ብልጭ አድርጋ ስታሳየኝ እኮ....." አቋረጠኝ።
"ተነስ ባክህ እንሂድ" አለኝ። ተናደድኩ ተኮሳትሬ ቀድሜው ወጣሁኝ። መኪና ውስጥ እየሄድን ዝም አልኩኝ ዕቃቃውን እንደተቀማ ህፃን እጄን አጣምሬ በመስኮቱ ወደ ውጪ እያየሁ ነበር እንደማላወራው የተረዳው ሳሚ ሙዚቃውን ከፈተው።

🎧🎧🎧🎧🎧
ኤፍሬም እኔን የጠየቀኝ ይመስል ስለ ውበቷ የዘፈነልኝ የሚመስለኝን የምወደውን ሙዚቃ ነበር
🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶

ዞሬ አየሁት እና ፈገግታዬን ሰጠሁት። "ኧረ ወንድሜ ለአንተ ብዬ ነው አልነገርካት ነገር ልጅቷ በየት ትወቀው ሁሌ እየተያዩ መሳቅ በአይን መሸኛኘት ይጎዳሃል። በህልምህ አትቃዥ ንገራት" አለኝ አፍ ሆኖ የሚነግርልኝ ይመስል። እኔም ሌላ ክርክር ውስጥ ላለመግባት የወሬውን ርዕስ አስቀይሬ ስለ ምንሄድበት ስራ ማውራት ጀመርኩ። ከደቂቃዎች በኋላም የምንገባበት ህንጻ ጋር ደርሰን መኪናውን ፓርክ እያደረግን እኔም ሳሚም የደነገጥነው። ህልሜ ናት......

ክፍል ፪ይቀጥላል

❤️‍🩹🥹መድኃኒት አዲስ ተከታታይ ታሪክ ❤️‍🩹🥹

በማንበብ አስተያየት ስጡ ወዳጆቻችሁን ጋብዙ!
https://t.me/yebezigetmoch

የግጥም መንደር

16 Jul, 19:50


"ደስታ በዙሪያህ የምትጠብቀው ነገር አይደለም,
አንተ ራስህ የምትፈጥረው ነገር ነው."
@yebezigetmoch 😍
join 💗

የግጥም መንደር

16 Jul, 19:50


ህይወት ሁሉ ጊዜ ሁለት አማራጭ አላት አንዱ
ምን አባሽ ብሎ ጥሎሽ ሲሄድ አንዱ ደሞ ምን
አባቴ ልሆንልሽ ምን ጎደለብሽ ብሎ ይመጣል ..

የግጥም መንደር

16 Jul, 19:50


በስህተት የ5ብር ካርድ ወደ ስልኬ ልከው
ማንም ሳይጠይቀኝ ለባለቤቱ መልሻለሁ 😁😋

የግጥም መንደር

08 Jul, 04:53


ፅናት ወዳንቺ የሚወስደኝ ከሆነ እስኪበቃሽ ድረስ ፀንቼ ጠብቅሻለው ።💔😔

የግጥም መንደር

08 Jul, 04:52


" የናፈከኝ ለታ"

ብዙ አለም ኣላውቅም
ብዙ አለም ኣልኖርኩም
ጊዜን ካንተ ጋራ
ቁጥር ኣልሰፈርኩም
ግን......የናፈከኝ ለታ
አይንህ ከአይኔ ሲያርፍ
አቅሜን እንዳሳጣኝ
በከንፈርህ መሳም
ልቤ እንደከዳኝ
በእቅፍህ አለም
ሚወስደኝ አታሎ
ደስታ እንደ ሞት ነው ወይ
እራሴን አስጥሎ
እኔ አላውቅም.......
ነብስ ድረስ ሚዘልቅ
ፍቅር ይሰማኛል
የናፈከኝ ለታ
ሰከንድ ያድርብኛል
ትዝታን እየካበ
አንተን አንተን እያለ
እኔን ይንደኛል
ማሰቤስ የታለ
ሸመትከው በፍቅርህ
ሸከፍከው በጀርባ
ልቁረጥ ያሉት ፍቅር
ለምለም ነው ሚረባ
የናፈከኝ ለታ........
አንተ አደርስበት
ጥልቅ ነው ስሜቱ
በሌለህበት
እልፍ ነው ፍሰቱ
ናፍቆትህ ትንግርቱ
.
.
.
💋💋💋🌹🌹🌹❤️❤️❤️🤌🤌🤌
@yebezigetmoch

የግጥም መንደር

08 Jul, 04:52


• ጥቂት አዉራ፡፡ ስታወራ ቀስ ብትል መልካም ነዉ

• አንድ ቦታ ላይ ብዙ አትታይ፡፡ ስራህ ላይ አተኩር

• ምርጥ የሰዉነት አቋም ይኑርህ

• ተግባቢና የተረጋጋ ሰዉ ሁን

• ማንም ትክክል ነህ እንዲልህ አትጠብቅ፡፡ ማንም ደጋፊህ እንዲሆን አትጎትጉት

• ስላለህ ነገር ደጋግመህ እየተናገርክ የመጎረር ስሜትን አስወግድ

• ፀዳ በል፡፡ በደንም ልበስ፣ ፏ በል!

• ምርጥ አዳማጭና መፍትሄ አምጪ ሁን

• አደርገዋለሁ ያልከዉን ነገር አድርገዉ

• በጣም ደስ ሲልህ ወይም በጣም ስታዝን ዉሳኔ አትወስን

• ሴቶችን በአስተሳሰባቸዉ መዝናቸዉ

• የግል ጉዳይህን ላገኘኸዉ ሰዉ አትናር

• ሰዉ ስላንተ የፈለገዉን ቢያስብ ከማንነትህ ጋር አታገናኘዉ

• ሃላፊነት መዉሰድን አትፍራ

• ማንንም ለመጉዳት ብለህ ጉድጓድ ከመቆፈርም ይሁን ከማስቆፈር ራስህን አሽሽ

• የጎዱህንና ‘ምንም የለዉም!’ ብለዉ የራቁህን ሰዎች ስኬታማ በመሆን አሳያቸዉ

• ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን ማንነት አትጉዳ፡፡ ትክክክል ብትሆን እንኳን ካመኑ ይመኑህ ካላመኑህ ጊዜዉ ያሳምናቸዋል

🌹 በቸር ያውላችሁ 🌹

@yebezigetmoch

የግጥም መንደር

08 Jul, 04:51


የፍቅር ደብዳቤ

👩‍❤️‍💋‍👨.... ፍፁም አይቼ የማላውቀው ዓለም የማላውቀው ስሜት ካንቺ ጋር በመሆኔ የሚሰማኝ ብቻ መንፈሴ ትረካለች ፍፁም ደስተኛ እሆናለሁ.....
@yebezigetmoch

የግጥም መንደር

08 Jul, 04:51


@yebezigetmoch 💔
💋🙈🥺

😞 ትዝታዬ😞

የግጥም መንደር

07 Jul, 07:07


💔 መቆየት ለፈለገው ልብህን
መሄድ ለፈለገው ደግሞ መንገዱን
ዘርጋለት‥
🌹💋😍

የግጥም መንደር

07 Jul, 06:40


ወጣሁኝ ከቤታችን ወደ ተለመደው ቦታችን አብረን ወደታየንበት ሳቅሽ ሳቄ ከሆነበት ሰውን ረስተን በፍቅር የሰከርንበት ህልም ያለምንበት ተኳርፈን ከታረቅንበት ከቦታችን ደረስኩኝ😒ቁጭ አልኩኝ......
ማኩረፊያዬ 💋 ቦታው ልክ እንደ እኛ ተለውጧል እኔ ልሙት! ብታይው ትገረሚያለሽ❤️🤌.....

ቤዛዊት የሴት ልጅ

💬💬💬💬
💬🐷🐷🐷💬
💬 በመጥፋታችን ይቅርታ 💬
💬💬💬💬
😳
🙏
👖
👟👟
Join 👏 👌👌🌹🌹🌹

የግጥም መንደር

19 Mar, 17:49


አለሌ ነበርኩ ። ከህንድ እስከ እብድ የቀረኝ የለም የምል አለሌ። የተኛኋቸው ሴቶች ጠቢቡ ሰለሞን ከተኛቸው የሚያንስ አይደለም አልቆጠርኳቸውም እንጂ።

ጀንጅኜ መዳረሻዬ ማራኪ ሆቴል ነው ።ሆቴሏ ሸጎጥ ያለች ሰዋራ ስፍራ ነች ፤ ከመኖርያዬም እሩቅ ነች ።

አስተናጋጆቹም ምቹ ናቸው። በእርግጥ ጉርሻ ምቹ የማያደርገው የለም ። ፈረንጁ እና መስኪ የሚባሉ አስተናጋጆችን የበለጠ አውቃቸዋለሁ ።

ጠብ እርግፍ ብለው ያስተናግዱኛል ፤ በእርግጥ መስኪ የምትባለው ትንሽ ተለቅ ትላለች ።
ፊት ከሰጠሁት ይጎነትለኛል ብላ ይሆን ፣ ተፈጥሮዋ ሆኖ ይሆን ፣ ነፍፍ ቺክ ስለማመላልስ ይሆን ፣ ስለማጨስ ወይም ስለምጠጣ ይሆን እኔ'ንጃ ብቻ
አትስቅልኝም አትኮሳተርብኝም ።

ፊቷ አልሰጥም።።ን ቢሸኝም ውበቷ ግን እንዳለ ነው። መስኪ ምንም ያህል ቲፕ ብሰጣት አመሰጋገኗ ሆነ አስተያየቷ አይለይም ተመሳሳይ ነው ።

ክላሴ ውስጥ አጭሼ ፣ ጠጥቼ ፣ ባልጌ ሹልክ ብለን በጓሮ እንሄዳለን ። በሌላ ቀን ሌላ ቺክ ይዤ እመጣለሁ ፣ ካልጠረረብኝ ቺክ አልገርብም ።

ሁሉንም እንደሙዳቸው እና እንደፍላጎታቸው እሰክሳቸዋለሁ ።
ላጤነቴ በነፃነት ታየው አልታየው ብዬ ሳልሳቀቅ ለመባለግ አግዞኛል።

ጓደኞቼ ሁሉ ሲያገቡ ፤ ቤተሰቦቼ የአታገባም ውትወታ የበረታ ወቅት ሶልያና የምትባል ልጅ ተዋወቅኩ ።

ባገኘኋት በሁለተኛ ቀን ለመቾመስ በት በት አልኩ አልተሳካልኝም ።
በውስጤ ስንቷ እንደ አንቺ አካብዳ ጭኗን ሳትከፍት የቀረች የለችም ብዬ ፈገግ ስል ምነው አለቺኝ

እርጋታሽ ደስ ይላል አልኳት

ውስጤ እንደላዬ የተረጋጋ እንዳይመስልህ አለቺኝ ። ይሆናል ግን ውስጥም ላይም አንድ ላይ ከመንቀዥቀዥ ይሻላል አልኳት ከንፈሯን ገለጥ አድርጋ ሳቅኩኝ አይነት አለቺኝ

በነገራችን ላይ

አንተም ረጋ ያልክ ነክ አለቺኝ... ስስቅ ። ውስጥህ ወዲ ወዲያ ስለሚል ነው እርጋታህ ያልታወቀህ አለችኝ ።

ይሆናል አልኳት

ሶልያና የበዛ እርጋታ አላት ፥ እርጋታዋ ይረብሸኛል ከደስታ ይልቅ ለድብርት አጋልጦ ነው የሚሰጠኝ።

አብሪያት የምሆነው እስከምደክላት ብቻ ነበር።

ትፈልጋለች ብዬ የማስበውን እነግራታለሁ ። ሲኒማ እጋብዛታለሁ ፤ ትያትር ትጋብዘኛለች ከንፈሯ ጋ ሳልደርስ ቀናቶች ነጎዱ

በጭራሽ የወሲብ ወሬ ለማውራት አታመችም ። ወሲብ ነክ ከተወራ ለመቀጠል ፊቷ አይጋብዝም።ወሲብ ነክ ወሬ ካወራሁ ለይሉኝታ እንኳን ፈገግ አትልም።

መንፈሳዊ ጉባኤ ትጋብዘኛለች። ለእሷ ደስ እንዲላት አንዳንድ አሰልቺ ፣ አንዳንድ ማራኪ ስብከቶችን እሰማለሁ ።

ቀልቧን ለመግዛት መንፈሳዊ መፅሃፍ እያነበብኩ ፤ በጉዳዩ ላይ ሰፊ እውቀት አለኝ ወሬ ሳወራት ቀልቧ ሲሳብ ወሬው ሲጥማት አያለው።

ሳይታወቀኝ የኔን መንገድ እየተውኩ በእሷ መንገድ መመላለስ ቀጠልኩ ።

ከሌሎች ስለተለየች ይሆን ፣ እንደምፈልገው
አለመሆኗ ይሆን ፣ የምፈልገውን ስላልሰጠቺኝ ይሆን ብቻ ቀልቤን ገዝታዋለች።

ውሎዋን ስራዬ ብዬ እከታተላለሁ ። ካልተደዋወልን ይታወቀኛል ። እንቅስቃሴዋ እየገቡኝ መጡ ። ሳላገኛት የት እና ምን እያረገች እንደሆነ መገመት ቻልኩ ።

ከደወለችልኝ ስግብግብ ብዬ አነሳለሁ ። በሂደት መንገዷ ምቾት ሰጠኝ ። ከተመላለስኩበት መንገድ በተሻለ ይሄኛው መንገድ ጣፈጠኝ

የድሮ አመሌ ውል ሲለኝ የምቀመጭላቸው ቺኮች ውልብ ብዬባቸው ሲደውሉ ሳላቅማማ የድሮ ስልክ ቁጥሬን ቀየርኩ ።

የትላንት የውድቀት መንገዳችንን ካልቀየርነው ለለውጣችን ሳንካ ይሆናል ።

አሁን ፈልጌ መፅሃፍ ቅዱስ አነባለሁ፤ እፆማለሁ ጉባኤ እከታተላለሁ ።መንፈሳዊ ጉዞ እሄዳለሁ ። ከሶሊያና ጋ እንፋቀራለን። የትላንት መንገዴን አልተረኩላትም ለዛሬው ማንነቴ ግን ማሃንዲሷ እሷው ናት ።

ለአምላኬ ስንቴ በእሷ ምክንያት ምስጋና እንዳቀረብኩለት። የትላንት ህይወቴን እንዴት አሁን እንደማልወደው ። ስለ ሴት አውልነት ሲነሳ ምንም ሃሳብ አልሰጥም ያ ዘመን ያሳፍረኛል።

ሶልያና አንድ እለት ስትፍነቀነቅ መጣች ምነው ስላት እቴቴ ስራ አገኘች አለቺኝ የት ስላት ባንክ

በቀላሉ ፍንክንክ የምትል አይደለችም የእናቷ ጉዳይ ግን ስስ ጎኗ ነው። ብቻዋን ስላሳደገቻት ይሆን ሁሉ ነገሯ ስለሆነች ይሆን ብቻ ስፍስፍ ትልላታለች።

ምን እንደምትሰራ አላውቅም ። በትምህርት ብዙ ያልገፋች ስለሆነች የት እና ምን ትሰራለች ብዬ አልጠየኩም ፤ እሷም ስራ ነች አልመጣችም ፣ ስራ ቀረች ነው እንጂ የት እና ምን እንደምትሰራ ነግራኝ አታውቅም ።

በጥንጡም በግዙፉም ወሬዎቾ መሃል እቴት ሳትል አትውልም ።

የድሮ ስራዋስ ስላት ። ውይ የድሮ ስራዋን እኮ አትወደውም ግድ ሆኖባት እንጂ አለቺኝ።

ስለ እኔ እንደነገራቻት እና እንደወደደቺኝ የነገረቺኝ እለት እንዴት ደስ እንዳለኝ ።

ባሻዬ ብላ ቴክስት አደረገችልኝ ። ደስ ስላት እና ስትቀልድ ባሻዬ ነው የምትለኝ ። ከእቴት ጋ እንደምንመሳሰል ነግሬህ አውቃለሁ ኣ ስትለኝ ሁሌ ብዬ የሳቅ ስቲከር ላኩላት ።

እንደ እሷ ቆንጀ ነኝ ግን ብላ ፎቶዋን ላከችልኝ ።

ማመን አልቻልኩም

ክው

ድርቅ አልኩ

የላከችልኝ ፎቶውን አገላብጬ አየሁት ፤ አልቀየር አለ ። የማራኪ ሆቴል አስተናጋጅ መስኪ የሶሊያና እናት ናት ፤ ሁለት አብረው ሆነው እና አንድ የመስኪን ማራኪ እንግዳ መቀበያ ጋ የተነሳችውን ፎቶ ላከችልኝ ።

ውስጤ ታወከ ።

ያ ሴት አውል አብርሃም ፤ ያ በየጊዜው ለቁጥር ስፍር የሌላቸውን ሴቶችን የሚያጋድመው ፣ የሚያጨሰው አብራሃም ፤ ያ በጥሩ አይን አይታው የማታውቀው አብራሃም ፤ የአንድ ልጇ ሶሊያና እጮኛ ነኝ ብሎ ፊቷ እንዴት ይቆማል??

ትላንቴ ተከተለኝ። እግዜር በተፀፀትንበት ትላንታችን ይቀጣናል እንዴ? ስንቴ ያመሰገንኩበት ጉዳይ መጨረሻው እንዴት እንደዚህ ሆነ ??

የማደርገው ጠፋኝ ። ጠፋሁ ። አንዳንድ ትላንት ትላንት ላይ ብቻ አይቆምም።
© Adhanom Mitiku

የግጥም መንደር

28 Feb, 12:00


የግጥም መንደር pinned «አደራ ጠርጥሪኝ ስምሽን ስሰማ እንባ አይኔን ካሞቀኝ ስላንቺ ሳወራ ሳግ ደርሶ ካነቀኝ ፀሀይ ከበረደኝ ሳቅ ከኔ ከራቀ መከፋት ደስታየን ከእኔ ከሰረቀ አደራ ጠርጥሪኝ ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ በእብዶች መካከል ደህና ከተሰኘሁ በዝናብ ሲርሱ ደርቄ ከታየሁ በትልቅ ሰው ለቅሶ ሳቄ ካመለጠኝ ሀገር ባሳቀ ቀልድ እንባ ካጠመቀኝ አደራ ጠርጥሪኝ ናፍቀሽኝ…»

የግጥም መንደር

28 Feb, 12:00


አደራ ጠርጥሪኝ

ስምሽን ስሰማ እንባ አይኔን ካሞቀኝ
ስላንቺ ሳወራ ሳግ ደርሶ ካነቀኝ
ፀሀይ ከበረደኝ ሳቅ ከኔ ከራቀ
መከፋት ደስታየን ከእኔ ከሰረቀ

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

በእብዶች መካከል ደህና ከተሰኘሁ
በዝናብ ሲርሱ ደርቄ ከታየሁ
በትልቅ ሰው ለቅሶ ሳቄ ካመለጠኝ
ሀገር ባሳቀ ቀልድ እንባ ካጠመቀኝ

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

ከጨረቃ ጋራ ሳወጋ ካመሸሁ
ከሚያውቁሽ ከሚያውቁኝ ከራሴ ከሸሸሁ
አለም ከደበተኝ ከከረፋኝ ሀገር
በሆነ ባልሆነው ካለኝ ነገር ነገር

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

ይሄው አሁን እንኳ
ስላንቺ እየፃፍኩኝ ላብ ሞልቷል ግንባሬ
ቁጭ ብየ ራሱ ልሩጥ ይላል እግሬ

እኔ እወድሻለሁ ማለቱን ትቻለሁ
በስምሽ መማሉን ረስቼዋለሁ
ለምን ለምን ለምን
ለምን አንቺን ብቻ ለምን ከሰው መርጦ
የሚያርበተብተኝ
የሚያብሰከስከኝ ከሌላው አብልጦ
....ማለቱን ካበዛሁ

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

አወ ናፍቀሽኛል አልክድም ወድቄ
ዝም ብለሽ ነይልኝ አታብዢ ጥያቄ
መልሴ ሁኝኝና
ከወደቅኩበት ጥግ ነይ ፈልገሽ አንሺኝ
መራቅሽ አሞኛል በመቅረብ ፈውሺኝ


አደራ......
https://t.me/yebezigetmoch

የግጥም መንደር

27 Feb, 20:05


ህይወት ትርጉም የሚኖራት አንተ እስካለህ ድረስ ነው፤ አንተ ከሌለህ እኮ ያ ለቤተሰቡ የሚያስበው፣ ለሚወዳቸው ዋጋ የሚከፍለው ጠንካራው ሰው የለም ማለት ነው።

መጥፎ ስሜት ሊሰማህ ተስፋ መቁረጥ ሊፈታተንህ ይችላል፤ ወዳጄ አንተ መበርታት ያለብህ ለራስህ ብለህ ብቻ አይደለም፤ በዙሪያህ ፈጣሪ ላስቀመጣቸው ስጦታዎችህም ስትል ነው!
https://t.me/yebezigetmoch
❤️🌹🌹🌹❤️❤️❤️

የግጥም መንደር

27 Feb, 20:03


በሰዎች ለመወደድ ብዙ ዋጋ እንከፍላለን፤ ሰዎች ደግሞ አይን የሚጥሉት ወይ አጥብቀው የሚወዱት ጠንካራ የሆነ ሰውን ነው። ማንም ደካማን አይወደውም፤ እንዲሁ የሚወድህ ፈጣሪ ብቻ ነው።

ወዳጄ ጠንካራ መሆን ከፈለክ ራስህን አክብረው፣ ራስህን ከነ ድክመትህ ውደደው እና የህይወትህን ትልቁን አላማ እወቀው እሱ ላይ አተኩር ከዛ ሰዎሰዎይች አንተ ላይ ያተኩራሉ፤ እሱኮ ጠንካራ ነው አላማ አለው ብለው ይወዱሀል፤ ሳታስበው ድንቅ ማንነት ገነባህ ማለት ነው!

https://t.me/yebezigetmoch

የግጥም መንደር

08 Feb, 17:26


🍃🍃ተስፋ 🌱🌱🌱
ደራሲ 📖ቤዛዊት የሴትልጅ🖊

❤️ክፍል ሰባት
.
.
.
.
.
ሀዘኔን ደስታዬ ያካፈልኳት ህይወቴን የሰጠኋት ሰናይት ዛሬ የኔ አይደለችም ጭራሽ የውሸት ድራማ ውስጥ በእሷ አለም ላይ ተገኝቻለሁ። ባያት ብዬ ስናፍቅ የኖርኩ እኔ ከንቱ አፍቅሪ ከፊቴ ሳያት እጅጉን ዘገነነኝ። መኪናውን አቁሜ ወደ ዮዳሄ ጋር ገባሁ።
      ሁለተኛ ፎቅ ላይ ካለው የውበት ሳሎን በሩን በርግጄ ገባሁ ሁሉም አፈጠጠ። ሴቶቹ በእሳት ይለበለባሉ ሌሎቹ ፊታቸውን እጅ እና እግራቸው ይታሻሉ። በአይኔ ሳማትር ዮዳሄ ጆሮዋ ላይ ኤርፎን አድርጋ ከሰው መሃል ተነጥላ ተልይታለች እና አላየችኝም። እኔም ሄጄ እጇን ያዝኩት በርግጋ ከዓለሟ ወጣች። "ምንድነው አንተ ደነዝ" አለች ቃል ሳይወጣኝ ጎትቻት ወደ መኪናው ወሰድኳት በጣም ደንግጣለች መደንገጧ እኔን ሊያረጋጋኝ አልቻለም። "ስሚ ህይወቴን እንዳልኖር ነው የመጣሽው ወይስ እንድሞት ነው ማነሽ....ከእኔ ምንድነው የምትፈልጉት" እንደ ክረምት መብረቅ አምባረቁባት። "አትጩህብኝ ምንድነው የምትዘላብደው ማነህ እና ነው ከአንተ የምፈልገው" ከእኔ ድምፅ በላይ ድምጿ ገነነ ፊቷ እያየሁት ጉበት መስሏል። "ሰናይት" ጠራኋት። "ምን ትሁን " አልተረጋጋችም። "ትሰሚኛለሽ ድሮም ስትቅለሰለሺ መጠርጠር ነበረብኝ የዋህ መስለሽ ነው የሰራሽልኝ ደግሞ ሰናይት ጓደኛዬ....." ተበሳጭቼ በቆመችበት ጥያት ሄድኩ።

       ያንን ጊዜ እያሰብኩ ስንከፍ ከእናት አባቴ ቤት ደረስኩ የወትሮ ብስጭቴ ከፊቴ ላይ ያነበቡት ቤተሰቦቼ ዝምታን መርጠዋል እኔም ክፍሌ ገብቼ ከወንድነቴ ጋር እየታገልኩ ወደ ውስጤ አለቀስኩ። ስልኬ በተደጋጋሚ ይደወላል ዮዳሄ ናት። እንዴት ነው የተዋወቅነው አውቃ ነው የመጣችው ግራ ገብቶኛል። የፅሁፍ መልእክት  ገባልኝ ከፈትኩት .."ለእኔ ጥሩ ነገር አይገባኝም አውቃለሁ። ላደረክልኝ ነገር አመሰግናለሁ አንተ ደነዝ።ልትሰማኝ ከፈለክ ወይ ልታወራኝ ከፈለክ ለአንተ ዝግጁ ነኝ" ይላል። ውስጤ የሆነ ነገር ተጎምዶ የወደቀ መሰለኝ የረሳሁት ነገር ያለ ይመስል ንዴቴ ተኖ ስለ ዮዳሄ ማሰብ ጀመርኩ። ደወልኩላት...... "ደነዝ እወነት የሰው ንዴት እኔ ላይ ትወጣለህ" አለችኝ። የኔን ቃል ሳትጠብቅ ፈገግ አልኩኝ ወደ ልቤ ደም እያዘራሁ "ተንኮልሽ ነው ቀድመሽ ብትነግሪኝ ደስ ባለኝ።ለእኔም ጥሩ ነገር አይገባኝም ግን ይሄም አይገባኝም።" አልኳት ድጋሜ ህመሜ አገርሽቶ።"የምትለው እኮ አልገባኝም ሰናይት ማናት" አለችኝ። ክው አልኩ እንዴት እንግዳዋን አታውቅም አልኩኝ። "እባክህ እናውራ ያለህበት እኔ እመጣለሁ" አለችኝ። ያለ መጠን ዝቅ ማለቷ የሌለባትን ትህትና ብታሳይ ይበልጥ ከልቤ ጠረጠርኳት መልሴን ሳልሰጣት ስልኩን ዘጋሁት። የዮዳሄ ግራ መጋባት እኔንም አወዛግቦኛል። ሰናይት ለእሷ የወንድሟ ሚስት ለእኔ ደግሞ የህልሜ እመቤት ነበረች ብቸኛዋ የልቤ ንግስት ህይወትን መኖርን ያወኩባት ሰው አድርጋኝ አውሬ ያደረገችኝ ከሰውተራ ቀላቅላ ከሀዘን መጋዘን የከተተችኝ ብቸኛዋ ህመሜ ናት። ቀኑን የምናፍቃት ለሊቱን የማለቅስላት የኔዋ ሰናይት የሌላ ናት የኔዋ ህልሜ የሌላ እውን ናት። እንባዬ በጉንጬ ቦይ ሰርቶ ይዘረገፋል ድጋሜ መልእክት ገባልኝ ዮዳሄ ናት "እባክህን ለዛሬ ብቻ ከጉድ አውጣኝ አንተን ነው ቤተሰቤ የሚጠብቀው ከቅዠት አለም አትክተተኝ አታሳፍረኝ እከፍላለሁ" ብላ ነበር። አሰብኩት የምወዳት የአይኗ የብርሃኑ ፍላፃ ጨለማዬን የሚያበራው ዛሬ ሊያጨልምብኝ በአንድ ገበታ የተቋደስን ተለያይተን ልንቀርብ። ምን አማረሽ ብዬ ላቀማጥላት የምሻ አፍቃሪዋ ተመልካች ልሆን አልሄድም ብዬ ስልኬን ዘጋሁ። መከፋቴ አይደለም ወደአለሜ መምጣቷ ማዕበሉን አስጀመረው። ድጋሜ መልእክቱ ገባልኝ "እናቴ አይኖቿ ከበሩ ላይ ነው አንተ መድሃኒቴ ወይም በሽታዬ ነህ ምርጫው የአንተ ነው" ይላል ደነገጥኩ። ግን ደግሞ አልሄድም አልችልማ ተነስቼ ወደ መስኮቱ ተጠግቼ ቆምኩኝ .....መድሃኒት እና በሽታ  ሁለት ምርጫ አለኝ ምንም አለመምረጥም መብቴ ነው።


     🫀🫀🫀ይቀጥላል....🫀🫀🫀
🍃🍃🍃🍃🍃ተስፋ🍃🍃🍃🍃🍃
💑አዲስ ተከታታይ ድርሰት👫
በቤዛዊት የሴትልጅ💛
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch

1,716

subscribers

219

photos

6

videos