የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

@ethioadbarat


ቤተክርስቲያንን ክርስቶስ የመሰረታት በደሙ ነው የነፃነው ዳኚዎቹ ደግሞ
እኛ ነን ይቺ በምድር የተተከለች የሰማይ ደጅ ባለቤቷም እኛው ነን
ያገባናልም።
~"የመውጊያን ብረት ብትቃወመው ለአንተ ይብስብሀል~"
ሐስ 9÷5

እናንተንም የምታውቁቸውን አድባራትና ገዳማት መላክ ትችላላችሁ
ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት 👉 @yidne27
👉 @Yisekal

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

14 Oct, 07:49


የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም🙏🙏

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

14 Oct, 07:42


#ዝቋላ_ገዳም
የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ
ቅዱስ ገዳም በ1168 ዓ.ም. ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ
ቅዱስ በዚህ ዓለም በሕይወተ ሥጋ በነበሩበት ጊዜ ከግብጽ ወደ
ኢትዮጵያ መጥተው ቅዱሳት በሆኑ እግሮቻቸው በመርገጥና
በመባረክ በተራራው አናት ላይ በሚገኘው ውብና ማራኪ በሆነው
ባሕር ውስጥ ለ1)///1ዐዐ ዓመታት በመጸለይ ከዘለዓለማዊው
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማይታበል ሕያው ቃል ኪዳን
የተቀበሉበት በ04//14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከዚህ ዓለም በሞት
ከተለዩ በኋላ ጽላታቸው የተቀረጸበት ቤተክርስቲያናቸው የታነጸበት
በክቡር ስማቸው ገዳም የተመሠረተበት አምላከ ገብረ መንፈስ
ቅዱስ ብርሃነ ረድኤቱን በየጊዜው የሚገልጥበት በሀገራችን
ኢትዮጵያ አሉ ከሚባሉት ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማት አንዱ ነው፡፡
የዚህን ታላቅ ገዳም አመሠራረትና ታሪክ እንዲሁም መልክአ ምድር
አቀማመጡን በመጠኑ ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡
የደብረ ዝቋላ ገዳም ከተመሠረተ ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው
የ8)!5/835 ዓመት እድሜን ያስቆጠረ ታላቅ ገዳም ነው፡፡
የመጀመሪያው መሥራች በውስጡ ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራዎችን
በመቀበል ገድላቸውን የፈጸሙበት ታላቁ ጻድቅ አቡ ገብረ መንፈስ
ቅዱስ ሲሆኑ እርሣቸው በ1ሺ4)//14ዐዐ ዓመት ውስጥ
በነበረውና በኢትዮጵያው ንጉሥ በአጼ ዳዊት ልጅ በሕዝበናኝ
(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት ካረፉ በኋላ ንጉሡ ሕዝበናኝ
(ሁለተኛ ስሙ እንድርያስ) በዚህ አምሳለ ደብረ ታቦር በተሰኘ፣
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የማይታበል
ሕያው ቃል ኪዳን ከልዑል እግዚአብሔር በተቀበሉበት ተራራ ላይ
በስማቸው ጽላት በማስቀረፅ ቤተክርስቲያን በማነጽ ገዳም
እንዲመሠረት ካደረጉ በኋላ በሺህ የሚቆጠሩ መናንያን መነኮሳት
በውስጡ ለዓለም ሰላም ለሕዝበ ክርስቲያን ይቅርታና ምሕረትን
ከእግዚአብሔር እየለመኑ ትሩፋን እየሠሩ መንፈሳዊ አገልግሎትን
እያገለገሉ እስከ ግራኝ ወረራ ድረስ ገዳሙን በማስፋፋት
ቆይተዋል፡፡
ኋላም ግራኝ መሐመድ የኢትዮጵያን ገዳማትና አድባራት ባቃጠለና
ባጠፋ ጊዜ ይህም ገዳም በግራኝ ወረራ መነኮሳቱ ተጨፍጭፈው
አልቀዋል፣ ቤተክርስቲያኑም ተቃጥሏል፣ ገዳሙም ፈርሷል፡፡ ይሁን
እንጂ ገዳሙ ዘወትር መንፈስ ቅዱስ የማይለየው እውነተኛ
የቅዱሳን ቦታ በመሆኑ ሥራውን ባህታውያን ሳይለዩት እስከ ንጉሥ
ማህለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ድረስ ለብዙ ዓመታት ያህል ጠፍ
(ባዶ መሬት) ሆኖ ቆይቷል፡፡
በኋላም የንጉሥ ወሰን ሰገድ ልጅ የሆኑት ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ
የታላቁ ጻድቅ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መካነ ገድል የሆነውን
የዝቋላን ገዳም እንደገና አሳድሰው እንደ ቀድሞው የመንፈሳውያንና
የመናንያን መነኮሳት መሰብሰቢያ አድርገው አቋቁመውታል፡፡
ከዚያም በኋላ አጼ ምኒልክ ለገዳሙ መናንያን መነኮሳት መተዳደሪያ
ሰፊ ርስት ጉልት ከመስጠታቸውም በላይ የመንፈሳዊ መተዳደሪያ
ሕግና ሥርዓቱንም በወቅቱ ከነበሩት መንፈሳውያን አባቶች ጋር
ሆነው በመወሰን ያወጡት ሕግ የሚሻሻለው በቅዱስ ሲኖዶስ
ተሻሽሎ እነሆ እስከ አሁን ያለው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ቤተክርስቲያንም አጼ ምኒልክ ያሠሩት ነው፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን
አጼ ምኒልክ ለደብረ ዝቋላ ገዳም ብዙ መጻሕፍትና ንዋየ ቅድሳትን
የሰጡ ሲሆን አስከ አሁንም በቅርስነት ተጠብቀው ይገኛሉ፡፡


የደብረ ዝቋላ ገዳምን መልክአ ምድር አቀማመጡን
ስንመለከት

የዝቋላ አቡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በታላቅ ተራራ ላይ
የተመሠረተ ውብና ማራኪ የሆነ ምን ጊዜም ጸጋ እግዚአብሔር
የማይለየውና ንጹህ ጤናማ አየር ያለው በአጠቃላይ ተፈጥሮ
ያደለው እውነተኛ መካነ ቅዱሳን ነው፡፡ ወደዚህ ታላቅ ገዳም
ለመድረስ ከአዲስ አበባ እስከ ዝቋላ ተራራ ‘2/82 ኪ.ሜ.
ርዝመት ያለው ሲሆን የተራራው ርዝመት በመኪና መንገድ 9/9
ኪ.ሜ. ነው፡፡ በእግር ተራራው ብቻ ከ2/2 ሰዓት ተኩል እስከ 3/3
ሰዓት ያስኬዳል፡፡ ይሁን እንጂ የዝቋላ ተራራ ዙሪያውን በደን
የተሸፈነ በመሆኑ ተራራውን ለመውጣት ጉዞ ሲጀምሩ ውብና
ማራኪ የሆነው የደን መዓዛ፣ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ፣ የቅዱሳን
ረድኤት ልብን እየመሰጠ ያለምንም ድካም ከተራራው አናት ላይ
ያደርሳል፡፡
ከዚያም ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቀዱስ ለዓለም ሰላም
ለኢተዮጵያ ምሕረትን በመለመን )/1ዐዐ ዓመት ሙሉ በውስጡ
የጸለዩበትን ባህር ዙሪያውን ጥቅጥቅ ባለ የተፈጥሮ ደንና የባሕር
ዛፍ አጣና በሚያካክል ቀጤማ ተከቦ ሲታይ ሰማያዊ ገነትን
የሚያስታውስ ምድራዊ ገነት እውነተኛ የጽድቅ ቦታ ለመንፈሳውያን
መኖሪያ የተፈጠረ መሆኑንና ታላቅነቱን ያስመሰክራል፡፡ በዚህም
የሐይቅ ጸበል ብዙ ሕሙማን ከልዩ ልዩ ደዌያቸው ይፈወሱበታል፡፡
የዚህ ሐይቅ አቀማመጥ ከተራራው አናት ላይ እንደ ገበታ ወይም
ሣህን በጎድጓዳ ቦታ ላይ ያለ ሆኖ ዙሪያው በደንና በቀጤማ
የተከበበ ነው፡፡ እጅግ በጣም የሚያስደንቀው ይህ ባህር ባልታሰበ
ጊዜ እንደ አምፖል ያለ ብርሃን በግምት ርዝመቱ ከ2 እስከ 3
ሜትር የሚደርስ በባህሩ መካከል ሲበራ ማየት በዝቋላ አቡነ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ለሚኖሩ መነኮሳት የተለመደ ነው፡፡
የብርሃኑም ዓይነት ነጭ ሲሆን ይህ ከላይ የጠቀስነው ዓይነት
ብርሃን በመካከሉ የሚቆም ሲሆን በቀጤማው ዙሪያ ደግሞ እንደ
አምፖል ዓይነት ብርሃን ባህሩን ከቦት ለብዙ ሰዓት ይቆያል
አንዳንድ ቀንም ሙሉ ሌሊቱን ሲያበራ የሚያድርበት ጊዜ አለ፤
ይህን ስንል ለአንባብያን ማመን ያስቸግር ይሆናል፡፡ ነገር ግን
የሚጠራጠር ሁሉ በዝቋላ ገዳም ለጥቂት ቀን ከተቀመጠና
እግዚአብሔር ከፈቀደለት አይቶ ማመን ይችላል፡፡
ከዚህ በላይ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን አስደናቂ ተአምርና
የገዳሙን ይዘት በመጠኑ አቅርበናል፡፡ በዝቋላ አቡ ገብረ መንፈስ
ቅዱስ ገደም በየዋሻውና በየጫካው ወድቀው ለዓለም ሰላምን
ለሕዝበ ክርስቲያን ይቅርታና ምሕረትን ከልዑል እግዚአብሔር
እየለመኑ የሚኖሩ ባህታውያን ያሉበት በብዙ የሚቆጠሩ አረጋውያን
አባቶችና እናቶች እንዲሁም አቅመ ደካሞች የሚጦሩበት አምላከ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ብርሃነ ረድኤቱን ሁል ጊዜ የሚገልጥበት
ታላቅ ገዳም ስለሆነ ምዕመናን በዚህ ቅዱስ ቦታ በመገኘት
የቅዱሳንን በረከት በመቀበል የታላቁ ጻድቅ የአቡነ ገብረ መንፈስ
ቅዱስ የቃል ኪዳናቸው ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ እያመላከትን
ጽሁፋችንን በዚሁ እናጠቃልላለን፡፡
የጻድቁ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን
አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ለመቀላቀል
👇👇👇👇👇

https://t.me/ethioadbarat

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

01 Oct, 12:07


ቤተ ክርስቲያን
የታነጸበት ቦታ ላይ እንዲያርፍ ያስረዳሉ፡፡
አጼ ዘርዓያዕቆብ መስከረም 21 ቀን 1446 ዓ.ም በራዕይ የተነገረኝ
ሥፍራ ይህ ነው በማለት ተራራውን ሠባት ጊዜ ከዞሩ በኋላ በገደል
ተንጠላጥለው በመውጣት በተራራው አናት ላይ ቀደም ሲል
የተሠሩትን አብያተ ክርስቲያናት በጥሩ ሁኔታ አሳንጸው መስቀሉን
በእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን በከፍተኛ ጥንቃቄ በተዘጋጀ ቦታ
አስቀምጠዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያኑንን ውስጥም በብረት ርብራብና ሰርገላ ሰርተው
እንደምድር ቤትና ፎቅ ደልድለው እንዳሰሩ የገዳሙ አባቶች
ይናገረል፡፡
ቅዱስ መስቀለ የ “ተ” ቅርጽ እንዳለው የሚነገር ሲሆን ይህንንም
ለማሳየት የእግዚአብሔር አብ ቤተ
ክርስቲያን በመስቀል ቅርጽ የታነጸ ሲሆን በቤተ ክርስቲያኑ ህንጻ ላይ
የተሳሉና የተቀረጹ የ“ተ” ቅርጽ ያላቸው መስቀሎች ይታያሉ፡፡
በግሸን አምባ በአራቱም የመሰቀል ክፍሎች ላይ አብያተ ክርስቲያናት
ተተክለዋል፡፡
በአምባው አምስት አብያተ ክርስቲያናት ሲኖሩ ከሁሉም ቀድሞ
የተተከለው የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡
የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን በግሸን አምባ በ517ዓ/ም በአፄ
ካሌብ ዘመነ መንግስት አባ ፈቃደ ክርስቶስ በሚባሉ አባት እንደተሰራ
ቀደም ብሎ ተጠቅሷል፡፡
በወቅቱ ቤተ ክርስቲያኑ በሳር ክፍክፍ እንደተሰራ የሚታመን ሲሆን
በአፄ ይኩኖአምላክ ዘመነ መንግስት ታድሷል፡፡
በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ደግሞ የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን
የግማደ መስቀሉ ማረፊያ ሆኖ በመመረጡ በወርቅና አልማዝ
አሸብርቆ እንዲያምር ተደርጎ ነበር፡፡
የተለያዩ ነገሥታት እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን ሲያድሱትና
ሲጠብቁት የቆዩ ሲሆን አሁን ያለውን ቅርጽ የያዘው በዳግማዊ
ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይታመናል፡፡
የቤተ ክርስቲያኑ አሰራር የመስቀል ቅርጽ ያለው ሲሆን ዲዛይኑንን
ዳግማዊ ምኒልክ ከእየሩሳሌም እንዳስመጡት ይነገራል፡፡
ጣራው እንጨት ሲሆን በሮቹም የአንጨት ጣውላ ሆነው በላያቸው
ላይ የመላዕክትና የመስቀል ቅርጽ በአዋቂዎች የተቀረጸባቸው
ናቸው፡፡ በውስጥ በኩል ደግሞ የእንጨት ቋሚዎች አሉት፡፡
መስኮቶቹ ብረትና መስታዎት በቅርብ ጊዜ የተገጠሙ ይመስላሉ፡፡
ውስጡ በቅዱሳን ሥዕላትና በነገሥታት ስዕል ያጌጠ ነው፡፡
ከእግዚአብሔር አብ ቤተክርስያን ቀጥሎ የዮርዳኖስ ፀበል ቦታ
ይገኛል፡፡
ይህ ቦታ መጀመሪያ ለክቡር መስቀሉ ማሳረፊያ ተብሎ የተቆፈረ ሲሆን
ለብዙ ጊዜ ወይም ከእግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ጣራ ውሃ
የሚጠራቀምበት በመሆኑ ለፀበል ቦታነት ያገለግላል፡፡
ሁለተኛዋ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ማርያም ስትሆን በክብ ቅርጽ
የተሰራችና በተለያዩ ቀለማት ያጌጠች ናት፡፡
ቤተ ክርስቲያኗ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራችው በአፄ ይኩኖአምላክ
በ1275 ነው፡፡
አፄ ይኩኖአምላክ የቅድስት ማርያምን ቤተ ክርስቲያን ለማሰራት
ያነሳሳቸው ወደ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ሴቶች መግባት
ሰለማይችሉ ሁለቱንም
ጾታዎች የሚያሳትፍ ቤተ ክርስቲያን በአምባው እንዲኖር የነበራቸው
ከፍተኛ ፍላጎት ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያኗ በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ እህት እማሆይ ዕሌኒ እንዲሁም
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባለቤት እቴጌ መነን እንደገና ታድሳለች፡፡
የቅዱስ ሚካኤል ሲሆን ከጎንደር በመጡ አቡነ ሚካኤል በሚባሉ
አባት የተተከለ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ በተራራው የምዕራብ ክፍል
የሚገኘ ሲሆን የተገነባውም በክብ ቅርጽ ነው፡፡
የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያ ሲሆን አቶ ይመስገን ገ/እግዚአብሔር
እና ወ/ሮ አበራሽ ንጉሤ በሚባሉ ፈቃደኞች በክብ ቅርጽ የተሰራ
ነው፡፡
ከቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ቅርብ እርቀት አምስተኛው የቅዱስ
ኡራዔል ቤተ ክርስቲያን ይገኛል፡፡
በግሸን ደብረ ከርቤ መስከረም 21፣ ጥር 21 እና መጋቢት 10
ዓመታዊ የክብረ በዓል ቀናት ናቸው፡፡
በተለይ መስከረም 21 እና ጥር 21 በርካታ የሀይማኖት ተጓዦች
ሰለሚታደሟቸው የበዓላቱ ድምቀት ከፍተኛ ነው፡፡ ለመስከረም 21
የንግስ በዓል ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በርካታ እንግዶች ወደ
ግሸን ያቀናሉ፡፡
መስከረም 17 ግማደ መስቀሉ በሚገኝበት ቦታ የመስቀል ክብረ
በዓል ልዩ በሆነ መንገድ የሚከበር ሲሆን መስከረም 21 ደግሞ
የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል ይከበራል፡፡
መስከረም 21 ከቅድስት ማርያም ክብረ በዓል በተጨማሪ አፄ
ዘርዓያዕቆብ የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን አሳድሰው ቅዱስ
መስቀሉን በክብር ያሳረፉበት ቀን በመሆኑ በዓሉ በድምቀት ነው
የሚከበረው፡፡
በግሸን የሚካሄደው ሁለተኛው ክብረ በዓል ጥር 21 የሚከናወነው
ነው፡፡
በዓሉም የአስተሪዮ ማርያም በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ ጊዜ ግሸን
ላይ ጋብቻቸውን የሚፈጽሙ ጥንዶች በርከት ይላሉ፡

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

@ethioadbrat
@ethioadbrat
@ethioadbrat

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

01 Oct, 12:07


#ግሸን_ደብረ_ከርቤ

ከደሴ ከተማ በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በ82 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ
የምትገኘው የግሽን ደብረ ከርቤ በ517ዓ.ም አባ ፈቃደ ክርስቶስ
በተባሉ አባት እንደተመሰረተች ይነገራል፡፡
ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ደግሞ ቦታዋ ከዕምነት ሥፍራነቷ
በተጨማሪ የነገሥታት ልጆች መኖሪያ በመሆን ማገልገሏን የታሪክ
ድርሳናት ይመሰክራሉ፡፡
ግሸን በክርስቲያኖች ዘንድ ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው የኢየሱስ
ክርስቶስ መስቀል ሰለሚገኝባት የበለጠ ትኩረት እንድታገኝ
አስችሏታል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል በአጼ ዳዊት ከግብጽ ወደ
ኢትዮጵያ እንዲመጣ ስምምነት ከተደረሰ በኋላ በልጃቸው በአጼ
ዘርዓያዕቆብ ዘመን
ቅዱስ መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በመስከረም 21 ቀን 1446
ዓ.ም ግሸን እንደገባና በእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ
በክብር እንደተቀመጠ አባቶች ይናገራሉ፡፡
ግሸን ደብረ ከርቤ ለቅዱስ መስቀሉ መቀመጫ እንድትመረጥ
ያስቻላት አጼ ዘርዓያዕቆብ
“አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል/መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ ላይ
አስቀምጥ/ የሚል ራዕይ በማየታቸው መሆኑ ይታመናል፡፡
ንጉሡ በራዕያቸው መሰረት በኢትዮጵያ ካሉት መልከዓ ምድራዊ
ስፍራዎች ውስጥ የመስቀል ቅርጽ ያለው
የቀራንዮ አምሳል የሆነ ቦታ ሲያፈላለጉና ሲያጠኑ ቆይተው ግሸንን
መርጠዋል፡፡
በተፈጥሮ የግሽን አምባ የመስቀል ቅርጽ ያለው ሲሆን ዙሪያውን
በጥርብ ድንጋይ የተከበበ ነው፡፡
ወደ አምባው ለመውጣትም ሆነ ለመውረድ የሚቻለው በአንድ
ጠባብ በር በኩል ብቻ ነው፡፡
ይህ በር ከመሠራቱ በፊት ወደ ቦታው ለምውጣትም ሆነ ለመውረድ
ብቸኛው አማራጭ ወገብን በመጫኛ በማሠር በመጎተት እንደነበር
ይነገራል፡፡
ለግሸን ደብረ ከርቤ የተሰጠውን ቃል ኪዳን በማክበርና የቅዱስ
መስቀሉ መገኛ መሆኗን በማመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ሀይማኖት ተከታዮች ዓመቱን በሙሉ ወደ ግሸን እየሄዱ
እንደሚሳለሙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
በተለይም በሚሊዮን የሚቆጠሩ እንግዶች መስከረም 21፣ ጥር 21
እና መጋቢት 10 በሚከበሩ ዓመታዊ ክብረ በዓላት ወቅት በግሸን
ደብረ ከርቤ ይታደማሉ፡፡
ለመስከረም 21 ክብረ በዓል ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በርካታ
እንግዶች ወደ ግሸን ያቀናሉ፡፡
መስከረም 17 ግማደ መስቀሉ በሚገኝበት ቦታ የመስቀል ክብረ
በዓል ልዩ በሆነ ሁኔታ የሚከበር ሲሆን መስከረም 21 ደግሞ
የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል ይከበራል፡፡
መስከረም 21 ከቅድስት ማርያም ክብረ በዓል በተጨማሪ አፄ ዘርዓ
ያዕቆብ የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን አሳድሰው ቅዱስ
መስቀሉን በክብር
ያሳረፉበት ቀን በመሆኑ በዓሉ በድምቀት ነው የሚከበረው፡፡
ቅዱስ መስቀሉ በመስከረም 21 ቀን 1446 ዓ.ም ወደ ግሸን እንደገባ
አባቶች ይናገራሉ፡፡
ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በየዓመቱ መስከረም 21 ቀን የግሽን ደብረ ከርቤ
ገዳም ዓመታዊ በዓል ይከበራል፡፡
ግሸን ደብረ ከርቤ የምትገኝበት ቦታ ወይና ደጋ የአየር ፀባይ ሲኖረው
በአብዛኛው የአካባቢው መልክዓ ምድር አቀመማመጥ ተራራማና
ወጣ ገባ ነው፡፡
የመሬቱ ወጣ ገባነት ካለው ዝቅተኛ የመሰረተ ልማት ዝርጋ ጋር
ተደማምሮ የግሸን አምባ መንገድን አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡
ከደሴ ወደ ዋድላ ደላንታ የአስፓልት መንገድ ተሠራ ሲሆን ከዚህ
መንገድ ወደ ቀኝ በመገንጠል 17ኪ.ሜ ጥርጊያ የገጠር መንገድ ጉዞ
በኋላ የአምባሰል የተራራ ሰንሰለት አካል ከሆነው የግሸን አምባ
ይደረሳል፡፡
የግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም አምባ ዙሪያውን ቀጥ ባላ ገደል
የተከበበ ሲሆን ወደ አምባው መግቢያው በር አንድ ብቻ ነው፡፡
ሰውም ሆነ ማንኛው ዕቃ የሚጓጓዘው በዚህ በር ነው፡፡
ቀደም ባሉት ጊዜያት ወደ ግሽን አምባ መውጫው በር የቅዱስ
ዑራኤል ቤተክርስቲያን በአለበት በኩል እንደነበር ይነገራል፡፡
ይህ በር በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ለመውጣም ሆነ
ለመውረድ እንዲያመች በደረጃ እንደተሠራ ይነገራል፡፡
የግሽን አምባ የመጀመሪያ መጠሪያ ደብረ-ነጎድጓድ ነበር፡፡
ቅዱስ ላሊበላ አስራ አንዱን አስደናቂ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት
ከማነጻቸው በፊት ወደ ግሸን ወጥተው እንደነበረ ይነገራል፡፡
በአምባውም ፍልፍል ቤተ ክርስቲያን ለመስራት ሞክረው ነበር፡፡
ግሸንንም ደብረ እግዚአብሔር በማለት ሰያሟት፡፡
ቅዱስ ላሊበላ ደብረ እግዚአብሔር የሚለውን ስም እንዲሰጡ
ያደረጋቸው የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን በአምባው መገኘቱ
እንደሆነ አባቶች ይናገራሉ፡፡
ይኩኖአምላክ ዘመነ መንግስት ግሸን ከእምነት ቦታነቱ በተጨማሪ
የአስተዳደር ቦታ በመሆን የነገሥታት ልጆች እንዲማሩና በዚያው
እንዲኖሩ በመደረጉ አካባቢው ደብረ ነገሥት ተባለ፡፡
ግሸን ደብረ ከርቤ የተባለችው ደግሞ በአፄ ዘርዓያዕቆብ ዘመነ
መንግስት ነው፡፡
አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ግማደ መስቀሉን ከሲናር ወደ ኢትዮጵያ
በማስገባት በዚህ አምባ ሲያሳርፉ አምባው የመስቀሉ መገኛ ነው
በማለት ደብረ ከርቤ ብለው ሰየሟት፡፡
አጼ ዘርዓያዕቆብ ግማደ መስቀሉን አሸክመው እየገሠገሡ ከብዙ
ድካምና ፍለጋ በኋላ ወደ ተራራው
በመምጣታቸው ‘ገሠገሠ’ የሚለው ቃል በግዕዝ ‘ጌሠ’ የሚል
ትርጓሜ ያለው በመሆኑ ከጌሠ በጊዜ ብዛት ወደ ግሸን አንደተለወጠ
ይነገራል፡፡
የግሽን አምባ ከቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሆነው ወደ ምስራቅ
ሲመለከቱ የተራራው ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ የመስቀል ቅርጽ ሆኖ
ይታያል፡፡
በአጼ ካሌብ ዘመነ መንግስት ወደ ዚህ ሥፍራ የመጡት ግሪካዊ
መናኝ/መነኩሴ/ አባ ፊሊክስ በኢትዮጵያዊ ሥማቸው አባ ፈቃደ
ክርስቶስ ተራራው
ላይ ለመውጣት መግቢያ በር በማፈላለግ ላይ እንዳሉ በአንዱ
የተራራ ጫፍ ላይ ማር ተንጠልጥሎ በማየታቸው ይህስ ‘አምባ-
ሰል’ ነው ብለው ተናገሩ ይበላል፡፡ ‘
ሰል’ በግሪክ ቋንቋ ማር ማለት ሲሆን አምባ ከሚለው የአማርኛ ቃል
ጋር ተጣምሮ ‘አምባሰል’ የማር አምባ የሚል ስያሜ እንዳገኘ
ይነገራል፡፡ ግሸን የምትገኝበት ወረዳ አምባሰል ይባላል፡፡
በአጼ ይኩኖአምላክ ዘመነ መንግስት ወይም ከ1363 ዓ.ም ጀምሮ
ከገዳምነት በተጨማሪ የነገሥታት ቤተሰቦች መኖሪያና የማዕከላዊ
መንግስት የማዕረግ ዕቃዎች ማስቀመጫ በመሆን አገልግላለች፡፡
ከአጼ ይኩኖአምላክ እስከ አጼ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግስት ድረስ
ባለው ጊዜ ውስጥ የነገሡ ነገሥታት ሁሉም በግሸን አምባ እንደኖሩና
እንደተማሩ ይነገራል፡፡
ፍትሐ ነገስተ፣ ነገረ መለኮት፣ ግብረ-ገብነትና የመንግስት አስተዳደር
ከግሽን አምባ ተምረው ነጥረው እንዲወጡ ለንጉሣዊ ቤተሰቦች
ትምህርት ይሰጥ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ከ590 በላይ የነገሥታትና የመኳንንት ልጆች በግሸን እንደተማሩባት
ይነገራል፡፡
የመንግስት ለውጥ በሚኖር ሰዓት በጃን ጠሪው /በንጉሥ ጠሪው/
አማካኝነት ብቃቱ፣ ትግስቱ፣ ህዝብን የማስተዳደርና መንግስትን
መምራት ይችላል ተብሎ የታመነበት ግለሰብ ከነገሥታት ልጆች
እየተመረጠ እንዲነግሱ ይደረግ እንደነበር በታሪክ ተመዝግቧል፡፡
ከዓመታት በኋላ የነገሡት የአጼ ዳዊት ልጅ አፄ ዘርዓያዕቆብም
አባታቸው ያመጡትን መስቀል ሲናር ድረስ ሄደው በመረከብ ወደ
ኢትዮጵያ አስገብተዋል፡፡
አጼ ዘርዓያዕቆብ መስቀሉን እንዳገኙ እንደ አባታቸው በተደጋጋሚ
“መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ” የሚል ራዕይ
በማየታቸው በኢትዮጵያ
ካሉት መልከዓ ምድራዊ ስፍራዎች ውስጥ የመስቀል ቅርጽ ያለው
የቀራንዮ አምሳል የሆነ ቦታ ካፈላለጉና ካጠኑ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶሰ የተሰቀለበት
መስቀል አሁን ግሼን አምባ በሚባለው ሥፍራ ላይ መስከረም 21 ቀን
1446ዓ.ም ደብረ ከርቤ አሁን እግዚአብሔር አብ

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

26 Sep, 21:15


#ቅዱስ_መስቀል

#ቤተ_ክርስቲያን_ከመሠረቷ_እስከ_ጉልላቷ_ያጌጠችው_በመስቀል_ነው

በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከማኅሌት እስከ መቅደሱ የመስቀል አገልግሎት እጅግ ብዙ ነው ማኅሌቱን ስንመለከት ሊቃውንቱ ገና ስቡሕ ብለው የሚጀምሩት በመስቀል ሲሆን እንዲሁም የመስቀልን ክብር በሚያወሳ ጣዕመ ዝማሬ በየዚቁ መሐል በማቅረብ ነው ።

በመቀጠልም ዲያቆኑ የምልጣን ምስባክ በሚሰብክበት ሰዓት መስቀልን ይዞ ነው እስመ ለዓለሙና አንገርጋሪው የሚቃኘው ስለዚህ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን #መስቀል_የማኅሌቱ_ጌጥ_ነው ።

በቅድስት ውስጥ በሚቀርበው አገልግሎት ውስጥ ስንመለከት ደግሞ መልክአ ሥዕሉ የሚጀመረው በመስቀል ነው ተአምረ ማርያም የሚነበበው በመስቀል ነው ኪዳን የሚደረሰው በመስቀል ነው ።

ወደ መቅደሱ ውስጥ ስንገባ ደግሞ ቅዳሴው የሚጀመረው በመስቀል ነው ገና ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት የመቀደሻ ንዋያተ ቅድሳት መጀመሪያ በመስቀል ተባርከው ነው ለአገልግሎት የሚውሉት ለምሳሌ ጻሕሉ ፣ ጽዋው ፣ ዕርፈ መስቀሉ ፣ ሙዳዩ ፣ መሶበ ወርቁ ፣ ዕጣኑ ፣ ልብሰ ተክህኖው ፣ መጎናጸፊያው ፣ ማኀፈዱ ወዘተ በመስቀል ይባረካሉ ።

ቅዳሴው ሲጀመር ደግሞ ረቡዕ ዓርብና ቅዳሜ ሲሆን ገና መግቢያው የሚታወጀው በመስቀል ዜማ ነው ይኸውም « መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ እምኵሉሰ ፀሐየ አርአየ ። መሰቀል አበራ ከሁሉ ይልቅ ፀሐይን አሳየ #ለፀሐይ_ፀሐይዋ_ሆነ » የሚለውን ዜማ እያዜሙ ወደ መቅደስ ይገባሉ ።

ከዚያም ዲያቆናቱ የመጾር መስቀል ካህናቱ የእጅ መስቀል ይዘው ቅዳሴውን ያከናውናሉ በእያንዳንዱ የጸሎት አንጓ የመስቀል ቡራኬ አለ መልእክት ከመነበቡ በፊት ዲያቆናቱ መስቀል ይሳለማሉ ።

እንዲሁም በንዋየ ቅድሳቱ ላይ መስቀል ይሳላል ፤ ይቀረጻል ፤ ይጠለፋል ለምሳሌ በካህናት ልብሰ ተክህኖ ላይ በጽዋው ክዳን ላይ በዕርፈ መስቀሉ ጫፍ ላይ ፤ በማኅፈዱ ላይ በመሶበ ወርቁ ላይ ፣ በጽናው ላይ በአጎበሩ ላይ ፤ በመጻሕፍት ድጉሰት ላይ መስቀል ይደረጋል ።

ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጥምቀት የምትፈጽመው በ40ና በ80 ቀን ሀብተ ወልድ ስመ ክርሰትና የምታድለው ፤ ልጅነት የምታጎናጽፈው በመስቀል ነው ሥርዓተ ጋብቻ ሲፈጸም ሙሽራውና ሙሽሪት እጆቻቸውን በመስቀሉ ላይ አነባብረው ቃለ መሐላ የሚፈጽሙት ቃል ኪዳናቸውን የሚያረጋግጡት በመስቀል ነው ።

ምእመናን የእንግድነታቸውን ኑሮ ጨርሰው በሞት ከዚህ ዓለም ሲለዩ ቤተ ክርስቲያን ክብርት ነፍሳቸው ለፈጣሪያቸው ክቡር ሰውነታቸውን ለመቃብር የምታረካክበው በመስቀል ባርካ ነው የምትሸኘው ።

አባቶቻችን የመስቀልን ክብር በብዙ መንገድ እንዲገለጥ አድርገዋል ዓመታዊና ወርኃዊ በዓል ሰይመውለታል መልክ ደርሰውለታል #መልክአ_ሕማማት ጽላት ቀርጸውለታል ፤ ቤተ ክርስቲያን አንጸውለታል መስተብቁዕ ደርሰውለታል #መስተብቁዕ_ዘመስቀል
ውዳሴ ደርሰውለታል ፤ ድርሳን ጽፈውለታል #ድርሳነ_መስቀል ክርስቲያኖች በስሙ እንዲጠሩ አድርገዋል ለምሳሌ ብርሃነ መስቀል ፣ ገብረ መስቀል ፣ ወለተ መስቀል፣ ኀይለ መስቀል ፤ወልደ መስቀል ፤ መስቀል ክብራ ወዘተ እያሉ ስመ ክርስትና ተሰይሞለታል ።

ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ከመሠረቷ እስከ ጉልላቷ  ያጌጠችው በመስቀል ነው

#እንኳን_ለብርሃነ_መስቀሉ_በሰላም_አደረሰን_አደረሳችሁ

https://t.me/ethioadbarat

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

24 Sep, 19:46


Lucky Draw አሁንም መክፍሉን ቀጥሎበታል !

ብቸኛው በእድላቹ ወዲያው በ24 ሰዓታት ውስጥ እየከፈለ የሚገኘው 100% ትክክለኛው Airdrop ነው

ለመሳተፍ ከእናንተ የሚጠበቀው ከታች ባለው ሊንክ መጀመር እና የተወሰኑ ሰዎች በመጋበዝ Spin ማድረግ ነው

በመጀመሪያው ዙር ስትጀምሩ 3 እድል ይሰጣቹዋል

አሁኑኑ ጀምሩት በተለያዩ የቴሌግራም አካውንት በተለያዩ አፕ ለየብቻ በማድረግ መስራት ይቻላል ጀምሩት
https://t.me/lucky_gems_official_bot/app?startapp=Hh6qxULrbiMT5A7L5YnG6Rw785QJEo2zfeGabLTCUrEnw

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

24 Sep, 10:27


https://t.me/Ameha_Tewahdo_Zcristos

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

22 Sep, 05:54


Lucky Draw አሁንም መክፍሉን ቀጥሎበታል !

ብቸኛው በእድላቹ ወዲያው በ24 ሰዓታት ውስጥ እየከፈለ የሚገኘው 100% ትክክለኛው Airdrop ነው

ለመሳተፍ ከእናንተ የሚጠበቀው ከታች ባለው ሊንክ መጀመር እና የተወሰኑ ሰዎች በመጋበዝ Spin ማድረግ ነው

በመጀመሪያው ዙር ስትጀምሩ 3 እድል ይሰጣቹዋል

አሁኑኑ ጀምሩት በተለያዩ የቴሌግራም አካውንት በተለያዩ አፕ ለየብቻ በማድረግ መስራት ይቻላል ጀምሩት
https://t.me/lucky_gems_official_bot/app?startapp=Hh6qxULrbiMT5A7L5YnG6Rw785QJEo2zfeGabLTCUrEnw

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

11 Sep, 07:14


#የኢትዮጵያ_አድባራትና_ገዳማት channel አባላት በሙሉ ልበ አምላክ ዳዊት “በቸርነትህ ዓመታትን  ታቀዳጃለህ፤ ምድረ በዳውም ጠልን ይጠግባል” (መዝ.፷፬.፲፩) በማለት እንደ ዘመረው ቸርነቱ ወሰን የሌለው አምላካችን እግዚአብሔር እንኳን   በሰላምና በጤና አሸጋገረን። እጅ ለእጅ ተያይዘን በመተባበር ዘመን ተሻጋሪ ተግባር ለመፈጸም ራሳችንን የምናዘጋጅበት፣ በአንድ አሳብ አቅደን በመሥራት፣  “ዘመኑን ዋጁ” ተብሎ የተነገረንን በተግባር ለመፈጸም የምንዘጋጅበት ዘመን ያድርግልን
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

"የጽድቅን ሥራ የምንሠራበት ከኾነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኃጢኣት የምንሠራበት ከኾነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመትም ክፉና መከራ የመላበት ይኾንብናል፡፡ አዲሱን ዓመት በበጐ ሥራ የምንጀምረው ከኾነ በዓመቱ በምናደርገው ማንኛውም ክንውን ላይ በጐ ተጽዕኖ ያሳድርብናል፡፡"

                 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የምወዳችሁ መንፈሳዊ እህትና ወንድሞቼ በቸርነቱ ስላደረሰን አዲሱ አመት በማስቀደስ አምላካችንን ምስጋና እናቅርብ
        እህት ውንድሞቼ እንኳን አደረሳችሁ እያልኩ በውስጥ መስመር እንኳን አደረሰን እንባባል ውስጥን ያድሳል
አዲሱ አመት አምላክ የውስጣችሁን መሻት ይፈጽምላችሁ ከልቤ እውዳችኃለው

        
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼   መልካም አዲስ አመት        🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

https://t.me/ethioadbarat

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

10 Sep, 13:28


ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ"
🌻 በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ፤ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፣ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ። 🌻መዝ ፷፭ ÷ ፲፩
 
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ🙏

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

06 Sep, 05:05


#በእንተ_ዕለታተ_ጳጉሜን
#ዓረፍተ_ሣህል
6ቱ ዕለታተ ጳጉሜን የሚሰበሰቡበት በውስተ መስኮት አው በቅሩበ መስኮተ ፀሐይ የሚገኝ
በምሥራቅና በምዕራብ ያለ የፀሐይ ምሕዋር/መጓጓዣ ነው::

ገና አምስት መቶ ሰማኒያ ስምንት (588) ስቁረታቶቿ ሳይከፈቱ በሰባት እጅ ክፍለ ብርሃን (የማይዘጋ ቋሚ ክፍለ ብርሃን) የምትታይበት የኬክሮስና የኬንትሮስ መጀመሪያ ነው::

መስኮቷን ሳታልፈው ገና በአድማስና በናጌብ መካከል የምትሄደው መንገድ በምሥራቅ ማልዳ 26 ካልዒት 15 ሣልሲት 30 ራብዒት ይፈጅባታል::

ማታም በምዕራብ ከገባች በኋላ ወደ መስዕ እስከምትመለስ ድረስ ከላይ የጠቀስነውን ያህል ይፈጅባታል::

የጠዋቱና የማታው (26 ካልዒት 15 ሣልሲት 30 ራብዒት) በሁለት ስናባዛው = 52 ካልዒት 31 ሣልሲት ይሆናል።
ይህንን በ30 አባዝተን ውጤቱን አሁንም በ 12 ወራት ውስጥ ያሉትን ዕለታት ስናሰላ
5 ዕለታት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ጊዜ ይገኛል።

እነዚህ ዕለታተ ጳጉሜን ከዓረፍተ ሣህል ከሚገኙ ጊዜያት የተውጣጡ ናቸው።

6ኛይቱ ዕለተ ጳጉሜንም (15 ኬክሮስ) በየ4 ዓመት ተጠራቅማ የምትገኝ ከዚሁ ከፍኖተ ዓረፍተ ሣህል ነው::

በ600 ዓመት 7ኛ ጳጉሜን አለች፤ ይህቺውም ከየዓመት 6 ካልዒት ሆና እየተረፈች በ600 ዓመት (600×6=3600) ካልዒት ትገኛለች፤ ይህንን ወደ ኬክሮስ ቢቀይሩት (3600÷60=60) ኬክሮስ ይሆናል ፤ ይህንንም ወደ ዕለት ቢቀይሩት 1 ዕለት ሆና 7ኛውን ዕለተ ጳጉሜን ታስገኛለች ይህቺውም ከሌላ ያይደለ ከዚሁ ከዓረፍተ ሣህል የተገኘች ናት።

የጳጉሜ ዕለታት ዕለታተ ፈውስ፤ ዕለታተ ምዕራገ ጸሎት ፤ ዕለታተ መድኃኒት ወምርያ  ሆነው መታሰባቸው ከዓረፍተ ሣህል ጋር የሚገናኝ አስደናቂ ምሥጢር ነው!!!

ዓረፍተ ሣህል ማለትም የይቅርታ ማረፊያ ግድግዳ ማለት ሲሆን ፀሐይ ጠዋትና ማታ ያላት ክፍለ ብርሃን የማያቃጥል የማይሰለች እንደሆነ ሁሉ ፀሐየ ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስም ርኁቀ መዓት ብዙኀ ሣህል አምላክ መሆኑን የሚያጠይቅ ምሥጢር ነው!!!

ዘመኑን ዘመነ ሣህል ዘመነ ምሕረት ያድርግልን!
አሜን!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው

https://t.me/ethioadbarat

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

05 Sep, 13:42


+++ሳያቋርጡ የመጸለይ ጥበብ+++

የሰው ልጅ በዚህች ምድር ላይ ሲኖር ለቅጽበትም ቢሆን አእምሮው ሊረሳውና ሊያቋርጠው የማይችለው ነገር ምን እንደሆነ አስባችሁት ታውቃላችሁ? ሰውነቱ በእንቅልፍ ተሸንፎ እንኳን ቢተኛም እያንቀላፋ አስታውሶ የሚያደርገው ክንውን የትኛው እንደሆነ አስተውላችኋል? እንደው አይሆንም እንጂ ሆኖለት ለደቂቃዎች ሰውነቱ ይህንን ተግባር በመርሳት ባያከናውነው ሕልውናው አጠያያቂ ሁኔታ ውስጥ ይወድቃል፡፡ ይህ ሰውነታችን ልምድ ያደረገውና ለአፍታ እንኳን መቋረጥ የማይፈልገው ተግባር አየር ማስገባትና ማስወጣት ወይም መተንፈስ ነው፡፡

ለዚህ ጽሑፍ ይህን የተፈጥሮ እውነት እንደ መነሻ የተጠቀምነው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ጸሎትን እንደ ነፍስ እስትንፋስ ይቆጥሯታል፡፡ አየር ያጠረው ወይም ወደ ሰውነቱ የማያስገባ ሰው በሕይወት የመቆየት ዕድሉ ጠባብ እንደሆነ ፤ እንዲሁ ከጸሎት የተለየች ነፍስም ወደ ሞት መንደር የመውረዷ ነገር የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ ነፍሳችን ሕያዊት የምትሰኘው በአረጋዊ መንፈሳዊ መጽሐፍ ላይ  ‹የነፍሴ ነፍሷ› ተብሎ ከተጠራው መንፈስ ቅዱስ ጋር በጸሎት ትስስርን ስትመሰርት ነው፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙም እንደሚያስተምረው ሰው ከእስትንፋሱ የበለጠ ዘወትር ፈጣሪውን በጸሎት ሊያስታውስ ይገባዋል፡፡

ጸሎት ማለት ምን ማለት ነው? ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ ሊቃውንት በፍትሕ  መንፈሳዊ አንቀጽ 14 ላይ ‹ጸሎትስ ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገራት ነገር ናት› ሲሉ የጸሎትን ትርጉም ይነግሩናል፡፡ እግዚአብሔር የሰው ልጆችን በልዩ ልዩ አይነት መንገድ ሊያናግራቸው ይችላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በራእይ በመገለጥ ወይም ቅዱስ ዳዊት ‹እግዚአብሔር ለሕዝቡ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል› ሲል እንደ ዘመረው በመጽሐፍ በኩል ማናገር ተጠቃሾቹ ናቸው፡፡ የሰው ልጆች ደግሞ ከፈጣሪያቸው ጋር የሚነጋገሩት ጸሎት በተባለ ድልድይ አማካኝነት ያነጋግሩታል፡፡

መተንፈስ ለሥጋዊው አካላችን የዕለት ተዕለት የማይቋረጥ ሥራው እንደሆነ ሁሉ የነፍስ እስትንፋስ የተባለች ጸሎትም ለክርስቲያን የየዕለት መንፈሳዊ ተግባር ናት፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹ሳታቋርጡ ጸልዩ› በማለት የሚመክረን (1ኛ ተሰ 5፡17)፡፡

በሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ሶርያዊው አባ ይስሐቅ (ማር ይስሐቅ) ቅዱሳን ምንም ዓይናቸው በእንቅልፍ ሽፋሽፍት ቢያዝ እንኳን ነፍሳቸው ግን ከእግዚአብሔር ጋር በሚደረግ የማይቋረጥ ንግግር (ጸሎት) ውስጥ ስለምትገኝ ተኝተውም ቢሆን ጸሎትን እንደማያስታጉሉ ይናገራል፡፡ እኛ በዓለም የምንኖር ግን የሥጋ ድካም ስላለብን ቀኑንም ፣ማታውንም በጸሎት የማሳለፍ ብርታቱ የለንም፡፡ በመሆኑም ‹ሳታቋርጡ ጸልዩ› የሚለው የሐዋርያው ትዕዛዝ ይከብድብናል፡፡

በዚህም ምክንያት እንደ እኛ ሥጋ ለባሽ የሆኑ አባቶቻችን ይህን ድካማችንን አይተው ቀኑን ሁሉ በጸሎት ማሳለፍ ባትችሉ እንኳን ቢያንስ በቀን ሰባት ጊዜ እግዚአብሔርን ስለ እውነተኛ ፍርዱ አመስግኑት ሲሉ ሰባት የጸሎት ጊዜያቶች ወስነውልናል (መዝ 119፡164)፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆን ግን አሁንም ከፈጣሪው ጋር ቀኑን ሙሉ በጸሎት የማሳለፍ ጽኑዕ ፍላጎት ላለው ክርስቲያን አባቶች የሚያስተምሩት ሌላ ‹ሳያቋርጡ የመጸለይ ጥበብ› አለ፡፡ ይህንን ጥበብ የምናገኘው ቅዱስ ጰላድዮስ (St. Palladius) የተባለው አባት ባሰባሰበውና የብዙ አባቶችን ዜና ሕይወት ይዞ በሚገኘው ‹መጽሐፈ ገነት› ላይ ነው፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው ፡-

በአንድ ወቅት አባ ሉቅዮስን (Abba Lucius) ለማየት የመጡ ጥቂት መነኮሳት እንዲህ አሉት ‹በእጃችን ምንም አይነት ሥራን አንሠራም፡፡ የቅዱስ ጳውሎስን ትዕዛዝ በማክበር ሳናቋርጥ እንጸልያለን እንጂ!›፡፡ አረጋዊው መነኩሴ አባ ሉቅዮስም ‹አትመገቡም? ወይም አትተኙምን?› ብሎ ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም ‹አዎን! እንተኛለን ፤ እንመገባለን› ሲሉ መለሱ፡፡ አባ ሉቅዮስም ‹ወንድሞቼ ይቅርታ አድርጉልኝና የምትሉትን ነገር (ሳያቋርጡ መጸለይን) እየፈጸማችሁ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ በእጆቼ ሥራን እየሠራሁ እንዴት ሳላቋርጥ እንደምጸልይ አሳያችኋለሁ፡፡ ዘወትር ጠዋት በእግዚአብሔር እርዳታ የዘንባባ ዛፍ ቅሪቶችን እሰበስብና እነርሱን ሽጬ አሥራ ስድስት ሳንቲሞችን አገኛለሁ፡፡ ከዚያም ሁለቱን ሳንቲሞች ከቤቴ በር ደጃፍ ላይ አስቀምጥና በቀረው ምግብ እገዛበታለሁ፡፡ የገዛሁትንም ምግብ ተመግቤ ስተኛ ፤ ያ ከቤቴ ደጃፍ ላይ ሁለቱን ሳንቲሞች የወሰደው ነዳይ ደግሞ ስለ እኔ ይጸልያል፡፡ እንዲህ እያደረግሁ በእግዚአብሔር ረድዔት ሳላቋርጥ እጸልያለሁ› በማለት ልምዱን አካፈላቸው፡፡   

ስለዚህ አንድ ክርስቲያን ከጸሎት ጋር በቀን ማከናወን ያለበትን ሥራ ሥርቶ ከጨረሰ በኋላ አመሻሽ ላይ ከሚያገኘው ትርፍ ለነዳይ ቢመጸውት ብዙውን ሰዓት በእንቅልፍ የሚያሳልፍበትን ሌሊት በምጽዋት እያካካሰ ሳያቋርጥ ሊጸል ይችላል ማለት ነው፡፡

ሳናቋርጥ እንጸልይ!!!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

https://t.me/ethioadbarat

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

03 Sep, 19:54


#መከራ ልመዱ

አባቶቻችን ቅዱሳን ሊቃውንት ሲተረጉሙ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በልብ መታሰቡ በቃል መነገሩ ከፍ ይበልና ማቴ ምዕ 14 ላይ ስታነቡ ጌታ ምን አለ አምስት እንጀራ አበርክቶ ህዝቡን ከመገበ በኋላ ቅዱሳን ሀዋርያትን እንዲህ የሚል ትዕዛዝ አዘዛቸዉ ህዝቡን እስከማሰናብት ድረስ እናንተ ተሻግራችሁ ቆዩኝ አላቸዉ።

በብዙ መንገድ አበዉ ይተረጉሙታል ተሻግራችሁ ቆዩኝ ማለቱ እናንተ በልቶ ሀጅ አይደላችሁም ማለቱ ነዉ ሀይማኖታችሁ ለእንጀራ አይደለም ይኀዉ ይሄ የመጣው በልቶ ሀጅ ነው በልቷል ይሂድ እናንተ ግን ከመብል ባሻገር ክብር ያላችሁ ሰዎች ናችሁ።

የናንተ ማዶ ያለ ክብር አላችሁ ተሻግራችሁ ተመልከቱ ከመብል ባሻገር፣ከልብስ ባሻገር፣ከሹመት ባሻገር፣ከዝና ባሻገር...የሰማይ ክብር አላችሁ እንደዛ ኑሩ ማለቱ ነበር።

ባህሩን ተሻግራችሁ ቆዩኝ አለና ሊሻገሩ ሲጀምሩ ሞገድ ተነሳ እመጣለሁ ብሏቸዋል ቀረ ማዕበሉ ግልብጥ ግልብጥ አለ የዚያን ጊዜ መርከቡ እስኪዳፈን ድረስ ኋላ በአራተኛው ሰዓተ ሌሊት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይግባውና በባህሩ ላይ ረመድ ረመድ እያለ መጣ።

#ኤራቅሊስ የተባለ ሊቅ

**ሲያስረዳ እግሮቹ ሳይረጥቡ በባህር ላይ ይራመድ ነበር ይላል እግሮቹ ሳይርሱ ሊቃውንት #አበው ደግሞ ሲናገሩ እንዲያውም ከተአምራቱ የተነሳ አንዱን እርምጃ ሲነቅለው በባህሩ ላይ አብዋራ ብን ብን ይል ነበር።

የባህር ጌታዋ ነኝ ማለቱ ነው ባህርን የፈጠርኩት እኔ ነኝ ባህርን የፈጠርኩት እኔ ነኝ ባህርን እኔ ስለፈጠርኩት በባህር ካለው የተነሳ አትደንግጡ የማዛት እኔ ነኝ ባህር እኮ አይን አላት አምላኳን የምታይበት

ቅዱስ ያሬድ
ባህር ክርስቶስን አየችው ሰገደችለት ይላል በምን አይኗ ነዉ?ፈጣሪዋ መሆኑን ታውቀዋለች ፀጥ ትልለታለች።

ቅዱስ ቄርሎስ

ደግሞ ምን ይላል "ባህርኒ ትገብር ለድንግል ምጢዋ ዘባና ለሐመር" ባህርም የድንግል ማርያምን በዓል ታከብራለች ይላል እንዴት ቢሉ? መርከቦች ወደ ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ደሴት ሲሄዱ በሰላም እንዲሄዱ ባህርም ሳታውክ ለመርከቦች በመመየት በዓል ታከብራለች ይላል ለምን አምላክ በድንግል ማርያም አድሮ ስላለ በዚያ ባህር ክርስቶስን ታየዋለች ከዛ በኃላ መጣ ማዕበሉን ፀጥ አጀረገና አይዟችሁ እኔ ነኝ ብሎ ይዟቸው ተሻገረ እስከዚያው ታዲያ ለምን ዝም አለ? 
መከራ ልመዱ ማለቱ ነዉ!!!

መከራ ልመዱ ለማለት ጌታ ትቶዋቸው ጥቂት ቆየ ይላል አሁንም ማሰብ ያለብን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ትቷት አይደለም መከራ የክርስትና አካሉ ስለሆነ ነዉ።

https://t.me/ethioadbarat

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

22 Aug, 06:00


"የህይወት እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፤ እርገትሽ ሳይሆን ወደ መቃብር መውረድሽ ይገርመኛል፤ የብርሃን እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትወጂኛለሽን? ብየ አልጠይቅሽም ፍቅርን የወለድሽ አንቺ ለአለሙ ሁሉ ፍቅርሽ የበዛ ነውና፤ አትናፍቂኝምን? ብየም አልጠይቅሽም ዘወትር እኔን ለመጠበቅ ከጎኔ እንደማትለይ አውቃለሁኝና፤ ሆኖም እመቤቴ ሆይ፦ እንደ ቶማስ አይሽ ዘንድ በእጅጉ እጓጓለሁ የቶማስ ንፅህናና ቅድስና ግን የለኝም እንደ ዮሃንስ ከጎንሽ ልሆን እጓጓለሁ የዮሃንስ ፀጋ ግን የለኝም።

እናቴ ሆይ፦ እንደ ኤልሳዕ የልቦናዬ አይን በርቶ ሰማያዊ ክብርሽን ላይ አልተቻለኝምና አዝናለሁ ኤልሳዕ በፀሎት ሃይል የግያዝን አይን እንዳበራ አንቺም አይኔን ታበሪልኝ ዘንድ ሃይልሽን በእኔ ላይ አበርቺ፡፡

ድንግል ሆይ፦ ይህን የምል የእምነት ማረጋገጫ ፈልጌ አይደለም በልጅሽ መሰረትነት የታነፅኩኝ በልጅሽ ስምም የተጠመቅኩኝ ነኝና፤ ነገር ግን ስለምትናፍቂኝ ይህን አልኩኝ ስለዚህም ነይ ነይ እምየ ማርያም እያልኩኝ እንደ እናቶቼም እለምንሻለሁ፡፡ የብርሃን ልብስሽን ለብሰሽ ነይ የክብር አክሊልሽን ደፍተሽ ነይ አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ነይ እናይሽ ዘንድ ነይ፡፡"

https://t.me/ethioadbarat

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

22 Aug, 05:39


https://youtu.be/JocRLzIDaGU?si=Le3M70zN4DgA6cnG

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

12 Aug, 04:51


" ድንግል ሆይ ከምልጃሽ በቀር ሊጠብቀኝ የሚችል እንደሌለ አወኩኝ ያለ ማህጸንሽም ፍሬ ሊራራልኝ የሚችል እንደሌለ ይህንንም አውቄ ወደ አንቺ ተጠጋሁ በልጅሽም አመንኩ እርሱንም አመለኩ ቸርነቱንም ተስፋ አደረኩ "


አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

@ethioadbarat
@ethioadbarat

የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ

10 Aug, 05:43


ሱባዔ

ሱባዔ ምንድን ነው ?
ሱባኤ በሰዋሰው ትርጉሙ "ሰባት"ማለት ሲሆን በመንፈስ አተረጋጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከ ዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪየ ጋር እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው ፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ ፦ ፈጣሪ አለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፋጥረትን ከመፋጠር ማረፋ ፥ለጸሎት የሚተጉ ምዕመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥር ፋጹምነት ያመለክታል ፡፡ (ዘፍ 2፥2 , መዝ 118፥164) አንድ ሰው 7 ቀናት ቢጾም "አንድ ሱባኤ ጾመ" ይባላል ፡፡

ሱባኤ መቼ ተጀመረ?
የተጀመረው ከውድቀት በሓላ በመጀመርያው ሰው በአዳም ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት እንዳስተማሩት የቤተ ክርስቲያናችን መዛግብት ያስረዳሉ በምላሹም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ስጋን ለብሼ ከ 5 ቀን ተኩል በኋላ አድንሃለሁ የሚለውን ቃል ኪዳን የሰማው ሱባኤ በመግባቱ ነው፡፡

ሱባዔ ለምን ይጠቅማል?
የሰው ልጅ ሓጢአት በሚስማማው የሥጋ ሰውነቱ ዘወትር ፈጣሪውን ይበድላል፡፡ በፈፀመው በደል ህሊናው ይወቅሰዋል ይጸጸታል፡፡ በመጀመርያ ደፋሮ በሰራው ሀጥያት በኋላ ይደነግጣል ይህ በማንኛውም ሰብአዊ ፋጥረት ኀሊና ውስጥ የሚፈራረቅ ክስተት ነው ፡፡ በዚህ ግዜ የፈጣሪውን ይቅርታ ለማግኝት ያስባል ይተክዛል፡፡ ሰው በደፋርነቱ የኃያሉን አምላክ ትእዛዝ ተላልፎ አለም ሲያስጨንቀው  ሸክሙን የሚያቃልልበትና የሚያስወግድበት  መንፈሳዊ ጥበብ ከቸሩ ፈጣሪ ተሰጥቶታል፡፡ ይህውም በጥቂት ድካም ሥጋ ያልተወሰነ ጸጋ እግዚአብሔር የሚያገኝበት ሥርዓት ሱባዔ ነው፡፡

1- እግዚአብሔርን ለመማጸን፦
ማንኛውም ሰው ሱባኤ ሲገባ በቁርጥ ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማፅኖ ሊኖረው ይገባል፡፡ ምንም የምንጠይቀው ( የምንማፀነው) ነገር ሳይኖር ሱባዔ ብንገባ የምናገኝው መልስ አይኖርም፡፡ ስለዚህ ሱባኤ ከመግባታችን በፊት፦ ሱባዔ የምንገባው ለምንድን ነው ?  በማለት እራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል ፡፡

2- የቅዱሳንን በረከት ለመሳተፍ
ቅዱሳን አባቶችና እናቶች የተጋደሉትን ተጋድሎ በማዘከር ቃል ኪዳን በተሰጣቸው ገዳማትና አድባራት የሚገባ ሱባኤ የቅዱሳን በረከት ተካፋይ ያደርጋል፡፡ በጾመ ነብያት የነብያትን፣ በጾመ ሀዋርያት የሀዋርያትን፣ በጾመ ፋልሰታ የእመቤታችንን በረከት ለመሳተፋ ሱባኤ መግባት የነበረ ነው፡፡

የሱባዔ አይነቶች፦
1- የግል ሱባኤ ( ዝግ ሱባዔ)፦
አንድ ሰው ብቻውን አመች ቦታ ማንም ሳያየው በግሉ የጸሎት በአቱን ዘግቶ በሰቂለ ኀሊና ሆኖ ፈጣሪው ብቻ እንዲያየው በኀቡዕ የሚፈፅመው ሱባኤ ነው ፡፡

2- የማህበር ሱባዔ፦
ካህናት ምዕመናን ወንዶች ሴቶች ሽማግሌወች ፤ወጣቶች ፤በአንድ ሆነው በቤተ ክርስትያንና አመች በሆኑ ቦታወች ሁሉ ተሰብስበው የሚገብት ሱባዔ ነው፡፡

3- የአዋጅ ሱባዔ፦
በሀገር  ላይ ድንገተኛ አደጋ ፤ አባር ቸነፈር ጦርነት ሲነሳ እንዲሁም በማህበረ ምዕመናን ላይ አስጊ የሆነ መቅሰፋት ሲከሰት እግዚአብሔር መዓቱን በምህረት ቁጣውን በትዕግስት እንዲመልስ የሚያዝ የሱባዔ አይነት ነው፡፡

ለሱባዔ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅት፦
ሱባኤ ከመግባታችንም ሆነ ከገባን ግዜ እንዲሁም ከጨረስን በኋላ ምእመናን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይገባናል፡፡

➢ ሱባኤ ከመግባት አስቀድሞ
በመጀመርያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል ፡፡
፪ ሱባኤ ለመግባት የወሰንበትን ምክንያት ከለየን በኋላ ምክንያታችንን ይዘን የንስሃ አባታችንን ማማከር ያስፈልጋል፡፡
፫ ለምን ያህል ቀናት መቆየት እንዳለብን መወሰን ያስፈልጋል ፡፡ሱባኤ ከዚህ እስከዚህ እቆያለሁ ብለን ዕቅድ የምንይዝበት ነው፡፡
፬ ወቅትና ቦታ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችን በአብዛሀኛው ግዜ ሱባዔ የሚገባው በአጽዋማት ወቅት በመሆኑ ይህንን መለየት ነው፡፡ ምክንያቱም በጾም ወቅት ብዙ አባቶች ጸሎት የሚይዙበት ስለሆነ ፀሎታችን ከእነርሱ ጋር አብሮ ያርግልናልና ነው፡፡ እዚህ ላይ በማንኛውም ግዜ ሱባኤ አይያዝም ለማለት አይደለም በማንኛውም ግዜ ፈተና ያጋጠመው ሰው ሱባዔ ሊይዝ ይችላል፡፡

➢ በሱባዔ ግዜ 
ሀ. በጸሎት ሰአት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ምስራቅ መልሶ መቆም ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰቂለ ህሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል፡፡
ለ . በቅደም ተከተል መፀለይ ይገባል በመጀመርያ አአተብ ከሚለው ተጀምሮ አቡነ ዘበሰማያትን ጠቅሶ ጸሎተ ሀይማኖትን መጨረስ ፡፡ሰግዱ እና ስለ መስቀል በሚያነሳው ላይ እየሰገዱና እያማተቡ መጸለይ ፡፡ በማስቀጠል አቡነ ዘበሰማያት ፤መዝሙረ ዳዊት ውዳሴ ማርያም ሌሎችንም ማስከተል ከዚያ 41 ግዜ ኪራላይሶ ይባላል ፡፡
ሐ.  በሱባዔ ግዜ ከተሐራሚው የሚጠበቀው ነገር ሐጢአቱን እያሰበ ማዘን ማልቀስ ለእያንዳንዱ በደል ማልቀስ ማዘን ይገባዋል ፡፡
መ.  በመጨረሻም ሱባዔ የገባው ሰው ሱበዔውን ሳይጨርስ ወይም አቋርጦ ከማንኛውም ሰው ጋር ፈፅሞ መገናኝት የለበትም ፡፡

3- ከሱባዔ በኋላ
ላቀረብነው ተማፅኖ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን ነገር  መጠበቅ ይኖርብናል። ሱባዔ የገባ ሰው ሁሉ ራዕይ ላያይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልስ አሰጣጥ ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡ ከሱባዔ በኋላ መጀመሪያ የምናገኝው የህሊና ሰላም ነው፡፡ ይህ ትልቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱባኤ ገብተን ያሰብነውን  ካላገኝን ዳግመኛ ተዘጋጅተን እስከ መጨረሻው ሰዓት በመማፀን መጽናት ይኖርብናል፡፡፡

መጭው ጾመ ፋልሰታ (የመቤታችን ጾም ) በመባል የሚታወቀው እና ቤተ ክርስቲያናችን አበይት አጽዋማት ብላ ከደነገገቻቸው ወስጥ አንዱ ነው ፡፡ በዚህ ወራት ብዙዎቹ አባቶቻችንና እናቶቻችን በረከተ ስጋ ወነፍስ ያገኙበት የበረከት ጾም ነው እኛም ቢቻለን በሱባኤ ባይቻለን አቅማችን የፈቀደውን እየጾምን አምላካችንን መጠየቅ እንዲሁም እመቤታችን በምልጃዋ  ታስበን ዘንድ መማፅን ያስፈልገናል ፡፡

https://t.me/ethioadbarat

23,437

subscribers

285

photos

1

videos