የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ(Wolaita Sodo Agricultural College)

@wolaitasodoagricollege


የግብርና ሙያዎች ቤት

የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ(Wolaita Sodo Agricultural College)

21 Oct, 18:38


ሚንስቴሩ የ2017 ዓ/ም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አደረገ።

የኢፌዴሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡

ለተፈጠሮና ማህበራዊ ሳይንስ የተቀመጡ መቁረጫ ነጥቦች ከታች በምስሎች ተቀምጠዋል።

የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ(Wolaita Sodo Agricultural College)

05 Oct, 18:12


በክልሉ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጄንሲ መሪነት በተለያዩ የሙያ ደረጃዎችና መስመሮች በኮሌጃችን ሲካሄድ የቆየው የምዘና ሂደት በሰላምና በስኬት መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጄንሲ መሪነት በተለያዩ የሙያ ደረጃዎችና መስመሮች ከቀን 23/01/17 ዓ/ም እስከ 25/01/17 ዓ/ም ድረስ ሲካሄድ የቆየው የሙያ ብቃት ምዘና ሂደት በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን የኮሌጃችን ትምህርት ሥልጠና ዘርፍ ኃላፊና ም/ዲን አቶ ታሪኩ ጨመረ ገልጸዋል፡፡

አቶ ታሪኩ አክለውም፣ የምዘናው ሂደት በሰላምና በሰኬት እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን ለተወጡ የኤጄንሲው ማኔጅመንትና መዛኞች፣ የኮሌጃችን ት/ት ክፍል ኃላፊዎች፣የሙያ ብቃት ምዘና ኮሚቴዎች፣የኮምፒውተር ባለሙያዎችና ሌሎችን አመስግነዋል፡፡

የኮሌጃችን ሙያ ብቃት ምዘና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ መ/ር በለጠ ቦቴ በበኩላቸው፣ ምዘናው የተሰጠው በሙያ ደረጃ አንድ እስከ ዓራት በሰብል ልማት፣ በተፈጥሮ ሀብትና እንስሳት እርባታ እንዲሁም በአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት መሰረት በሆሊስቲክ ሲኦሲ በሰብል ልማት፣እንስሳት እርባታ፣ በተፈጥሮ ሀብት፣እንስሳት ጤና፣ በመሰኖና ዲሬይኔጅና በሕብረት ሥራ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት የሙያ መስመሮች መሆኑን አብራርተዋል፡፡

መ/ር በለጠ አያይዘውም ፣ በሦስቱ የሙያ ዘርፎች ከደረጃ አንድ እስከ ዓራት የተመዘኑትን 305(ሦስት መቶ አምስት) እና በስድስቱ የሙያ ዘርፎች በሆሊስቲክ ሲኦሲ የተመዘኑትን 376(ሦስት ሰባ ስድስት) ተመዛኞችን ጨምሮ በአጠቃላይ 681(ስድስት መቶ ሰማኒያ አንድ) ተመዛኞች መመዘናቸውን አስረድተዋል፡፡

በምዘናውም በኮሌጃችን ተከታታይ ትምህርት መርሐ-ግብር ሥልጠናቸውን ያጠናቀቁ የሣምንቱ መጨረሻ ቀናትና የክረምት ተመራቂ ተማሪዎችን ጨምሮ የግል ተመዛኞች መመዘናቸውን በመጥቀስ፤ የክረምት ተማሪዎቹ የተመዘኑት በሰብል ልማትና በተፈጥሮ ሀብት በሙያ ደረጃ ሦስት እንደሆነ አመላክተዋል፡፡