መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

@spritualbook12


ይህ ቻናል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት በተለያየ ዘመን የተጻፉ መጽሐፍት እና ገድላት የሚያገኙበት ነው።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

22 Oct, 03:13


እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል አደረሰን አደረሳችሁ ።
በመጽሐፈ ስንክሳርም ተመዝግቦ እንደምናኘው ቅዱስ ሚካኤል በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠርቶለታል፤ እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙም በጊዜው እንዲወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲያደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲያደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልዳልና፡፡ (ስንክሳር ኅዳር ፲፪)።
    ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን መላእክት እኛን እንደሚጠብቁና እንደሚራዱ እንዲሁም ስለእኛ በፊቱ አንደሚቆሙ ሲያስተምረን ‹‹ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁል ጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ›› ብሎናል፡፡ (ማቴ.፲፰፥፲) እኛን ይጠብቁ ዘንድ የተሰጡን ቅዱሳን መላእክት ስለእኛ እንዲህ የሚቆረቆሩና ስለመዳናችን የሚተጉ ከሆነ በቅድስናው ልቆ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ሚካኤል እንዴት ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ይበልጥ አይቆም? (ሉቃ.፲፫፥፮-፱) እንዴትስ በተሰጠው ሥልጣንና ኃይል አይረዳን? (መዝ.፴፫፥፪) እርሱ ‹‹ስለሕዝብህ ልጆች የሚቆመው›› መባሉም እኛን በጸሎቱና በተራዳኢነቱ የጽድቅ ሕይወታችንን በሚገባ እንድናከናውን እንደሚራዳን የሚያሳይ ኃይለ ቃል ነው፡፡

የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ጸሎቱና በረከቱ በእኛ ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን፤ አሜን፡፡

መልካም ቀን

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

19 Oct, 04:18


ታላቁ ቅርሳችን ቅዱስ ላሊበላ እና የኢትዮጵያ ሥልጣኔ በታሪከ ነገሥት መጽሐፍ።

"ኢትዮጵያ የሚገርሙ እና የሚያስደምሙ ታሪካዊ እሴቶች ያላት ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም ዓቀፍ አደባባይ ገንና እንድትታይ ካደረጓት ሁለግብ ሀብቶቿ በግንባር ቀደምነት የላስታ የሮሐ አድባራት ይጠቀሳሉ፡፡ ላሊበላ መንፈሳዊነት ከዓለማዊነት ፍንትው ብሎ ተለይቶ ረቆ የሚታይበት መካነ መንፈስ ነው፡፡

በዚያ ዘመን ከኢትዮጵያ አልፎ በሌላው ዓለም ያልነበረው እና አቻ የሌለው የላሊበላ ዘመን ታሪክ ድንቅ ሥራ ብዙ ሊባልለት የሚችል ቢኾንም ብዙ እንዳይባልለት አንዳች አፍአዊም ኾነ ውስጣዊ ተፅዕኖ የነበረበት ይመስላል፡፡ ያ ዘመን በተለይ አውሮጳ 1500-1000ዓ ም ከዚያም ባለፈ የጨለማ ዘመን በሚሉት ኹኔታ ቢገኙም የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እና ኢትዮጵያ ግን ከሀገራዊ አንድነቱ ባሻገር ድንቅ የኪነ ሕንፃ ባለቤት ነበሩ:: ይህን ዐይነት ሥራ አይደለም አፍሪካ 1500 እና 400 ዓመታት በኋላ ዘመነ ዳግም ልደት/ renaissance ተብሎ የተነሣው ምድረ አውሮጳም ማሳየት የቻለ አይመስልም፡፡ ዛሬም ቢኾን፡፡

የዘመነ ላሊበላ ሥልጣኔን ስንመለከተው ሀይማኖታዊ ብቻ አይደለም:: አጠቃላይ የኾነ የማንነት ሥልጣኔም ጭምር እንጅ፡፡ እንደውም ከአክሱም ድቀት በኋላ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ክብር የተመለሰበት ጅማሮ ነው የቅዱስ ላሊበላ ዘመን። ምንም እንኳን ዓለም ዐቀፉ ኹኔታ ተስማሚ ባይኾንም ነገሥተ ላስታ ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ግብጽን ጨምሮ ከአህጉረ ባሕረ ሜድትራንያን ጋር ግንኙነት ነበራቸው፡፡ እራሳቸውንም በማኅበራዊው እና ሥልጣኔው ተወዳዳሪ ማድረጋቸውን ገድላቱም ኾነ ታሪክ ነገሥቱ ይጠቁማሉ፡፡"

ታሪከ ነገሥት ገጽ146_148

ይህ መጽሐፍ ከገበያ ጠፍቶ የነበረ ቢሆንም ዳግም ለሕትመት በቅቷል ።ከገበያ መልሶ ሳይጠፋ ወደ መጽሐፍት መደርደሪያችሁ ታስገቡት ዘንድ ምክሬ ነው።

ዋና አከፋፋይ ሀሁ መጽሐፍት መደብር ።

አድራሻ አራት ኪሎ አብርሆት ቤተ መጽሐፍት ጎን
ስ.ቁ 0911006705
0924408461

ይህ በፌስቡክ መንደር መገኛችን ነው።
https://www.facebook.com/groups/325620972980210/

በቅርቡ ከሕትመት የወጣውን ታረከ ነገሥት መጽሐፍ ቴሌግራም t.me/spritual23 በመጠቀም መዘዝ ይችላሉ።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

18 Oct, 11:34


የመጽሐፍ ጥቆማ:- ታሪከ ነገሥት
ጽሐፊ መምህር ደሴ ቀለብ
የገጽ ብዛት 563
የሸፈን ዋጋው :-860
ይዘት ከሚኒልክ 1ኛ እስከ ሚኒልክ 2 የነገሥታትን ታሪክ የያዘ ።

ሐይቅ እስጢፋኖስ

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ሐይቅ እስጢፋኖስ ።
ሐይቅ እስጢፋኖስ በጥንቱ መልክዐ ምድር የአምሐራና የአንጎት መገናኝ ላይ የነበረ ገዳም ነው።አመሠራረቱ ከአቡነ ኢየሱስ ሞዓ መምጣት 300 ዓመታት ቀድሞ ነው።

ሐይቅ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የተሠራው በ842 ዓ.ም.ነው።ሐይቅ እስጢፋኖስ በቅዱሳት መጻሕፍት፣የጽሕፈት ትምህርትና በማኅበራዊ የምንኩና ሕይወትና በተግባረ ዕድ የተደራጀ ነበር።

በሐይቅ እስጢፋኖስ ከጋሳጫ፣ከሳይንት፣ከበጌምድርና ከሸዋ በሚመጡ ተማሪዎች ከ800 በላይ መነኮሳት በትምህርተ ሀይማኖት ሰልጥነው፣በንቡረ ዕድነትማዕረግ ተመርቀው በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ተሰማርተዋል።ለምሳሌ፦አቡነ ኂሩት አምላክ ዘጣና ቂርቆስ እስጢፋኖስ፣አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ፣አቡነ ጸሎተ ሚካኤል ዘደብረ ጎል፣አቡነ አሮን ፣አባ ሠረቀ ብርሃን፣አባ ዘኢየሱስ፣የደብረ ሊባኖስ ገዳም መስራች አቡነ ተክለሃይማኖት ይጠቀሳሉ።
" አባ ኢየሱስ ሞዐ የተመሠረተዉ እና በመካከለኛዉ ዘመን የሀገራችን የመጀመሪያዉ” ዩኒቨርሲቲ ተብሎ የሚታወቀዉ የሐይቅ ገዳም ለባህል እና ታሪክ መጠበቅ ታላቅ ባለውለታ ነዉ። ገዳሙ እና አካባቢዉ በተለይም የሰሎሞናውያኑ እና የታላላቅ አበው የዕውቀት ምንጭ ሆኖ አገልግሏል:: አቡነ ተክለ ሀይማኖት እና ይኩኖ አምላክም የተማሩት በዚሁ ገዳም ሲኾን በኋላ ተመልሰዉ ቢመጡም በመጀመሪያዉ የቆይታ ዘመናቸዉ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሐይቅ ከአባ ኢየሱስ ሞዐ ገዳም/ ዩኒቨርሲቲ ወደ ዘጠኝ/ዐሥር ዓመት ተቀምጠዋል።

በዚያም መጻሕፍትን የቤተ ክርስቲያን ታሪክን እና የገዳም ሥርዐት ዕውቀትን እንዳሰፉ ፕሮፌስር ታደሰ ታምራት ገልጸዋል፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን እና ይኩኖ አምላክን ያስተማሩት የአባ ኢየሱስ ሞዐ ገዳም/ ዩኒቨርሲቲ ቤተ ትምህርት ሐይቅ ብዙ ሊቃውንትን ያስገኘ ገዳም ሲሆን በኋላ ዘመንም አባ ጊዮርጊስን የመሰሉ አባት ተገኝተወብታል፡፡ እንደ ሌሎች አባቶች ኹሉ አቡነ ተክለ ሀይማኖትም የራሳቸዉን ገዳም ደብረ አስቦን መሥርተዋል፡፡"

ታሪከ ነገሥት ገጽ 152

ይህ መጽሐፍ ለረጅም ጊዜ ከገበያ ጠፍቶ የነበረ ቢሆንም ሁልጊዜ የጠፉና የጥንት መጽሐፍትን በማሳተምና በማከፋፈል ለአንባቢያን በማቅርብ የሚታወቀው ሀሁ መጽሐፍት መደብር ጥቂት ኮፒዮችን አሳትሞ ይዞልን ቀርቧል ። መጽሐፉ በዋናነት በሀሁ መጽሐፍት መደብር ቢከፉፈልም በሁሉም መጽሐፍት ቤቶች ያገኙታል።

ሀሁ_መጽሐፍት_መደብር
አድራሻ ቁ.1 አራት ኪሎ አብርሆት ጎን
2 ሜክሲኮ ደብረወርቅ ሕንጻ
ስ.ቁ 0911006705/0924408461

ይህ በፌስቡክ መንደር መገኛችን ነው።
https://www.facebook.com/groups/325620972980210/

በቅርብ ለሕትመት የበቃውን ታረከ ነገሥት መጽሐፍና ሌሎችንም መጽሐፍ ለማዘዝ ይህን ቴሌግራም t.me/spritual23 በመጠቀም ማዘዝ ይችላሉ። በየትኛውም ዓለም ያሉ አንባቢያን መጽሐፍትን ቢያዙ እንልካለን ።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

14 Oct, 16:50


እንኳን ለአባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

ምድረ_ከብድ_አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ _ገዳም

ምድረ ከብድ  ደቡብ ውስጥ ጎራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ነው የሚገኘው፡፡ ምድረ ከብድ ትርጉሙ ከባድ ስፍራ፣ ጽኑ ቦታ፣ ከፍ ያለ በረከት የሚገኝበት ማለት እንደሆነ የገዳሙ አባቶች ይናገራሉ፡፡

ከአዲስ አበባ 122 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ከጢያ ትክል ድንጋዮች አቅራቢያ የሚገኘው ምድረ ከብድ በንጉሥ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት  በራሳቸው በጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የተመሰረተ ገዳም ነው፡፡ ጻድቁ በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ ኖረው ያረፉትም በዚሁ ገዳም ነው፡፡

በግራኝ  ጦርነት የቃጠሎ ጉዳት ደርሶበት ነበር፡፡ የሸዋው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ናቸው በድጋሜ ያሰሩት፡፡ አሁን የምናየውን ህንጻ ቤተክርስቲያን በሳር ክዳን ያሰሩት ፊታውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ ሲሆኑ ወደ ቆርቆሮ ክዳን እንዲቀየር ያደረጉት ደግሞ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ናቸው፡፡

ቦታቸው ለመርገጥ ያብቃን አሜን።

1,424

subscribers

1,464

photos

11

videos