አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

@snetsehuf


✔️📚ማንበብ ያሻግራል ❗️❗️❗️
በዚህ ቻናል እናንተን የሚመጥኑ የተለያዩ ግጥሞችን ፣ አጫጭር ና መሳጭ ታሪኮችን ታገኛላችሁ። እናንብብ ፤ በማንበባችን እናተርፋለን እንጂ ፤ ከቶ አንከስርም። @snetsehuf

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

02 Oct, 04:03


የአነቃቂ ንግግር ዲስኩር አቅራቢ እንዲህ ሲል ለተሰበሰበው ህዝብ ንግግር አደረገ፣

"የህይወቴ ምርጥ ጊዜያት ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ያሳለፍኳቸው ጊዜዎች ናቸው"

ይህንን ሲናገር ህዝቡ በድንጋጤ  ክው አለ። ተናጋሪው የህዝቡን ስሜት ከተረዳ በኋላ እንዲህ ሲል ጨመረበት ፣

"ያቺ ሴት እናቴ ናት! " ብሎ ሲናገር ህዝቡ በፉጨትና በጭብጨባ አቀለጠው።

ይህንን ንግግር ያዳመጠው ሌላው ሰው ቤቱ ሄዶ ሊሞክረው ፈለገና ራት ላይ ለሚስቱ "የህይወቴ ምርጥ ጊዜያት ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ያሳለፍኳቸው ጊዜዎች ናቸው...." ብሎ ቀጣዩን ሃሳብ ከመናገሩ በፊት ሚስቱ በያዘችው የጋለ መጥበሻ አናቱን ብላው አሁን ሆስፒታል ይገኛል።

ባሻዬ!

1.የአንዳንድ አነቃቂዎችን ንግግር እንደ አደገኛ ጨዋታ በቤት ውስጥ አትሞክረው፣

2. copy ያደረግኸውን ንግግር በአግባቡ paste ካላደረከው አደጋው የከፋ ነው።

በአጭሩ Don't copy if you cannot paste.
@snetsehuf

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

02 Oct, 03:53


ገላጣ
(በእውቀቱ ስዩም)

ዛሬ  የተከበረውን የዓለም አቀፍ ራሰ በራዎች ቀን ሳልዘክር ወደ ምኝታየ ብሄድ የሶቅራጥስ አጽም ይወጋኛል፤

ሊቁ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ  “በራሕ”የሚለውን ቃል ሲተረጉሙት-“ በራ፥ መላጣ፥ ራሰ ገላጣ፥ ከቦታው የታጣ፥ የራሱ ቁርበት፥ ሳንባና ጉበት የሚመስል “ ይላሉ (መጽሀፈ ስዋሰው ወግስ ፥ ገጽ 287፤ በትርጉሙ  ውስጥ ያሉትን አሉታዊ  ቃላት ብዛት ለተመለከተ  አለቃ ባለ ሙሉ ጠጉር እንደሆኑ መገመት አያቅተውም፤

አለቃ “ራሰ ገላጣ “  ቢሆኑ ኖሮ “ራሰ በራ ” የሚለውን  ሲተረጉሙ “ራሱ የበራለት፤ ታጥቦ የተወለወለ የንጉስ ብርሌ የመሰለ፥  መላጣ፥ ከፎረፎርና  ከቅማል ስጋት ነጻ የወጣ “ብለው ሊተረጉሙት ይችሉ ነበር፤

በታሪካችን ትልልቅ ራሰ በራ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ነበሩ፤  ከጌቶች መካከል ብንጠቅስ፥ ራስ ስኡል ሚካኤል፥ አጤ ምኒልክ፥ ራስ ዳርጌ፥  መለስ ዜናዊ፥ ከደራሲ ፥ሀዲስ አለማየሁ፥ ጃርሶ ኪሩቤል ሞትባይኖር፥ መንግስቱ ለማ፥ ሊጠቀሱ ይችላሉ፤  ( ሎሬት ጸጋየ ገብረመድህን ራሰ በራ ነው ወይስ የተሸጋሸገ ጎፈሬ ነው የሚለው በታሪክ ሲያከራክር ይኖራል )

“ለኔ እየሰጠችኝ ደረቁን እንጀራ
እስዋ በነካካው በራሰው ልትበላ"

የሚለውን ጥንታዊ ውስጠ ወይራ  ዘፈን መናሻ አድርገን ብንናገር ፥ ሴቶች ከሚያበጥር ይልቅ የሚወለውል ወንድ የበለጠ እንደሚማርካቸው መረዳት አያቅትም፤

ስለ ጸጉር ጨዋታ በተነሳ ቁጥር ፈገግ የምታሰኝኝ ድምጻዊ  አብነት አጎናፍር የተናገራት ናት፤ አብነት እንዲህ አለ፤

“   ከጥቂት ጊዜ በፊት  ጸጉር ላስተክል ቱርክ ሄጄ ፤ ጸጉር የሚተከለው ሰውየ መላጣ መሆኑን ሳይ ትቸው ተመለስኩ"🙂
@snetsehuf

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

23 Sep, 08:35


https://t.me/major/start?startapp=392137374

👑 Join me in @Major game and earn $MAJOR token soon!
⭐️ 750 rating bonus for you.
⭐️ 1000 rating bonus if you are Premium.






አሁን ላይ ካሉት ኤርድሮፖች ውስጥ በጣም አሪፍ የሚባለው ነው ያልጀመራችሁ ቶሎ ጀምሩ https://t.me/major/start?startapp=392137374

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

14 Sep, 04:06


ማን ያውቃል
(በእውቀቱ ስዩም)

የመስቀል ወፍና የአደይ አበባ
ቀጠሮ እንዳላቸው መስከረም ሲጠባ
ማን ያውቃል?

(ገጣሚ መንግስቱ ለማ)

ከሁሉ አስቀድሜ፥  እጅግ የሚያምር የበአል ስርአትን ለፈጠሩልን ካህናት አባቶች እና እናቶች ምስጋና አደርሳለሁ፤ ላይን ውብ የሆነውን አበባ፥ ለጆሮ የሚጥመውን  ማህሌት፤ ለአፍንጫ ጣፋጭ የሆነውን እጣን እና የሚያውድ ሳር ሁሉ  አግኝተን  የምናጣጥመው በበአል ነው፤
 
ይገርማል!

“የማይታረድበት አመትባል  እና  ጋቢ የማይለብስ ባል ግርማ ሞገስ የላቸውም  “ ይል ነበር ጋሽ አሽኔ፥ የሰፈራችን ሸማኔ  -፥የጋቢው ምርት የጠበቀውን ያክል አልሄድለት ሲል፤

  ለዚያ ነው ትናንት እንዃን  አደረሳችሁ ከማለት የተቆጠብኩት፤ በውነት ትናንትና  ' እንኳን ተቃረባችሁ እንጂ እንኳን አደረሳችሁ” ለማለት የማይቻልበት ሁኔታ ላይ ነበርን፤

በዚህ አገር ታሪክ  ውስጥ፥ ከተመዘገቡት ማሰቃያ ስልቶች አስከፊው   “ወፌ  ይላ” መገረፍ ይመስለኝ ነበር፤   ከፊትለፊትህ ባለው ቴሌቪዥን  የአውዳመት  የሙዚቃ ቪድዮ ውስጥ ፥ አጋም የመሰለ ያዶሮ ወጥ በትልቅ ሰታቴ ውስጥ  ሰንተከተክ እያየህ  በጦም ፍርፍር ማሳለፍን  የመሰለ  ስቃይ የለም፤ ለማንኛውም፥ በቀጣይም  እንዲህ ያለ ሁኔታ ሊደገም ስለሚችል እነ ደመረ ለገሰ፥ የአመት በአል የሙዚቃ ቪድዮ ስትሰሩ ፥ የሱፍ ፍትፍተና ስንግ ቃርያን ማካተትን አትርሱ፤

ዘልዛይመር ያልያዛችሁ የኔ ዘመነኞች እንደምታስታውሱት፥ ልጆች እያለን በእንቁጣጣሽ መባቻ፥ የአበባ ስእል  ቤት ከቤት እያዞርን ፍራንካ እንሰበስብ ነበር፤ እኔ ከፍተኛ የስእል ፍላጎት ቢኖረኝም፥ አበባ መሳል ብዙ አይሳካልኝም፤ የሰፈራችን አባዎራዎች የዘረጋሁላቸውን ወረቀት  ይቀበሉና ፥የመርዶ ደብዳቤ የሚያነቡ ይመስል ፊታቸውን  ዝፍዝፍ አድርገው ይገረምሙኛል፤  ሽልንግ  ይሰጠኛል ብየ ስጠብቅ “  አሁን ይሄ አበባ ነው አሜባ ?” የሚል ዘግናኝ ሂስ የሚሰጠኝም አይጠፋም ፤  አጋነንከው በሉኝና፥የኛ ሰፈር ወላጆች ልጆቻቸውን "አበባ" ብለው  መሰየም  ያቆሙት  የኔን ስእል ካዩ በሁዋላ ይመስለኛል፤

  በተቃራኒው ደስታ የሚባል ጉዋደኛ ነበረኝ፤ ደስታ የንቁጣጣሽ ስእል ሰሎ ቤት ለቤት ሲያዞር እናቶች ተቀብለው ፥ስእሉን አይተው ያንን የጥይት ማስቀመጫ ሳንዱቅ የሚያክል ግንባሩን ስመው ፤ ብር ይሰጡትና ስአሉን በፍሬም አድርገው ከዋናው በር ፊትለፊት ባለው ግድግዳ ላይ ይሰቅሉታል፤ “ስታድግ አፈወርቅ ተክሌን የምትተካ ሰአሊ ይወጣኻል” የማይለው ሰው  አልነበረም፤ 
በቅርብ የሆነ ጊዜ ሳገኘው የዲሽ ጥገና  ባለሙያ ሆኖ አገኘሁት፤

የልጅነታችንን አስንተን ሰናወጋ በትካዜ እንዲህ አለ፤

“ የስእል ችሎታየ የሆነ ጊዜ ላይ  ጥሎኝ ቢጠፋም፥ ከቤት ወደ ቤት የሚያዞረኝ አባዜ ግን አብሮኝ ቀጥሏል"

“የመስቀል ወፍና ትልቅ ዲፎ ዳቦ
የበአል ቀንና  ማንአልሞሽ ዲቦ
ቀጠሮ እንዳላቸው ማን ያውቃል?

( ገጣሚ፥ መንግስቱ ሀይለማርያም)

መልካም አውዳመት ፤  በጎ ዘመን ይሁንላችሁ!
@snetsehuf

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

05 Sep, 15:38


https://youtu.be/oEIWfiQQfdY?si=QlrQzZIWwAo6cBIQ

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

03 Sep, 15:46


https://youtu.be/cCR2yZw1lO0?si=DGRxr2PhA0Z_gT5d

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

02 Sep, 13:49


https://youtu.be/X6nkwY9G-YY

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

28 Aug, 17:21


https://youtu.be/08Bqpv58hQg?si=b6pWrjFqD6JlLjS1

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

27 Aug, 18:16


t.me/empirebot/game?startapp=hero392137374

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

27 Aug, 17:14


https://t.me/major/start?startapp=392137374

👑 Join me in @Major game and earn $MAJOR token soon!
⭐️ 750 rating bonus for you.
⭐️ 1000 rating bonus if you are Premium.

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

27 Aug, 12:15


https://youtu.be/EVXqITNqrPQ

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

27 Aug, 11:44


ቀጣዩ CATS ነው ቶሎ ጀምሩት Dogs አይታቹሃል 3 ሳምንት ነው የቆየው ይሄም እንዳያመልጣችሁ

ይህ Bot ቴሌግራም መጠቀም ከጀመርንበት ቀን አንስቶ ያለውን ጊዜ በማስላት 🐈 Cats Token እየተሰጠ ይገኛል ይህንን Bot Start
CATS ለመጨመር ሰዎችን  INVITE አድርጉ

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

27 Aug, 11:43


t.me/catsgang_bot/join?startapp=01J2Pp8Qbp5peEDVpky27
Meow, lets see who is OG 😼

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

14 Aug, 04:51


https://youtu.be/5zvS_c5enKs?si=pkShPo9JQrJX_o5p

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

10 Aug, 12:20


ተንታኝ

(በእውቀቱ ስዩም)

ቅድም የሆነ ምግብ ቤት ቁጭ ብየ ፤ ከፊቴ በተንጣለለው ቲቪ ማራቶን ስመለከት  ከጎኔ የተቀመጠ ተመጋቢ  ያጉተመትማል፤

“ይረባሉ ብለህ ነው?” አለኝ፤

“ያቅማቸውን እየሞከሩ ነው “ አልኩት፤

“ ለሜሳ የተባለው ባለፈው መሰናክል ላይ ወድቆ ሆስፒታል መግባቱን ሰምተሀል መቼም”

“ የወደቀውኮ ወድዶ አይደለም፤ አደናቅፎት ነው፤ በነገራችን ላይ ስሙ ለሜሳ ሳይሆን ለሜቻ ነው”አልሁት ፤

“ ከተሸነፈ በሁዋላ እንኩዋን ስሙን ዜግነቱንና ጾታውን  አሳስቼ ብጠራው መብቴ ነው’ አለ ሰውየው

አስከትሎ እንዲህ አለ፤ ”   እንደ ነገርኩህ  መውደቁ አይደለም ችግሩ፤  እንዴት በወሳንሳ ሆስፒታል ይገባል?  መሰናክሉ ቢያደናቅፈው መሰናክሉን  እንክትክት አርጎ እንክትካቹን  ከእግሩ ላይ እንደ አቧራ አራግፎ  መሮጥ ነበረበት ፤  የኛ አትሌቶች ፍጥነት እንጂ ጉልበት የላቸውም፤ ጡንቻማ ላመል አታገኝባቸውም ፤ የጀመይካ    ያጭር ርቀት ሯጮችን  ተመልከት ፤ እግራቸው ያንጋፋ ዝግባ ግንድ ነው የሚያክለው፤ ደረታቸው ከደራርቱ ቱሉ አደባባይ ይሰፋል፤   የክንዳቸውን ፈርጣማነት  ስትመለከት  በትርፍ  ጊዜያቸው ቦክስና ነጻ ትግል እንደሚወዳደሩ ትገምታለህ፤  በሲኖትራክ  ብትገጫቸው ራሱ አይወድቁም፤ ቢወድቁ እንኳ  የወደቁበት መሬት  ይጠረመሳል፤”

“ህም “ አልሁና ወደ ማራቶኑ ማፍጠጤን ቀጠልሁ፤

ሰውየው ቀጥሏል፤
 
“ የኛ አትሌቶች ገንቢ ምግብ መመገብ  አለባቸው፤  ሩጫ በድርቆሽ ፍርፍርና በበሶ   የሚዘለቅ አይደለም፤ ፍሪምባና ሻኛ እየበሉ  ክብደት ማንሳት አለባቸው፤ ይልቁንም ውድድሩ  ቢያንስ ሀለት ወር ሲቀረው ከወሲብ መታቀብ አለባቸው፤ ከሚስታቸው ጋራ ከተኙ  እንኩዋ ካንድ ዙር በላይ እንዳይሄዱ ክትትል ሊደረግባቸው ይገባል፤”

ታምራት ቶላ አንደኛ  ሲወጣ የምግብ ቤቱ ተስተናጋጆችና አስተናጋጆች ቆመን ማጨብጨብ ጀመርን፤  ሰውየው ከተቀመጠበት ሆኖ መዳፎቹን በዝግታ  ማማታት ጀመረ፤

“ተነስተህ አታጨበጭብም?” ስለው፤

“ ይቅርታ፥ ዲስክ ላይ ችግር ስላለ፤ መቀመጡን እመርጣለሁ”
@snetsehuf

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

09 Aug, 15:40


https://youtu.be/OgYi-52Kzrc?si=yYuJArTUEaaXl7IQ

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

03 Aug, 15:09


ታጋይና ትግል
(በእውቀቱ ስዩም)
እኔ እምለው፤   እግረኛ መቅጣት የከተማይቱ ዋነኛ የገቢ ምንጭ ሆኖ ቀረ ማለት ነው?    በቀደም እዚህ ቀበና  መንገድ  ዳር ካለው አግዳሚ ወንበር  ላይ ተቀምጨ እናፈሳለሁ፤  ባቅራቢያየ የቆመ ደንብ አስከባሪ፥  ተነስቼ የሆነ ስህተት እስክፈጽም ድረስ በጉጉት ሲጠብቀኝ ቆየ፤ በመጨረሻ ሰበብ ቢያጣ  " የሳይክል ነጂዎች ወንበር ላይ ተቀምጠሀል" ብሎ መቶ አምሳ ብር  ቀጣኝ🙂
 
በነገራችን ቅዳሜ፥ ከፖለቲካ ውጭ የሆነ ቀን ሆኖ መከበር ይኖርበታል፤ በቅዳሜ ቀን ስለፍቅር ስለ ኪነጥበብ ስለ ፍልስፍና ስለ ተፈጥሮ ብቻ እየቀደድን እንድንውል የሚያዝ ህግ መውጣት አለበት፤

ይህን ስል አንድ የማውቀው ሰውየ ትዝ አለኝ ፤ ሰውየው የ "ያ ትውልድ አባል “ ነው፤ ለነገሩ እኔ ራሴ ለካ  ሳላስበው “ያ ትውልድ”  ሆኛለሁ ፤ ለመግባባት እንዲመቸን ይሄንን ሰውየው “  የቀድሞው -ያ ትውልድ አባል ነው፤ የመሰረተ ትምርት ዘመቻ ላይ ተሳትፏል ፤ ጎህ መጽሄት ላይ ደርግን በመቃወም  ጽፏል፤  በመጨረሻ በሱዳን በኩል ወጥቶ ብዙ አመት ሰው በላው ካፒታሊዝምን እያገለገለ  ኑሮዋል፤ እና አሁን በቅርቡ ወደ አገሩ ገብቶ አንዲት ወጣት ሴት  አግብቶ መኖር ጀምሯል ፤ 

ሚስትዮዋ ብዙ ነገሩ ቢመቻትም  ወሬው ያሰለቻታል፤ ከሚያወራው ዘጠና በመቶው ፖለቲካ ነው ፤”  እስቲ ዛሬ እንኳ  ስለ ፍቅር ብቻ እናውራ “ ስትለው “ እሺ  ይቅርታ “ ብሎ  ብዙ ሳይቆይ ወደ ትንታኔ እና ወደ መፈክር ይመርሻል፤

ሴትዮዋ  ምርር ሲላት ዘዴ ፈጠረች፤  ፖለቲካ  ማውራት ሊጀምር  ቶሎ ብላ ትስመዋለች፤ ወይ ትዳራዋለች፤

   ከሌሊቶች ባንዱ ሌሊት  ለመተቃቀፍ ሲሞክሩ የሆነ ነገር ተከሰተ!  የሰውየው መራቢያ አካል  እንደ ብር የመግዛት አቅም ተዳከመበት! ይሁን እንጂ “  እንዲህ አይነት ነገር ፥ያጋጥማል “ ብሎ አቅፏት፤ ስሟት  በመተኛት ፋንታ ፥ ሰውነቷ ላይ ተንበልብሎ    ይወራጭ ጀመረ ፤

መጨረሻ ላይ ቢቸግራት ፥
 
“ አልሆነልህምኮ፤ ለምን አርፈህ አትተኛም?”

ስትለው ፥ የመለሰው መልስ ያስተክዘኛል፤

“ዝምበይ !  ታጋይ ይሞታል እንጂ ትግል አይሞትም”
@snetsehuf

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

31 Jul, 19:22


ልውውጥ
(በእውቀቱ ስዩም)

በመጀመርያ እጅግ  ቸር እና ታታሪ ለሆነው የጎፋ ህዝብ መጽናናትን ከልቤ  እመኛለሁ፤ ሀዘኑን ያቅልላችሁ ወገኖቼ!


  ስሙኝማ !  ትናንትና “ እንኳን ደስ ያላችሁ “ ብሎ የሚጀምር የኢኮኖሚ ሀተታ ሲዘዋወር  አየሁ፤  በአለቃ ተከለወልድ መዝገበቃላት እገዛ ልረዳው ብሞከርም ምንም ሊዘልቀኝ አልቻለም፤  ያም ሆኖ፥ የአማርኛው አለቅጥ መወሳሰብ የሆነ ከበድ ያለ ነገር እየመጣ እንደሆነ  መገመት ችያለሁ፤

ትዝ ይለኛል፤  የሆነ ጊዜ አንድ መስራያ ቤት ውስጥ ተቀጥሬ  ለሰባት ወራት ሰርቼ   ተባረርሁ፤  አለቃየ ቢሮው ጠርቶ “ ከዛሬ ጀምሮ ተባርረሀል  “ አላለኝም፤  በፈገግታ “ ከዛሬ ጀምሮ  ወደ መስርያቤታችንን በመመመላለስ   እንዳትደከም ባብላጫ ድምጽ  ተወስኗል” ነበር  ያለኝ ፤ እኔም ተጨንቆና ተጠቦ በአክብሮት ስላባረረኝ ደስ ብሎኝ ራሴን የመግደል ውሳኔየን ለመጭው አምሳ አመት አራዘምኩት🙂

እንዳለመታደል ሆኖ፥ የኢኮኖሚስቶች እና ያይዶል ዳኞች   አማርኛ  ምንም አይገባኝም፤
ትናንት አንድ አንጋፋ ኢኮኖሚስት  በሚድያ ቀርቦ “ ብር ዋጋ እያጣ ስለሆነ ገንዘባችሁን እቃ ላይ አስቀምጡ ” የሚል ምክር ለገሰ፤  ምክሩን ሰምቼ አምስት መቶ ብር ሞሰብ ላይ  አስቀመጥኩ፤ በሁዋላ ሳጣራ ለካ እቃ  ግዙበት  ማለት ነው፤  

አንዱ ደግሞ “ ከዚህ በሁዋላ የኢትዮጵያ ብር ዋጋ ስለማይኖረው ግብይት የሚካሄደው በምርት እና ባገልግሎት  ልውውጥ  ነው”  ሲል ተናገረ፤  ይሄ እንኳ ግልጥ ሆኖልኛል፤ የተቀቀለ እንቁላል ሰጥተህ  የተቀቀለ በቆሎ ትቀባለለህ፤ በኪራይ ቤት የምትኖር ሀኪም ከሆንህ የቤት ኪራይ በብር አትከፍልም፤ በምትኩ፤ የአከራይህን ቤተሰቦች በታመሙ ቁጥር በነጻ መድፌ ትወጋለህ፤     አሁን እኔ፤ ምሳ ካሰኘኝ  ለሬስቶራንቱ ባለቤት አንድ  አጠር ያለ ወግ  አነብለታለሁ፤  በለውጡ ድርቆሽ ፍርፍር  ያዝዝልኛል  ፤ 

ከዚህ በላይ ምን እፈልጋለሁ ዠለስ? ከተኩስ ልውውጥ ወደ ሸቀጥ ልውውጥ መሄድምኮ  መሻሻል  ነው!

“ኑሮ እንዴት ነው” ሲሉት “ ተመስጌን ነው!  ከነገ ይሻላል”  ያለው ሰውየ ግን ሀውልት ሊሰራለት ይገባል፤

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

30 Jul, 04:33


Invite your friends and get bonuses for each invited friend! 🎁

Your referral link: https://t.me/avagoldcoin_bot?start=82f724038f688f197b32
Start belut zare yalkal

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

29 Jul, 18:24


https://youtu.be/uEJt2jq1VBQ?si=JJiGoKWP4q1NZtH4

1,091

subscribers

38

photos

1

videos