ስኬታማ ተማሪ

@sketamatemari


❇️ሰቃይ ተማሪ የመሆን ህልማችሁን ከስኬታማ ተማሪ ጋር እውን አርጉ!
❇️Subscribe ያድርጉ ስኬታማ ተማሪ ይሁኑ👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCN7ohAHhgQ1KSWAMFXb-Tkw
❇️Tik Tok:- vm.tiktok.com/ZMjRnQD79/
ለማስታወቂያ:- @sketamamarket

ስኬታማ ተማሪ

21 Oct, 13:43


#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ እንደሚገለጽ አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ " በ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ይገለጸል " ብሏል።

ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቅርቧል።

@sketamatemari

ስኬታማ ተማሪ

21 Oct, 12:13


የ2017 ስልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና የመቁረጫ ነጥብ:

የተፈጥሮ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት

የስልጠና ደረጃ 1 እና 2
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 141 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 137 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 138 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 134 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 124 እና ከዚያ በታች፡፡

የስልጠና ደረጀ 3 እና 4
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 142 ከዚያ በላይ፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 138 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 139 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 135 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 125 እና ከዚያ በላይ፡፡

የስልጠና ደረጀ 5
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 179 ከዚያ በላይ፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 167 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 170 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 162 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 154 እና ከዚያ በላይ፡፡


የማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት

የስልጠና ደረጃ 1 እና 2
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 ከዚያ በታች፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 135 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 134 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 124 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 124 እና ከዚያ በታች፡፡

የስልጠና ደረጀ 3 እና 4
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 140 ከዚያ በላይ፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 136 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 135 እና እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 125 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 125 እና ከዚያ በላይ፡፡

የስልጠና ደረጀ 5
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 172 ከዚያ በላይ፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 164 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 165 እና እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 160 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 154 እና ከዚያ በላይ፡፡

@sketamatemari

ስኬታማ ተማሪ

20 Oct, 10:02


@sketamatemari

ስኬታማ ተማሪ

16 Oct, 18:05


#AAU #ORIENTATION

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በዩኒቨርስቲያችን ተወዳድራችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎችን በሙሉ አጠቃላይ ገለፃ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ ስለሚደረግ:

• ከአዲስ አበባ ውጪ የመጣቹ የራሳችሁን ወጪ ሸፍናችሁ ለምትማሩ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ (FBE) ኮሌጅ ትልቁ አዳራሽ

እንዲሁም

• ከአዲስ አበባ የራሳችሁን ወጪ ሸፍናችሁ ለምትማሩ እና በመንግስት ወጪያችሁ ተሸፍኖ ለምትማሩ አዲስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ (6 ኪሎ) በሚገኘው ልደት አዳራሽ አጠቃላይ ኦሬንቴሽን የሚሰጥ መሆኑን እያሳወቅን በቦታው እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

@sketamatemari
@sketamatemari

ስኬታማ ተማሪ

15 Oct, 14:00


#Update

ትምህርት ሚኒስቴር መስማት ለተሳናቸው የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው ተሸፍኖ) የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት እንደሚከተለው ይሆናል፦

► የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከስድስት መቶ 192
► የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከስድስት መቶ 186
በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ ከሰባት መቶ 224
► በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ሴት ከሰባት መቶ 217 እና ከዚያ በላይ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡


@sketamatemari
@sketamatemari

ስኬታማ ተማሪ

14 Oct, 09:08


#ASTU

For first-year students

Pre-Engineering Class Schedule.

ASTU GENERAL

ስኬታማ ተማሪ

12 Oct, 18:01


አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ወደ ተቋሙ የሚገቡ አዲስ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን ጥቅምት 3 እና 4/2017 ዓ.ም ይቀበላል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ አካባቢዎች ለሚመጡ ተማሪዎች መገናኛ እና ቃሊቲ ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት ማዘጋጀቱን ገልጿል።

በዚህም እሑድ 5፡00 ሰዓት እንዲሁም ሰኞ 4፡00 ሰዓት በተጠቀሱት ቦታዎች በመገኘት፣ የዩኒቨርሲቲውን ሎጎና የእንኳን ደህና መጣችሁ ባነር የተለጠፈባቸው አውቶቡሶችን መጠቀም እንደምትች ተገልጿል፡፡

@sketamatemari
@sketamatemari

ስኬታማ ተማሪ

12 Oct, 12:42


ለ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ ለመማር ቅበላ ላገኛችሁ የአንደኛ ዓመት ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የወጣ የቅበላ እና ምዝገባ ማስታወቂያ

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 የትምህርት ዓመት በመደበኛው የቅድመ-ምረቃ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚኒስቴርና በዩኒቨርሲቲው የቅድመ-ምረቃ ትምህርት መግቢያ መስፈርት መሠረት ቅበላ ላገኛችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች ጥቅምት 5 እና 6 2017 ዓ.ም በየተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓሶች በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ያሳውቃል፡፡ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ

1.የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ኮፒ፣
2. አራት ጉርድ ፎቶግራፎች፣
3. የማደሪያ ምድብ (Dormitory) ለተሰጣችሁ ብርድልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ ያስታውቃል፡፡
• ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትኖሩ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል UAI በተፈተናችሁበት ሀG ቁጥር በመጠቀም ከታች ባለው ሊንክ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን
https://portal.aau.edu.et/NewStudent/DormitoryPlacement
ያሳውቃል፡፡
• በተጠቀሱት ቀናት (ጥቅምት 5 እና 6) ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ
ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና
መናኸሪያዎች ዩኒቨርስቲው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ መሆኑን
እንገልጻለን፡፡
• ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ ሆኖ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅበላ ያገኛችሁ ተማሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችና ዶክመንቶች ይዛችሁ ሪፖርት የምታደርጉት ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን ያሳውቃል፡፡
https://portal.aau.edu.et/NewStudents/Welcome.www.aau.edu.et
• ለሁሉም ተማሪዎች አጠቃላይ ስለ ዩኒቨርስቲዉ ገለፃ (Orientation) ቅዳሜ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ይሆናል፡፡
• የትምህርት ኮርሶች ምዝገባ ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ሲሆን • የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያዉ ሰሚስተር ትምህርት የሚጀመረዉ ማክሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ይሆናል፡፡
• ስለምዝገባ ሂደቶች በተመለከተ እና ተጨማሪ መረጃ ከታች ካሉት ሊንኮች ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን::
https://portal.aau.edu.et/NewStudents/Welcome
www.aau.edu.et
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር


@sketamatemari
@sketamatemari

ስኬታማ ተማሪ

10 Oct, 13:32


#MoE

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በ 'Remedial' ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ ሞልተው እንዲጨርሱ መገለጹ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ " አንዳንድ ትምህርት ቤቶች በሲስተም ችግር ምክንያት የተማሪዎቻችንን የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርስቲ ምርጫ መሙላት ተቸግረናል " ባሉት መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር የምርጫ መሙያ ጊዜውን እስከ ረቡዕ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

@sketamatemari

ስኬታማ ተማሪ

09 Oct, 14:40


የትምህርት መረጃዎችን ለማግኘት ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/Sketamatemari
https://t.me/Sketamatemari

ስኬታማ ተማሪ

08 Oct, 18:43


#MoE #Placement

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ማመልከቻቸውን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንዲልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

Via Tikvah

@sketamatemari
@sketamatemari

ስኬታማ ተማሪ

08 Oct, 16:03


#MoE

በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ተወስኗል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የወሰዱና እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ ተብሏል።

★ በመንግስት ተቋማት ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ የሪሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

@sketamatemari