ራዕይ ለሰው ልጅ እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው። ራዕይ ያለውን ማንኛውንም ሰው የትኛውም ኃይል ከሚደርስበት ቦታ ሊመልሰው፤ ከተሰፈረለት ኮታ ሊያጎድለው፤ ከሕይወቱ ከፍታ ሊያወርደው አይችልም።
እኛ የአምላካችን ምርጥ ሥራዎች ነን። ሌሎቹን “ይሁን” ብሎ በቃል ሲጠራቸው እና ከሌሉበት ሲመጡ እኛን ግን “በመልኩ፣ በአምሳሉና በእስትንፋሱ” ከምድር አፈር አበጅቶ የራሱን የሕይወት እስትንፋስ “እፍ” ብሎብን ነው የሠራን።
በሕይወት ትልቁ ኪሳራ ሱቃችን የተዘጋ ቀን የምንበላው ያጣን ቀን ከሰው እኩል መልበስ ያቃተን ቀን ሳይሆን የመንኖርለት የሕይወት ዓላማ እና ራዕይ ያጣን ቀን ነው፡፡ ራዕይ ማጣትን ምንም ዓይነት ተግባር፣ ምንም ዓይነት እገዛ፣ ምንም ዓይነት ስልጠና አይተካውም። አምላክህ በእራሱ ፈቃድ እና እቅድ ጾታህን፣ ስፍራህን፣ ሥራህን እና ዘመንህን ወስኖ ለራዕይ እና አላማ እንደፈጠረህ እወቅ ይህንም እመን።
#ተፅዕኖ_ፈጣሪነት_ለምን_እስከምን ?
የንጉሱ ሴት ልጆች ነን!
የስልጠና ሰአት ቅዳሜ ከ4:00-6:00
ቅዳሜ ከ10:00-12:00
የማማከር አገልሎት
ሰኞ እና እሮብ ሙሉ ቀን
ለመመዝገብ ከታች የሚገኙትን ስልኮች ወይም በአካል በመገኘት ይመዝገቡ:: ከሀገር ውጪ የምትገኙ በቴሌግራም ቀጠሮ መያዝ የምትችሉ ይሆናል::
ለበለጠ መረጃ
0989656552