Sancho Gebre

@sanchogebre


ሰላም 🕊

sanchogebre.com
linktr.ee/SanchoGebre

Sancho Gebre

22 Oct, 15:30


#ደሊላ በቅርብ ቀን!

ውድ አድናቂዎቼ እና አክባሪዎቼ በሙሉ ከሁሉ በማስቀደም የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ "ደሊላ" የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ ያጠናቀኩ ሲሆን ይህም ስራ በምነው ሸዋ ዩትዩብ ቻናል በቅርብ ቀን እንደሚለቀቅ ልጠቁማችሁ እወዳለሁ።

በዚህ ስራ ላይ ለተሳተፋችሁና የበኩላችሁን ለተወጣችሁ በሙሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ!!!

#delila #sanchogebre

Sancho Gebre

07 Oct, 09:33


ልደት እና ምስጋና!!!

ከፍጥረታቱ ሁሉ የሰውን ልጅ ልዩና ድንቅ አድርጎ በአምሳሉ የፈጠረ ልዑል እግዚአብሔር በልቦናው ባሰበልን ቀን ሁላችንን ወደ ምድር እንዳመጣ ሁሉ፥ እኔም በቅዱስ ፍቃዱ መስከረም 27 ቀን ይህችን ምድር ተቀላቀልኩ። በህይወቴ ላይ አዲስ አመት ጨምሯልና የዓለሙ ሁሉ መድኃኒት የሆነው መድኃኔዓለም ስለቸርነቱ የተመሰገነ ይሁን።

በህይወቴ በተፈጠሩ ውጣ ውረዶች ሁሉ አብሮኝ ስለነበረ እና በድክመቴ ስላልተወኝ ፈጣሪዬን በአደባባይ ከፍ አድርጌ አመሰግነዋለሁ። ስለ ሚደንቅ ምህረቱ እና ስለ ፍጹም ፍቅሩም አባታችን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።

በለተያዩ አጋጣሚዎች የመልካም ልደት ምኞታችሁን ላደረሳችሁኝ ወዳጆቼ እና አክባሪዎቼ በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ።

Sancho Gebre

22 Sep, 08:49


Yoo Yoo Gifaataa!
Yoo Yoo Masqala!
Hashshu ubbaaka shaakennan qorennan Wolaytta layttaa laamiyaa Gifaattaa baallaasi saruwan gattees.

Sancho Gebre

21 Sep, 08:22


Tonight in Djibouti 🔥🔥
ዛሬ ማታ በጅቡቲ 🔥🔥

Sancho Gebre

31 Aug, 14:53


"ሰላሜ" ከካሜራ ጀርባ... ተጋበዙልኝ!

https://youtu.be/CZ6AMjatS4E?si=OWT6qAZpTUK_H0Du

Sancho Gebre

23 Feb, 15:23


"አናፍ ኮቱ"ተለቋል!
https://youtu.be/6QZxz2gc6ds

Sancho Gebre

21 Feb, 14:28


አናፍ ኮቱ | ANAAF KOOTTU - አርብ ማታ በሆፕ ኢንተርቴይመንት ዩትዩብ ቻናል ይጠብቁን!
:
#sanchogebre #AnaafKoottu

Sancho Gebre

21 Feb, 14:27


Channel photo updated

Sancho Gebre

19 Feb, 13:40


አናፍ ኮቱ | ANAAF KOOTTU - አርብ ማታ

ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ አድናቂዎቼ እና አክባሪዎቼ? ከሁሉ በማስቀደም የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ "አናፍ ኮቱ" (Anaaf Koottu) የሚል አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ በሆፕ ኢንተርቴይመንት ዩትዩብ ቻናል የፊታችን አርብ እንደሚለቀቅ ልጠቁማችሁ እወዳለሁ።

ዘፈኑ ሙሉ በሙሉ ኦሮምኛ ሲሆን ሀገራዊ ሀሳቡን ጠብቆ በዘመናዊ መንገድ ተቀናብሯል። ከዘፈኑ ሀሳብ ጋር የሚጣጣም ቪዲዮ ሀረር ላይ ቀርጸናል። እንደተለመደው ስራችንን ተመልክታችሁ አስተያየታችሁን ትሰጡኝ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ።

ሠላም ለውድ ሀገራችን እና ለመላው ህዝባችን ይሁን!

Sancho Gebre

16 Feb, 15:06


"አናፍ ኮቱ" በቅርብ ቀን በሆፕ ኢንተርቴይመንት ይጠብቁን!
:
#sanchogebre #AnaafKoottu

Sancho Gebre

16 Jan, 16:14


Coming Soon! #AnaafKoottu
#sanchogebre

Sancho Gebre

12 Jan, 16:17


Coming Soon! #AnaafKoottu
#sanchogebre

Sancho Gebre

17 Nov, 15:52


#habibideyda ተለቋል!
#Rafary ft #sanchogebre

https://youtu.be/uNqZCZTE1TI

Sancho Gebre

17 Nov, 09:37


ዛሬ ማታ ሀቢቢደይዳ/Habibideyda #Rafary ft #sanchogebre

Sancho Gebre

14 Nov, 09:52


ሀቢቢደይዳ/Habibideyda የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ ከሶማሊያዊው ራፋሪ/Rafary ጋር በመጣመር (በፊውቸሪንግ) የተሳተፍኩበት ስራ በቅርብ ቀን በEla Tv ይለቀቃል።

Sancho Gebre

20 May, 09:31


#selame MP3

Sancho Gebre

19 May, 16:24


#ሰላሜ ተለቋል!
https://youtu.be/B1w-tywkCj0

Sancho Gebre

19 Apr, 15:17


ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ አድናቂዎቼ እና አክባሪዎቼ? ከሁሉ በማስቀደም የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ "ሰላሜ" የሚል ስያሜ የሰጠነውና በጥሩ ሁኔታ ያዘጋጀነው አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ በምነው ሸዋ ዩትዩብ ቻናል በቅርብ ቀን እንደሚለቀቅ ልጠቁማችሁ እወዳለሁ።

ይህን ሙዚቃ የሰራነው ባለፉት ጥቂት አመታቶች ውስጥ ዓለማችን ላይ እጅግ ተወዳጅነት እያገኘ ባለው "Amapiano" በተሰኘው አዲስ የአፍሪካ የሙዚቃ ስልት ሲሆን እኔና ጊልዶ ካሳ በጋራ ተጫውተነዋል። ሙዚቃውም የሚፈልገውን ተንቀሳቃሽ ምስል አልብሰነዋል።

ሰላም ለውድ ሀገራችን እና ለመላው ህዝባችን ይሁን።

Sancho Gebre

05 Feb, 19:36


አንድ ሲኖዶስ!
አንድ ፓትርያርክ!
አንዲት ቤተ ክርስቲያን!
የአባቶቼን ትዕዛዝ እቀበላለሁ፣ ከጎናቸውም እቆማለሁ፡፡

Sancho Gebre

05 Feb, 19:35


Channel photo updated