Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

@qesestube


የዩትዩብ ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ !!! ይህን ሊንክ በመጫን 👉👇 https://www.youtube.com/c/QesesTube ሰብስክራይብ ያድርጉ
በቻናሉ ሚለቀቁ ትምህርቶች
- ሀዲሶች ፣ ፈትዋዎች ፣ ኢስላማዊ ታሪኮች ፣ ኒካህን እና ትዳርን የሚመለከቱ ትምህርቶች ...........ወዘተ በተለያዩ ኡስታዞች ይቀርብላችኋል !!!

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

22 Oct, 06:50


በመርካቶው ቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባችሁ ወገኖች ሁሉ። ከምንም በፊት ሶብር አድርጉ። አላህ ሰጠ። አላህ ነሳ። ሙስሊም በደስታውም በሀዘኑም ጌታውን ያስባል። ጌታችን እንዲህ ይላል፦

{ وَلَنَبۡلُوَنَّكُم بِشَیۡءࣲ مِّنَ ٱلۡخَوۡفِ وَٱلۡجُوعِ وَنَقۡصࣲ مِّنَ ٱلۡأَمۡوَ ٰ⁠لِ وَٱلۡأَنفُسِ وَٱلثَّمَرَ ٰ⁠تِۗ وَبَشِّرِ ٱلصَّـٰبِرِینَ (155) ٱلَّذِینَ إِذَاۤ أَصَـٰبَتۡهُم مُّصِیبَةࣱ قَالُوۤا۟ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّاۤ إِلَیۡهِ رَ ٰ⁠جِعُونَ (156) }
"ከፍርሃትና ከረሃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር። እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ፡ 'እኛ ለአላህ ነን፤ እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን' የሚሉትን።" [አልበቀረህ፡ 155-156]

አልሐምዱ ሊላህ በሉ። የሙእሚን ወጉ ይሄ ነው። በመከራውም በደስታውም ጊዜ ጌታውን አይረሳም። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
عَجَبًا لأَمْرِ المُؤْمِنِ، إنَّ أمْرَهُ كُلَّهُ خَيْرٌ، وليسَ ذاكَ لأَحَدٍ إلَّا لِلْمُؤْمِنِ، إنْ أصابَتْهُ سَرَّاءُ شَكَرَ، فَكانَ خَيْرًا له، وإنْ أصابَتْهُ ضَرَّاءُ، صَبَرَ فَكانَ خَيْرًا له.
"የሙእሚን ነገሩ ይደንቃል። ሁለ ነገሩ መልካም ነው። ይሄ ለሙእሚን እንጂ ለማንም አይደለም። አስደሳች ነገር ቢያገኘው ያመሰግናል። ይሄ ለሱ መልካም ነው። ጉዳት ቢያገኘውም ይታገሳል። ይሄ ለሱ መልካም ነው።" [ሙስሊም፡ 2999]

በማመስገን ታተርፋላችሁ እንጂ አታጡም። በአይነ ህሊናችሁ ቃኘት ቃኘት ብታደርጉ አገር ምድሩ በፈተና ተጥለቅልቆ ታያላችሁ። የባሰ የገጠማቸውን ተመልከቱ። ንብረት ብቻ ሳይሆን ሙሉ ቤተሰብ ያለቀበት ስንት ጉድ አለ። አስቡ። ለመፅናናት ይጠቅማችኋል። ከተስፋ መቁረጥ ይታደጋችኋል። ከባሰ ሁሉ በላይ የባሰ አለ። ከባሰው ያዳናችሁን አመስግኑ። ተስፋ መቁረጥ፣ አጉል ብስጭት ያለፈውን ላይመልስ ከሁለት ያጣ ያደርጋል። ደግሞም እወቁ! አያልፍ የመሰለው ሁሉ ያልፋል። ኢንሻአላህ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ከምንም በላይ ግን ዱንያ ነው። ትልቁ ኪሳራ የኣኺራ ኪሳራ ነው። ጌታችን እንዲህ ይላል፦
{ قُلۡ إِنَّ ٱلۡخَـٰسِرِینَ ٱلَّذِینَ خَسِرُوۤا۟ أَنفُسَهُمۡ وَأَهۡلِیهِمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۗ أَلَا ذَ ٰ⁠لِكَ هُوَ ٱلۡخُسۡرَانُ ٱلۡمُبِینُ }
" 'ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በቂያማ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ንቁ! ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው' በላቸው።" [አዙመር፡ 15]

አላህ ሶብሩን ይስጣችሁ። በተሻለ ይተካችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

22 Oct, 06:40


https://youtu.be/azuZaXXzPzA

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

19 Oct, 15:47


https://youtu.be/RrYJrmK-XPc

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

18 Oct, 17:17


በበላ እና በችግር እንደዚህ እንመከራለን! የቁርኣን እና የሀዲስ ምክር አልሰማ ስንል !

[ ኡስታዝ አህመድ አደም]

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/c/QesesTube

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Qesestube

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

17 Oct, 17:46


https://youtu.be/oZZ2iLhxNrk

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

17 Oct, 16:22


https://youtube.com/shorts/Q3dBlCkmUGc?feature=share

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

13 Oct, 16:04


https://youtu.be/kB3TBoF6Nck

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

11 Oct, 18:08


https://youtu.be/5NbnX3uqJkA

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

10 Oct, 15:53


https://youtu.be/oZZ2iLhxNrk

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

10 Oct, 12:34


"ኑሩን ከኑሩ ኸለቀው ጀሊሉ"
~
ይሄ ንግግር ሱፊዮች አካባቢ ተደጋግሞ የሚሰማ ነው። ምን ማለታቸው ነው?
* "ኑሩን" ሲሉ ነብዩን ﷺ ማለታቸው ነው።
* "ጀሊሉ" ሲሉ አላህ ማለታቸው ነው።
* "ከኑሩ" ሲሉ ከአላህ ኑር ማለታቸው ነው።
* ኸለቀው = ፈጠረው

ጥቅል መልእክቱ:-
አላህ ነብዩን ﷺ ከራሱ ኑር (ብርሃን) ነው የፈጠራቸው እያሉ ነው።
አንዳንዶቹ ይህንን መነሻ በማድረግ በግልፅ ነብዩ ﷺ የአላህ ክፍል (ጁዝእ/ part) ናቸው ብለዋል። ይሄ መሰረተ-የለሽ እምነት ነው። ለዚህም በተለያዩ ነጥቦች ምላሽ መስጠት ይቻላል።

1- ነብዩ ﷺ ምንም አይነት መለኮታዊ ድርሻ የላቸውም። ፍጡር ናቸው። ባሪያ ናቸው። ባሪያ ደግሞ የአላህ ክፍል ሊሆን አይችልም። መልክተኛ ናቸው።
2- ነብዩ ﷺ ከኑር (ከብርሃን) ነው የተፈጠሩት የሚሉ አካላት መሰረተ ቢስ ወሬ እንጂ አንድም የቁርኣንም ይሁን የሐዲሥ መረጃ ማቅረብ አይችሉም።

3- በአፈጣጠር በኩል ነብዩ ﷺ እንደሌላው የአደም ዘር ሰው ናቸው። እዚህ ላይ ጥርጣሬ ሊገባን አይገባም። አላህ እንዲህ ሲል አዋጅ እንዲናገሩ አዟቸዋል፦
{قُلۡ إِنَّمَاۤ أَنَا۠ بَشَرࣱ مِّثۡلُكُمۡ}
" 'እኔ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ' በላቸው።" [ከህፍ፡ 110]

4- ወላጆቻቸው እና ዘር ማንዘራቸውም የሚታወቁ ናቸው። እሳቸውን ጨምሮ ሁሉም እንደ ሌላው የሰው ዘር የአደም ዘር ናቸው። አደም ከጭቃ መፈጠራቸው ግልፅ ነው።

5- ነብዩ ﷺ ሞተዋል። ስለዚህ "ከአላህ ኑር ነው የተፈጠሩት፣ የሱ ክፍል (ጁዝእ/ part) ናቸው'' የሚል ሰው የአላህ ክፍል ሙቷል እያለ ነው። ይሄ ሰቅጣጭ ድምዳሜ ነው። ለነገሩ እነዚህ ሰዎች የነብዩን ﷺ መሞትም ሊከራከሩ ይችላሉ። የሱፊያ እምነት በብዙ ነጥቦች ከ0ቅል ጋር የተኳረፈ እምነት ነው። እንኳን ነብዩን ﷺ ፤ በየመንደሩ ያሉ ሸይኾች ሲሞቱ "አልሞቱም፤ ሌላ አገር ወጥተዋል" እያሉ የሚያምኑ ብዙ ናቸው። ለማንኛውም ነብዩ ﷺ መዲና ሞተው ሶሐቦች አጥበው፣ ከፍነው፣ ሶላተል ጀናዛ ከሰገዱባቸው በኋላ ዓኢሻ ቤት ውስጥ ቀብረዋቸል። አላህም ሟችነታቸውን እንዲህ ሲል አስረግጦ ተናግሯል:-
{إِنَّكَ مَیِّتࣱ وَإِنَّهُم مَّیِّتُونَ}
"አንተ ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው።" [አዙመር: 30]

"ሲሞት እንገላገለዋለን" ሲሉ ለነበሩ ጠላቶችም ''እርማችሁን አውጡ እሱ አይሞትም" አይደለም ያላቸው። ይሄውና ምላሹ፦
{وَمَا جَعَلۡنَا لِبَشَرࣲ مِّن قَبۡلِكَ ٱلۡخُلۡدَۖ أَفَإِی۟ن مِّتَّ فَهُمُ ٱلۡخَـٰلِدُونَ (34) كُلُّ نَفۡسࣲ ذَاۤىِٕقَةُ ٱلۡمَوۡتِۗ}
"(ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረግንም። ታዲያ ብትሞት እነሱ ዘውታሪዎች ናቸውን? ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት።" [አልአንቢያእ፡ 34-35]

ማምታቻ:-
-
ነብዩ ﷺ ከኑር (ከብርሃን) ነው የተፈጠሩት የሚሉ አካላት አንድ እንዲህ የሚል የሚያቀርቡት "ሐዲሥ" አላቸው፦
أولُ ما خلق اللهُ نور نبيِّكَ يا جابرُ
"መጀመሪያ አላህ የፈጠረው የነብይህን ኑር (ብርሃን) ነው፣ ጃቢር ሆይ!"
ግና ይሄ ወሬ በየትኛውም የሐዲሥ ድርሳናት ውስጥ የማይገኝ መሰረተ ቢስ ወሬ ነው። [አሓዲሡን ሙንተሺረህ ላ ተሲሕ፡ ቁ. 393] ሱፊዩ አሕመድ አልጉማሪ ራሱ መሰረተ ቢስ የፈጠራ ወሬ እንደሆነ ገልጿል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

08 Oct, 18:23


https://youtu.be/FqAp_c-WYYw

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

08 Oct, 07:34


መታረም ያለበት እሳቤ
~
"የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የወንጀላችን መብዛት ነው። ወደ አላህ እንመለስ" በሚባል ጊዜ "ኧረ ከወንጀል ጋር የሚያያዝ አይደለም ፤ የታወቀ ሳይንሳዊ ምክንያት ያለው ነው" የሚሉ ሰዎች አሉ። እንጂ የፈጣሪ ስራ አይደለም ነው ድምዳሜያቸው። ለሆነ ክስተት ሳይንሳዊ ትንታኔ ወይም የታወቀ ምክንያት ኖረው ማለት ያ ክስተት የፈጣሪ ስራ አይደለም ማለት አይደለም። በፈጣሪ የሚያምን ሰው ያለሱ መሻት በምድርም ይሁን በሰማይ የሚሆን ነገር እንደሌለ ያምናል። ስለዚህ ዝናቡም፣ ንፋሱም፣ ማእበሉም፣ ድርቁም፣ መብረቁም፣ የመሬት መንቀጥቀጡም፣ የፀሐይ ግርዶሹም፣ ወረርሽኙም፣ ... ሁሉም በአላህ ውሳኔና መሻት የሚፈፀም ነው። ደረስንበትም አልደረስንበትም ከአላህ ውሳኔዎች ጀርባ የሱ ጥበብ አለ።

በአላህ የሚያምን አካል ትልልቅ መቅሰፍቶች ቀርቶ ትንንሽ ፈተናዎች ሲገጥሙት እንኳ የራሱን ድክመት ይመለከታል። ሰበቡ ወንጀሌ ሊሆን ይችላል ብሎ ወደ ጌታው ይመለሳል። እውነታውም እንደዚያ ነው። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ وَمَاۤ أَصَـٰبَكُم مِّن مُّصِیبَةࣲ فَبِمَا كَسَبَتۡ أَیۡدِیكُمۡ وَیَعۡفُوا۟ عَن كَثِیرࣲ }
"ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሰሩት (ሃጢኣት) ምክንያት ነው። ከብዙውም ይቅር ይላል።" [አሹራ፡ 30]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

07 Oct, 07:49


በዑመር ኢብኑ-ል-ኸ-ጥ'ጧብ ዘመን የመሬት መንቀጥቀጥ ገጥሞ ነበር

ዑመርም እንዲህ አሉ፦ «ወይ እኔ፣ ወይ እናንተ፤ አላህን አምፀናል፣ ወንጀል ተዳፍረናል፣ አዲስ ነገርን ፈጥረናል፣ .....»

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/c/QesesTube

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Qesestube

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

06 Oct, 16:44


https://youtu.be/0VhmweYO7RM

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

05 Oct, 16:15


https://youtu.be/pRTJpfDwS4c

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

04 Oct, 18:38


ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ኣደም ቱላ ስለ ኢሬቻ በዓል የተናገሩት!

ለሌሎችም ሼር አድርጉላቸው!

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

04 Oct, 17:38


https://youtu.be/yZiXfGs_Yn8

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

04 Oct, 07:52


እምነታቸውን ለሚያስቀድሙ ሙስሊሞች
~
አላህን "ዋቃ ጉራቻ" (ጥቁር ጌታ) እያሉ መጥራት በእስልምና የሚፈቀድ አይደለም። እንደ ኢስላም የፈጣሪን መገለጫዎች (ሲፋት) በቁርኣንና በሐዲሥ ከመጣው ውጭ ማንም ቢሆን በራሱ አመለካከት ላይ ተመሰርቶ መግለፅ አይችልም። የራስን የቆዳ ቀለም ተከትሎ ፈጣሪን ነጭ፣ ቀይ ወይም ጥቁር እያሉ መጥራት መታረም ያለበት ጥፋት ነው። ፈረንጆቹ የጌታ ምስል ነው እያሉ የነጭ ማለትም የፈረንጅ ቅብ ያለው ምስል እንደሚጠቀሙ ይታወቃል። በነጮች ዘረኝነት ከተማረሩ ጥቁሮች ውስጥ ሌላ ፅንፍ በመያዝ "ጌታ ጥቁር ነው" እስከማለት የደረሱ አሉ። በየትኛውም ዘር ውስጥ ያሉ ሙስሊሞች በዘር ተጠቅልሎ ከሚመጣ መሰል ብልሹ አስተሳሰብ ራሳቸውንም ወገናቸውንም ሊጠብቁ ይገባል። ኢስላም ከዘራችንም፣ ከቋንቋችንም እንዲያውም ከህይወታችንም በላይ ነውና።



👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/c/QesesTube

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

03 Oct, 16:10


https://youtu.be/dOWFQif3q9c

2,942

subscribers

169

photos

17

videos