መዝገበ ሃይማኖት

@mezgebehaymanot


በዚህ ቻናል እግዚአብሔር በረዳን መጠን "በመዝገበ ሀይማኖት"አስተማሪ፣ጹሑፎችና በአውዲዮ ስብከቶች፣በየዕለቱ የሚከበሩ የቅዱሳን ታሪክ ተጋድሎ ያባቶችን ምክር(ብሂለ አበው)ለተለያዮ ለተሳሳቱ ትምህርቶች ቤተ-ክርስቲያናችን የምስጠውን መልስ እንዲሁም መንፈሳዊ ግጥም፣ወግ፣መንፈሳዊ ጨውውቶች ይተላለፉበታል
t.me/mezgebehaymanot


ለማንኝው ሐሳብ @Belete_Kebede_Z_Alatenos ያድርሱን

መዝገበ ሃይማኖት

22 Oct, 19:11


"#ጥቅምት_13" #የጻድቁ_ አባታችን_አቡነ አረጋዊ_እና የጻድቁ_ገብረ_ክርስቶስ_ወ #_ሙሴ_ብእሴ_እግዚአብሔር_ክብረ_በዓል #ሥርዓተ_ዋዜማው ላይ ከሊቃውንቱ ጋር አብረን እድናመሰግን እንደ ሚከተለው ተዘጋጅቷል

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

ዋዜማ
ሃሌ ሉያ
ዳኅንኑ ዝስኩ አረጋዊ አቡክሙ፤ ጻድቅ ወኄር፤ በተአምኖ ዔለ፤ በተአምኖ ተጋደለ፤ ዔለ፤ ውስተ አድባር ወበዓታት።
👉t.me/mezgebehaymanot👈

ምልጣን
በተአምኖ ዔለ፤ በተአምኖ ተጋደለ፤ ዔለ፤ ውስተ አድባር ወበዓታት፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ።

በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ
አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ ጸሎትከ ወትረ ይብጽሐነ፣ አባ ጸሊ በእንቲአነ።
👉t.me/mezgebehaymanot👈

እግዚአብሔር ነግሠ
ወረደ ብርሃን ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር፤ ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ፤ ጸሎቱ ለገብረ ክርስቶስ ወበረከቱ የሃሉ ምስሌነ።
👉t.me/mezgebehaymanot👈

ይትባረክ
ኪያከ መሠረት አንተ ብነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ እስመ ጸሎተ ጻድቅ ይሰምዕ እግዚአብሔር፤ ይቤሎሙ ዮሴፍ፤ ዳኅንኑ ዝስኩ አረጋዊ ጻድቅ ወየዋኅ።
👉t.me/mezgebehaymanot👈

ሰላም
ደምፀ ወተሰብከ ውስተ ዓለም፤ ዜና ምግባሩ ትሩፍ ለአረጋዊ ኮከበ ገዳም፤ ደምፀ ወተሰብከ ውስተ ዓለም፤ ጽጉያን እሙንቱ እምጽጌ ሮማን፤ ወቀይሐን እምኮለ ገዳም፤ ደምፀ ወተሰብከ ውስተ ዓለም፤ ደቂቀ ኄራን ልዑላነ ዝክር ወስም፤ ደምፀ ወተሰብከ ውስተ ዓለም፤ እንዘ የዓርጉ መሥዋዕተ ሰላም፤ ደምፀ ወተሰብከ ውስተ ዓለም፤ ደምፀ ወተሰብከ ውስተ ዓለም።

አዘጋጅ :-በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ) አላቲኖስ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_በዓል ❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

አዘጋጅ :-በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ) አላቲኖስ በድጋሚ ተለጠፈ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot

በዪቲዩብ ቻናላች ስብስክራይብ ያድርጉ
#ሰብስክራይብ #Subscribe በማደግ ይቀላቀላሉ https://youtube.com/channel/UC0-pqPv3c7alERhdDpW1wrQ

በ Facebook በፔጃችን "መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇... ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉t.me/mezgebehaymanot👈 ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ🤳🤳🤳

[email protected]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

መዝገበ ሃይማኖት

22 Oct, 04:21


የተባረከ ቀን በመልካም ምክር ይጀመራል

ልጄ! ሐሰተኛ አትኹን፤ ሕሰት ከስርቆት ያደርሳልና፤ ወርቅ ውዳሴ ከንቱ የምትወድ አትኹን ይህ ሁሉ ከስርቆት ያደርሳልና አለ ናትናኤል።
👉  t.me/mezgebehaymanot👈

ልጄ! አጒረምራሚ አትኹን፤ ማጒረምረም ሰውን ወደ ስድብ ያደርሰዋልና፤ ክፉ ነገር የምታስብ ተጋፊ አትኹን፤ ክሕደት በዚህ ይመጣልና፤ ኃዳጌ በቀል (ይቅር ባይ) ኹን፤ ቂም በቀል የሌላቸው ሰዎች መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉና፤ ይቅር ባይ ርኅሩኅ ኃጢአት በሌለበት በንጹሕ ልብ ሁሉን የምትወድ ኹን፤ ትሑት ቸር ኹን፤ ከሰማኸው ቃል የተነሣ በመፍራት ከክፉ ሥራ ተጠብቀህ ኑር፤ አትታበይ ሰውነትህን ከትዕቢተኞች ጋር አንድ አታድርግ፤ ከትሑታን ከደጋግ ሰዎች ጋር ነው እንጂ፣ ያገኘህን መከራ ሁሉ አመስግነህ ተቀበል፤ ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ምንም ምን የሚደረግ እንደሌለ ዕወቅ አለ፤ ይሁዳ ታዴዎስ።
👉  t.me/mezgebehaymanot👈

ልጄ! ቃለ እግዚአብሔር የሚነግርህን የሕይወት ምክንያት የኾነህን ለልጅነት ያበቃህን ሰው እንደ ዐይን ብሌን ውደደው በመዐልትም በሌሊትም አስበው እግዚአብሔር እንደ አከበረው አክብረው፤ እግዚአብሔር ስሙን ከሚጠሩበት ቦታ ከዚያ ይኖራልና፤ በትምህርታቸው ትጽናና ዘንድ እየሔድክ ሌሎች ቅዱሳንን ጠይቅ፤ ከቅዱሳን ጋር የሚውል ቅዱስ ይኾናልና።
👉  t.me/mezgebehaymanot👈

በሚቻል መጠን አክብረው፤ ከደከምክበት ከሥራህ ፍሬ ስጠው፤ እግዚአብሔር በእርሱ ምክንያት መንፈሳዊ ምግብን የዘለዓለም ሕይወትንም እንድታገኝ አድርጎኸልና፤ የሚያልፈውን የዚህን ዓለም ምግብ ልትሰጠው ይገባሃል፤ ለሠራተኛ ዋጋው ይገባዋልና፤ በዐውድማ የበሬውን አፉን አትሰረው፤ ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማነው? አለ ቶማስ።
👉  t.me/mezgebehaymanot👈

የተጣሉትን በፍቅር አንድ አድርግ እንጂ ሰውን የሚለያይ ሥራ አትሥራ፤ በእውነት ፍረድ፤ ለባለጸጋ አድልተህ በድኻው አትፍረድ፤ ብዕል ለእግዚአብሔር ቁም ነገሩ አይደለምና፤ ትዕቢተኛውን መናፍቁን አታክብረው፤ መጽሐፍም አትጥቀስለት፤ እንደ አነጋገሩ መልስለት እንጂ፤ ስትጸልይ አትጠራጠር፤ የምትለምነውን አስተውል እግዚአብሔር ይፈጽምልኻል።
👉  t.me/mezgebehaymanot👈

በምትመጸውትበት ጊዜ ክፉ ነገርን አታስብ፤ ከሰጠህ ዋጋህን ታገኛለህና፤ የሰጠህ ምንም ምን ገንዘብ በእጅህ ቢኖርህ ከኃጢአትህ መዳንን ሻ ፈልግ፤ ያገኘኸውን በምትሰጥበት ጊዜ ወላዋይ ኣትኹን፤ ዋጋህን የሚሰጥህም ማን እንደሆነ ዕወቅ፤ የለመነኸንም አታሳፍረው፤ ማናቸውንም ሁሉ ከነዳያን ጋር ተካፈል እንጂ ገንዘቤ የግሌ ነው አትበል፤ በኀላፊው ገንዘብ እርስ በርሳችሁ አንድ ከኾናችሁ በማያልፈው እንደምን አንድ አትኾኑም።
👉  t.me/mezgebehaymanot👈

ወንድሞቼ! እማልዳችኋለሁ፤ ዕድሜ ሳላችሁ ከዚህም ጋር በጎ ሥራ መሥራት ሲቻላችሁ የአላችሁን መስጠት ቸል አትበሉ፤ እግዚአብሔር የሚመጣበት ቀን ቅርብ ነውና፤ የሚታየው የማይታየው ሁሉ ያልፋል እግዚአብሔር ይመጣል፤ የሚሰጠው ዋጋም ከእሱ ጋር ነው፤ ለራሳችሁ ፈጻምያነ ሕግ ኹኑ፤ እግዚአብሔር እንደ አስተማራችሁ ሌሎችን አስተምሩ፤ የተማራችሁትን ጠብቁ፤ በተማራችሁት ላይ አትጨምሩ፤ ክተማራችሁትም አታጉድሉ አለ በርተሎሜዎስ፤ ወንድሞቼ! የቀሩትን ትእዛዛት መጻሕፍት ያስተምሩዋችኋል አለ ጴጥሮስ።
👉  t.me/mezgebehaymanot👈

(#ሃይማኖተ_አበው_ዘስምዓት 125፥10-16)

👉  t.me/mezgebehaymanot👈

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_ዕለት ❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot
 

መዝገበ ሃይማኖት

20 Oct, 09:09


"ላለማመን እንጂ ለማመን በዙሪያችን ብዙ ምስክሮች አሉልን"

✥የሰንበት የነፍስ ስንቃችን

ዓይነ ሥውሩ ቅዱስ ዲዲሞስ በአንድ ወቅት የእግዚአብሔርን መኖር የሚክዱ ተመራማሪዎች የራሳቸውን እውቀት መነሻ በማድረግ የእግዚአብሔርን አለመኖር ከነገሩት በኋላ "እስኪ አንተ እግዚአብሔር መኖሩን በተጨባጭ አስረዳን?" ሲሉ ጠየቁት። ቅዱስ ዲዲሞስ ተመራማሪዎቹ ጭልጥ ብለው መሳሳታቸውን ቢያውቅም በጥሞና ያዳምጣቸው ነበር እንጂ አልተበሳጨም። ለጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት "ምሽት ተመልሳችሁ ኑ" አላቸው።👉  t.me/mezgebehaymanot👈

እነርሱም የቀጠሮአቸውን ሰዓት አክብረው ምሽት ተመልሰው መጡ። ቅዱስ ዲዲሞስም "እስኪ ወደላይ አንጋጣችሁ የሰማዩን ገጽታ ተመልከቱ" አላቸው። እነርሱም እንዳላቸው ሰማዩን ተመለከቱ። እርሱም "በሰማይ ላይ ምን ምን ይታያችኋል?" አለ።
👉  t.me/mezgebehaymanot👈

እነርሱም "ከዋክብት" ብለው መለሱለት። እርሱም "በስጋዊ አይናችሁ የማየት ችሎታ እነዚህን ክዋክብት በቀን ማየት ትችላላችሁን?" አላቸው። እነርሱም "አንችልም" አሉት። እርሱም "ለምን ማየት ያቅታችኋል?" ሲል ጥያቄውን በጥያቄ ደገመላቸው። እነርሱም "ምክንያቱም ከዋክብትን ለማየት የግድ መምሸት አለበት" አሉት። እርሱም "በእርግጥ ትክክል ናችሁ የመለሳችሁት ምላሽ ትክክል ነው። ይሁን እንጂ በተፈጥሮ እንደምናውቀው የተሰወረውን ነገር ለማግኘት ብርሃን ያስፈልጋል እነዚህን የምታዩአቸው ከዋክብት ለማየት ግን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ ሊኖር የግድ ነው። እንደዚሁ ሁሉ እግዚአብሔርንም ለማየት ቁሳዊ ነገርን ማየት በሚቻልበት በሳይንስ መሳሪያና ፍልስፍና ሳይሆን በእምነት ብቻ ማረጋገጥ እንደሚቻል ልነግራችሁ እወዳለሁ።" በማለት አስረዳቸው።
👉  t.me/mezgebehaymanot👈

 በድጋሚ "በሰማያት ገጽታ ላይ ከዋክብት እንደሚታዩ ነግራችሁኛል። ይሁን እንጂ እኔ ዓይነ ሥውር ስለሆንኩ በምን ታረጋግጥሉኛላችሁ?" ሲል አዲስ የጥያቄ ርዕስ ከፈተላቸዉ። እነርሱም ግራ ተጋብተው ምላሽ አጡ፤ እናም ከመናገር ይልቅ ዝምታን መረጡ። እርሱ ግን የእኔ ዓይነ ስውርነት የከዋክብቱን አለመኖር አያረጋግጥም፤ እኔ አየሁም አላየሁም ከዋክብቱ ዘወትር አሉ። እኔም ምንም ዐይነ ሥውር ብሆንም እንኳን ከዋክብቱን ሳልመለከት እናንተ አይታችሁ በነገራችሁኝ ምስክርነት ብቻ የከዋክብቱን መኖር አምኜ ተቀብየዋለሁ አላቸው። እኔ አንዳች ከዋክብት ሳልመለከት የከዋክብቱን መኖር እንዳመንኩ እናንተም በሥጋዊ አይናችሁ ባትመለከቱም እንኳን በእምነት እግዚአብሔር መኖሩን አታምኑምን? ብታምኑ መልካም ነው።" ሲል በትሕትና ጠየቃቸው። እነርሱም በጥያቄ መልክ ያቀረበላቸውን አስተሳሰቡን እና ምስክርነቱንም ተቀብለው የእግዚአብሔርን መኖር በእምነት አረጋገጥን አሉት።
👉  t.me/mezgebehaymanot👈

በዚህ የክርክርና የውይይት ሁኔታ ዓይነ ሥውሩ ቅዱስ ዲዲሞስ (በትሕትናውና በድክመቱ) የተናገሩትን አድምጦ የእነርሱን ዕውቀታቸውንና አስተሳሰባቸውን ተጠቅሞ ክብራቸውን ሳይጋፋ የእግዚአብሔርን መኖር በማሳመን ረታቸው። ክርክራቸውም በዚህ ተደመደመ።
👉  t.me/mezgebehaymanot👈

(#ብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ  "የሕይወት መንገድ" በመምሕር ሰለሞን በቀለ ከተተረጎመ መጽሐፍ የተወሰደ)

👉  t.me/mezgebehaymanot👈

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_ዕለተ_ሰንበት ❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot
 

መዝገበ ሃይማኖት

18 Oct, 04:18


ከገመዱ ላይ ምን ነበር

✥የማለዳ የነፍስ ስንቃችን

ሰውየው ከሰው በር ላይ የሆነ ነገር ይሰርቃል ትንሽ ቆይቶ ግን ይጸጸታል ተጸጸቶም አልቀረ የንስሐ አባቱ ዘንድ ሄዶ አባ  ገመድ ከሰው ደጅ ሰርቄያለው ይቅር ይበሉኝ ብሎ ይናዘዛል አባም የንስሐ ኑዛዜውን ተቀብለው ቀኖና ሰተው እግዚአብሔር ይፍታህ ብለው ሸኙት።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

በሌላ ጊዜ ሰውየው ተመልሶ መጣ አባ "ምነው መልሰህ በደልክ እንዴ" ሲሉ ጠየቁት ሰውዬውም እየተንተባተበ "አይ አባ የባለፈው ስርቆቴ ነው" አላቸው አባም "ላለፈውማ ቀኖና ሰጥቼ ንስሐ ገብተሃል እግዚአብሔርም ምሮሃል ሂድ" ብለው መለሱት ሰውየውም ቅር እየተሰኘ ሄደ። ነገር ግን ሄዶ አልቀረም ተመልሦ ለሦስተኛ ጊዜ መጣ። አባም ግራ ተጋብተው "አሁንስ ለምን ተመልሰህ መጣህ" ሲሉ ጠየቁት   ሰውየውም በፍርሃት ድምጽ "የ...የባለፈው ገመድ" አላቸው ያኔ አባ አንድ ነገር አስቡና ቀና ብለው በፈገግታ ከተመለከቱት በኋላ "ልጄ ከገመዱ ጫፍ ላይ ምን ታስሮ ነበር?" ብለው ጠየቁት ሰውየውም አንገቱን አቀርቅሮ በቀስታ "በ...በ...በሬ" አላቸው።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

እኛስ! ስንቶቻችን በሬ የሚያክል ኃጢያት ሰርተን የገመድ ንሰሐ ገብተን ይሆን? መልሱን ልቦናችን ያውቀዋል።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_ዕለት❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

ከዚሁ መንደር የተገኘ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot

መዝገበ ሃይማኖት

17 Oct, 02:23


በጸሎት ውስጥ በመትጋት ብዛት ወደ እግዚአብሔር መድረስ ትችላላችሁ !!

✥ የማለደ የነፍስ ሰንቃችን ትምህርት

✥እግዚአብሔርን ከወደዳችሁት ትጸልያላችሁ። አብዝታችሁ የምትጸልዩ ከሆናችሁ ከቀን ወደ ቀን ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር እየጨመረና እየጠለቀ ይሄዳል። ይህ ደግሞ የተለመደ ነገር ነው ምክንያቱም አንድ ሰው ከወደዳችሁ ከእርሱ ጋረ መነጋገርን ትወዱታላችሁና። ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ጸሎት ነው።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥በመጸለይ እንዴት መጸለይ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ። ለማለት የፈለግሁት ወደ እርሱ ፍቅር በሚመራችሁ መንገድ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ ትማራላችሁ ለማለት ነው።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥በጸሎት ውስጥ በመትጋት በጸሎታችሁ ውስጥ ወደ ምትናገሩት ወደ እያንዳንዱ ቃል ጥልቀት ልትደርሱ ትችላላችሁ። ከዚህ በተጨማሪ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ ወደ እግዚአብሔር እየተጠጋችሁ ትመጣላችሁ ከእርሱ ጋር ለመነጋገርም ትናፍቃላችሁ። ስለሆነም ጸሎት እንዴት እግዚአብሔርን መውደድ እንዳለባችሁ ያስተምራችኋል።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥እንዲህ ባለ ጠባይ በጸሎታችሁ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገሩ አንደበታችሁ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ እየለመደ ይመጣል። ይህ ደግሞ አዲስ ቋንቋ መማር የሚፈልግ ሰው ይመስላል። ይህ ሰው ይህን ቋንቋ በሚገባ ባያውቅና መጀመርያ ላይ ቢሳሳትም እንኳ ይህን ቋንቋ መናገር አለበት። ብዙ ጊዜ በመደጋገም ግን አንደበቱ ቋንቋውን ይለማመደዋል በሚገባ እስከሚጠቀምበት ድረስም ቀላል እየሆነለት ይመጣል።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥በእናንተም ቢሆን እንዲሁ ነው ይበልጥ ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገራችሁ ስትመጡ አንደበታችሁ ይበልጥ ከእርሱ ጋር መነጋገርን እየለመደ ይመጣል። ከዚህ በኋላ በፍቅር ስሜት ውስጥ ሆናችሁ ከእርሱ ጋር መነጋገርን ታውቃላችሁ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_ዕለት❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot

መዝገበ ሃይማኖት

16 Oct, 04:27


✥ታማኝ ሁን የማለደ የነፍስ ሰንቃችን ትምህርት

" በልያ ላይ ታማኝ ከሆንክ እግዚአብሔር 'ራሔልን' አደራ ይሰጥሃል እና 'በጲጥፋራ ቤት' ታማኝ ከሆንክ እግዚአብሔር 'በፈርዖን ቤተ መንግሥት' ላይ ያሳድግልሃል።  ‘በሚታየው’ ላይ ታማኝ ከሆንክ፣ እግዚአብሔር ‘የማይታየውን’ አደራ ይሰጥሃል፣ ‘በዚህ ሥጋዊ አካል’ ላይ ታማኝ ከሆንክ፣ እግዚአብሔር ‘መንፈሳዊውን አካል’ አደራ ይሰጥሃል። 
👉  t.me/mezgebehaymanot👈

ምስጢሩን በምታውቀው እና በሚታዘዝልህ 'በራስህ' ላይ ታማኝ ከሆንክ፣ እግዚአብሔር 'በሌሎች ነፍስ' ላይ አደራ ይሰጥሃል።  እግዚአብሔር በብዙ አደራ እንዲሰጥህ በጥቂቱ ታማኝ ሁን"
👉 t.me/mezgebehaymanot👈

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሺኖዳ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_ዕለት❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot
 

መዝገበ ሃይማኖት

16 Oct, 03:51


✥ሰቆቃወ ድንግል ዓዲ(ሌላ)፦
ኀበ አዕረፍኪ እግዝዕትየ ማርያም ታሕተ ጽላሎተ ዕፅ እምፃማ፤ፈያት ክልኤቱ ሶበ በጽሑኪ በግርማ፤ እምትሕዝብተ ሞቱ ማሕየዊ ለወልድኪ ንጉሠ
ራማ፤እፎኑ አዕይንትኪ ማያተ አንብዕ አዝንማ፤ አዕይትየ ለገብርኪ ክልኤሆን ይጽለማ
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ዚቅ፦
ሐፃቤ ርስሐትየ ይኩን አንብዕኪ ዘአንፀፍፀፈ ዲበ ምድር አመ ወልድኪ ይፄዓር በመልዕልተ
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥የሰንበት መዝሙር
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ፨ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤
ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ ፨ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ ፤
ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ ለደቂቀ ፳ኤል መና ዘአውረድከ ፨ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ ፨ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤
ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ ፨ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤ ወከመ ወሬዛ ኃየል መላትሒሁ ጒርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል ፨ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤
ሰማየ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ ፨ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤
በከዋክብት ሰማይ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ ፨ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ ፤
ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኩሉ ዕለት ፨ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤ ወኲሉ ይሴፎ ኪያከ፡፡
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈


✥ አመላለስ
ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤
ወኲሉ ይሴፎ ኪያከ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

አዘጋጅ :-በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ)✍️ አላቲኖስ

╔✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_በዓል❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot

  በዪቲዩብ ቻናላች ስብስክራይብ ያድርጉ
#ሰብስክራይብ #Subscribe በማደግ ይቀላቀላሉ https://youtube.com/channel/UC0-pqPv3c7alERhdDpW1wrQ

በ Facebook በፔጃችን "መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇...  ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉t.me/mezgebehaymanot👈 ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ🤳🤳🤳

[email protected]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
 

መዝገበ ሃይማኖት

15 Oct, 15:19


2017 ሦስተኛ ሳምንት ሰንበት የጽጌ ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋር አብረን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

✥ እንኳን ለጾመ ጽጌ ሦስተኛ ሳምንት በሰላም አደረሳችሁ ✥

✥ ሰላም ለኲልያቲክሙ / ነግሥ/

ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኀኒት መስቀል፡፡
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ዚቅ
ዝኬ ዘተዘርዓ ቃለ ጽድቅ በትውክልተ መስቀል፤ ወፍሬሁኒ ኮነ መንፈሰ ህይወት፤ ተስፋሆሙ ለእለ ድኅኑ፤ ወበጽጌሁ አርዓየ ገሃደ አምሳለ ልብሰተ መለኮት፤ ዕቊረ ማየ ልብን፤ ጽጌ ወይን ተስፋሆሙ ለጻድቃን።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ማኅሌተ ጽጌ፦
በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል፤
ወጸገይኪ ጽጌ በኢተሰቅዮ ማይ ወጠል፤
ወበእንተዝ ያሬድ መዓርዒረ ቃል፤ ምስለ ሱራፌል
ይዌድሰኪ ወይብል፤ ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ
በትእምርተ መስቀል።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ወረብ፦
በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል/፪/
ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ያሬድ ወይብል ሐጹር
የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል/፪/
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥. ትመስል እምኪ / ማኅሌተ ጽጌ /

ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤
ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ፤
ወካዕበ ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤
እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤
ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኪ ዕረፍተ፡፡
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ወረብ፦

ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እምኪ፤
ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ዚቅ፦

እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ፨ ወእምኲሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ፨ ከመ ትኲኖ ማኅደረ ለመንፈስ ቅዱስ፨ ወምስጋድ ለኲሉ ዓለም፡፡
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈


✥ማኅሌተ ጽጌ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፣
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፣ወንዒ ሠናይትየ
ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ
ርኅሩኅ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ወረብ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ ሰላማዊት፤ ተመየጢ ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ በአምሳለ ወርቅ ይግበሩ ለኪ ኮሰኮሰ ዘብሩር፤ አመ ወለደቶ አርአያ ወሰደቶ፤ በትእምርተ መስቀል፤ ትፍሥሕትኪ ውእቱ፤ ብርሃንኪ ውእቱ ሰላምኪ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ ዓዲ (ወይም)ዚቅ፦
ወይቤላ ንዒ ንሑር፤ኀበ ደብረ ከርቤ ውስተ
አውግረ ስኂን፤ እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ማኅሌተ ጽጌ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ ፣ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየሐቱ እምዕንቄ
ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ዚቅ፦
ነያ ሠናይት ወነያ አዳም፤ አግዓዚት ማርያም ጽርሕ ንጽሕት፤ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት
ወኁብርት፤ ወዲበ ርእሳኒ አክሊል፤ ፅሑፍ
በትምህርተ መስቀል።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ ዓዲ(ወይም) ዚቅ፦
በወርቅ ወበዕንቍ ወበከርከዴን ፤ ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ፤ትርሢ


✥ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየሐቱ እምዕንቄ
ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ዚቅ፦
ነያ ሠናይት ወነያ አዳም፤ አግዓዚት ማርያም ጽርሕ ንጽሕት፤ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት
ወኁብርት፤ ወዲበ ርእሳኒ አክሊል፤ ፅሑፍ
በትምህርተ መስቀል።

✥ዓዲ(ወይም) ዚቅ፦
በወርቅ ወበዕንቍ ወበከርከዴን፤ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት፤ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ፤ትርሢተ መንግሥቱ አንቲ መድኃኒቶሙ ለነገሥት
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ሰቆቃወ ድንግል፦
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ።

✥ወረብ፦
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም/፪/
ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ተዓይል/፪/
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ዚቅ፦
አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤
አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤ እንዘ ከመ ዝናም
ያንደፈድፍ፤እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ
ሐፍ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ወረብ፦
አመ አመ አጒየይኪ ዕጓለኪ በሐቂፍ/፪/
እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ እምአዕይንትኪ
አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ/፪/
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

መዝገበ ሃይማኖት

15 Oct, 06:33


ናታኒም ገብሬ ይባላል!ዛሬ ከንጋት ኮከብ ት/ቤት ወጥቶ እስካሁን ወደ ቤቱ አልተመለሰም!!እናትና አባት ተጨንቀዋል!
#ሼር በማድረግ አፋልጉን🙏
0910682333
0952444848
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

╔✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#አፋልጉኝ_እናተ_ደግ_ልቦች_❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

ስለ መልካም ትብብራችሁ ከወዲሁ ከልብ እናመሰግናለን 🙏🙏🙏

መዝገበ ሃይማኖት

15 Oct, 04:29


አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከቤተክርስቲያን የተገኘ ብሩህ ኮከብ

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ) አላቲኖስ

✥ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ (ግብጽ ) ነው :: አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌያስ ይባላሉ :: ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል :: አንድ ቀን አቅለያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን "" ንስኢ ወልደ ዘይትሌአል ቅርኑ አምኑኅ ሰማይ ... ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ "" የሚል ድምጽ ሰማች :: በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ ::
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

✥ አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው "" ስብሐት ለአብ , ስብሐት ለወልድ , ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን >> ብለው በማመስገናቸውና ሀላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ : ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መልአክትን ይመስላሉ ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመድብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ ፍሱሐ ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል :: አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአረገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል ::
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ከዚህ ቡሐላ ሐብተ ፈውስ ተሰጥቷቸውል :: በአንድ ቀን እልፍ እውራንን እና እልፍ አንካሳ ፈውሰዋል :: በዋላ ግን ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመጡ ግብር የሚያስፈቱአቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው :: በገድለህ : በትሩፋትህ : ከሞት ነፍስ ክርደት ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ ::
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው :: ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? "ዘኬድከ ጸበለ - እግረከ ይልህሱ ወበ ውእቱ ይጽግቡ ... የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ :: ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው : ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ ::
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ : አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር : በዚህ መልኩ 30 አመት ከቆዩ ቡሐላ ጌታ በአንድነት በሶስትነት ተገልጾ ምን ላደርግልህ ትሻለህ ? አላቸው ::
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድር ገቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት :: 3000 ሐጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል :: ከዚህ ቡሐላ ሁር ምድረ ኢትዮጵያ ወበህኒ አልውከ ነፍሳት ወታወጽኦሙ .... ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው :: ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል ::
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ዳግመኛም ወደ ዝቁዋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር :: 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ ዘገብረ ተዝካርከ ወዘጽውአ ስምከ እምህር ለከ ብሎሀል አላቸው ::
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከባህሩ አልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል :: ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ ተንስእ ወጽእ መሀርኩ ለከ ኩሎ ኢትዮጵያ ... ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል ::
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ከዚህ ቡሐላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7 አመት እንደ ትኩል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል :: ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው :: 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል :: ከዚያ ተነስተው ወደ ዝቁዋላ ሲሄዱ ስላሴን በአምሳሌ አረጋውያን ከጥላው ስር አርፈው አገኙዋቸው ::
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነንሀል አዝለክ አንድ አንድ ምህራፍ ሸኘን አሉዋቸው :: አዝለው ከሸኙዋቸው ቡሐላ በአንድነት በሶስትነት ሆኖ ታያቸው :: ድንግጠው ወደቁ : እግዚአብሔር ግን አንስቷቸው ሂድ ዝቁዋላ ሄደህ ጠላቶችህን ተበቀላቸው አላቸው :: በዛበነ መብረቅ ደርሰው 7 ቱን ሊቃነ መላእክት አጋዥ አድርገው እልፍ አእላፍ አጋንንትን አጭደዋል ::
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ፤
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

አዘጋጅ :-በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ)✍️ አላቲኖስ

ምንጭ ገድለ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ተአምር 14

╔✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_በዓል❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot

  በዪቲዩብ ቻናላች ስብስክራይብ ያድርጉ
#ሰብስክራይብ #Subscribe በማደግ ይቀላቀላሉ https://youtube.com/channel/UC0-pqPv3c7alERhdDpW1wrQ

በ Facebook በፔጃችን "መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇...  ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉t.me/mezgebehaymanot👈 ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ🤳🤳🤳

[email protected]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

መዝገበ ሃይማኖት

14 Oct, 07:01


የ2017 "#ጥቅምት5 " አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የ ክብረ #_በዓል_ሥርዓተ_ማኅሌት ላይ ከሊቃውንቱ ጋር አብረን እድናመሰግን እንደ ሚከተለው ተዘጋጅቷል

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለሕፅንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ፤ ማያተ ኢያሱ ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ፤ እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ፤ ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ፤ ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ዚቅ
በአፍአኒ አንትሙ፣ ወበውሣጤኒ አንትሙ፤ በገዳምኒ አንትሙ፤ ብርሃኑ ለዓለም (ለኢያሱ) አንትሙ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለሕፅንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤ ጸሎተ ቅዱሳን ውኩፍ፤ ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አእላፍ፤ ለረዲኦትየ ከመ ዘይሠርር ዖፍ፤ እንዘ ትሠርር ነዓ በ፪ኤ አክናፍ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ዚቅ
ከመ መዓዛ ቅዱሳን፤ ውስተ አብያተ ክርስቲያን፤ ይሰምዖሙ ጸሎቶሙ ለንጹሐን ከመ መዓዛ ቅዱሳን።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ዚቅ
እስመ ርእየ ሕማማ ለዓመቱ፤ ወገብረ ኃይለ በመዝራዕቱ፤ መዝገቡ ለቃል ጽጌ እንተ ኢትትነገፍ መድኃኒተ ሕዝብ፤ መዓዛሆሙ ለቅዱሳን።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኆኅያቲሁ ቅሩጽ፤ ኀበ ዓምደ ብርሃን ጽዱል ወአኮ ዘዕፅ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኃያል ሠዋቄ ትንቱናን እምዳኅፅ፤ ለዝክረ ስምከ ሠናየ ዜና ወድምፅ፤ ትሴብሕ ኢትዮጵያ ወትዜምር ግብፅ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ዚቅ
ኮከብ ብሩህ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ፤ ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ፤ ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ፤ አማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ፃማ ቅዱሳን ዲቤሁ አዕረፈ፤ አፈዋተ ወንጌል ጸገየ ዘልፈ፤ አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሃይማኖተ ተአጽፈ፤ ኀበ ዓምደ ወርቅ ስሙ ተጽሕፈ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ወረብ
ኮከብ ብሩህ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ/፪/
ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ አማን በአማን ሐዋርያ/፪/👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለጒርኤከ ኅሩመ መብልዕ ዘኮነ፤ ወእስከ ስቴ ማይ መነነ፤ ሶበ ረድኤተከ ርእዩ ወኪዳነከ እሙነ፤ ይቤሉከ ኲሉ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አቡነ፤ በኪዳንከ አሥራተ ንሥአነ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ወረብ
አሥራተ ንሥአነ አሥራተ ንሥአነ/፪/
ገብረ መንፈስ ቅዱስ አሥራተ ንሥአነ/፪/
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ዚቅ
በመንግሥተ ሰማያት ይነግሥ ምስሌከ፤ ኃጥእ ዘገብረ ተዝካረከ፤ ወጸውዓ ስመከ እንዘ ይብል አምላከ ተካየድከ፤ በእንተዝ ንሥአነ ለሕዝብከ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አሥራተ በኪዳንከ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለአዕጋሪከ እለ ኢሖራ በፍናዊሃ፤ ለዛቲ ዓለም ዘዕበድ ጥበባቲሃ፤ ለኢትዮጵያ ምድርነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያሃ፤ ውስተ ገፀ ኲሉ ደወላ ዜና ነገርከ በዝኃ፤ ወእስከ ጽንፋ ለምድር ነቢብከ በጽሐ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ዚቅ
ዝንቱሰ ብእሲ መምህርነ፤ ዘተፈነወ ውስተ ምድርነ፤ ይክሥት ብርሃነ ይፈውስ ዱያነ፤ ሐዋርያ ዘኮነ ወተሰምዓ ዜናሁ፤ ውስተ ኲሉ ምድር።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ወረብ
ዝንቱሰ ገብረ ሕይወት ተፈነወ ውስተ ምድርነ/፪/
ይክሥት ብርሃነ ይፈውስ ዱያነ ሐዋርያ ሐዋርያ ዘኮነ/፪/
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

አንገርጋሪ
ኮከብ ብሩህ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ፤ ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ፤ ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ፤ አማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

አመላለስ
አማን በአማን/፬/
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ/፬/
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

እስመ ለዓለም
ንጉሥኪ ጽዮን አሠርገዋ ለምድር በጽጌያት፤ ወለሰማይኒ በከዋክብት፤ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን፤ ብርሃኖሙ ለመሐይምናን፤ ዘየአምር እምቅድመ ሕሊና፤ ዘይኄሊ ልብ አርአየ ኃይሎ፤ በላዕሌነ ወጸገወነ ሠናይቶ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

አመላለስ
ዘይኄሊ ልብ አርአየ ኃይሎ/፪/
በላዕሌነ ወጸገወነ ሠናይቶ/፪
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ወረብ
ንጉሥኪ ጽዮን አሠርገዋ ለምድር በጽጌያት አሠርገዋ ለምድር/፪/
"ውእቱ ክብሮሙ"/፪/ ለቅዱሳን/፪/
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

አዘጋጅ :-በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ)✍️ አላቲኖስ

╔✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_በዓል❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot

  በዪቲዩብ ቻናላች ስብስክራይብ ያድርጉ
#ሰብስክራይብ #Subscribe በማደግ ይቀላቀላሉ https://youtube.com/channel/UC0-pqPv3c7alERhdDpW1wrQ

በ Facebook በፔጃችን "መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇...  ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉t.me/mezgebehaymanot👈 ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ🤳🤳🤳

[email protected]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

መዝገበ ሃይማኖት

14 Oct, 06:25


"ጥቅምት 4"የጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ክብረ በዓል #ሥርዓተ_ዋዜማው ላይ ከሊቃውንቱ ጋር አብረን እድናመሰግን እንደ ሚከተለው ተዘጋጅቷል

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

ዋዜማ
ሃሌ ሉያ
አንተ አጽናዕኮሙ ለአድባር በኃይልከ፤ ወቅኑታን እሙንቱ በኃይል፤ ዝንቱሰ ብእሲ መምህርነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ
አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ ጸሎትከ ወትረ ይብጽሐነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

እግዚአብሔር ነግሠ
ጼና አልባሲሁ ለአባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከመ ጼና ስኂን፤ አልባሲሁ ዘሜላት፤ ዘወረደ ውስተ ገነት፤ ከመ ይርአይ ሥነ ጽጌያት።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ይትባረክ
ኪያከ መሠረት እንተ ብነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ እስመ ጸሎተ ጻድቅ ይሰምዕ እግዚአብሔር፤ ይቤሎሙ ዮሴፍ ዳኅንኑ ዝስኩ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ ወየዋህ።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

ሰላም
ደምፀ ወተሰብከ ውስተ ዓለም፤ ዜና ምግባሩ ትሩፍ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ ኮከበ ገዳም፤ ደምፀ ወተሰብከ ውስተ ዓለም፤ ጽጉያን እሙንቱ እምጽጌ ሮማን፤ ወቀይሐን እምኮለ ገዳም፤ ደምፀ ወተሰብከ ውስተ ዓለም፤ ደቂቀ ኄራን ልዑላነ ዝክር ወስም፤ ደምፀ ወተሰብከ ውስተ ዓለም፤ እንዘ የዓርጉ መሥዋዕተ ሰላም፤ ደምፀ ወተሰብከ ውስተ ዓለም፤ ደምፀ ወተሰብከ ውስተ ዓለም።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈

አዘጋጅ :-በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ)✍️ አላቲኖስ

╔✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_በዓል❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot

  በዪቲዩብ ቻናላች ስብስክራይብ ያድርጉ
#ሰብስክራይብ #Subscribe በማደግ ይቀላቀላሉ https://youtube.com/channel/UC0-pqPv3c7alERhdDpW1wrQ

በ Facebook በፔጃችን "መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇...  ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉t.me/mezgebehaymanot👈 ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ🤳🤳🤳

[email protected]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

መዝገበ ሃይማኖት

14 Oct, 02:17


የሕጻኑ ልዮ መልስ

✥አንድ መምህር በስብከተ ወንጌሉ መርሐግብራቸው ስለ መንግስተ ሰማያት ጥሩ አድርገው ይተርኩና ሕዝብ ሁሉ መመሰጡን ሲያዩ "አሁን ከእናንተ መኻል መንግስተ ሰማያት መግባት የማይፈልግ አለ??" ብለው በጅምላ ሲጠይቁ ሁሉም በህብረት "የለም!" ብለው መለሱ።

✥ በዚህ ያልረኩት መምህር "እስኪ መንግስተ ሰማይምት መግባት የምትፈልጉ እጃችሁን ወደላይ አውጡ" ይላሉ። ሁሉም ያወጣል

✥አንድ ሕጻን ግን ትንንሽ እጆቹን በጉንጮቹ ላይ አድርጎ ክርኑን በጉልበቶቹ ላይ ተክሎ በሚያሳዝን አኳኋን ተቀምጦ መምህሩን ብቻ ያያል። የሕጻኑ ሁኔታ የገዛችው መምህር ወደ ሕጻኑ ጠጋ ብለው "ማሙሽዬ አንተ ለምን እጅህን አላውጣህም? መንግስተ ሰማይ መግባት አትፈልግም?" አሉት

✥ ሕጻኑም ነቃ ብሎ "መግባትማ እፈልጋለሁ ነገር ግን እናቴ ጉባኤው እንዳለቀ የትም መሔድ የለም ባስቸኳይ እቤት እንድትመጣ ስላለችኝ ነው" አለ ይባላል።

✥ሕጻኑ የእናቱን ዐደራ ማስታወሱ የሚደነቅ ነው። የሕጻን ነገር ያልነው ግን መንግስተ ሰማይ ላለመግባት ያቀረባትን ምክንያት ለመጥቀስ ነው።

✥ዛሬም በየዓውደ ምህረቱ ማዕደ እግዚአብሔር ተዘርግቶ፤በጸሎት በእግዚአብሔር ፊት ቆመን በቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጸሎት እየደረሰ ልባችን እቤት ሆኖ በሐሳብ ሰረገላ የተቋጠረ ሲፈታ፤ የተፈታ ሲቋጥር ጊዜውን የምንጨርስ ስንቶች አለን።

ጭንቀታችን ተወግዶ፣ ሐሳባችን ሞልቶ ፣የጎደለን በዝቶ ቢታየን እንኳን በምድራዊ ሐሳባችን ተገዝተን እንዳንቀር በፍጹም ልባችን ወደ አንተ እንድንቀርብ ቅዱስ አምላክ ሆይ አንተ እርዳን 👐

ከእነዚሁ መንደር የተገኝ

╔✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_ዕለት❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot

  በዪቲዩብ ቻናላች ስብስክራይብ ያድርጉ
#ሰብስክራይብ #Subscribe በማደግ ይቀላቀላሉ https://youtube.com/channel/UC0-pqPv3c7alERhdDpW1wrQ

በ Facebook በፔጃችን "መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇...  ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉t.me/mezgebehaymanot👈 ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ🤳🤳🤳

[email protected]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

መዝገበ ሃይማኖት

13 Oct, 00:28


✥የዕለተ ሰንበት የነፍሰ ስንቃችን

“ብዙ እናቶች ስቃይ ካለበት የወሊድ ሰዓት በኋላ ልጆቻቸውን ሌሎች እንዲመግቡላቸው ለእንግዶች ይሰጣሉ። ክርስቶስ ግን እኛ ልጆቹን በብዙ መከራ እና ስቃይ በመስቀል ላይ ከወለደን በኋላ ሌሎች እስኪመገቡን ድረስ አይተወንም። በገዛ ሥጋ እና ደሙ እየመገበ ራሱ ያሳድገናል። በዚህ ሁሉ መንገድም ከራሱ ጋር አንድ ያደርገናል።”
በንስሐ ወደእርሱ ቀርበን በቅዱስ ቍርባን ታትመን እራሳችንን አዘጋጅተን ወደ ጠራን እንድንሄድ በቸርነቱ ይርዳን አሜን 👐
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_ዕለተ_ሰንበት❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏
በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot

መዝገበ ሃይማኖት

12 Oct, 17:11


"ሰው ወደ ኃጢአት በተራመደ መጠን ሃሳቡ ደካማ ይሆናል። ወደ ኃጢአትም ያዘነብላል። በውስጡም ለኃጢአት ሥፍራ ያዘጋጃል። ተጨማሪ እርምጃ በተራመደ ቁጥር በልቡ ውስጥ የነበረው ፍቅረ እግዚአብሔር ይቀንሳል። መውደቁም ግልጽ እየሆነ ይሄዳል።
👉t.me/mezgebehaymanot👈

ስለዚህም በመጽሐፍ "አንች ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው" ተብሏል። (መዝ. 136፥8-9) የባቢሎን ልጅ (የምርኮ ሀገር) የተባለ ኃጢአት ነው። ልጆች የተባሉት ፈቃዳተ ኃጢአት ናቸው። እነዚህን ልጆች የተባሉ ፈቃዳተ ኃጢአት የሚፈጠፍጣቸው ዓለት የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። (1ቆሮ. 10፥4)  ስለዚህ ኃጢአትንና ፈቃዳቱን ሁሉ በክርስቶስ አጋዥነት የሚቋቋምና በአእምሮው ሲታሰብ ጀምሮ ኃጢአትን የሚጠላ ሰው ብፁዕ ነው።"
👉t.me/mezgebehaymanot👈

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_አዳር❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏
በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot

መዝገበ ሃይማኖት

11 Oct, 03:26


✥ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየሐቱ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
ማርያም አክሊለ ጽጌ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ/፪/
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ዚቅ
ከርካዕ ዘተተክለት በቤተ መቅደስ፤መራኁቱ ለጴጥሮስ፤አንቲ ውእቱ ደብተራ ስምዕ ዘጳውሎስ፤አማን አክሊሉ ለጊዮርጊስ
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ሰቆቃወ ድንግል
በቤተ መቅደስ ዘልሕቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ሥሩዓ፣ ኅብስተ ኅቡዓ ወጽዋዓ ወይን ምሉዓ፤እፎ ከመ ነዳይ ሲሳየ ዕለት ዘኃጥአ፤ተአገሠት በብሔረ ግብጽ ረኃበ ወጽምዓ፤አልቦ ከማሃ ዘረከበ ግፍዓ
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ወረብ፦
እፎ ከመ ነዳይ ዘኃጥአ ሲሳየ ዕለት/፪/
በቤተ መቅደስ ዘልሕቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ኅብስተ መና ኅቡዓ/፪/
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ዚቅ
እሴብሕ ጸጋኪ ኦ ዑጽፍተ ልብሰ ወርቅ እግዝዕትየ ወለተ ዳዊት ንጉሥ ዘተሐፀንኪ በቤተ መቅደስ ወተዓንገድኪ በፈሊስ እምሀገር ለሀገር እንዘ ተዓውዲ በተፅናስ
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥መዝሙር፦
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ፤ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ ለዘሀሎ መልእልተ አርያም።አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ።ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት ብሩህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወለምድርኒ አሠርገዋ በጽጌያት ንፁህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወሠርዓ ሰንበተ ለነባረ ያዕርፉ ባቲ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌ:ማ- መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት። ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ።
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥አመላለስ፦
መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት/፪/
ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ/፬/
👉t.me/mezgebehaymanot👈

አዘጋጅ :-በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ)✍️ አላቲኖስ

╔✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_በዓል❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot

  በዪቲዩብ ቻናላች ስብስክራይብ ያድርጉ
#ሰብስክራይብ #Subscribe በማደግ ይቀላቀላሉ https://youtube.com/channel/UC0-pqPv3c7alERhdDpW1wrQ

በ Facebook በፔጃችን "መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇...  ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉t.me/mezgebehaymanot👈 ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ🤳🤳🤳

[email protected]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

መዝገበ ሃይማኖት

11 Oct, 03:26


2017 ሁለተኛ ሳምንት ሰንበት የጽጌ ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋር አብረን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።

✥ እንኳን ለጾመ ጽጌ ሁለተኛ ሳምንት በሰላም አደረሳችሁ ✥

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

✥ ነግሥ
(የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል ፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤እንተ በሥሉስ ትትገመድ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከተ፤ሐረገ ወይን፤ሲሳዮሙ ለቅዱሳን፤ሐረገ ወይን፤ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ ወጸገወ ሰላመ ለኩሉ።
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ማኅሌተ ጽጌ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ(ጽላተ) ኪዳን፤ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፤ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን፤ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን፡፡
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ወረብ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን ዘኮንኪ ለዕረፍት ትእምርተ ኪዳን/፪/
ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ብርሃን ዕለተ ብርሃን/፪/
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ዚቅ
ሰንበቶሙ ይእቲ ለጻድቃን ትፍሥሕት፤ሰንበቶሙ ይእቲ ለኃጥአን ዕረፍት፤ኅቡረ ንትፈሳሕ ዮም በዛቲ ዕለት፡፡
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ማኅሌተ ፅጌ፦
ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዓረብ ወተርሴስ፤በድንግልና ማርያም ሥርጉተ ሥጋ ወነፍስ፤ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ፤ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ፤ እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ወረብ፦
እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ/፪/
ተአምረ ነቢር አርአይኪ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ/፪/
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ዚቅ
አንቲ ውእቱ ንጽሕት እምንጹሐን ድንግል ኅሪት ዘነበረኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ ሥርግው በወርቅ ንጡፍ ወልቡጥ በዕንቍ ባሕርይ ዘየኃቱ ዘብዙኅ ሤጡ ከመዝ ነበርኪ በቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽሑ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ አሠርተ ወክልኤተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፣ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ወረብ፦
ንዒ ርግብየ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሰናይትየ ወንዒ ሰናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ/፪/
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ አግዓዚት ከመ ጎሕ ሠናይት ታቦተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ዕፀ ጳጣስ ደብተራ ፍጽምት ማኅደረ መለኮት
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ዓዲ
ንዒ ርግብየ ኲለንታኪ ሠናይት ፀምር ፀዓዳ እንተ አልባቲ ርስሐት መሶበ ወርቅ እንተ መና በትረ አሮን እንተ ሠረፀት።
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ወቦ ዘይቤ ዚቅ
ይዌድስዋ ትጉሃን፤ይቄድስዋ ቅዱሳን፤ሰሎሞን ይቤላ ርግብየ ሠናይት፤ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ፍጽምት፤ዳዊትኒ ይቤላ ስምዒ ወለትየ ወርይዪ ወአጽምዒ ዕዝንኪ
👉t.me/mezgebehaymanot👈

✥ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
👉t.me/mezgebehaymanot👈

መዝገበ ሃይማኖት

10 Oct, 19:05


ቅዱሳን አባቶቻችን ሁል ጊዜ ከወደቃችሁ በኋላ ወዲያውኑ መነሳትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ አስፈላጊ ነው ይሉናል፡፡ ሁላችንም ያለማቋረጥ ኃጢአትን እንሠራለን፤ ተንሸራተንም እንወድቃለን፡፡ ምንም እንኳን በቀን መቶ ጊዜ ብንወድቅም ወደ ኋላ ዞር ብለን ሳናይ ተነስተን ወደ እግዚአብሔር መመለስ አለብን የሆነው ሆኗል፤ ያ ጊዜም አልፏል፡፡ ከእግዚአብሔር እርዳታ እንጠይቅ፤ ተስፋችንን ከውስጣችን ሊያጠፋ ለሚፈልገው ዲያብሎስ፤ "እግዚአብሔር ከእኔ በላይ እኔን ይወደኛል ይቅርም ይለኛል" እንበለው፡፡

(አረጋዊ ታዴዎስ)


╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_ዕለት❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏
በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot

መዝገበ ሃይማኖት

09 Oct, 07:53


╔✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_በዓል❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

አዘጋጅ :-በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ)✍️ አላቲኖ

6,006

subscribers

1,173

photos

37

videos