መሳጭ አባባሎች

@mesach_ababaloch


_________________
#AmharicQuotes
...
JOIN US

መሳጭ አባባሎች

22 Oct, 02:32


አንድ አይነ ስውር ህጻን ልጅ "አይነ ስውር ነኝ እባካችሁን እርዱኝ" የሚል ጽሁፍ ይዞ መንገደኛውን ይማፀናል

ከፊት ለፊቱ ባስቀመጠው የገንዘብ መሰብሰቢያ ዘንቢል ውስጥ ትንሽ ሳንቲሞች ተቀምጠዋል

በዚያ መንገድ ሲያልፍ የነበረ አንድ ሰው ሳንቲም ከመፀወተው በኃላ እይነ ስውሩን አስፈቅዶት ጽሁፉ የተጻፈበትን ወረቀት ገልብጦት ከጀርባው ሌላ ጽሁፍ ጻፈበት

ወዲያውኑ እግረኛው ሁሉ ዘንቢሉ ውስጥ ሳንቲም እየወረወረ ሞላው

የዚያኑ ቀን ረፋድ ላይ ሰውዬው ወደ አይነስውሩ ልጅ ባቀናበት ወቅት "ምን ብለህ ነው የጻፍከው? ከዚያን ሰአት ጀምሮ እኮ ዘንቢሌ በሳንትም ተሞላ" ሲል ይጠይቀዋል

"ዛሬ ደስ የሚል ቀን ነው: እኔ ግን ላየው አልችልም" የሚል ነው የጻፍኩልህ ብሎ መለሰለት

ሁለቱም ጽሁፎች የልጁን አይነስውርነት ይገልጻሉ ነገር ግን ሰዎች ሲያነቡት የኮረኮራቸው የዛሬን ቀን ውብነት ለማየት መታደላቸው ሲረዱ ነው ።

መሳጭ አባባሎች

17 Oct, 05:07


ምርጥ አባት !👌

ቢሊየነር እናትና ፡ ሚሊየነር አባት እያላቸው ያለሞግዚት የሚያድጉት ፡ የአሳፕ ሮኪና የሪሀና ልጆች ።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ አሳፕ ሮኪ ሲናገር. . እስከ 35 አመት ልጆች ሳልወልድ የቆየሁት በሞግዚት ለማሳደግ አይደለም ፡ ልጅ ከወለድኩ ያለሞግዚት ከባለቤቴ ጋር በመተጋገዝ እንደማሳድጋቸው ለራሴ የገባሁትን ቃል ነው አሁን እየተገበርኩ ያለሁት ።

ስለዚህ ሪሀና ቤት በማትኖርበት ወይም ፡ የሙዚቃ ዝግጅት ካላት ፡ ሁሉንም ነገር ትቼ ልጆቼን ለመንከባከብ የልጆቼ አባት እና ሞግዚት ሆኜ እቤት እውላለሁ ። መቼም ልጆቼ በሞግዚት አያድጉም ይላል ።
ምርጥ አባት !
(✍️ዋሲሁን ተስፋዬ )

መሳጭ አባባሎች

08 Oct, 13:56


የሆነ ገጽ ላይ አንብቤው ነው፡፡አሁን እኛጋ አብዛኛው በስፋት ያለ ይመስለኛል!

ሰባቱ ማሕበራዊ ኃጢያቶች
/The Seven Social Sins/-M.Gandi

1. በስራ ያልተገኘ ብልጽግና
/Wealth without work/

2. ሕሊና የሌለበት ደስታ
/Pleasure without conscience/

3. መልካም ባህሪይ የሌለበት እውቀት
/Knowledge without character/

4. ግብረ ገብነት የሌለበት ንግድ
/Commerce without morality

5. ሰብዓዊ ርህራሄ የሌለበት ሳይንስ
/Science without humanity/

6. መስዋእትነት የማይከፈልበት ኃይማኖት
/Religion without sacrifice/

7. መርህ አልባ ፖለቲካ
/Politics without principles/
ናቸው!

#Share

መሳጭ አባባሎች

04 Oct, 08:16


' እንዲህ ሆነች ብዬ '
****
አደጋ ቢያገኛት የኔዋን ቆንጅዬ ፡
እንደምን ልተዋት እንዲህ ሆነች ብዬ ፣
ድሮ ያኔ ድሮ እኔን ስትወደኝ ፡
ከሷ ፍቅር በቀር ከቶ ምን ነበረኝ ፣
ምን መልክሽ ቢጠፋ ቢበላሽ እሳቱ ፡
እኔስ ካንቺ ውጪ መች ሊሞቀኝ ቤቱ ፣
ፍቅር መሰጠት ነው ትርፍን የማይፈልግ ፡
አንቺን ትቼ ታድያ እንዴትስ ላፈግፍግ ፣
ዘመድ ጓደኞቼ ዛሬ ሰርጋችን ነው ፡
ምነው ለምትሉ ምላሹ ፍቅር ነው ።
*****
በክንፈ ጀማነህ ( የእልፍነሽ ልጅ)

መሳጭ አባባሎች

03 Oct, 07:45


Call us.
+251901135018

መሳጭ አባባሎች

02 Oct, 13:57


የመኖር ትርጉሙ

የመኖር ትርጉሙ፤
የእንባ ቅብብል ነው በትውልዶች መሀል፤
አባትህ ያነባው ላንተም ይደርስሃል፤
ሰው የሆንኩ ለታ ደርሶኛል ይህ እጣ፤
አልቅሼ እንደገባሁ አስለቅሼ ልውጣ።

✍️በውቄ በዳዳ

መሳጭ አባባሎች

26 Sep, 08:37


የእውቀት፣ የክህሎት እና የጥበብ ቅንጅት!

1. እውቀት ማለት፣ ምን እንደሚደረግ ማወቅ ማለት ነው፡፡

አንድ ሰው በአንድ ጉዳይ ላይ ምን እንደሚደረግ ያውቃል ማለት ስኬታማ ነው ማለት አይደለም፡፡ ብዙ ሃሳብ መሰንዘር የሚወዱና ተግባር ላይ ግን ብዙም የሌሉበት ሰዎች እዚህ ክፍክ ውስጥ ይመደባሉ፡፡

እንደዚህ አይነት ሰዎች ምን እንደሚደረግ የማወቃቸውን የመረጃ እውቀት ወደ “እንዴት ይደረግ” ደረጃ ሊያሳድጉት ይገባቸዋል፡፡

2. ክህሎት ማለት፣ አንድ ነገር እንዴት እንደሚደረግ ማወቅ ማለት ነው፡፡

አንድ ሰው በአንድ ጉዳይ ላይ ምን እንደሚደረግ ከማወቅ የጽንሰ ሐሳብ እና የመረጃ እውቀት አልፎ፣ እንዴት እንደሚደረግ ተግባራዊ እውቀት ሲኖረው እዚህ ይመደባል፡፡

ሆኖም፣ ምንም እንኳን እንዴት እንደሚደረግ የማወቅ ብቃቱና ልምዱ ቢኖረውም እሱ ብቻውን ረጅም ርቀት ላይሄድ ስለሚችል መቼ እና በምን መልኩ ሊረግ እንደሚገባው ወደማወቅ ደረጃ ማደግ ያስፈልጋል፡፡

3. ጥበብ ማለት፣ አንድ ነገር መቼ እንደሚደረግ ማወቅ ማለት ነው፡፡

በመረጃ መልክ ወደ ማወቅ የመጣነውን እና ከዚያም አልፈን እንዴት መደረግ እንዳለበት ክህሎቱን ያዳበርንበትን ነገር በወቅቱ መደረግ ይኑርበት እና አይኑበት የመለየት ብልሃት ጥበብ ይባላል፡፡ ምንም አይነት የመረጃም ሆነ ተግባራዊ ክህሎት የመጨረሻ ስኬታማነቱ ያለው በጥበብ ሲያዝ ነው፡፡

መረጃ-ተኮር ከሆነው እውቀት፣ ተግባር-ተኮር ወደሆነው ክህሎት፣ ከክህሎት ደግሞ ብልሃት-ተኮር ወደሆነው ጥበብ ስናድግ ከአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ቀደም ብለን እንገኛለን!

መሳጭ አባባሎች

20 Sep, 07:00


ለፈገግታ

ልጅ» እንዳባቴ ሃብታም መሆን ነው የምፈልገው።

ጠያቂው» አባትህ ሃብታም ነበር?
ልጅ» አይ እሱም እንደኔ ሃብታም መሆን ይፈልግ ነበር።

😆😂😂

ሃብታም መሆን ጥሩ ነው፤ ነገር ግን ሃብት ሁሉንም ነገር እንደማይገዛ ልንገነዘብ ይገባል።

መልካም ቀን!

መሳጭ አባባሎች

19 Sep, 05:35


1. ‹‹መከራ ሠውን ይሠራዋል፤ ቁሳዊ ብልፅግና ግን አስፈሪ ጭራቅ ያደርገዋል፡፡››

2. ‹‹ከሁሉ መጀመሪያ ሠው ሁን! የሠብዓዊነትን ቀንበር ለመሸከም አትፍራ፡፡››

3. ‹‹መሞት ምንም አይደል፡፡ አለመኖር ግን አስከፊ ነው፡፡››

4. ‹‹ብልህ ሠዎች ከሕይወት መከራ መፅናኛቸውን የሚፈልጉት ከመፅሐፍ ነው፡፡››

5. ‹‹ጊዜው ከደረሠ ሃሳብ በላይ ሃይለኛ የለም፡፡››

6. ‹‹ሌላ ሠው ማፍቀር የፈጣሪን ሌላኛውን ፊቱን ማየት ነው፡፡››

7. ‹‹የሃብታሞች ገነት የተሠራው ከደሃዎች ሲዖል ነው፡፡››

8. ‹‹የማያለቅሱ ማየት አይችሉም፡፡››

9. ‹‹ምንም ዓይነት ጦር ወይም መሣሪያ ጊዜው የደረሠ ሃሳብን ሊያስቆመው አይችልም፡፡››

10. ‹‹ሠዎች ጥንካሬ አላጠራቸውም፡፡ ያጠራቸው ፈቃድ ወይም ፍላጎት ብቻ ነው፡፡››

11. ‹‹ሕሊና ማለት በሠው ውስጥ የፈጣሪ መኖር ነው፡፡››

12. ‹‹ልማድ ወይም ሱስ ስህተቶችን መንከባከቢያ ስፍራ ነው፡፡››

መሳጭ አባባሎች

19 Sep, 04:30


የመጥረቢያ «ሌባ»

ሰውየው ገጠመኙን እንዲህ ያጫውተናል :-

«ትላንት መጥረቢዬ ጠፋኝ። ጎረቤቴ እንደሰረቀኝ ጠረጠርኩ🤔። በአይነ ቁራኛ ተከታተልኩት👀። አካሄዱ መጥረቢያዬን የሰረቀ ሰው አካሄድ ነበር🚶‍♂️። ንግግሩም መጥረቢያዬን የሰረቀ ሰው ንግግር ነበር🧔። እንቅስቃሴዎቹ ሁሉ መጥረቢያዬን እንደሰረቀ የሚያሳብቁ አይነት ነበሩ🕴። ሌሊቱን ሙሉ ቅስሜ ተሰብሮ አደርኩ🙄። ስለተዘረፍኩት መጥረቢያዬ በምን መንገድ መጠየቅ አለብኝ እያልኩ ሳሰላስል እንቅልፍ ሳይወስደኝ ነጋ🏜። ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ልጄ መጥረቢያውን በሳር ክምር ሸፍኖት አገኘሁ።😏

ዛሬ ደግሞ ጎረቤቴን ትላንት ባየሁት አይኖቼ በትኩረት አየሁት👀። መጥረቢያዬን የሰረቀ ሰው ምልክት አጣሁበት😏። ገጽታው ፋስ የሰረቀ አይመስልም😔። እንቅስቃሴው እና ንግግሩ የስርቆት ልምድ ያለው ሰው🙁 በጭራሽ አይመስልም። ሙሉ በሙሉ ንጹህ ሰው ሆኖ ታየኝ🧔። በመጨረሻም ሌባው እኔው እራሴ እንደነበርኩ አስተዋልኩ🙊። የጎረቤቴን አማና በልቻለሁ🙉። የጉርብትና ውሌን አፍርሻለሁ🙈። ንጹህ የሆነን ሰው በሌለበት በስርቆት ለመክሰስ አንድ ሌሊት ሙሉ ዕንቅልፍ ሳይወስደኝ እያሰላሰልኩ ከዕድሜዬ ላይ የተወሰነውን ክፍል ሰርቂያለሁ😡።»



በራሳችን መጥፎ ጥርጣሬ ምክኒያት እምነት ያጣንባቸው ስንት እና ስንት ንጹኋን አሉ ??? ኧረ ለመሆኑ በመጥፎ ጥርጣሬ ምክኒያት ስንት እና ስንት ቤቶች ፈረሱ ??? የስንት ህጻናት ቀሪ የህይወት ዘመን ተበላሸ ? በአጉል ጥርጣሬ ምክኒያት ስንት እና ስንት ደጋግ ጓደኞችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አጣን ???

ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጥያት ነውና እንዲሁ ለመጠራጠር ከመቸኮል ሰከን እንበል

መሳጭ አባባሎች

17 Sep, 13:26


ይነበብ❗️
የአነቃቂ ንግግር ዲስኩር አቅራቢ እንዲህ ሲል ለተሰበሰበው ህዝብ ንግግር አደረገ፣
"የህይወቴ ምርጥ ጊዜያት ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ያሳለፍኳቸው ጊዜዎች ናቸው"
ይህንን ሲናገር ህዝቡ በድንጋጤ ክው አለ። ተናጋሪው የህዝቡን ስሜት ከተረዳ በኋላ እንዲህ ሲል ጨመረበት ፣
"ያቺ ሴት እናቴ ናት! " ብሎ ሲናገር ህዝቡ በፉጨትና በጭብጨባ አቀለጠው።
ይህንን ንግግር ያዳመጠው ሌላው ሰው ቤቱ ሄዶ ሊሞክረው ፈለገና ራት ላይ ለሚስቱ "የህይወቴ ምርጥ ጊዜያት ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ያሳለፍኳቸው ጊዜዎች ናቸው...." ብሎ ቀጣዩን ሃሳብ ከመናገሩ በፊት ሚስቱ በያዘችው የጋለ መጥበሻ አናቱን ብላው አሁን ሆስፒታል ይገኛል።
ባሻዬ!
1.የአንዳንድ አነቃቂዎችን ንግግር እንደ አደገኛ ጨዋታ በቤት ውስጥ አትሞክረው፣
2. copy ያደረግኸውን ንግግር በአግባቡ paste ካላደረከው አደጋው የከፋ ነው።
በአጭሩ Don't copy if you cannot paste.

ተፃፈ፡ በተስፋዬ ሀይለማርያም(ባሻዬ)

መሳጭ አባባሎች

17 Sep, 03:58


የንቦች እድሜ ዘለግ ታለ አርባ ቀን ነው። በዚህ ድሜያችው ብዙ ማይሎችን ተጉዘው አበቦችን ቀስመው ማር ይሰራሉ። አንድ ንብ በህይወት ዘመኑ ካንድ የቡና ማንኪያ የማይበልጥ ማር ነው የሚሰራው። ማሩን የሚሰሩት ለራሳቸው ሊመገቡት ነው።

የሚገርም እውነት
አርባ ቀን ብቻ ለመኖር ማር ይሰራሉ
አርባ ቀን ብቻ ኖረው ማር ይሰራሉ
አርባ ቀን ብቻ ኖረው ብዙ ሺ አበቦችን ይቀስማሉ
አርባ ቀን ብቻ ኖረው ብዙ እጥዋቶች ንዲራቡ ምክኛት ይሆናሉ
አርባ ቀን ብቻ ኖረው በሰሩት ማር መድሃኒት ይሰራል፥ ለምግብነት ይውላል፥ ሰሙ ጧፍ፥ ተረፈ ምርቱ ለከብቶች ምግብም ይሆናል።

ጥያቄው አንተ አርባ አመት ኖረህ ምን ሰራህ ነው!!!

Fun fact

የማር እንጀራ ባለ ስድስት ጎን ቅርፁን ያገኘው ከንቦች የክንፍ ውልብልቢት በሚወጣ የድምጥ ፍሪኩዌንሲ ነው። ምን ማለት ነው፥ በድምጥ ፐርፌክት ቅርን መስራት ይቻላል። አንድ ጎበዝ ታዳጊ በድምጥ ፍሪኩዌንሲ ታግዞ ግርጦችን የሚሰራ 3D printer አንድ ቀን ሰርቶ ያሳየን ይሆናል። the sky is the limit if you observe clearly and if you observe better!


Source - Fb

መሳጭ አባባሎች

15 Sep, 02:17


Remember the Kodak company? In 1997, Kodak had about 160,000 employees.
And about 85% of the world's photography was done with Kodak cameras. With the rise of mobile cameras over the past few years, Kodak Camera Company is out of the market. Even Kodak went completely bankrupt and all his employees were fired.

At the same time many more famous companies had to stop themselves. Like

HMT (clock)
BAJAJ (स्कूटर)
DYANORA (TV)
MURPHY (RADIO)
NOKIA (Mobile)
RAJDOOT (Bike)
Ambassador (car)

None of the above companies had bad quality. Why are these companies out yet? Because they could not change themselves over time.

Standing in the present moment you probably don't think how much the world could change in the next 10 years! And today's 70%-90% jobs will be completely over in the next 10 years. We are slowly entering the era of "Fourth Industrial Revolution".

Check out today's famous companies-

UBER is just a software name. No, they have no cars of their own. Yet today the world's largest taxi-fair company is UBER.

Airbnb is the largest hotel company in the world today. But funny thing is they don't own a single hotel in the world.

Similarly, examples of countless companies like Paytm, Ola Cab, Oyo rooms etc can be given.

There is no work for new lawyers in America today, because a legal software called IBM Watson can advocate much better than any new lawyer. Thus, almost 90% of Americans will not have any jobs in the next 10 years. The remaining 10% will be saved. These will be 10% experts.

The new doctor is also sitting down to work. Watson software can detect cancer and other diseases 4 times more accurately than humans. Computer intelligence will surpass human intelligence by 2030.

90% of today's cars will not be seen on the roads in the next 20 years. Leftover cars will either run by electricity or hybrid cars. The roads will slowly become empty. Gasoline consumption will decrease and oil producing Arab countries will slowly become bankrupt.

If you want a car you have to ask for a car from a software like Uber. And as soon as you ask for a car, a completely driverless car will come and park in front of your door. If you travel with several people in the same car, the rent of a car per person will be less than a bike.

Driving without driver will reduce the number of accidents by 99%. And this is why car insurance will stop and car insurance companies will be out.

Things like driving on earth will no longer survive. Traffic police and parking staff won't be required when 90% of vehicles disappear from the road.

Just think, there used to be STD booths in the streets even 10 years ago. All these STD booths were forced to close after the mobile revolution came in the country. Those who survived have become mobile recharge shops. Again online revolution in mobile recharge. People started recharging their mobile online sitting at home. Had to replace these recharge shops again. Now these are just mobile phones to buy and sell and repair shops. But this will also change very soon. Mobile phone sales are increasing directly from Amazon, Flipkart.

The definition of money is also changing. There used to be cash but in today's age it has become "plastic money". Credit card and debit card round was a few days ago. Now that too is changing and the era of mobile wallet is coming. Growing market of Paytm, one click of mobile money.

Those who cannot change with age, age removes them from the earth. So keep changing with the times.

Keep creating great content, keep moving with time.

TMA

#themodernafrica


በደንብ ይነበብ፣ እራሳችንን እና ልጆቻችን እናዘምን።

ወደድንም ጠላንም መጭው ጊዜ ይሄው ነው!

መሳጭ አባባሎች

13 Sep, 05:55


እውነተኛ ሰዎች ስትለያቸው ያለቅሳሉ፣ ሃሰተኛ ሰዎች ደግሞ እያለቀስክ ጥለውህ ይሄዳሉ።

ፈጣሪ ከሃሰተኛ ሰዎች ይጠብቃችሁ..!

መልካም ቀን!

መሳጭ አባባሎች

12 Sep, 08:47


አዲስ ዓመት ትናንት ወይስ ዛሬ ብላችሁ ለተወዛገባችሁ በሙሉ፤ 🤠

መልካም አዲስ ዓመት!

መሳጭ አባባሎች

03 Sep, 16:57


አቁም

👉 የማይፈልጉህን መፈለግ።

👉 ስለ ሰው አብዝቶ መጨነቅ።

👉 ያንተ ያልሆነ ፍቅር ማሳደድ።

👉 እራስህን ከሌሎች ጋር ማወዳደር።

👉 ሰዎች ላይ ጥገኛ መሆን።

👉 ስማይረዳህ ሰው ችግርህን መናገ።

ይቀላቀላሉን 🙌

መሳጭ አባባሎች

02 Sep, 03:29


ሰውየውም ምንም እንኳን ስሜት አካልቦት መጥፎ ድርጊት ለመፈፀም ቢነሳሳም ከዚያ በፊት ባለው ህይወቱ በጥሩ እምነት ታንፆ ያደገ ነበርና ይህንን ስትለው ወደ ቀደመ ማንነቱና እምነቱ ተመልሶና የጋለው ስሜቱ ሙሽሽ ብሎ ቀዝቅዞ ይቅርታ ጠይቆ ምንም ሳያደርግ አሰናበታት ይባላል።
ውድ አንባቢ! አንተስ ከታሪኩ ምን ተማርክ? ፈጣሪህን የሚያህ መሆኑን ረስተህ ወይም ንቀህ ሰውን ግን ፈርተህ ተደብቀህ የፈፀምከው ድርጊት አለ?
_________
አስተማሪና አዝናኝ ፅሁፎችና ቪዲዮዎች እንዲደርሷችሁ ገፅን Follow አድርጉ!

መሳጭ አባባሎች

02 Sep, 03:27


አንዱ በር ግን መቸም አይዘጋም!
በአንድ ወቅት አንድ በፈጣሪ የሚያምን የተከበረ ሰው ባልና ሚስት የሆኑ ድሀዎችን በአትክልተኝነት ይቀጥራቸዋል። ይህ የተከበረ ሰውዬ አንድ ቀን በረንዳው ላይ ቁጭ ብሎ ሲመለከት የአትክልተኛው ሚስት በጣም ውብ መሆኗን ያይና ያለወትሮው ስሜቱ ይነሳሳበታል። ከእሱና ከእነሱ በቀር በግቢው ውስጥ ማንም እንደሌለ ካረጋገጠ በኃላ ሆን ብሎ ባሏን የሆነ ነገር እንዲያመጣለት ራቅ ወዳለ ቦታ ይልከዋል። ባሏ ወደተላከበት ቦታ ሲሄድ እሱና የአትክልተኛው ሚስት ብቻ ይቀራሉ። ይህኔ ይህ የተከበረ ሰው የአትክልተኛውን ሚስት ጎትቶ ብዙ በር ወዳለው ዘመናዊ ቤቱ ያስገባታል። ልጅቱም ሰውየው ኃያልና የተከበረ ስለሆነ እምቢ ብለው ባሌንም ሆነ እኔን ሊጎዳን ይችላል ብላ በመፍራት ዝም ብላ ትገባለታለች።
ሰውየው ቤቱ ውስጥ ካስገባት በኃላ ልብሶቹን እያወላለቀ፡- "ማንም እንዳያየን ሁሉንም በሮችን ዝጊያቸው ይላታል።"
ልጅቱም በሮችን ስትዘጋጋ ከቆየች በኃላ፡- "አሁን የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ ጌታዬ! ከአንዱ በር በቀር ሁሉንም ዘግቻቸዋለሁ። አንዱን በር ግን መዝጋት አልቻልኩም!" ትለዋለች።
ሰውየውም ዞር ዞር ብሎ አይቶ ሁሉም የቤቱ በሮች እንደተዘጉ ካረጋገጠ በኃላ ስለየትኛው በር እንደምታወራ ግራ ገብቶት፡- "የትኛውን በር ነው መዝጋት ያልቻልሽው?" ሲላት
ልጅቱም አንገቷን ደፍታ፡- "አይታይዎትም ጌታዬ! በእኛና በእግዚአብሄር መካከል ያለው በር እኮ ክፍት ነው። ልዘጋው ብሞክርም አልቻልኩም። እሱም ከቅድም ጀምሮ እያየን ነው። ከቻሉ እርስዎ ይዝጉትና የፈለጉትን ያድርጉ።" ብላ መለሰችለት።

መሳጭ አባባሎች

29 Aug, 03:51


This is what a king looks like in his last moments of life 🦁
The scene was captured by photographer Larry Pannell, who released this shocking photo in 2018 📸.

"We found him lying in the grass, exhausted and unable to move. We were no more than a meter away from him as he died in the shade of a tree. Dropping my camera, we stared at each other, closing our eyes for what seemed like an era. I just wanted him to know that he wouldn't die alone as he struggled to breathe, his chest only gets hurt from time to time. Then one last tickle, his last breath, he was gone. The king was dead.

Life is short. Power is ephemeral. Physical beauty is short-lived, I have seen it in lions. I have seen it in old people. Everyone who lives long enough will become weak and very vulnerable at some point.

Therefore, let us be humble. Help the sick, the weak, the vulnerable and most importantly never forget that we will leave the stage one day.

Credit: Larry Pannell.

መሳጭ አባባሎች

25 Aug, 07:33


ባቡጀ ነፍስ ይማር 😥😥😭


ባቡጂ ጌታቸው :-

ሰይፉ ጥያቄ :- 40 ሺህ መፅሐፍ አንብበሀል ?

ባቡጂ ጌታቸው መልስ :- አያ ከ14 ሺህ በላይ መፅሀፍት አንቢቢያለሁ

* የመጀመሪያ ፍቅረኛዬን ክበብ ይዣት ሄጄ

* በ35 ሳንቲም ኬክ
* በ25 ሳንቲም ወተት ጋበዝኳት

* ሴት በጣም ነው የምወደው

* የመጀመሪያ ፊልሜን ስሰራ 2ቴ ማሳል ብቻ ነበር 2ቴ አስዬ ፊልሙ ሲመረቅ አባቴን ምርቃት ላይ ጋበዝኩት

* አባቴን ፊልሙን ካዩው በኃላ አባቴ የታለህ ሲለኝ አግዳሜ ወንበር ላይ ማስለው እኔ ነበርኩኝ አልኩት ከዛ ዘጋኝ ከ2 ቀን

* ኬክ ጋጋሪ ነበርኩኝ
* ቀለም እቀባ ነበር
* የቀን ስራ እሰራ ነበር

* ፊስቡክ ሰው ሲጠቀም ሳይ ይደክመኛል

ባቡጂ በአንድ ወቅት ከተናገረው !

ባቡጂ የልጅነት ድምቀታችን ነበር በርካታ ፊልሞች ላይ ተውኗል !!
በተለይ ኮሜዲ ዘውግን ይችልበታል !!
ግን በቃ የመኖር ግዳጁን ፈፀመ !!

ነብስህ በሰላም ትረፍ !!