ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

@mahkelay


ይህ ለማዕከላውያን ክፍል አባላት የተዘጋጀና የተለያዩ የክፍሉ ማስታወቂያዎች እና መረጃዎች የሚለቀቁበት ይፋዊ ገፅ ነው።

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

21 Oct, 19:19


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ለጥቅምት አማኑኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል መዝሙር ማጥናት የሚችሉ አባላት ስም ዝርዝር
ቤዛዊት ትግሉ
ናርዶስ ዮሐንስ
ኑሃሚን ይርጋ
ረቂቅ ተሰማ
ፅናት ክብሩ
አስቴር ግዛቸው
ቤተልሄም ስዮም
ትዕግስት አንድአምላክ
ፍቅር ፍቃዱ
መቅደላዊት አላቅማቸው
ኩሜ ተገኝ
ቤዛዊት ገዛኸኝ
ሰላም ጌታሰው
ኤፍራታ ኢዮብ
ቃልኪዳን አድማሱ
ዮርዳኖስ ተገኝ
ቃልኪዳን ፈለቀ
የአብስራ በላቸው
ጽዮን ስንታየው
ረድኤት ሰለሞን
ሰላም ግርማ
ሰላም ከበደ
ያኔት ታሪኩ
ፍሬህይወት መውለድደግ   
መስፈርት አባላት ክትትል አቴዳንስ ብዛት የታየው ከ37 አቴንዳንስ 70% ትምህርት ክፍል ውጤት ከ100 30%  ነው

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

21 Oct, 16:16


ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ pinned «፨ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ። - ነገ የተጨማሪ ቀን ትምህርት ይጀምራል ። ሰዓት : 10:45 ቦታ : አዳራሽ ማሳሰቢያ : ማርፈድም መቅረትም አይቻልም።»

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

21 Oct, 16:06


፨ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ።
- ነገ የተጨማሪ ቀን ትምህርት ይጀምራል ።
ሰዓት : 10:45
ቦታ : አዳራሽ
ማሳሰቢያ : ማርፈድም መቅረትም አይቻልም።

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

19 Oct, 12:36


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

እንኳን ለዘመነ ጽጌ 3ኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ በሰላም አደረሳችሁ።

በኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁለተኛ ሳምንት የጽጌ ማኅሌትን በአንድ ልብ በአንድ ቃል ለማመስገን ይረዳን ዘንድ  ይህ ስርዓተ ማኅሌት እንደሚከተለው ቀርቧል።

🌸 እንኳን አደረሳችሁ🌸

🏡ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
https://t.me/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org

🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

19 Oct, 06:55


ለጥቅምት አማኑኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል መዝሙር ማጥናት የሚችሉ አባላት ስም ዝርዝር
1.ቤዛዊት ትግሉ
2.ናርዶስ ዮሐንስ
3.ዳናዊት ኤልያስ
4.ኑኃሚን ይርጋ
5.ረቂቅ ተሰማ
6.ጽናት ክብሩ
7.አስቴር ግዛቸው
8.ቤተልሔም ስዩም
9.የዓለምወርቅ ግርማ
10.ትዕግስት አንድአምላክ
11.ሩት ተመስገን
12.ፍቅር ፍቃዱ
13.መቅደላዊት አላቅማቸው
14.ርብቃ ክብሩ
15.ኩሜ ተገኝ
16.ቤዛዊት ገዛኸኝ
17.ሰላም ጌታሰው
18.ኤፍራታ እዮብ
19.ሔለን እንዳለ
20.ቃልኪዳን አድማሱ

መስፈርት
አባላት ክትትል አቴዳንስ ብዛት የታየው 37 አቴንዳንስ
70% አቴንዳስ

ትምህርት ክፍል ውጤት ከ100
30% ውጤት

ቅሬታ ከመርሐ ግብር በኋላ ቢሮ
በተለያየ ምክንያት መሰለፍ የማትችሉ አባላት እንድታሳውቁ ይሁን

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

17 Oct, 18:42


ከመደርደሪያችን

             የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል  
           እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት

       የሕይወት ምግብ የሆኑትን ቅዱሳት መጻሕፍት    
 ሊመግብዎ መደርደሪያውን ሞልቶ ይጠብቅዎታል።
    ከመደርደሪያዎ ሊጠፋ የማይገባውን ይህንን መጽሐፍ በቤቶ ከተሰነዱ ሌሎች መጻሕፍት ጋር ቤተሰብ እንዲያደርጉት እና በቃሉ ተጠቅመው ወጣትነቶን እንዲያሳምሩ  የሰንበት ት/ቤታችን ሱቅ የጀርባው ዋጋ 400 የሆነውን መጽሐፍ በ 20 % ቅናሽ በዚህ ዋጋ 320  ለአንባብያን አቅርበናል።

ይህ ቅናሽ የሚቆየው እስከ መጽሐፍ ዳሰሳው ቀን ብቻ ነው ያለን ኮፒዎች ጥቂት ስለሆኑ ቀድመው በማዘዝ መውሰድ ይችላሉ።

ለማዘዝ https://t.me/mes_suk

እና 0989196891 ይደውሉ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

17 Oct, 13:27


እነሆ ክረምቱ አለፈ በረከትም ሆነ ምድርም በአበባ ተጌጠች ተሸለመች
# ፅጌ ማለት አበባ ማለት ሲሆን ዘመነ ፅጌ ማለት የአበባ ወራት (ወቅት )ማለት ነው። የተዘራው ዘር በቅሎ ለፍሬ ዝግጁ መሆኑን የምናይበት መሬት ደምቃ አሸብርቃ የምትታይበት ወቅት በመሆኑ ነው
* ከመስከረም26 ጀምሮ እስከ ህዳር 5 ቀን ያለውን ወቅት ቤተክርስትያናችን ዘመነ ፅጌ እያለች ትጠራዋለች
# ዘመነ ፅጌ የክረምቱን ማለፍ ተከትሎ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በእናቱ ጀርባ ላይ ሆኖ ንጉስ ሔሮድስን ሽሽት ወደ ግብፅ ሀገር መሰደዱን የሚታሰብበት ወቅት ነው።
* በዚህ ወቅት የእመቤታችንን ከልጇ ጋር በበረሀ መሰደድዋን በማሰብ ሊቃውንቱ በሰንበት ማህሌተ ፅጌ የተሰኘውን የአባ ፅጌ ድንግልን እና የአባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሀንታ ድርሰት በማህሌት ይቆሙታል።
# የእመቤታችንን ፍቅሯን እናትነቷን አማላጅነቷን በማሰብ ሊቃውንቱ ጋር ሆነን በዝማሬ እናወድስበታለን እመአምላክን ከነልጇ እናስብበታለን።

* ፈልቀሽ የተገኘሽ ከአፈ መላእክት፣
ያሬድ የተማረሽ ከላይ ከሰማያት፣
እንከን የሌለብሽ አዲሷ ምስጋና።

# ምስጢርሽ ሲገለጥ በአስደናቂ ዜማ፣
ከሰማይ መንጭተሽ በምድር ሲሰማ፣
በቃናሽ መሰጠሽ ልቡናን በመክፈት፣
ማርከሽ ትወስጃለሽ ነፍስን ወደ ገነት።

* የፍቅር መግለጫ የሕይወታችን አርማ፣
ጣእምሽ ልዩ ነው ሲገለጥ በዜማ።
የአድባራቱ ሁሉ ቋንቋና ድምጻቸው፣
የካህናት ቅኔ ሰምና ወርቃቸው፣
ለህዝብ ሁሉ የነፍስ ምግባቸው፣
ማኅሌት እኮነሽ ጸጋና ሃብታቸው

# ደረሰ ሰዓቱ_እንገስግስ መቅደሱ
ሊዘረጋልን ነው_ቅኔ መወድሱ
የአባ ጽጌ ድንግል_የምስጋናው ሻማ
ሊበራ ሊነድ ነው_ለነፍስ የሚስማማ

# ተጠርተው በፍቅሩ_ የሄዱት ምዕመናን
መስቀልያ አጣፍተው_ተውብው በብርሃን
ሐሴት ተጎናፅፈው_በቅድስቷ ድንኳን
ሲታይ በረከቱ_ መዓዛ ወ ዕጣን
ይወስዳል በሀሳብ_ ወደ ሰማይ ዙፋን።

* የስደቷን ነገር_ መከራዋን አይቶ
ከአለማመን መንፈስ_ ፈቅዶ ተለይቶ
የክርስቶስ ፍቅር_ እውነቱ ሲገባው
ጣቶቹን አንስቶ_ ማሕሌቷን ጻፈው
አባ ጽጌ ድንግል_ የእውነት አበባ ነው።

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

17 Oct, 09:58


እንባ
ከፈሳሾች መርጠህ ካደረከኝ እንባ
አልቃሹን አድርገው ለሀጥያቱ ሚያነባ
ልክ እንደ ይሁዳ ጩኸቱ ላይሰማ
ፀጥታ በዋጠው በቀለጠው ጩኸት
                       ልቡን ከሚያደማ
ልክ እንደ ከሀዲው ትንቢቱን ፈፃሚ
ደብዛዛውን ስህተት በጥፋት አቅላሚ
መፍሰስ እንኳ ባልችል ከባለሽቷይቱ
አሳልፈህ አትስጠኝ ለእንደዚ አይነቱ
ምሕረትን ያሰጠ ልብህን ያባባ
መሆን እንኳ ባልችል የራሄልን እንባ
ሳቁ አንሰቅስቆት ከሚያነባ ከንቱ
የሳቅ ቀመር ከእንባ ከተምታታ ስልቱ
ከአለም ወራዚ ቋሳን ከሸመቀ
እንደባልቴት ዲናር ራሱን ከደበቀ
ልክ እንደ ጨለማ ላይዛለቅ ነገር
ምሕረትን ባያሰጥ ሽባን ባይተረትር
ከሕግህ ጠባቂ ከቅዱስ ባልወርድም
ነካታን ፈውሼ ላዘልል አልልም
እንደእናትህ እንባ ፍጥረትን ባልቀድስ
ከንቱነት ካሰረው በከንቱ ከሚያለቅስ
ከእንደዚ አይነቱም እባክህ አልፍሰስ
መሆን እንኳ ባልችል አፅናኝ የዘመኑ
ከንቱ እንዳያፈሰኝ መልሰኝ ከአይኑ ።

                     ፀሀፊ:- ቅድስት ጌታሁን
                         ከሥነ-ፅሁፍ ክፍል

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

15 Oct, 03:19


ለድርሰት ቡድን አባልነት የተመዘገባችሁ
1,ዮናስ እልኩ
2,አማኑኤል ተስፋዬ
3,ፅዮን አንሙት
4,ቃልኪዳን ብርሀኑ
5,ራኬብ አሸብር
6,ገሊላ ስለሺ

     ከዚህ በላይ ስማቹ የተጠቀሰ አባላት ለድርሰት ቡድን መግቢያ ፅሁፍ አስገቡ ተብላችሁ አላስገባችሁም እና የውድድር ጊዜው ሳያበቃ ሀና እንድሪስን (    @Hana_Endris28 ) እንደታወሯት ይሁን

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

14 Oct, 09:46


ምድብ ዩሐንስ አፈወርቅ
 
1. ኤደን ጠንክር
2. ዮርዳኖስ አለማየሁ
3. ማህሌት አድነው
4. ተአምር አበበ
5. እድላዊት ዮሴፍ
6. እድላዊት ዳዊት
7. ቤተልሔም ሀብታሙ
8. መቅደላዊት ትእግስቱ
9. ሔለን እንዳለ
10. የዓለምወርቅግርማ
11. ምህረት ኤርምያስ
12. ቤተልሔም ስዩም
13. ፍቅርተ ሲሳይ
14. ሃና ባህሩ
15. ቃልኪዳን አስራት
16. ምህረት ደሳለኝ
17. ሜሎና በዳሳ
18. ሕይወት ኤልያስ
19. ይድድያ ፈጠነ
20. ቃልኪዳን ደጀኔ
21. ማህደር ወንደሰን
22. ጫልቱ ተስፋዬ
23. ትዕግሥት ዘውዴ
24. መስከረም ቢረዳ
25. ቅድስት ጌጡ
26. እናት በቀለ
27. ዮሃና ኤፍሬም
28. ኤፍራታ እዮብ
29. ሔርሜላ ኃ/ገብርኤል
30. ጽዮን ካሳሁን
31. ሳሮን አዲስ
32. አስቴርፈታ
33. ሃና ሽፈራው
34. ትዕግሥት ሳህሌ
35. ፅጌረዳ ድንቅነህ
36. ረድኤት ዳንኤል
37. ምህረት ደበበ
38. ኑኃሚን ብርሃኑ
39. በለጠች አሰግደው
40. ምህረት ታደሰ
41. እድላዊት አሰግደው
42. ቤዛዊት ገዛኸኝ
43. ጽዮን ጌታነህ
44. ሰላም ግርማ
45. ሔዋን ፍቃዱ
46. ቅድስት ገ/ሚካኤል
47. ኤልዳና ቀኝጌታ
48. መቅደላዊት እንዳለ
49. ጁልያና ቀኝጌታ
50. ባንተ ሲሳይ
51. ኢዮብ ጠንክር
52. ዘዳግም ባህሩ
53. በእምነት አለማየሁ
54. ዮናስ ኤፍሬም
55. ናትናኤል ወንደሰን
56. ዳናዊት ኤልያስ
57. ኤልዳና አቻምየለህ
58. ሩት ሲሳይ
59. ቤተልሔም ተመስገን
60. ሩሀማ ሚሊዮን
61. ናታን አክሊሉ
62. ፀጋዘአብ ወሰንየለህ
63. የአብስራ ፀጋ
64. ጌድዮን መሸሻ
65. ርብቃ ሰሎሞን
66. ረድኤት ታደሰ
67. ያኔት ነብዩ
68. ፀጋ ማሞ
69. ፀጋ ዥቦቴ
70. ቤዛዊት አስናቀ
71, ያኔት ታሪኩ


ነገ ማክሰኞ 11:00 ሰዓት እንድትገኙ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

13 Oct, 15:12


🍂 #ኢትዮጽያዊው_ቄርሎስ በመባል የሚታወቁ “የምስራቃውያን ከዋክብት የትምሕርታቸው ልጅ የኾንኹ” ብለው ራሳቸውን የገለጹ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ 

        ጥቅምት 3  በዓለ ጽንሰታቸው ነው

+  አባቱ ሕዝበ ጽዮን
 +  እናቱ አምኃ ጽዮን ይባላሉ

🍂ኢትዮጵያዊው ሊቅና ጻድቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ከቅዱስ ያሬድ ቀጥሎ ታላቅ ቦታ የያዘ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ነው፡፡

🍂አባ ጊዮርጊስ የተወለደው በ1357 ዓ.ም በወሎ ክፍለ ሀገር በቦረና ወረዳ ሰግላ በተሰኘች ቦታ ነው። ወላጆቹ ልጅ ስለሌላቸው ዘወትር እያዘኑ ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር።

አባ ጊዮርጊስ የተወለደው በቅዱስ ዑራኤል አብሳሪነት መሆኑን ድርሳነ ዑራኤል ላይ ተዘግቦ እናገኛለን ፡፡ 

 አባቱ ጠቢብና የመጻሕፍት ዐዋቂ፤ የእግዚአብሔር ወዳጅና በቤተ መንግሥት በነበረችው ድንኳን “ሥዕል ቤት” ከሚያገለግሉ ካህናት ወገን ሲሆን የሰግላ ሀገረ ገዥም ነበር።
🍂የአባ ጊዮርጊስን እናት እምነ ጽዮን ከወለቃ /የዛሬው ደቡብ  ወሎ፣ ቦረና/  ከሹማምንት ወገን የሆነች ደግ ሰው ነበረች ።

🍂መንፈሳዊ ትምሕርትን ከአባታቸው በሚገባ ተምረዋል
  በ1341 ወደ ኢትዮጵያ ከመጡትና እስከ አጼ ዳዊት ዘመነ መንግስት ጳጳስ ከነበረሩት አቡነ ሳላማ ዘንድ ማዕረገ ዲቁናን ተቀብለዋል።

🍂ከዚያም ከ1376 - 1405 ዓ/ም ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ የአባ ኢየሱስ ሞዐ ገዳም ወስደው ከታላቁ ሊቅ ዓቃቤ ሰዓት አባ ሠረቀ ብሃን ቤተ ጉባኤም ተምረዋል።

🍂ይኹን እንጂ የቀለም ትምሕርት አልረዳ ቢላቸው በፍጹም ልባቸው ከእመቤታችን ወላዲተ አምላክ ሥዕል ፊት ቆመው ቀን ከሌት በተሰበረ ልብ እየጸለዩ በጾም በጸሎት ተወስነው አየማጸኑ ሳለ በነሐሴ 21 ቀን አመቤታችን ተገልጻላቸው በዕውቀትና በትምሕርት የሚያተጋቸውን ኃይል አሳድራላቸዋለች።

  🍂አባ ጊዮርጊስ የያሬድን ዜማ ከአቡነ ሳሙኤል ዘጋርማ እንደተማረው ገድሉ ይነግረናል፡፡ በዚያ ዘመን በዐፄ ዳዊት አማካይነት በሰሜን ኢትዮጵያ የያሬድ ድጓ ዋና ማዕከል በሆነው በደብረ ነጎድጓድ ተሾሞ ያስተምር ነበር፡፡

🍂በመንፈሳዊ ድርሰት በኩል ኢትዮጵያዊው ሊቅ ጻድቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እስከአሁን በሀገራችን አምሳያ የላቸውም ቅዱሳት እጆቻቸው ከብዕርና ከጽኑዕ ተግባረ እድ ሳይቦዝኑ ዋሻ እየፈለፈሉ የውኃ ጉድጓድ እየቀቆፈሩ ድልድይ እየሠሩ ጣዕመ ዓለም ንቀው ምልዐ ዘመናቸውን በተጋድሎ አሳልፈዋል።

🍂በጊዜውም በትምሕርታቸው የተመሠጡ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትና ምእምናን በእኛ ዘመን በፈቃደ እግዚአብሔር የተነሡ “ #ዳግማይ_ዮሐንስ_አፈወርቅ” ሲሏው።

🍂ዓጼ ይስሐቅ ደግሞ” #ኢትዮጵያዊው_ቄርሎስ” ብለዋቸዋል።

🍂በምልዐ ዘመናቸው ከደረሷቸው መጻሕፍት መካከል።ከብዙ በጥቂቱ በቅደም ተከተል ገድላቸው እንዲህ ይገልጻቸዋል
   / መጽሐፈ ምስጢር፣ መዝሙረ ክርስቶስ፣ መጽሐፈ አርጋኖን፣ ውዳሴ መስቀል፣ ኆኅተ ብርሃን፣ ተፈሥሒ ማርያም፣ ሊጦን ፣ ዕንዚራ ስብሐት ፣ ተአምኆ ቅዱሳን ፣ ውዳሴ አምላክ ፣ መልክዐ ስዐል፣ . . ./ ሌሎች ብዙ ድርሰቶችንም ደርሰዋል።

🍂በኹለንተናቸው የፈጣሪያቸውን ምስጋና ሳያቋርጡ ለቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ሥርዓት ሲጋደሉ የኖሩና በቅድስና ሕይወት የአጌጡ የተዋሕዶ ኮከብ ታላቁ ጻድቅ አባ ጊዮርጊስ 🍂ዘጋስጫ በስድሳ ( 60 ) አመታቸው በ1417 ዓ/ም በወርኃ ሐምሌ 7 ቀን ዐርፈዋል ።

በጥቅምት 3 ቀን የጽንሰታቸው መታሰቢያ ነው
     

የጻድቁ አባታቸን የአባ ጊዮርጊስ ረድኤት በረከት አይለየን 🙏🏽

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሣት ስዕላት ሠዓሊ

1,160

subscribers

1,394

photos

37

videos