🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

@kuniselfiyajada123


🎀ውዷዬ ሸሪአዊ እውቀት በመቅሰም ላይ አደራሽን አልባሌ ነገሮችን ራቂ ጊዜሽን ለአሄራሽና ለዱንያሽ በምሚጠቅምሽ ነገር ላይ አውይ
ዛሬ በስደት ያገኘሻትን ፀጋ ነገ ላታገኛት ትችያለሽና ዛሬ ነው ያንቺ ቀን በጊዜሽ ተጠቀሚበት ሸሪአዊ እውቀትን ቅሰሚበት
https://t.me/kuniselfiyajada123

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

22 Oct, 14:53


በመርካቶው ቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባችሁ ወገኖች ሁሉ። ከምንም በፊት ሶብር አድርጉ። አላህ ሰጠ። አላህ ነሳ። ሙስሊም በደስታውም በሀዘኑም ጌታውን ያስባል። ጌታችን እንዲህ ይላል፦

{ وَلَنَبۡلُوَنَّكُم بِشَیۡءࣲ مِّنَ ٱلۡخَوۡفِ وَٱلۡجُوعِ وَنَقۡصࣲ مِّنَ ٱلۡأَمۡوَ ٰ⁠لِ وَٱلۡأَنفُسِ وَٱلثَّمَرَ ٰ⁠تِۗ وَبَشِّرِ ٱلصَّـٰبِرِینَ (155) ٱلَّذِینَ إِذَاۤ أَصَـٰبَتۡهُم مُّصِیبَةࣱ قَالُوۤا۟ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّاۤ إِلَیۡهِ رَ ٰ⁠جِعُونَ (156) }
"ከፍርሃትና ከረሃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር። እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ፡ 'እኛ ለአላህ ነን፤ እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን' የሚሉትን።" [አልበቀረህ፡ 155-156]

አልሐምዱ ሊላህ በሉ። የሙእሚን ወጉ ይሄ ነው። በመከራውም በደስታውም ጊዜ ጌታውን አይረሳም። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
عَجَبًا لأَمْرِ المُؤْمِنِ، إنَّ أمْرَهُ كُلَّهُ خَيْرٌ، وليسَ ذاكَ لأَحَدٍ إلَّا لِلْمُؤْمِنِ، إنْ أصابَتْهُ سَرَّاءُ شَكَرَ، فَكانَ خَيْرًا له، وإنْ أصابَتْهُ ضَرَّاءُ، صَبَرَ فَكانَ خَيْرًا له.
"የሙእሚን ነገሩ ይደንቃል። ሁለ ነገሩ መልካም ነው። ይሄ ለሙእሚን እንጂ ለማንም አይደለም። አስደሳች ነገር ቢያገኘው ያመሰግናል። ይሄ ለሱ መልካም ነው። ጉዳት ቢያገኘውም ይታገሳል። ይሄ ለሱ መልካም ነው።" [ሙስሊም፡ 2999]

በማመስገን ታተርፋላችሁ እንጂ አታጡም። በአይነ ህሊናችሁ ቃኘት ቃኘት ብታደርጉ አገር ምድሩ በፈተና ተጥለቅልቆ ታያላችሁ። የባሰ የገጠማቸውን ተመልከቱ። ንብረት ብቻ ሳይሆን ሙሉ ቤተሰብ ያለቀበት ስንት ጉድ አለ። አስቡ። ለመፅናናት ይጠቅማችኋል። ከተስፋ መቁረጥ ይታደጋችኋል። ከባሰ ሁሉ በላይ የባሰ አለ። ከባሰው ያዳናችሁን አመስግኑ። ተስፋ መቁረጥ፣ አጉል ብስጭት ያለፈውን ላይመልስ ከሁለት ያጣ ያደርጋል። ደግሞም እወቁ! አያልፍ የመሰለው ሁሉ ያልፋል። ኢንሻአላህ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ከምንም በላይ ግን ዱንያ ነው። ትልቁ ኪሳራ የኣኺራ ኪሳራ ነው። ጌታችን እንዲህ ይላል፦
{ قُلۡ إِنَّ ٱلۡخَـٰسِرِینَ ٱلَّذِینَ خَسِرُوۤا۟ أَنفُسَهُمۡ وَأَهۡلِیهِمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۗ أَلَا ذَ ٰ⁠لِكَ هُوَ ٱلۡخُسۡرَانُ ٱلۡمُبِینُ }
" 'ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በቂያማ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ንቁ! ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው' በላቸው።" [አዙመር፡ 15]

አላህ ሶብሩን ይስጣችሁ። በተሻለ ይተካችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

21 Oct, 19:07


ደስ የሚል ቂርአ ተጋበዙ

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

21 Oct, 17:53


30 ምክሮች ለሙስሊሟ እህቴ!
~
1- ሒጃብሽ ሰፋ ያለና ረዘም ያለ ይሁን ።
2- አካሄድሽ ረጋ ያለና አደብ የተላበሰ ይሁን ።
3- በየቀኑ ብታጠፊ በየቀኑ ወደ አላህ ተመለሺ።
4- በአለባበስሽና በሥነ-ምግባርሽ ለሌሎች ሴቶችና ለሴት ልጆችሽ ምሳሌ ሁኚ።
5- ሊፕስቲክ ተቀቢዎች በዝተዋል፤ ግና ብዙዎች ስላደረጉት ጉዳዩ ትክክል ነው ማለት አይደለም ።
6- አዝማሚያው ያላማረሽን ቅርርብ በአጭር ቁረጪ።
7- ስትቀመጭ ሰብሰብ ሰተር ብለሽ ተቀመጭ።
8- ያልተፈቀደልሽን ባዕድ ወንድም ሆነ ሊያገባሽ የሚፈቀድለትን የቅርብ ዘመድ አትጨብጭ።
9- ከላይ አላህን ሳይታዘዙ፤ ዉስጤ ንፁህ ነው አላህን ፈራለሁ ማለት ቅጥፈት ነው።
10- ከባዕድ ወንድ ጋር ስታወሪ መቅለስለስ በሽታ ያለበትን በሽታውን መቀስቀስ ነው።
11- መስመር እየሳቱ የሚመስሉ የስልክ ወሬዎችንና ቻቶችን ቁረጪ።
12- በማይረባ ነገር እና ማ/ዊ ሚዲያ ላይ ዉድ ጊዜሽን አታጥፊ።
13- ወንድ ከኋላ እየተከተለ ደረጃ አትው።
14- ሙዚቃ የተቆጣጠረዉን ልብ ቁርአን ለቆት ይወጣል ።
15- እየተኳኳሉና እየዘለሉ አላህን እና መልዕክተኛዉን እወዳለሁ ማለት ዉሸት ነው።
16- ሒጃብና ኒቃብ እየለበሱ መጥፎ መሥራት የኢስላምን ንጽሕት ሙስሊምን ሥም ጭምር ማጠልሸት ነው።
17- ሆነብለሽ ወንዶችን አትፈታተኚ።
18- በሐራም መንገድ ገንዘብም ሆነ ትዳር ባገኙት አትቅኚ።
19- ያለ ኒካሕ የተወለደ ልጅ አባት የለዉም ።
20- ደረትሽን አትክፈቺ አታሳብጪም።
21- ቀሚስሽን ከኋላም ሆነ ከፊት አትቅደጂ።
22- ፀጉርሽን አትጎዝጉዢ አትቀጥይ።
23- ሽቶም ሆነ ዶድራንት አትቀቢ።
24- ሊፍት ስትገቢ ከወንድ ጋር ብቻሽን አትግቢ።
25- ብቻሽን ባዶ ቤት ዉስጥ አትደሪ።
26- ተሰተሪ በሁሉም ነገር አላህ ይሰትርሻል።
27- ስትስቂ በስሱ፤ ሰታወሪ ድምጽሽ ዝቅ ይበል ።
28- በሥራ ቦታ ከሰዎች ጋር ባለሽ ግንኙነት ቀይ መስመር ይኑርሽ።
29- ተግባቢ እና ትህትና ያለሽ ሁኚ ።
30- በተቻለሽ መጠን አላህን ፍሪ።
አላህ ይሠትረን።
=t.me/Sle_qelbachn1

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

20 Oct, 04:25


ያረቢ እስቲ እኛ በሱ ቦታ ብንሆንስ? እራሳችን እንፈትሽ

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

20 Oct, 04:23


እኔ በህይወት አለሁ ውዱእ አድርጌ የመግሪብን ሶላት መስገድ እፈልጋለሁ። የአሱር ሶላት አለፈኝ የመግሪብ ሶላትም ሊያልፈኝ ነውን ? እባካችሁ ሶላቴን ልስገድ

ሰላትን የማንሰግድ ሰዎች አላህ
ፊት መልሳችን ምን ይሆን?

🌐https://t.me/ibrahim_furii

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

20 Oct, 04:20


አል-ታቢዒይ ቀታዳ አላህ ይዘንለትና እንዲህ አለ፦

በአላህ እምላለሁ ከአንተው የአካል ክፍል የሆኑ ምስክሮች  አሉብህ ተጠንቀቅ! በድብቅም ሆነ በግልጽ አላህን ፍራው። እርሱ አላህ ምንም ዓይነት ሚስጥር አይደበቅበትምና።

📚تفسير الطبري || 20\410

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

19 Oct, 18:05


💎እውቀት ፈላጊ እህት ወንድሞቻችንን፡ከእንደነዚህ አይነት የአቂዳ ቀማኞች ሁሌም እናስጠነቀቅቃለን።
"""
📸እናንተ ሙስሊሞች ሆይ ከእንደነዚህ ያሉ የአቂዳ ደሀዎች በጭራሽ እምነታችሁን ልትወስዱ አይቻልላችሁም።ኸይር እንማራለን ብላችሁ ገብታችሁ አቂዳችሁን ሽጣችሁ እንዳትመለሱ ስንል ከወዲሁ እናሳስባለን።

እንደጥቅል ይሄ ማስታወቂያ #የአብዱሏህ_አል_ሀረሪ የጥቢ ልጆች (የጀመአቱ_ል #አሕባሽ) ነው እያልኳችሁ ነው።

አቡ ኡበይዳ
t.me/AbuOubeida

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

19 Oct, 15:45


🚫 ወንድ ልጅ በሚያገባ ወቅት እግሩን እና እጁን በሂናዕ ማጌጥ ይፈቀድለታልን?

🌴ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁላህ ተጠይቀው ሲመልሱ እንዲህ አሉ፡-

❝ወንድ ልጅ በሰርጉ ቀንም ሆነ ከዚያም ውጪ እግሩን እና እጁን  ሂናዕ መቀባት በእሱ ማጌጥ የተከለከለ ነው አይፈቀድለትም ምክንያቱም በሂናዕ ማጌጥ ለሴቶች ብቻ የሆነ ጌጥ ነውና ወንድ ቢያደርገው ሴትን ይመሳሰላል  ስለዚህም ወንዱ ሴትን ልጅ መመሳሰሉ ሴትም ልጅ ወንድን ልጅ መመሳሰሏ ትልቅ ኃጢአት ነውና።❞

📚"فتاوى نور_على_الدرب" (11/ 415-416
══════ ❁ ══════
https://t.me/Mohammedseid21

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

19 Oct, 06:55


... وَعَسَى أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ وَعَسَى أَن تُحِبُّوا شَيْئًا وَهُوَ شَرٌّ لَّكُمْ وَاللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ}

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

18 Oct, 10:12


ዘራፊው ፋኖ ህዝብ እያመሰ ነው


በደቡብ ወሎ ደሴ በተለያዩ አካቢወች እየተሰገሰጉ የዋሁን ህዝብ እየደበደቡ ሆን ብለው ሰላማዊ ዜጋ ላይ መሳሪያ እየዘረፉ ንፁሀኖችን እያስፈራሩ ሲሆን ህዝቡ በውስን የቀናት ቅፅበት እጅግ እየተማረረ እንደሆነ እየገለፀ ነው።

የሚገርመው ህፃናት አግቶ ብር ለመቀበልና ከቤተሰብ ላይ ችግር ለማድረስ ከሰው በር ላይ እየደፈጡ ስለሆነ ህዝቡ ልጆቹን በጥንቃቄ ይይዝ ዘንድ ለመጠቆም እንፈልጋለን‼️

በሰሜን ወሎ የተለያዩ ወጣቶችን እያገተ እስከ ❹ሚሊየን ተቀብሎ ገንዘቡን ከተቀበለ በኋላ እየገደለ የመጣው ደናቁርቱ የፋኖ መንጋ አሁን ማህበረሰቡን በመመሳሰል እየደፈጠ ወደ ደቡብ ወሎ እየገባ በአንዳንድ ቦታወች ላይ አደጋ እየጋረጠ መጥቷል።

....መረጃውን ሸር በማድረግ ህዝባችንን እናንቃ‼️

https://t.me/nuredinal_arebi

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

18 Oct, 05:12


🌸بســـــــم اللــــه الرحمــــن الرحيــــــم»

የጅመኣ  ግብዣ
ሱረቱል ካህፍ
       🇸🇦በወንድማችን  ቶውፊቅ አልሀበሽ
📚"ተ
   📚"ጋ
     📚"በ
        📚"ዙ
            📚"ል
               📚"ን
سورة_الكهف

📚][]ሱረቱ ከህፍ 📎ውብ ቲላዋ@[]
ቁርአን የልብ መርጊያ ለደረቀ ልብ ማረስረሻ ነው።
{የጁመዓ ቀን ሱናዎች}

↩️💎 ‏سنن يوم الجمعة
💎الغسل
💎 الطيب
💎السواك
💎 لبس الجميل
💎 قراءة سورة الكهف
💎 التبكير لصلاة الجمعة
💎الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي

➊ ➛መታጠብ
➋ ➛ሽቶ መቀባት
➌➛ ሲዋክ መጠቀም
➍ ➛ጥሩ ልብስ መልበስ
➎ ➛ሱረቱል ካህፍን መቅራት ከቻልን
➏ ➛ለጁመዓ ሶላት መጣድ
➐ ➛በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት


እንዲሁም ብለዋል ﷺ የጁመዕ ሌቀኑ ለይ በኔ ሰለዋትን  አብዙ። ሶለዋታችሁ እኮ ለኔ ይቀርብ ነው።
«اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ
 

➛በሰለዋት በዚክርያውለን

ﷺ  ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ  ﷺ ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺﷺ ﷺ ﷺ ﷺ

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

17 Oct, 18:56


ደስ የሚል ንግግር

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

17 Oct, 18:55


«ኒቃብ ለብሳ መጥፎ የምትሰራ አውቃለሁ» .........ካለህ
....
«ሙናፊቅ ሆኖ ከነብዩ ጀርባ ሶፈል አወል የሚሰግድ ሰው አውቃለሁ»  በለው ።

በሙናፊቁ ምክንያት ሶላትን እንደማንቃወመው ሁሉ በሴቷ ምክንያት ኒቃብን አንከለክልም። በህክምና ስም የሚያጭበረብር ዶክተር ካለ ዶክተሩን እናስወግዳለን እንጅ ህክምናና ሆስፒታልን አንዘጋም።

ጉድለት ያለው ሰዎቹ ጋር እንጂ ዲናችን ላይ አይደለም። የአላህ ዲን ሙሉ ነው።ሰዎች በሚሰሩት ጥፋት የሚወቀሱት ሰዎቹ እንጅ የተደበቁበት ውብ የዲን ድንጋጌ አይደለም።
#ኒቃብ #ኒቃብ #ያ #ሙስሊማት!

http://t.me/ibnuyasir11

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

17 Oct, 16:11


ሰሞኑን ትንሽ አሞኝ ነበር። ዛሬ በአንፃሩ ለውጥ አለኝ አልሐምዱ ሊላህ። ህመም ጋር በተያያዘ ጥሩ ያልሆነ ልማድ አለኝ። ሃኪም ቤት መሄድ አልወድም። ህመሜ ከባድ ደረጃ ሲደርስ ወይም መንቀሳቀስ ሲያቅተኝ ግድ ሲሆን ነው የምሄደው። እንደተለመደው መቋቋም ሲያቅተኝ በአቅራቢያ ያለ ሃኪም ቤት ገባሁ። ሳውቀው በጣም ህዝብ ይርመስመስበት ነበር። ፀጥ ረጭ ብሏል። ከኔ ውጭ ሁለት ታካሚ መሰለኝ ያየሁት። ያውም አንዷ ድንገተኛ። ለህክምናዬ ያወጣሁትን የገንዘብ መጠን ሳይ ሰውን ያሸሸው ይሄ የተጋነነ ዋጋ ዋና ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አሰብኩ።
ሰው አማራጭ ስለሌለው ወይም አማራጩ ስለሚያንስ ብቻ በዚህ ልክ መጨከን ጥሩ አይደለም። በርግጥ እኔ የሄድኩበት የሙስሊም ቤት አይደለም። ነገር ግን የሙስሊሞቹም የባሱ እንጂ የተሻሉ እንዳልሆኑ በተደጋጋሚ አይቻለሁ፣ ሰምቻለሁም። ለዚህ የዋጋ ንረት የተጠቃሚውም ድርሻ ቀላል አይደለም። የህክምናውን ጥራት በሚከፍለው ብር መጠን የሚለካ አለ። ክፍያው ዝቅ ሲል ለተቋሙ የሚሰጠው ግምት አብሮ ዝቅ ይልበታል። እንዲህ አይነቱን ሳይነቃ እንደነቃ የሚያስብ ወይም ጥጋበኛ እንተወውና ለሰፊው ህዝብ ግን አንድ ነገር ማለት ጥሩ ነው። አስገዳጅ ሁኔታ ካልገጠማችሁ በስተቀር ህክምናችሁን በመንግስት ተቋማት አድርጉ። ለዚህ አንዱ ምክንያት የህክምና ዋጋ ነው። ከዋጋ ያለፉ ሌሎችም ምክንያቶች በተጨባጭ አሉ። ለነገሩ ህዝባችን አሁን በመንግስት ተቋማት ለመታከምም የሚያቅተው ደረጃ እየደረሰ ነው። አላህ ይድረስልን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

16 Oct, 18:39


ዋኢል ብን ሀጀር በዘገቡት ሐዲስ እንዲህ ብለዋል፡-

«كانَ رسول الله ﷺ إذا رَكعَ فرَّجَ أصابعَه ، وإذا سجَدَ ضَمَّ أصابعَه»

የአላህ መልእክተኛﷺ በሩክዕ ጊዜ ጣቶቻቸውን የሚነጣጥሉ ሲሆኑ በስጁድ ጊዜ ደግሞ ጣቶቻቸውን የሚሰበስቡ
ነበሩ።

📚(ሶሂህ አል-ጀሚዕ || 4733
)

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

16 Oct, 18:22


«ጋብቻ የእብደት በሽታን ለማስወገድ ከሚጠቅሙ መድኃኒቶች አንዱ ነው። ላጤነት ደግሞ የእብደት በሽታን ከሚያስከትሉ ምክንያቶች አንዱ ነው።»
📚ኒሃየቱል‐መጥለብ፥ ኢማም አል‐ጁወይኒይ፥ ቅፅ 12፥ ገፅ 34
...

منقول

🎀 ‏يا أختي الكريمة أصلحي بينك وبين الله يصلح الله بينك وبين الناس

16 Oct, 16:48


አላለም እንዴ ሀብታም ከሆናችሁ ባላችሁን ሌላ እንዲያገባ መኸር አግዙት።አጥሽ


ሴቶችዬ ትስማሙ ይሆን ለማንኛውም በርቱ

8,168

subscribers

351

photos

269

videos