የሁለቱም ሀገር ስኬት በሆነው ተውሂድ (የአላህ አንድነት) ፀንቶ ለመዘውተር በሚረዳው ታላቅ የምሽትና የንጋት ዚክር ውስጥ:>
በተውሂድ አምሽቶ በተውሂድ ማንጋት አለበት።
عَنْ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ : كَانَ نَبِيُّ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ إِذَا أَمْسَى قَالَ : " أَمْسَيْنَا وَأَمْسَى الْمُلْكُ لِلَّهِ، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ ". قَالَ : أُرَاهُ قَالَ فِيهِنَّ : " لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ، رَبِّ أَسْأَلُكَ خَيْرَ مَا فِي هَذِهِ اللَّيْلَةِ وَخَيْرَ مَا بَعْدَهَا، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا فِي هَذِهِ اللَّيْلَةِ وَشَرِّ مَا بَعْدَهَا، رَبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْكَسَلِ، وَسُوءِ الْكِبَرِ، رَبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنْ عَذَابٍ فِي النَّارِ، وَعَذَابٍ فِي الْقَبْرِ ". وَإِذَا أَصْبَحَ قَالَ ذَلِكَ أَيْضًا : " أَصْبَحْنَا وَأَصْبَحَ الْمُلْكُ لِلَّهِ ".
صحيح مسلم: 2723
የአላህ ነብይ ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም አመሻሽ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር:>
《አምሰይና ወአምሰልሙልኩ ሊላህ።ወልሀምዱሊላህ ። ላኢላሀ ኢለላህ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለህ ፤ ለሁልሙልኩ ወለሁልሀምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ።ረብቢ አሰአሉከ ኸይረ ማ ፊ ሃዚሂለይለህ ወኸይረ ማ በዕደሃ። ወአዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ሃዚሂለይለህ ወሸሪ ማ በዕደሃ። ረብቢ አዑዙ ቢከ ሚነልከሰል ወሱኢልኪበር ።ረብቢ አዑዙ ቢከ ሚን ዓዛቢን ፊንናሪ ወዐዛቢን ፊልቀብር።》
የንጋት ወቀት ሲሆን የሚቀየረው:
"አምሰይና" በሚለው ምትክ "አስበሕና"
"ኸይረ ማ ፊ ሃዚሂለይለህ ወኸይረ ማ በዕደሃ" በሚለው ምትክ "ኸይረ ማ ፊ ሃዘልየውሚ ወኸይረ ማ በዕደህ"።
"ሚን ሸሪ ሃዚሂለይለህ ወሸሪ ማ በዕደሃ"
በሚለው ምትክ " ሚን ሸሪ ሃዘልየውሚ ወሸሪ ማ በዕደህ"።
ከዚህ ዚክር ከሚገኙ ነጥቦች ውስጥ
👌የሁሉ ነገር ንግስና (ሉኣላዊነት) ለአላህ ብቻ ሆኖ ያመሻል ያነጋልም።
👌ምስጋና ሁሉ ለአላህ ነው።
👌ከአላህ በስተቀር እውነተኛ አምላክ የለም። አንድም ተጋሪ የለውም።
👌አላህ ብቻ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው። አንዳች አይሳነውም።
👌 ዘውታሪ መልካም ነገር ሁሉ የሚጠየቀው ከአላህ ብቻ ነው።
👌 ከሁሉም ክፉ ነገር ጠባቂው አላህ ብቻ ነው።
👌ስልቹነትና መጥፎ እርጅና አላህን ከማምለክ ያግዳሉ።
🤲ከቀብርና ከጀሃነም እሳት ቅጣት አላህ ይጠብቀን።
አዝካሮች ሁሉ በተውሂድ የተሞሉ ናቸው !
✍ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊያህ)
http://t.me/Abuhemewiya