Inclusive Education (Ethiopia)

@inceth2013


This channel is created to share new ideas and developments regarding Inclusive Educatio in Ethiopia.

Inclusive Education (Ethiopia)

01 Sep, 14:28


Great thanks brother sole!!

Inclusive Education (Ethiopia)

01 Sep, 06:22


እንዴት ናችሁ ወገኖቼ ረዥም ጊዜ ተጠፋፍተናል፡፡ የአካል ጉዳተኞች ዕኩል የስራ እድል ተጠቃሚነትን በተመለከተ በሀገራችን ያሉ የህግ ማዕቀፎችን ለጥፌላችኋለሁ መልካም ንባብ፡፡

Inclusive Education (Ethiopia)

05 Jul, 14:17


ጠንካራ ስነ ልቦና ችግሮችን መሻገሪያ ድልድይ ነው- ወጣት በለጠ ቡቱና
~~~~
በጠንካራ ስነ ልቦና አለመቻልን ወደ መቻል የቀየረው በለጠ ቡቱና የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል አንዱ ነው፡፡

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያለፉትን አምስት ዓመታት በማታው የትምህርት መርሐ ግብር በማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ተማሪ በለጠ ቡቱና ጠንካራ ስነ ልቦና ካለ የማይታለፍ መንገድ የለም ብሏል።

ወጣት በለጠ ወላጅ እናትን በልጅነት ማጣትን ጨምሮ ህይወቱን በርካታ ፈተናዎችን ተጋፍጧል።

የአካል ጉዳት ያለበት ወጣት በለጠ አጋዥ አባትም የሌለው በመሆኑ የመኖር ተስፋውን ሊያደበዝዝ ቢችልም ለችግርና ለፈተና እጅ ባለመስጠት ጉዞውን ማስቀጠል ችሏል።

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ሲያመጣ በሲዳማ ክልል አርቤጎና ወረዳ የ20 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ከተደረገለት በኋላ ወደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ አቅንቷል።

ዩኒቨርሲቲውም ከ1 ዓመት የትሞህርት ቆይታ በኋላ ነፃ የትምህርት፣ የማደሪያና የምግብ አገልግሎቶችን አመቻችቶለታል።

ተማሪ በለጠ ቡቱና አካል ጉዳተኝነት ሳያግደው የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ካስመረቃቸው 4 ሺህ 800 ተማሪዎች ውስጥ አንዱ በመሆን በ3 ነጥብ 2 አጠቃላይ ውጤት የመጀመሪያ ዲግሪውን  አግኝቷል።

ወጣቱ ተመራቂ ለዚህ ምዕራፍ ባደረሰው ብርቱ የስነ-ልቦና ዝግጅት ወደፊት ለሀገሩ የላቀ አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ ስለመሆኑም ነው የተናገረው።

ምንጭ (ኤፍ ቢ ሲ)

Inclusive Education (Ethiopia)

16 May, 06:47


የንግግር ተግዳሮት ከምንላቸው ውስጥ አንዱ አይነት ነው። ስታተሪንግ። ከዚህ ምን እንማር ይሆን?

Inclusive Education (Ethiopia)

14 May, 02:47


ይህ በጣም አስቸኳይ........መልዕክት
እባኮትን አሁን ይህንን መልዕክት ለቤተሰቦችዎ እና ለጓደኞችዎ ያድርሱ።
ሰዎች በነዚህ ቁጥሮች ጥሪ ሲደርሳቸው ቆይቷል
ስልክ፡
+375602605281
ስልክ፡
+37127913091
ስልክ፡
+37178565072
ስልክ፡
+56322553736
ስልክ፡
+37052529259
ስልክ፡
+255901130460
ወይም ከ+255 +370 +371 +375 +381 +563 በነዚህ ኮድ የሚጀምር ማንኛውም ቁጥር እነዚህ ሰዎች አንድ ጊዜ ብቻ ደውለው ስልኩን ይዘጋሉ መልሰው ከደወሉ የእውቂያ ዝርዝሮን በ 3 ሰከንድ ውስጥ መገልበጥ ይችላሉ እና የባንክ ወይም የክሬዲት ካርድ ዝርዝሮች በስልክዎ ላይ ካለዎት ያንንም መገልበጥ ይችላሉ...
+375 ኮድ ከቤላሩስ ነው።
+371 ኮድ ለላቲቫ ነው።
+381 ኮድ ከሰርቢያ
+563 ኮድ ከቫልፓራይሶ
+370 ኮድ ከቪልኒየስ
+255 ኮድ ከታንዛኒያ አትመልሱ ወይም አትንኩ።
እንዲሁም, አትጫኑ #90 ወይም #09 በማንኛውም ደዋይ ሲጠየቅ ከሞባይልዎ ላይ ሲም ካርድዎን ለማግኘት፣ በእርስዎ ወጪ ጥሪ ለማድረግ እና እርስዎን እንደ ወንጀለኛ ለመቅረጽ የሚያገለግል አዲስ ዘዴ ነው። ማንኛውንም ጣልቃ ገብነት ለማስቆም በተቻለዎ መጠን ለብዙ ወዳጆች ይህንን መልእክት ያስተላልፉ!!

Inclusive Education (Ethiopia)

23 Apr, 05:07


ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር   መጋቢት 24/ April 2
World Autism Awareness & Acceptance Day

የኦቲዝም ቅድመ-መገለጫዎች
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉ከኦቲዝም ጋር አብሮ የሚኖር ልጅ ያላቸው ወላጆች ልጆቻቸው ከሁለት አመት በፊት በነብሩት ጊዜያት የእድገት ሂደታቸው ላይ ችግር እንደነበራቸው ይናገራሉ፡፡ ምንም እንኳ የአቲዝም ልየታ(Diagnosis) ሶስት -አራት አመት በፊት ባይደረግም፤ ነገር ግን ይሔን እክል መለየት ከተቻለበት ጊዜ ጀምሮ የቋንቋ እድገት መዘግየት እና ሌሎች መሰል የልጆች ተግዳሮቶችን በአፅንኦት ተመልክቶ ድጋፍ ማድረግ (Early-Intervention) ያስፈልጋል።  ዋና ዋና የሚባሉ እድሜያቸው ከሁለት አመት በታች በሆኑ ልጆች ላይ ሚሰተዋሉ የኦቲዝም መገለጫ ምልክቶች ተከታዮቹ ሲሆኑ፡- የማህበራዊ መስተጋብር ችግር (Socialization problem)፤ የተግባቦት ችግር (communication problem)፤ የመደጋገም ባህሪ እና ፍላጎት (Repetitive behavior)፤  ጨዋታ እና ስሜት እና ሌሎች ባህሪያት፡፡ ከተጠቀሱት ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ሶሰቱ ምልክቶች በመደበኛነት ኦቲዝምን ለመለየት(Diagnosis) የምንመለከታቸው መገለጫዎች ናቸው፡፡👇

1⃣ የማህበራዊ መስተጋብር ችግር (Socialization problem)

☑️ዝቅተኛ  የሆነ ማህበራዊ መስተጋብር
☑️ሰዎችን ችላ ማለት
☑️ሌሎች ልጆች ላይ ፍላጎት ማጣት
☑️አብሮ መጫወት አለመፍለግ
☑️ደስታን ለማካፈል አለመፈለግ
☑️በራሳቸው አለም መሆን
☑️ከእድሜ እኩዮቻቸው ጋር ግንኙነት አለማድረግ (አለመኖር)
☑️ብቻ መሆንን መምረጥ
☑️ሌሎች የሚያደርጓቸውን ነገር አለመቀላቀል
☑️ለሌላው ግድ የለሽ መሆን
☑️የአዋቂን ትኩረት ወደራሳቸው መሳብ አለመቻል
☑️ሰዎችን አለመለየት
☑️የሌሎችን ተኩረት መምራት አለመቻል  
☑️ድምጾችን ችላ ማለት
☑️ወደ ላይ ከፍ ለማድረግ እጅ ሲሰጣቸው አለመያዝ  
☑️የዐይን ግንኙነት (Eye Contact) አለመኖር
☑️ፍቅርን ማሳየት አለመቻል   
☑️ማህበራዊ ፈገግታ አለመኖር
☑️ምቾት አለመፈለግ   
☑️የሰውነት ምልክት አለመኖር
☑️መነካት አለመፈለግ    
☑️ፊት ላይ የሚኖር የስሜት መገለጫ አለመኖር
☑️ማህበራዊ ምላሽ አለመስጠት  
☑️ሰላም አለማለት👋

2⃣የተግባቦት ችግር (communication problem)

☑️በንግግር ቋንቋ መግባባት አለመቻል
☑️የሰውነት ምልክትን አለማወቅ እና አለመጠቀም  
☑️ማህበራዊ ወሬ አለመኖር
☑️ፍላጎትን ለማሳየት መጠቆም (pointing) አለመቻል
☑️የተወሰኑ የፊት መገለጫዎች ብቻ መኖር
☑️የዐይን እንቅስቃሴን አለመቆጣጠር
☑️ያልተለመደ የዐይን ግንኙነት መኖር 
☑️ድምፅን እና ድርጊትን መድገም
☑️ፈገግታ አለመኖር   
☑️በህፃንነት ጊዜ መኮላተፍ አለመቻል(አለመኖር)
☑️ቋንቋን መረዳት ላይ ችግር መኖር
☑️በፊት አግኝተዋቸው (አውቀዋቸው) የነበሩ ቃላትን ማጣት

3⃣ የመደጋገም ባህሪ እና ፍላጎት

☑️በመደበኛነት የሚከሰቱ (ቅደም ተከተል ያላቸው) የቃላት ንግግር (ድምፆች) መኖር
☑️የእጅ አና የጣት ያልተለመደ እንቅስቃሴ
☑️የሙሉ ሰውነት ያልተለመደ እንቅስቃሴ
☑️ያልተለመደ (የተደጋገመ) ነገር ማድረግ
☑️ከእቃዎች ጋር ያልተለመደ (የተደጋገመ) ቁርኝት

4⃣ ጨዋታ እና ስሜት (sensory)

☑️መጨዋታ አለመኖር
☑️እቃ እቃ ጨዋታ አለመኖር
☑️በድምፅ ቶሎ መረበሽ
☑️ሙቀት እና ቅዝቃዜ አለመሰማት
☑️ሌላ ሰውን አይቶ መጫወት አለመቻል
☑️ያገኙትን ነገር ወደ አፍ ማስገባት
☑️መስማት የተሳናቸው ይሆናሉ ተብለው ሊጠረጠሩ ይችላል
☑️ለነገሮች ፤ለእንቅስቃሴ እና ለእቃ ቅርፅ ያልተለመደ የሆነ እይታ መኖር

5⃣ ሌሎች ባህሪያት

☑️ትኩረት አለመሰብሰብ      
☑️ለነገሮች እና ለሁኔታዎች አለመጓጓት
☑️የባህሪ መለዋወጥ      
☑️ለስም ምላሽ አለመስጠት
☑️የእንቅልፍ ችግር 
☑️ዝም ብሎ መሮጥ 
☑️እራስን መጉዳት
☑️ያልተለመደ ፍርሀት
☑️ምግብ መቀነስ  ወይም የተወሰኑ የምግብ አይነቶችን ብቻ መብላት
☑️በጣም ዝም ማለት
☑️ለእንስሳት ግድ የለሽ መሆን
☑️ሲኮረኮሩ በጣም ደስተኛ መሆን

☝️ከላይ ከተጠቅሱት የኦቲዝም መገለጫዎች መካከል የተወሰኑት የእድገት መዘግየት (developmental delay) ያላቸው ልጆች ላይ ሊስተዋል ይችላል፡፡ ኦቲዝም ያላቸው ልጆችን እና ኦቲዝም ሳይኖራቸው የእድገት መዘግየት ያላቸው ልጆችን ያነፃፀሩ ጥናቶች፤ ኦቲዝም ያላቸው ጨቅላ እና ለትምህርት ያልደርሱ ልጆች የሚያሳዩትን ምልክቶች እና መለያ ባህሪዎቹ ላይ ግልፅ የሆነ መረጃ ያቀርባሉ፡፡ በጣም ትናንሽ በሆኑ ልጆች ላይ የመደጋገም ባህሪ እና ፍላጎት አለመኖር ኦቲዝም የመከሰት እድል አይኖርም ማለት አይደለም፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ጨቅላ በሆኑ ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ልጆች ላይ መሰረታዊ የሆኑ የተግባቦት  እና ማህበራዊ ክህሎቶች እጥረት በመጀመሪያዎቹ ሁለት አመታት ይስተዋላል፡፡

Inclusive Education (Ethiopia)

27 Mar, 06:20


ጥሩ ጅማሮ ነው። ሌሎች ክልሎችም መሰል ትኩረት ሊሰጡ ይገባል።

Inclusive Education (Ethiopia)

27 Feb, 11:52


International Guidelines for
the Education of Learners
with Down Syndrome.

Inclusive Education (Ethiopia)

20 Feb, 11:55


15ኛው አለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤ በቀጣዩ አመት በኢትዮጵያ ይካሄዳል

15ኛው አለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤ በ2017 ዓም በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በቀጣዩ አመት ዓለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ለማዘጋጀት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ጉባኤው ከጥር 6 እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል። ስምምነቱን የተፈራረሙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ትብብሩ ጉባኤውን በተሳካ መልኩ ለማካሄድ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰዋል። በዚሁ ወቅት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የዓለም የምልክት ቋንቋ ጉባኤ በቀጣይ አመት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

ይህንን ተከትሎ ሚኒስቴሩ ጉባኤውን ከብሔራዊ መስማት ከተሳናቸው ማህበርና ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለማካሄድ ዝግጅት መጀመሩን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ስም ከፍ የሚያደርጉና የአገራትን ትስስር ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራትን ዩኒቨርሲቲው እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ ረገድ ጉባኤው በኢትዮጵያ እንዲካሄድ የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። የዩኒቨርሲቲው ምሁራን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በመተባበር ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ፡ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በጉባዔው ከተለያዩ የአለም አገራትና ተቋማት የተወጣጡ ከ600 በላይ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

FEBRUARY 16, 2024
ዘጋቢ ስለእናት እስክንድር

Inclusive Education (Ethiopia)

01 Feb, 11:46


Dear all,

Please access a free online course in English on basic hearing health using the link below, with a focus on supporting children with hearing loss in educational settings, produced by World Wide Hearing.
To access the free course, sign in here: https://training.wwhearing.org/

Inclusive Education (Ethiopia)

09 Jan, 11:22


📸 Watch this video on Facebook
https://www.facebook.com/share/357hbcse7fQYYP64/?mibextid=xfxF2i