:- መዝ34፤1 ዛሬ ዛሬ ብዙ አይነት ትምህርቶች በበዙበት ዘመን ፣ብዙ አይነት ትምህርት ለመማር የምንሰለፈውንና ፣ በየሚዲያው ተጥደን የምንውለውን ያህል እግዚአብሔርን ስለ መፍራት ለመማር የሚፈልግ ሰው መሆን አለመፈለጋችንን ያህል ክስረት የለም።
እግዚአብሔር መፍራትን የሚያስተምሩንን እንፈልግ።
:- እግዚአብሔርን በመፍራት ለመኖር የሚፈልግ እግዚአብሔርን ስለመፍራት እውቀትን ይፈልጋል አጥብቆ ይማራል ፣ እግዚአብሔርን መፍራት በትምህርት ነው የሚመጣው። መዝ34፤1 ዘዳ14፤23, 17፤19, ምሳ2፤5, 9፤10
ምሳ15፤33።
:- መዝ 34፤1 እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋይ ትልቁ ትምህርቱ ለትውልዱ ከምንም ነገር ( ከገንዘብ፣ከፃታ፣ ከቁሳቁስ..) በላይ የሚያስተምረው ፤ እግዚአብሔርን መፍራትን ነው።
:- 2ዜና26፤5 በተለይ በዚህ ዘመን ከምንም ነገር በላይ ልንፀልይ የሚገባን ነገር ቢኖር እግዚአብሔር መፍራትን የሚያስተምሩንን ሰዎች እግዚአብሔር እንዲያስነሳልን ነው።
:- ኢዩብ28፤28, ትልቁ ጥበብ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ፤ ስለ ብዙ ነገሮች ማወቅና መተንተን ሳይሆን። ምሳ1፤7, 9፤10
:- ኢዩብ15፤4 እግዚአብሔርን መፍራት በእግዚአብሔር ፊት ሊቋረጥ የማይገባው አምልኮም ነው። it is #worship
:- መክ12፤13 እግዚአብሔርን መፍራት ማለት :-
የእግዚአብሔርን ህግ ወይም ቃል በተግባር መኖር ማለት ነው። በተጨረማመ ሀይማኖተኛ ፉት መታየትና መንፈሳዊ ንግግር በማብዛት መንፈሳዊ መስሎ ለመታየት መሞከር ሳይሆን።። it is #obedance to the word !
:- ምሳ3፤7 እግዚአብሔርን መፍራት ማለት:- ለሁሉ ነገራችን እግዚአብሔርን በመታመን መኖር ማለት ነወ
it is #Trusting God.
:- 2ዜና19፤7 እግዚአብሔርን መፍራት ማለት :-
- ሌላውን ሰው ላለመበደል መትጋት
- በሰው ፊት አለማዳላት። ዘር። ሀብት ማእረግ እያየን
- ጉቦ አለመስጠትም አለመቀበልም ነው።
:- ምሳ8፤13 ,መክ5፤7 እግዚአብሔር መፍራት ማለት :-
- ክፉ ድርጊትንና መንገድን መጥላት ማለት ነው
- ከትእቢተኛነትና አልታዘዝ ባይነት ወቶ ትሁትና ታዛዥ መሆን ማለት ነው
- በአንደበቱ ጠማማነት ፣ስድብን፣ውሸትን የማይናገር ሰው መሆን ማለት ነው
:- ሮሜ13፤18, መዝ14፤6 እግዚአብሔርን መፍራት የሌላቸው ሰዎች ፤ የሰላምን የእርቅን መንገድ አይቀበሉም
:- ዘዳ6፤13, 10፤20 እግዚአብሔርን ስለ መፍራትን እንድንማር ብቻ ሳይሆን ፤ እግዚአብሔርን በመፍራት እንድንኖር ታዘንማል። it is a #commandment
:- መክ5፤7 በንግግራችን ሁሉ እግዚአብሔርን እንድንፈራ ማስጠንቀቂያ ተሰቶናል ።when we #talk let us fear God
:- ዘፍ20፤11 እግዚአብሔርን መፍራት የሌለበትን ቦታ ለይተን ማወቅና ከዚያ ስፍራ ስፍራ መሸሽ ፣ካልሆነም በጥንቃቄና በጥበብ መመላለስ ይገባናል። run away or walk in wisdom , when you see the place that no fear of God .
:- ምሳ10፤27, 14፤27, 24፤4 ኢሳ33፤6 ምሳ19፤2 እግዚአብሔርን የመፍራት ጥቅሞችና ትሩፋቶች :-
- ዘመንን ታረዝማለች
- ከሞት ወጥመድ ታስመልጣለች
- የህይወት ምንጭ ናት
- ትህትናና ክብርን ታስገኛለች
- ባለጠግነት፣ክብርና ህይወት ታስገኛለች
- ወደ ህይወት ይመራል
- በጥጋብ ያኖራል
- ከክፉ ነገር ይጠብቀናል
- በዘመናችንን የሰላምና የፀጥታ ፣የጤንነት ያደርግልናል
👉 በመጨረሻም እግዚአብሔርን ወደ መፍራት እሚወሰወዱንን ትምህርቶች ፈላጊ፣ እግዚአብሔርን መፍራትን ለትውልዳችን የምናስተምር አስተማሪዎች፤ እግዚአብሔርን በመፍራት የምንኖር ልጆች መሆን ይብዛልን።
ትውልዴ ሆይ በቃ እግዚአብሔር በሁሉ እንፍራ !!🙏
ፓስተር ውብሸት ነኝ
ከ focus international ministry/solas 🙏
https://t.me/focusinternationalministry