ፈለገ ጥበባት +++

@felegetibebat


+++የቀደምት ኢትዮጵያውያን ስልጣኔን ማሳየት እንዲሁም ገዳማት እና አድባራትን ማሳወቅ፡፡+++

የተረሱ አድባራትና ገዳማትን ማስታወስ ፤የ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን ጥበብ እውቀትን በምንችለው ሁሉ መመርመር የአባቶቻችን ልጆች በመሆን ትላንት በዛሬ እና በነገ ውስጥ ማስቀጠል ማስቻል ነው።

ፈለገ ጥበባት +++

22 Oct, 16:59


ይህንን ድንቅ ትንታኔ በጹሑፍ ይዠላችሁ እመጣለሁ

አፋር  ላይ ስለሚነሳው የመሬት መንቀጥቀጥ በዘረ ደሸታዊያን እይታና ሚስጥራዊው ካርታ ዋቢ አድረጌ የምነግራችሁ ይኖራል...
ሚስጥራዊያን የኩሽ ዘሮች ዘረ ደሸቶች ለመላው ህዝብ አድርስልን ስላሉኝ ታላቅና ከፍተኛ የጥንቃቄ መልዕክት እና የ5500 አመቱ ቀመርና ካርታ...

ኢትዮጵያን ለሁለት የሚከፍለው አሰብ ላይ ስላለችው አለት የመሰንጠቋ ሚስጥር ...

ይህንን አስደናቂ ፕሮግራም በዮቱብ ማየት የማትችሉ በጹሑፍ ይዠላችሁ ቀርባለሁ!

በዪቲብ ለማየት ሊንኩን ተጫኑ👇👇

https://youtu.be/i9UoN13JupM

ፈለገ ጥበባት +++

21 Oct, 17:01


https://youtu.be/i9UoN13JupM

ፈለገ ጥበባት +++

21 Oct, 16:20


ከደቂቃወች በኋላ

አፋር  ላይ ስለሚነሳው የመሬት መንቀጥቀጥ በዘረ ደሸታዊያን እይታና ሚስጥራዊው ካርታ ዋቢ አድረጌ የምነግራችሁ ይኖራል...
ሚስጥራዊያን የኩሽ ዘሮች ዘረ ደሸቶች ለመላው ህዝብ አድርስልን ስላሉኝ ታላቅና ከፍተኛ የጥንቃቄ መልዕክት እና የ5500 አመቱ ቀመርና ካርታ...

ኢትዮጵያን ለሁለት የሚከፍለው አሰብ ላይ ስላለችው አለት የመሰንጠቋ ሚስጥር ...

ይህንን አስደናቂ ፕሮግራም ይዠላችሁ ቀርባለሁ!

ፈለገ ጥበባት +++

20 Oct, 07:57


በዛሬዋ አፋር (በጥንቷ ኦፌር) ማህጸን ውስጥ ስላሉት ሚስጥራዊ ሁነት ብዙም ሲነገር አልሰማም።  በጥንት መዛግብት ዙርያ ብራናን ያገላበጡና ምርምር የሚያደርጉ የእኔ አይነት ተንከራታቾችም ጊዜ ይግለጠው ብለው ዝምታቸውን ቢያጸኑም ከዘረ ደሸት ጉያ የተገኙ መምህሬን ዋቢ አድርጌ እውነቱን እገልጠዋለሁ።

ኢትዮጵያን ከሁለት የሚከፍለው የሰሞኑ የ አፋሩ የመሬት መሰንጠቅ ምክኒያት ና መዘዙ? ቀደመው ያስጠነቀቁት   ጥንታውያኑና ሚስጥራውያኑ ዘረ ደሸቶች ምን ይላሉ?

አፋር ላይ ስላለችው የመሬት እንብርት  ስለ ሚስጥራዊዋ የድንጋይ አለት ምንነትና ሚስጥር ሁሉ እነግራችሁ አለሁ!

ሃሳብ አስተያየት ጥቆማ

@Nabuti21 ላይ አድረሱኝ!

ዝ ውእቱ ፍኖተ አበው !

ፈለገ ጥበባት +++

19 Oct, 16:00


https://youtu.be/Y2rGqfR8-yo

ፈለገ ጥበባት +++

19 Oct, 15:36


ከ ደቂቃወች በኋላ

የመጨረሻው መጨረሻ ስለ ሆነው የአርማጌዶን ጦርነት ዙርያ ስለ ተሰጡ የአባቶቻችን የጥንቃቄ መልዕክት ይዠላችሁ ቀርባለሁ!

ፈለገ ጥበባት +++

22 Sep, 13:13


     የምስራች

ፈለገ ጥበባት በአዲስ ይዘት የተለያዩ አስደናቂ ኩነቶችን በማዘጋጀት ለአንባቢና ለተመልካች አስደሳችና ማራኪ  በሆነ መንገድ እየመጣ ይገኛል።

  ከሰሜን ተራሮች እስከ አፋር ምድር ድንቅና ሚስጥራዊ ሁነቶችን ፤ ከየረር ተርሮች እስከ ባሌ ፤ ከ ጣና ሐይቅ ገዳማት እስከ ገርአልታ አስደናቂ ቦታወችን እናስሳለን...

የቅኔ፣ የአቋቋሙ፣ የአቡሻክሮቹን ሊቃውንቱ ጋር የምናወጋበት የህይወት ተሞክሮወቻቸውንም የቆሎ ተማሪ ቤት ትዝታቸውን ከ አንደበታቸው እንኮመኩማለን።

  
ረቂቅ ሃይል ስለተጎናጸፈ ስለ እጽዋት ና ማዕድናት ሃይልና ጥቅም በሰፊው የምናቀርብም ይሆናል።

ወድ አንባቢያን እና ተመልካቾቻችን ቢጨመሩ፣ ቢሰሩልን፣ ብናውቃቸው፣ የምትሏቸውን ሃሳቦች በውስጥ መስመር ማስቀመጥ ትችላላችሁ።

@Nabuti21 ላይ እገኛለሁ!

ፈለገ ጥበባት +++

18 Sep, 17:19


እፀ አብኖስ ......

እፀ አብኖስ... ይህ እፅ በገነት ምድር ከታላቅ ክብር ጋር ተዳምሮ የተፈጠረ ሲሆን የራሱ ሃይልና መክስት እንዳለው ይታመናል።
ይህንን እጸ አብኖስ ሃይሉን የተረዱ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ አካላት በህቡዕ እያሰሱት ይገኛል እንዲሁም በፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥም ሃሉን ይገልጡታል ።

አባታችን አዳም ከገነት ወደ ምድር በተመለሰ ወቅትም በንስር መሪነት አዕዋፋት ለአዳም ከገነት ካመጡለት የእጸዋት አይነት አንዱ ይሄው እፀ አብኖስ እንደሆነ አባቶቻችን ያስተምራሉ፤ በተጨማሪ አባታችን ኖኅም ይህንን እፅ ለደውል ይጠቀምበት እንደ ነበር የተለያዩ ድርሳናት ያስረዳሉ። " መጥቅዕሰ ተወጥነ በኖኅ፤ ወገብረ መጥቅዓ እምዕፀወ አብኖስ " እንዲል።
ስለዚህ የዚህ እፅ ተክል አሁን ላይ የት አካባቢ ይገኛል ? አባቶችስ ለምን አይንተ ጥበብ ይጠቀሙበታል?ይህ እፅ ከእፀ መሰውር (clocking device ) እንዳይታይ ለመሰወር ) ከሚያገለገለው ክታብ ጋር ምን ግኑኝነት ይኖርው? መስጥመ አጋነት አጋንትን ወደ ጥልቁ ለመወርወርስ ይህ እፅ ፍቱን መዳሀኒት ይሆን? ለዚህ ሁሉ ጥያቄወች መልስ እንዳለው ይታመናል፡፡
ይህንንም በመ'መርመር እውቀትን እና ጥበብን ታሳድጉ ዘንድ ፍለጋችሁን አጽኑ!

ይህ ፈለገ ጥበባት ነው ያላችሁን ሃሳብ አስተያየት @Nabuti21 ላይ ማድረስ ይቻላል።

ፈለገ ጥበባት +++

11 Sep, 08:25


በመላው አለም የምትገኙ ቤተሰቦቸ እንኳን አደረሳችሁ ።
  በምድራችን ሁሉ ሰላም ይሰፍን ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳን።

እግዚአብሔር ቢፈቅድ በዚህ አመት ብዙ ነገሮችኝ የምንገልጥበት አመት ይሆናል።

@Nabuti21

ፈለገ ጥበባት +++

14 Aug, 17:15


   ሚስጥራዊውን ካርታ አገኘሁት


ኢትዮጵያ ቡናማ ቀይ የተራራ ሰንሰለቶች ያሉባት የምስራቅ አፍሪካ ፈረጥ ናት ።
ለበርካታ አመታት ስሟ ከሚስጥራዊነቷ ጋር የሚነሳ፤ ሁለነገራ ለሰወች ሩቅ የሆነች ምድር ...

   ኮስሞስ ስለ እጣኗን ስለ ድንቅ ማዕድኖቿ  የጻፈላት፤ ታላቁ አሳሽ እነ ሁዋን ቤርሙዴዝ፤ ክርስቶፈር  ደ ጋማ፤ ጀምስ ብሩስ፤ እና ሄነሪ ሰልት፤ ህይወታቸዎን ለአደጋ በማጋለጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘልቀው ከበረከቷ ተቋድስዋል ።...

አንድ ጠቢብ  የከረሰ ምድር አጥኝ ሊቅ ሰው ፍለጋየና እና  መቃተቴን ያስተዋሉ  የዘመናት ሚስጥሩን እፈታ ዘንድ  በትውልድ ቅብብሎሽ የተገኘን ሚስጥራዊ ካርታን አሳዩኝ።

  ሰባት  ረቂቃን ቦታወች ተቀምጠዋል ..እኒህን ሚስጥራዊ ቦታወች ለ ሺ ዘመናት በከርሰ ምድር አጥኝወች ተመርምረዋል፤ በማዕድን ቆፋሪወች ተበርብረዋል፤ በአለማቀፍ በአሳሾች ታስሰዋል።

የካርታውን ጥብቅ ሚስጥር ለመፍታት..

ጂማሮየን..በቀይ ባህር ዳርቻ  በሚገኘው  ኤርትራ የአፋር አካባቢ እንዳደርግ ካርታውን አስጨብጠው የትውልድ አደራውን አወረሱኝ። ...የካርታውም ቁልፍ ለመፍታት የሰለሞንን የማዕድን  ሃብቶች እንደሚጠብቁ በአፈ ታሪክ የሚነገረውን በጂቦች የተወረረውን  አካባቢ  ሐረርን ..የሚስጥራት ሁሉ ሙዳይ የሆነን በሰሜን ኢትዮጵያ ወዳለ  አንድ ገዳም ይመራኛል..ሌላኛው ወደ ወሎ  ይጠቁመኛል...
ምናልባት የእኒህ ሚስጥራዊ ቦታወች መገኘት አንድ ታላቅ የትውልድ እንቆቅልሽን ይፈታል

ካልታተመው መጽሐፍ.....

ይህ ፈለገ ጥበባት ነው ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ

@Nabuti21 አድርሱኝ

ፈለገ ጥበባት +++

04 Aug, 16:30


The secret of zion chalice

የጽዮናዊዝም ጸዋ ማህበር ሚስጥር!

ፍለጋ አያልቅም የሰው ልጂ ከ ስጋዊ ምኞትና ፍላጎት በዘለለ ለሚኖረበት ጽኑ  አላማና  እውነተኛ ማንነትን  በጥብቅ የመፈለግ የማሰስ የመጠየቅ የመ'መራመር ባህሪ ሊላበስ ይገባዋል።
እንደ እድል ሁኖ የተፈጠርንባት ምድር በአንጡረ ሀብቷ ወደር የማይገኝላት ተፈልጎ እና ታስሶ የማያልቅ  እጂግ ጥንታዊ ማንነት ያላት ፤ የተለየች ምድር ነች ኢትዮጵያ።

እንደ መረገም ሆኖ የመጣንባቸው መንገዶች ደካማ የፖለቲካ  አመራሮቻችን እንዲሁም የሃይማኖት አባቶቻችን ቸልተኝነት ብዙ ዋጋ ቢያስከፍልም  ያረፈደብን የማንነት ፍለጋወች ግን ዛሬም ከተዳፈኑበት የሚገልጣቸውን ይፈልጋሉ።

ኢትዮጵያን ጨምሮ የ አለምን ታላላቅ ሚስጥራት ዶሴን በመሰብሰብ፣ በማጥናት፣ እንዲሁም በረቀቀ መንገድ የራስ ለማድረግ በተለያየ ዘመን እጂግ ሚስጥራዊ የስለላ ድርጅቶች እና የጸዋ ማህበራት ተመስርተዋል።
ከማህበራቱ ጥንክርና የተነሳ ለበርካታ መቶ አመታት ሰንሰለታቸው ሳይቋረጥ፣ ሚስጥራቸው ሳይገለጥ፣ ማንነታቸውም ይፋ ሳይወጣ፣ ዘመንን ያስረጁ፣ እጂግ ተጽኖ ፈጣሪ የስለላ ድርጅቶች ሆኑ የጸዋ ማህበራት ይገኛሉ። ዛሬም ድርስ ጓዳችን የምትፈጸም እያንዳንዷን የሀገር ህልውና በቀላሉ ለማወቅ እጂግ ሚስጥራዊ በሆነ የስለላ መረብ ይጠቀማሉ ሀገራችን በዚህ ተንኮለ ከተጠለፈች ቆየች ።

በተለይ የጽዋ ማህበራት አንዳንዶቹ እጂግ በረቀቀ መልኩ ከመከናወናቸው የተነሳ ህልውናቸው ያለ እስከማይመስል ድረስ ህቡዕ ናቸው። ሚስጥራቸውም ከማህበራቸው የሚወጣው ከማህበሩ በድንገት አፈንግጦ የወጣ በሌሎች ማህበራት የተሰለበ ሰው ሲኖር ብቻ ነው ።

ከእኒህ ሚስጥራዊ የጽዋ ማህበራት አንዱ እና ዋናው የጽዮን የጽዋ ማህበራት ነው።
ጸዮናዊነት በሂብሪው እየሩሳሌም የሚል ትርጉም ሲኖረው ይህም ግንደ ቃሉ የተወረሰው ከመጻህፍ ቅዱስ ነው።
ይህ ሃይማኖታዊነቱ የገነነ፣ በፖለቲካውም ስር የሰደደ፣ እንቅስቃሴ በዘመናዊ መልክ በ19 ኛው ክፈለ ዘመን ቢቋቋምም ለበርካታ መቶ አመታት ከጀርባው ሚስጥራዊ እንቅስቃሴወችን ሲያከናውን የኖረ ማህበር ነው።
አሁን አሁን ይህንን ጽዮናዊነት መጠሪያ አለም እንዲረዳው የተደረገው በቋሚነት እስራኤላውያንን እንደ አሽዋ ከተበተኑበት አህጉራት ወደ አገራቸው ለመሰበሰብ የተቋቋመ ታላቅ ዝና ያለው ማህበር እንደሆነ ብቻ ነው።
ነገር ግን ይህ የጽዋ ማህበር እንደ አውሮፖ የዘመን ስሌት በ 1099 ወይም 11ኛው መቶ ክ/ዘመን በ አውሮፓ የተበተኑት ሊቃውነት በሚስጥር ተሰባስበው የመሰረተቱ የጽዮን ቤተ እምነት የተሰኘው ሃይማኖታዊ ተቋም በገሃዱ አለም የሚገኝ ሚስጥራዊ የሆነ ድርጂት ነው።

በ1975 በፖሪስ ብሄራዊ ቤተ መዛግብት (ቢብልዮቴክ ናስዮናስ) ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው ና ሚስጥራዊው ሰነድ( ሌ ዶስዮ ስክሬ) ተብሎ የሚታወቀው የብራና ጽሁፍ እንደ ሰረ አይዛክ ኒውተን፣ ሳንድሮ ቦቲቼሊ፣ ቪክቶር ሂዩጎ፣ እና ገናናው ሊኦናርዶ ዳ ቬንች፣ ያሉ በርካታ በርካታ የጽዮን ቤተ እምነት አባላትን ስም ይፍ አድርጓል።

እኒህ አለም ላይ በዘመናቸው ገናና የነበሩ ሰወች ከተመሰረተበት ከ1099 እስከ 21ኛው ክ/ዘመን በተለያየ ዘመናት ተጽኖ ፈጣርያን ግለ ሰቦች የሆኑ የሚስጥሩ የጽዮን ማህበር መሪወችም ነበሩ።

ይህ ማህበር ለ900አመታት አካባቢ ሚስጥሩ እንደ ተጠበቀ፣ ህቡዕ እንቅስቃሴው እንደ ቀጠል ፣ አለም ላይ የነበሩ ሚስጥራዊ ኩነትና ታቦተ ጽዮንን ጨምር የቅዲስ ጽዋውን ቅርሶችን እንቅስቃሴወችን ሲመረምሩ ለመውሰድም ሲጥሩ እና ፍላጎታቸውን በስውር ሲያስፈጸሙ ኑረዋል።

ይህ ህቡዕ ድረጂት ሚስጥሩ በፖሪሱ ቢብልዮቴክ ናስዮናል ሚስጥራዊ ሰንድ እስከተጋለጠ ድረስ በርካታ እንቅስቃሴወቹን ከውኗል።

የእስራኤሉ የስለላ ድረጂት ሞሳድ ን ጨምሮ የጽዮን ፕሮቶኮሎች ከፍተኛ የመንግስት አካላት ና ፖለቲከኞች ጭምር ያሉበት አይሁዳውያኑ ስብስብ ወደ ፊት ክርስቶስ ይወለዳል በሚል አሁን በቅረብ የሰሎሞን ቤተ መቅደስን ገንበተው የሰሎምንን ታቦት የጽዮንን ጽላት ይጠባበቃሉ።

በእርግጥ የሌዋዊው ሙሴ ጽዮን፣ የሰሎሞን መጽናኛ ታቦተ ጽዮን፣ ከ እስራኤም ምድር ወደ ኢትዮጵያ ከመጣች እንሆ ሶስት ሺ አመታትን ስላስቆጠረች በረከት ከ እስራኤል ምድር ጸጋም ከእየሩሳሌም ተነስቷል...ወደ ሀገሯ ትመለስ ዘንድ የቅዱስ ሰሎሞን ምኞቱም ነበረች!
በሰሎሞን ስረወ መንግስት ከመነበሯ የተነሳችውን ጸዮን ወደ ፊት ይወለዳል በሚሉት በመሲሁ ኢየሱስ ትመለሳለች ብለው በቀቢጸ ተስፋ ቤተመቅደሱን አንጸው ጽዮንን ከመነበሯ ኢየሱስን ከዙፋኑ እስኪ መጡ ይጠበቃሉ።

ይህ ታቦተ ጽዮንን ከ ኢትዮጵያ ለመውስድ በተለያዩ አዝማናት ቢሞከርም ከመንበሯ ትነሳ ዘንድ ፈቃደ እግዚአብሔር አይደለምና ፈጽሞ ሊያገኟት አልተቻላቸውም።
በተለይ እስራኤል ከተበታተነችበት አገግማ በ1948 እንደ ሃገር ከተመሰረተች ወዲህ የጽዮን ጽዋ ማህበር ጨምሮ ሞሳድና የተለያዩ ሚስጥራዊ ተቋማት እንደ ኦፐስ ዴይ ያሉ የቫቲካን የካቶሊክ ሚስጥራዊ ማህበር እምነትን ከመመረዝ አንስቶ ታቦተ ጽዮንን ለመውስድ ቢታሰብም ታቦተ ጽዮን የነበረችበት፣ ያለችበት፣ ወደ ፊትም የምትኖርበት፣ ሁኔታ እጂግ መግነጢሳዊ ሃይሏ በጊዜ የሚገለጥ ሚስጥር ነው እንዳሉት አበው ተሰውራባቸዋለች።

እንዲሁም በዚህ ዘመኝ በረካታ ሚስጥራዊ እቃወችን እንዲሁም የአዳምን ኤዶም ''ቅዱሱን ምድር '' ለመውረስ ይሞክራሉ.. .. ግን አይችሉም ።
ይህ የታቦተ ጽዮን ሁነት ለሁለት ሶስት ሽ አመታት ለኢትዮጵያ ፈተና የሆነባት ነገር ቢሆንም አሁን ላይ አላማና ግቡ ተጠምዞ የፖለቲካ አሰላለፉ ተቀይሮ ኢትዮጵያ ለሽ ዘመናት ያጸናትን የወጠራትን ጂማት ለመበጣጠስ እጂግ አሳዘኝ በሆነ ሴራ ተጠልፋለች።

ባልተፈጠርኩ የሚያስብለውን ይህን እለት ይህን ዘመን ይህ ክስተት ሀገሪቱን ሊያፈርስ ህዝቦቿን ሊያጠፋ የመጣብን ውስብስብ ሴራ በእውኑ ያልፍልን?

ቦ ጊዜ ለኩሉ.......!

ይህ ፈለገ ጥበባት ነው ያላችሁን ሃሳብ አስተያየት @Nabuti21 ላይ አድረሱኝ።

ፈለገ ጥበባት +++

01 Aug, 14:20


ምልሰት..

በህልሜ ይመስለኛል.....

በሰሜን ተራሮች በአንዱ ፣የሚስጥሩ አንባ ማህጸነ ደብረ ደደክ   ......ወ አመሳለ ሲና ራስ ደጀን አቀናሁ!

ተፈጥሮው ድንቅ፣ ውበቱ ግሩም፣ ከሰማዮ ጋር የሚያወጉ ተራሮች ይታያሉ   ፤ከሸማኔ ጥበብ በላይ   ተፈጥሮ ራሱን  እንዴት ባለ ጥበብ ሸምኖ ያለብሳል ?


የትኛው ጠቢብ እስትንፋስን አላብሶ እንዲህ እፁብ ድንድ አድርጎ ይፈጥራል ?

   ራስ ደጀን ለ1500 ዓመታት በላይ የስውሩየቅዱስ ያሬድ መኖርያ  ሚስጥራዊው የአፍሪካ ጣሪያ ፤ ምድር የታመቀውን አየሯን ማስተንፈሻው አንዱ ይህ ራስ ደጀን ሲሆን  ሌላው ሜዲትራንያን ስር ... ያልተገለጠ እውነት ያልተነገረ ምስጢር ....አለ!

የአፋሩ ኤርታሌ የበርባኖስ

የሰሜኑ ራስ ደጀን የብሄረ ህያዋን
የጎጃሙ ግዮን የገነት ትይዮ ናቸው....

ይህ ማለት ባህሪያቸውን የሚወራረሱ፣  ረቂቅ ሚስጥርን  የሚቃመሱ ፣ የ ሰማይ እና የምድር  ትይዮ ሀይል  የሚካፈሉበት ፣ድንቅ ተፈጥሮአዊ ኮድ ያላቸው ናቸው...



አበ ቴውድሮስ  ወ ውሉደ  ኢትዮጵያ  ...ወደ ራስ ደጀን ሰሞኑን አቅንች አለሁ...እጂግ አድካሚ አንዲሁም አስደማሚ ከምድረ በዳ ላይ የሚያውድ የእጣን ጢስ ያሸተቱኩበት፤ ገቢረ ታምራቱ በተፈጥሮ ለዛ በግልጽ የሚታይበት ፤ ድምጻቸው ብቻ የሚሰሙ ስውራን  ሰወችን የሚያነጋግሩበት፤ ድምጻቸው እንጂ ፊታቸው ፈጽሞ ማየት የማያቻል   ወደ ቦታው ለሚያቀና  ለጨነቀው መጽናኛን፤ ለደከመው ረፍትን  ለህሙማን ፈውስን የሚያመጡ፤ ጸሎት ልመናቸው የሚደርስ ሃብተ ትንቢት የሞላባቸው ስውራን ....ከ ለሊቱ 9 ስአት የተጀመረ የእግር ጉዞ የሰሜን ተራሮችን በብረድና ቁር አቀበትና ቁልቁለት ከ 4600 ሜትሮች በላይ ከፍታን እየወጣሁ እጓዛለሁ  እወጣ እወርዳለሁ ....  ቅዱስ ያሬድ ያስተማረበት ሆጮው፤ ከየት መጣ የማይባል የ እጣኑ ሽታ የሚያውድበት  ፤ያሬድ በበትረ ሙሴው ያፈለቀውን  ጸበል አልፌ.... በስውራን  አባቶች  የተባረከን ቡራኬ አግኝቸ ..ከ መናንያን ጋር ልነጋገር ከስውራኑ ጋ በረከት ልካፈል ወደድኩ....ከቆላና ደጋ የተሰባሰበው ሰው ቀጭኗን መንድ ዘጋግተወ መተላለፊያ እስካጣ ድረስ መድረሻ አጣሁ..... እንደ ግማሽ ጎን ገበቴ የሚመስል ተራራ  ላይ የሚገኙትን መናንያን አግኝቸ የልቤን እጠይቃቸው ዘንድ ወደድሁ  ...

ከድካሙ አንጻር የሚንቀጠቀጡ  እግሮቸን ዘርግቸ ከጋራው ላይ ተደግፌ ገደም አልኩ ...

ወደ ሰማዩ አንጋጥጨ .... ያሬድ ያሬድ ያሬድ አደራየን እበላ ዘንድ ተውከኝ እላለሁ....የደብረ ደደኩ ምሲጥር ይፈታልኝ ዘንድ ደጂህ የቆምኩትን ከርታታ ስለምንስ ተውከው?  ከ ደገኞች ደብረ ጻድቃን  ዘር የሚወጣው ውሉደ ደደክ የት ነው ያለው?  አንተ ያሬድ  እውነትን ያውቅ ዘንድ ከ ራስ ደጀን እስከ ግዮን የተንከራተተው ጎስቋላ አደራየን እወጣ ዘንድ አትረዳኝም እላኣለሁ...ስውራኑን አገኝ ዘንድ ተመኘሁ ግን አልቻለኩም...አንገቴን አቀርቅሬ ቁልቁል ወደ ሸለቆው ልወርድ ስነሳ የያዝኩትን  ጸበል ለማገዝ መንገድ ላይ የተቀበለኝ ከዛም የተጠፋፋነው  ህጻን  ልጂ  ከ ጸበሉ ጋር በፌስታስ የታሰረች ወረቀትን አቃብሎኝ ከህዝቡ መሃል ገብቶ ተሰወረ.....መንገድ  ባናወዘው እግሮች ቁልቁል ወደ ዋሻው አቀናሁ....

ቅዱስ ያሬድ  የተሰወረበትን ዋሻ ተመልክቸ   ....... 13 ስአታት ቆይታ በኋላ ምሽት  11:30  ላይ ብዙሃኑ ሊያዮት የሚመኙትን የሰውራኑ መኖርያ የድንቅ ተፈጥሮ መገኛ ቅዱስ ያሬድ ገዳም ደረስኩ....

ጎኔን አሳርፌ በሃሳብ እንቀዋለላለሁ ለሰው የማልነግረው አደራ የማላካፍለው ምስጢር....እንቅልፍ ሲጥለኝ ከወዲያ በኩል በዜማ ..

አሠርገዋ ለኢትዮጵያ ፤ በስብሐት ወበሃሌ ሉያ ፤ ያሬድ ካህን ፀሐያ ፤ አስተካልሐ በቅዳሴ ፤ በዘሱራፌል አርአያ ፤ ያሬድ ካህን ፀሐያ ፤ ለበግዕ በትንሣኤሁ ፤ ደመ ጥብሑ አርወያ ፤ ያሬድ ካህን ፀሐያ ፤ በመኃልይሁ አቅነያ .....እያሉ የሚያዜሙ ሊቃውንት ድምጽ  ቀሰቀሰኝ....

በትራሴ ካደረኳት ሻንጣየን ከኪሷ መዝዠ የተጻፈችውን የተጠቀለለች ወረቀት ተመለከትኩ.....


"ለሁሉም ጊዜ አለው በደም የተገነባው ንግስና  በ ባርነት ይጠናቀቃል፤ ልቡ የደነደነች  ፈርኦን ቀኝ እጂ ትሰላለች፤ አቅም ያጣ ሽባ ሁኖ ይዋረዳል በወንድሙም ይገደላል፤ ማቅ የለበሰች ገላ እንደ ሃጫ በርዶ ትነጻለች።  
የተመረጡት እስኪ ስቱ ዘመኑ ቢከፋም ጨለማው ቢረዝም፣ እረኞች በጎቻቸውን ለ ተኩላ ቢሰጡ እንኳ ቀኖቹ እንደ ደረሱ እወቅ!

ከ ደጀን አንባ ፀሐይ ይወጣል ..ሙቀት ያለው የማያቃጥል ፤ብርሃን ያለው የማይጨልም ፀሐይ  ..ፀሐዩ ለተመረጡት ያበራላቸዋል ለግፉአን ይጨልማል ...

  ግን ለወሊሃ እዘኑ ለርብ'ም  አልቅሱ! ''ትላለች


ከ ተደላደልኩበት ከሞቀ ቤቴ ቅጀ'ት የመሰለ የ ራስ ደጀን ጉዞየ  ተራ ህልም እንደሆነ አሰብኩ.....እስክነቃ ድረስ እንደ አቤሜሌክ እተኛ ዘንድ ወደድሁ፤ ያየሁትን ህልም 'ህልም እልም'  ብየ  ፀሐይዋ ወጥታ ከእንቅልፌ እስክነቃ ተኛሁ......ይህ ምልሰት ነው

ከትውልድ ማን አስተዋለ?

@Nabuti21 ላይ እገኛለሁ

ፈለገ ጥበባት +++

25 Jul, 17:10


ፈለገ ጥበባት +++ pinned «ሰላም በመላው አለም የምትገኙ የፈለገ ጥበባት ተከታታዮች እደምን ከረማችሁ።    ከበርካታ ጊዜያት በኋላ ወደ ፈለገ ጥበባት ገጽ ተመልሻለሁ፤ ፈለገ ጥበባት ላይ እጂግ አስደናቂ የጉዞ ታሪኮች ፤ የተወሳሰቡና ጥንታዊ እወቀቶች፤ ያልተገለጡ እና ሚስጥራዊ እውነቶችን እየገለጥን ለአመታት አበረን የቆየን ቢሆን በመሃል በአንድንድ ምክንያቶች ተቋርጦ ቆይቷል።   በውስጥ መስመር በጉጉት እንደምትጠበቁ በተደጋጋሚ…»

ፈለገ ጥበባት +++

25 Jul, 17:07


ሰላም በመላው አለም የምትገኙ የፈለገ ጥበባት ተከታታዮች እደምን ከረማችሁ።
   ከበርካታ ጊዜያት በኋላ ወደ ፈለገ ጥበባት ገጽ ተመልሻለሁ፤ ፈለገ ጥበባት ላይ እጂግ አስደናቂ የጉዞ ታሪኮች ፤ የተወሳሰቡና ጥንታዊ እወቀቶች፤ ያልተገለጡ እና ሚስጥራዊ እውነቶችን እየገለጥን ለአመታት አበረን የቆየን ቢሆን በመሃል በአንድንድ ምክንያቶች ተቋርጦ ቆይቷል።
 
በውስጥ መስመር በጉጉት እንደምትጠበቁ በተደጋጋሚ የምትገልጹልኝ ወዳጆቸ እንሆ መጥቻለሁ።
 
ከዚህ በፊት በተለመደው አስደናቂ ቆይታወቻችን የተለያዩ አወደ ሃሳቦች ተጨምረው ፈለገ ጥበባትን ከተሸሸግችበት ትወጣ ዘንድ ጊዜዋ ደርሷል....

@Nabuti21  እገኛለሁ

ፈለገ ጥበባት +++

04 Mar, 14:04


ከዘመን ጫፍ ላይ ተንጠልጥየ በጠፍ ጨረቃ ቃጥቸ ደግሞ ዘመንን ቀምረው ሲያመሰጥሩ ተመልክቸ ጻፍ ጻፍ ሲለኝ ከ ሰሜን ባሻገር ባለች በባሩድ ሽታ በተመላች ከተማ ውስጥ ሁኝ እክተብላችሁ ዘንድ ተገደድኩ!


ከለታት በአንዱ ቀን በድንገት ከቤቴ ተንስቸ መጓዝ ጀምርሁ....ሰው ወደ ለለበት፣ ድምጽ ወደ ማይሰማበት፣ ሁካታ ጠብ ክርክር  ንትርክ ወደ ማልሰማበት ወፌ ወደ መራችኝ ...

ስለ እውነት ግን ደክሞኝ ነው.... መኖር ያደክማል አይደል? እልፍ መከራ መስማቱ ፣  የተጨነቀች ነብስ ብኩን የሆነችን ስጋ ማየቱ፣ ተስፋ የሌለውን ተስፈኛን መመልከቱ፣  ...ምህረት የማያመጣው ጸሎታችን.. የማያርግ መስውእታችን... የማን'ባረክበት ብኩርናችን .. ...ነጻ የማያወጣን ትምህርታችን...እያሰብኩ

የኢትዮጵያ  የነጻነት ቀንዲሉ የሚለኮስበት ቀን አንገት የደፋችው አገር የምትቃናበት ጊዜ የደፈረሰው የሚጠራበት ....
ጊዜ ይኖር ይሆን? እላለሁ ..በጠቆረው ዝናባማ ደመና ፣በሚያካፋ የዝናብ ነጠብጣብ፣ ጨርቁን ጥሎ እንደ አበደ ሰው የለበስኩት ፎጦ እየጎተትኩ ...ጯክ ብየ በ ምድረበዳ አወራለሁ ..

እላለሁ ...
'የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል
       አለህም እንዳልል እንዲህ ይደረጋል'

      እላለሁ..


ተስፋ የተሰጠን ተስፋችን  የት ሄደ? እላለሁ

የማይነጋ ለሊት  ስንጠብቅ ...እንኖር ዘንድ ተውከን እላለሁ...ነጠብጣቡ ወደ ዶፍ ዝናብ ተቀይሮ መዝነብ ጀመረ... ከመምህሬ አድባር ዛፍ  ስር ከመሰለ ከወዲያ ማዶ ከ ገደሉ ጫፍ ከተንዘራፋው ዋርካ እጃቸውን  የሚያወዛውዙ ሰው ይታዮኛል.....ና ወዲህ ተጠለል በሚመስል ምልክት እየጠሩኝ...

ወደ ዋርካው  ተጠጋሁ ...በል ከዚህ ይሻልሃል ሰላም ሁን ብለው ሲሰናበቱኝ ...መባርቅቱ በበዛበት ብልጭ ልጭታው በጸናበት ስአት የት ሊሄዱ ነው? አልኩ እና መመርኮዣ ዘንጋቸውን ያዝ አደረኩ....

ልጀ ሆይ የሰማይ ምሰሶዋ  ለቋል፤

የምድርም መሰርቷ ተናውጿል....

አመጸኛ በዝቷል
  ሃጥያት ተንሳራፍቷል
    የማያልፈው ዝናብ ከ ሚመታኝ የሚልፈው ዝናብ ያርጥበኝ ... ልጀ ሆይ ሰማዮን እንዳታየው ማን አይንህን ጋረደህ ? ልቡናህ እንዳያስተውል ማን አዚም አደረገብህ....?

  እኔስ በቀን መሽቶብኛል፣ ከዚህ የባሰው ውሽንፍር ሳይመጣ   ወደ ማደርያየ ልገስግስ...አንተ ግን ሰው ሁን!

ቀጠሉ..  አመጸናል እና !
ምን አልባት እንደ ኖህ ዘመን  ዛፉ ተቆርጦ ጉቶ እስኪ ቀር ይቆረጣል...

መኪና ወዳልገባበት መንገድ ወደ ሌላለበት ልጓዝ .....እንደ ርብ ከመሆን ወሊሃንም ከመምሰል ግን ይሰውረን ልጀ ...

ልብህ ከፈቀደ አንተም ሳይመሽ ተከተለኝ .....

ይህንን ከአመታት በፊት አልነገኩህም ወይ የሚል መልእክት በማላቃቸው አረጋዊ ዘንድ ተላከልኝ...


ለጠቢብ አሃቲ ቃል ትብቁእ ! ለጥበበኛ ሰው አንድ ቃል ትበቃዋለች !

በሉ ደና ሁኑልኝ...

  

ፈለገ ጥበባት +++

02 Aug, 11:21


በቀደም እለት እግሬ ወደ አመራኝ ቦታ በድንገት ከቤቴ ተንስቸ መጓዝ ጀምርሁ....ሰው ወደ ለለበት፣ ድምጽ ወደ ማይሰማበት፣ ሁካታ ጠብ ክርክር  ንትርክ ወደ ማልሰማበት ወፌ ወደ መራችኝ ...

ስለ እውነት ግን ደክሞኝ ነው.... መኖር ያደክማል አይደል? እልፍ መከራ መስማቱ ፣  የተጨነቀች ነብስ ብኩን የሆነችን ስጋ ማየቱ፣ ተስፋ የሌለውን ተስፈኛን መመልከቱ፣  ...ምህረት የማያመጣው ጸሎታችን.. የማያርግ መስውእታችን... የማን'ባረክበት ብኩርናችን .. ...ነጻ የማያወጣን ትምህርታችን...እያሰብኩ

የኢትዮጵያ  የነጻነት ቀንዲሉ የሚለኮስበት ቀን አንገት የደፋችው አገር የምትቃናበት ጊዜ የደፈረሰው የሚጠራበት ....
ጊዜ ይኖር ይሆን? እላለሁ ..በጠቆረው ዝናባማ ደመና ፣በሚያካፋ የዝናብ ነጠብጣብ፣ ጨርቁን ጥሎ እንደ አበደ ሰው የለበስኩት ፎጦ እየጎተትኩ ...ጯክ ብየ በ ምድረበዳ አወራለሁ ..

እላለሁ ...
'የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል
       አለህም እንዳልል እንዲህ ይደረጋል'

      እላለሁ..


ተስፋ የተሰጠን ተስፋችን  የት ሄደ? እላለሁ

የማይነጋ ለሊት  ስንጠብቅ ...እንኖር ዘንድ ተውከን እላለሁ...ነጠብጣቡ ወደ ዶፍ ዝናብ ተቀይሮ መዝነብ ጀመረ... ከመምህሬ አድባር ዛፍ  ስር ከመሰለ ከወዲያ ማዶ ከ ገደሉ ጫፍ ከተንዘራፋው ዋርካ እጃቸውን  የሚያወዛውዙ ሰው ይታዮኛል.....ና ወዲህ ተጠለል በሚመስል ምልክት እየጠሩኝ...

ወደ ዋርካው  ተጠጋሁ ...በል ከዚህ ይሻልሃል ሰላም ሁን ብለው ሲሰናበቱኝ ...መባርቅቱ በበዛበት ብልጭ ልጭታው በጸናበት ስአት የት ሊሄዱ ነው? አልኩ እና መመርኮዣ ዘንጋቸውን ያዝ አደረኩ....

ልጀ ሆይ የሰማይ ምሰሶዋ  ለቋል፤

የምድርም መሰርቷ ተናውጿል....

አመጸኛ በዝቷል
  ሃጥያት ተንሳራፍቷል
    የማያልፈው ዝናብ ከ ሚመታኝ የሚልፈው ዝናብ ያርጥበኝ ... ልጀ ሆይ ሰማዮን እንዳታየው ማን አይንህን ጋረደህ ? ልቡናህ እንዳያስተውል ማን አዚም አደረገብህ....?

  እኔስ በቀን መሽቶብኛል፣ ከዚህ የባሰው ውሽንፍር ሳይመጣ   ወደ ማደርያየ ልገስግስ...አንተ ግን ሰው ሁን!

ቀጠሉ..  አመጸናል እና !
ምን አልባት እንደ ኖህ ዘመን  ዛፉ ተቆርጦ ጉቶ እስኪ ቀር ይቆረጣል...

መኪና ወዳልገባበት መንገድ ወደ ሌላለበት ልጓዝ .....እንደ ርብ ከመሆን ወሊሃንም ከመምሰል ግን ይሰውረን ልጀ

ልብህ ከፈቀደ አንተም ሳይመሽ ተከተለኝ .....


ለጠቢብ አሃቲ ቃል ትብቁእ ! ለጥበበኛ ሰው አንድ ቃል ትበቃዋለች !


  

ፈለገ ጥበባት +++

16 Jul, 16:37


https://youtu.be/ySeBfL83b80

ፈለገ ጥበባት +++

15 Jul, 18:11


ሰላም!
  በፈለገ ጥበባት ከሺ አመታት በፊት በ ነብያቱ በራዕይ ስለ ታየችው ዘጠነኛዋ የደም ጸሐይ ፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ ስለ ተነገረው የአርማጌዶን ጦርነት የጦርነቱ ቦታው ጊዜው መቸ እንደሆን  እነማን በዚህ  ይሳተፋሉ በመጻህፍ ቅዱስ የተነገረው የጎግና ማጎግ ጦርነት እና ማጎጋዎያን የቶቤል ዘሮች እነማን እንደሆኑ ይቀርብላችኋል..

ፈለገ ጥበባትን በማስተዋወቅ  ሃላፊነታችሁን ተወጡ!

ፈለገ ጥበባት +++

06 Jul, 17:42


ፈለገ ጥበባት +++ pinned «https://youtu.be/DrtZi2LyDbE»

ፈለገ ጥበባት +++

06 Jul, 17:42


https://youtu.be/DrtZi2LyDbE