Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

@ethiopianedilu


አሀዱ ብለን ከጀምበር መውጣት ጋር ፈንጥቀን፤ አብረን የህይወት ስንክሳርን ልንፈትሽ የሀገር ሁነቶችን በስነ-ተውህቦ ከሽነን ልንዳስስ ፦
ስነ-ፁሑፍን፣ ታሪካችን፣ አሁናው ክስተቶችን፣ የወንጀል ተረኮች፣ ገድሎች፣ ስነ-ግጥሞች፣ የጀብድ ታሪኮችን በፁሁፍ ከትበንና በስነምስል አዋህደን እናደርሳለን። የመንገዳችን ተካፋይ የሀሳባችን ተጋሪ ትሆኑ ዘንድ በክብር ጋበዝን።

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

18 Sep, 08:49


በሁለት ሰይፍ የተበሉት የዘውዳዊ ስርዓት ምሰሶዎች የ1960ዎቹ ባለስልጣናት እንዴት ተገደሉ? #derg #Hailis...
https://youtube.com/watch?v=WZTzKcRVIwE&si=2OoplwlPPfPIxHNO

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

08 Sep, 06:20


Ethiopian Military; በሠራዊት ቀን አከባበር ላይ የቀረቡ የወታደራዊ ትርኢቶች
https://youtube.com/watch?v=x_yAotc6Qbk&si=P0mifLApMu0w0mIG

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

28 Aug, 04:58


ህዳሴ ብስራቱን አበሰረ አሁናዊ ያለበትን የግንባታ ደረጃ The renaissance heralded #africancap...
https://youtube.com/watch?v=tF0H1HJV8OY&si=yaGFyh634gB5s5Gl

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

15 Aug, 19:38


10 የፕላኔታችን ግዙፍ ከተሞች Top The largest cities in the world #topcity #larges...
https://youtube.com/watch?v=TxluUjAT4t4&si=mw7cdikrcbu3H33_

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

09 Aug, 11:58


የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ አስደናቂ እውነታዎች፤ ልዩ ክስተቶች፤ አሳዛኝ ሁነቶች
https://youtube.com/watch?v=WVT3CJWdWVo&si=2hO0EJGIb_4Famw4

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

09 Aug, 11:56


ባላምባራስ ማሩ የዓፄ ዮሐንስ አጫዋችና ሰላይ የነበሩ


ታሪክ አብዛኛውን ጊዜ የሚጻፈው ስለ ነገስታትና ታላላቅ ሰዎች ነው። ነገር ግን ሌሎች የማናውቃቸው ታሪካቸው ሊያስደስተን የሚችሉ ግለ ሰቦች ተረስተው ይቀራሉ። አንዳንዴ ግን ባጋጣሚ የውጭ ጎብኝዎች መጽሐፍ ውስጥ ጥልቅ ብለው እናገኛቸዋለን። ከእንደነዚህ አይነት ሰዎች መካከል አንዱ ባላምባራስ ማሩ ናቸው።

ባላምባራስ ማሩ ከአድዋ ጦርነት በኋላ እንግሊዝ ጎብኝዎች አግኝተዋቸው ያቆዩልን ታሪክ አለ።

በዚያን ዘመን ባላምባራስ እድሜያቸው ሃምሳዎቹ መሀል ነበር። ጭንቅላታቸው ትልቅ ቁመታቸውም በጣም አጭር ነበር። የሚኖሩትም በአቢ አዲ ነበር። ባላምባራስ ቁመታቸው ቢያጥርም ደፋርና ማንንም የማይፈሩ ነበሩ። የማያውቃቸው ሰው ወይም ሰካራም ካናደዳቸው እግሩ መሃል ገብተው ዘርጥጠው ከጣሉ በኋላ ከጀርባው ዞረው ማንቁርቱን በማነቅ ትንፋሽ አሳጥተው ሁለተኛ እንዳይለምደው ካላደረጉ አይለቁም ነበር። ባላምባራስ ረጅም ቆንጆ ሴት አግብተው እንደሳቸው ድንክ ያልሆኑ ቆንጆ ቆንጆ ልጆች አፍርተው ነበር።

ባላምባራስ ከማጫወት ስራቸውም በተጨማሪ የአጼ ዮሐንስ ሰላይም ነበሩ። በአንድ ወቅት ጆንያ መሀል ተደብቀው ሴረኞችን በምስጢር አዳምጠው በማግስቱ እንዲያዙ አድርገዋል። ሰው ግን ይህን ሳያውቅ አጼን እግዜር ይነግራቸዋል በማለት ይፈራ ጀመር። ባላምባራስ ማሩ ከሁሉ በላይ የሚደነቁበት አንዱ እጅግ ጎበዝ የፈረስ ጋላቢ ነበሩ። ሰውነታቸው በመቅለሉም ግልቢያ የሚደርስባቸው አልነበረም። በጠመንጃ ኢላማ መምታትም ጎበዝ ነበሩ። ጦር ሜዳም ሄደው ድርቡሽ ገዳይ ስለ ነበሩ ፤ ጀግንነታቸው መፎከሪያቸው ነበር።

ባላምባራስ በአጼ ዮሐንስ ባለሟልነታቸው ዘመን ስላደረጉትና ስለ ወጋቸው ምንም ማስረጃ አላገኘሁም። ለእኔ ባላምባራስ ማሩ ክብር የሚገባቸው ድንቅ ሰው ናቸው። ድንገት የልጅ ልጆቻቸው ወዘተ ካሉ ትንሽ የታሪክ እርጥባን ቢያደርጉልን ግሩም ነው።

በባህላችን ነገሥታትና መኳንንት ቤት የሚያዝናና ድንክ መኖር የክብር ምልክት ነበር። እነዚህ ድንክዬዎችም ስራ ከመጀመራቸው በፊት ልምድ ያለው ሌላ ድንክዬ ያሰለጥናቸዋል። ተወዳጅ ለመሆን ድንክዬ ከጨዋታው ሌላ ታሪክ አነጋገር ቅኔና ብሂሎችን ጠንቅቆ ማወቅ አለበት። አብዛኛው እንዲህ አይነቱ ድንክ ባህላዊ የቤተ ክህነት ትምህርት አዋቂና ሊቅ ነበር። ምንም ይህ ባህል ለኛ ኋላ ቀር ቢመስለንም በብዙ ስራ ለተጠመደው ንጉሥ ወይም ባለ ስልጣን በመዝናናት አእምሮውን የሚያድስበት ዘዴ ነበር። ከእምዬ ምኒልክ ወዲህ ይል ባህል ቀርቷል።

ባላምባራስ ማሩን ቸሩ አግዜር ነፍሳቸውን ይማር።

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

12 Jul, 22:09


ደበበ ለትያትር ትምህርት ዘርፍ ካበረከታቸው አስተዋፅኦዎች መካከል ለትምህርቱ መጐልበት ይረዳ ዘንድ በ1973 ዓ.ም. መጽሐፍ ማሳተሙ የሚጠቀስ ነው። መጽሐፏ ‹‹የቴአትር ጥበብ ከጸሐፌ ተውኔቱ አንፃር›› የሚል ርዕስ ያላት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የትያትር ሙያተኞች እንዲበራከቱና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ሰፊ ድርሻ አበርክታለች። ደበበ በዚህ ዘርፍ ውስጥ የተጻፉ የንባብ መጻሕፍት ያለመኖራቸውን ክፍተት ተገንዝቦ ክፍተቱት ለመሙላት ሙያዊ አሻራውን ያሳረፈ የዘርፉ ባለውለታ ነው።

ደበበ ጸሐፌ ተውኔትም ነው። በርካታ ተውኔቶችን ጽፎ ለመድረክ አብቅቷል። አንዳንዶቹ ደግሞ ለበርካታ ጊዜያት ያህል በቴሌቪዥን ታይተውለታል፡፡ ደበበ ከጻፋቸውና ከተረጐማቸው ተውኔቶች መካከል ‹‹ከባህር የወጣ ዓሳ››፣ ‹‹እናትና ልጆቹ››፣ ‹‹እነሱ እነሷ››፣ ‹‹ሳይቋጠር ሲተረተር››፣ ‹‹የሕፃን ሽማግሌ››፣ ‹‹ማክቤዝ››፣ ‹‹ክፍተት››፣ ‹‹እድምተኞቹ›› እና ‹‹ጋሊሊዮ ጋሊሊ›› ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ በነበረባቸው ዓመታት ከሰራቸው የምርምር ስራዎችና ከፃፋቸው መጻሕፍት መካከል፡-
* የትያትር ጥበብ ከጸሐፊ ተውኔት አንፃር
* ደራሲው በአብዮት አውድ
* ዋዜማ ጦርነት ግጥሞች
* ሕዝባዊ ስነ-ግጥም
* Profile of Peasantry in Ethiopian Novels
* A Critical Analogy of Ethiopian Novels
* Foreign Scholars on Amharic Novels
* A Critical Analogy to Amharic Poetry
* The Need for Marxist Approach in the Teaching of Literature
* Post-Revolution Ethiopian Theaters … የሚሉትና ሌሎች ስራዎቹ ይጠቀሳሉ፡፡

በ1973 ዓ.ም. ለአንባቢያን የቀረበው ‹‹ማርክሲዝምና የቋንቋ ችግሮቹ›› የሚለው መጽሐፉ ለሕትመት ከበቁ ስራዎቹ መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡ በ1960 ዓ.ም. (ደበበ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረበት ወቅት) ከታተሙ ሦስት አጫጭር ታሪኮች መድበል ውስጥ አንዱ የደበበ ሥራ ነበር፡፡
ደበበ ሰይፉ ከእነዚህ ረቂቅ ከሆኑ ምሁራዊ አስተዋፅኦዎቹ በተጨማሪ በበርካታ ኪነ-ጥበባዊ ጉዳዮች ላይም አሻራውን ያሳረፈ ባለሙያ ነበር፡፡ በቀድሞው ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ውስጥ በመሳተፍ ለኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ መስፋፋት ሰፊ እገዛ አድርጓል። በኢትዮጵያ ሬዲዮ ውስጥም የኪነ-ጥበብ ዘርፍ ፕሮግራሞች አማካሪ ሆኖ ሰርቷል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋዎች ተቋም የጥናት መጽሔት አሳታሚ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሆኖ አገልግሏል። የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ፕሬዝደንት በመሆንም ጉልህ ድርሻ አበርክቷል። ‹‹ብሌን›› የተሰኘችው የማኅበሩ የሥነ ጽሑፍ መጽሔት እንድትታተምም አድርጓል፡፡ ከዚህም በተጨማሪም በወቅቱ በርካታ የሙያው ባለቤቶች እንዲሰባሰቡና ከውጭ አገሮች በተለይም ከሶቭየት ኅብረት ጋር ሙያዊ ድጋፍና ትብብር እንዲደረግም ጥሯል።

አንጋፋው ደራሲና ሃያሲ አቶ አስፋው ዳምጤ በአንድ ወቅት ስለ ደበበ ሲናገሩ ‹‹ደበበ ስራ ይወዳል ስራው ጥንቅቅ ያለ ነው። … ለቴአትር ዲፓርትመንት ከመከፈቱ ጀምሮ መጽሐፍ ጽፎለታል። ፅንሰ ሃሳቡን እንዲረዱት አድርጓል። ስለ ደበበ ካስደነቁኝ አንዱ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታው ነው። የደራሲያን ማኅበር ሊቀመንበር ሆኖ እኔ ስራ አስፈፃሚ ሆነን ሠርተናል። ቀድሞ ከነበረው የማኅበሩ የሥራ ዘመን ያልታየ እንቅስቃሴ አድርጓል። የሚሉት አቶ አስፋው ‹እነሆ› የተሰኘች የአጫጭር ልብ ወለዶች እና ‹የጽጌረዳ ብዕር› የሚል የግጥም መድብል መድብሎች እንዲሁም ‹ብሌን› የተሰኘች መጽሔት ታትመዋል›› በማለት የደበበን ጥንካሬ ገልፀዋል።
ታዋቂው የወግ ፀሐፊና ሃያሲ መስፍን ኃብተማርያም ደግሞ ‹‹ … ደበበ በጣም ጠንካራ፣ ትጉህ ሠራተኛ፣ ለተሰለፈበት ዓላማ ወደኋላ የማይል፣ በማስተማር ፈጣሪ (Innovator) ዓይነት ነበር። የምናስተምረውን ኮርስ ‹እንዲህ ብናደርገው፣ እንዲህ ብንለው› እያለ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንድናሻሽል በማድረግ በኩል ፈር ቀዳጅ ነበር ... ደበበ ደራሲ ብቻ አይደለም። ጥሩ የማስተማር ችሎታም ነበረው›› ብሏል።

የስነ-ጽሁፍ መምህር የነበረው ብርሃኑ ገበየሁ በበኩሉ ‹‹ … የደበበ አቀራረቡ ቀላልና የማያሻማ ነው። ድምፀቱ ደግሞ ሐዘን ከሰበረው ልብ የሚፈልቅ እንጉርጉሮ። የአቀራረብ ቀላልነት ውበቱ ነው። ይርጋለምና ልጅነቱ በተናጋሪው ህሊና አንድም ሁለትም ናቸው፤ የማይፈቱ›› በማለት ስለ ደበበ ሰይፉ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ባሰፈረው ጽሑፉ ገልጿል። ደበበ ወንድሞቹና እህቶቹ ልክ እንደእርሱ አንባቢ እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡ ለታናናሾቹም መጽሐፍት እየገዛ ይሰጥ ነበር፡፡
ደበበ ከ1985 ዓ.ም. በኋላ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ባሉ ሰዎችና ሁኔታዎች ማዘኑን ቤተሰቦቹ ይናገራሉ፡፡ ከግንቦት ወር 1985 ዓ.ም. በኋላ የማስተማር ስራውን አቆመ፡፡ ነገሮችን አብራርቶ ከመግለጽ ይልቅ ዝምታን መርጦ ለስድስት ዓመታት ያህል ቤት ውስጥ ዋለ፡፡ ከሰው ጋር የሚገናኝበት ዕድልም አልነበረውም፡፡ ‹‹ደበበ እንዴት ነህ?›› ሲባልም ‹‹ደህና›› ብሎ አጭር ምላሽ ከመስጠት ባሻገር የተብራራ ንግግር አይናገርም ነበር (በጣም ለሚወዱት ወላጅ እናቱ ግን መልስ ይሰጥ ነበር ተብሏል)

በመጨረሻም በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ዓለም ውስጥ ትልቅ ድርሻውን ያበረከተውና ምሳሌ መሆን የቻለው ገጣሚ፣ ፀሐፊ ተውኔት፣ ደራሲ፣ ሃያሲ፣ ተርጓሚ፣ መምህርና የስነ ጽሑፍ ተመራማሪ ደበበ ሰይፉ ሚያዚያ 16 ቀን 1992 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ስርዓተ ቀብሩም ሚያዚያ 17 ቀን 1992 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ-ክርስቲያን ተፈፀመ። በወቅቱም በርካታ የስነ ጽሑፍ ባለሙያዎችና የሕትመት መገናኛ ብዙኃን ስለደበበ ታላቅነት ደጋግመው ጽፈዋል፡፡

የስነ-ጽሁፍ መምህር ገዛኸኝ ጌታቸው፣ ደበበ ሰይፉ እንዳረፈ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ እንዲህ ብሎ ጽፎ ነበር። ‹‹ዛሬ የኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ አንድ ለጋ ብዕር አጣ፤ ነጥፎ አይደለም ታጥፎ ነው። ዛሬ የኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ የዋህ ሃሳብ አጣ። ከፍቶ አይደለም በኖ ተኖ እንጂ። ዛሬ ብዙዎቻችን ካወቅነው ብዙ ነገር አጣን። ካላወቅንም እሰየው፤ ከእንጉርጉሮና ከፀፀት ተረፍን።››
በ1995 ዓ.ም በጀርመን የባህል ተቋም ውስጥ በወይዘሮ ተናኘ ታደሰ አስተባባሪነት ዶክተር ፈቃደ አዘዘ፣ ዶክተር ዮናስ አድማሱ እና ገዛኸኝ ጌታቸው ‹‹የደበበ ሰይፉ ምሽት›› የሚል ደማቅ ዝግጅት አሰናድተውለታል። ደራሲያኑ ነብይ መኮንን፣ አበራ ለማ እና አብርሃም ረታ ቅኔ ዘርፈውለታል።

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

12 Jul, 22:09


የደበበ ሰይፉ 74ኛ ዓመት የልደት መታሰቢያ

ገጣሚ፣ ፀሐፊ ተውኔት፣ ደራሲ፣ ሃያሲ፣ ተርጓሚ፣ መምህርና የስነ ጽሑፍ ተመራማሪ ደበበ ሰይፉ የተወለደው ከዛሬ 74 ዓመታት በፊት ሐምሌ 5 ቀን 1942 ዓ.ም ነበር፡፡

ደበበ ሰይፉ ሐምሌ 5 ቀን 1942 ዓ.ም ከበጅሮንድ ሰይፉ አንተንይሥጠኝ እና ከወይዘሮ የማርያምወርቅ አስፋው ባለውለታው፣ የማንነቱ መገኛ፣ የዕውቀቱ መፍለቂያና መድመቂያ መሆኗን በግጥሙ ባሞካሻት ይርጋለም ከተማ ተወለደ፡፡ ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ልዩ የማንበብ ፍቅር ነበረው፡፡ ፊደል የቆጠረው በቄስ ትምህርት ቤት ነው፡፡ የትምህርት አቀባበሉ አስደናቂ ስለነበር መምህሩ የቤተ ክህነት አገልጋይ እንዲሆን ፈልገው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አባቱ ወደ መደበኛ/ዘመናዊ ትምህርት ቤት እንዲገባ አደረጉት፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ይርጋለም ከተማ ውስጥ በሚገኘው ራስ ደስታ ትምህርት ቤት አጠናቀቀ፡፡

በመቀጠልም ወደ አዲስ አበባ በመዛወር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በኮከበ ጽባሕ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ትምህርት ቤት ተማረ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተናውን በማለፍ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ)ን ተቀላቀለ፡፡ ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲገባ የቢዝነስ ትምህርት ክፍል ተማሪ ሆኖ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ደበበ የነፍሱ መሻት ስነ-ጽሑፍ እንጂ ቢዝነስ ስላልነበር የቢዝነስ ትምህርቱን ለአንድ ዓመት ያህል ከተማረ በኋላ ወደ ስነጽሑፍ ትምህርት ተዛወረ፡፡ በ1965 ዓ.ም ከዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ-ጽሑፍ ትምህርት ክፍል በከፍተኛ ማዕረግ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመረቀ፡፡ ቀጥሎም በ23 ዓመቱ በዚያው በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሥነ-ጽሑፍን ማስተማር ጀመረ። ከአምስት ዓመታት በኋላ ደግሞ በእንግሊዝኛ ስነ-ጽሑፍ (English Literature) የሁለተኛ ዲግሪውን እንደለመደው በከፍተኛ ማዕረግ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡

መረጃዎች ዕንደሚያሳዩት የጥናትና የምርምር ውጤቶች በስፋት መሠራት በመጀመራቸው እንደ ደበበ ሰይፉ ያሉ መምህራን በዚህ ትምህርት ክፍል ውስጥ መቀላቀል ሲጀምሩ የትምህርት ክፍሉም እያደገና እየተስፋፋ የመጣበት ዘመን ነበር። ደበበ የኢትዮጵያ የሥነ-ግጥም እና የሥነ-ጽሐፍ ታሪክንና በዚህ ታሪክ ውስጥ ደግሞ ኪነታዊ አስተዋፅኦዋቸው ሰፊ የሆኑትን ታላላቅ ጸሐፊያንን ታሪክና የአፃፃፍ ቴክኒካቸውንም ጭምር እያጠና ማቅረብ ጀመረ። ያለፈው የጥበብ አሻራ ለመጪው ጥበብ የሚያቀብለውን መረጃ እያዛመደ ትውልድን በጥበብ ማስተሳሰር አንዱ ተግባሩ ነበር።

ደበበ በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ የሚገኙ የታሪክ፣ የስነ ግጥም፣ የትያትር፣ የፍልስፍና፣ የፖለቲካ … ጽንሰ ሃሳቦችን ከጥንታዊ ሰነዶች ውስጥ እየፈተሸ በማውጣት ‹‹ትውልድ እንዲህ ነበር፣ እንዲህም ኖሯል፣ እንዲህም አስቧል .›› እያለ በትውልድ መካከል የመሸጋገሪያ ድልድይ ሆኖ አገልግሏል።

ደበበ የተዋጣለት ገጣሚ ነበር። በአገጣጠም ችሎታው ውብ እና ማራኪነት የተነሳ ብዙዎች ‹‹ባለቅኔው ደበበ ሰይፉ›› እያሉ ይጠሩታል። ይህ በስነ-ግጥም ዓለም ውስጥ የተሰጠው ፀጋ ከሌሎች ጉዳዮች ሁሉ ገዝፎ የሚነገርለትም ነው። ደበበ ሲነሳ ገጣሚነቱ አብሮ ብቅ የሚልለት የጥበብ ሰው ነው። እነዚህ የግጥም ትሩፋቶቹ በአንድ ላይ ተሰባስበው ‹‹የብርሐን ፍቅር›› በሚል ርዕስ ታትመዋል። ይቺ የሥነ-ግጥም መጽሐፍ ደበበ ቀደም ሲል በተማሪነት እና በአስተማሪነት ዘመኑ ሲፅፋቸው የነበሩት ግጥሞች ተካትተው የሚገኙባት ድንቅ መፅሐፉ ነች።

ከዚች መፅሐፉ በተጨማሪ በ1992 ዓ.ም በሜጋ አሳታሚ ድርጅት አማካኝነት ‹‹ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ›› በሚል ርዕስ ሁለተኛዋ የሥነ-ግጥም መፅሐፉ ታትሞ ለንባብ በቅታለች። ነገር ግን በዚህ ወቅት ደበበ በሕይወት የለም ነበር። የዚችን መፅሐፍ አጠቃላይ ገፅታ በተመለከተ አስተያየት የሰጠው ታዋቂው የወግ ጸሐፊና ሃያሲ መስፍን ኃብተማርያም ‹‹ደበበ ሰይፉ በርዕስ አመራረጡና በሚያስተላልፋቸው ልብ የሚነኩ መልዕክቶች ብቻ ሳይሆን በስንኞቹ አወራረድና የቤት አመታቱ በአጠቃላይ በውብ አቀራረቡ ተደራሲያንን የሚመስጥ ገጣሚ ነው። ስለ ተፈጥሮ ሲገጥም ፀሐይና ጨረቃ፣ ቀስተ ደመናና የገደል ማሚቶ ያጅቡታል።

ስለ ፍቅር ስንኞች ሲቋጥር የፍቅረኞችን ልብ እንደ ስዕል ቆንጆ አድርጐ በቃላት ቀለማት ያሳያል። ክህደት ላይ እንደ አንዳንድ ገጣሚያን አያላዝንም። ይልቁንም ውበትና ህይወትን አገናዝቦ ‹ያውላችሁ ስሙት፤ እዩት› ማለትን ይመርጣል ... እኔ እንደማውቀው ደበበ ሰይፉ በገጣሚነቱ ሁሌም ዝምተኛ ነው። አይጮህም። ጮሆም አያስበረግግም። ይልቁንስ ለዘብ ለስለስ አድርጐ 'እስቲ አጢኑት' ይለናል። ደግመን እንድናነብለት የሚያደርገንም ይኸው ችሎታው ነው" በማለት ጽፏል።

ደበበ ከገጣሚነቱ ባሻገር ሐያሲም ነበር፡፡ ሐያሲ ታሪክ አዋቂ ነው። ያለፈውን ከአሁኑ ጋር እያነፃፀረ የሚያስረዳና የሚተነትን ባለሙያ ነው። የሒስ ጥበብን ከታደሉትና በኢትዮጵያ የዘመናዊ ሂስ ጥበብ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት ሰዎች መካከል ደበበ ሰይፉ አንዱ ነበር። ደበበ ያለፉ ታሪኮችንም ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የሚሰጣቸው በሳል አስተያየቶች ከልብ የነበሩና ለለውጥ የሚያነሳሱ እንደነበሩ የሚያውቁት ሁሉ ይመሰክሩለታል፡፡ ደበበ ሰይፉ በሥነ ግጥም ተሰጥዖውና በሚያነሳቸው ርዕሰ ጉዳዮች በኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ስማቸው ጐልቶ ከሚነሱ ከያኒያን መካከል አንዱ መሆኑን ቀደም ያሉት ኃያስያን ጽፈውታል።

የደበበ ችሎታ በዚህ ብቻም አያበቃም። ደበበ የትያትር ጥበብ መምህር ከመሆኑም በላይ በዘርፉ ውስጥ ግዙፍ የሚባል አስተዋፅኦ አበርክቶ አልፏል። ደበበ በመድረክ ላይ የሚሠሩ ቴአትሮችንና የቴአትር ጽሑፎችን የያዟቸውን ሐሳቦች በመተንተንና ሒስ በመስጠት ለዘርፉ ዕድገት የበኩሉን ሚና ተጫውቷል።

ደበበ የቃላት ፈጣሪም ነው። ለአብነት ያህል በትያትርና በሥነ-ጽሑፍ ዘርፎች ውስጥ በእንግሊዝኛ ቋንቋ መጠሪያ የሆኑ ሙያዊ ቃላትን ወደ አማርኛ በማምጣት አቻ የሆነ የአማርኛ ትርጉም በመስጠት ይታወቃል። በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ ክፍለ ትምህርት ውስጥ እስከ አሁን ድረስ መጠሪያ የሆኑትንና ‹‹ገፀ-ባህርይ››፣ ‹‹ሴራ››፣ ‹‹መቼት››፣ ‹‹ቃለ-ተውኔት›› … እየተባሉ የሚገለፁትን መጠሪያዎች የፈጠረው ደበበ ሰይፉ ነው። ‹‹Character›› ለሚለው የእንግሊዝኛ መጠሪያ ‹‹ገፀ-ባህርይ›› በማለት አቻ ትርጉም ሰጥቶታል፡፡ ‹‹Setting›› የሚለው የእንግሊዝኛ መጠሪያ በውስጡ ጊዜ እና ቦታን መያዙን በመረዳት ‹‹መቼት›› ብሎ ወደ አማርኛ ቋንቋ ተረጐመው። መቼት ማለት ‹‹መቼ›› እና ‹‹የት›› ማለት ሲሆን፤ ጊዜንና ቦታን ይገልፃል። ‹‹Dialogue›› የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል ተዋንያን በትወና ወቅት የሚናገሩት ሲሆን፤ ይህን ቃል ‹‹ቃለ-ተውኔት›› በማለት በአማርኛ የተረጐመው ደበበ ሰይፉ ነው። ደበበ እነዚህንና ሌሎችንም ሥነ-ጽሑፋዊ ቃላትን በመፍጠር ቃላቱ በትውልዶች አንደበት፣ አእምሮ እና ብዕር ውስጥ ለዘላለም እንዲኖሩ ያደረገ ጥበበኛ ነው።

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

08 Jul, 16:16


Kenenisa Bekele is a true legend in long-distance running. Despite facing numerous challenges and injuries, Bekele's determination and passion never wavered. From dominating the track with his blistering speed to making a remarkable comeback in marathons, he continues to inspire many. The middle-distance track superstar hasn't matched his track and cross-country accomplishments, where he earned 19 global titles. Still, whenever he was written off, he silenced his critics with a strong comeback race, none more so than with his last chance run to make the African nation's team for Paris 2024. Bekele's journey reminds us that setbacks are stepping stones to more significant achievements. #Olympic2024

ሀያላኑ ቀነኒሳ በቀለና ኤሊዩድ ኪፕቾጌ ለ20 ዓመታት ያደረጉት ፍጥጫና በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚያደርጉት ትንቅንቅ
https://youtube.com/watch?v=iS_bA4V7spg&si=b-rBkncrGFwIgTHV

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

22 Jun, 12:37


ፍፁም የተለወጠው ከፒያሳ አድዋ ሙዚየም እስከ አራት ኪሎ Addis Ababa Piazza to 4Kilo
https://youtube.com/watch?v=08E2FOC55GI&si=2x9uckTBbzL8cOD2

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

19 Jun, 10:47


https://youtu.be/zMqjczqbnSM?si=txavQ1_fB5oO-Uwp
በ2024 ከፍተኛ ተከፋይ ስፖርተኞች The World’s 10 Highest Paid Athletes
https://youtube.com/watch?v=zMqjczqbnSM&si=txavQ1_fB5oO-Uwp

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

04 Jun, 12:25


https://www.blogger.com/#

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

04 Jun, 12:24


***
በመስከረም ወር 1965 ዓ.ም ንጉሠ ነገሥቱ የመጨረሻቸው የሆነውን የአውሮፓ ጉብኝት በምዕራብ ጀርመን አደረጉ፡፡ ጃንሆይ ያረፉበት ሆቴል ድረስ እንድመጣ ተጠራሁ፡፡ የአንድ መቶ ዶላር ኖት ሰጡኝና በጀርመን የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ኃይሎች መገበያያ ወደ ሆነው PX Supermarket ሄጄ ‹‹ቪታሊስ›› የተሰኘ ግማሽ ደርዘን የጠጉር ቶኒክ ገዝቼ እንድመጣ አዘዙኝ:: የዚያን ቀን ምሽት የጠጉር ቶኒኩንና በመልስ የተቀበልኩትን ገንዘብ ሰጠኋቸው፡፡ ጃንሆይ መልሱን ቆጠሩና ‹‹ምን! ዋጋው ሰላሳ ዶላር ነው?›› አሉና ጠየቁኝ፡፡ ‹‹ግርማዊነትዎ! አዎ!›› አልኩና ደረሰኙን አሳየኋቸው፡፡ ‹‹የማይታመን ነው! ይኼ ነገር እንዴት ተወዷል?›› አሉና አጉተመተሙ፡፡ የመልሱን ገንዘብ እንድወስደው እየሰጡኝ ‹‹ፍራንክፈርት ስትመለስ የኪስ ገንዘብ ይሰጥሃል›› አሉኝ፡፡ የታዘብኩት ነገር፣ ለእቃዎች ዋጋ ጃንሆይ ምን ያህል ትኩረት እንደሚሰጡ ነው፡፡ የግል ኑሯቸውን በተመለከተ ጃንሆይ በጣም ቁጥብ ናቸው፤ ሁኔታዎች ሲፈቅዱ ደግሞ ጃንሆይ ለጋስ እንደሆኑ የታዘብኩበት አጋጣሚ ጥቂት አይደለም፡፡ በዚያን ጊዜ ግን በአገሪቱ በጣም ውስን የሆነ የውጪ ምንዛሪ ነበር - ለንጉሠ ነገሥቱም ጭምር!
***
በሚያዝያ ወር 1966 ዓ.ም አንድ ምሽት የክብር ዘበኛ ዋና አዛዥ የነበሩት ጀነራል አበበ ገመዳ፣ ራስ አስራተ ካሳ ቤት ተገኝተው ከተነጋገሩ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ ተሰናብተው ይሄዳሉ፡፡ ይህንን አስመልክተው ዶ/ር አስፋ ወሠን ሲጽፉ ‹‹ከምሳ በኋላ በአትክልቱ ስፍራ ስንዘዋወር አባቴ ያስጨነቀውን ጉዳይ ያካፍለኝ ጀመር፡፡ ለካስ ባለፈው ምሽት ጀነራል አበበ ከቤታችን የመጡት አማጺ ወታደራዊ መኮንኖች ችግር ከመፍጠራቸው በፊት በቁጥጥር ሥር ለማዋል ጃንሆይ እንዲፈቅዱ ለመምከር ኖሯል... የዚያን እለት ጠዋት አባቴና የመከላከያ ሚኒስትሩ ጀነራል አቢይ አበበ ያቀረቡት ሃሳብ በጃንሆይ እምቢተኛነት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ፡፡ በአትክልቱ ውሥጥ የምናደርገው ሽርሽር ሊያበቃ ሲል፣ አባቴ ፍርሃቱን ፍርጥርጥ አድርጎ ሲገልጽልኝ ‹መጨረሻችን ተቃርቧል የሚል ሥጋት አለኝ፡፡ አማጺ ወታደሮች ለጃንሆይ ታማኝ እንደሆኑና የሚቃወሙትም ባለሥልጣኖቻቸውን ብቻ እንደሆነ አድርገው፣ ሀሰተኛ ተስፋ ለምስኪኑ ንጉሠ ነገሥት የሚመግቡ ኃይሎች፣ በቤተ መንግሥቱ ውሥጥ አሉ፡፡ ነገር ግን የአማጺዎቹ ዋንኛ ዒላማ ራሳቸው ንጉሠ ነገሥቱ እንደሆኑ ጃንሆይ አሁን በቅርቡ ይረዱታል፡፡ በዝግታ ከምትሰምጠዋ መርከብ ላይ ምንም ሳያደርጉ ተቀምጦ ከማለቅ በስተቀር ሌላ አማራጭ ያለ አይመስለኝም››› ብሎኝ ነበር፡፡ አባቴ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ሁናቴ እንደዚህ ተስፋ ቆርጦ አይቼው አላውቅም፡፡
***
በሚያዝያ መጨረሻ 1966 ዓ.ም የአባቴን 52ኛ ዓመት የልደት በዓል በመጠነኛ ዝግጅት ካከበርን በኋላ፣ በጥናት ከፍሉ ውስጥ እኔና አባቴ ብቻ ቀረን፡፡ የጃንሆይ መንግሥት ሊወድቅ በቋፍ ላይ እንዳለ አጫወተኝ:: በአባቴ አስተያየት፣ በዘውድ ሥርዓቱ ላይ የተጋረጠው ተጨባጭ አደጋ የተማሪዎች ወይም በየጊዜው የሚሰለፉ ተቃዋሚዎች ሳይሆን የጦር ሠራዊቱ ንቅናቄ ነው፡፡ ከ1953 ዓ.ም የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ በኋላ ሌላ የከፋ አደጋ በመንግሥት ላይ ሊደርስ ይችላል ብሎ አባቴ ለረጅም ጊዜ ሲጨነቅበት ቆይቷል:: ከአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ የተጣጠፈችና በደም የተበከለች ወረቀት አውጥቶ ሰጠኝ፡፡ ከታህሳስ 1953 ዓ.ም የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መሪዎች አንዱ ከነበሩትና በኋላ ከተገደሉት የፖሊስ ሠራዊት ጠቅላይ አዛዥ ከጀነራል ጽጌ ዲቡ ኪስ የተገኘች መሆንዋን ነገረኝ፡፡ ወረቀቷ የልዑላን፣ የመሳፍንትና የባለሥልጣናት ስም ዝርዝር የያዘች ሲሆን በስማቸው ትይዩ ደግሞ መፈንቅለ መንግሥቱ ከተሳካ በኋላ ቤታቸውን የሚወርሱት የአመጹ ዋና ዋና ተዋንያን ስም ተጽፏል፡፡ የቤተሰባችን ስም ከሰፈረበት ትይዩ፣ ቤታችንን የሚወርሰውን ግለሰብ ስም አየሁ - ጀነራል መንግሥቱ ንዋይ!
***
ሰኔ 24 ቀን 1966 ዓ.ም ልዑል ራስ አሥራተ ካሣ፣ ከመኖሪያ ቤታቸው በወታደሮች ተያዙ:: ከመያዛቸው በፊት አስቀድመው ያዘጋጁትን አንድ ኤንቨሎፕ ለጃንሆይ በእጃቸው እንዲሰጥላቸው ለልጃቸው ለሙሉጌታ አሥራተ አደራ ሰጥተው ነበር፡፡ ሙሉጌታ በአደራ የተቀበለውን ኤንቨሎፕ ለማድረስ ወደ ቤተ መንግሥት ውሥጥ ሲገባ፣ ጃንሆይን ያገኛቸው በመኝታ ክፍላቸው ውሥጥ ነበር፡፡ ራስ አሥራተ በደርግ መታሰራቸውን ጃንሆይ ሰምተዋል፡፡ ‹‹የቀኝ እጃችንን ዛሬ ቆረጡት! ግልገሎቿን የተነጠቀች ድመት ምን ለማድረግ ትችላለች? መጮህ ብቻ! እኛም ከመጮህ በስተቀር ለማድረግ የምንችለው ምንም የለም!›› አሉ፡፡ ከራስ አሥራተ የተላከላቸውን ኤንቨሎፕ ሲመለከቱም ሙሉጌታን እንዲከፍተው አዘዙት:: ኤንቨሎፑ የያዘው ቀደም ባሉ ሳምንቶች፣ ንጉሠ ነገሥቱ ከኢትዮጵያ የሚወጡበትንና ጥገኝነት የሚያገኙበትን ሁኔታ አስመልክቶ፣ ራስ አሥራተ ካሣ፣ ከአሜሪካና ከብሪታንያ ኤምባሲዎች ጋር ያደረጉትን የደብዳቤ ልውውጥ ነበር፡፡ የአሜሪካ መንግሥት፣ ለንጉሠ ነገሥቱ፣ ጥገኝነት ለመስጠትና ከኢትዮጵያ ክልል ከሚወጡበት ጊዜ ጀምሮም፣ ለደህንነታቸው ተገቢውን ጥበቃ ለማድረግ ዋስትና ሰጥቶ ነበር፡፡

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

04 Jun, 12:24


***
በ1957 ዓ.ም የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ሄንሪክ ሉብክ ኢትዮጵያን ሲጎበኙ፣ በአሥመራ ቤተ መንግሥት የቁርስ ግብዣ ተደርጎላቸው ነበር፡፡ ከቀረበላቸው ቁርስ ውስጥ ገንፎውን እንግዶቹ በጣም ወደውት ነበርና የፕሬዚዳንቱ ባለቤት የገንፎውን መጣፈጥ ምሥጢር ለማወቅ ኦስትሪያዊቷን የቤተ መንግሥቱን ዋና ሼፍ አስጠርተው አነጋግረው ነበር፡፡ የምግቡ መጣፈጥ አንዱ ምሥጢር በተለይ የተሰራው ማብሰያ ድስት መሆኑ ተገለጸላቸውና፣ አንዱ ድስት ተጠቅልሎና በካርቶን ታሽጎ፣ ለፕሬዚዳንቱ ባለቤት በስጦታ ተበረከተላቸው፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ ያገለገለ ድስት ለጀርመኑ ፕሬዚዳንት ባለቤት በስጦታ መሰጡትን ያወቁት እንግዶቹ ከሄዱ በኋላ ስለነበር፤ ተመሳሳይ አዳዲስ ድስቶች ተገዝተው፣ ጀርመን ወደሚገኘው የፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ቤት እንዲላክ አስደርገዋል፡፡
***
በከሸፈው የታህሳስ 1953 ዓ.ም መፈንቅለ መንግሥት ማግሥት፣ ጃንሆይ የብራዚል ጉብኝታቸውን አቋርጠው በአስመራ በኩል ወደ አዲስ አበባ አመሩ፡፡ የንጉሳዊው ቤተሰብ፣ ከፍተኛ ባለስልጣኖችና ሌሎች የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አየር ማረፊያውን ከበው፣ የጃንሆይን መምጣት በጉጉት ይጠባበቁ ነበር:: ንጉሠ ነገሥቱን የያዘቸው ዲሲ 6 አውሮፕላን እንዳረፈች፣ የመውረጃው ደረጃው ቀርቦ ቀይ ምንጣፍ አውሮፕላኑ ድረስ ተዘረጋ፡፡ ከአውሮፕላኑ ቀድመው የወረዱት የንጉሠ ነገሥቱ ልዩ ረዳት ጀነራል ደበበ ኃይለ ማርያም ነበሩ፡፡ ጃንሆይ ወታደራዊ ዩኒፎርማቸውን እንደለበሱ፣ ገና ከአውሮፕላኑ ብቅ እንዳሉ፣ ዙሪያውን ከቦ የነበረው ሕዝብ፣ እልልታና ጭብጨባ አሰማ፡፡ የንጉሠ ነገሥቱ እግር መሬት እንደረገጠ፣ አልጋ ወራሹ ልዑል አስፋ ወሠን፣ የጃንሆይ እግር ሥር ተደፉ፡፡ ከመፈንቅለ መንግሥቱ አድራጊዎች ጋር በመተባበራቸው ይቅርታ መጠየቃቸው ነው፡፡ ጃንሆይ እግራቸው ሥር የተደፋውን ልጃቸውን ለማንሳት ምንም ሙከራ ሳያደርጉ በቁጣ፤ ‹‹ለእኛ ክብር የሚሆነው፣ አንተ ሞተህ ለቀብርህ ብንገኝ ነበር! ተነስ!›› ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
***
ስለ ኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የሚደረጉ ጥናቶች ሁሉ፣ ስለ እቴጌ መነን የሚጽፉት ከግርጌ ማስታወሻ ያልዘለለ መሆኑ፣ እቴጌይቱ በንጉሣዊው ቤተሰብ ላይ የነበራቸውን ሚና አኮስሶ የሚያሳይ እንደሆነ ዶ/ር አስፋ ወሰን ጽፈዋል፡፡ እቴጌ መነን ምንም እንኳ እንደ እቴጌ ጣይቱ በመንግሥት የእለት ተእለት ፖለቲካዊ ውሣኔ ተሳታፊ ባይሆኑም፣ ለንጉሠ ነገሥቱ የቤተሰብ ሕይወት አለኝታነታቸውን በተግባር ያስመሰከሩ ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያን ለሚጎበኙ የውጪ እንግዶች የሚሰናዱ መስተንግዶዎችና ግብዣዎች የሚከናወኑት በእቴጌ መነን ብርቱ ቁጥጥር ነበር፡፡ በስደቱ ዘመን የእንግሊዝ አገር ብርድና ቅዝቃዜ፣ ጤናቸውን ጎድቶት ስለነበር በውጪ አገር ጉብኝቶች ጃንሆይን ተከትለው ለመሄድ ፍላጎት አላሳዩም፡፡ እቴጌ መነን መንፈሳዊ እመቤት እንደመሆናቸው፣ የሞት ፍርድን አጥብቀው ይቃወሙ ነበር፡፡ ‹‹የሰውን ሕይወት መልሶ ለመውሰድ ሥልጣን ያለው የፈጠረው እግዚአብሔር ብቻ ነው›› ይሉ ነበር፡፡ በአገር ክዳት ወንጀል ተከሰው ሞት የተፈረደባቸው አንዳንድ ሰዎች፣ ቅጣቱ ሳይፈጸምባቸው የቀረው በእቴጌ መነን አማላጅነት የተነሳ ነበር፡፡
***
ራስ ተፈሪ ንጉሠ ነገሥት ተብለው ዘውድ ለመድፋት ሲዘጋጁ፣ እቴጌ መነንን ለመፍታትና በውበታቸው የታወቁት ወ/ሮ አስቴር መንገሻን (የራስ ስዩም መንገሻ እህት) ለማግባት ያውጠነጥኑ እንደነበር ታውቋል፡፡ ንጉሡ ይህንን ሀሳባቸውን እንዲተዉ ያግባቡት ራስ ካሣ ነበሩ፡፡ ‹‹ወ/ሮ መነን በክፉም በደግም ከጎንዎ አልተለዩም፡፡ ከእንግዲህ ውለታቸውን መክፈል ደግሞ የእርስዎ ተራ ይሆናል›› በማለት ራስ ካሣ ሀሳባቸውን ማስቀየራቸው ተጠቅሷል:: እቴጌ መነን ይህንኑ ጉዳይ አንስተው ከዶክተር አስፋ ወሰን እናት ጋር ሲጫወቱ፤ ‹‹ጃንሆይ እኔን ትተው ሌላ ቢያገቡ ኖሮ፣ እኔም ቤቱን ትቼላቸው ወጥቼ፣ ራስ ኃይሉን አገባ ነበር›› ብለዋል፡፡ የጎጃሙ መሥፍን ራስ ኃይሉ፣ የዐፄ ኃይለ ሥላሴ ብርቱ ተቃዋሚ የነበሩ ሲሆን ለወ/ሮ መነን ያላቸውን ፍቅር ሳይደብቁ ይናገሩ ነበር ይባላል፡፡
***
በሐምሌ ወር 1964 ዓ.ም ንጉሠ ነገሥቱ፣ 80ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ያከብሩ ስለነበር፣ ክረምቱ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ደምቆ ነበር፡፡ የልደታቸው ዕለት ጠዋት ራስ አሥራተና ባለቤታቸው፣ ጃንሆይን “እንኳን አደረሰዎ” ለማለት ወደ ቤተ መንግሥት አመሩ:: ጃንሆይ የተቀበሏቸው ከመኝታ ክፍላቸው ጋር በተያያዘው የእንግዳ መቀበያ ክፍል ነበር፡፡ ራስ አስራተ በተለይ ያዘጋጁትን ስጦታ ካበረከቱ በኋላ ጃንሆይ አልጋ ወራሻቸውን አሳውቀው፣ ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ከዚህ የተሻለ ጊዜ እንደሌለና “ይህንን ከፈጸሙ በታሪክ ውስጥ ስምዎ ለዘላለም ሲነሳ ይኖራል” ሲሉ በጃንሆይ እግር ስር በመውደቅ ተማጸኑ፡፡ ጃንሆይ ራስ አሥራተ ከእግራቸው ላይ እንዲነሱ ካደረጉ በኋላ፣ የሚከተለውን ምላሽ ሰጡ፤ ‹‹እስኪ ንገረን እባክህ? ንጉሥ ዳዊት ሥልጣኑን በፈቃዱ ለቅቋል? ወይስ ሥልጣኑን በፈቃዱ የለቀቀ የኢትዮጵያ ንጉሥ በታሪክ ውስጥ ነበር? እግዚአብሔር እስከፈቀደልን ጊዜ ድረስ እንገዛለን፡፡ እኛ ከሄድን በኋላ ለኢትዮጵያ የሚጠቅማትን እርሱ ያውቃል›› ብለው ነበር፡፡

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

04 Jun, 12:24


ጃንሆይ በቅርብ ዘመድ ዓይን

“--ጃንሆይ ራስ አሥራተ ከእግራቸው ላይ እንዲነሱ ካደረጉ በኋላ፣ የሚከተለውን ምላሽ ሰጡ፤ ‹‹እስኪ ንገረን እባክህ? ንጉሥ ዳዊት ሥልጣኑን በፈቃዱ ለቅቋል? ወይስ ሥልጣኑን በፈቃዱ የለቀቀ የኢትዮጵያ ንጉሥ በታሪክ ውስጥ ነበር? እግዚአብሔር እስከፈቀደልን ጊዜ ድረስ እንገዛለን፡፡ እኛ ከሄድን በኋላ
ለኢትዮጵያ የሚጠቅማትን እርሱ ያውቃል››”

ዶ/ር አስፋ ወሰን አሥራተ፣ የታዋቂው መሥፍን፣ የልዑል ራስ ካሣ የልጅ ልጅ ናቸው፡፡ አያታቸው ራስ ካሣ፣ የዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመድና የቅርብ ወዳጅ ነበሩ፡፡ አባታቸው ልዑል ራስ አሥራተ ካሣ፣ በተለያዩ ጠቅላይ ግዛቶች በአገረ ገዢነት፣ በኤርትራ የንጉሠ ነገሥቱ እንደራሴ፣ በመጨረሻም የዘውድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን፣ በደርግ ተይዘው እስከታሰሩበት ጊዜ ድረስ አገልግለዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1948 ዓ.ም የተወለዱት ዶ/ር አስፋ ወሰን፤ ትምህርታቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው የጀርመን ትምህርት ቤት እንዲሁም በቱቢንገን ዩኒቨርሲቲ፣ ካምብሪጅ ዩነቨርሲቲ በሚገኘው የማግደሊን ኮሌጅና በታሪክ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በተቀበሉበት በፍራንክፈርት ዩኒቨርሲቲ ተከታትለዋል፡፡
ዶ/ር አስፋ ወሠን በጀርመንኛ ቋንቋ ባቀረቧቸው መጻሕፍት፣ ከፍተኛ ተነባቢነት በማግኘታቸው፣ ሁለት የተከበሩ የጀርመን የሥነ ጽሑፍ ሽልማቶችን ለመቀበል በቅተዋል:: ከዚህም ሌላ እ.ኤ.አ በ2014 ዓ.ም ‹‹King of Kings›› በሚል ርዕስ ስለ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ታሪካዊ አነሳስና አሳዛኝ አወዳደቅ በጀርመንኛ ቋንቋ መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡ መጽሐፉ ከታተመ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ተተርጉሞ፣ ለመላው ዓለም አንባቢያን ቀርቧል፡፡ መጽሐፉ ስለ ጃንሆይ እስካሁን የማናውቃቸውን አዳዲስ ጉዳዮች ይዟል፡፡ ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡
***
ጃንሆይ ወደ ጠቅላይ ግዛት ወይም ወደ ውጪ አገር ካልሄዱ፣ ከቀትር በኋላ በመናገሻ ከተማቸው በመኪና የመዘዋወር ልማድ ነበራቸው፡፡ በዚህ ጉዞ የንጉሣዊ ቤተሰቡ ልጆች፣ ጃንሆይን አጅበው እንዲሄዱ ይፈቀድላቸው ነበር፡፡ ጃንሆይ ብዙ ጊዜ መጓዝ የሚወዱት ፕሬዚዳንት ሩዝቬልት ባበረከቱላቸው ሽንጣምና ባለ ሶስት ረድፍ ወንበር ባላት ካዲላክ ሊሞዚን ነበር፡፡ በሹፌሩና ከኋላ ባለው መቀመጫ መካከል ዙሪያውን በሮዝውድ የተጌጠ የመስተዋት መከለያ አለ:: ከመስተዋቱ ዝቅ ብሎ ባለው ሠሌዳ ላይ H.I.M (His Imperial Majesty) የሚል ጽሑፍ ተቀርጾበታል፡፡ ከሹፌሩ ጀርባ የንጉሠ ነገሥቱ ልዩ ረዳት የሚቀመጥ ሲሆን ከዚሀ ጀርባ ያለው መሐል ወንበር ላይ ልጆች ተደርድረው፣ ጃንሆይ ደግሞ ከመጨረሻው ወንበር ላይ ይሰየማሉ:: ንጉሡ እንደ ጥንት ሮማውያን ገዢዎች፣ በከተማ ውስጥ እየተዘዋወሩ፣ ምጽዋት መስጠት ያስደስታቸዋል:: አንዳንድ ጊዜ እኛም እንድንመጸውት ረብጣ የብር ኖቶች ይሰጡናል:: ምጽዋቱን መስጠት ገና ከመጀመራችን፣ በመጠኑ ዝቅ ባለው የመኪናው መስኮት በኩል፣ ከየአቅጣጫው የሚሰነዘሩ እጆች፣ ብሮቹን ከመቅጽበት ይናጠቋቸዋል፡፡

***
ጃንሆይን ያለ ንጉሣዊ ፕሮቶኮል እንደ ማንኛውም ተራ ሰው ሲንቀሳቀሱ መመልከት የተለመደ ነገር አይደለም፡፡ በአንድ ወቅት በአስመራ የእንደራሴው መኖሪያ ቤተ መንግሥት ውስጥ ጃንሆይ ከራስ እምሩና ከአባቴ ከራስ አሥራተ ጋር ፑል ሲጫወቱ ለማየት ዕድል ገጥሞኝ ነበር፡፡ ጃንሆይ የፑል ማጫወቻውን እንደተመለከቱ ወደ ራስ እምሩ ዘወር ብለው፤ ‹‹ልጅ እያሱ ቤት ልጆች ሆነን ፑል እንጫወት እንደነበር ታስታውሳለህ? እስኪ ጨዋታው አልጠፋህ እንደሆነ እናያለን›› አሉና ኮታቸውን አውልቀው ለአባቴ ሰጡት፡፡ ሁለቱ ትልልቅ ሰዎች ጥቂት ከተጫወቱ በኋላ ራስ እምሩ፣ አባቴን ወደ ጨዋታው እንዲገባ ሲጠይቁት፣ የጃንሆይን ኮት ለኔ ሰጠኝና ወደ ጨዋታው ገባ፡፡ እንደተመለከትኩት በጨዋታው ጃንሆይ ከአባቴም ሆነ ከራስ እምሩ የተሻለ ችሎታ አላቸው፡፡ ይህ ቀን ንጉሠ ነገሥቱ ያለ ኮት ወይም ያለ ካባ፣ በሸሚዝ ብቻ ሆነው የተመለከትኩበት የመጀመሪያውም የመጨረሻውም አጋጣሚ መሆኑን መናገር አለብኝ፡፡ ንጉሡን የከበባቸው ያ ሁሉ አስፈሪና የሚያርድ ግርማ ሞገስ፣ በድንገት ከራሳቸው ላይ ወልቆ ራሱን በጨዋታ የሚያዝናና ተራ ሰው ሆኑ፡፡ በቆምኩበት ቦታ ደርቄ፣ የጃንሆይን ኮት በተዘረጋው እጄ ላይ እንደያዝኩ፣ ንጉሠ ነገሥቱ ድንጋዮቹን እያጋጩ፣ ተራ በተራ በጉድጓዱ ውስጥ ሲያስገቡ ፍዝዝ ብዬ እመለከት ነበር፡፡ በመጨረሻ ጨዋታው በጃንሆይ ድል አድራጊነት ሲጠናቀቅ፣ ኮታቸውን አቀበልኳቸው፡፡ ጃንሆይ ኮታቸውን አስተካክለው ለብሰው ሲጨርሱና እንደገና ወደ ‹‹ግርማዊ ንጉሠ ነገሥትነት›› ሲለወጡ ተመለከትኩ፡፡

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

20 May, 13:53


Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች pinned «ጥንታዊ አስደናቂ ታሪኮች፤ ሲራራ ሰራዊት፣መቆራኘት፣የሚስጥር ዘበኛ፣ የሴት ትወና ጅማሮ https://youtube.com/watch?v=VIfDKu6epWg&si=gfwXPipD4u2WDRQx»

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

15 May, 10:57


ጥንታዊ አስደናቂ ታሪኮች፤ ሲራራ ሰራዊት፣መቆራኘት፣የሚስጥር ዘበኛ፣ የሴት ትወና ጅማሮ
https://youtube.com/watch?v=VIfDKu6epWg&si=gfwXPipD4u2WDRQx

Ethiopian History's ኢትዮጵያ ታሪኮች

17 Apr, 11:56


በህልምም የማይታሰበው ከሰላሌ እስከ ባሌ የተዘረጋው የወንጀል መረብ፤ ሁለት ልጆቹን ወደ ገደል..? #የወንጀል ተረኮች
https://youtube.com/watch?v=Q0YubxgH57Y&si=DNost4RKkjETByn5