ኢተዮ መረጃ

@ethiomereja16


ኢተዮ መረጃ

27 Oct, 18:16


ያሳዝናል
========
ጋዛን ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ያገናኝ የነበረው ብቸኛው የጀዋል ካምፓኒ ዓለም አቀፉ የኢንተርኔት ገመድ በጽዮናዊያኑ ቦምብ መመታቱን ተከትሎ ጋዛዊያን ድምፃቸው ታፍኖ ያለ ማቋረጥ ከ3 ሰዓታት በላይ የቆዬ እጅግ ዘግናኝ የቦምብ ጥቃት እየዘነበባቸው ነው።

በተጨማሪም በባህርም፣ በአየርም፣ በምድርም እሳት እየዘነበባቸው ነው።
ጠብቃ ጠብቃ እስራኤል ከሰሞኑ የከፋውን ጭፍጨፋ ዛሬ በጨለማ ጀምራለች።

ከ40 ሺህ በላይ ታማሚዎች የሚገኙበትን ዋነኛውን አልሺፋ ሆስፒታልንም አጋይታለች።
አንድም ፈለስጢናዊ በህይዎት ማየት አትፈልግም።

አምቡላንሶች እንኳ ወደ ሟቾችና ቁስለኞች ዘንድ በማምራት ማንሳት አልቻሉም።

እስራኤል ወንጀሏና የምትፈጽመው ዘግናኝ ጥቃት ተቀርፆ በሚዲያ እንዳይወጣባት ድምጿን አጥፍታ እየጨረሰች ነው።

በጘ-ዝ'ዛ ታሪክ ይቀር የማይለው የጦር ወንጀልና የዘር ማፅዳት ጭፍጨፈሰ እየተፈጸመ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አሁንም በዝምታ ላይ ነው።




በጣም ነው የሚያሳዝነው!

ኢተዮ መረጃ

09 Jan, 07:41


----
ኢራቅ ሰሞኑን ኢራቅ የዓለምን ሕዝብ ስታስደንቅ ነው የዋለችው፡፡ የዓለም ሚዲያዎች እስከ አሁን ስለእርሷ እያወሩ ነው፡፡ የዚህን መንስኤ ለማወቅ ካሻችሁ ከዚህ በታች ያለውን ፎቶግራፍ ማየት አለባችሁ፡፡
----
ፎቶው በቅርቡ በተጠናቀቀው የቀጠር የዓለም ዋንጫ ወቅት የተነሳ ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል፡፡ ይህ ፎቶ የተነሳው ዐርብ ዕለት ነው፡፡ ቦታው ደግሞ የኢራቅ ሶስተኛዋ ትልቅ ከተማ የሆነችው በስራ ናት፡፡

አዎን! ኢራቅ 25ኛው የባሕረ ሰላጤ ሀገራት የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር አዘጋጅ ናት፡፡ ዝግጅቱ ባለፈው ዐርብ የኢራቅ መሪዎች፣ የባሕረ-ሰላጤው ሀገራት ከፍተኛ የመንግሥት ተወካዮች፣ ስምንቱን የባሕረ-ሰላጤ ሀገራት የወከሉ ብዙ ስፖርተኞች እና ብዙ ሺህ ሕዝብ በተገኘበት በበስራ ከተማ ትልቁ ስቴዲየም እጅግ በደመቀ ሁኔታ ተከፍቷል፡፡ ስፖርተኞቹ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውድድራቸውን ያካሄዳሉ፡፡
-----
ለሃያ ዓመታት በአሜሪካ አውዳሚ መሣሪያዎች በተከፈተባት ወረራ፣ እርሱን ተከትሎ በተፈጠረው ጦርነት፣ በሽብር፣ በፍንዳታ፣ በአንጃዎች የእርስ በእርስ ውጊያ፣ በእልቂት፣ በሕዝብ መፈናቀል እና በISIS ጽንፈኞች ትርምስ ስትናጥ የከረመችው ኢራቅ ከችግሯ ሁላ አገግማ ይህንን ትልቅ ውድድር ለማዘጋጀት መብቃቷ በጣም አስደሳች ነገር ነው፡፡ ይህቺ ታላቅና ጥንታዊት ሀገር ለወደፊቱም አሁን በጀመረችው የተሐድሶ ጉዞ ተራምዳ እንደ ጥንቷ ባቢሎኒያ እና እንደ አባሲድ ኸሊፎች መቀመጫዋ “በግዳድ አል-ሸምሲያ” እንድታንጸባርቅ መልካሙን ሁሉ እንመኝላታለን፡፡
------
አፈንዲ ሙተቂ

ኢተዮ መረጃ

12 Aug, 08:36


የሕዳሴ ግድብ 3ኛው ዙር ውኃ ሙሌት በስኬት ተጠናቅቋል፡፡

ዓባይ ላይ ግድብ ለመገንባት ስንነሳ ወንዙን የራሳችን ብቻ የማድረግ ፍላጎት አድሮብን እንዳልሆነ ከመጀመሪያውም ስንናገር ነበር፡፡ እኛ ማግኘት የሚገባንን ጥቅም እናግኝ ስንል ልክ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ ሌሎቹ የዓባይ ሥጦታዎች - ሱዳንና ግብጽ ከወንዙ በየድርሻቸው እንደሚጠቀሙበት እያሰብን ጭምር ነው፡፡ እውነትን ይዘን ተነስተን፣ በገዛ ሐቃችን ገንብተን፣ በቃላችን መሠረት፣ ማንም ላይ ጉዳት ሳናደርስ እነሆ 3ኛውን ዙር ውኃ ሙሌት በታሰበው ጊዜ ማጠናቀቅ ስለቻልን የዓባይ ልጆች ሁሉ እንኳን ደስ ያለን!!

የዓባይ ወንዝ ለሺህ ዘመናት ሦስቱን ሀገራት አስተሳስሮ እንዳኖራቸው ሁሉ÷ በእሱ ላይ የተገነባው ግድብ ከሌሎች ጎረቤቶቻችንም ጋር በትብብር እንድንኖር ያስችለናል፡፡ ግድቡ ደለል የሚያስቀር በመሆኑ በጎርፍ ምክንያት በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የሚወድመውን ሀብትና የሚጠፋውን የሰው ሕይወት ቁጥር እንደሚቀንስ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ባለፈ ግድቡ የሚያመነጨውን ኤሌክትሪክ - በኃይል ምንጭነት፣ በውኃው አናት ላይ የሚነጠፈውን ውብ ገጽታ -በመዝናኛነት፣ በውኃው ጉያ የሚሰግሩትን አሳዎች - በምግብነት ከጎረቤቶቻችንና ከዓለም ጋር እንጋራዋለን፡፡

ኢተዮ መረጃ

03 Aug, 16:19


የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ስብሰባችንን አካሂደናል። ባለፈው ዓመት የሚያበረታታ የወጪ ንግድ አፈጻጸም፣ ቀጥተኛ የውጭ ሙዓለ ነዋይ ፍሰት መጨመር ታይቷል። ባለፉት ሁለት ወራት የዋጋ ግሽበት መቀነስ፣ ከፍተኛ የአረንጓዴ ዐሻራ ክንውን፣ የበጎ ፈቃደኝነት ተግባራት፣ የሬሚታንስ ጭማሪ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥራ ክንውን የተመዘገቡበት እንደ ሆነ አረጋግጠናል። በዚህ ዓመት የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ መቀጠል በእጅጉ አስፈላጊ ነው።

Our macroeconomic committee meeting today confirmed remarkable export performance this past year; better FDI flows; decreased inflation past two month;
optimal green legacy, volunteer activities, remittance and automation performance. It is key we build and expand on this year’s achievements.