Eshet Pre-Primary,Primary and Middle school

@eshetprime2013


Eshet Pre-Primary,Primary and Middle school
👉 @eshetprime2013
Eshet Library 👉 @eshetprimelibrary

Eshet Pre-Primary,Primary and Middle school

21 Oct, 16:33


ይህ የተሻሻለው የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ጭማሪ ከጥቅምት ወር ጀምሮ እንደሚከፈል ገንዘብ ሚንስቴር አስታውቋል።

Eshet Pre-Primary,Primary and Middle school

20 Oct, 18:55


የነጭ ሽንኩርት መድኃኒትነት

1. ነጭ ሽንኩርት ስራን በትክክል ለማከናወን፣ የሰውነት ሕዋሳትን ጤናማ ለማድረግ ፣ድካምን ለማስወገድ፣ዕድሜን ለመጨመር፣በአይጥና በልዩ ልዩ ተባዮች የሚመጡትን ተስቦ በሸታዎችን ለመከላከል ነጭ ሽንኩርት መብላት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

2. ማንኛውም ሰው መጥፎ ሽታ ባለበት አካባቢ ለፅዳት ከመሰማራቱ በፊት ነጭ ሽንኩርት ከትፎ ቢበላ ከማንኛውም በሽታ ከሚያመጡ ተዋህሲያን ለመዳን ይቻላል፡፡

3. በቂ ሕክምና በሌለበት አካባቢ በቁስል ለሚሰቃይ ሕሙማን በነጭ ሽንኩርት ጭማቂ አጥቦ በቁስሉ ዙሪያ በመደምደም በፋሻ ወይም በንፁህ ጨርቅ በማሰር ሕመምተኛውን ለመፈወስ ይችላል፡፡

4. ነጭ ሽንኩርት ቀቅሎ እንፋሎቱን የካንሰርንና የቲቢ በሽታዎችን ለመከላከልና በሳንባ አካባቢ ብርድና ጉንፋን ለማዳን ፍቱን መድኃኒቱ ነው፡፡

5. ብርድ ብርድ በሚያሰኝ ሕመምና በተለይም በጥርስ ሕመም ለሚሰቃዩት ሕሙማን ሁለት ራስ ነጭ ሽንኩርት የውስጠኛውን ሽፋናቸውን በመላጥ በሁለቱም ጉንጫቸው በተለይም በተነቃነቀው ጥርስ በኩል ነክሰው ረዘም ላሉት ሰዓት ቢጠቀሙበት መልሶ መልሶ ይጠነክራል፡፡

6. ለአስም፣ ለጉሮሮ ክርካሪ ወይም ኮርታ ለተባለው በሽታ እንዲሁም ጉሮሮ ለማፅዳት የነጭ ሽንኩርት ጭማቂ በስኳር ወይም በማር መጠጣት የተፈተነ መድኃኒት ነው፡፡

7. ነጭ ሽንኩርት የራስ ምታትና የደም ብዛት ያለባቸው ሰዎች ከ3 እስከ 5 ቀናት በማከታተል ሦስት ሦስት ፍንካች በቀን ሦስት ጊዜ ቢበሉ ከድካምና ከደም ብዛት ሊፈወሱ ይችላሉ፡፡

8. በደም መርጋት ምክንያት ለሚሰቃዩ ፣የልብ በሽታን፣ የፊንጢጣ ኪንታሮትና የእግር ደም ሥር እብጠት varicose የተባሉትን በሽታዎች ለመከላከልና ለመዳን ነጭ ሽንኩርት በመብላት መፈወስ ይችላል፡፡

9. ነጭ ሽንኩርት ችፌን፣የጨጓራ በሽታን፣ ወረርሽኝን፣ ኮሌራን፣ ሳይቲካን፣ የቁርጥማት ሕመምን ወዘተ... በርካታ የጤና ዕክሎችን ይከላከላል/ያድናል፡፡

ሰላም እና ጤና ከሁላችን
ጋር ይሁን!

Eshet Pre-Primary,Primary and Middle school

20 Oct, 18:03


የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ተከታዩን ሊንክ ተጠቅማችሁ የምዝገባ ቁጥር ወይም Username በማስገባት ውጤቶቻችሁን ማየት ትችላላችሁ 👇
https://result.ethernet.edu.et

ከሐምሌ 22 እስከ ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም የተሰጠውን ስልጠና፣ ከ49 ሺህ በላይ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች መውሰዳቸው ይታወሳል፡፡

Via MoE

Eshet Pre-Primary,Primary and Middle school

18 Oct, 17:47


የት/ቤቱ መምህራን ፣ ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት በተገኙበት ጥልቅ የሆነ ውይይት በማድረግ የተቋሙን ጠንካራ ጎኖች አጠናክሮ በማስቀጠል እንዲሁም የነበሩ ውስንነቶችን በማረም እንደወትሮው ሁሉ የ2017 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱን ስኬታማ በሆነ አግባብ ለመከወን መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን የመወያያ አጀንዳዎችም፦
1ኛ. የት/ቤቱን ራዕይ፣ ተልዕኮ እና
ዕሴቶች ለት/ት ማህበረሰቡ ማስረፅን
በተመለከተ
2ኛ. የት/ቤቱ መሪ ዕቅድ እና
ኬፒአይ ( KPI) ዕቅድ
3ኛ. የት/ቤት መሻሻል ዕቅድ
4ኛ. የመልካም አስተዳደር ዕቅድ
5ኛ. የኪራይ ሰብሳቢነት ማክሰሚያ
ዕቅድ ዋና ዋናዎቹ ናቸው ።

ጥቅምት 2017ዓ.ም